Telegram Web Link
ይህን መፅሐፍ የምትፈልጉ @yebezawit2 ላይ ጠይቁ!!
📖📖📖📖📖
👍 በአናሳ ድምፅ ምክንያት የተቋረጠው ታሪክ እነሆ😊 በሰጣችሁኝ ገንቢ አስተያየት ምክንያት አቅርቢያለሁ😍
📖📖መልካም ንባብ📖📖
🔖ቤዚ የራጉኤል ልጅ🔖
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
🙏እጅግ በጣም አመሰግናለሁ ❤️
አመሰግናለሁ ❤️❤️😱
🙏አመሰግናለሁ ❤️❤️
💯💯🔖ማስታወቂያ 🔖💯💯
የሰባራ ልቦች መሪ ገፀባህሪ
ዶክተር ልዑል
የወንድሙ ስም አቤል በሚል እንዲተካ
🙏በትህትና🙏 እጠይቃለሁ!
🙏አመሰግናለሁ
📚መልካም ንባብ📖
Forwarded from የግጥም መንደር via @like
💕💕💕ሰባራ ልቦች💕💕💕

ክፍል ስምንት🍀💖💖
ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ*

.....ሰምሃል ከምወደው ጓደኛዬ ከዶክተር ማርቆስ ጋር በፍቅር ጣቶቻቸው ተጠላልፈው አፍለአፍ ገጥመው ነበር።እብድ ሆኜ ፊቴን አዙሬ ከሆቴሉ ወጣሁኝ።በቃ ከዛ በኋላ ነገሮች ተመሰቃቀሉ እሷም ማርክን አግብታ ለሰርጓ ጠራችኝ ለስሜቴ የምትጠነቀው ሰምሃል እንደ ቀልድ ጋበዘችኝ ጎትቼ አልመልሳት ነገር ፍቅር ሃይል አይጠቀመም ለምን እንዳገባችው እኔ ምን እንዳጎደልኩባት ሳላውቅ እና ሳይገባኝ አሳልፌ ሰጠኋት። ምስኪን እኔ! ፍቅር ከቶ አይወድቅም ብዬ አምን ነበር ግን የኔ ፍቅር እንደ ረከሰ ነገር ተቆጥሮ ዋጋውም ጥንቡን ጥሎ ወድቆ ተሰባብሯል።ወደቀ ተሰበረ....ሰምሃል ዛሬም ድረስ ትታወሸኛለች ስለእሷ አላስብም ብዬ ለራሴ ቃል ስገባ ይበልጥ ትናፍቀኝ እና ስጨነቅ እውላለሁ።ቤተሰቦቼ ሰርጌን ለማየት ናፍቀው ቀርተዋል።የእናት የአባቴ "ልጄ ሊያገባ ነው" የሚል ኩራት ተቀብሯል።አሁን ላይ ብቻዬን ነኝ ብቻዬን! .....

........እንደምንም ከነበርኩበት ሀሳብ ወጣሁኝ እና እጄን ኪሴ ውስጥ ከትቼ ወደ ውስጥ ተመልሼ ገባሁኝ።....መንጋት አይቀርም እና የንጋቱ ብስራት በከተማው የመኪናዎች ድምፅ ተበስሯል።ዛሬን አያደርገው እና በአእዋፋት ዜማ ነበር ንጋት የሚበሰረው። እኔም መንጋቱን አይቼ ዶክተር ሰገንን ምንም ሳልል ወጣሁኝ እና ወደተመደብኩበት ዋርድ ተመለስኩኝ።...ስልኬን አውጥቼ ወደ ቤት ደወልኩኝ።ስልኩ ጠራ...ደገመ.....የሚያነሳው የለም...መልሼ ደወልኩኝ.....አሁንም በስልኩ ውስጥ የእናቴ ድምፅ ብጠብቅም ልሰማው አልቻልኩም። ልቤ ተሸበረ ለወንድሜ ለልዑል ደወልኩት

"ሄሎ ዶክተሩ ወንድሜ" አለኝ። በትንሹ ጭንቀቴ ቀለል አለ።

"ደህና አደርክ አንተ ጅል" አልኩኝ ፊቴን ከቧንቧው በሚወርደው ውሃ እየዳበስኩ።

"ያውም..." ወሬውን ስለማውቀው አቋረጥኩት እና
"እቤት ስደውል ስልኩን አያነሱም የተፈጠረ ነገር ካለ ብዬ ነው" አልኩት

"ኧረ ምንም የለም ወንድሜ ምን አልባት አልተነሱም ይሆናል ቆይተህ ደውልላቸው።" ብሎ አረጋጋኝ። እኔም እሺ ብዬ ስልኩን ዘጋሁት እና ሰአት ቆጠራ ጀመርኩኝ።
ሰራዬን ሰርቼ በሰአቴ ቦርሳዬን ይዤ ወደ ቤት የሚወስደውን መንገድ ብቻዬን ማዝገም ጀመርኩኝ። ቀኑ ሙሉ ከቤት ስልክ ስላልተደወለልኝ እና ስደውልም ሳልተመለሰልኝ ሀሳብ ገብቶኛል።የግቢውን በር በቁልፍ ከፍቼ ገባሁኝ ስገባ ግን ያየሁት ነገር የዘቀዘችብኝ ፀሀይ ዳግም የፈነጠቀች ያህል ሰምሃል ብትመለስ አልያም ያየሁት ነገር ውሸት ቢሆን የሚሰማኝ ስሜት ብዬ የማስበው ሲሰማኝ ታወቀኝ። በሆነው ሁሉ የማማርረው አምላኬ ድንቅ እንዳደረግልኝ ተሰማኝ ሰምሃል ከእኔ ጋር እያለች አንድ ሆኜ ብዙ ነበርኩ አሁን ላይ ግን ለአንድ ራሴ መሆን አቅቶኝ ያለህመም ፈገግ ብዬ አላውቅም።....ቤቱ በእጣኑ ጭስ ሞልቶ ቡና እየተፈላ ነበር ፈንዲሻው ፈክቶ ለቡናው ሌላ ድምቀት ሆኖታል። ይበልጥ የደነቀኝ ቡና የምታፈላው እድል መሆኗ ነበር ቆሜ ቀረሁኝ መደንገጥ መደመሜ ፊቴ ላይ ያነበበችው እናቴም ፈገግ ብላ አየችኝና "ደህና መጣህ ልጄ" ብላ እንባዬን እንደ ዶፍ እንድለቀው አስገደደችኝ ምን አልባት እንዲህ ስሆን ላየኝ ማካበድ ሊመስል ይችላል ግን አይደለም! የሚወዱትን ማጣት ጉድለት ብቻ አይደለም የመቃብር ኑሮ እንጂ አሁን ግን መቃብሩ ተከፍቶለት በህይወት እንደ ወጣ ሰው ነው ደስታዬ የበዛው እናቴ በፍቅር ጠርታኝ ሰላሜን ጠየቀች።ምንም ሳልመልስ ወደ ክፍሌ ሮጬ ገብቼ በሩን ዘግቼ ተንሰቅስቄ አለቀስኩኝ። ሲጢጥጥ ብሎ በሩ ተከፈተ እድል ናት ከንፈሯን ሸሸት አድርጋ በጥርሶቿ ብልጭታ ቀልቤን ገዝታ እንዳያት አስገደደችኝ። ጠጋ ብላ እጄን ይዛ አይኗን ጨፈን አድርጋ ገለጠች በርታ የምትለኝ ያህል ተሰማኝ እኔም መልሼ አይኔን ጨፈን አድርጌ ገለጥኩት እሷም ጥርሶቿን ሳትሸሽጋቸው ተመልሳ ወጣች። ልብሴን ቀይሬ እየፈራሁ ወደ ሳሎን ገብቼ ተቀላቀልኩኝ እና ፈንዲሻውን ዘግኜ መብላት ጀመርኩ ብዙም ሳይቆይ ወንድሜ ልዑል መጣ።ቤታችን ደስ የሚል ድባብ ኖረው እኛ ስንስቅ ስንጫወት የእድል ድምፅ ግን ከራሷም አልፎ አይሰማምነበር በአንድ ጎን የእሷን የዝምታ ምክንያት እያሰላሰልኩ ምግብ በልተን ተጫውተን ለመኝታ ወደየ ክፍላችን ገባን አልጋዬ ላይ ጋደም ብዬ ደጋግሜ ባነበው የማይሰለቸኝን የበአሉ ግርማ መፅሐፍ የሆነውን ኦሮማይን እንደ መዝሙረ ዳዊት እየደገምኩ ሰምሃልን እና እድልን ሳልፈልግ ማነፃፀር ጀመርኩ።ደግሞ ተመልሼ አእምሮዬን ራሴ ተቆጥቼ ንባቤን እቀጥላለሁ።...."ግን ምን ሆና ነው...ማነው እንዲህ የጎዳት....እድል ማናት?.." አእምሮዬ በጥያቄ ተሞልቶ ንባቤን አመሰቃቀለው እና መፅሀፉን ዘግቼ በመስኮቴ በኩል ወደ ማዶ አሻግሬ እያየሁ ቆምኩኝ ከሩቅ ሆነው የሚያበሩት የከተማዋ መብራቶች ቀልቤን ወስደውት ለሰአታት ያህል ፈዝዤ ቀረሁ እናም መለስ ብዬ ወደ ግቢያችን ቁልቁል ስመለከት ግን እድልን አየኋት ክው ብዬ ቀረሁ...

ይቀጥላል....

ቀጣይ ክፍል እንዲለቀቅ
ድምፅ መስጠት አትርሱ!
💞💞💞💞💕💕💕💕💕💕

@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
💔💔💔ሰባራ ልቦች💔💔💔
😣😣ክፍል ዘጠኝ 😣😣😣
ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ
@yebezawit2
ብቻዋን ታጉተመትማለች እጇን ታወራጫለች አላየችኝም እና ጠጋ ብዬ በረንዳው ላይ ቆምኩኝ።ድንገት የምታወራው ድምጿ ከንፋሱ ጋር በጆሮዬ ሽው አለ..."አባቴ ነው የበደለኝ" ደነገጥኩ ማስታወስ ችላ ነው የደበቀችኝ ወይስ ምንድነው አልኩኝ።ዝም አለችኝ ያየችኝ መስሎኝ ባስተውላትም እሷግን የኔ መኖር አልታያትም ዝም ብላ በተመስጦ ሰማይ ላይ አንጋጠጠች እና ምርር ብላ አለቀሰች።"እንዴት የድሮ ታሪኬን አላውቅም እኔ ማነኝ?" እያለች ከእግዜር ጋር ግብ ግብ ገብታለች።እኔም ላለማስደንገጥ ጉሮሮዬን ጠረግ አድርጌ ወጣሁኝ ግን መደነገጧ አልቀረም ።"አልተኛህም እንዴ?" አለች በሹራቧ ፊቷን እየሟዠቀች።"እንቅልፍ በቀላሉ አይመጣም" አልኳት ጎኗ እየተቀመጥኩ።የሚነፍሰው ነፋስ አጥንትን ሰርስሮ ገብቶ ይቆረጣጥማል ለእድል ግን ተመችቷት ነበር።"በሰላም" ደግማ ጠየቀችኝ"ምን ሰላም አለ ሁሉም ጥያቄዬ አልመለስ ብሎኝ ተቸገርኩ" አልኳት። ከልቤ ነበር ብስጭቴ።ጥርሷን ብልጭ አደረገችልኝ ደስ አለኝ።"አይ አንተ ሁሉም ጥያቄ መልስ የለውም እኮ" መለሰችልኝ።ለፈገግታዋ ፈገግ ብዬ አሽኮረመምኳት ስታፈር ሰበር ያደረገቻቸው አይኖቿ ሳወራ ቀና አሉ እና ጨረራቸውን ለቀቁ።"አንቺ ግን ምን እየሰራሽ ነው" አልኳት። ፊቷን በአንዴ ቋጠረችውና "እራሴን ከምድር አጥቼው ከሰማይ እየፈለኩት ነው እኔ ማነኝ ታሪኬስ ቤተሰቤስ ምንዶነኝ እኔ ለምን እንዲህ ሆንኩኝ እያልኩ ነው" ብላ የሚዋጉት አይኖቿ ጥቁር ደመና ያዘለ ሰማይ መሰሉ እንባዋ ይዘረገፍ ጀመር ላባብላት ጠጋ አልኩኝ።ሰውነቷ ግን ውሃ እንደነካው ዶሮ ተርገፈገፈብኝ የምይዘውን አጣው መንቀጥቀጧ ሊቆም አልቻለም እንባዋም በተመቸው በኩል ይምዘገዘጋል።"እድል ተረጋጊ" እሷም ራሷን እየተቆጣጠረች ተመለሰች።ከንፈሯን እያንቀጠቀጠች "እባክህ ነገ ጅማ ውስደኝ" ወለሉ ላይ ተዘረረች።እጅጉን ደነገጥኩኝ ከወለሉ ላይ አንስቼ ወደ ክፍሌ አስገባኋት እና ህክምና ሰጠኋት ከደቂቃዎች በኋላ ቀስ ብላ አይኖቿን ገለጠቻቸው። ፈገግ አልኩኝ ሳያት ምክንያቱ ሳይገባኝ።ጅማ የሚለው ቃሏ ጆሮዬ ላይ ደጋግሞ ያቃጭላል።ግን ምን ብዬ ልጠይቃት......"ደህና ነሽ?" አልኳት።እሷም እጇን ራሷ ላይ ተጭና "ደ..ህ..ና ነ..ኝ.." ትንፋሿ ቁርጥ ቁርጥ እያለ መለሰችልኝ። እንደደከማት ግልፅ ነው ከክፍሌ እንድትወጣ ማድረግ አልችልምና ብርድልብሱን አልብሻት ወንበሬ ላይ እግሬን ቆልፌ ተቀምጬ እመለከታት ጀመር።አይኗን ከድና ከዚህ አለም ተሻግራ ሌላ የሰላም አለም ያረፈች ነው የሚመስለው።ሰምሃል ታወሰችኝ....ናፍቆት አይደለም ለካ ይሄ ትዝታ ነው...ሰክራ እጅግ እየጮኸች ስታስቸገር ነበር እዛው ሆቴል ክፍል ይዘን አስተኝቻት አይኗን በስስት እያየሁ ለሊቱ ነግቶ ፀሀይ ደርሳብኛለች። አይ ሰምሃል.....ያን ውበቷን ያን መልካምነቷን አሳልፋ ሰጠችብኝ እሷነቷን ፍቅሯን አጣሁት...ፈገግ አልኩኝ።

.....መንጋት መጨለም የተፈጥሮ ህግ ነውና እኔም ባለሁበት እንዳሸለብኩ ፀሀይ ከምስስራቅ ቤቷ ወጥታ ምድር በነበልባሏ ሞቃለች።"ልዑል ልዑል" የእናቴ ድምፅ ከእንቅለፌ አባነነኝ።አይኖቼን እያሸሁ እድልን አየኋት እድለም ተነስታ ነበር።"ደህና አደርሽ" አልኳት። እድልም በአዎንታ ፈገግ አለችልኝ እኔም ተነስታ ፊቷን እንድትታጠብ ነግሪያት ልወጣ ስል በሩ ተበረገደ እማዬ ነበረች።ደነገጥኩ እናቴም እድልን ከአልጋው ጫፍ ተቀምጣ ስታያት በአእምሮዋ የሆነ ነገር አስባ ሳቅ እያለች"ቁርስ ቅረቡ ብዬ ነው" አለችና ማስተባበያን ሳትሰማ ወጣች እኔም እድልን ዞሬ ሳላያት ወጣሁኝ እና በጠዋቷ ፀሀይ ጀርባዬን ገርፌ የእድልን ከክፍሌ መውጣት ተከትዬ ተመልሼ ገባሁና ልብሴን ቀይሬ ቻው ሳልላቸው ብን ብዬ ከቤቴ ወጣሁኝ።

ውስጤ ብዙ ሀሳብ ጅረት ሆኖ ይንፎለፎላል ሳቅ እያልኩ እክሳተራለሁ።እድልን ሳስብ ደስ ቢለኝም ብታስደንቀኝም ሰምሃል ላይ በሀሳብ የሸፈትኩ እየመሰለኝ ራሴን እወቅሳለሁ...ምን አይነት ፍቅር ነው? አልኩኝ። የሆስፒታሉ ግቢ እንደገባሁ ወደ ሜዲካል ዳይሬክተሩ ጋር ገባሁኝ እና በጥድፊያ ስለ መጣሁበት ጉዳይ እነግረው ጀመር."እ ፈቃድ እፈልጋለሁ ከአዲስ አበባ ለልተወሰነ ጊዜ እወጣለሁ እና" ፀጉሬን አክኬ ዝም አልኩኝ።የባህሪዬ መለወጥ አስደንግጦታል የተከበረውን ዶክተር "እሺ ዶክተር ሰላም ነህ ግን" አለኝ እኔም "ሰላም እሆናለሁ እባካችሁ እረፍት ስጡኝ" መላ ሰውነቴ ተንዘፈዘፈብኝ። ዶክተሩም በአርምሞ ተመልክቶኝ ፍቃዱን ለአስራአምስት ቀን ሰጠኝ እና በመልካም ዕድል ምኞት ከክፍሉ አስወጣኝ።እኔ በደስታ እየፈነጠዝኩ ስከንፍ ወደ ቤቴ ተመለስኩኝ ሁኔታዬ ቤተሰቤንም አስደንግጧል እማዬ እድልን የእጅ ስራ እያለማመደቻት ነበር ቁምሳጥኔን ከፍቼ በትንሹ ቦርሳዬ ውስጥ መክተት ጀመርኩ። ልቤን ጠላሁት በሀጢያት ያደፈ በዝሙት የቆሸሸ መሰለኝ እንባ እንባ አለኝ።ፈጥኜ እንደወሰንኩ ቢገባኝ ልክ ነኝ ነገ...ዛሬ... አልልም ቀጠሮ ሳበዛ ብዙ ነው ያጣሁት ይበቃኛል ከዚህ በላይ ራሴን ረስቼ የፍቅሬን የንፅህና ፍሬ ማጣትን አልወደድኩም...ይሄን ማንም ባይረዳኝም እረዳቸዋለው!😭😭

💔💔💔ሰባራ ልቦች💔💔💔💔
😣😭😭አሳዝኝ ገፆች ከነገ ጀምሮ ይገለጣሉ!
😊ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ(bezi ye raguel lij)
@Yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
😭😭😭😭😊😊ይቀጥላል ነገ ምሽት😭
😁😁😁እኔን ያገኘው የዛሬ ደስታ በእጥፉ እናንተንም ያግኝ💜
ልዩ ቀን መስከረም 04/2013

