Telegram Web Link
ጤናማ ትውልድ ለመፍጠር ታሳቢ ያደረገ የ90 ቀናት የማስ ስፖርት ንቅናቄ ማስጀመርያ መርሃ ግብር በ43 የመንግስት ትምህርት ቤቶች ተካሄደ።

(ሰኔ 30/2017 ዓ.ም) የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ጤናማ ትውልድ እንዲፈጠር እና በአካል ብቃት የዳበረ ትውልድ ለማፍራት የ90 ቀናት የማስ ስፖርት ንቅናቄ ማስጀመርያ መርሃ ግብር በ43 የመንግስት ትምህርት ቤቶች አካሂዷል።

በንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ምከትል ኃላፊ አቶ አሊ ከማል እንዳሉት የ90 ቀናት የማስ ስፖርት ንቅናቄ ማስጀመርያ ላይ ተማሪዎችና መምህራን እንዲሁም የአስተዳደር ሠራተኞች በማሳተፍ ጤናማ ትውልድ እንዲፈጠር በአካል ብቃት የዳበረ ትውልድ ማፍራት ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብሩክ ተ/ማርያም በበኩላቸው ጤናማ ትውልድ እንዲፈጠር በአካል ብቃት የዳበረ ትውልድ ለማፍራት የ90 ቀናት የማስ ስፖርት ንቅናቄ ማስጀመርያ መርሃ ግብር በ43 የመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚካሄድ መሆኑን ገልጸው፣የማስ ስፖርት ንቅናቄው ዋና ዓላማው በተማሪዎች፣መምህራን እና የአስተዳደር ሠራተኞች መካከል ወንድማማችነትና እህትማማችነትን ለማጠናከር አስተዋጽኦ ያሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አቶ ብሩክ ተ/ማርያም አክለውም በክረምት ወቅት በሁሉም ትምህርት ቤቶች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያለማቋረጥ የሚካሄድ በመሆኑ ከዛሬ ጀምሮ ባሉት ቀናት ትምህርት ቤቶች ክፍት እንደሚሆኑና ተማሪዎች እና መምህራን እንዲሁም የትምህርት ማህበረሰቡ አካላት በሳምንት 3ቀን ለ2ወራት የሚሣተፋበት የማስ ስፖርት እንቅስቃሴ እንደ አንድ ተግባር ተወስዶ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ አሳውቀዋል።
23👍4
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ጤናማ ትውልድ ለመፍጠር ታሳቢ ያደረገ የ90 ቀናት የማስ ስፖርት ንቅናቄ ማስጀመርያ መርሃ ግብር በትምህርት ቤቶች ተካሄደ።

(ሰኔ 30/2017 ዓ.ም) የማስ ስፖርት ማስጀመሪያ ንቅናቄ ላይ የ90 ቀናት የማስ ስፖርት ንቅናቄ ማስጀመርያ ላይ ተማሪዎችና መምህራን እንዲሁም የአስተዳደር ሠራተኞች በማሳተፍ ጤናማ ትውልድ እንዲፈጠር በአካል ብቃት የዳበረ ትውልድ ማፍራት ላይ በትኩረት የሚሰራ መሆኑ ተገልጻል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
7
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ጤናማ ትውልድ ለመፍጠር ታሳቢ ያደረገ የ90 ቀናት የማስ ስፖርት ንቅናቄ ማስጀመርያ መርሃ ግብር በትምህርት ቤቶች ተካሄደ።

(ሰኔ 30/2017 ዓ.ም) የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት የ90ቀን እቅድ አንዱ አካል የሆነው የ2017 ዓ.ም የክረምት የተማሪዎችና የመምህራን ስፖርት ንቅናቄ ማስጀመርያ መርሃ ግብር በዛሬው እለት በረጲ ጃፓን አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤትና በየማነ ብርሃን ቅድመ አንደኛ ፣ አንደኛ ደረጃና መካከለኛ ደረጃ ትምርት ቤት ተካሂዷል።

ትውልድን በአካል ብቃት እና በስነልቦና ማብቃት አንዱ የትምህርት ተግባር በመሆኑ የክረምት ወቅት በሁሉም ትምህርት ቤቶች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መካሄድ ስላለበት ከዛሬ ጀምሮ ባሉት ቀናት ተማሪዎች እና መምህራን እንዲሁም የትምህርት ማህበረሰብ የሚሳተፋበት የስፖርት እንቅስቃሴ በሁሉም የትምህርት ተቋማት እንደሚካሔድ አቶ ገነነ ዘውዴ የክፍለ ከተማው ትምህርት ፅህፈት ቤት ገልፀዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
13
2025/07/09 20:56:17
Back to Top
HTML Embed Code: