የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ፕሮግራም ለክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት በተዘጋጀ የ90 ቀን የንቅናቄ ሰነድ ዙሪያ ኦረንቴሽን ተሰጠ።
(ሰኔ 16/2017 ዓ.ም) በመርሀ ግብሩ የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት የዘርፉ አስተባባሪዎች ፣ የዘርፈ ብዙ ቡድን መሪዎች እንዲሁም የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት እና የልዩ ፍላጎት ትምህርት ባለሙያዎች እና የጎልማሶች ትምህርት የሚያስተምሩ አመቻቾች ተሳታፊ ሆነዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የልዩ ፍላጎትና ጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገመቺስ ፍቃዱ በ2017 ዓ.ም ክረምት ወቅት በከተማ ደረጃ በ680 በጎ ፍቃደኞች አማካይነት ለ11ሺ ጎልማሶች የትምህርት አገልግሎቱን ለመስጠት እቅድ መዘጋጀቱን እና ቢሮው ለክፍለ ከተሞች እቅዱን ከፋፍሎ ማውረዱን ገልጸው ክፍለ ከተሞችም በወረደላቸው እቅድ መሰረት በጎ ፍቃደኞችን አስተባብረው ጎልማሶቹን በመመዝገብ በየማስተማሪያ ጣቢያዎች እንዲማሩ በማድረግ እቅዱ እንዲሳካ የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ መልዕክት አስተላልፈዋል።

❤30👍3👎2🖕2😎1
በከተማ አስተዳደሩ በ2017 ዓ.ም ክረምት ወቅት ለጎልማሶች በሚሰጠው የትምህርት አገልግሎት የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ያጠናቀቁ እና ከተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለእረፍት ወደየአከባቢያቸው የመጡ ወጣቶች ተሳታፊ እንደሚሆኑ የቢሮው የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ባለሙያው አቶ ጌታቸው በላይነህ የንቅናቄ ሰነዱን ባቀረቡበት ወቅት ጠቁመው የክረምት ትምህርቱ የጎልማሶችን መሰረታዊ የማንበብ፣የመጻፍና የማስላት ክህሎት በማሳደግ ሁለንተናዊ ህይወታቸውን ማሻሻል እንዲችሉ በማሰብ የሚሰጥ በመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ በማስፈጸሚያ እቅዱ በተቀመጠው መሰረት ኃላፊነቱን መወጣት እንደሚገባው አመላክተዋል።
በመርሀ ግብሩ የ2018 ዓ.ም የልዩ ፍላጎትን የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት እቅድ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc

❤35🖕4😁2
የ2017 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት በነገው ዕለት ይፋ ይሆናል፡፡
(ሰኔ 16/2017 ዓ.ም) የ2017 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት በነገው ዕለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት በማለፊያ ነጥቡ ላይ ውይይት ካደረጉ በሃላ ይፋ ይደረጋል።
የ2017 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና በአጭር ጊዜ ታርሞ ይፋ መደረጉ ተማሪዎች ለቀጣዩ የትምህርት አመት ከወዲሁ በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ የሚያስችል ሲሆን የ2017 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ከሰኔ 3-4/2017 ዓ.ም ድረስ በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ 194 የመፈተኛ ጣቢያዎች ለተከታታይ ሁለት ቀናት መሰጠቱ ይታወሳል፡፡ ።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
(ሰኔ 16/2017 ዓ.ም) የ2017 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት በነገው ዕለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት በማለፊያ ነጥቡ ላይ ውይይት ካደረጉ በሃላ ይፋ ይደረጋል።
የ2017 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና በአጭር ጊዜ ታርሞ ይፋ መደረጉ ተማሪዎች ለቀጣዩ የትምህርት አመት ከወዲሁ በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ የሚያስችል ሲሆን የ2017 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ከሰኔ 3-4/2017 ዓ.ም ድረስ በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ 194 የመፈተኛ ጣቢያዎች ለተከታታይ ሁለት ቀናት መሰጠቱ ይታወሳል፡፡ ።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
😱465❤161👍98🙏82🖕33😢28👏12😁12👌10💩9🥰7
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት የ2017 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የማለፊያ ውጤት 50% እንዲሆን በዛሬው እለት ወስነዋል።
(ሰኔ 17/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በከተማ አስተዳደሩ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት በየአመቱ መሻሻል እያሳየ መሆኑን ገልጸው ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራቱ ዘንድሮም ከአምናው የተሻለ ውጤት ለመመዝገብ ችላል ብለዋል።
ዶክተር ዘላለም አያይዘውም በ2017 ዓ.ም የሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርትን ለማሻሻል ተግባራዊ የተደረገው ስትራቴጂ በተማሪዎች ውጤት መረጋገጡን ጠቁመው ፈተናውን በአጭር ጊዜ በማረም ውጤቱ ይፋ እንዲሆን ቀን ከሌት ሲሰሩ ለቆዩ የፈተና ክፍል ባለሙያዎችና ሂደቱን ሲደግፉ ለነበሩ አመራሮች ምስጋና አቅርበዋል። በቀጣይ ጥቂት ቀናትም የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ውጤት ይፋ እንደሚደረግ አስታውቀዋል። ውጤቱም ዛሬ ከሰዓት ይፋ ይደረጋል ብለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ በበኩላቸው በከተማ አስተዳደሩ በ2017 ዓ.ም 70,525 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸውን ገልጸዋል፡፡

❤274😱145👍97🖕27👏23😢23🕊17👎15👀14🔥9😁6
በከተማ አስተዳደሩ በበይነ መረብ (online) ለሚሰጠው የ2017ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ የቅድመ ዝግጅት አካል የሆነ የሙከራ ፈተና በሁሉም የመፈተኛ ጣቢያዎች ተሰጠ።
(ሰኔ 17/2017 ዓ.ም) በዛሬው እለት በተሰጠው የሙከራ ፈተና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አመራሮችን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ የሁለቱ ሴክተር ባለሙያዎች በየፈተና ጣቢያው በመገኘት ሂደቱን የተከታተሉ ሲሆን በዛሬው እለት የተሰጠው የሙከራ ፈተና በስኬት መጠናቀቁን ከየፈተና ጣቢያው የተገኙ መረጃዎች ያሳያሉ።
የዛሬው የሙከራ ፈተና ከሰኔ 23/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሚሰጠው መደበኛ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በአግባቡ መዘጋጀት እንዲችሉ ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረላቸው የሙከራ ፈተናውን የወሰዱ ተማሪዎች አረጋግጠዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ሙሉ ለሙሉ በበይነ መረብ ለመስጠት የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ የሚገኝ ሲሆን የዛሬው የሙከራ ፈተና ፈተናውን በበይነ መረብ ለመስጠት የተዘጋጁ የመሰረተ ልማቶች ብቁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቴክኖሎጂ እና መሰረተ ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ዳኜ አስታውቀዋል።

❤126👍40🖕19👎9😁8👏5