😊😊😊እንኳን ደስ አለሽ በሉኝ!😍😍😍
👉ሙሉን ታሪክ ከሰአታት በኋላ...
ቤዚ የራጉኤል ልጅ
ፍቅር የሞላው ደስታ ቤታችሁን ይጎብኝ 💜

ይሄን የቴሌግራም ቻናል ከከፈትኩ ጊዜ ጀምሮ ብዙ ሰዎችን አግኝቼበታለሁ በይበልጥ ደግሞ #የማማከር ስራ ከጀመርኩ በኋላ በስልክም እየተደወለ ከሀገር ውጪ ያሉ እህቶቼም ጭንቀታቸውን እያካፈሉኝ ቆይተዋል....እናም ዛሬ ደግሞ ልዩ ስጦታ ተበረከተልኝ💜💜💜
😊😊እንቅልፋም ነኝና ከቤተክርስቲያን መልስ አልጋዬ ላይ ጋደም ብዬ የዘማሪ ቴዎድሮስ ዮሴፍ መዝሙር እየሰማሁ አይኖቼን ጨፍኜ ወደ ሰማያዊ አለም በሀሳብ ከነፌ ነበር...ስልኬ ጠራ...አዲስ ቁጥር ነበር 0912....ብሎ የሚጀምር ነበር አነሳሁት
"ሄሎ"
"ሄሎ...ቤዛዊትን ማግኘት እችላለሁ" አንድ በደስታ ብዛት የሚፍነከነክ የወንድ ድምፅ ነበር።
"ነኝ ይቅርታ ማን ልበል?" አልኩኝ።
"ቤዚዬ ፀሎትሽ ምክርሽ እኮ ረዳኝ"
ማንነቱን ሳይነግረኝ ከደስታው ምንጭ ጨልፎ አጠጣኝ። እንባ እና ሳቅ እያጀበው ቀጠለልኝ..
"ረፍዶብኛል ብዬ ራሴን በፀፀት ስጎዳው ነበር ግን ሰአቱ ነበር ሰላም እኮ ይቅርታዬን ተቀበለችኝ" እንባው ቀደመው።
ትዝ አለኝ....Z ተጫዋቹ ነበር።
Z እና ሰላም እጅግ የሚዋደዱ ፍቅረኛሞች ነበሩ Z ስለእሷ ነግሮኝ አያቆምም ደውሎ ካርድ ቢዘጋበት እንኳን ሞልቶ ስለእሷ ሴትነት ብቻ ነበር የሚያወራኝ የሚገርመው ግን ከተለያዩ ስድስት አመታት አልፈዋል በመሀላቸው በተፈጠረ ተራ አለመግባባት ነበር የተለያዩት እናም ከጊዜ ብዛት ነገሮችን ሲመለከት ጥፋቱ የሱ ሆኖ አገኘው። ይቅርታም ሊጠይቅ አሰበ ግን የረፈደ መስሎት መፀፀቱን ጠላው።ሁሌም እየወደዳት እና ስሟን እያነሳ ለመኖር ቃል ገባ ጓደኞቹ እናስታርቅህ ቢሉት ድፍረት የለኝም የሌላ ብትሆንስ ብሎ አሻፈረኝ አላቸው።ነገሩ እንዲህ ነበር የተጀመረው እናም እኔና ዜድ በቴሌግራም ተዋወቅን አወራን ብዙ ብዙ በስልክ ብቻ! እናም እኔ በአንዳንድ የግል ጉዳይ ስልኬን አጥፍቼ ጠፋሁ እናም ዜድ ከራሱ ጋር በወሰነው ውሳኔ ከስልክ አልፎ በአካል አግኝቶ ሊያወራት ሰላምን ቀጠራት"የተባረከች ሴት" አገኘችው ከልቡ ያለውን እውነት ነገራት 💜እውነት አንድ ናታ💜 ሰምታ ተመለሰች አወጉ ብዙ ተወቃቀሱ በመጨረሻም እርቅን ፈጥረው ፍቅራቸውን አድሰው 😍አንድ ላይ ሆኑ😍 እግዚአብሔር ያጣመረውን ማን መለየት ይችልና!?..
እና ዛሬ በእንባ እየታጀበ እንዲህ ተብዬ ስለራሴ ተነገረኝ..
"ቤዚ አላውቅም ድልድይ ነሽ ብልሽ ይሻላል ፍቅሬን በአንቺ አድርጎ ሰጠኝ ትዝታዬን አደስኩት አንቺ ስትመክሪኝ አንድ ነገር አልሽኝ 'አንድ ነገር ልንገርህ ለይቅርታ ረፈደ ቢባል ኖሮ ማናችንም ቆመን ባልተራመድን ነበር #ጥፋት ምንም ነው የሚያስብ የሚሰራ ሰው ነው የሚያጠፋው #የሚፀፀተው ደግሞ አዋቂ ሰው #ይቅርታ የሚጠይቅ ደግሞ የተባረከ እና የተመረጠ ነው። መንገድህን አፅዳ ይቅርታ ጠይቃት አውራት ከዛ እሷ ትወስን' አልሽኝ እናም ጠየኳት ደስ አላት እግዚአብሔር ለእኔ ጠብቆ አቆያት እድለኛ ነኝ" አለኝ። "እናመሰግንሻለን" አሉኝ በጩኸት ለሁለት!!
💜ከዚህ በላይ ምን ደስታ አለ!💜
ለሰው የደስታው ምክንያት መሆን🙏
😊አምላኬ ሆይ፦ አመሰግንህ ዘንድ ምክንያቴ ብዙ ነውና #ተመስገንልኝ !😍😍😍😍
@yebezawit2
ቤዛዊት የሴትልጅ

ምንም ሳላደርግ የሰዎችን ደስታ የሚያሳየኝ ፈጣሪዬ ይመስገን!!

🙏🙏😊😊ሰላም እደሩልኝ😊😊🙏🙏
💜💜ድምፅ መስጠትም አትርሱ😉
📖የተቆለፈበት ቁልፍ📖
ማግኘት ያልቻላችሁ @yebezawit2 ላይ አናግሩኝ💜💜💜ያለምንም ክፍያ!
እጅግ ደስ የሚል ልዩ መፅሀፍ 😊😊😊
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
የተቆለፈበት_ቁልፍ_ዶክተር_ምህረት_ደበበ.pdf
12.4 MB
የተቆለፈበት ቁልፍ ዶክተር ምህረት ደበበ

join and share @yebezigetmoch
💔💔ሰባራ ልቦች💔💔
ክፍል አስር
ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ
@yebezigetmoch


..."ምን ሁነህ ነው የምትዋከበው" በሚል አስተያየት እድል ቆማ እያየችኝ ነበር እኔም "አፍጥኚው ልብስሽን አዘጋጂ ወደ ጅማ እንሄዳለን" አልኳት። ደስታ እና ሃዘን ተደበላለቀባት "አትይኝ እድል በቃ ጅማ እንሂድ እባክሽ መቆም ሁላ ነው ያቃተኝ" አልኳት። እውነትም ውስጤ የእሳት ነበልባል ይንቦጎቦጋል ለምን? ቢሉኝ መልሴ አንድ ሆኗል ሰምሃልን የበደልኩ እየመሰለኝ ስለሆነ እድልን ወደ መጣችበት ለመመለስ ወስኛለው እናም የዘመኔ ፍፃሜ በሰምሃል ፍቅር መንኜ መመንኮስ ነው ምኞቴ። "አሁን በዚህ ጊዜ ጅማ መሄድ ምን ይሉታል" እናቴ ጠየቀችኝ። አልመስኩላትም ዝም አልኹኝ። እድልም አንድ ረጅም ቀሚስ እና ኮቷን ይዛ መጣች።"ምንድነው" አልኳት እሷም በፈገግታ ብቻ መለሰችልኝ። ልብሷ መያዝ የፈለገችው ይሄ መሆኑ ስለገባኝ ቦርሳዬ ውስጥ ከትቼ ይዣት ወጣሁ እናቴንም ዞር ብዬ "መርቂኝ" አልኳት እድልን ሸኝቼ እንደማልመለስ በልቤ ቃል ስለገባሁ "የልብህን አይን ያብራልህ" ብላ እድልን ስማ በረንዳው ላይ ቆማ ቀረች።እኔም ግቢያችን ውስጥ የቆመውን መኪና ከፍቼ አስገባኋት እና እኔም ገባሁ......ዝምታ መሀላችን ነግሷል እኔ ግን አፌን አጉተመትማለው እድል ግን ቃል ቀርቶ መተንፈሷም አያሳታውቅም በስሱ የከፈትኩት ሬዲዮ ሙዚቃ ጋበዘ ሙዚቃውን ከፍ አደረኩት እድል ግን ምንም አላለችም ውስጤ በሀሳብ እየናጠ እየተንገላታሁ የአዲስአበባን ምድር ለቀን ወጣን ሄድን....ተጓዝን....ነጎድን

ሰዉ ከወዲያ እና ከወዲህ ይተራመሳል የጅማ ከተማ ፀሀይ ስትዘቀዝቅ ደረስን እድል ዝም ባለችበት በዛው አሸልባለች እኔም መኪናውን ወደ አንድ ሆቴል እያስገባሁ "እድል እድል" አልኳት። እድልም እንደምንም እየተንጠራራች ተነሳች። "ደረስን እኮ አንቺ እንቅልፋም" አልኳት። የመኪናውን ሞተር እያጠፋሁ እሷም እንደ እብድ እያደረጋት ከመኪናው ዘላ ወሰደች ደነገጥኩ ከመኪናው ወርጄ ተከተልኳት ከሆቴሉ ወጥታ ቁልቁለቱን በፍጥነት መራመድ ጀመረች ብጠራት ልትሰማኝ አልወደደችም ከመንገዱ ዳር ተቀምጠው በቆሎ ከሚሸጡት ጋር ስትደርስ ቆማ ማማተር ጀመረች እኔም አጠገቧ ስደርስ እጇን ያዝኳት ተመናጭቃ አስለቀቀችኝ "እኔን አታውቁኝም" ነጋዴዎቹ ላይ አፈጠጠች "እድል ተረጋጊ በዚህ ሁኔታ አይሆንም" አልኳት እሷ ግን አራስ ነብር መስላለች "ንገሩኝ አታውቁኝም" መጮህ ጀመረች እንባዋም ይወርዳል ምን ብዬ እንደማረጋጋት ግራ ገባኝ "እሺ ሐጂንስ አታውቁትም ሐጂ ሁሴንን" ማንን እንደምትጠይቅ ባይገባኝም አብሪያት ከነጋዴዎቹ ላይ አይኔን ተክዬ መልሳቸውን ስንጠብቅ ድንገት ከኋላችን "የጥላዬ ልጅ ነሽ" የሚል ድምፅ ተሰማን እኔና እድል እኩል ዞርን አይታቸው "እማማ" ስትል እንደምታውቃቸው ገባኝ። ዝም ትላለች ስል ታወራለች አታወራም ስል ከብረት ጠንክራ እየተወናጨፈች በቁጣ ታወራለች ማንነቷ ስውር ቅኔ ነው።"የኔ ልጅ የትጠፍተሽ ነው" ጠየቋት። "ደግሞ የማንን ስም ነው የምጠይቂ እሳቸው እንደሆን የድሮ ሰው ናቸው" አሉ ጭራሽ ያልገባኝ ነገር ተወሳስቦ እንደማይፈታ ግልፅ ሆነልኝ።እድል ተንሰቅስቃ እያለቀሰች "ሐጂ ሁሴን" ማለት ጀመረች ግራ ገባኝ። "እማማ ምንድነው" አልኳቸው እንዲያው ከነገሩኝ በሚል ተስፋ እሳቸውም ግራ መጋባታቸው ከፊታቸው ላይ እየተነበበ "እኔ ምኑን አውቄ ልጄ ሳውቃት ደህና ልጅ ነበረች እኮ" አሉ በሀዘኔታ እየተመለከቷት እድል ግን መንገዱ ላይ ተቀምጣ አንገቷን በእግሮቿ መሀል ደብቃ ተንሰቀሰቃለች "ሃጂ ማናቸው" አልኳቸው ፍንጭ የማገኝ መስሎኝ።" ሐጂ እኮ እዚህ አካባቢ የነበሩ ደገኛ ሰው ነበሩ እኔ እንኳን ልጅ እያለሁ ነው ያረፉት እና በታሪክ ነው የሚታወቁት የእሷ እንደዚህ መጠየቅ ግራ ገባኝ እኮ ልጄ ግን አንተ ምኗ ነህ" ብለው ጠየቁኝ ዶክተሯ ጓደኛዋ ወንድሟ ምን እንደምል ግራ ገባኝ እና ስንተባተብ "እናቷም እንዲያው ደክመዋል እኮ" አለችኝ "ቤቷ ቅርብ ነው " ጠየኩኝ። "አታውቀውም እንዴ ጎሬ እኮ ነው ቤቷ" መለሰሉኝ። ጎሬ....ጎሬ የት ነው..? ማን ይነግረኛል እና ከሌላ ቦታ ጅማ ድረስ እንዴት አወቋት ሴትየዋ እንደሚጠቅሙኝ በማሰብ ስልክ ካለቸው ብዬ ጠየኳቸው እሳቸውም ስልክ እንደማይዙ ከፈለኳቸው ግን መነሃሪያው ጋር ብመጣ እንደማገኛቸው ነግረውኝ እድልን አቅፌ ወደ ሆቴሉ ገባሁ። ሀሳብ እንቅልፌን ነጠቀኝ መብሰልሰል ጀመርኩ ብዙ አሰብኩ
እድል ማናት
ለምን ዝምታን መረጠች
ለምን ጅማን መረጠች እንዴት የዚህን ያህል ሰፈሯ ሳይሆን አወቋት.....ትርምስምስ ምስቅልቅል ያለ ሀሳብ ልቤን አፈነኝ....
"አዲስ አበባ አዲስ አበባ" የሚል ድምፅ አባነነኝ ስነሳ እድል አልጋው ላይ የለችም በአንድ እግሬ ጫማዬን አጥልቄ በሌላኛው እግሬ ባዶ እግሬን እየሮጥኩ ወጣሁኝ እና እንግዳ መቀበያው ላይ ያለችውን ወጣት ጠየኳት "የሆነች ልጅ ወደ ታች ወርዳለች" አልኳት "አዎ እያለቀሰች ነው የወጣችው" ብላ የብስጭት አየር እፍ አለችብኝ እየሮጥኩ ወጣሁ ግን የለችም ወደ ላይ ወደታች ተመለከትኩኝ እድል ግን የለችም ማልቀሷ ይበልጥ አሳሰበኝ መንገድ ላይ ብትወድቅ ማን ያነሳታል እያልኩ ተብሰለሰልኩ እና የትላንትናው እንስት ታወሱኝ ወደ መነሃሪያው በሩጫ ሄድኩኝ። አሰብኩት እድል ብትጠፋ ምን እንደምሆን የእናቴ ምርቃት ታወሰኝ ተኝቼ ሳይሆን ጎኗ ሆኜ ልጠብቃት ይገባታል እኔ ግን አሸለብኩኝ ወይ ብቆልፈውስ ኖሮ ራሴን በፀፀት አለንጋ መግረፍ ጀመርኩ የትላንትናዋ ሴትዮ ያሳዩኝ ቦታ ስደርስ ግን አይኖቼ ፈጠው ቀሩ የሴትየዋ ፔርሙዝ መሬት ላይ ወድቆ ቡናው ይፈሳል ሰው እየተጯጯኸ ክብ ሰርቶ ይመለከታል እግሬ ተንቀጠቀጠ ወንድነቴ ወኔዬ ሸሸኝ እድልን በሰዎች መሀል ተዘርግታ አየኋት ቀስ ብዬ መጠጋት ጀመርኩ......ይቀጥላል!!!

😭😭😭አዛኝ ክፍሎች ቶሎ ቶሎ እንዲለቀቅ ድምፅ ይስጡ!!
💔💔ሰባራ ልቦች💔💔
ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ
😊😊😊😊😊😊😊😊😊
የግጥም መንደር 😍
ሌላ ሰው ዶ.ር ምህረት ደበበ.pdf
53.2 MB
📖📖የመፅሐፍ ጊዜ📖📖
አዘጋጅ 💕ቤዚ የራጉኤል ልጅ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹ፍቅር ያሸንፋል🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ለሐሳብ ለጥያቄ ለአስተያየት
@yebezawit2 👈👈👈
💔💔💔ሰባራ ልቦች💔💔💔
ክፍል አስር
👉በቤዛዊት የሴትልጅ የተፃፈ 🇪🇹


..... እንደምንም ከቆሙት ሰዎች ጋር ደርሼ ተመለከትኳት መሬቱ ላይ ተኝታ እድል ታለቅሳለች "እኔ ማን ነኝ...ታሪኬን የማላውቅ" ትጮሀለች ለተመለከታት የምትወዳት እናቷን ያጣች ነበር የምትመስለው አሳዘነችኝ ሳላውቀው በልቤ አነባሁላት ሀዘኗ ተስተጋብቶብኝ ፊቴን አጠቆርኩኝ። "እድል" አልኳት በረከክ ብዬ ፀጉሯን እየዳበስኩ ተነስታ ተቀመጠች"ምን ልሁን በቃ ውሰዱኝ..." ተቆጣች።"ተረጋጊ" ወደ ደረቴ አስጠግቼ እንደ ልጅ አባበልኳት ሁኔታዋ ያስደነገጣቸው ሰዎችም ዝም ስትል አንድ ሁለት እያሉ ተበተኑ።የትላንትናዋ እመቤት አቅፊያት እንዳለው ጠጋ ብለው "ታማለች እንዴ" ብለው ጠየቁኝ። እኔም አላውቀውም እውነት ነው ላያት የታመመች ትመስላለች ግን ህመሟን ማንም ከእሷ በቀር አያውቀውም እኔም "አይ ደህና ናት ይልቅ ወደ ጎሬ እንዴት ነው የምሄደው?" በአጋጣሚው ተጠቅሜ ጠየኳቸው ሴትየዋም "በዚህኛው መስመር ነው።" ብለው የጋምቤላ መሄጃውን መንገድ ጠቆሙኝ።
እድልን ሳያት በሀዘን ተጎሳቁላ ዝም ብላለች።እውነቷን የምታውቀውን አጥታለች አንድ የምታስታውሰው ነገር ቢኖራትም ግን የጠቀማት አይመስልም። ሴትየዋን መልሼ ጠየኳቸው "የማን ልጅ ናት ቤታቸውስ?" አልኳቸው ሴትየዋም "የቡና ነጋዴዋ የእልፌ ልጅ ናት ከጥምቀተ ባህሩ እታች ናቸው።" ብለው በሀዘኔታ እድልን ተመከቷት። እኔም እድልን ደግፌ ወደ መኪናው አስገብቻት ለመኝታ የቀረውን ገንዘብ ከፍዬ ወደ ኢሉባቡር ጎሬ አቀናሁ። የመንገዱ ዳር እና በጥቅጥቅ ደን የተሸፈነ ተፈጥሮአዊ ውበቱን ያላጣ በጭጋግ የተሸፈነ ፀሀይ የሚናፍቀው ምድር ነው በቃ ዙሪያውን እያየው ስገረም ሴትየዋ ከነገሩኝ ከጥንታዊቷ ከማርያም ቤተክርስቲያን ጋር ስደርስ መኪናውን አቆምኩኝ እድልም በእንባ ደም የለበሰውን አይኗን ከብለል ከብለል አድርጋ አጥፍቶ ይቅርታን እንደሚማፀን ህፃን ተመለከተችኝ እኔም እጇን ጠበቅ አድርጌ ይዤ "ጠብቂኝ" ብያት ከመኪናው ወርጄ አንድ አዛውንትን ቀስ ብዬ ተጠግቼ "ደህና አረፈዱ አባባ" አልኩኝ።"አካም ቡልቴ" አዛውንቱ በኦሮምኛ መለሱልኝ መስማትም መናገር አልችልም እና "አማርኛ አይችሉም" አልኩኝ ከተረዱኝ ብዬ "አፋን አማሪፋ ኢንቤኩ" መለሱልኝ። እኔም መግባባት እንደማንችል ሲገባኝ "በቃ ሰላም ይዋሉልኝ አባባ" አልኳቸው እሳቸውም አልፈውኝ ቀስ እያሉ ቁልቁለቱን እየተንቀጠቀጡ ወረዱ እኔም ጎዳናው ላይ ወገቤን ይዤ ቆሜ ሰውን ሳማትር "ምን ልርዳህ ወንድሜ" የሚል ድምፅ ሰማሁ ደስ አለኝ የብስራት ዜና የሰማሁ ያህል ተሰማኝ....አንድ ቱታ የለበሰ መልከመልካም ወጣት ነበር። ስመለከተው በበረሃ ውሃ እንደፈለቀለት ሰው ፊቴን በደስታ አበራሁት እና "እዚህ አካባቢ የቡና ነጋዴ የሆኑትን የእልፌን ቤት ፈልጌ ነው" አልኩት። ወጣቱም "እእ ቤታቸው..." አቋረጥኩት እና ቆይ አብራኝ የሆነች ልጅ አለችና ካላስቸገርንህ ብትወስደን" አልኩት። ወጣቱም ሰይጣናዊነት ያልተናወጠው ባለሀገር ነውና "እሺ ረኮን ቀቡ" አለኝ መጨረሻ ላይ ያለው ነገር ባይገባኝም ወደ መኪናው ጋር ሄድኩኝ ስሄድ ግን ያቺን የደከመቸውን እድል እንደጠበኳት አላገኘኋትም ከአፏ እና ከአፍንጫዋ ደም ፈሶ ራሷን ስታለች "ወንድሜ ወንድሜ ! እርዳኝ" አልኩና ወጣቱን በጩኸት ጠራሁት እሱም ሮጦ መጥቶ ተመልክቶ በድንጋጤ "ማሎ ማሎ" ቀጠለ "ነገርጋራ ነገርጋራ" ብሎ በእጁ ሌሎች ሰዎችን ጠራቸውእና አግዘውኝ ቅርብ ካለው ጤና ጣቢያ አስገብተናት ውጪ ቆምን ወጣቱም " ዴሚቲ እትዬ እልፌቲ ሂሚ" ሲል ሰምቼ ቀና ብዬ አየሁት ትርጉሙ ገብቶኝ ሳይሆን እልፌ የሚል ነገር ስለሰማሁ ነበር"እሷ እድል አይደለች ልጃቸው" አለኝ። ተመስገን አልኩኝ በልቤ ደግሞ ለእናቷ አዘንኩላቸው "አዎ ናት ግን በዚህ ሁኔታ..." ስለው ወጣቱ "እሷን በማጣታቸው ቤተሰቡ ከውጪ የመጣችው ልጃቸውም ተሰቃይተው ሊሞቱ ነው" አለኝ እና ሌላኛውን ፈርጣማ ወጣት ላከው እና ከጎኔ ተቀምጦ ያወጋኝ ጀመር "እንዴት እንደተሳቃዩ እኮ ምን አይነት ምስኪን ልጅ እንደሆነች አትጠይቀኝ ለእህቷ ብላ ነው ከከተማ የገባች ምን ዋጋ አለው እንዲህ ሆና መጣች" አለኝ በያዘው ዱላ መሬቱን መታ መታ እያደረገ። ታሪኳ ቀልቤን ሳበው "ማለት እህት አዲስ አበባ ናት" አልኩት። ወጣቱም "ኧረ አይደለም እህቷ የቀድሞ ወዳጇን ይቅርታ ብላ መሞትን ስትናፍቅ ብታይ ነው አዲስ አበባ የሄደች ቤት እንዳይከለክሏት ያው ጠፋታ ነው።" አለኝ።ጭራሽ ግራ ገባኝ "እና.." አልኩት ሰፋ አድርጎ ከነገረኝ ብዬ "እኔ አፈር ልብላላት ደግ ልጅ እኮ ናት ለሰው ሟች ዝምተኛ " አለ በሀዘን እየተወሰወሰ። "እህቴ እህቴ" በለቀሶ አንዲት ሴት ወደ እኛ ጋር መጣች አይኖቼን ማመን አቃተኝ ሰውነቴ ላብ አጠመቀው....

ይቀጥላል
😭😭አሳዛኝ የመጨረሻ ክፍሎች እንዲለቀቁ ድምፅ ይስጡ!!
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
📖📖📖የግጥም መንደር📖📖📖
💔💔💔ሰባራ ልቦች💔💔💔
🍒🍒🍒ክፍል አስራአንድ
ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ
@yebezawit2

... አንዲት ቀጠን ብላ ፊቷ በማዲያት የበለዘ ምስኪን ሴት ነበረች ወደ ሆስፒታሉ በለቅሶ የገባችው።የሆነ ቦታ እንደማውቃት እየተሰማኝ "ተረጋጊ አሁን ደህና ናት" አልኳት ከውስጥ ሆኜ ያየው ይመስል።እሷም ስታየኝ ደንግጣለች።ግን "የት ነው ማውቅሽ" ብዬ መጠየቅ የምችልበት ቦታ አይደለሁም እና ዝምታን መርጬ ወንበሩ ላይ ቁጭ አልኩኝ።እሷም መቆም ያቃተውን እንባዋን በሹራቧ እየሞዠቀች ቆማ መጠበቅ ጀመረች ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ ነርሷ መጥታ "የእድል ቤተሰቦች" አለች። ተከተልናት....ዶክተሩ ወንበሩን ስቦ እየተቀመጠ "አረፍ በሉ" አለ በእጁ ወንበሩን አመልክቶ። ተቀመጥን ሰውነቴ ዝናብ እንደመታው ሰው ይንቀጠቀጣል። "እእ አሁን እድል...." ካርዱን አገላበጠ። "እህቴ ምንሆነች" ወጣቷ ጠየቀች። "አሁን ደህና ናት ነገር ግን አንድ ነገር አለ" "ምንድነው?" ጠየኩት እኔ በተራዬ። "እድል በአሁን ሰአት ሰውነቷ መታዘዝ አይችልም" "እህቴን በላኋት" ተንሰቅስቃ ማልቀስ ጀመረች። "ይቅርታ ዶክተር እኔም ዶክተሯ ነኝ እና ያለውን ነገር ብትነግረኝ" አልኩት። ዶክተሩም ፈገግ ብሎ ፍንጭት ጥርሱን ብቅ አደረገ እና "ኧረ ጥሩ ነው" ብሎ ስለ እድል ይበልጥ ተንትኖ ነገረኝ እና ካርዷን ሰጠኝ። የተስፋ ጭላንጭል ወገግ አለልኝ እድል ጥሩ ህክምና ካገኘች መዳን ትችላች እናም ለዚህ ደግሞ መፍትሄው ጭንቀቷን አቅልሎ ፊዞቴራፒ ማሰራት ነው። ከዶክተሩ ክፍል ወጣን። ወጣቷ በለቅሶ ብዛት ልትሞት ደረሰች "እባክሽን ተረጋጊ የአንቺ እንደዚህ መሆን ለእሷ አይጠቅማትም" አልኳትና ወደ እድል ክፍል በሩን ከፍቼ ገባሁኝ።

እድልም ስታየኝ ፈገግ ብላ ፊቷን አበራችልኝ። "ደህና ነሽ" አልኳት አጠገቧ ተቀምጬ እጇን ይዤ።"ደህና ነኝ" መለሰችልኝ ደስ አለኝ። "አስጨነቅሽኝ እኮ አይኖችሽን ከድነሽ" አልኳት። "ለእኔ የሚጨነቅ አገኘሁ" አለችኝ። ደነቀኝ በትክክል ለምጠይቃት መለስ እየሰጠችኝ ነው። "አሁን መውጣት ከቻልሽ ወደ ቤት እወስድሻለሁ" አልኳት። "አይይ አትውሰደኝ እባክህ እህቴን አይኗን ማየት አልችልም ሞት እና ህይወት መሀል ላይ ሆና መአት አልድገምባት" ብላ አለቀሰች። "እሺ እሺ አታልቅሺ ሌላ ቦታ እንሄዳለን" አልኳት። "አውቃለሁ ሁሉንም ዶክተሩ እንደነገረህ" ብላኝ ከክፍሉ ብቻዬን አስወጥቶ የነገረኝ ነገር ትዝ አለኝ። እውነት ነው ለሌላ እንዳላወራ ተነግሮኛል። "አዎ እድል ነግሮኛል ግን አታስቢ እና ግን አንዲት ሴት ስለአንቺ እያለቀሰች....." አቋረጠችኝ "ምህረት ናት" አለችኝ። ልክ ነኝ ይህቺን ሴት አውቃታለሁ።"መሰለኝ ምንሽ ናት?" ጠየኳት። "የእህቴ የአክስት ልጅ ናት" መለሷ አስደመመኝ። "ማለት አልገባኝም ለአንቺስ" ብዬ የደስታ ጨረር የሚያመነጩ አይኖቿን ተመለከትኳቸው።"እእ እንደነግርህ ከፈለክ ከዚህ ቦታ አስወጣኝ እሷ ሳታየኝ" አለችኝ እና ቀስ ብላ እጇን እጄ ላይ አሳረፈች ለምን እንደሆነ ሳይገባኝ ልቤን ነዘረኝ ደስ የሚል ሊገባኝ እና ልረዳው የማልችለው ደስታ ተሰማኝ። ምን አልባት እሷ አስባው ላይሆን ይችላል ግን ሳላውቀው በእድል ብዙ ነገር ሆኛለሁ ሲከፋኝ ደስታዬ ስቃጠል ማብረጃዬ ስጠማ ውሃዬ እየሆነች እንደሆነ ተሰምቶኛል በሰምሃል ዛሬ አላዝንም ሴትነት የሚባለውን ነገር እድል ጋር እያየሁት ነው ትሁትነቷ ዝምታዋ ፈገግታዋ ሌላ ነው።.....አይ እኔ በቃ ልወዳት ነው....ወደድኳት ማለት ነው? ፍቅር ያዘኝ ማለት ይሆን...ለራሴም ቅኔ ሆነብኝ መቼ ነው እንዲህ የሆንኩት ማለት ጀመርኩ።.."እሺ በቃ አህትሽን ላሳምን እና ይዤሽ እወጣለሁ" ብያት ከተቀመጥኩበት ተነሳሁ "ምግብ ግን እፈልጋለሁ " አለች። "እሺ አመጣልሻለሁ" አልኳት። "አይ አስወጣኝ እና እበላለሁ" አለችና ፈገግ አለች። እኔም ለፈገግታዋ ፈገግታዬን መልሼላት በሩን ከፍቼ ወጣሁኝ....😊😊😊😊

😭😭ያልተጠበቁ ክስተቶችን ይዞ ቀጣይ ክፍል ይቀርባል
ድምፅ መስጠት አትርሱ!!
💔💔ሰባራ ልቦች💔💔
👉ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ 👈
🍒🍒የግጥም መንደር🍒
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
🔖ማስታወቂያ 🔖

በተወሰኑ ቀናት ያለምንም ክፍያ ጠቃሚ ምክሮችን ለማግኘት እና ለማማከር
0983744901 👈👈
ላይ #ሙሉ ስማችሁን በቴክስት ብቻ ልከው እስከ 16/2013 ድረስ ይመዝገቡ!!!

👍👍👍
አመሰግናለሁ
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
ለተጨማሪ ጥያቄ @yebezawit2
💔💔💔ሰባራ ልቦች💔💔💔
ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ

👉ክፍል አስራሁለት 👈
@yebezigetmoch

"እንዴት ናት ገብቼ ልያት እባክህን" ወጣቷ ምህረት ተማፀነችኝ እኔም ትከሻዋን ሰበቅ አድርጌ "አሁን እጅግ ፀጥታ እና እረፍት ያስፈልጋታል እና አሁን አንቺ ወደ ቤት ሄደሽ የሚለበስ እና የሚበላ ነገር አምጭላት" አልኳት በሀሳቤ ከእድል ጋር የት እንደምንሄድ እያሰብኩኝ።"ሰዎች እልካለሁ" አለችኝ እድልን ቆማ ለመጠበቅ።"አይሆንም አንቺ ሂጂ እና ልብስሽንም ቀይረሽ ነይ እንዲህ ሆነሽ ካየችሽ ስሜቷ ይጎዳል" አልኳት።አመነችኝ የጨነቀው.... አይደል ነገሩ በማያሳምን ምክንያት ተስማምታ ወጣች።እኔም የእሷን መራቅ ተከትዬ ይዣት ወጣሁኝ እና ወደ ጅማ ተመለስን።"ጥሩ ጠላፊ ነህ" አለችኝ አይኖቿን እያንከባለለች። "ያው ተጠላፊዋም የዋዛ አይደለችም" አልኳት ከአንድ ተለቅ ካለ ሆቴል ግቢ መኪናዬን እያስገባሁ። ውስጤ ብዙ እየጠየቀኝ ላላስጨንቃት ብዬ ጥያቄዬን አምቄ ይዤዋለው። "እንኳን ደህና መጣችሁ" እንግዳ መቀብያው ጋር ያለችው ውቧ እንስት ተቀበለችን። ክፍሉን ተከራይተን ገባን እና አልጋው ላይ አስቀመጥኳት መንቀሳቀስ አለመቻሏ ለእድል አልከፋትም።ምግብ ከተመገብን በኋላ ስልኬን ቻርጅ ላይ አድርጌ በመስኮቱ የጅማን ነዋሪ መታዘብ ጀመርኩ።"እርግጠኛ ነኝ ለምን በአንዴ ተለወጠች እያልክ ነው" አለችኝ ጁሱን እየተጎነጨች እድል።"አዎ ገርሞኛል" መለስኩላት ፊቴን አዙሬ።"ተቀመጥና እስኪ የጓጓህለትን ታሪኬን ልንገርህ" አለችኝ ወንበሩን ሳብ አድርጌ ተመቻችቼ ተቀመጥኩኝ እሷም ደገፍ ብላ ተቀመጠች "ትውልዴ ኤርትራ ነው አባቴ ነው ኢትዮጵያ ያመጣኝ እና በጥሩ ሁኔታ ነበር ያደኩት ግን ልክ አስራ ሰባት አመት ሊሞላኝ ሲል የሚወደኝ አባቴ ለጓደኛው ልጅ አደራ ሰጥቶኝ ያርፋል እናም ይህቺ አደራ የተቀበለችው እህቴ ደግሞ ተቀብላ ታሳድገኛለች ታላቄ ናት እናም እወዳት ነበር ቀስ እያለ ግን ነገሮች ተባላሹ እናም እንደምታየኝ ብዙ ጊዜ ዝም የምለው አሳልፋ ለአንድ ጫታም ሰውዬ ሸጣኝ ነበር ከዛ ለማንም እንዳላወራ ትገርፈኝ ምግብ ትከለክለኝ ነበር።" እንባዋ ያለመቆም ህመሟን እየዘነበ ይናገራል።"ታላቅነቷን ግን ስለማከብር እኔም ዝም ማለት ጭምትነት አበዛሁ ፍልቅልቋን እኔነቴን አጣሁ ከዛ በኋላ ጓደኛ ይዛ ነበርእና እወነተኛ አፍቃሪዋን ክዳ ለጥቅሟ ስትል ሌላ ሰው አገባች ደስታ ለሌለበት ህይወቷ ራሷን ገበረች እሱም አልበቃ ሲላት የእሱን ንዴት እኔ ላይ እየተወጣች በብዙ ጎዳችኝ በመድሃኒት አደከመችኝ በወንዶች ተጫወተችብኝ ግን ሁሌም የልመናዬ ልመና እንዲሰጠኝ ነውና ልቦና ይቅር እላታለሁ ስለእሷ እና ስለበፊት ፍቅራችን አነባለሁ ልክ ውጪ ስትሄድ ግን እረፍት አገኘሁ በቃ ተገላገልኩ ብዬ ከአባዬ እህት ለእኔ ግን ፀጉሬን ገላዬን አጥባ ያሳደገችኝ መብላቴን ተጨንቃ የምታረጋግጥው ከእናቴ ጋር መኖር ጀመርን በቃ ሁሉም የእሷ ልጅ እንደሆንኩ ነው የሚያውቀው እውነት ነው ልጇ ነኝ እናም ስሟ ስሜ ሆነ የእለፌ ልጅ ተብዬ ተከበርኩኝ ተወደድኩኝ ግን ልቤ አንካሳ ነበር እምነት የራቀው የቀረበውን የሚሸሽ ያጀበውን የሚፈራ እምነተ ቢስ በመሆኑ ተጎሳቆልኩ በሰው ሚዛን ስዳኝ ሰው የማልወድ እመስላለሁ በእግዚአብሔር አይን ግን በእርሱ ሚዛን ግን የደከመች ማረፊያ አጥታ የምትንገላታ ደካማ ሴት መሆኔ ግልፅ ነው ብቻ በብዙ ልፋት ህመሜን ለማዳን ስጥር ታዲያ እህቴ ታማ በወራት ወደ ሀገር ቤት ተመለሰች የካንሰር እና የደም ግፊት ታማሚ ሆና ልትሞት ጊዜያት ሲቆጠሩ ሁሌም እኔን ትወቅሳለች አትወጂኝም ስበድልሽ እረግመሽኛል ትለኛለች እውነት እኔ ግን አልችልም እሷ ላይ የሚዘጋ በር የለኝም በደጉ ጊዜ መከታዬ ናት አብረን ተደስተን አዝነናል አጥተን አግኝተናል እና ልረግማት አልችልም መንገዷን እንዲያቀና እንጂ መንገዷን እንዲዘጋ ለመለመን ድፍረቱ የለኝም ምክንያቱም ይህች አለም እንኳን ለእኔ ለጌታዋም አልሆነችም እና የሰማይ ደስታን እያሰብኩ እፅናና እና እበረታ ነበር። ለዚህ መሰለኝ ሁሌ የዘራሁትን አጨድኩ ነፍሴ ተቃጠለች ትለኛለች መውደዴ እና ሀዘኔታዬ ፌዝ ነበር ለእሷ ፍቅርህ በወደድከው ሰው ሳይከበር እና ሜዳ ሲወድቅ እንደማያት ስብራት የለም እንደምወዳት እንድታውቅልኝ ብዬ ይቅርታ ለመጠየቅ የምትፈልገውን ወዳጇን ፍለጋ ፎቶውን ሳላይ ስሙን እና አፍቃሪነቱን ይዤ መጣሁ ግን አጣሁት ላገኘው አልቻልኩም በዛ ላይ ከቤተሰቤ ጠፍቼ መሄዴ ሙሉ መረጃ ለማግኘት መከራ ሆነብኝ ሃሳቤ አንካሳ ሆኖ ቀረ እናም ይሰራበታል የተባለ ሆስፒታል እብድ መስዬ ገባሁ ግን አልተሳካም ሊመጣ አልቻለም። መውደዴን እና ለእሷ ያለኝን ቦታ ሳትሞት ላሳያት ብሻማ አንካሳ ነውና አልሆነም ጎደልኩኝ በሽተኛ ለመሆን ስጥር ውሸት ወልጄ ውሸት ሳሳድግ እውነተኛ አንተን እና ቤተሰብህን አገኘሁ በቃ ከበደኝ ለዚህ ነው ጅማ ውሰደኝ ያልኩህ ቤተሰቤ ጋር እንዳደረስከኝ አንተም ብዙ ሳጠይቀኝ እንድትሄድ እኔም እያየሁ እህቴን ወደ አፈር እንድሸኛት ግን እውነቴ ተጋለጠብኝ ከምንም ነገር ምንም ሆኜ ቀረሁኝ" አለችኛና ዱብዳውን አወረደችብኝ።"አልገባኝም እድል ምን ግራ ነገር ነው የምትነግሪኝ" አልኳት ያወራችው ነገር እኔ ጋር ትርጉም አጥቶ ሚዛን አልደፋ አለኝ።"ስለዚህ ያሁሉ ድራማ ነው ወንድሜ አሊሾ ያውቃል" ጠየኳት አይኔን ጎልጉዬ "አ...አ...አዎ ያውቃል" ቃሉን ከአፏ ጎትታ አወጣችው።ስልኬን አወጣሁ ደወልኩኝ ደገምኩ ስልኩ ዝግ ነው እናቴ ጋር ደወልኩ ዝግ ነው ይበልጥ ጥያቄዬ ይጎርፍ ጀመር "እናቴስ" "አያውቁም" መለሰች።"ማንን ልመን" ጠየኳት "ውስጥህን" ስትመልስ አልፈራችም።"ቆይ ህመምሽስ ምንድነው" "ህመም ነው ሰው ሲያገኝ የሚድን ሲያጣ የሚብስበት ህመሜ የኔ ህመም ነው እንደአዘንክ እና እንደደነገጥክ ግልፅ ነው ግን እመነኝ አሁን አንተ መመለስ ትችላለህ እኔ ለትንሽ ጊዜ ባለችው ጊዜያት እፈልገዋለሁ" አለችኝ እንባዋን እየጠረገች። እጄን እግሬን መላ ሰውነቴን በነገር እየወዘወዝኩ ተብሰለሰልኩ። ደግነቷ ገዝፎ ታየኝ የእምነቷ ፅናት የፍቅሯ እውነት እኔንም እንዲህ ብትወደኝ ብዬ ተመኘሁኝ ማንም ይመኛል ደግሞም ሲገፉት የሚደግፍ ሲርቁት የሚከተል ሲያጠፋ የሚምር ሲጠፋ የሚፈልግ እንዲህ ያለ ሰው በዚህ ክፉ ሀሳብ በሞላበት ጊዜ ከየት ተገኝቶ ቢገኝ ግን ማን አይኑን ያሻል በዛ ላይ ሲጨመር ውበት እኔጃ እየኖርኩ ሳይሆን አንድ መጥፎ ደራሲ ሊያጓጓኝ በስሜ የደረሰው ታሪክ መሰለኝ።ግን እውነት ነው ብቻዬን ስብራት እና ፍቅር ውስጥ ነኝ....ቆይ እሺ ብተዋት እግዜር አይታዘበኝም. እዛው ማሰቤን ቀጠልኩኝ እሷም መልሴን ለመስማት ጡት እንዳየ ህፃን ተቁለጨለጨች "ስሙ ግን ማነው?" ጠየኳት። እንደማልርቃት ቢገባት ተፍነከነከች። "እእ ንገሪኝ ስሙን ከሆስፒታሉ መረጃ ልውሰድ" አልኳት።ጉሮሮዋን ጠራርጋ "እ....." ይቀጥላል!

😭ሰባራ ልቦች ልብ ሰባሪ የፍቅር ታሪክ💔
🍒🍒ይቀጥላል🍒🍒
ድምፅ መስጠት አይርሱ
🙏እናመሰግናለን🙏
💀 @yebezigetmoch
💀 @yebezigetmoch
💀 @yebezigetmoch
👉 @yebezawit2 👈
💔💔💔ሰባራ ልቦች😭😭😭
🌹🌹ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ🌹🌹🌹
😐😐ክፍል አስራሶስት 💔💔🙋
@yebezawit2

"እእ...ስሙን ንገሪኛ?" አልኳት።"አ..አክሊል ነው ስሙ" ደነገጥኩኝ "አክሊል ማን የት ነው የተማረው" አልኳት " አክሊል ማን እንደ ሆነ ባላውቅም የተነገረኝ የዋህ እና ጥሩ ዶክተር እንደሆነ ጨዋታ አዋቂ ሲበዛ ትሁት መሆኑን አውርታልኛለች" አለች። እኔም በሩን ከፍቼ ትቻት ወጣሁኝ...ባንኮኒውን ተደግፌ አስተናጋጁ የሚቀዳልኝን ጂን ጨለጥኩት። እኔን ነኝ ብዬ አስቤ ነበር ኧረ አክሊል ስትልም ሰምሃል ነበር የመጣችብኝ ግን ሰምሃልን አውቃታለሁ ክፋትን የማታውቅ ንፁህ ሰው ናት ህፃን ልጅ ልቡ እን ውሃ የጠራ ነውና ሀሳቤን እንደሞኝነት ቆጠርኩት። እንደምንም ተነስቼ ወደ ክፍሌ ስመለስ እድል ቁጭ ብላ እያነባች ነበር ምንም ማለት አልችልምና ከእሷ ጎን አጠገብ ካለው አልጋ ላይ ተንጋልዬ ተኛሁኝ። ግነሰ እንቅልፍ የለም አይኖቼን ስከድን ሰምሃልን ከአያታለሁ ደግሜ እገልጥ እና በመዳፌ ፊቴን እሞዥቃለሁ ነገሮች እንደዚህ መሆኗቸው እያብከነከነኝ ስልኬ ጠራ እንደምንም ከኪሴ ውስጥ አውጥቼ አነሳሁት "ሄሎ" አልኩኝ አይኖቼን ጨፍኜ።
"ሄሎ ወንድሜ ደውለህ እኮ ስልኬ ዝግ ነበር" ወንድሜ አሊሾ ነበር። ከተኛሁበት ተነሳሁ
"ምንድነው አሊሾ የሰማሁት እድል የነገረችኝ ማለት..."
አላስጨረሰኝም "ወንድሜ ተረጋጋ ነገሮች እንደዚህ ይሆናሉ ብዬ አልገመትኩም ያው ሚስጥሩን እራስህን እንድትደርስበት እና ቃል የገባኸውን የሙያ ግዴታህን እንድትወጣ ነው" ብሎ ነገሩን አቀለለብኝ
"ያልገባህ ነገር አለ ልጅቷ ጤነኛ ነት ለምን እብድ ናት መባል ፈለጋችሁ" ብዬ ጮውኩበት።

"ስሜትህን ለመቆጣጠር ሞክር" አሊሾ ተቆጣ።"ስማ ይሄ የሙያ ግዴታህ ብቻ ሳይሆን ሰብአዊነት ለሚሰማው ሰው ነኝ ለሚል ሁሉ ግዴታው ነው።ቢገባህ እና ብትረዳት ለንፁህ ፍቅሯ ስትል ልትረዳት እና የጥሩ ታሪኳ አካል ልትሆን ይገባሀል" አለኝ እና "እኔ ደስታ ላይ ነኝ አባት ሆኛለሁ እናትም እዚህ ናት ሰው ከሆንክ ደስታን ይዘህ መጥተህ ልጄን ታቅፈዋለህ እንዳላዝንብህ ተጠንቀቅ ስለ ፍቅር ለአንተ አልነግርህም" ብሎ ስልኩን ጆሮዬ ላይ ዘጋው።

ቀስ ብዬ እድልን አየኋት።"ይ...ቅ...ርታ የእውነት በዚህ መልክ የሚጎዳህ አልመሰለኝም አለመኖርን ለመታገል ስል የመኖር ጣዕምን ያጣሁት" ብላ ዝም አለች እኔም አተኩሬ አንዴ እንደ ወንድ ከዛም እንደ ዶክተር ግራ ሲገባኝ እንደ ወንድም ሆኜ አየኋት ታሳዝናለች ሶስቱም እይታዬ አንድ ነው የዋህ እንደ ርግብ ናት እና ክንፍ ሆነህ በውብ ሰማይ ላይ አብርራት አለኝ።"ችግር የለም በራሴ ነው ያዘንኩት ነገ እናወራለን አሁን ተኚ" አልኳት። እሷም "እሺ አንተም ተኛ ደህና እደር" ብላ እንዳግዛት አየችኝ እኔም ተነስቼ አገዝኳት እና ብርድ ልብሱን አልብሻት ወደ ቦታዬ ተመልሼ እመለከታት ጀመር።በዚህ ውበት ላይ የሚገርም ስብእና ማነው እንደዚህ ሰውን የሚወድ እና ለሰው ዋጋ የሚከፍል ያውም የገዛ እህቷ አይደለችም የአደራ እንጂ ግን እንደዛም ተበድላ ተሰቃይታ ከደሟ አዋህዳት አካሏ አድርጋታለች በተፈላጊው ሰው ቀናሁኝ በዚህች ንፁህ ሴት በፍቅር ዋጋ ከፍላ መፈለጉ እድለኝነት ነው። እኔ ግን ይበልጥ በልቧ ጓዳ መሸሸግን ፈለኩ በቃ ከዚህ አለም በእሷ ተደብቄ በሴትነቷ መንኜ መኖርን የውበት ልክ የሰውነት ማሳያ....
ለሊቱ ግርማው ተገፎ ፀሀይ ፍንትው ብላለች ቀስ ብዬ ከአልጋው ወርጄ ወደ መታጠቢያ ክፍል ገብቼ ተጣጥቤ ወጣሁኝ እድል ግን ከእንቅልፏ አልነቃችም።ቁርስ አዝዤ እድልን ቀስ ብዬ ቀሰከስኳት እሷም አይኖቿን ቀስ ብላ ከፈተቻቸው እና አየችኝ "ደህና አደርሽ" አልኳት ፊቷን የጋረደውን ፀጉሯን በእጄ ወደ ኋላ እየመለስኩት። በሀሳቤ አሰብኩኝ በእሷ ፍቅር ወድቄ ጥዋት ስነቃ በደረቴ ውላ ባያት ብዬ ተመኘሁኝ በፈገግታዋ እና በሚያምር እይታዋ ፈዛ እያየችኝ "ደህና አደርክ ባሌ" እንድትለኝ ተመኘሁኝ። ምን አይነት ሀሳብ እንደ ሆነ ባይገባኝም የእውነት ወድጃታለሁ በቃ ደስ የሚል ስሜት እና ነገ የሚባል ተስፋ እንዲኖረኝ በቃሏ ሳይሆን በአይኖቿ መርታ አሳይታኛለች።" ደህና አደርክ" አለች። በውብ ፈገግታዋ "እግዚአብሔር ይመስገን...እንደዚህ እንቅልፋም መሆንሽን አላውቅም ነበር" አልኳት። "ጭንቀቴን አንተን አሸክሜ ተኛሁኝ አይደል" አለችኝ። አይኖቿን በአይኖቼ አተኩሬ እያየሁ "ከዚህ በኋላ ከጎንሽ ነኝ ምንም አትደብቂኝ" አልኳት። እንደ ጠዋቷ ፀሀይ ፊቷ አበራ።"አመሰግናለሁ" ብላ በእጇ ጉንጬን ዳበሰች። እኔም እጇን ይዤ "አታመስግኚኝ ይልቅ አሁን ተነሺ እና ወደ ፊዚዮትራፒ ህክምና ትሄጃለሽ" አልኳት። እሷም በአውንታ ራሷን ነቀነቀችልኝ።
በቃ አሁን ይበልጥ ደስተኛ ነኝ በየቀኑ እድል ህክምናዋን ትከታተላለች ውብ ጊዜም እያሳለፍን ነው እሷ መንፈሳዊውን አለም ስታሳየኝ እኔ ደግሞ አለማዊን እያሳየኋት እጅ ለእጅ ተያይዘናል እህቷ ለመሞት ያላትን ጊዜ በሰው አድርጌ አጣርቼ ወደ አዲስ አበባ መጥተን ዶክተር አክሊልን ፍለጋ ለመሰማራት ዛሬ የእድል ዶክተርን ፍቃድ ማግኘት አለብን በእርግጥ መንቀሳቀስ ጀምራለች እጅግ በሚገርም ፍጥነት ለውጥ አላት ደስ የምትለዋ ተወዳጇ እድል እኔን በምን አይኗ እንደምታየኝ ባላውቅም እኔ ግን ከማፍቀር በላይ እያፈቀርኳት ነው። ለህክምና ዶክተሯ ጋር ስትገባ ለምንለያየው ጥቂት ጊዜ ጨለማው ገዝፎ ይታየኛል እሷ ከጎኔ ስትሆን የህይወት ሻማዬ ይበራል ንፋስ ሳያጠፋው ይደምቃል ከሄደች ግን ውሃ እና ንፋስ ይፈራረቁበታል።
"አሁን በጣም ጥሩ ለውጥ ላይ ነሽ እናም ወደ አዲስአበባ መሄድ ትችላላችሁ" ዶክተሩ አበሰረን።
መንገድ ጀምረናል ወደኋላ እየተወን ወደፊትእየገሰገስን ስልኬ አቃጨለ ዶክተር ዘውዱ ነው ስለ ዶክተር አክሊሉ እንዲጠይቅ የጠየኩት ወዳጄ ነው። መኪናዬን ከአንድ ጥግ አቁሜ ።"ሄሎ" አልኩኝ። እና ሰላምታን ተለዋወጥን
"ዶክተር አዝናለሀ ዶክተር አክሊል የሚባል ሰው የለም አንተ ባልከኝ የእድሜ ደረጃ አንድ ሰው ነው ያለው እሱም የቆየ ነው" አለኝ።
ተበሳጨሁ "እሺ በቃ አመሰግናለሁ" ንዴቴ ከድምፄ ያስታውቃል።
ስልኩን ዘጋሁት።"ምንድነው አልተሳካም?" አለች እድል። እኔም "አዎ" መለስኩላት።"አትናደድ ገና ብዙ በሮች አሉን እንሞክራለን ተስፋ ላለው ሰው ሁሌም መውጫ አለው" አለችኝ ቀና ብዬ አየኋት "ምነው እንደዚህ አትየኝ እውነቴን ነው እንዳውም አንድ ታሪክ ታወሰኝ።አንድ ሰው በዝሆኖች ፓርክ ሲያልፍ ዝሆኖቹ ከሰንሰለት ወይም ከወፍራም ገመድ ይልቅ በቀጭን ገመድ እግራቸው ላይ ብቻ ታስሮ ተመልክቶ ደንቆት እዛ ያለውን ሰው ይጠይቀዋል 'እንዴት በዚህ ገመድ ታሰሩ በጥሰው ቢወጡስ' አለው ሰውየው 'ከልጅነታቸው ጀምሮ እንደዚህ ታስረው ስለአደጉ መበጠስ የሚችሉ አይመስላቸውም' አላቸው። እናም ምን መሰለህ ገመዱን ጎትቶ መበጠስ መቻሉን አእምሮአችን ካመነ ሁሉም ቀላል ነው ስለዚህ አግዘፍህ አትየው" ብላ አየችኝ። ይበልጥ ወደድኳት "አንቺ ግን...." ስልኬ ጠራ። ዶክተር ዘውዱ ነው "አቤት" አልኩት አንስቼ።
"ሳልነግርህ ዘጋኸው....አክሊሉ ሳይሆን አክሊል የሚባል ሰው በአንዲት ዶክተር ፋይል ውስጥ አግኝቻለሁ በዛ ጊዜ አብረው የተመረቁ ናቸውና..." የሰማሁት መላ ሰውነቴን ሲነዘረኝ ታወቀኝ ዝም አልኩ።
"ሄሎ ዶክተር...ዶክተር...አይሰማም"
.......
......
.......
......ዝም በቃ ዝም አልኩኝ።
😭😭አሳዛኝ ታሪክ ሰባራ ልቦች💔💔💔
ድምፅ በመስጠት ቀጣይ ታሪክ ያግኙ💕💕

😭😭ለሁሉም
2025/07/04 14:32:36
Back to Top
HTML Embed Code: