🌐በፅሁፍ ላይ የሚታዩ ስህተቶች
📛በWhats'app ,facebook,Telegram
እና ሌሎችም በምንፃፃፍበት ጊዜ ልብ መባል ያለባቸው ነገሮች:-
🔹ሠለላሁ ዐለይሂ ወሠለም
صلى الله عليه وسلم
🔘የነብዩ ሙሐመድ ሥም በሚነሣበት ጊዜ ሰለዋት ማውረድ ግዴታ ነው❗
ነቢዩ ሠለላሁ ዐለይሂ ወሠለም ሥሥታም ሰው ማለት የእኔ ሥም ተነሥቶ ሰለዋት የማያወርድ ነው ብለዋል፡፡እንደዚሁም አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ ቁርኣን ላይ አላህ እና መልእክተኛው ነቢዩ ላይ ሰለዋት ያወርዳሉ፡፡
እናንተ ያመናችሁ ሆይ ነብዩ ላይ ሰለዋት አውርዱ በማለት አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ አዟል፡፡
🔹1/አላህ ሰለዋት ያወርዳል ማለት ነቢዩን ያወድሣቸዋል ፣ ከፍ ያደርጋቸዋል ማለት ነው፡፡
🔸ሰዎች ደግሞ ነብዩ ላይ ሰለዋት ማውረድ ማለት ለነብዩ ዱዓ ማድረግ ማለት ነው፡፡
📌የነብዩን ሠለላሁ ዐለይሂ ወሠለም ሥም በምናነሳበት ጊዜ በፅሁፍም ይሁን በቃል ሠለላሁ ዐለይሂ ወሠለም መባል አለበት፡፡
💥ሰሓቦች ነቢዩን "እርሶ ላይ እንዴት ነው ሰለዋት የምናወርደው" ብለው ጠየቋቸው ?
☄ነብያችን ሠለላሁ ዐለይሂ ወሠለም
( "አሏሁመ ሰሊ ዐላሙሐመድ ወዐለ ኣሊሙሐመድ... በሉ" ) ብለዋቸዋል፡፡
📌በዚህ የነቢዩ ሠለላሁ ዐለይሂ ወሠለም ሐዲስ መሠረት ሰለዋት የሚባለው፣ ወይም ደግሞ በትክክል አንድ ሰው ሰለዋት አውርዷል ማለት የሚቻለው ሠለላሁ ዐለይሂ ወሠለም ሲል ነው ወይም (አሏሁመ ሰሊ ወሠሊም ዐለይሂ .. ወዘተ) ሲል ነው፡፡
♨ በተረፈ ከዚህ ውጭ በአማርኛ (ሠ,አ,ወ) ተብሎ አጫጭር ፊደሎችን መፃፍ ተገቢ አይደለም ሰለዋት ዐለ ነቢይ ሙሉ በሙሉ መፃፍ አለበት፡፡
🔹2/ ሱብሐነሁ ወተአላ
سبحانه وتعالى
የሚለውንም በተመለከተ ከተፃፈ ሙሉ በሙሉ መፃፍ አለበት እንጂ (ሰ,ወ,አ) ተብሎ አይፃፍም፡፡
🔸3/ ረዲየሏሁ ዐንሁ የሰሀቦች ሥም በሚነሳበት ጊዜ አህለ ሱና ወል ጀመአ የሁሉም ሰሓቦች ሥም ሲነሣ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) ይባላል ዐሊይ ኢብን አቢ ጣሊብንም ጭምር ማለት ነው፡፡
ምክኒያቱም አንዳንዶች ዐሊይ ሲባል ከረመሏሁ ወጅሀሁ ይላሉ ይህ ቢድዓ ነው፡፡
ለዐሊይ ብቻ ተለይቶ አይባልም! ከተባለ ለሁሉም ሰሀቦች ከረመሏሁ ወጅሀሁ ከተባለ ምንም አይደለም፡፡
የየትኛውም ሰሀቢይ ሥም ከተነሳ ረዲየሏሁ አንሁ ይባላል፡፡
☄ ሴት ከሆነች ረዲየሏሁ ዐንሃ ይባላል፡፡
🔗አባትም ልጅም ሙስሊም ከሆኑ ደግሞ ረዲሏሁ ዐንሁማ ይባላል፡፡
♻ ለምሳሌ አዒሻ ብንል ረዲየሏሁ ዐንሁማ ይባላል፡፡አባቷም ሙስሊም ስለሆነ ማለት ነው፡፡
☄እሱ ብቻ ሙስሊም የሆነ ከሆነ ግን አባቱ ካልሠለመ ረዲየሏሁ ዐንሁ ይባላል፡፡
✨በዚህ አንዳንድ ሠዎች ይሳሳታሉ አባቶቻቸው ሙስሊም ያልሆኑ ሰሓባዎችን ረዲሏሁ ዐንሁማ ይላሉ ይህ ትልቅ ስህተት ነው፡፡
ለምሳሌ፦ (አቡ ሁረይራህ ረዲየሏሁ ዐንሁማ) ይህ ስህተት ነው ትክክለኛው
( አቡ ሁረይረህ ረዲየሏሁ ዐንሁ) ነው
🔸 ረዲየሏሁ ዐንሁ በሚፃፍበት ጊዜ ሙሉ በሙሉ መፃፍ አለበት፡፡(ረ,አ) ተብሎ መፃፍ የለበትም፡፡
🔹4/ ( አሠላሙ ዐለይኩም )
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ብለን በምንፅፍበት ጊዜም ይህ አይነት ችግር አለ ብዙ ሠዎች (as wr wb ) ብለው ይፅፋሉ፡፡ ሲመልሡም (ws wr wb ) ብለወ ይፅፋሉ
💎ኢሰላማዊ ሰላምታን በዚህ መልኩ መፃፍ ተገቢ አይደለም፡፡
ከተቻለ አሠላም ዐለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ ብለን ሙሉውን ሰላምታ እንፃፍ ካልቻልን ግን አሰላም ዐለይኩም ብቻ ብለን እንፃፍ
ለመጀመሪያው መልስ:-
🔸(ወዐለይኩም አሠላም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ)
ለሁለተኛው ደግሞ
🔹(ወዐለይኩም አሠላም) ብሎ መመለሥ ዋጂብ ነው፡፡
📌አሏህ በተከበረው ቃሉ የሚከተለውን ብሏል
( ሠላምታ ከቀረበላቸሁ የቀረበላችሁን ዓይነት ሠላምታ መልሡ፣ ወይም የተሻለ መልስ መልሱ )
🔗አንዳንድ ሰዎች ወመጝፊረቱሁ ወሪድዋኑሁ የሚሉት ነገር ተገቢ አይደለም፡፡❎
ከረሱል ሠለላሁ አለይሂ ወሠለም አልተገኘም፡፡
አሠላም ዐለይኩም ብሎ ለፃፈ ሠው ወዐለይኩም አሠላም ብለን እንመልሣለን እንጂ w w w ወይም
ws wr wb ተብሎ አይመለስም
⭐እነዚህ አራት ነጥቦች ኸይር ሥራ ናቸው፣ የሙስሊም መለያ እና መታወቂያም ናቸው፡፡
🔸ሙስሊም ሰዎች ሲገናኙ አሠላም ዐለይኩም ፣
🔹የአላህ ስም ሲነሳ ሱብሓነሁ ወተዓላ( ዐዘ ወጀል) ይባላል፡፡
🔸የነብዩ ሥም ሲነሳ ዐለይሂ ሥሠላቱ ወሠላም (ሠለላሁ ዐለይሂ ወሠለም) ይባላል፡፡
🔹የሰሓቦች ሥም ሲነሳ ረዲየሏሁ ዐንሁ (ዐንሁም) አላህ ስራቸውን ይውደድላቸው ይባላል፡፡
👉 እነዚህ ሁሉ ዒባዳ ከመሆናቸው አንፃር ድካምና ጊዜ ይጠይቃሉ ጊዜያችንን መሥዋዕት አድርገን ልንፅፍና መልስ ልንሰጥ ይገባል፡፡
ቸኩዬ ነው እንዲህ ሆኜ ነው ወዘተ የሚሉት በቂ ምክንያት አይደሉም
💎ዒባዳ እሥከሆነ ድረስ ልንደክምበት ይገባዋል
📍ሌላው ከዚህ የተለየ በ whatsapp, facebook እና በሌሎችም ሰዎች በሚፃፃፉበት ጊዜ የሚፈፀሙት ስህተት አለ፡፡
እርሱም :- ቁርአንን ከዐረብኛ ውጭ በሆነ ፊደል መፃፍ ነው ይህ ደግሞ በጥብቅ የተከለከለ ነው❗ ዑለማዎች ሐራም ነው ብለዋል።❎
🚩ቁርአንን በማንኛውም ከዐረብኛ ውጪ ባሉ ቋንቋዎች መፃፍ አይቻልም❗ነገር ግን ትርጉሙን መፃፍ ይቻላል፡፡
💎አላህ ጠቃሚ ዕውቀት ከመልካም ስራ ጋር ይወፍቀን፡፡ አሚን❗
ወሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱሏህ
✍ኡስታዝ አሕመድ ኣደም
🔗ቅንብር ቢንቱ ሙሐመድ
@yasin_nuru @yasin_nuru

↪የሴት ልጅ መሕረሞች እነ
ማን ናቸው?
↪ለምንስ አስፈለገ?!
🚩ውዱ ነቢያችን
የሚከተለውን ብለዋል
("በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምን ሴት ከሷ ጋር መሕረም ሳይኖራት መጓዝ አይፈቀድላትም " )
💥ሴት ልጅ ለብቻዋ ( መሕረም ሳይኖራት) መጓዝ የምትችለው ለሂጅራ (በሀገሯ እምነቷን በአግባቡ መከተል ተከልክላ ስትሰደድ) ብቻ ነው።
ለሴት ልጅ (በየትኛውም እድሜ ላይ ብትኖር)
⛤መሕረም ያስፈለገበት አንዱ ምክንያት ሴት ልጅን ከተለያዩ ድንገተኛና የሚገመቱ ከሆኑ መንፈሳዊም ይሁን አካላዊ ጉዳቶችና ጥቃቶች ለመጠበቅ ሲሆን ይህን ኀላፊነት መወጣት የሚችሉ ሰዎች እነማን እንደሆኑና የሴት ልጅ መሕረም ማን እንደሆነ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እራሳቸው ገልጸዋል እነሱም የሚከተሉት ናቸው:-☞☞
🔮(አባትና አያት፣ ባል፣ወንድ ልጅና የልጅ ልጆቿ፣ ወንድሞች የወንድምና የእህት ልጆች፣ በአባትም ይሁን በእናት በኩል ያሉ አጎቶች (የወላጆቻችን ወንድሞች)፣ የወላጆቻችን አጎቶች፣ የጡት ወንድሞች፣ የአንዲት ሴት የሴት ልጇ ባል (አማች)፣ የእንጀራ አባት
( የእናት ባል) ሲሆኑ ከዚህ ውጭ ያሉ ወንዶች ቀረብ ያሉ ዘመዶች እንኳን ቢሆኑ
📌ለምሳሌ፥ (የአጎትና የአክስት ልጆች) መሕረም መሆን አይችሉም!
↪ይህን የሸሪዓ ህግ በመጣስ መሕረም ከማይሆኗቸው ወንዶች እየተጓዙ የተለያዩ ጥቃቶች የደረሱባቸው ብዞዎች ናቸው!
አይደለም ራቅ ያለ ዘመድና ባዕዱ ይቅርና ከላይ ከተጠቀሱ ቅርብ ዘመዶችና መሕረም ሊሆኑ ከሚችሉ ሰዎች ውስጥም አንዱ በመጥፎ ስነምግባር የሚታወቅና የሴትን ክብር አይጠብቅም የሚባል ሰው ከሆነ ከሱ ጋር መጓዝ አይፈቀድላትም!
💥ትክክለኛ መሕረም ይሆን ዘንድ ታማኝና ከሴት ልጅ አደጋን መከላከል የሚችል መሆን አለበት ፣እድሜውም ጠቃሚና ጎጂን ለይቶ ለማወቅና ጥቃትን ለመከላከል የደረሰ መሆን አለበት፣ እንደዚሁም
ጾታው ወንድ መሆን አለበት ✅
↔ሴት ለሴት በየትኛውም መልኩ መሕረም ልትሆን አትችልም❗
🔸በዘመናችን በርካታ ሴቶች በሸሪዓው መሕረም ከማይሆናቸው ወንድ ጋ ለብቻቸው መኪና ላይ ሲጓዙ
ይታያል!ይህ ትልቅ ስህተትና ዲኑ የማይፈቅደው ተግባር ነው!ረጅም ጉዞ ባይሆንና ከተማ ውስጥ እንኳን ቢሆን አይቻልም!❎
♨ምክንያቱም ነቢያችን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የሚከተለውን ብለዋል
(" አንድ ወንድ ከባዕድ ሴት ጋ ተነጥሎ ለብቻቸው አይቀመጡም ሶስተኛው ሸይጣን ቢሆን እንጂ! ")
መቼም ሸይጣን ባለበት ቦታ ላይ መጥፎ ነገር ማሰብ ወይም መከሰቱ የማይቀር ነው
🔸"ተነጥለው ለብቻቸው" የሚለው ነብያዊ ቃል ቤት ውስጥ አንድ ክፍል ላይ መሆንን ብቻ ሳይሆን መኪና ውስጥ ለብቻቸው መጓዝንም ጭምር እዚህ ውስጥ እንደሚካተት በዘመናችን ያሉ ዑለማዎች ገልጸዋል!
በዚህ መልኩ ለብቻቸው ከከተማ የወጡና ራቅ ብለው የሄዱ እንደሆነ ጥፋትና ቅጣቱ የተነባበረ ይሆናል አደጋውም ይከፋል!
ይህን ነቢያዊ መመሪያ የጣሱ በርካታ እህቶችም አምነዋቸው አብረዋቸው ይጎዙ በነበሩ ሾፌሮች ወደውም ይሁን ተገደው ተደፍረዋል!!
ህይወታቸው ላይም ብዙ ችግሮች ደርሷል የሰው ልጅ ደካማ ነው ስሜት በሩ ካልተዘጋጋ ሁሉንም ሊያጠቃ የሚችል ነገር ነው! ዛሬ ያልተከሰተው ነገ ሊከሰት ይችላል!
🔹ከተማ ውስጥም ቢሆን ከአጅነቢይ ሾፌር ጋ ለመሄድ ከተገደዱ ከነሱ ጋ ሌላ ሶስተኛ ታማኝ ሰው አብሯቸው ሊኖር ይገባል።
🔸እንደዚሁም በየትኛውም መልኩ ከአጅነቢይ ወንድ ጋ ( ማንም ይሁን ማን) በር ዘግተሽ አትቀመጪ!
⛔አንድ ክፍል ውስጥም ከባዕድ ወንዶች ጋ ተቀላቅለሽ አታሳልፊ የራስሽንም ይሁን የወንድሞችሽን ኢማን ለአደጋ አታጋልጪ! ዘመኑ የፊትና ነው የብዙዎች ቀልብ ደርቃለች አኼራም ተረስቷል፣አላህን ከማስቀይም ተጠንቀቂ! ነገ መገናኘታችሁ አይቀርምና!
✨አላህ ከክፉና እሱንም ከሚያስቆጣ ነገር በሙሉ ይጠብቅሽ!

ስማኝ ወንድሜ! ዕድሜህ ከ30 ዓመት በታች ከሆንክ አንብበው — ምክንያቱም እነዚህ 10 ስህተቶች ህይወትህን ሙሉ ድሃ አድርገው ያስቀሩሃል ... .
ይህ በሃያዎቹ ዕድሜያቸው ውስጥ ለሚለፉ፣ ነገር ግን ትኩረታቸው ለተሰረቀ፣ ወይም ህይወት ውለታ እንዳለባት ለሚያስቡ ወጣቶች ሁሉ ማስጠንቀቂያ ነው፡፡
ከ30 ዓመት እድሜህ በፊት የምትወስናቸው ውሳኔዎች ወይግዛትህን ይገነባሉ ወይ ደግሞ አቅምህን ይቀብራሉ፡፡
ጠጋ በል፣ አእምሮህን አሰራው — ከ30 ዓመት በፊት ወንዶች የሚሰሯቸው ድሃ፣ ግራ የተጋቡና አቅመ ቢስ ሆነው እንዲቀሩ የሚያደርጓቸው 10 አደገኛ ስህተቶች እነሆ፡
1. ዓላማን ከማሳደድ ይልቅ ሴቶችን ማሳደድ የሃያዎቹ ዕድሜህ ራስህን ለመገንባት ነው — ቆንጆ ሴቶችን ለማስደመም አይደለም፡፡
ሴቶች ሁሌም ይኖራሉ፣ የማግባት ጊዜህም ይመጣል ። ሴቶች አንተን እንዲያሳድዱ የሚያደርግ ህይወትን በመገንባት ላይ አተኩር።
2. የ9-5 ስራ በቂ ነው ብሎ ማሰብ ወርሃዊ ደሞዝህ በረከት ይመስልሃል?
በጎን ሌላ ነገር የማትገነባ ከሆነ ወጥመድ ነው፡፡ ንግድ ጀምር። ክህሎት ተማር። ጊዜህን መልሰህ ግዛ።
3. ለማደግ ከመዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ይልቅ ለማስደመም ማውጣት
ያ አይፎን፣ የዲዛይነር ጫማዎች፣ በክለብ የምትጠጣቸው መጠጦች — የወደፊት ህይወትህን በዝምታ እየገደሉ ናቸው፡፡ ሀብት እንጂ እዳ አታከማች። ገንዘብህን አባዛው እንጂ አታባክነው፡፡
4. መርዛማ ጓደኞችን እና ስሜታዊ ጥገኛዎችን ማቆየት የጓደኞችህ ስብስብ እንድታድግ የማይገፋፋህ ከሆነ፣ ወደ ኋላ እየጎተቱህ ነው፡፡
ለመካከለኛነት ኑሮ ታማኝ መሆን የለብህም፡፡ ቁረጣቸውና ከፍ በል።
5. ከሴቶች ጋር ስሜታዊ ድክመት ማሳየት ሴት እንድትሰድብህ፣ እንድታታልልህ፣ ችላ እንድትልህ ትፈቅዳለህ — እና አሁንም ትለምናለህ? ወንድሜ፣ አቋምህን አስተካክል። ሴቶች የሚያከብሩት ሀይልንና ድንበርን ብቻ ነው፡፡
6. መፅሐፍትን፣ መማርን እና ራስን ማስተማርን ችላ ማለት ሳምንቱን ሙሉ ፓርቲ ማድረግ፣ መፅሐፍ ማንበብ የለም፣ እድገት የለም?
በ30 ዓመትህ ግን ህይወት ታስተምርሃለች፡፡ አንብብ። ተማር።
7. ገንዘብ እንዴት እንደሚሰራ አለመማርታገኛለህ። ታወጣለህ። ትከስራለህ። ትደግመዋለህ። ገንዘብን እንዴት መቆጠብ፣ ኢንቨስት ማድረግ፣ ማባዛት እና መጠበቅ እንዳለብህ ተማር።
7. ገንዘብ እንዴት እንደሚሰራ አለመማርታገኛለህ። ታወጣለህ። ትከስራለህ። ትደግመዋለህ። ገንዘብን እንዴት መቆጠብ፣ ኢንቨስት ማድረግ፣ ማባዛት እና መጠበቅ እንዳለብህ ተማር። ገንዘብ ወደ ስሜታዊ ሰው አይመጣም — ወደ ስልታዊ ሰው ነው የሚመጣው፡፡
8. ያለ ዲሲፕሊን ወይም መዋቅር መኖርበፈለግከው ሰዓት መነሳት። ሁሌም የጊዜ ሰሌዳ የለህም፡፡ ምንም ግብ የለህም። ይህ የተሸናፊዎች አኗኗር ነው፡፡ ቀንህን አዋቅር፣ ጊዜህን ተቆጣጠር፣ እና በዓላማ ተንቀሳቀስ።
9. ጊዜ አለ ብሎ ማሰብ ጊዜ የለም ወንድሜ። ህይወት ቀድሞውኑ እየሮጠች ነው፡፡ በ30 ዓመትህ፣ እኩዮችህ ዋና ስራ አስፈፃሚዎች፣ የቴክኖሎጂ ግዙፎች፣ ባለሃብቶች ይሆናሉ፡፡ አሁንም ''ነገሮችን እየደረስኩበት ነው'' የምትል ከሆነ፣ ህይወት በየጠዋቱ በጥፊ መምታት ትጀምርሃለች።
10. ሁሉንም ሰው ማመን ሁሉም ሰው ጓደኛህ አይደለም፡፡ ሁሉም ሴት እጣ ፈንታህ አይደለችም፡፡ ብልህ ሁን። እቅዶችህን በዝምታ ያዝ። ጉልበትህን ጠብቅ። የወደፊት ህይወትህ በማስተዋልህ ላይ የተመካ ነው፡፡
ስለዚህ እንደ ተዋነይ የምመክርህ :
የሃያዎቹ ዕድሜህ ለጨዋታ አይደለም — ቦታ ለመያዝ ነው፡፡ ከ30 ዓመትህ በፊት የምትገነባው ነገር ከፍ እንደምትል ወይም በመካከለኛነት ውስጥ እንደምትበሰብስ ይወስናል።
እኩዮችህ TED Talks ሲሰጡና በግል አውሮፕላን ሲበሩ አንተ የጸጸት ታሪኮችን የምትናገር ሰው አትሁን።
ወንድ ሁን። ራስህን አስተካክል። ንቃ።
Bini Girmachew-እንደወረደ የቀረበ

"ይሻላል!"
🔸ከመጥፎ ጓደኛ ☞ብቸኝነት ይሻላል
🔹ከማይረባ ወሬ ☞ዝምታ ይሻላል
🔸ከዝምታ ይልቅ☞ ዚክር ማለት ይሻላል
🔹ከፍልስፍናና ከአህለል ቢድዓ ዕውቀት☞ ጅህልና ይሻላል
🔸ከመጥፎና አላህን ከማይፈራ የትዳር አጋር☞ ላጤነት ይሻላል
🔹መጥፎ ከሆነና በሁለቱም ዓለም ከማይጠቅም ልጅ☞ መሀንነት ይሻላል
🔸ለይል ሲሰግዱ አድሮ በማግስቱ ከማውራት☞ፈርድ ሰግዶ ተኝቶ ማደር፣ ጾምኩኝ ለማለት ከመጾም ደግሞ
☞ እየበሉ መዋል ይሻላል
🔹የማይረባ ነገር እየሰሩ ወይም አላህን እያስቀየሙ ቁጭ ብሎ ከማደር☞ ተኝቶ ማደር ይሻላል
🔸ሰደቃ ሰጥቶ ከመመጻደቅ
☞ አለመስጠትና መልካም ንግግር ይሻላል
🔹ሰውን ከማማት
☞መምከር ይሻላል
🔸ሰውን ከመመቅኘት
☞ እርሱ ከደረሰበት ለመድረስ መስራት ይሻላል
🔹ውስጥን ሳያጠሩ ውጭን ከማሳመርና ብዙ ስራን ከመስራት
☞ውስጥ ጠርቶና ተስተካክሎ ትንሽ ስራ መስራት ይሻላል
🔸በርካታ ሙሓደራዎችን ከማድመጥ ☞ትርጉሙን የሚያውቁትን አንድ የቁርኣን አንቀጽ እያስተነተኑ ደጋግሞ ማድመጥ ወይም ማንበብ ይሻላል
🔹የካፊር ፀባዩ ምንም ቢያምር ከርሱ☞ የፀባይ ችግር ያለበት ሙስሊም ይሻላል
🔸ከሰነፍና ደካማ ሙእሚን
☞ ንቁና ጠንካራ ሙእሚን ይሻላል
🔹ዱኒያ ላይ ስሜትን እየተከተሉ ከመዝናናት ☞ላጭር ጊዜ ስሜትን ተቆጣጣሮ ጀነት ላይ ሁሌም መደሰት ይሻላል
🔸ሰዎችን ከመለመንና ከነሱ ስጦታ
☞አላህና የርሱ ስጦታ ይሻላል!

ውሸት የሙናፊቅነት ምልክት❗
🔸አላህ በተከበረው ቃሉ
"ምእምናን ሆይ፥ አላህን ፍሩ ከእውነተኞች ሁኑ" ብሏል
🔹ውዱ ነቢያችንም፥ صلى الله عليه وسلم ሙስሊም እንደማይዋሽና ውሸት የሙናፊቅ ባህሪ እንደሆነ ገልጸዋል!
🔸ሁሉንም ዓይነት ውሸት እንጠንቀቅ
በተለይ ደግሞ ለዲን ጥቅም ብዬ ነው እያሉ መዋሸት ትልቅ ጅልነት(ሞኝነት) ነው!
▫ለቀልድና ለጫወታም እያሉ ቢሆን አይቻልም
▪ውሸት በዱኒያ ውርደት በኣኺራ ቅጣት ያስከትላል!
▫ውሸታም ዝምድናን ያቆራርጣል
ወዳጆችን ይለያያል
▪በህይወትና ሪዝቁም በረካን ያጣል
አላህ በሁለቱም ዓለም ከሳዲቆች ያድርገን!

አላህን መፍራትና ትሩፋቶቹ
🔹አላህን መፍራት ማለት፥ ያዘዘውን በመታዘዝና የከለከለውን በመከልከል በእኛና በአላህ ቅጣት መሀል መከላከያ አጥር ማጠርና መጠንቀቅ ማለት ሲሆን
🔸ወንጀልን በሙሉ በመራቅ መልካም የተባሉ ስራዎችን ሁሉ የሰራ ሰው የተሟላ የአላህ ፍራቻ ባለቤት ነው
🔹ወንጀል በተዳፈርንና ግዴታዎችንም በተውን ቁጥር ለአላህ ያለን ፍራቻ እቀነስ ይሄዳል
🔸አላህን በዱኒያ እያለ የፈራው ሰው ኣኺራ ላይ ሙሉ ሰላም ይሰጠዋል
ዱኒያ ላይ ግን ያልፈራው ሰው ኣኺራ ላይ ሰላም አያገኝም!
💥አላህን በመፍራት፥
1/ወንጀል ይሰረዛል
2/ ጥሩና መጥፎ ለይቶ ማወቅ የሚያስችል የንጹህ ተፈጥሮ/አዕምሮ ባለቤት መሆን ይቻላል
3/መልካም ስራዎች ሁሉ ገር ይሆናሉ
4/ ከሁሉም ዓይነት ችግርና መከራዎች መውጫ ቀዳዳ ይገኛል ጉዳዮቻችንም ገር በገር ይሆናሉ
5/ ካልታሰበ አቅጣጫ ሪዝቅ ይመጣል (ዱኒያ ብቻ ሳይሆን ጠቃሚና አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች በሙሉ)
6/ ስራችን ያማረ ይሆናል
ከወንጀልም እንጠበቃልን
7/ ህይወቱን በዲን ላይ ቀጥ ብሎና አላን በመፍራት ላይ ያሳለፈ ሰው አላህ ኻቲማውን ያሳምርለታል

🍃"13ቱ" የጥሩ ሚስት መገለጫዎች🍃
① የትም ብትሆን አላህን ትፈራለች፣ በሁሉም ነገር የነቢዩን ሱና ትከተላለች
②ባሏ ያዘዛትን በሙሉ -ከዲን ጋር የሚጋጭ እስካልሆነ ድረስ- ትታዘዛለች
③ከሷ ጥሩን ነገር እንጂ እንዳያይ፣ እንዳይሰማና እንዳያሸት ጥረት ታደርጋለች
④ቤትና ንብረቱን እንዲሁም
ቤተ-ሰቦቹን ትጠብቃለች
⑤እሱ የማይፈልገውን ሰው
አትጠጋም አታስጠጋምም
⑥ ባሏን ሳታሳውቅ ሱና ጾም አትጾምም
ከቤትም አትወጣም
⑦ የባሏንና የቤቷን ሚስጥር
በሚገባ ትጠብቃለች
⑧ ባሏን በመልካም ነገር ላይ
ታግዛለች ሲሰንፍ ታበረታታዋለች፣
ሲረሳ ታስታውሳለች
⑨ሐላል ከስብ እንዲከስብ ሐራምን እንዲርቅ ዘወትር ትገፋፋዋለች፣ለእሷና ለቤቱ ብሎ ዲኑ የማይፈቅደውን
ስራ እንዳይሰራም ታሳስበዋለች
①∅ ደስታና ሃዘኑን ትጋራለች፥
እርሱ ሐሳብና ጭንቀት ውስጥ ሆኖም እሷ አትስቅም፣ እሱ ማረፍና መደሰት በሚፈልግበት ወቅት ላይም እሷ በተቃራኒው ተከፍታ አታስከፋውም
①①በሚያደርግላት ነገር በሙሉ
ይብዛም ይነስ ታመሰግነዋለች
①② ቤቷን እያቀዘቀች የሰው ቤት አታሞቅም ቤቷንም እያፈረሰች የሰው ቤት አትገነባም!
①③ አላህ የሰጣትን ልጆች በኢስላም ስርዓት ቀርጻ ታሳድጋለች ትልቁ የእሷ ስራም ይህ እንደሆነ በማወቅ በስራዋ ትኮራለች! ልጅም ያጣች እንደሆነ ታግሳ ተስፋ ሳትቆርጥ ጌታዋን ትለምናለች
አበቃ
▫የጥሩ ባልን መገለጫ በቅርብ ቀን
ይጠብቁን ኢንሻአላህ
"ሁላችንም አላህ ሳሊሖች ያድርገን"

18ቱ የጥሩ ባል መገለጫዎች
🔸ጥሩ ትዳር መስርቶ መኖር የማንኛዋም ሴት ምኞት ነውvየጥሩ ትዳር መሰረቱ ጥሩ ባል ነው፣ከጥሩ ባል መገለጫዎች በጥቂቱ እነሆ፥
1/ በሁሉም ነገር አላህን ይፈራል
2/ ከሚስቱ ጋር በጥሩ ስነ-ምግባር ይኗኗራል
3/ በተቻለው ያክል ቃሉን ይሞላል
4/ ለሚስትና ለልጆቹ መልካም አርዓያ ይሆናል
5/ ንግግርና ተግባሩ አንድ ነው (አታላይ አይደለም)
6/ ሚስቱን ያከብራል ለሷ ያለውንም ፍቅር ይገልጻል
7/ ሸሪዓ የሰጣትን ሐቅ ይጠብቃል
8/ ዘመድና ቤተሰቦቿን ያከብራል
9/ በሆነ ባልሆነው አይጨቃጨቅም
10/ ትርፍ ቃል ከመናገር በመታቀብ በመልካም ንግግሮቹ ሚስቱን ያስደስታል
11/ ሚስቱ አላህን እንድትታዘዝና ዲኗን እንድታውቅ ይገፋፋል ያግዛታልም
12/ ስትደሰትም ይሁን ስትከፋ ስሜቷን ይጋራል
13/ ከሚስቱ ጋር በመተባበር ልጆቹን በኢስላማዊ አደብና እውቀት ቀርጾ ያሳድጋል
14/ ሚስቱ ጥሩ እንድትለብስለትና ጥሩ እንድትሸት እንደሚፈልገው ሁሉ እርሱም ከሷ ጋር ሲሆን ይሄን ያደርጋል የመላ ሰውነቱን ንጽህናም ይጠብቃል
15/ ቤቷን ሳትጎዳ ቤተሰቦቿን መጠየቅ ስትፈልግ ከመፍቀድም አልፎ የሚያስፈልጋትን ነገር እንደ አቅሙ ያሟላላታል
16/ ለቤቱ በቂ ወጪ ያደርጋል ለልጆቹና ለሱ በምታደርጋቸው ነገሮች ሁሉ ያመሰግናታል
ድምበር ሳያልፍ፥ አለባበሷን፣ ገጽታዋንና የምትሰራቸውን ምግቦች ያደንቃል
17/ በሁሉም ነገር ላይ እርጋታና ትዕግስትን ተላብሶ ይኖራል
18/ አለመግባባትና ግጭቶች ሲፈጠሩም ሚስቱን እንደ እህቱ በመቁጠርና ለሷ በማዘን ችግሩን ለመፍታት ብዙ ነገሮችን በመተውና ቁጣውን ዋጥ በማድረግ መፍትሄ ይፈልጋል::
አበቃ
አላህ ለርሰበርሳችን ጥሩዎች ያድርገን
ላገቡትም ላላገቡትም መልካምና ስኬታማ ትዳር ይወፍቀን

🍃ህልምና ቅዠት በኢስላም እይታ🍃
💥ዲነል-ኢስላም ህይወታችን ላይ ሊገጥሙን ለሚችሉ ነገሮች በሙሉ ህግና ስርዓት አስቀምጧል፣ይህን አውቀን መኖር፥ በዲናችን እንድንተማመንና ህይወትን ከሚረብሹ ነገሮችም ሰላም ለማግኘት ይረዳል
▪ብዙ ሰዎች በየጊዜው የሚያስጨንቅ/የሚያሳስብ ህልም አየሁ እያሉ ያወራሉ በርካቶችም የህልምን ፍቺ እንደፈትዋ ይጠይቃሉ! የምናየውን ሁሉ ህልም ፍቺ ለማወቅ መጣር ተገቢና አስፈላጊ አይደለም
▪የህልም ህግ በኢስላም ባጭሩ እንደሚከተለው ነው፥
🔸((ጥሩ ህልም ያየ ሰው ይደሰት ጥሩ ነገርም ይጠብቅ፣መጥፎ ህልም ያየ ሰው ደግሞ ቀጥሎ የሚገለጹ ነገሮችን ከማድረግ ጋር ችላ ብሎ ይተወው)) የሚል ነው
▪ይህ በእንዲህ እንዳለ፥
ነቢያችን صلى الله عليه وسلم ጥሩ ህልም ከአላህ እንደሆነና እንዲህ ዓይነቱን የሚያስደስት ህልም ያየ ሰውም፥
1/ አል-ሐምዱ ሊላህ الحمد لله
በማለት ጌታውን እንዲያመሰግን
2/ ለሚወዳቸው ሰዎችም እንዲናገር ሲመክሩ፤
🔹መጥፎ ወይም አስፈሪ ህልም (ቅዠት) ከሸይጣን እንደሆነ ገልጸው በዚህ የተጠቃ ሰውም፥
1/ ሶስት(3)ጊዜ
أعوذ بالله من الشيطان الرجيم
"አዑዙ-ቢላህ ሚነሽ'ሸይጣኒ'ርረጂም" በማለት ከህልሙ/ከቅዠቱ ክፋት በአላህ እንዲጠበቅ
2/ ሶስት ጊዜ ወደ ግራ "እትፍ- እትፍ" እንዲል
3/ ለማንም እንዳይናገር
4/ ህልሙን ሲያይ (ሲቃዥ) ተኝቶበት ከነበረው ጎኑ ወደሌላ ጎኑ ዞሮ እንዲተኛ
5/ ተነስቶም እንዲሰግድ መክረው፤
6/ ይህን ካደረገም ያየው መጥፎ ህልም ምንም እንደማይጎዳው ገልጸዋል
▪እነዚህ ምክሮች፥ ቡኻሪ፣ ሙስሊምና አቡ ዳውድ ከዘገቧቸው ሰሒሕ ሐዲሦች ተወሰደው የተቀናበሩ ናቸውና ህልም ባዩ ቁጥር ትርጉሙን ለማወቅ ወይም ደግሞ አደጋ ሊደርስብኝ ነው ብሎ ከመጨነቅ በመታቀብ የአዛኙን ነቢይ ምክር ተቀብሎ የተረጋጋ ህይወት መኖር ይበጃል::

በ40 አመትህ በኢኮኖሚ ምክንያት ያለማግባትህ ከሚያስጨንቅህ በ20ዎቹ እድሜህ ላይ ተፍ ተፍ እያልክ ጠንክረህ ሰርተህ በጊዜ ጎጆ ቀልስ!
🏷በወንጀል ምክንያት የሚመጣን ቅጣት ሊያስቀሩ የሚችሉ 10 ነገሮች
✨የአላህን ምህረት ማግኘት ትልቅ ዕድል ነው፣ወንጀላችንን ያለሱ ማንም ሊምረንና ይቅር ሊለን አይችልምና!
▪ሙእሚን ወንጀሉ ያሳስበዋል
▪ሙናፊቅ ግን ከምንም አይቆጥረውም
🔸ቁርኣንና ሐዲሥ የወንጀል መዘዙ ሰዎች/ሰሪዎቹ ላይ እንዳይደርስ የሚያደርጉ 10- ነገሮች እንዳሉ አመላክተዋል እነሱም፥
① ተውበት (ተጸጽቶ ወደ አላህ መመለስ)
②ኢስቲጝፋር ማድረግ
③ መልካም ስራዎችን ማብዛት
④ ስንሞት ሙእሚኖች የሚያደርጉልን ዱዓና ኢስቲጝፋር ለምሳሌ ሰላተል-ጀናዛ ላይ
⑤ ለሞተ ሰው የሚደረጉ መልካም ነገሮች ለምሳሌ ሰደቃ...
⑥ የነቢዩ صلى الله عليه وسلم ምልጃ
⑦ ሙእሚንን ዱኒያ ላይ የሚገጥሙ የተለያዩ ችግርና መከራዎች
⑧ የቀብር ጭንቀትና ፈተና/ድንጋጤ
⑨ የቂያማ ቀን መከራና ስቃይ
①∅ ከወንጀለኛው ወይም ከሰው ልጆች በኩል ምንም ሳይደረግ በአላህ እዝነትና ይቅር ባይነት በወንጀላችን ምክንያት ኣኺራ ላይ ይጠብቀን የነበረ ቅጣት ሊቀር ይችላል::
(ከሸይኹል-ኢስላም ንግግር የተወሰደ)
▪ወንጀልን መጀመሪያውኑ ከበሽታ በላይ እንጠንቀቅ ከተፈተንን ግን ተስፋ አንቁረጥ የአላህ ረሕመቱ ሰፊ ነው!
ከላይ ከተጠቀሱ ነገሮች በአንዱ ምክንያት ምህረትን እንደምናገኝ ተስፋ እናድርግ
ዛሬ ነገ ሳንልና ሞት ሳይቀድመን ተጸጽተን እንመለስ!
🔸መስፈርቱን ያሟላ ተውበት የማይሰርዘው ወንጀል የለም!
አብሺሩ ያ ዒባደላህ
(لَا تَقْنَطُوا مِنْ رَحْمَةِ الله)

#ዱኒያ ላይ የሚገኙ #3ቱ ከወንጀል መታጠቢያ ወንዞች:-
🏷ታላቁ ኢማም ኢብኑል -ቀይም የሚከተለውን ብለዋል:-
"لأهل الذنوب ثلاثة أنهار يتطهرون بها في الدنيا:
١- نهر التوبة النصوح
٢- نهر الحسنات المستغرقة للأوزار
٣- نهر المصائب المكفرة
📚الإمام ابن قيم الجوزية رحمه الله مدارج السالكين
🔷ወንጀለኞች ዱኒያ ላይ ወንጀላቸውን አጥበው የሚያስወግዱባቸው ሶስት(3) ወንዞች አሉላቸው:-
◼1ኛው/ ጥርት ያለና የተሟላ የተውበት (የጸጸትና የንሰሃ) ወንዝ፣
◼2ኛው/ ከብዛቱ የተነሳ ወንጅሎችን በሙሉ ሊውጣቸውና ሊሰርዛቸው የሚችል የብዙ መልካም ስራ ወንዝ፣
◼3ኛው/ ወንጀሎችን የሚያራግፉ ህይወት ላይ የሚገጥሙ አደጋና ችግሮች ወንዝ ናቸው።
🔶የአላህ ባሮች ሆይ፤ ወንጀል መርዝ ነው፣ የዱኒያም የኣኺራም ህይወታችሁን እንዳያበላሽ ተጠንቀቁት!
🔹አላንህም እርሱን ከሚያስቆጣ ነገር እንዲጠብቀን ዘወትር ለምኑት፣
🔸ባለፈው ህይወቱ እራሱን በወንጀል ያቆሸሸ ሰውም ከመሞቱ በፊት ከላይ በተጠቀሱና "ሙከፊራቱዝዙኑብ" በሚባሉ መሰል ነገሮች እራሱን ያጥራ!
✍🏻 ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም

ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ሊሞቱ 9ቀን ሲቀራቸው ምን ተፈጠረ!
ነብያችን ሊሞቱ 9ቀን ሲቀራቸው ከ ቁርኣን የመጨረሻ ኣያ ወረደች።
ሀጅ ካረጉ ቡሃላ የ ህመም ምልክት ይታይባቸው ነበር ከዛ በ ኡሁድ ጦርነት የሞቱት ቀብር ጋ ሄደው እንዲ አሉ ፡ የ አላህ ሰላም በናንተ ላይ ይሁን እናንተ ቀዳሚዎች ናችሁ እኛም አንከተላቹሀለን አላህ ካለ እኔም እቀላቀላቹሀለው አሉ..🤲
ነብዩ ለሞት 3ቀን ሲቀራቸው ህመሙ እየባሰባቸው ሙቀታቸውም በጣም ሲጨምር እንዲ አሉ ፡ ሚስቶቼን ሰብስቧቸው..❤️❤️
አስቡት ፡ ሁሉንም የጠሩበት ምክንያት ኣይሻ ቤት ሆኜ ልታከም ብለው ለማስፈቀድ ነው🤍🤍
ነብዩ መይሙና ቤት ነበሩ ከዛም ወደ ኣኢሻ ቤት ለመሄድ አቡበክር እና ፈድል ኢብን አባስ ደገፏቸው ነብዩ በዛ ሰአት ባጋጠማቸው ድካም እግራቸውን መሬት ላይ እየጎተቱ ሄዱ💔💔
ሰሃቦች የነብዩን ድካም ሲያዩ በጣም ደንግጠው መስጅድ ውስጥ ተሰብስበው ያወሩ ጀመሩ የአይሻ ቤት በሩ ክፍት ነበር ነብዩም የሰሃቦችን ድምፅ ሰምተው ምንድነው ሲሉ ለእናንተ ተጨንቀው ነው አሏቸው🥺
አሉ፡ ወደነሱ ውሰዱኝ ፣መቆም ይፈልጉ ነበር ግን አልቻሉም ሰሃቦቹ ደገፏቸው ሚንበር ለይ መውጣት ፈልገው አልቻሉም የሚንበሩ ደረጃ ለይ ቆመው ታዋቂውን ዳእዋቸውን አሉ😍
ሰዎች ሆይ ከሴቶች ጋር ባለህ ግንኙነት አላህን ፍሩ እኔ እመክራችኋለሁ።🥰
ከዛም ነብዩ አሉ የሆነ ሰው አላህ ከ ዱንያ አና አስመርጦት አሱጋ ያለውን ነገር ይመርጣል🥺🥺
እራሳቸውን ነበር የሚሉት ማንም አላወቀም ነበር ከ አቡበክር በስተቀር አቡበክርም ቁጭብሎ ማልቀስ ጀመረ😢😢
ነብዩም ከመውረዳቸው በፊት የመጨረሻ ዱኣ እንዲ አሉ ፡( አላህ ይጠብቃቹ አላህ ባለ ድል ያርጋቹ አላህ ያጠንክራቹ አላህ ይደግፋቹ )

(94)የዛዱል መዓድ ፈታዋ
ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
🔵በዛዱል መዓድ ፈታዋ ተጠይቀው መልስ የተስጠባቸው ጥያቄዎች
1 /አባቴ ታሞብኛል አንደበቱም ተይዟል ቆሞም መስገድ አይችልም ተቀምጦ እና ተኝቶ የሚሰጋደውን አሰጋጋድ አብራሩልኝ? ፋቲህ በልቡ ውስጥ መቅራት ይችላል?ዱዓም አድርጉለት
2/ አንደንድ ሰዎች ቁርአን ቅሩ ሲባሉ ትርጉሙን አናውቅም እየሰራንበትም አይደለም ምን ጥቅም አለው ?ይላሉ ይህ እንዴት ይታያል?
3/ የኢሻ ሰላት ወቅት ከገባ በኋላ የወር አበባዬ ቢመጣ ስፀዳ ቀዳ አወጣለሁ ማውጣት አለብኝ?
4/ አንድት ሴት የወር አበባ ወይም ከወሊድ ከጠራች ከኢሻ ቡሀላ ብትታጠብ የመግሪብ ሶላት ግድ ይሆንባታል? ወይም ከአሱር ሰላት ቡሀላ ብትታጠብ የዙሁር ሰላት ግድ ይሆናል? ያብራሩልኝ
5/ከሰውነታችን ውስጥ አየር(ጋዝ)ከወጣ እስቲንጃእ ያስፈልጋል?ወይስ ውዱእ ብቻ በቂ ነው?
6/የሌሊት ሰላት ፈጅር ስንት ደቂቃ እስኪቀረው መስገድ እንችላለን?
7/የዛሬ 4አመት አካባቢ ቤት እንዲገዛልኝ ለአጎቴ ልጅ 350 ሺህ ብር ልኬለት በብሎኬት የተሰራ ቤት ገዛልኝ ነግር ግን ሰሞኑን ለእኔ ሳይነግረኝ በ500 ሺህ ብር ሸጦ ለእኔ በ350ሺህ ብር ከጭቃ የተስራ ቤት ገዝቶ ትርፉን ወሰደ ሂሳብ ዘግተናልም አለኝ ትርፉን መውሰድ ይበቃለታል?
8/ወንድሜ በባህር ሂዶ ከጠፋ አራት አመት ሆነው እና ሞቶ ነው በማለት ቁርአን ገዝቸ በስሙ ለመስጅድ ሰጠሁ መጀመሪያ ማረጋገጥ ነበረብኝ ወይስ ችግር የለውም?
9/ባለቤቴ ቤተሰብ ሳያውቅ ወንድና ሴቶችን ከቤት ሴቲችን እያስጠፋ እያገናኘ ያለኒካህ 3ቀን 4ቀን አብረው እንዲቆዩ ያደርጋል ከዚያም ቤተሰብን ይጠይቃሉ ላይስማሙም ይችላሉ ይህን ስራ ተው ሀራም ነው ብለውም አልሰማ አለኝ የልጆች እናት ነኝ ምን ይሻለኛል?
#እና_ሌሎችም_ፈትዋዎች_አሉ

የዝሙት ሰበብና መዘዞች
ዝሙት አላህ እጅግ የሚጠላው ከባድ ወንጀል ነው።ከኣኺራ በፊትም እዚሁ ዱኒያ ላይ ወንጀሉን ከሚፈጽሙት ግለሰቦች አልፎ ለሀገርና ለዓለም የሚተርፉ ብዙ መዘዞች አሉት!
ለዚህም ነው አላህ ዝሙትን አትስሩ ሳይሆን "ዝሙትን አትቅረቡት" ያለው።
ኣይ ብሎ ዝሙትን የቀረበው ሰው ብዙ ጊዜ እራሱን ዝሙት ላይ ወድቆ ነው የሚያገኘው!
የዝሙት መስፋፋት እና ወንጀሉ ላይ የመውደቅ ሰበብቦች ብዙ ሲሆኑ
ከነዚህም በጥቂቱ:-
1/ ስሜት ቀስቃሽ ምስሎችን ማየትና እንደዘፈን ያሉ ድምጾችን ማድመጥ፣
2/ በዲኑ ከማይፈቀድ ተቃራኒ ጾታ ጋር ተነጥሎ/ ተገልሎ መቆየት፣
3/ በወንድና በሴት መካከል የሸሪዓን ስርዓት የጣሰ ቀረቤታ እንዲሁም ቀልድና ጨዋታ መኖር፣
4/ "ልንጋባ ነው" በሚል ምክንያት ኒካሓ ሳይታሰር በፊት መቀራረብና ወሬ ማብዛት!
5/ ከላይ ሲታዩ ጥሩ የሚመስሉ ሰዎችን በማመን ቀርቦ ሳያጣሩ ራስንም ይሁን ልጅን ወይም እህትን ለነሱ በማይገባ መልኩ አሳልፎ መስጠት (መጠጋት)!
6/ ለሕክምና፣ ለሩቃ፣ ለትምህርት፣ ለስራና ወዘተ እያሉ ሴቶች ያለ አጃቢ ወንድ (ወሊይ) ባዕድ ወንድ ጋር መቅረብ!
7/ በቢሮ ስራ ምክንያት የሴትና ወንድ መቀራረብና አንዳምዴም አምሽቶ መግባት፣ ከዚህም አልፎ ከስራ አለቃ ጋር ክብርን ጥሎ መቀራረብ!
8/ ከተማ ውስጥም ይሁን ከከተማ ውጪ፣ ሀገር ውስጥም ይሁን ከሀገር ውጭ ሴት ልጅ ከባዕድ (መሕረም ካልሆነ) ወንድ ጋር በአንድ መኪና ውስጥ መጓዝና ወዘተ
♦️የዝሙት ወንጀል ላይ መውደቂያ ምክንያቶች ናቸው።
♦️እህቴ ሆይ፥ በምንም ምክንያት ከባእድ ወንድ ጋር አንድ ክፍል፣ አንድ ግቢ፣ አንድ መኪና ውስጥ ለአፍታ እንኳ ቢሆን እንዳትቆዪ!!
ይህን ምክር ያልተገበርሽ እንደሆነ በዋነኝነት የምትጎጂው አንቺው እራስሽ ነሽ።
🏷️ነቢዩ የሚከተለውን ብለዋል "ባዕድ ወንድና ባዕድ ሴት ለብቻቸው ተነጥለው አይቆዩም ሶስተኛቸው ሽይይጣን ቢሆን እንጂ!"ሽይጣን ደግሞ በመጥፎ ነገር ያዛል!
▪️ወንድሜ ሆይ ከእሳትና ከአውሬ ከምትሸሸው በላይ ከዝሙትና ከበሮቹ ሽሽ!
▪️እህቴ ሆይ ባልሽን ከእህትሽ፣ ከሰራተኛሽ ወዘተ ጋር ትተሽው አትሂጂ!
▪️ሀገር ውስጥም ይሁን ውጭ ሀገር ሰው ቤት በሰራተኝነት ተቀጥረሽ የምትሰሪ እህቴ ሆይ ከወንድ አሰሪሽም ጋር ይሁን ከልጆቹ ወዘተ ጋር ለአፍታም እንኳ ቢሆን ለብቻሽ እንዳትሆኚ ዲንሽም ዱኒያሽም እንዳይበላሽ ተጠንቀቂ!
አላህ በዱኒያ ከውርደት በኣኺይራእሳት ይጠብቀን
ኣሚን

የአላህ ባሪያዎች ሆይ...
🔹በሰማይም ይሁን በምድር ላይ የሚከሰት ነገር በሙሉ በአላህ ውሳኔና እርሱም ለሚያውቀው የላቀ ጥበብና ምክንያት ነው።አላህ የሚወስናቸው ውሳኔዎችም በሙሉ ለባሮቹ መልካምና በሁለቱም ዓለም (በገሃድ ሲታይ ጎጂ ቢመስሉም) ጠቃሚዎች ናቸው።
🔸የግልም ይሁን አጠቃላይ በሽታዎች (ወረርሽኞች) ከጥንት ጀምሮ በተለያዩ ምክንያቶች ይከሰታሉ፣ከምክንያቶቹም አንዱ ለበዳዮች ቅጣት ሲሆን ለምእምናን ደግሞ እዝነት፣ ወንጀል ማበሻና የሰምዓትነትን ማዕረግ ማግኛ መንገድ ነው።
🔹{በግፋቸው(የአላህን መልእክተኛ በማስተባበላቸው) ምክንያት እነሆ ቤቶቻቸው ፈራርሰው ባዶ ሆነዋል። በዚህም ውስጥ ለሚያውቁ ሰዎች ትልቅ ተአምር አለ።እነዚያ ያመኑና ጌታቸውን ይፈሩ የነበሩትን አዳናቸው!}ሱረቱ አን'ነም 51- 53
▪️ከበሽታዎች ለመዳን ሰበቦችን ከማድረስ ጋር ይበልጥ ደግሞ አላህን እንፍራ፣ ልንቶብትና ወንጀሎችንም ልንርቅ ይገባናል!
ዞሮ ዞሮ መሞትም ይሁን መታመም ቀድሞ የተቀደረ/ የተከተበ ነውና በቀደር አምነን እራሳችንን እናረጋጋ። ከበሽታ ይልቅ ብዙኃኑን የሚጎዳው ከልክ ያለፈ ጭንቀትና ስጋት ነው!
"አላህ የከተበልን ወይም የከተበብን ነገር እንጂ እኛ ላይ አይደርስም!"
🔸ከዚህም ጎን ለጎን በምንችለው ያክል እራሳችንና ቤተሰቦቻችን እንጠብቅ።
በበሽታው የተጠቃ ሰውም ሌሎችን ላለመጉዳት የሚችለውን ሁሉ ማድረግና የባለሙያዎችን ምክር መስማት ግዴታ ይሆንበታል!
🔹ይህ በእንዲህ እንዳለ በወረርሽኝ በሽታ መሞት ለሙእሚኖች *የሸሂድነትን ደረጃ* የሚያስገኝ በመሆኑም አማኞች ሆይ አብሽሩ !ሁሉም ለኸይር ነው!
ዳሩ ሞት እንኳ ቢሆን "ኣኺራ ለሙተቆች ከዱኒያ ትሻላለች!"
በበሽታ የተያዘ ሁሉ ይሞታል ማለትም አይደለም!
ደግሞስ ተውሒድና ሱንና ላይ ከሆኑ መሞት ምን ችግር አለው?!
ሆን ብሎ ራስን ላደጋ ማጋለጥ ግን በዲኑ የተከለከለ ነው።
በመልካም ስራም እድሜ መርዘሙ ሌላ መልካም ነገር ነው።
🗞️በተረፈ የጠዋትና የማታ እንዲሁም በአጠቃላይ ከጊዜና ከሁኔታዎች ጋር ተያይዘው የሚባሉ ዚክርና ዱዓዎችን እናብዛ።ችግሮችን በሙሉ ማስወገድ የሚችለው ጌታ አላህ የመጣውን በላ እንዲያነሳልንም ዱዓ እናዘውትር።
🔸በተጨማሪም የጤና ባለሙያዎችና የዘርፉ ተጠሪዎች የሚሰጧቸው መመሪያዎችን ከዲኑ እስካልተጋጩ ድረስ በመከተል ከቀደር ወደ ቀደር እየሸሹ ራስንና ሌሎችንም መጠበቅ ተገቢ ነው እንላልን።
✍🏻ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም