Telegram Web Link
ሀላፊው አክለዉም ቤት ለመምህራን መኖሪያቸው ብቻ ሳይሆን የስራ ቦታው ጭምር መሆኑን ገልጸው በፍጥነት በቅርብ ቀናት ውስጥ ወደ ስራ የሚገባ መሆኑን የተናገሩ ሲሆን ስራዉ እንዲሳካ እስካሁን ከፍተኛ አስተዋጽዎ ላበረከቱት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ፣ ለቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ እና ለህብረት ስራ ኮሚሽን ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ደንቃለም ቶሎሳ በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ እያደረገ ላለው ስራ ምስጋና አቅርበው የቀረቡ አማራጮች የመምህራኑን አቅም ታሳቢ ያደረጉ እና በፍጥነት ወደግንባታ የሚያስገቡ መሆናቸውን ተናግረው መምህራን የቀረቡትን አማራጮች በደንብ ተገንዝበው በፍጥነት ወደ ግንባታ በመግባት እንዲቻል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የግንባታ አማራጮች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች አስተዳደር ቢሮ የዲዛይን ዝግጅት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሆኑት በአቶ ጳውሎስ ታምራት ከዲዛይን ዝግጅት ፣ ከቤቶች ካሬ ስፋት እንዲሁም ከዋጋ መጠን አኳያ አቅርበዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
ከተማ አቀፍ የ90 ቀናት የክረምት በጎ ፍቃድ የተማሪዎችና የመምህራን የማስ ስፖርት ንቅናቄ ማስጀመርያ መርሃ ግብር በገላን ጉራ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተካሄደ።

(ሰኔ 30/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከተማ አቀፍ የ90 ቀናት የክረምት በጎ ፍቃድ የተማሪዎችና የመምህራን የስፖርት ንቅናቄ ማስጀመርያ መርሃ ግብር ''ማስ ስፓርትን በትምህርት ቤቶች ባህል በማድረግ ጤናማ ንቁና ብቁ ትውልድ እንፈጥራለን!'' በሚል መሪ ሀሳብ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በገላን ጉራ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አካሂዳል።

በንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊዎች አቶ ዲናኦል ጫላና አቶ ሳምሶን መለሰ ፣ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ከበደ ድሪባ ፣ የትምህርት ባለሙያዎችና አመራሮች ፣ መምህራንና ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ ሁሉንም አካላት ያሳተፈ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የተደረገ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ብቁና ንቁ የሆነ ትውልድ ለመፍጠር ትውልድን በአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች እና በስነ ልቦና ማብቃት አንዱ የትምህርት ተግባር መሆኑን ጠቅሰው በHንድሮ የ90 ቀናት የክረምት በጎ ፍቃድ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር መሰረት በሁሉም ክፍለ ከተማዎች የተጠናከረ ከተማ አቀፍ የ90 ቀናት የክረምት በጎ ፍቃድ የተማሪዎችና የመምህራን የስፖርት ንቅናቄ መርሀግብሮች የሚካሄድ መሆኑን ተናግረዋል።

ሀላፊው አክለውም በክረምት ወቅት በሁሉም ትምህርት ቤቶች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያለማቋረጥ የሚካሄድ በመሆኑ ከዛሬ ጀምሮ ባሉት ቀናት ትምህርት ቤቶች ክፍት እንደሚሆኑና ተማሪዎች እና መምህራን እንዲሁም የትምህርት ማህበረሰቡ አካላት የሚሣተፋበት የማስ ስፖርት እንቅስቃሴ እንደ አንድ ተግባር ተወስዶ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ አሳውቀዋል።

በተያያዘ ዜናም በ2017 የትምህርት ዘመን በ57 ቀናት ተገንብቶ ትምህርት መስጠት የጀመረው ገላን ጉራ ቁጥር 2 ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በከተማ አቀፍ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ፈተና መቶ ፐርሰንት ያሳለፈ ሲሆን በትምህርት ቤቱ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች በመድረኩ እውቅና የሰጥቷል።

በተጨማሪም የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ተከናውናል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ክቡር ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በሚገኘው በገላን ጉራ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከተማሪዎች ከመምህራንና ከትምህርት አመራሮች ጋር በመሆን የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር አከናውነዋል፡፡

(ሰኔ 30/2017 ዓ.ም) በመርሀ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊዎች አቶ ዲናኦል ጫላና አቶ ሳምሶን መለሰ ፣ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ከበደ ድሪባ ፣ የትምህርት ባለሙያዎችና አመራሮች ፣ መምህራንና ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
2025/07/08 11:57:57
Back to Top
HTML Embed Code: