Telegram Web Link
አራት ትውልድ በአንድ መድረክ!
አራት ትውልድ በአንድ መድረክ!

ታማኝ በየነ በቅርቡ በመላው ኢትዮጵያ የተጎዱ ወገኖቻችንን ለመደገፍ ያለመ የሙዚቃ ኮንሰርት ለማዘጋጀት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ከሰብዓዊነት በቀር የወገንተኝነት ሀሳብ የሌለው ይኼ ዝግጅት ታማኝ በየነን የሚገልጸው እንደሆነ አምናለሁ። ታማኝ በዚህ ተግባር የኖረ ትልቅ ሰው ነው። ዛሬ ወይንም ትላንት አይደለም ለወገኖቻችን "አለሁ" ማለትን የጀመረው። በተለያዩ አጋጣሚዎች በወገኖቻችን ላይ ይደርሱ የነበሩ ጭቆናዎችን ካለበት ሆኖ ለዓለም ህዝብ ሲያስተላልፍና ድጋፍ ሲያሰባስብ ለወገኖቻችንም ብርታትና የፍትህ ድምጽ ሲሆን ኖሯል።

ታማኝ በየነ በ1979 በኢትዮጵያ በፖለቲካዊ እና በተፈጥሯዊ አጋጣሚዎች ተጎድተው የነበሩ ወገኖቻችንን ለመደገፍ በወቅቱ የነበሩትን አንጋፋና ወጣት ድምጻውያንን በማሰባሰብ ለወገኖቻችን ትልቅ ድጋፍ አድርገው ነበር። ዛሬም በእኛ እድሜ አራት ትውልዶችን በአንድ የሚያሳትፍ /ከአንጋፋ እስከ ወጣት ድምጻውያን/ የሚሳተፉበት ትልቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም አዘጋጅቷል። እኛም የዚህ መልካም ዓላማ ተሳታፊዎች በመሆናችንና በሙያችን ወገኖቻችንን ለማገዝ በመጠራታችን ብሎም የቀደሙ የሙያ አጋሮቻችን የፈጸሙትን ተግባር ለመፈጸም በመብቃታችን ትልቅ ደስታ ይሰማናል።

አርቲስት ታማኝ በየነ ወገኖቻችንን ለማገዝ ያለመሰልቸት የሄድክበትን እርቀት እናደንቃለን። ለፈጸምካቸውም መልካም ተግባሮች በሙሉ ከልብ እናመሰግናለን።

ነገን የተሻለና ያማረ ለማድረግ፥ ለመጪው ትውልድም ይሁን አሁን ላለው ዜጋ ምቹ የሆነ አገር ለመፍጠር አንድነታችን አማራጭ የሌለው የጉዟችን ስንቅ ነው። በአንድ ገበታ ተመግበው በአንድ መድረክ ለአንድ ቅዱስ ዓላማ ቆመው ያለፉ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ያሉን እድለኛ ትውልዶች ነን። ከነሱ የወረስነውን መልካም ተግባር እንደግማለን። ምክንያቱም የኔ ትውልድ የአባቶቹ ልጅ የሆነ ጀግና ትውልድ ነው።

ያሬድ ነጉ
የኔ ትውልድ የአባቶቻችንን ታሪክ ይመልሳል!

💚💛❤️

https://youtu.be/VxtAy6-hSIc
ተጠመቅን ዳንን!

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሰን አደረሳችሁ!
የደራሮን በአል አስመልክቶ በጌዴኦ ምድር በዲላ ከተማ ከጌዴኦ ብሔረሰብ ጋ አስደሳችና ምርጥ የፍቅር ጊዜ አሳልፈናል። እንግዳ ተቀባዩ የጌዴኦ ብሔረሰብ ከወጣት እስከ አዛውንቱ ፍቅርን የሚያውቅ ታላቅ ህዝብ ነው።

የጌዴኦ ብሔረሰብ የዘራውን ላሳጨደው፣ ዓመቱንም ከክፉ ለጠበቀው ፈጣሪው ምስጋና የሚያቀርብበትን በዓል አብረን በማክበራችን ፍጹም ደስተኞች ነን። የአመት ሰው ይበለን።

በልዩ ልዩ ድንቅ እሴቶቻችሁ እና በፍጹም ጨዋነታችሁ የምትታወቁ መላው የጌዴኦ ብሔረሰቦች ስለነበረን ቆይታ ከልብ እናመሰግናለን። ከቁጥር ሳያጎድል ዳግም በሰላም ያገናኘን!

ያሬድ ነጉ

https://youtu.be/AzlDt-BRoFs
ድምጼን ለምስኪኑ ለወገኔ!

በሳውዲ አረቢያ እስር ቤት የሚገኙ ወገኖቻችን ለብዙ ወራቶች ይኼ ነው በማይባል ስቃይ ውስጥ ነው የሚገኙት። የሚቆረቆርላቸው ህዝብና መንግስት እንደሌለ ሁሉ፥ ከሰብዓዊነት የሞራል ስብዕና በወረደ እይታ እየታዩ እንደሆነ በሚያሳብቅ መልኩ ያለ ፍትህ በእስር ቤት ተጥለው በባዕድ አገር ትልቅ ስቃይ ውስጥ ይገኛሉ። ይኼ እንደ አገርም ሆነ እንደ ሰብዓዊ ፍጡር የሚኮነን ተግባር ነው። በባዕድ አገር ያለ ስቃይ ህመሙ ቀላል እንዳልሆነ ሁሉም ይረዳዋል። የሚመለከተው የመንግስት አካልም ሆነ መላው ህዝባችን ይኼንን ግፍ በጽኑ ሊያወግዝና መፍትሄ ሊያፈላልግ ይገባል። ብርቱ ሰዎች በግል ጉዳያቸው የቱንም ያህል የተጠመዱ ቢሆኑም ሌሎች በስቃይ ውስጥ የሚገኙ ወገኖቻቸውን ለማገዝ በጭራሽ ወደኋላ አይሉም የሚል ጽኑ እምነት አለኝ። በስቃይና በድካም ውስጥም ብንገኝ የወገኖቻችንን ጥቃት አንፈቅድም። ትኩረት ይገባቸዋልና በሳውዲ እስርቤት ውስጥ ለሚሰቃዩ ወገኖቻችን ድምጻችንን እናሰማለን!!!

ያሬድ ነጉ!
Afro East Carnival Concert!

የምስራቅ አፍሪካ ወጣት እና እውቅ ሙዚቀኞች የሚሳተፉበት "አፍሮ ኢስት ካርኒቫል የሙዚቃ ኮንሰርት" በአገረ ታንዛኒያ ይካሄዳል። ኢትዮጵያን ወክዬ እኔ የምሄድ በመሆኑ እና እንዲህ ያሉ አጋጣሚዎች ለአገራችን የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ከፍታ መልካም አጋጣሚ ናቸው ብዬ ስለማምን እጅጉን ደስተኛ ነኝ። እንዲህ ያሉ ጥበባዊ መድረኮች የአገራችን ወጣት ሙዚቀኞች ከሌላ አገር ሙዚቀኞች ጋ ተጣምረው የመስራት ሞራላቸውን የሚያነቃ ሲሆን የአገራችንን የሙዚቃ ባህሪ ለሰፊው ዓለም ህዝብ ለማድረስም ቀላል መንገድን ያቀናል።

ታላላቆቻችን የደከሙለት ኪነጥበባዊ ሙያ በዚህ ልክ ተከብሮ ከጎረቤት አገር ዝነኛ አርቲስቶች ጋ በአንድ መድረክ ላይ ለጉራማይሌ አድማጮች የአገራችንን የሙዚቃ ምት ብሎም ኢትዮጵያዊ ዜማችንን ለሌሎች የአፍሪካ ወንድሞቻችን ለማቅረብ መብቃት እንደ ወጣት አርቲስት የምደሰትበት ሲሆን እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ የምኮራበት የህይወቴ መልካም አጋጣሚ መሆኑን ለመግለጽ እወዳለሁ።

በሁሉም መስክ ኢትዮጵያ ተሳክቶላት ፊት መሪ እንድትሆን እመኛለሁ። 💚💛❤️

ያሬድ ነጉ
እውነት እና እምነት ያለው ሰው ጽኑ ነው። 'ረጅም የድል መንገድንም ይጓዛል። በዳኛም ሆነ በከሳሽ ፊት በፍጹም አንገቱን አይደፋም። እውነቴን ይዤ እምነቴን አጥብቄ እኖራለሁ። አዎ! እኖራለሁ በከንቱ ሳይሆን በእውነት እኖራለሁ። ምክኒያቱም እውነትም እምነትም አንድ ነው።

ያሬድ ነጉ
በህይወት ጉዞ ውስጥ ብዙ ገጠመኞች ይመጣሉ። አብዛኛዎቹ ገጠመኞች በተለያዪ መልኮች የምንፈተንባቸው ናቸው። ከነዚህም መኃል ጽናታችንን፣ ትዕግስታችንን፣ ደግነታችንን /ልባችንን/ የሚፈትሹ ይሆናሉ። በሶስቱም መስፈርቶች የበቃን ብንሆን የተፈጥሮን ስርዓት በተወሰነ መልኩ የጠበቅን እንሆን ነበር። ጽናት፣ ትዕግስት እና ደግነት መጥፎ ለተባሉ ለብዙ ክስተቶች መክሸፍ ምክኒያቶች ናቸው።

አባታችን ጽናትን፣ ትዕግስትን እና ደግነትን በልባችን ያኑርልን!

ያሬድ ነጉ

https://youtu.be/Cnsag5-D6JA
Channel photo updated
አብሮ የመስራት ባህል በአገራችን እንዲዳብር ወጣት ድምጻውያን በጥምረት የሚሰሯቸው ስራዎች እጅግ መበረታታት ያለበት ተግባር ነው። አለፍ ሲልም ከጎረቤት ሀገራት ባለሙያዎች ጋ የሚደረግ ኪነጥበባዊ ጥምረት ሊደነቅ እና ልዩ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ተግባር ነው።

የኪነጥበብ ሙያ፥ ቋንቋን፣ ባህልን እና አንድ ማህበረሰብን በልዩ ሁኔታ ለተቀረው ዓለም የሚያስተዋውቅ እንደመሆኑ መጠን በሚኖረው የስራ ጥራት ላይ ጥንቃቄ መውሰድ አስፈላጊ ነው። በተለይ ደግሞ ባህላችንን ለምንወድ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ጥንቃቄ ፍጹም አስፈላጊ ነው።

አርቲስት ያሬድ ነጉ ከታንዛኒያዊው አርቲስት ሪቫኒ ጋ በጥምረት የሰሩት ሙዚቃ በአማርኛ፣ በሶማሊኛ፣ በእንግሊዝኛ እና በአረቢክ ቋንቋዎች የተቀነቀነ ነው። ይኼ ጥምረት መልካም የሚባል ጥምረት ሲሆን ለሌሎች ወጣት ድምጻውያንም አዳዲስ የጥምረት እድሎችን የሚያመቻች ነው ብዬ አምናለሁ። በተጨማሪም በቀጣይ የኛን ሀገር የሙዚቃ ምት ከነርሱ የሙዚቃ ምት ጋ በማዋሃድ ብዙ ስራዎችን መስራት የሚያስችል ጥሩ ማነቃቂያ ነው።

https://youtu.be/zG0ZG11qcgk

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ያጉቴ ቁርጥ

ያጉቴ ቁርጥ እና ክትፎ ቤት ጥር 6 እና 7 የምረቃ ሥነስርዓት ተጀመረ።

በያጉቴ ቁርጥ እና ልዩ ቁርጥ ቤት ለዐይን የሚማርክ፣ ሲበሉት የሚጥም፣ ለስለስ ያለ ሥጋ ያገኛሉ።

ጥሬ ሥጋ፣ ክትፎ፣ ጎረድ ጎረድ፣ ሸክላ ጥብስ፣ ጎድን ጥብስ እና ሌሎችንም የምግብ ዐይነቶች አዘጋጅተን እንጠብቃችኋለን።

ይምጡና ይዝናኑ!

አድራሻ ቦሌ ቡልቡላ ማሪያም ሠፈር
ወንድማማቾች አጠገብ

ስልክ🤳 +251924038081

ያጉቴ ልዩ ቁርጥ እና ክትፎ ቤት
2025/10/15 20:18:32
Back to Top
HTML Embed Code: