የ6ኛ ክፍል ተማሪ ሳለች ለእናቷ የገባችውን ቃል ያሳካችው ተመራቂ፡፡
(ሰኔ 21/2017 ዓ.ም) የአብስራ ሽፈራው ትባላለች። የ6ኛ ክፍል ተማሪ ሳለች አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በእናቷ ምርቃት ላይ ተገኝታ ነበር። ያኔ ታዲያ "በዚህ ግቢ ተምሬ እመረቅበታለሁ" ስትል ለእናቷ ቃል ገብታላት ነበር።
እንሆ ዛሬ የአብስራ ያን ቃሏን አሳክታለች። ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሳይኮሎጂ ትምህርት ክፍል 3.5 በማምጣት በከፍተኛ ማዕረግ በዲግሪ ተመርቃለች።
አካል ጉዳተኝነት ያልበገራት የአብስራ በመምህሮቿ የተመሰገነች ታታሪ ተማሪ ስትሆን፤ ለዚህ ስኬቷ ደግሞ የእናቷ አበርክቶ ትልቅ ድርሻ ይወስዳል።
በ4 ዓመታት የዩኒቨርሲቲ ቆይታዋ እናቷ እርሷን በማመላለስ እና በማበረታታት ለዚህ አብቅታታለች።
የአብስራ እናት "ልጆቻችን አካል ጉዳተኞች ናቸው ብለን በየቤቱ ደብቀን ይበልጥ ከምንጎዳቸው ፤ መስዋዕት ከፍለን ካሰቡበት እናድርሳቸው" ስትል ለወላጆች መልዕክት አስተላልፋለች።
#EBC #EBCdotstream #AAU #Graduation
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc

❤107👍19👏12
በአዲስ አበባ ከተማ የ2017 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርኃ ግብር በመካሄድ ላይ ይገኛል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፤የከተማ አስተዳደሩ ሌሎች አመራሮች፤ የሃይማኖት አባቶች ፤ የሃገር ሽማግሌዎች ፤ የሃገር መከላከያ ሰራዊት አባላት፤ ፖሊስና ሌሎች የጸጥታ አካላት፤ መምህራን፤ ህክምና ባለሙያዎች ፤ መገናኛ ብዙሃን፤ ወጣቶች፤ ሴቶች፤ ተማሪዎችና ሌሎች በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት የ2017 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርኃ ግብር በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

❤19👏10💔5😁1
የልዩ ፍላጎትና ጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ዳይሬክቶሬት በተግባር የተደገፈ የምልክት ቋንቋ የክህሎት ስልጠና ሰጠ።
(ሰኔ 22/2017 ዓ.ም) የክህሎት ስልጠናው ለልዩ ፍላጎት መምህራን፣በየትምህርት ቤቱ በተቋቋሙ የድጋፍ መስጫ ማዕከላት እና በዙሪያቸው የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን ለሚደግፉ ተዘዋዋሪ መምህራን እንዲሁም ለርዕሳነ መምህራን እና ለትምህርት ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን ስልጠናውን የምልክት ቋንቋ መጽሐፍ በማዘጋጀት እና በዘርፉ የማሰልጠን ከፍተኛ ልምድ ባላቸው ባለሙያ መሰጠቱን ከስራ ክፍሉ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የልዩፍላጎትና ጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገመቺስ ፍቃዱ በከተማ አስተዳደሩ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ፍትሀዊ የሆነ የትምህርት ስርአት ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ 2,321 የሚሆኑ መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች የትምህርት አገልግሎት በማግኘት ላይ መሆናቸውን ገልጸው እነዚህን ተማሪዎች በአግባቡ መደገፍ እንዲቻል ለመምህራን እና ርዕሳነ መምህራን የምልክት ቋንቋ የክህሎት ስልጠና መስጠት በማስፈለጉ መርሀግብሩ መዘጋጀቱን አመላክተዋል።

❤14👍3
ዳይሬክተሩ አያይዘውም ስልጠናው በተግባር ተደግፎ በዘርፉ መጽሐፍ እስከማዘጋጀት የደረ ሰ ልምድ ባላቸው ባለሙያ እንደመሰጠቱ የክህሎት ማሳደጊያ ስልጠናውን የወሰዱ አካላት በየትምህርት ቤቱ ለሚገኙ ባለድርሻ አካላት ተመሳሳይ ግንዛቤ በመፍጠር የአካቶ ትምህርት ስርአቱ በአግባቡ ተግባራዊ እንዲሆን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።
የቢሮው የልዩ ፍላጎት ትምህርት ባለሙያው አቶ ፀጋዬ ሁንዴ በበኩላቸው ስልጠናው የመምህራንን እና ርዕሳነ መምህራንን የምልክት ቋንቋ ክህሎት በማሻሻል መስማት የተሳናቸው ተማሪዎችን በአግባቡ በመደገፍ በከተማ አስተዳደሩ ተግባራዊ የተደረገው የአካቶ ትምህርት በሚጠበቀው ደረጃ ውጤታማ እንዲሆን ታስቦ መዘጋጀቱን ገልጸው ቢሮው በቀጣይ ለሌሎች ባለድርሻ አካላት ተመሳሳይ ስልጠና መስጠቱን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አስታውቀዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ!

❤15👍4🥰1