Telegram Web Link
ተግተዉ የሰሩትን ሁሉ እናመሰግናለን !


የከተማ አስተዳደራችን 15,960 ፕሮጀክቶችን ከዛሬ ጀምሮ ለህዝብ አገልግሎት ክፍት ማድረግ ጀምረናል ።


በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች የተገነቡ አጭር እና አቋራጭ መንገዶች ፤ የትራፊክ ማሳለጫ ተሻጋጋሪ ድልድዮች የትራፊክ ፍሰትን በማቀላጠፍ እና ፕሮጀክቶቻችን በማያያዝ ለነዋሪው ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እድገት ጉልህ ድርሻ ያለቸው ናቸው ።

ፕሮጀክቶቹ ከ50 እስከ 60 ስፋት ያላቸዉ ድልድዮቹ እስከ 300 ሜትር ርዝመት ያላቸዉ ግዙፍ መንገዶች ያካተቱ ናቸው።
እነዚህ ፕሮጀክቶች፤ ከዉጪ በሚገኝ ብድር ይገነባል ተብሎ የተጀመረ ቢሆንም ብድሩ ሳይገኝ ቀርቶ በከተማ አስተዳደሩ አቅም መገንባት የተቻለ ነዉ።


የከተማችን ነዋሪዎችም የተገነቡ መንገዶችን በአግባቡ እንድትጠቀሙበት አደራ እያልኩኝ ፤ግንባታው ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ የበኩላችሁን ድርሻ ላበረከታችሁ የአዲስ አበባ ከተማ መንገድ ባለስልጣን ፤ የመንግስት እና የግል ድርጅቶች ፣ ኮንትራክተሮች ፣ አማካሪ ድርጅቶች እና የአቃቂ ቃሊቲ እና የቦሌ ክለከተማ አመራሮች እና ነዋሪዎች እና ድርሻ ለነበራችሁ ሁሉ በከተማ አስተዳደሩ እና በራሴ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።


ፈጣሪ ኢትዮጵያ እና ህዝቦቿን ይባርክ!
በ25/75 ፕሮግራም የተደራጁ ቤት ፈላጊ መምህራንን ወደ ስራ ለማስገባት እንዲቻል በቀረቡ የግንባታ አማራጮች ላይ ውይይት ተካሄደ።

(ሰኔ 29/2017 ዓ.ም) በመርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የመምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ ፣ የቢሮ ስትራቴጂክ ካውንስል አባላት ፣ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የስራ ኃላፊዎች ፣ የህብረት ስራ ኮሚሽን አመራሮች ፣ በየደረጃው እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የሚገኙ የመምህራን ማህበር አባላት ፣ ርዕሳነ መምህራን እንዲሁም ከየትምህርት ቤቱ የተውጣጡ የመምህራን ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ የመምህራንን አቅም እና ወቅታዊ ዋጋን ታሳቢ በማድረግ በቀረቡ የዲዛይን አማራጮች ዙሪያ በማህበር ለተደራጁ መምህራን ግንዛቤ በመፍጠር በቀጣይ በፍጥነት ወደ ግንባታ እንዲገቡ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ጠቁመው በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የመምህራን ማህበር አባላት እንዲሁም ከየትምህርት ቤቱ የመጡ ተወካይ መምህራንና የትምህርት አመራሮች የቀረቡትን አማራጮች መሰረት በማድረግ ለመምህራን ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡
ሀላፊው አክለዉም ቤት ለመምህራን መኖሪያቸው ብቻ ሳይሆን የስራ ቦታው ጭምር መሆኑን ገልጸው በፍጥነት በቅርብ ቀናት ውስጥ ወደ ስራ የሚገባ መሆኑን የተናገሩ ሲሆን ስራዉ እንዲሳካ እስካሁን ከፍተኛ አስተዋጽዎ ላበረከቱት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ፣ ለቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ እና ለህብረት ስራ ኮሚሽን ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ደንቃለም ቶሎሳ በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ እያደረገ ላለው ስራ ምስጋና አቅርበው የቀረቡ አማራጮች የመምህራኑን አቅም ታሳቢ ያደረጉ እና በፍጥነት ወደግንባታ የሚያስገቡ መሆናቸውን ተናግረው መምህራን የቀረቡትን አማራጮች በደንብ ተገንዝበው በፍጥነት ወደ ግንባታ በመግባት እንዲቻል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የግንባታ አማራጮች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች አስተዳደር ቢሮ የዲዛይን ዝግጅት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሆኑት በአቶ ጳውሎስ ታምራት ከዲዛይን ዝግጅት ፣ ከቤቶች ካሬ ስፋት እንዲሁም ከዋጋ መጠን አኳያ አቅርበዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
2025/07/06 00:38:39
Back to Top
HTML Embed Code: