በትላንትናው ዕለት የተጀመረውና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በበይነ መረብ (online) የሚሰጠው የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በዛሬው ዕለትም በመሰጠት ላይ ይገኛል።
(ሰኔ 24/2017 ዓ.ም) ፈተናው በከተማ አስተዳደሩ በ108 የማስፈተኛ ጣቢያዎች ሙሉ ለሙሉ በበይነ መረብ በመሰጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን ፈተናው ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ቀደም ሲል ተማሪዎቹ የልምምድ ፈተና እንዲወስዱ መደረጉን እና በቂ ኦረንቴሽን መሰጠቱ እንዲሁም በየመፈተኛ ጣቢያው መሰረተ ልማቶቹን ዝግጁ የማድረግ ስራን ጨምሮ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሲሰሩ መቆየቱ ይታወቃል።
ሁለተኛ ቀኑን ባስቆጠረው የመጀመሪያ ዙር ፈተና ከ13ሺ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን በበይነ መረብ በመውሰድ ላይ የሚገኙ ሲሆን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ፣ የቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ዲናኦል ጫላና አቶ ሳምሶን መለሰ በጋር በመሆን ፈተናው ከሚሰጥባቸው ጣቢያዎች መካከል በአድዋ ድል መታሰቢያ እና አብሮህት ቤተ መጻሕፍት ተገኝተው የሁለተኛዉን ቀን ፈተና በማስጀመር ተማሪዎችን አበረታተዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc

በበይነ መረብ (online) እየተሰጠ የሚገኘው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ለ2ኛ ቀን እየተሰጠ ይገኛል ።
(ሰኔ 24/2017 ዓ.ም) በከተማ አስተዳደሩ በ2017 ዓ.ም በበይነ መረብ (Online) እየተሰጠ የሚገኘው የ 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ሁለተኛ ቀን እየተካሄደ ይገኛል::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ከቢሮው ምክትል ቢሮ ሀላፊዎች ከአቶ ወንድሙ ዑመር ፣ ከአቶ ዲናኦል ጫላና ከአቶ ሳምሶን መለሰ እንዲሁም ከቦሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ መስፍን ታደሰ እና ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰማህኝ አስታጥቄ ጋር በመሆን በዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፣ ቦሌ ሕብረተሰብና አሳይ የፈተና መስጫ ጣቢያዎች ላይ ተዘዋውረው የፈተናውን ሂደትን በመመልከት ተማሪዎችን አበረታተዋል፡፡
ተማሪዎች በሁለተኛ ቀን ፈተና በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ Apttitude በከሰዓቱ መርሀ ግብር ደግሞ physics የትምህርት አይነቶችን የሚፈተኑ ይሆናል::