Telegram Web Link
3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉበዔውን 2ኛ ቀን ውሎ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡


(ሀምሌ 5/2017 ዓ.ም) ምክር ቤቱ በሁለተኛ ቀን ውሎው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃጸም ሪፖርት ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል::



መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
12👍3
በመትከል ማንሰራራት !

ዛሬ ጠዋት ከምክር ቤት አባላት ጋር በእንጦጦ ተራራ ላይ ችግኝ ተክለናል።


ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ


ከንቲባ አዳነች አቤቤ


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
5
የከተማው ካቢኔ በአራት ተቋማት አወቃቀር ላይ አፅድቆ በላከው የውሳኔ ሃሳብ መሰረት በአቀረበው በደንብ ቁጥር 13/2016 መሰረት በረቂቅ ደንብ ላይ ምክር ቤቱ ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ አፀድቋል፡፡

(ሀምሌ 5/2017 ዓ.ም) የቱሪዝም ኮሚሽን ለብቻው ወጥቶ መደራጀትን አስመልክቶ አስፈላጊነቱ ላይ በአፅንኦት ተወያይቷል::
በዚህም መሠረት
1-ቱሪዝም ዘርፍ ራሱን ችሎ በኮሚሽን እንዲቋቋም፤
2-የዲዛይን እና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ እና የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ፅ/ቤት ጋር እንዲወሀድ::
3 ማህበራዊ ትረስት ፈንድ ፅ/ቤት ከህብረተሰብ ተሳትፎ እና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ጋር እንዲወሃድ::

4-የከተማ ውበትና አረንጋዴ ልማት ቢሮ የህዝብ መፀዳጃ ቤቶችን የማልማት ተግባር ለውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ማስተላለፍን ያከተተ ማሻሻያዎች ላይ ምክርቤቱ ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡

በ3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በአራት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ምክር ቤቱ ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል::

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
11👏3
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት 350.13 ቢሊየን ብር ሆኖ ፀደቀ።


(ሀምሌ 5/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት 350.13 ቢሊየን ብር ሆኖ በምክር ቤቱ ፀድቋል፡፡


ረቂቅ በጀቱ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን አማካኝነት ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡


በቀረበው ረቂቅ ላይ አጠቃላይ 350.13 ቢሊየን ብር በምን መልኩ ለማግኘት እንደታሰበ ተዘርዝሯል፡፡


ከዚህ ውስጥ ከታክስ ገቢ 238 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ እንደታቀደ አቶ አብዱልቃድር አብራርተዋል፡፡


የምክር ቤቱ አባላት በረቂቅ በጀቱ ላይ ሃሳብ እና አስተያየት እንዲሁም ጥያቄዎች አንስተዋል፡፡


በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን በተነሱት ጥያቄዎች ላይ ምላሽና ማብራሪያ ከሰጡ በኋላ የ2018 በጀት 350.13 ቢሊየን ብር ሆኖ በሙሉ ድምፅ ፀድቋል፡፡




መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
51👏2🔥1
2025/07/13 06:05:46
Back to Top
HTML Embed Code: