Telegram Web Link
በበጀት ዓመቱ በመንገድ ልማት ዘርፍ፡-

(ሀምሌ 4/2017 ዓ.ም)
የከተማውን የመንገድ መረብ ሽፋን የሚያሳድጉ፣ የትራፊክ ፍሰቱን የሚያሳልጡ፣ የመንገድ ድህንነቱን የሚያረጋግጡ፣ለኢንቨስመንት ምቹ ሁኔታ የሚፈጥሩ፣ የጉዞ ጊዜንና ገንዘብን የሚቀንሱ የመንገድ ግንባታና ጥገና ስራዎችን በማከናወን በዚህም፡-

371 ኪ.ሜ. የሚሸፍን አስፓልት

95.2 ኪ.ሜ የኮብል

16.1 ኪ.ሜ ጠጠር ግንባታ

107 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድ ግንባታ

3.7 ኪ.ሜ የድጋፍ ግንብ እና የድሬንጅ ግንባዎች

1‚180 ኪ.ሜ የሚሸፍን የመንገድ ጥገና ስራዎች ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርጓል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
12👏3
የሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማትን በተመለከተ፦

(ሀምሌ 4/2017 ዓ.ም)

የመንገድ መሠረተ ልማት፡- 135 ኪ.ሜ የተሽከርካሪ መንገድ፣ 246 ኪሎ ሜትር የእግረኛ መንገድ፣141 ኪ.ሜ የብስክሌት መንገድ፣ 43 ኪ.ሜ የመሮጫ ትራክ፣ 53 የተሽከርካሪ እና እግረኛ መሻገሪያ ድልድዮች፤190 ኪ.ሜ የጎርፍ ማስወገጃ ሥርዓት ዝርጋታና፣ 83 ኪ.ሜ የድጋፍ ግንብ ሥራ ተሰርቷል።

የትራንስፖርት ሥርዓት ለማሳደግ ፦ 153 ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያዎች፣ በአንድ ጊዜ 35,000 ተሸከርካሪዎችን የማስተናገድ አቅም ያላቸውና 33 የባስ እና ታክሲ ዘመናዊ ተርሚናሎች፤

የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ፦ 1,122 ስማርት እና 1708 ኖርማል በአጠቃላይ 2830 የመብራት ምሰሶዎች ተተክሏል፤ 179.6 ኪ.ሜ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ፤ 5,048 የኤሌክትሪክ ምሰሶ ማዛወር፤ 22.41 የመሬት ውስጥ መካከለኛ የኤሌክትሪክ መስመር መቅበር፤ 324 የዲስትሪቢዩሽን ትራንስፎርመሮችና 7.9 ኪ.ሜትር ፒቪሲ ዝርጋታ ሥራ ተሰርቷል።

የሕዝብ መዝናኛዎችና ማረፊያዎችን ማስፋፋት፦ የአረንጓዴ ልማት ፤ የህዝብ መዝናኛ ፕላዛዎች ፤ ዘመናዊ የመንገድ ዳር የሕዝብ መፀዳጃ ቤቶች (Public toilets)፣ ስፍራዎች ተገንብተዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
40👎6😁2
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በሚገኙ ስራ ክፍሎች የ4ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸምን መሰረት ያደረገ ድጋፍና ክትትል ተካሄደ፡፡

(ሀምሌ 4/2017 ዓ.ም) ድጋፍና ክትትሉ የስራክፍሎቹን የ2017 በጀት አመት የ4ኛ ሩብ ዓመት የሪፎርም ፣ የአገልግሎት አሰጣጥ፤የመልካም አስተዳደር እንዲሁም የቁልፍ ሥራዎች አመላካች (KPI) ተግባራት አፈጻጸምን መሰረት አድርጎ መካሄዱን ከቢሮው የሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ድጋፍ ክትትልና ምዘና ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቢሮ ኃላፊ አማካሪ እና የዘርፉ አስተባባሪ ወይዘሮ አበበች ነጋሽ በበጀት አመቱ አጠቃላይ የሪፎርም ስራዎችን ጨምሮ የቁልፍ ሥራዎች አመላካች ተግባራት አፈጻጸምን መሰረት በማድረግ ከቢሮ ጀምሮ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ በተደጋጋሚ ድጋፍና ክትትል መደረጉን ጠቁመው ድጋፍና ክትትሉ በ2017 ዓ.ም የበጀት አመት የነበሩ አፈጻጸሞችን መነሻ በማድረግ በ2018 ዓ.ም የተሻለ ስራ ለመስራት የሚያስችል መሆኑን ከሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ድጋፍ ክትትልና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፈንታሁን እያዩ ጋር በመሆን የምዘና ሂደቱን በተከታተሉበት ወቅት አስታውቀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ድጋፍ ክትትልና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፈንታሁን እያዩ በበኩላቸው በትላንትናው እለት ተመሳሳይ ድጋፍና ክትትል በክፍለከተማ ትምህርት ጽህፈትቤቶች መካሄዱን ገልጸው በቀጣይ ከቢሮ ጀምሮ አስከ ትምህርት ቤት ድረስ የበጀት አመቱን አፈጻጸም መሰረት ያደረገ ምዘና የሚካሔድ መሆኑን አመላክተዋል፡፡


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
32👍8🥰1
2025/07/13 18:35:24
Back to Top
HTML Embed Code: