Telegram Web Link
💯ማስታወቂያ 💔💔
ሰባራ ልቦች
ከነገ ከሐሙስ ጀምሮ #በረጅም አቀራረብ እንዲሁም በሁለት ክፍል በልዩ ሁኔታ ይቀጥላል!!
ሰአት🌻 የመጀመሪያ ክፍል 1:45pm
🌻ሁለተኛው ክፍል 3:00 ምሽት ላይ ይጠብቁን!!

😭😭አሳዛኝ ታሪክ😭😭
ድምፅ መስጠት አይርሱ!ምክንያቱም ብርታቴ ነው🙏🙏🙏
አመሰግናለሁ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💔 ነፍስ እንኳን ከአካል ትለያለችና
ምንም ነገር እስከመጨረሻው ከእኔ ጋር
ይቆያል ብለህ አታስብ...
╔══❖•ღڿڰۣ✿•°•✿ڿڰۣღ•❖══╗​​​
ღ ❥............🍃🌹🍃.........
@yebezawit2 @yebezawit2
@yebezigetmoch
❥............🍃🌹🍃.............
🌹🌹 #LOVE🦋🦋
​​╚══❖•ღڿڰۣ✿•°•✿ڿڰۣღ•❖══╝​​​​
💕ሰባራ💕 ልቦች💕💕
ክፍል ስድስት💓💓💓
🍬ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ💕
@yebezawit2

...እንባዋ ህመሟን ይናገራል።"እኔ ማነኝ ስል እራሴን አላውቀውም ሁሌ እኮ ዝም የምለው ለምጠየቀው ጥያቄ መልስ ስሌለኝ ነው የገዛ እናቴ እኮናት አውጥታ የጣላቸኝ አባቴም አሳልፎ ሽጦኛል እስኪ ልጠይቅህ ወላጆችህ የበደሉህ በምን ምክንያት ነው?" አለችኝና ተመለከተችኝ እኔም ህመሟ የቆሰለውን የልቤን ህመም አስረስቶ የሷን እንዳስብ አስገደደኝ።"በእርግጥ በሴት ምክንያት ነው የጣላነው።የምወዳት እና ለእሷ ብቻ የምኖር የሚመሰለኝ ሴት ነበረች ስለእሷ የምናገረው ሁሉ ካላት ነገር ጋር አይወዳደርም ሁሉም ያንሳታል ግን ይሄ ፍቅር ሸክላ ሆኖ ወድቆ ተሰበረ።ስለእሷ የደከመ ሰውነቴ ሞተ አከተመ።ያው እኮ ላገባት ነበር ሙሉ እኔነቴን ልሰጣት ሀሳቧ ሀሳቤ ህልሟ ህልሜ ሊሆን ነበር...ነበር ስል ያመኛል" ንግግሬን አቋረጠች።"እድለኛ ነህ አንተ ፈጣሪ ከዚህ ትዳር መንጭቆ ያወጣህ በአላማ ነው የሀዘን ውሃ ሳይወስድህ መርከብ ሆኖ አስመልጦሀል ደስተኛ መሆን ነው ያለብህ አሁን የወደፊቱን ብቻ አስብ።"ብላኝ ተነስታ ወደ ቤት የሚወስደውን መንገድ መጓዝ ጀመረች እኔም ራመድ ብዬ ተከተልኳት።ወዲያው ግን ተለወጠችብኝ።ሰውነቷ ኤሌክትሪክ እንደያዘው ሰው መንቀጥቀጥ ጀመረ።ወዲያው ተዝለፍልፋ መሬቱ ላይ ወደቀች።ደነገጥኩ! ከአጠገቧ ያለውን ድንጋይ አንስቼ ወደራሷ እስከምትመለስ መጠበቅ ጀመርኩኝ።ከደቂቃ በኋላ በዛው ሞት የመሰለ እንቅልፍ ወሰዳት።እኔም አቅፌ ወደቤት ይዣት በረርኩ።ኳኳ...ኳኳ...ኳኳ...ኳኳ በሩን በሀይል አንኳኳሁ እናቴ ነበረች የከፈተችው እሷም ሶፋው ላይ እንዳስተኛት እየመራች ወደሳሎን አስገባናት እና አሳረፍናት ወንድሜ ከአባቴ ጋር ነበር ሁሉም ተረባረቡባት ከክፍሌ መድሃኒት ላመጣ ስገባ እናቴ ግን በእንባ ጸበል ትረጫታለች።ስመለስ ሁሉም ከቧት በስስት ነበር የሚመለከቷት ይሄን ፍቅር በእድል አየሁት ከመጣች ጊዜ ጀምሮ ሁሉም አይኑን ያሳረፈው እሷ ላይ ነበር ጠዋት ተነስታ ከእማዬ ጋር ቁርስ ታዘጋጃለች ከዛ ሮጣ መጥታ ከእንቅልፍ ቀስቅሳ ጎትታ ፊቴን እንድታጠብ ውሃ ታፈስልኛለች ቃል ሳይወጣት።ስራዋ ግን ከቃል በላይ ሆና የራቀኝ ተስፋ ወደ እኔ ቀርቧል።ተመስገን! እንድል እና ሳልፈልግ ወደ ቤት መግባትን እንድጓጓ አድርጋኛለች።

......አይኗን አሽታ ቀስ ብላ ተነሳች። ስታየን እንባ ተናነቃት እና እናቱን እንደሚፈልግ ህፃን አይኗን እያንከባለለች ሁላችንንም አየችን እራሷን በራሷ ማረጋጋት ጀመረች።"እድል" አልኳት በቀስታ።እሷም ፈገግ ብላ አየችኝ ፈገግታዋ ደህና ነኝ የሚል መልስ ነው።"የኔ ልጅ አስጨነቅሽን እኮ" አለቻት እናቴ ስስ ፀጉሯን እየዳበሰች።
...ከሰአታት በኋላ ምግብ ቀርቦ እየተመገብን ስልኬ አቃጨለ። እድልም መብላቷን አቁማ ጆሮዋን ይዛ ከሆነ ነገር ለመሸሽ ይመስል ፊቷን አዙራ መታገል ጀመረች።ደንግጩ ስልኩን አጠፋሁት።ልዑልም "ምነው እድሌ ይደብርሻል እንዴ ስልክ?" አላት በቀጥታ። እሷም እናቴን ተመለከተቻት።እኔም ምንም ሳልል ስልኬን ይዤ ወጣሁኝ እና ደወልኩላቸው።"ሄሎ"አልኩኝ ስልኩ ሲነሳ።"ሄሎ ዶክተር" አለች ዶክተር ሰገን። ድምጿ እንደ ሆነነ ነገር መላ ሰውነቴን በሚረብሽ ስሜት ነዘረኝ።"ዶክተር ሰገን ደህና አመሸሽ" አልኩኝ። መልሷን ላለመስማት ስልኳን ከጆሮዬ እያራኩኝ። እሷም የምጠላው ሳቋን ለቀቀችው።የሚያስቅ ነገር አወራሁ እንዴ አልኩኝ በልቤ ግን አያስቅም።"ምን ነበር" አልኳት። "እንደሱ አትልም አውቃለሁ ትጠላኛለህ...ይልቅ ዛሬ ተረኛው ዶክተር አባቱ አርፈው አንተ እረፍት ስለሆንክ እንድትሸፍንለት ነው ያው እኔ ቀድሜ ልንገርህ ብዬ ነው" አለችኝ።"አልገባኝም የማን አባት " አልኳት።እሷም እየተሞዘዘች "የዶክተር ብሩክ ነው እና ያው አንተን ተክቶ ነው የሄደው" አለችኝ። ዶክተር ብሩክ ለኔ ልዩ ሰው ነው ብዙ ጊዜ አብረን ሰርተናል እና እንሸፋፈናል በጣምም እወደዋለሁ አባቱ ማረፋቸው በእርግጥ እንደ ሰው ቢያሳዝንም ግን እሱ አባቱን ስለማይወዳቸው የሚከፋው አይመስለኝም ይመስለኛል ለዚህም ነው እኔን ለአንድምሽት እንድሸፍንለት የፈለገው።በማግስቱ እንደሚመጣም እርግጠኛ ነኝ። ብሩክ ከልጅነቱ ጀምሮ በስቃይ እንዳደገ በተደጋጋሚ አጫውቶኛል። ቀልድ አዋቂነቱ የማላውቃትን ዝዋይን ለማየት እንድጓጓ ያደርገኛል። ያደገው ከአያቱ ጋር ሲሆን አባቱ የኔ ልጅ አይደለህም በማለቱ እናቱ ለአባቱ አባት ጥላ ሄደች።የት እንዳለች አያውቅም አትናፍቀውም።ዛሬም የአባቱ መሞት ቢያሳዝነውም ልቡን የሚሰብረው አይመስለኝም ለዚህ ነው ስትነግረኝ ልቤ ያልተሸበረው።"አመሰግናለሁ" ብዬ ስልኩን ዘግቼ ለብሩኬ ደወልኩለት ስልኩ አይነሳም ወዲያው ግን መልዕክት ገባልኝ።"ወንድሜ ዛሬን ሸፍንልኝ ነገ መምጣቴ አይቀርም ቀድሞ ለሞተ ሰው ስራዬን አልበድልም" ብሎ ነበር እኔም "እሺ እግዚአብሔር ያፅናህ" ብዬ መለሼለት ወደ ውስጥ ዘለኩኝ። ስገባ ገበታው ተነስቶ እድል የእናቴ እግር ላይ ተኝታ ቲቪ እያየች ነበር። ምንመ ሳልል ክፍሌ ገብቼ ልብሴን መቀየር ጀመርኩ ግን ደግሞ አንድ ነገር አሳስቦኛል ዶክተር ሰገን ከብሩክ ጋር ነው የምትሰራው ህፃናት ክፍል ከእሷ ጋር ለሊቱ አመት ነው ሆኖ ነው የሚረዝምብኝ እና በሀሳብ እየተብከነከንኩ ወጣሁኝ።.....
💕💕💕ይቀጥላል💕💕💕

ድምፅ ይስጡ!💕💕💕
💞ሰባራ ልቦች💞
በቤዛዊት የሴትልጅ የተፃፈ🍭
💕💕የግጥም መንደር💕💕
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የግጥም መንደር
📖 Sticker
💔💔💔ሰባራ ልቦች💔💔💔

ድምፅ ይስጡ!!
3:00
🌺🌺ሰባራ ልቦች🌺🌺
💔ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ 🇪🇹💖
🍀🍀ክፍል ሰባት🍁🍁
@yebezawit2 🍓

....."ከስራ ደውለው ስለጠሩኝ መሄድ አለብኝ" አልኩኝ የሸሚዜን ኮሌታ እያጠፍኩ።"እንዴ በዚህን ሰአት" እማዬ ከስንት ጊዜ በኋላ እንደዚህ አይነት ጥያቄ ጠየቀችኝ።"ብሩኬ አባቱ አርፈዋል እና እንድሸፍንለት" እማዬ "ውይ ውይ አፈር በበላሁ የኔ ጌታ" አለች። አይ የኔ እናት! ለስኔቱ አፈር ትበይ አልኩኝ በልቤ ከበፊት ጀምሮ ሰው ሲወድቅ ሲታመም ሲመረቅ ሲያገባ ቆንጆ ሲሆን...ብቻ ብዙ ብዙ ምክንያት እየፈለገች አፈር በበላሁ እያለች ደግነቷን በዚህ ትገልፃለች ፍቅሯንም ታንፀባርቃለች።"አይ ብዙም አላዘነም ግን መሄድ አለብኝ" አልኩኝ ሌላ ማብራሪያ ላለመስጠት። እድልም ቀና ብላ በህመም ተመለከተችኝ እና በድንጋሜ የእናቴ እግር ላይ በዝምታ ተኛች እኔም ፀጉሯን ዳበስ አድርጌ" አታስቢ ነገ ከሰአት እመጣለሁ ስመጣ ደግሞ ልዩ ነገር አመጣልሻለሁ" አልኳት። "ደህና እደሩ ችግር ካለ ደውሉልኝ" ብዬ ወጣሁኝ። ልዑል ተከትሎኝ ወጣ።"ወዴት ነህ?" አልኩት ሰአቱ መምሸቱን ለማሳየት ጨረቃዋን እየተመለከትኩ።"ባክህ አንድ በርድ የሆነች ቺክ ጠብሼ ምንም በቃ ትናፍቀኛለች እንዲሁ" አለኝ እጁን ኪሱ ውስጥ እየከተተ። "ጠበስኩ ብለህ እንዳያርብህ" አልኩት አቀበቱን ተያይዘን እየወጣን።" አንተ እኮ ሁሌ እንደ ሽማግሌ ስለምታስብ እንጂ ብትሞክረው..." ዞሬ አፈጠጥኩበት።ደንግጦ ዝም አለ።"ልዑል እባክህ ስለፍቅር ስለሴት ምንም ብትለኝ እኔ ስሜት አይሰጠኝም" አልኩት።መበሳጨቴን እንዲረዳኝ ጮክ ብዬ።"ግን እድል አሪፍ ናት ምን ሆና ነው እንዲህ የሆነችው" አለኝ። እኔም ትንሽ በጥሞና ካሰብኩ በኋላ "አላውቅም ልዑሌ ባስብ ባነብ ብፈልግ መነሻውን የዚህ ሁላ ችግር ጫፍ ላውቀው አልቻልኩም።እሷም እንደምታያት ዝም ማለት ፈገግ አልያም ማልቀስ ነው የእሷ መግባቢያ እና ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላውቅም" አልኩት። "ከባድ ነው ወንድሜ ግን ተስፋ አትቁረጥ አንተ እኮ በከፍተኛ ማዕረግ የተመረክ ምሁር ነህ እና መፍትሄ አለህ" አለኝ። ግን እሱ እንዳለው አይሆንም ምክንያቱም እኔ እስኪገባኝ ድረስ ምሁርነቴ እና ማዕረጌ ለእድል አይሰራም። "በቃ ልዑሌ ራስህን ጠብቅ" ብዬው ወደ ሆስፒታሉ ቅፅር ግቢ ገባሁ እና ህፃናት ክፍል አቀናሁ።መምጣቴን ስትጠብቅ የነበረችው ዶክተር ሰገን ስልኳን መነካካቷን አቁማ በፈገግታ ተቀበለችኝ። የሚገርመኝ ነገር ቢኖር በእጇ ላይ ያለውን የትዳር ቀለበት እንኳን ሰው አይቶ ይታዝበኛል አትልም ስሜቷን በእሷ ቤት አውጥታ በግልፅነት የኖረች ይመስላታል ግን እውነት ለመናገር ግን በሀሳቧ መማገጧ ሞት ነበር ሊፈረድባት የሚገባው። ኮቴን አውልቄ ጋውኔን ለብሼ ከእሷ ጋር ላለመሆን በረንዳው ላይ ወጥቼ ብቻዬን ተቀመጥኩ እና ጨረቃዋ ከደመናው ጋር ስትታገል እየተመለከትኩ ወደ ኋላ ተመለስኩኝ።........

የግቢ ተማሪ ነበርኩ እጅግ የምወዳት ሰምሃል የምትባል የኤሌክትሪክ ኢንጂነሪንግ ተማሪ ነበረች የተዋወቅነው በዩኒቨርስቲያችን ውስጥ በሚካሄደው የግቢ ጉባኤ ላይ ነበር። ድምጿ ስትዘምር ለተመለከታት ከወንዝ ዳር በዜማ እንደሚያጅቡት አእዋፋት ነው ድምጿ ይስረቀረቃል።ግቢ ጉባኤ ላይ እሷ ካልዘመረች ሀሳብ ይይዘኝ ነበር ብቻ አንድ ሁለት ስል ፍቅር ታፍሶ ከማያልቅበት ከፍቅር ቤት ፍቅር ከሆነ አባት ከፈጣሪዬ ልጅ ከሆነችው ከሰምሃል እውነተኛ ፍቅር ያዘኝ። ብዙ ጊዜ ስለምገኝ እና የግቢው ሰቃይ በመሆኔ ለመግባባት ብዙ አልከበደኝም የሚገርመው ሰምሃል ባገኘኋት ቁጥር ይበልጥ ትናፍቀኝ እና አፈቅራት ጀመር።እያየኋት እንደ እህል እራባታለሁ ሳቋ ስትለየኝ ጆሮዬ ላይ ያስተጋባል ልነግራት ፍቅሬን ላወራት ድፍረትን ታጥቄ ስሄድ ግን በፊቷ ፀዳል በጥርሶቿ ብልጭታ በአይኖቿ ነፀብራቅ በውበቷ የድፍረት ትጥቄን አስፈትታ በፍርሃት ታርበደብደኛለች። ሳላገኛት ስውል ስለእሷ ይበልጥ እጨነቃለሁ።የሚገርመው እኔ ዶክተር ብሩክ ዶክተር ዘርዓይ እና አሁን ውጪ ያለው ዶክተር ማርቆስ ምግብ ቢርበኝ ቢከፋኝ ስቄ እሸውዳቸዋለው ሰምሃል ስትናፍቀኝ ግን ከሳቄ ጀርባ ህመሜ ይሰማል እናም ሁሌ እንድነግራት ይገፋፉኝ ነበር እኔ ግን አቅም አጥቼ ከፍቅሯ ሃይል ፈሪ መሆኔን አልተረዱኝም።ሰምሃል እምነቷ ላይ ያላት ፅናት እኔም ፈጣሪዬን እንዳይ አድርጋኛለች። ታዲያ አንድቀን ላገኛት ቀጥሪያት ስንገናኝ ከጓጀኛዋ ጋር መጣች ቢከፋኝም አይኗን ካለማየት ይሻላል ብዬ መከፋቴን አስተባበልኩ። ምግብ በልተን እዛው ግቢ አካባቢ በእግራችን ስንዟዟር ጓደኛዋ "እኔ የምልህ ቀለሜ ሰምሃልን ወደሀታል" ብላ እንደ እርጎ ዝንብ ጣልቃ ገባች። ሰምሃል አፍጣ አየችኝ እኔም በደብዳቤ ፅፌ ኪሴ የነበረውን ወረቀቱን ሰጥቻት ጓደኛዋን በልቤ አመስግኜ ከአጠገባቸው ብን ብዬ ጠፋሁ። ግን ለሊት ላይ ሰምሃል ደወለችልኝ ተአምር ሆነብኝ አንስቼ ሳወራት 'ከዶርም ውጣ' አለችኝ እኔም ትሰድበኝ ይሆን እያልኩ ስወጣ እሷ ግን ተጠመጠመችብኝ እና "የኔ አይናፋር" አለችኝ። በቃ የከበደኝ ነገር በአንድ ጊዜ ቀለለኝ። ምድር ጠበበችኝ የደሴታዬ መፍሰሻ ሆነችልኝ ውበቷ ውበቴ ሆኖ በፍቅር ቆየን። እያበሳጨችኝ እያስቀናችኝ በፍቅር እያሸነፈችኝ ብዙ ውብ ጊዜያትን አሳለፍን እናም ስራ በገባሁ በሁለተኛው ወሬ ነበር ቀለበት አስሬላት ሰርፕራይዝ ያደረኳት።ግን ነገሮች እንደፈለኩት አልሆነም። ለሰርግ ልንዘጋጅ ሽማግሌ ሊላክ አስራ አምስት ቀናት ብቻ ሲቀሩት ያልታሰበ ዱብዕዳ የወረደብኝ። ከጥንቁር አንበሳ ሆስፒታል ወጥቼ ወደ ቤት እየተመለስኩ እጭኛዬ ሰምሃል ደወለችልኝ....

"ሄሎ አክሊሌ" አለችኝ። አክሊሌ ስትለኝ ሰውነቴ የማያውቀው ደስታ ይሰማዋል።
"ወዬ የኔ ፍቅር...ደህና ዋልሽ" አልኳት።መኪናዬን ከቆመበት ለማስነሳት ቁልፉን ተጭኜ እየከፈትኩ።
"ዋልኩልህ.አንተስ ከስራ ወጣህ እንዴ" አለችኝ።
"አዎ አሁን ወደቤት ልገባ መኪናዬ ውስጥ ነኝ አልኳት። ቀበቶዬን እያሰርኩ።
"ከቻልክ ላግኝህ" አለችኝ።
ተበሳጨሁ!!! ምክንያቱም ለእሷ አለመቻል አልችልም የግድ መቻል አለብኝ። ለእሷ ጊዜ አላጣም መኖሬ ይቆማል እንጂ ፍላጎቷን እምቢ አልችልም ብዬ አላሳዝናትም ስታዝን ማየት በጣም ያመኛል። አስታውሳለሁ የመጨረሻ አመት ውጤቷ ተበላሽቶ ቀኑ ሙሉ በደረቴ ላይ ውላ ስታለቅስ የምሆነውን አጥቼ እግሯ ላይ ወድቄ ነበር እንዳታለቅስ ለምኛት አስተማሪውን በገንዘብ ተደራድረን ውጤቱን ያስተካከለው ከዛ በኋላ እሷም ታውቃለች ስታለቅስ ልቤ እንደሚጎዳ ተርዳታ ቢከፋት እራሱ ስትነግረኝ ላለማልቀስ እየታገለች ነው።
"ላንቺ የማልችለው የለም እመጣለሁ ማሬ እንዳውም ናፍቀሽኛል ያለሽበትን ላኪልኝ" አልኳትና ስልኬን ዘጋሁት።
ያለችኝ ቦታ ስሄድ ግን አይኖቼ ያዩትን ማመን ከበደኝ ጉልበቴ ሲብረከረክ ወንድነቴ ከእኔ ሲሸሽ ታወቀኝ የያዝኩትን አበባ ጨምደድ አድርጌ ቆሜ ቀረሁኝ።
💖💖💖ክፍል ስምንት ይቀጥላል💖💖💖

🍀ታሪኩ እንዲቀጥል ድምፅ👍 መስጠት አትርሱ🌺
🍓🍓ሰባራ ልቦች💔💔
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
You Are The Reason
Calum Scott
@yebezigetmoch
🍓🍓🍓🍓 @yebezawit2 🍓🍓🍓
🇪🇹🍀🇪🇹🍀🇪🇹🍀
ዛሬ ተሰጥቶናል ነገ ሚስጥር ነው ትላንት አልፏል

የበደሉንን የበደልናቸውን ይቅር ማለት እና ይቅርታ መጠየቅ #ክብር ትህትና እና እረፍት ነው!!
ዛሬ እስኪ ራሳችንን እናድምጥ እና ያሳዘነውን ሰው ይቅርታ ጠየቀን አዲስ አመትን በምህረት እና በይቅርታ እንጀምር💖🙏🙏🙏
ይቅርታ ያለፈውን ነገር ባይመልስም ወደፊቱን ብሩህ ያደርጋል እና ዛሬ አሁን ጀምሩ በቴክስት በመደወል ይቅርታ ይበሉ!

ይቅርታንም ይቀበሉ!

ወንድሜ እህቴ ይህን መልዕክት ለሚፈልጉት ላኩ💖💖💖" እውነት አንድ ናት" በእውነት ከልብ ይቅርታን ይጠይቁ!

አንተም አንቺም ይቅርታውን ከተቀበላችሁ መልሰው ይህን ይላኩ "ይቅርታ ድልድይ ነው መገናኛ መንገድ" ከአንተ ከአንቺ የሚበልጥ ስህተት የለም እና ትላንት አልፏል በማለት ፍቅር እንደ አዲስ ዝሩ!

ፍቅር ያሸንፋል
🇪🇹አንድ ኢትዮጵያ🇪🇹
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
Forwarded from መቃን ዲጂታል መጽሔት (👑Bezi Ye Raguel Lij👑)
ይቅርታን ልቀምም

እቴ እኔ እና አንቺ ሆነን አንድ ላይ
ምድር ጠባኝ አንሶኝ ነበር ሰማይ
ታውቂያለሽ ስወድሽ ዘመንን ነጉዷል
ራሴን አግኝቻለሁ እኔ ከአንቺ ስውል

ግን ታዲያ ብዙ ሳልቆይ ደስታ ሲበዛ
መንከባከብ ትቼ ብጠፋ እንደ ጤዛ
እንዴት ልመለስ አይደል በደሌ የዋዛ

ፈዘዝኩና እንዲያው ፍቅርሽን ገፍቼ
ርቄም ላልደሰት ላልኖር ረክቼ
በአንደበቴ አራኩሽ
ቃሌ ከጉያዬ ወሰደሽ

ከእቅፍሽ ስወጣ ልብሽም ሲያዝንብኝ
ከምንም በላይ ብርዱ ነው የጎዳኝ
አይበርድሽ ብዬ አቅፌሽ ታይቻለሁ
አንቺ ሳትሞቂ እኔ ግን ሞቂያለሁ
በፍቅርሽ ወላፈን ራሴን ስቻለሁ

ሴት ሲሉ እንዲያው በጨዋታ
አይታየኝ ካንቺ ሌላ ሴት ሁሉን የምትረታ።

ይሄን ዘንግቼ ርቄ ሄጃለሁ
እኔ ተጎድቼ እኔው ታምሚያለሁ
አልጋ ቢቀረኝም በቁሜ ተኝቻለሁ።

ግን አለ መላው ከእጄ ነው
ልብሽን ድንገት ገርበብ ካደረገው
ሰብስቤ በደሌን ሳልሰቀር ሁሉንም
ፍቅርሽ እንዳገኝ ይቅርታን ልቀምም!!

ቤዛዊት የሴትልጅ

💖💖ለሚወዱት ሰው ይቅርታን ይጠይቁ💖💖
🙏ይቅርታ ያለፈውን ጊዜ ባይለውጥም የወደፊቱን ግን ብሩህ ያደርጋል🙏

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
በብራና ዘመን ቀለምን ቀምመን
እንዘርፋለን ቅኔ ለፍቅር የሚሆን።


#ቅኔ_እና_ጦቢያ

#በብራና_ዘመን_ለምን_ተላለፍነ!!

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

ያግኙን፦ለሀሳብ አስተያየት
👉 @poet_amanbot
👉 @aman0777
💕💕💕ሰባራ ልቦች💕💕💕

ክፍል ስምንት🍀💖💖
ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ*

.....ሰምሃል ከምወደው ጓደኛዬ ከዶክተር ማርቆስ ጋር በፍቅር ጣቶቻቸው ተጠላልፈው አፍለአፍ ገጥመው ነበር።እብድ ሆኜ ፊቴን አዙሬ ከሆቴሉ ወጣሁኝ።በቃ ከዛ በኋላ ነገሮች ተመሰቃቀሉ እሷም ማርክን አግብታ ለሰርጓ ጠራችኝ ለስሜቴ የምትጠነቀው ሰምሃል እንደ ቀልድ ጋበዘችኝ ጎትቼ አልመልሳት ነገር ፍቅር ሃይል አይጠቀመም ለምን እንዳገባችው እኔ ምን እንዳጎደልኩባት ሳላውቅ እና ሳይገባኝ አሳልፌ ሰጠኋት። ምስኪን እኔ! ፍቅር ከቶ አይወድቅም ብዬ አምን ነበር ግን የኔ ፍቅር እንደ ረከሰ ነገር ተቆጥሮ ዋጋውም ጥንቡን ጥሎ ወድቆ ተሰባብሯል።ወደቀ ተሰበረ....ሰምሃል ዛሬም ድረስ ትታወሸኛለች ስለእሷ አላስብም ብዬ ለራሴ ቃል ስገባ ይበልጥ ትናፍቀኝ እና ስጨነቅ እውላለሁ።ቤተሰቦቼ ሰርጌን ለማየት ናፍቀው ቀርተዋል።የእናት የአባቴ "ልጄ ሊያገባ ነው" የሚል ኩራት ተቀብሯል።አሁን ላይ ብቻዬን ነኝ ብቻዬን! .....

........እንደምንም ከነበርኩበት ሀሳብ ወጣሁኝ እና እጄን ኪሴ ውስጥ ከትቼ ወደ ውስጥ ተመልሼ ገባሁኝ።....መንጋት አይቀርም እና የንጋቱ ብስራት በከተማው የመኪናዎች ድምፅ ተበስሯል።ዛሬን አያደርገው እና በአእዋፋት ዜማ ነበር ንጋት የሚበሰረው። እኔም መንጋቱን አይቼ ዶክተር ሰገንን ምንም ሳልል ወጣሁኝ እና ወደተመደብኩበት ዋርድ ተመለስኩኝ።...ስልኬን አውጥቼ ወደ ቤት ደወልኩኝ።ስልኩ ጠራ...ደገመ.....የሚያነሳው የለም...መልሼ ደወልኩኝ.....አሁንም በስልኩ ውስጥ የእናቴ ድምፅ ብጠብቅም ልሰማው አልቻልኩም። ልቤ ተሸበረ ለወንድሜ ለልዑል ደወልኩት

"ሄሎ ዶክተሩ ወንድሜ" አለኝ። በትንሹ ጭንቀቴ ቀለል አለ።

"ደህና አደርክ አንተ ጅል" አልኩኝ ፊቴን ከቧንቧው በሚወርደው ውሃ እየዳበስኩ።

"ያውም..." ወሬውን ስለማውቀው አቋረጥኩት እና
"እቤት ስደውል ስልኩን አያነሱም የተፈጠረ ነገር ካለ ብዬ ነው" አልኩት

"ኧረ ምንም የለም ወንድሜ ምን አልባት አልተነሱም ይሆናል ቆይተህ ደውልላቸው።" ብሎ አረጋጋኝ። እኔም እሺ ብዬ ስልኩን ዘጋሁት እና ሰአት ቆጠራ ጀመርኩኝ።
ሰራዬን ሰርቼ በሰአቴ ቦርሳዬን ይዤ ወደ ቤት የሚወስደውን መንገድ ብቻዬን ማዝገም ጀመርኩኝ። ቀኑ ሙሉ ከቤት ስልክ ስላልተደወለልኝ እና ስደውልም ሳልተመለሰልኝ ሀሳብ ገብቶኛል።የግቢውን በር በቁልፍ ከፍቼ ገባሁኝ ስገባ ግን ያየሁት ነገር የዘቀዘችብኝ ፀሀይ ዳግም የፈነጠቀች ያህል ሰምሃል ብትመለስ አልያም ያየሁት ነገር ውሸት ቢሆን የሚሰማኝ ስሜት ብዬ የማስበው ሲሰማኝ ታወቀኝ። በሆነው ሁሉ የማማርረው አምላኬ ድንቅ እንዳደረግልኝ ተሰማኝ ሰምሃል ከእኔ ጋር እያለች አንድ ሆኜ ብዙ ነበርኩ አሁን ላይ ግን ለአንድ ራሴ መሆን አቅቶኝ ያለህመም ፈገግ ብዬ አላውቅም።....ቤቱ በእጣኑ ጭስ ሞልቶ ቡና እየተፈላ ነበር ፈንዲሻው ፈክቶ ለቡናው ሌላ ድምቀት ሆኖታል። ይበልጥ የደነቀኝ ቡና የምታፈላው እድል መሆኗ ነበር ቆሜ ቀረሁኝ መደንገጥ መደመሜ ፊቴ ላይ ያነበበችው እናቴም ፈገግ ብላ አየችኝና "ደህና መጣህ ልጄ" ብላ እንባዬን እንደ ዶፍ እንድለቀው አስገደደችኝ ምን አልባት እንዲህ ስሆን ላየኝ ማካበድ ሊመስል ይችላል ግን አይደለም! የሚወዱትን ማጣት ጉድለት ብቻ አይደለም የመቃብር ኑሮ እንጂ አሁን ግን መቃብሩ ተከፍቶለት በህይወት እንደ ወጣ ሰው ነው ደስታዬ የበዛው እናቴ በፍቅር ጠርታኝ ሰላሜን ጠየቀች።ምንም ሳልመልስ ወደ ክፍሌ ሮጬ ገብቼ በሩን ዘግቼ ተንሰቅስቄ አለቀስኩኝ። ሲጢጥጥ ብሎ በሩ ተከፈተ እድል ናት ከንፈሯን ሸሸት አድርጋ በጥርሶቿ ብልጭታ ቀልቤን ገዝታ እንዳያት አስገደደችኝ። ጠጋ ብላ እጄን ይዛ አይኗን ጨፈን አድርጋ ገለጠች በርታ የምትለኝ ያህል ተሰማኝ እኔም መልሼ አይኔን ጨፈን አድርጌ ገለጥኩት እሷም ጥርሶቿን ሳትሸሽጋቸው ተመልሳ ወጣች። ልብሴን ቀይሬ እየፈራሁ ወደ ሳሎን ገብቼ ተቀላቀልኩኝ እና ፈንዲሻውን ዘግኜ መብላት ጀመርኩ ብዙም ሳይቆይ ወንድሜ ልዑል መጣ።ቤታችን ደስ የሚል ድባብ ኖረው እኛ ስንስቅ ስንጫወት የእድል ድምፅ ግን ከራሷም አልፎ አይሰማምነበር በአንድ ጎን የእሷን የዝምታ ምክንያት እያሰላሰልኩ ምግብ በልተን ተጫውተን ለመኝታ ወደየ ክፍላችን ገባን አልጋዬ ላይ ጋደም ብዬ ደጋግሜ ባነበው የማይሰለቸኝን የበአሉ ግርማ መፅሐፍ የሆነውን ኦሮማይን እንደ መዝሙረ ዳዊት እየደገምኩ ሰምሃልን እና እድልን ሳልፈልግ ማነፃፀር ጀመርኩ።ደግሞ ተመልሼ አእምሮዬን ራሴ ተቆጥቼ ንባቤን እቀጥላለሁ።...."ግን ምን ሆና ነው...ማነው እንዲህ የጎዳት....እድል ማናት?.." አእምሮዬ በጥያቄ ተሞልቶ ንባቤን አመሰቃቀለው እና መፅሀፉን ዘግቼ በመስኮቴ በኩል ወደ ማዶ አሻግሬ እያየሁ ቆምኩኝ ከሩቅ ሆነው የሚያበሩት የከተማዋ መብራቶች ቀልቤን ወስደውት ለሰአታት ያህል ፈዝዤ ቀረሁ እናም መለስ ብዬ ወደ ግቢያችን ቁልቁል ስመለከት ግን እድልን አየኋት ክው ብዬ ቀረሁ...

ይቀጥላል....

ቀጣይ ክፍል እንዲለቀቅ
ድምፅ መስጠት አትርሱ!
💞💞💞💞💕💕💕💕💕💕

@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
🥀ማንነትህን በተሻለ ማንነት መቀየር በጣም ከባድ ነው
ችለህ አንዴ ከቀየርከው ግን በህይወትህ ከወሰንካቸው
ሁሉ ምርጡ እንደሆነ ትገነዘባለህ🥀



📩Admin @yebezawit2
ከፍቅር
🌻🌻ፍቅር🌻🌻🌻በፍቅርስለፍቅር😍😍😍ከፍቅር
ፍቅርደስ ይላል...ይሄን ደስታህን ላለማጣት ተንከባከበው💕💕💕 ከአምላክ ነውና የተሰጠህ አመስግን😍😍😍 የዛኔ ህይወት በራሷ ልዩ ጣዕም ይኖራታል💖💖💖
💞💞ፈጣሪ የምትወዱት ይስጣችሁ🙏🙏🙏

🌻🌻🌻መልካም አዲስ አመት🌻🌻🌻
ቤዛዊት የሴትልጅ
💞💞ፍቅር💞💞💞

ፈጣሪ ንፁህ ፍቅር እና ልቦና ይስጣችሁ!

🌻🌻እሰይ እሰይ መጣ አውዳመቱ🌻🌻
🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼

  🌻
🌻🌻🌻
  🌻🌻🌻🌻
🌻🌻 🌻🌻
🌻🌻 🌻🌻
  🌻🌻🌻🌻🌻🌻
  🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌻 🌻🌻
🌻🌻 🌻🌻
🌻🌻 🌻🌻

🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌻 🌻🌻
🌻🌻 🌻🌻
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌻
🌻🌻
🌻🌻
🌻🌻

🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌻 🌻🌻
🌻🌻 🌻🌻
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌻
🌻🌻
🌻🌻
🌻🌻

🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼
🌼🌼
🌼🌼
🌼🌼
🌼🌼


🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼   🌼🌼
🌼🌼🌼🌼 🌼🌼
🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼
🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼
🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼
🌼🌼 🌼🌼 🌼🌼
🌼🌼 🌼🌼🌼🌼
🌼🌼 🌼🌼🌼
🌼🌼 🌼🌼

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼
🌼🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼
🌼🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

🌻🌻 🌻🌻
🌻🌻 🌻🌻
🌻🌻 🌻🌻
🌻🌻 🌻🌻
🌻🌻 🌻 🌻🌻
🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻
🌻🌻 🌻🌻🌻 🌻🌻
🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻 🌻🌻
🌻🌻🌻🌻 🌻🌻🌻🌻
🌻🌻🌻 🌻🌻🌻


🌻🌻🌻🌻
🌻🌻🌻🌻
🌻🌻🌻🌻
🌻🌻🌻🌻
🌻🌻🌻
🌻🌻
🌻🌻
🌻🌻
🌻🌻
🌻🌻

🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌻
🌻🌻
🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌻
🌻🌻
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

  🌼
🌼🌼🌼
  🌼🌼🌼🌼
🌼🌼 🌼🌼
🌼🌼 🌼🌼
  🌼🌼🌼🌼🌼🌼
  🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼 🌼🌼
🌼🌼 🌼🌼
🌼🌼 🌼🌼

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼 🌼🌼
🌼🌼 🌼🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼 🌼🌼
🌼🌼 🌼🌼
🌼🌼 🌼🌼
🌼🌼 🌼🌼


@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
💖💖መልካም ልደት💖💖ውዷ እናቴ


🌻🌻የኔ #አውዳመት የኔ ስጦታ የመኖሬ ምክንያት የህይወቴ ብርታት አንቺ የኔ እናት በመሆንሽ ምን ያህል ታደልኩኝ?እኔን ልታኖሪ መኖርማቆምሽን ሳስብ ልቤ በፍቅርሽ ይወድቃልስነ ስርአትን ፈሪሃ እግዚአብሔርን የተማርኩብሽ አፍ መፍቻዬ ነሽ💕💕 እራሴን ሌሎች ጋር ስፈልግ አጣዋለው አንቺ ውስጥ ግን ራሴን አገኘዋለሁ መኖርሽ ለኔ ምግቤ ነው 😘😘ፈገግታሽ ደግሞ ነፀብራቄ 💞💞ሁሌም ሳቂልኝ 😂😂ሁሌም አብሪልኝ😍😍😍 የኔ #ኮከብ እወድሻለሁ 💕💕💕 መልካም ልደት የኔ እናት 🔥🔥🔥 የምትወጃት ተአምረኛዋ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በፀጋ በበረከት እና በጤና በሰላም ታኑርሽ!🙌 ሁሌም አባት ቤተሰብ ሆኖ የሚጠብቀን የሚያኖር ቸር አባት አማኑኤል በፍቅር ጥላ ስር በሰላሙ ያኑርሽ!💞 የቅዱሳን አምላክ እርሱ ረጅም ዕድሜ እና ጤና ይስጥሽ የኔ #ጀግና ሴት 🍀🍀🙏🙏 ስለአንቺ ምንም ማለት እንደማልችል ታውቂያለሽ በቃ እርሱ ዘመንሽን ይባርከው...ከፍቶሽ እንዳላይ💞መልካም ልደት
💟💟💟🍰🍰🍰🍩🍩🍩🍮🍮🍮🍯🍟🍟🍬🍬🍬🍬🍬🍬🍬🍬🍬🍬🍬🍬

የአንቺ መሆኔ መታደሌ
💕💕ቤዛዊት የሴትልጅ💕💕💕
መስከረም አንድ 🌻🌻🌻🍰
🍩አዲስ አመት + የጀግናዋ ሴት ልደት = የብርሃን አመት🔥🔥💟
የኔ 🌍 በአንቺ ህይወቴ ሞላ ሀዘኔ ተነነ ደስታዬ በዛ
በአንቺ ሁሉ አለኝ ደስደስ
እንግዳ ሆንኩኝ ለአለም እንደ አዲስ😍😍
💟መልካም ልደት💟 የኔ ውበት እናቴ🍰🍰🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂ነፍ አመት በፀጋው ኑሪልኝ!አማኑኤል አባቴ ይጠብቅሽ🌍 የአንቺ ልጅ በመሆኔ እኮራለሁ!💕💕💕💕🍯🍯🍯
#ስሜ ነሽ 😍😍😍😍
🎂🎂🎂happy birthday 🎂🎂🎂
ዛሬውኑ የሚቀጥለውን ዓመት ግብህን ግልጽ አድርግ!

ነገ ወደ አዲስ አመት ከመግባትህ በፊት አንድ ነገር ላስታውስህ፡- በሚቀጥለው ዓመት ያለህን ግብ በሚገባ ሳታውቅ ወደ አዲስ አመት መግባት ማለት እጅግ አክሳሪ ጉዳይ ነው፡፡ ግብህን ግልጽ አድርገህ ያልጀመርከው ነገር ብዙ ከሄድክ በኋላ እንደገና እንድትመለስና ብዙ ከጠመጠምክ በኋላ እንደገና እንድትፈታ ያደርግሃል፡፡

ዓልመህ ተነሳ እንጂ ዓላማህን እግረ-መንገድህን እየፈጠርከው አትሂድ፡፡ የምትደርስበትን ሁኔታ ቀድመህ አይተህ ተነሳ እንጂ የደረስክበት ቦታ ደስ ስላለህ ብቻ ዓላማህ እንደሆነ አድርገህ አትቀበለው፡፡ ግብህን አውቀህ ደስ ብሎህ ተነሳ እንጂ አንድ ደስ የሚል ነገር እስከሚያጋጥምህ ድረስ እያዘገምክ አትሂድ፡፡ የውስጥ ደስታህንና እርካታህን በየእለቱ ከሚገጥምህ ገጠመኝ ጋር አታገናኘው፡፡ በዚያ ምትክ ዓላማን በማወቅ፣ ግብን በማውጣትና እዚያ ጥግ ለመድረስ ጉዞን በመጀመርህ ምክንያት ደስተኛ ሁን፡፡ ከዚያም ጉዞህን ቀጥል፡፡

ወደ የት መሄድና መድረስ እንደሚፈልግ የማያውቅ ሰው ያለበትን ደረጃ እያየ ከማዘን ያለፈ ነገር ማድረግን በፍጹም አይችልም፡፡ ሃዘንና ለራስ ከንፈርን መምጠጥ ማንንም የትም አድርሶ ስለማያውቅ፣ የት መድረስ እንደምትፈልግ ግልጽ የሆነ ንድፍ ሊኖርህ ይገባል፡፡ ያንን ካደረግህ በኋላ የሚቀጥለውን አመት ግህን አስመልክቶ ያለህ እቅድ መቼ ተከናውኖ ማየት እንደምትፈልግ የጊዜን ገደብ በግልጽ ማስቀመጥ ተገቢ ነው፡፡ የቀን ገደብ ወይም ቀጠሮ ያላስቀመጥክለት ነገር የመከናወኑ ነገር አጠራጣሪ ነው፡፡

የቀን ገደብ ማውጣት መነሳሳትን በውስጥህ ከመፍጠሩ ባሻገር የግምገማ ነጥብን እንድታስቀምጥ ይረዳሃል፡፡ ይህ መነሳሳት በየቀኑ፣ በየሳምንቱ፣ በየወሩና በየዓመቱ፣ ማከናወን ያለብህን ነገሮች እንድታስብ ይጋብዝሃል፡፡ ይህንን ከግብ አንጻር የሆነ መነሳሳት ይዘህ ስትራመድ አንዳንድ ጊዜ አቅምህ አናሳ እንደሆነ ማየትህ የማይቀር ነው፡፡ ንድፍህን እንዴት ተግባራዊ ለማድረግ እንደምትችል ማሰብ የምትጀምረው ያን ጊዜ ነው፡፡ ምናልባት ራስህን ማሻሻል የሚያስፈልግህን ሁኔታ ትደርስበት ይሆናል፡፡ ምናልባትም ደግሞ ድጋፍ ሊሰጥህ የሚችልን ሰው ማሰብና ማነጋገር ሊኖርብህ ይችላል፡፡

ግብ ማለት መጨረሻ ላይ ስኬታማ እንደሆንን የምናውቅበትና ለማየት የምንፈልገው ስእል ሲሆን፣ እቅድ ማለት እዚያ ግብ ለመድረስ መውሰድ የሚገቡን እርምጃዎች ጥርት ባለ መልኩ ሲቀመጡና ስናያቸው ማለት ነው፡፡ ተግባር ማለት ደግሞ ያንን ለመውሰድ የወሰንነውን እርምጃ ተግባራዊ የምናደርግባቸው ጥቃቅን እንቅስቃሴዎች ናቸው፡፡ ስለዚህም፣ ግብን፣ እቅድንና የየእለት ተግባርን ስኬታማ በሆነ መልኩ በመያዝ በገንዘብ መበልጸግን ከፈለክ በግብ አወጣጥ ዘዴ፣ ግቡን ተግባራዊ ለማድረግ እቅድን በማውጣት ብልሃትና የተግባር ሰው በመሆን ቆራጥነት ማደግ የግድ ነው፡፡ ፍላጎትህ ምኞት ሆኖ እንዳይቀር ግብን አውጣ፡፡ ግብህ ከንቱ ሆኖ እንዳይቀር ግልጽ የሆነና ቀን ገደብ ያለው የእንቅስቃሴ እቅድ አውጣ፡፡ እቅድህ ከንቱ እንዳይሆን ደግሞ መተግበር ጀምር፡፡ ይህንን መስመር መከተል ስትጀምር ብዙም ሳትቆይ የስኬትን ጣእም ማጣጣም ትጀምራለህ፡፡

🌼🌼መልካም አዲስ ዓመት🌼🌼
2025/07/04 22:56:24
Back to Top
HTML Embed Code: