Telegram Web Link
አስረሽ ፍቺኝ

መመለስ አልችልም ፈርቼሻለሁ
ጠልተሽኝ ይሆን ብዬ አስባለሁ
አዎ ራሴን ፍለጋ ጠፍቻለሁ
ያለአንቺ ራሴን አጥቻለሁ
አሁን ግን ሲገባኝ ሲፈታልኝ ቅኔው
ከልብሽ ልመለስ ብዬ ፈራው
እውነት ግን ጠልተሽኛል..?ጨክነሽ
የኔን መጎዳት እንዴት ላሳይሽ
ደራሲው ገጣሚ ዜመኛው
ተዋናዩ ጋዜጠኛ ሰአሊው
ከሚሉት በላይ እኔ ታምሚያለሁ
መድሃኒቴን እንዳላገኝ ፈርቻለሁ
ያጣሁሽ እየመሰለኝ በራሴ አዝናለሁ
ታዲያ ለዚህ ሁሉ በደሌ እና ፍርሃቴ
አንቺን ገፍቼ ራሴን በመፈለግ ሀጥያቴ
ንስሃ ያለው ከልብሽ ነውና እቴ
ኑዛዜዬን ስሚ ከልቤ ውስጥ ያለውን
አንቺን እርቄ የቀኑ ሳያንስ አጥቻለሁ ለሊቴን
ማለዳ ስነሳ ገና ከአልጋዬ ሳልወርድ
ወደ አንቺ ያመጣኛል የናፍቆት መንገድ
ራስህን ፈልግ ብዬ ልቤን ስገፅፀው
መልሶ መላልሶ ይመጣል ከአንቺው
ከጨረቃም ጋር ራሴን ልፈልግ ስኳትን
ልክ እንደጨረስኩ የሀሳብ ዳገት አቀበቱን
ማረፊያዬ አንቺ ጋር ይሆናል ስለአንቺ መደነቅ
ስለውበትሽ ስለ ንፅህናሽ ማድነቅ
ምኑን ልንገርሽ መልሱ አንድ ነው
ራሴን ስፈልግ ራሴን አጥቻለው
አንቺን አርቄ ማንነቴ መሆንሽን ረስቻለው
ግን ውዴ ልብሽ ምንም ቢጨክንም
እሺ በይኝ ከአንቺ አልራቅ ግድየለም
ከባህር የወጣ አሳ አልሁን ማሪኝ
ፈተሽ እንዳሰርሽኝ አስረሽ ፍቺኝ።

09/10/2012(03:43pm)
ፃፍኩት እኔ ቤዛዊት የሴትልጅ
"...በቃል መጠላት ይቻላል፤ በቃል መወደድ ይቻላል ፤ በቃል ማሸነፍ ይቻላል ፤ በቃል መሸነፍ ይቻላል። በቃል ሁሉንም ማድረግ ይቻላል። በቃል ሁሉንም መሆን ይቻላል። የሁሉም ነገር ቁልፍ ቃል ነው። ልዩነቱ፣ ቁልፉ ለበጎም ለክፉም መዋሉ ነው።...ከአፋችን የሚወጡ ቃላት ትሩፋቶች ነን። ከአፋችን በሚወጡ ቃላት ጥፊ ሊያስልሱን ወይም ግርማ ሞገስ ሊያላብሱን ይችላሉ።...።


..ቃል ውድ ሀብት ነው። ክቡር ድንጋይ(ORE) ነው።"

📖ክቡር ድንጋይ
"ጨለማ ፀጥታ ነው። ጨለማ ሰላም ነው። ትኩረትህን የሚስብ ምንም የምታየው ውጫዊ ነገር የለም። የምታየው ነገር ቢኖር የውስጥክን አንተነትክን ነው። በብርሀን ሌሎችን እናያለን፣ በጨለማ ግን ራሳችንን እናያለን። ለሰው ራሱን እንደማየትና እንደማወቅ ያለ ኃይል የለውም። ጨለማ ደግሞ ይህን ኃይል ያጎናፅፍሀል።"
📖እመጓ
@yebezigetmoch
🍇🍇🍇🍇🍇🍇💞💞💞💞💞💞
ህይወት እንዲህ ናት.....በፈለገችበት እንጂ በፈለክበት መንገድ አትወስድህም.....አንተም ከመታገል ይልቅ #ወደህ ተቀበል....ምርጫ የለህም! ህይወት መንገዱን ስትስጥህ አንተ ደግሞ ዙሪያዋን በውብ አበቦች አስጊጥ ያኔ ያማረ መንገድህ አይሰለችህም

🥀💐🥀 ቤዚ የራጉኤል ልጅ
💐💐💐ሰላም ለእናንተ ይሁን🙏🙏🙏

የግጥም መንደር ቤተሰቦች እንደምን ከርማችኋል
❤️ሰባራ ልቦች የሚለውን ድረስቴን ከነገ ከ ምሽቱ 1:00 ጀምሮ የማቀርብ መሆኑን ለመግለጽ እወዳለሁ
💘ሰባራ ልቦች💔

#እንዳያመልጣችሁ!!!
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
ማሳሰቢያ

የምክር አገልግሎት በምስጠበት እንዲሁም አስተያየት በምቀበልበት አድራሻ
ስለሐይማኖት
ስለዘርኝነት
ፀያፍ ንግግሮችን መላክ አጥብቆ የተከለከለ ነው‼️‼️
📵ለነዚህ ጉዳዮች መደወልም አይቻልም❗️

📨📨የምክር ድጋፍ📨📨 ለምትፈልጉ ወዳጆቼ ግን 📥 እቀበላለሁ
📝አስተያየት ለመስጠት ለምትፈልጉም

@yebezawit2 ይጠቀሙ🖋

🖍ቤዚ የራጉኤል ልጅ(የሴት ልጅ) 🖍
📌 @yebezigetmoch
📌 @yebezigetmoch
📌 @yebezigetmoch
🌟🌟ሰባራ ልቦች🌟🌟
👀
👃 ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ 👀
👄 👃
👄
💓💓ክፍል አንድ💓💓

"ዶክተር ዶክተር" የሲስተር ዳና ድምፅ ነበር። ከሆስፒታሉ እየወጣሁ ነበር እና ቆም ብዬ ጠበኳት"በቃ ከዚህ በኋላ እኛ ጋር አትሰራም ማለት ነው?" የጠራችኝ ለዚህ መሆኑ ቢያበሳጨኝም ፈገግ ብዬ "አንድ ግቢ ውስጥ እኮ ነን እንገናኛለን" አልኳት። የኔን ከህፃናት ዋርድ መውጣት እንደ ትልቅ ነገር ቆጥራው። "እቸኩላለሁ" በቆመችበት ጥያት ወጥቼ ከሆስፒታሉ ወደ ሽሮሜዳ የሚወስደው ቁልቁለት ይዤ መራመድ ጀመርኩ። ከነገዋ ዕለት ጀምሮ የአእምሮ ህሙማን ክፍል ነው የምሰራው ጨንቆኛል ፍርሃት ውስጤ አድሯል.......ሰው ራሱን ሳያድን እንዴት ሌላውን ያድናል ብቻ ፀበልም ቢሆን እየሰጠኋቸው አምላኬን ብማፀን ይሻለኛል። ሀሳቤ እንደ ባህር ሰፍቶ እንደ ውቅያኖስ ጥልቅ ሆኖ ከቤተሰቦቼ ቤት ደረስኩ። ከኪሴ የግቢውን በር ቁልፍ አውጥቼ ከፍቼ ገባሁ። በረንዳው ላይ እናቴ አባቴ እና እንደመስቀል ወፍ ባሻው ጊዜ ብቅ የሚለው ወንድሜ ተቀምጠው ቡና እየጠጡ ነበር። "ደህና ዋላችሁ" መልሳቸውን ሳልጠብቅ ወደ ክፍሌ ገባሁኝ። ምክንያቱም ቆሜ እህ ብዬ እነሱን መስማት ከጀመርኩ አግባ ውለድ መኪና ያዝ ብዙ ብዙ ትዕዛዝ ያዘንቡብኝ እና ያልሻረውን ቁስለቴን ይነካኩታል.....ያሳምሙኛል....ሰባራ ልቤን ከተኛበት ቀስቅሰው በትላንት ትዝታ እንዲሰቃይ እንዲያለቅስ ያደርጉታል.....ለዚህም ብዙም አልቀርባቸውም ብዙም አልርቃቸውም በልኩ! በመስመሩ!...የድሮ ህይወታችን ግን ሌላ ገፅ ነበረው ደስታ ሳቅ ጨዋታ ከእኛ ቤት ጠፍቶ አያውቅም የሳቃችን ድምፅ ጣሪያውን እስኪሰነጥቅ ነበር የምናሽካካው በተለይ ልክ እንደዚህ ክረምት ሲገባ በረንዳው ላይ ቡና ይፈላል በቆሎ ይቆላል ከዛም በጨዋታ ታጅቦ መከካት ነበር። ያ ጊዜ እያልኩ ላለማውራት ሞክሬ ብዙ ጣርኩኝ ግን ህመሜን መርሳት የማላውቀውን ሰው እንደማስታወስ ከበደኝ ከራሴም ከአለምም እርቄ ብቸኛ መሆን መርጫለሁ። ለካ ብቸኝነት ሰላም ነው....ነፃነት....ግልፅነት....እውነት ያለው ብቸኝነት ውስጥ። ሌላ ቦታ ግን በማስመሰል ቅብ የተለበጠ ተራ ነገር ነው። የመኝታ ቤቱን በር ገርበብ አድርጌ ከአልጋዬ ጫፍ ከመቀመጤ ወንድሜ መጣ "አንተ ልጅ ግን በቃ እንደዚህ ሆነህ እስከ መቼ ልትኖር ነው" በሀዘኔታ አይን ቁልቁል ተመለከተኝ።"ውይ ዳግም እስኪ ተወኝ ደክሞኛል" አልኩት ከምክሮቹ ለመሸሽ። "አውቃለሁ ልዑሌ አንተ ለሌሎች ጀግና እና ጠንካራ ሀኪም ነህ ለራስህስ መቼ ነው የምትኖረው መቼ ነው ከዚህ ማንነትህ ተለያይተህ ያን ተጫዋች እና ፍልቅልቁን ልዑልን የምትሆነው እማዬ አታሳዝንህም አባዬስ..." ረጅም ምኩሩን አቋርጬ ከክፍሌ ተነስቼ ወጣሁኝ። ተከትሎኝ መጣ። "ውይ እስኪ ተወኝ" አልኩት እና ውሃ በብርጭቆ ይዤ ወደ ክፍሌ ተመለስኩ እና አልጋዬ ላይ ተዘረርኩ። "ወይኔ ልዑል ሰው መሆን ያቅተኝ" አልኩኝ። ሰባራ ማንነቴ አበሳጭቶኝ። ከአድማሱ ባሸገር የተሰወረች ፀሀይ ለምድር ጨለማ ትታለች። እነ እማዬ ወደ ቤት ገብተው እያወሩ ነበር። ስልኬ ጠራ ዶክተር አሊ ነበር አብሮ አደጌ መካሪዬ እና ወዳጄ ነው በጣም ነው የምወደው አስረኛ ክፍል እያለን ነበር ቤተሰቦቹ በመኪና አደጋ ያጣቸው ከዛ በኋላ እኛ ቤት ነው ያደገው ሰርጉንም ቢሆን እናቴ ነበረች የደገሰችወ።አስታውሳለሁ አሊ ካገባ በሶስተኛው ወር ነው እኔን የልብ ስብራት የገጠመኝ።"አሊሾ" አልኩኝ ስልኩን አንስቼ።"የት ነህ?!" ሰላምታ ሳይሰጠኝ ጠየቀኝ።"እቤት ነኝ ያው ከነገ ጀምሮ አብረን ነው የምንሰራው" አልኩት። እሱም የአእምሮ ህመሟን ክፍል ስለሚሰራ።"እሱን ብዬ ነው የደወልኩት ዘይነብን አሟት ሆስፒታል እየወሰዷት ነው እኔ ደግሞ አዳሪ ነኝ እና ልትሸፍንልኝ ትችላለህ?"አለኝ። ከተኛሁበት ተነሳሁ ደነገጥኩ"በቃ አሊሾ አንተ ውጣ እኔ እሸፍንልሀለሁ" ብዬ ስልኩ ዘጋሁት እና ልብሴን ለብሼ ከቤት ወጣሁኝ።"ለራስህ ነው እንጂ ለሰውማ መቼ አነስክ" የእማዬ ቃል ልቤን ወጋው ዞሬ ሳልመለከታቸው በሩን ከፍቼ ወጣሁኝ። ሆስፒታሉ ቅርብ ስለሆነ ትንሿን አቀበት በእልህ በብስጭት ሙጥጥ አድርጌ ጨረስኳት። ከሆስፒታሉ ስደርስ አሊ የለም። የአሊ ክፍል ገብቼ ጋውኔን ከመልበሴ ቀጭኗ ነርስ በሩን ከፍታ ገባች።"ዶክተር ሰባት ቁጥር ያለችውን ልጅ ልታያት ይገባል" አለችኝ።"ለምን?ምን ችግር" አልኩኝ። በነገር በተወጠረው ጭንቅላቴ ለማሰብ እየሞከርኩ።"ዶክተር አሊ ሁሌ ነው የሚያያት እና እሱ ካላያት አትተኛም አንተ መጥተህ እንደምታያት ነግሯት ስለሄደ እየጠበቀችህ ነው" አለችኝ። አይ አሊ ከእብድ ጋር ቀጠሮ አሲዞልኛል። አሁን ምን ልላት ነው? እኔ እንደሆን የያዘ ይዞኝ እንጂ ቆይቻለሁ ካበድኩ። ወደ ውስጤ ተነፈስኩ እና ከተሽከርካሪው ወንበር በብስጭት ተነስቼ ወደ ሰባት ቁጥሯ ታካሚ ጋር አቀናሁ።እውነትም አይኗ ፈጦ ተቀምጣለች። ስታየኝ የሚያምር ፈገግታ አሳየችኝ ደነገጥኩ ልቤ በሀይል ሲመታ ይታወቀኛል።"ሰላም እንዴት ነሽ" አልኳት አጠገቧ ካለው ወንበር እየተቀመጥኩ።ግንቧሯን ቋጠረች አይኖቿ እንባን አረገዙ።ከኋላዬ የነበረችው ቀጭኗ ነርስ"ስሟ ዕድል ነው ዝም ብለህ ታሪኩን ጀምርላት ከዛ ራሷ ትተኛለች" ብላኝ መንገዱን አሳይታኝ ጥላን ወጣች። ሁሉም ታካሚ ተኝቷል።"እሺ ዕድል" አልኩኝ። ልቤን አፍኖኝ የየዛኝ አንዳች ነገር እንዳልተነፍስ እየታገለኝ።ፈገግ አለች። አታወራም.....ስሜቷ በፊቷ ገፅ ላይ ይነበባል። ደገፍ ብዬ ተቀመጥኩኝ እና ጣሪያውን መመልከት ጀመርኩኝ። እሷም አይኔን ተከትላ ተመለከተች። ፈገግ ስትል ተመለከትኳት"አንድ በጣም ሚስኪን ልጅ አለ ሀዘን የከበበው ደስታ የራቀው። ቤተሰቡ ሁሉ ሊረዱት ያልቻሉ ልቡም ማንነቱም እንደ ሸክላ የተሰበረበት። እና ምን ሆነ መሰለሽ...." ከማለቴ ሸርተት ብላ ትራሷን ተንተርሳ አይኖቿን ከደነች።"ከአለም ርቆ ወደ ልቡ ቢዘልቅም ከአጠገቡ ያሉት በጠቅላላ ሳለለፈ ነገር ሁሉ እየጠየቁት ራሱን እንዳያገኝ ተብትበው አሰሩት። በንግግር ድንጋይ ወግረው ገደሉት። ከዛ በብቸኝነት ጉድጓድ ውስጥ ቀበሩት። ሲያሳዝን" አልኩኝ። እሷ ግን ተኝታለች። የኔ ታሪክ መሆኑ መች ገባት በደህና ጊዜ አብዳ። ቀስ ብዬ ከተቀመጥኩበት ተነስቼ እጆቼ እየተንቀጠቀጡ ብርድልብሱን አልብሻት ከክፍሉ ወጣሁኝ እና ተነፈስኩ። እንዴት እንደምዘልቅ አላውቅም ከነገ ጀምሮ እኔ ነኝ የዚህ ዋርድ ዶክተር ምን አለ የዛኔ በአርፊ ውጤት ባልመረቀ ማዕረጉ ቢቀርብኝስ....? ለነገሩ እኮ ይሄ ይመጣል ብዬ መች አሰብኩ ከራሴ ጋር ፍቅር በነበረኝ ጊዜ የወሰንኩት ውሳኔ ዛሬ ከራሴ ጋር ስጠላ ተወቃሽ ሊሆን አይገባም.....ግን አጠፋሁ ወይ አልገባም ማለት ነበረበኝ ስራ በለቀኩኝ....አሁንም ብቻዬን አጉተመትማለው። ለካ አብጃለሁ......በራሴ ፈገግ አልኩኝ እና ወደ ራሴ ክፍል ገብቼ መፅሀፌን ገልጬ ማንበብ ጀመርኩ........ይቀጥላል!

🌟🌟🌟ሰባራ ልቦች🌟🌟🌟
👀ይቀጥላል👀
@yebezawit2
💓 ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch

💓💓ድምጽ መስጠቶን አይርሱ💓💓
💓💓💓ሰባራ ልቦች👫👫👫

💜💜💜ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ💜💜💜
💜💜💜@yebezawit2 💜💜💜

🍟🍟🍟ክፍል 2🍟🍟🍟

የመፅሐፉ ግማሽ ጋር ስደርስ እንቅልፌ እንደ ልጅ ያዳፋኝ ጀመር ጠረጼዛውን ተንተርሼ ተኛሁኝ።"ዶክተር..ዶክተር" ከእንቅልፌ የነርሷ ድምፅ አባነነኝ አጠገቧ የትላንትናዋ ወጣት ልጅ አለች። "እድል" አልኩኝ መምጣቷ ገርሞኝ።"ዶክተር አሊ ሁሌ ቁርስ ይጋብዛታል ከዛ ነው መድሃኒት የምትወሰደው" አለችኝ ለዕድል አስተረጓሚ የሆነችው ነርስ።"እኮ እኔ ልጋብዛት!?" አፍጥጬ ጠየኳት።ነርሷም በአዎንታ ራሷን ነቀነቀች። ስልኬን ይዤ ወደ በረንዳው ወጣሁ እና ለአሊ ደወልኩለት ደህና አደርክ ሳልለው "አንተ ከእብድ ጋር አንተ በላህና እኔም ልበላ?እኔ ዶክተር እንጂ ሞግዚት አይደለሁም" እንደ ተልባ ተንጫጫሁበት። ትዕግስተኛው አብሮ አደጌ ግን በአንድ ቃል አፌን ለጎመው"እብድ" አለኝ። ለካ እኔም ጨረቅ የያዘኝ እብድ ነኝ ስልኩን ዘጋሁት እና ወደ ውስጥ ተመለስኩ።"እሺ ዕድል ነይ" ብያት ይዣት ወጣሁ። ዶክተር አሊ ለምን ከእሷ ጋር እንደሚሆን ለማወቅ ጓጓሁ አታወራም ስሜቷን እንዴት ይሆን የሚረዳው።የሆስፒታሉ ምግብ ቤት ጋር ደረስን።ዕድል መራመዷን አቆመች።"ምነው ዕድል አልኳት" ዝም መልሷ ዝምታ ነው አንስቼ በድንጋይ ብፈነክታት ተመኘሁ....ይኸው ማበዴ ግልፅ ሆነልኝ....የትኛው ዶክተር ነው ታካሚውን በድንጋይ የሚወግረው? "ምነው?" መልሼ ጠየኳት። ተለቅ ተለቅ ያሉትን አይኖቿን ከብለል ከብለል አድርጋ ጠቆመችኝ በፌስታል ይዘው ሲወጡ ኤሌክትሪክ እንደያዘው ሰው ከፀጉሬ ጫፍ እስከ እግሬ ጫፍ ነዘረኝ።"እና ይዤ ልምጣ" አልኳት በፈገግታ መለሰችልኝ። ፈገግታዋ ልክ እንደ ጠዋቷ ፀሀይ ያሞቃል ፈገግ ብዬ አየኋት እና ወደ ምግብ ቤቱ ገብቼ ምግቡን ይዤ ወጣሁኝ። ይህቺ ልጅ እብድ አይደለችም እንዴ አልኩኝ እኔ ስወጣ እሷ በደንጋይ የተዘጋጀው ወንበር ላይ ተቀምጣለች።ስነስርዓት አላት ጨዋነቷም ይነበብባታል። አጠገቧ ሄጄ ተቀምጥኩ እና"አንቺ ግን ጤነኛ ነሽ አይደል?" አልኳት ፌስታሉን እየከፈትኩ። እጅግ ደስ አላት። ድነሻል የተባለች ነው የምትመስለው። አይ ያማታል አልኩኝ በውስጤ። ምግቡን ከፍቼ ሰጠኋት እሷ ግን እኔ እንዳጎርሳት ነበር የምትጠብቀው።እኔ ግን ማጉረስ አልችልም ምክንያቱም ህመም አለብኝ ያን ጊዜ እያልኩ ማሰብ የማልፈልገው ጥቁር ትውስታ አለብኝ። "እድልዬ አንቺ እኮ ጎበዝ ነሽ በእጅሽ ነው መብላት ያለብሽ" አልኳት ላለሟጉረስ። እሷ ግን እምቢ አሻፈረኝ አለች። ነርሷ መጣች። ግራ መጋባቴን ተርድታ ነበር እና መጥታ ታጎርሳት ጀመር ፈጣሪ ያክብራት የድሮ ቅዠት ውስጥ ከመግባት ነው ያዳነችኝ።

የራሴን ችግሮች ትቼ ስለ እሷ የህመም ደረጃ ማጥናት ጀመርኩ። መነሻም መደረሻም የለውም ስሜቷን የምትገልፀው በብስጭት በማኮርፍ በማልቀስ እንጂ ቃል ከአፏ አይወጣም።ሰው አትነካም አትረብሽም።መድሃኒቷን ሳታስቸግር ነው የምትወስደው።ፊቷ ላይ ያሉት ጠባሳቸው ግን የተደበቀ ህመሟን ያሳብቃሉ።ካርዷ ላይ ምንም ነገር አይገልፅም አድራሻም የላትም ፖሊስ ነው ያመጣት የሚጠይቃትም የለም ምን አልባት ዘመድ ስለሌላት ይሆን አሊ የቀረባት...ብዬ አሰብኩኝ።ጓደኛዬ አሊ ከቀናት በኋላ መጣ "እህ ወንድሜ" አለኝ ቦርሳውን ጠረጴዛ ላይ አስቀምጦ ወንበር እየሳበ"እንዴት ነህ አሊሾ" አልኩት።"ምን ባክህ ሚስቴን እርግዝናው ከብዷት ፈቃድ ጠይቄ እኮ ልይህ ብዬ መምጣቴ ነው" ብሎ ሁለት መርዶ ነገረኝ አንዱ እና ዋናው የሚስቱ የእርግዝና መክበድ ሌላኛው ደግሞ የእሱ ፈቃድ መውጣት ለብቻዬ ላክም ለብቻዬ ልጋፈጥ...ፍርሃት ልቤን አራደው።"ምነው ምን ሆነች ለኔ ይሁን" አልኩኝ። የአሊ ባለቤት ለኔ እህቴ ናት በተጎዳሁባቸው ጊዜያት እነሱ ቤት ስከርም በሚገባ ተንከባክባኛለች። በዛ ላይ ትህትናዋ ሌላ ነው በቃ ትክክለኛ ውሃ አጣጭ ናት ለባሏ ያላት ፍቅር ክብር ይለያል አሊ የወደቀ ትንሽ እቃ ካነሳ ወይም የበላበትን ሳህን ካጠበ በቃ ለእሷ ታምር ነው ስታሞግሰው ታድራለች እያንዳንዱን የአሊን ስራ ስትደግፍ ስታሞግስ ላያት ሚስት ብቻ ሳትሆን ደጋፊ ነው የምትመሰለው ልዩ ሴት ናት። እኔ ወንድሙ እንዲህ ካሞገስኳት እሱ እንዴት ይገልፃት ይሆን? "ምን ባክህ መንታ ነው ያረገዘችው እና መንቀሳቀስ ሳይቀር አቅቷታል ከጎኗ ሆኜ ብከታተላት ጥሩ ነው" አለኝ። "አይ ዶክተር ማግባት ጥቅሙ" አልኩት ፊቴ የተደረደረውን ወረቀት እየሰበሰብኩ። "ወሬ አለብህ አንተም እኮ ስታገባ...." አላስጨረስኩትም። "ዕድልን ምን ያህል ታውቃታለህ" አልኩት። ወሬውን ማረሳሳቴ መሆኑን ገብቶታል ፈገግ ብሎ"ስለ ዕድል ማንም አያውቅም ያመጧት ፖሊሶችም ራሷን ስታ በነበረችበት ጊዜ ነው እና እነሱም አያውቁም የፈለጋት ቤተሰብም የለም።በብቸኝነቷ በነቃችበት ጊዜ በጣም ተጎድታለች። በዛ ላይ ሆስፒታሉ ለታካሚዎች የሚሰጠው ምግብ አይስማማትም እና የግድ መብላት ስላለባት ከእኔ ጋር ነው ወጥታ ከምግብ ቤቱ ገዝተን የምንበላው። ማታ ደግሞ ታሪክ ካልነገሯት አትተኛም በቃ የግድ አጠገቧ የሆነ ሰው ተቀምጦ ሊያወራት ይገባል ነርሶቹ መድሃኒት ከሰጧት በኋላ አብረዋት እንዲቆዩ አትፈልግም ከእኔ ጋር ጓደኛዬ ናት ጨዋታ ትወዳለች ተግባቢ ናት" አለኝ። አሊ አብዷል ተመስገን እኔ ብቻ አይደለሁም አልኩኝ በልቤ። ዕድል እኮ ጓደኛ ልትሆን ቀርቶ ታካሚዬ መሆኗን ሳስብ እበሳጫለሁ እንዴት አክማታለሁ ህመሟን ሳትነግረኝ። "በቃ እሺ አሊሾዬ መጥቼ እጠይቃችኋለሁ" አልኩት። እሱም "እሺ እቤት ስመጣ በሰፊው እናወራለን ወንድሜ" ብሎኝ ከተቀመጠበት ተነሳ።"ዕድልን አደራ እንደምታድናት አምናለሁ" ብሎ የእብድ አደራ ሰጠኝ። በመሀል በሩ ተበረገደ ዕድል ናት።ይሄን ነው መሸሽ....."ዕድል" አልኩኝ። እሷ ግን በራሪ አይኖቿን አሊ ላይ አሳርፋ የኔን ድምፅ አልሰማችም ቦርሳውን ቀስ ብላ አየች። አይኖቿ እንባ አርግዘው ፊቷ ጥቁር ደመና መሰለ።"እድልዬ አታኩርፊ እመለሳለሁ እኮ እንደነገርኩሽ ሚስቴ ታማለች እና ከማንም በላይ እኔ አስፈልጋታለሁ" አላት ዶክተር አሊ። ኧረ እብደት ሲባባስ አልኩኝ። ምንም ለማትመልስ ልጅ ስለ ሚስቱ መታመም ያብራራላታል። "ደግሞ እሱ የእናቴ ልጅ ነው ልክ እንደ እኔ ሆኖ ይጠብቅሻል በፍፁም ብቻሽን አይተውሽም" አላት። ወደእኔ እየተመለከተ። "አዎ እድል እኔን እንደ ጓደኛሽ ከፈለክሽ እንደ አባትሽ ካሻሽ እንደ ወንድምሽ ኧረ አያትሽም አጎትሽም አድርጊኝ" አልኳት በብስጭት እና በፍርሃት እሳት ውስጤ እየተለበለበ። ድምፅ የሌለው ሳቋን ሸለመችኝ።"በቃ አሁን ከወንድሜ ጋር ልተውሽ ደግሞ ልጆቼ ሲወለዱ ትመጫለሽ" ብሎ አቀፋት። እሷም እንደ አባቷ ስሩ ተሸጎጠች። አሁን ልክ እንደ እዚህ ስሬ ልትለጠፍ ነው። ኤጭ! ምነው ባላክምስ ቢቀርስ እንዴ ደግሞ መድሃኒት ከሰጧት አይበቃትም የምን መቅበጥ ነው እያልኩ በልቤ አጉተመተምኩ። "በቃ ወንድሜ ሰላም ዋሉ" ብሎ ከእድል ጋር አጋፍጦኝ ከክፍሉ ወጣ። እድልም በአይኖቿ ሸኘችው። ምን ያህል ብትወደው ምን ያህል ቢቀርባት ነው። በእርግጥ አሊሾ እንኳን ሰውን ሰይጣንንም በፍቅር ያሸንፋል።"እሺ እድል እና እንዴት ነሽ?" አልኳት ወንበሩን ስቤ እያስቀመጥኳት። በስስት አይን አየችኝ። አንተስ መቼ ነው የምትሄደው ወይም አትሂድ የምትል ነበር የምትመሰለው"አታስቢ እኔ ውጣ ብለሽ ካልገፈትርሽኝ የምወጣበት ምክንያት የለኝም ሚስትም ድስትም የለኝም" አልኳት። ተደሰተች ተፍለቀለቀች። ተሳካልኝ ማለት ነው። "ለምንድነው የማታወሪው" አልኳት። ግንባሯን ቋጠረች።
"እሺ እሺ አታኩርፊ በቃ ሻይ ትጠጫለሽ" አልኳት።ተመልሳ እንደ ልጅ ቦረቀች። ደስ የምትል እብድ ሻዩን እየጣን ታሪክ እየተረኩላት ነበር የኔ ስልክ ያቃጨለው ደንግጣ ከተቀመጠችበት ተነስታ አንገቷን እንዳቀረቀረች ጣቶቿን መፍተል ጀመረች።

፨፨፨፨፨.......ይቀጥላል!.....፨፨፨፨፨

💜💜ሰባራ ልቦች💜💜
👫ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ( @yebezawit2 )👫
💓ድምፅ መስጠት እንዳትረሱ💓
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
💜💜💜ከእናንተው የመጡ አስተያየቶች💜💜💜

😍 ማርኮን___ ሰላም ቤዚ የራጉኤሏ እንዴት ነሽ የምትለቂያቸው ፅሁፎች ደስ ይላሉ ነገር ግን ከክርስቶቤል በኋላ ብዙም አትለቂም ጠፍተሻል እና ከቻለሽ ከታሪኩ ጎን ለጎን ተጨማሪ መልዕክቶችን ብታስቀምጭልን እላለሁ።

💓 ኤደን...ቤዚዬ በቅርቡ ነው ቻናልሽን የተቀላቀልኩት ታሪኩንም ያነበብኩት እና የጨረስኩት ትላንት ነው። በጣም ነው ያዘንኩት አዲሱ ታሪክሽንም በጉጉት እጠብቃለሁ የእውነት አድናቂሽ ነኝ።

💜 ብሌን ቤዚዬ በርቺ አደራ ግን ያለሽን ትህትና ወደ ፊት እንዳትቀንሺ እንዳትለወጪ

🍟 በረከት ችሎታሽን ሳላደንቅ አላልፍ ግን አሁን ላይ ፅሁፍ ቀንሰሻል እና ይሻሻል። በተረፈ ግን በርቺ እግዚአብሔር ይረዳሻል መንገዱን አውቀሽበታል የራጉኤል ልጅ።

💛ሊያ ቤዚዬ ጌታን በጣም ነው የምቀናብሽ በቃ ሁሉም ነገር አለሽ የጎደለሽ የለም ተባረኪ በአንቺ የተፈቀረ ግን ታድሎ...ደግሞ አዲሱ ታሪክ ጅማሬው ደስ ይላል።

💙 ሰላሜ ነሽ ማርያም....ቤዚ ጥሩ ነገር ነው ቻናልሽ ላይ የማነበው እና ደስ ይላል። ግን አንድ ነገር ልምከርሽ ሰዎች ያው ያለሽን ጉብዝና በገለፁልሽ ቁጥር ኩራት እንዳይዝሽ ተጠንቀቂ በእርግጥ እንደማታደርጊው አውቃለሁ ግን አስተያየት ስለጠየቅሽ ነው እና ነቀፋዎችንም ችላ አትበይ ካለሽበት አቋም ሳትወርጂ ወደ ፊት ከፍታ ላይ አይሻለሁ ብዬ ተስፋ አለኝ ማርያም እናቴ ትጠብቅሽ እህት ቤዛዊት😘

💓💓💓ሁላችሁንም አብዝቼ እወዳችኋለሁ አከብራችኋለሁ🙏🙏🙏 በየቀኑ ስገባ መልዕክት አገኛለሁ አሁንም ክበሩልኝ💜💜💜
😍ቤዛዊት የሴትልጅ😍

ያዝናኑኝ መልዕክቶች

💜zion 😃 አንቺ ልጅ ምን እንደምፈራልሽ ታውቂያለሽ አብደሽ እንዳይለይልሽ ነው አስለቀሽኝ እኮ......

😂one love😃 ሰውዬሽ ግን ዝም ብለሽ ስትጭሪ አይቶ እንዳይፈታሽ

😃😃😃 አሁንም ለአስተያየት @yebezawit2 ን ይጠቀሙ💙💙💙

💛💛💛የግጥም መንደር💛💛💛


@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
🚺 #ለትዳርሽ_ብቁ_ነሽን ? 🚺

#ለሴቶች_ብቻ 👧💏

🌀 ባለቤትሽ ወደ ቤት በገባ ጊዜ በእጅሽ ያለውን ነገር ትተሽ እሱን ለመቀበል ካልሄድሽ፣ ከፊቱ ላይ የተመለከትሺውን የድካም ስሜት ካላስረሳሽ
{ አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}

🌀 ባለቤትሽ አንቺ በእጅሽ ሰርተሽ የማታባይው ከሆነ ከምግብ ቤቶች ከተመገበ ፣ ልብሶቹን የማታዘጋጂለት ከሆነና ወደ ማጠቢያ ቤት ከወሰደ
{አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}

🌀 ባለቤትሽ በተቆጣ ጊዜ በአስር ቃላት የምትመልሺለት ከሆነ፣ድምፅሺን ከፍ አድርገሽ ካወራሽው{አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}

🌀 ከባለቤትሽ አጠገበ በተቀመጥሽ ጊዜ ጠረንሽ ጥሩ ካልሆነ፣የልብስሽን ንፅህና ካልጠበቅሽ፣እሱን የሚማርኩ ካልሆኑ {አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}

🌀 ከሱጋ በተጣላሽ ወቅት ወደ እናትሽ ቤት፣ወደ እህትሽ፣ ወደ ጓደኛሽ ቤት የምትሄጂ ከሆነ
{አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}

🌀 ከባለቤትሽ ቤተሰቦች ጋር ስትሆኚ የሱን ቤተሰቦች መልካምን በማድረግ የማትንከባከቢ ከሆንሽ {አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}

🌀 በፀሎት ጊዜ እሱን የማትቀሰቅሺ ከሆንሽ፣ ፈጣሪን በመታዘዝ ላይ የማተበረታቺው ከሆነ፣ ክልክል ነገራቶችን እንዲተው የማታደርጊ እና ወደ ውበት የማትገፋፊው ከሆንሽ
{አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}

🌀 ባልሽ የሚወዳቸውን እና የሚጠላቸውን ነገሮች ለይተሽ ካላወቅሽ {አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}

ፍቅር የሚያወሩት ብቻ አይደለም!!
💜💜በተግባርም መገለፅ ይፈልጋል እና ባልሽን ተንከባከቢው😘😘



🚹 #ለትዳርህ_በቁ_ነህን? 🚹
የሚለውን ነገ ምሽት እንመለስበታለን.....

💙💙💙 ከተሳሳትኩ አርሙኝ
💛💛💛 ጥያቄም ካላችሁ እቀበላለሁ
@yebezawit2
💜💜💜አድርሱኝ💜💜💜


ሰናይ ምሽት

@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
💙💙💙ሰባራ ልቦች💜💜💜
👸👸ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ👸👸

💛💛ክፍል ሶስት💛💛
ስልኩን ቶሎ ዘጋሁት "ምነው ዕድል" አልኳት። የቋጠረችውን ግንባሯን ፈታች "ገባኝ ስልክ አትወጂም" አልኳት። እሷም ፈገግ አለች።መልሷ ፈገግታ እና መኮሳተር ናቸው።ብዙ ልጠይቃት ብፈልግም መነሻ ሀሳብ የለኝም ለምን እንዲሆንሽ ማለት ደግሞ ከበደኝ።ከእድል ጋር ስራ በገባሁባቸው ቀናት ሁሉ አብረን ጊዜ እናሳልፋለን።ዛሬም እንደተለመደው ወደ ስራ ለመሄድ ሻወር ወስጄ ልብሴን ለባብሼ ወጣሁ እነ እማዬ ቁርስ እየበሉ ነበር።ተሰብስቦ መብላት እንዴት እንደናፈቀኝ.....እንደ በር ጠባቂ ውሻ በሰሀን ለብቻዬ መብላት እጅእጅ ብሎኛል።"ልዑል አንዴ ና ወደዚህ" እማዬ ናት።ከአጠገባቸው ያለውን ወንበር ስቤ ተቀመጥኩኝ።"እቸኩላለሁ ምንድነው ሰላም አይደላችሁም" አልኳቸው ከዝምታቸው ጀርባ ያለውን ለማወቅ ጓጉቼ። እናቴም ልትጎርስ ያዘጋጀችውን እንጀራ መልሳ ሳህኑ ላይ ቁጭ አድርጋ ወንበሩን ደገፍ አለች። አስጨነቁኝ...መልሰው ስለማልወደው ጥያቄ እንዳያነሱልኝ አልኩኝ በልቤ"መቼ ነው የምትረጋጋው መቼ ነው ደስተኛ የምትሆነው መቼ ነው የምትስቀው እስኪ ንገረኝ ምን አጎደልንብህ ፊትህን ከስክሰህ ትገባለህ ድምፅህን ሳታሰማ ትወጣለህ ለምን ልዑል በዛች ልጅ ምክንያት ይኸው ጨላልመክ ቀረህ...አትሆንህም እያልክ ተጣብቀህ ለእኛም ሰቀቀን ሰጠኸን" የፈራሁት ነገር ተነሳ።"እማዬ እባክሽ ልሂድ ስለዚህ ጉዳይ አናውራ" አልኳት። "ለምን ታወራለች እንጂ ያኛው ሳቅ ና ጨዋታ ያልተለየበት ልጃችንን እኮ ያጣነው አሁን ምን ላይ ነህ እኛ አናውቅህም አብረን ሆነን እኮ ተለያይተናል ሀሳብህ ምንድነው ለምን ጓደኛ አትይዝም ፍቅር እኮ በፍቅር ነው የሚታከመው አንተ ብቻ አይደለህም የተጎዳኸው ወንድምህም እኛም ተጎድተናል......" አባዬ በብስጭት ነበር የሚናገረኝ። "ደህና ዋሉ" ጥያቸው ከቤት ወጣሁ።እንዴት እንደምራመድ አላውቅም በቃ ጅምር ቀኔ ሲጨላልም ታየኝ።የተጎዳሁ እኔ የሚጨነቁት እነሱ ለምን ምን አለ ከድሮም ዝምተኛ ብሆን ልዑል ልዑል ምን ሁነህ ነው በቃ ራስህን አጥፋ ከራሴ ጋር ስነታረክ ከሆስፒታሉ ደረስኩ እድል ሁሌ እንደምትሆነው ፊቴ በፈገግታ ቆመች።ገፍትሪያት ደረጃውን ወጥቼ ወደ ክፍሌ ገባሁኝ ሴቶች ሁሉ መርዝ ናቸው ደግሞ እናቴ አባቴ እንደሚለው መድሃኒት ሆናለታለች።አሊሾም ቢሆን ጥሩ ሚስት አለችው እኔስ ወረቀቱን በብስጭት ማተረማመስ ጀመርኩ።በሩ ተንኳኳ "አትግቡ" አልኩኝ በንዴት። በሩ ግን ሲጥጥ ብሎ ተከፈተ የህፃናት ክፍል የምትሰራው አፈቀርኩ ባይ ዶክተር ሰገን ናት አንገቷን ከበሩ ኋላ ብቅ አደረገች"አትገቡ ነው ያልኩት" አልኳትኝ ያን ሰፊ ፊቷን በመፀየፍ እየተመለከትኩ።"አስቸኳይ ነው ውዴ" ብላ በሩን ገርበብ አድርጋ ገባች ለምን እንደሆነ ሳላውቅ ጣቷን ተመለከትኩት የጋብቻ ቀለበት አድርጋለች።"ማፈሪያ" አልኩኝ ጮክ ብዬ።"ምን" አለችኝ ደንግጣ።"ምንም አሁን አስቸኳዩ ጉዳይ ምንድነው" አልኳት። ደብዳቤውን ጠረጼዛው ላይ አስቀምጣ "ከራስህ ጋር አትመስልም"ብላ ጥላኝ ወጣች። ኡፍፍ ተመስገን ጥርግ በይ አልኩኝ ደብዳቤውን እየከፈትኩ። የቦርዱ ደብዳቤ የስብሰባ ጥሪ ነው አንድ አመት ሆስፒታል በቆየችው በእድል ላይ ሊወያዩ ነው። መገፍተሬ ታወሰኝ ተስፈንጥሬ ወጣሁኝ ወደ ክፍሏ ስሄድ የለችም በመስኮቱ ተመለከትኩኝ ብቻዋን አይኗን ይዛ ተቀምጣለች። ስበር ወደ እሷ አቀናሁ። አጠገቧ ቁጭ አልኩኝ።ቀስ ብላ አይኗን ለቀቀችው።ከአሁን ከአሁን ተበሳጨች ስል እሷ ግን ረስታዋለች ፈገግ አለችልኝ።እጄን በእጇ ያዘች።"ይቅርታ ተናድጄ ነበር እድል" አልኳት።እድል ግን በዝምታ አይኖቼን ተመለከተች "ምነው አላመንሽኝም" አልኳት። እሷም አይኗን ሰበር አድርግ ተመልሳ ቀና አለች። የምትሆነው ግራ ገባኝ በአይኖቿ የሰማይ አእዋፋቱን እንድመለከት ጠቆመችኝ። አየኋቸው በነፃነት ነው የሚበሩት ለነሱ አለቃቸው የራሳቸው ክንፍ ነው የግላቸው። ስለእሷ ምን ሊወሰን ይሆን ብዬ ሀሳብ ይዞኛል። "እድልዬ መጣሁ እሺ" ብያት ወደ ቦርዶ መሰብሰቢያ ክፍል አቀናሁ። የአእምሮ እስፔሻሊስቶች እና ሌሎች ዶክተሮች ነበሩ የሚጠብቁት እኔን ነበር እና ከመቀመጤ ስብሰባው ጀመረ።የተወሰነው ሰው አላገገመችም ትቆይ ሲሉ አብዛኞቹ ግን እሷ ጉዳት ስለማታደርስ የስነልቦና ድጋፍ እየተደረገላት በውጪ መከታተል ትችላለች።እያሉ ሀሳባቸውን ያጋራሉ።እኔ ግን ውስጤ ተረብሿል እድል ለእኔ ታካሚዬ ብቻ አይደለችም መካሪዬ ናት "እሺ ዶክተር ልዑል አንተስ ምን ትላለህ ካለህ ቅርበት" የሚለው የስፔሻሊስቱ ድምፅ ከሀሳቤ አባነነኝ "ያው እድል ሰው አትጎዳም እና የሚያስፈልጋት የስነልቦና ድጋፍ ነው ባትቆይ ባይ ነኝ" አልኩኝ።በስተመጨረሻ እድል ከሆስፒታሉ ወጥታ የስነልቦና ህክምና እንድታገኝ ተወሰነባት። በራሴ ተበሳጨሁ.....እጄን ጋውኔ ውስጥ ከትቼ ወደ ክፍሌ አቀናሁ። አሊ ጋር ደወልኩለት....

"አሊሾ እንዴት ነህ" አልኩት።

"ይመስገን ወንድሜ እንዴት ነህ" አለኝ።

"እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ነኝ...አሊሾ እድል እኮ ከሆስፒታሉ ትውጣ ተባለ" አልኩት።

"ምን?! ለምን አንተ አትከራከርላትም መሄጃ እኮ የላትም እኔ እኮ እስከ ዛሬ ያቆየኋት ብዙ ትግል ታግዬ ነው ሰው አልጎዳችም ተብሎ ማስወጣት" እንደ እብድ አደረገው። ስልኩን ጆሮዬ ላይ ዘጋው።

እንድትወጣ ካደረጉ ሰዎች መሀል አንዱ እኔ መሆኔን ቢያውቅ ምን ያደረገኝ ይሆን እያልኩ አሰብኩ።ለነገሩ ማለዳዬ በመጥፎ ተጀምሮ ድሮስ ሊቀናኝ ነው። ከራሴ ጋር እያወራሁ በሩ በሀይል ተበረገደ አሊ ነበር። አሊ ለታካሚዎቹ ጠበቃም ነው የማይወደው ሰው የለም ሌላው ቀርቶ አንሶላ አጣን የሚሉት ለአሊ ነው ማንንም ከማንም አይለይም ንፁህ ፍቅር ነው የሚሰጣቸው ታካሚዎቹ ቤተሰቡ ናቸው።"ልዑል ግን ምን አረኩህ ካርዷን ስጠኝ አሁን" አለኝ።"የት ልትወሰደው ነው" አልኩት። እሱ ግን አልመለሰልኝም ካርዱን ይዞ ወጣ እኔም ተከተልኩት የሜዲካል ሀላፊው ጋር ነበር የሄደው በሩ በርግዶ ዘው ብሎ ገባ "ምንድነው የምትሰሩት ዘመድ የሌላትን ልጅ ገና ለመዳን የምትታገል ልጅ ማስወጣት ልክ ነው ትላላችሁ ለእሷ ህመም ጨምራችሁ ሌላ ብታድኑ እኮ ትርጉም የለውም" እንደ መብረቅ ጮኸ። ነገር ግን የእሷ እንደእዛ መሆን መፍትሄ ሳያመጣ ቀረ። ጭንቅላቱን እንደተመታ ዘንዶ እየተወራጨ ከክፍሉ ወጣ።"አመሰግናለሁ ልዑል ጥሩ ስራ ነው የሰራኸው" ብሎ ካርዱን አሳቅፎኝ ጥሎኝ ሄደ።የእድል ከዛ ሆስፒታል እርግጥ ሆኗል እኔም ግራ ገብቶኛል ወንድሜ እና ጓደኛዬ ለተጠነቀቀላት ልጅ እኔ ልሆን አልቻልኩም። አሰብኩት መናገር አትችልም ዘመድም የላትም እንዴት ትሆናለች ኑሮዋ ምን ሊሆን ነው በእርግጥ የስነልቦና ድጋፍ ብቻ እንደሚያስፈልጋት ባምንም ስትወጣ የሚገጥማት ግን አሳስቦኛል አንገቴን አቀርቅሬ ወደ ክፍሌ ገባሁኝ......

🙌🙌🙌ይቀጥላል🙌🙌🙌

💙💙💙💙ሰባራ ልቦች💙💙💙💙
🔑🔑ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ🔑🔑
💙💙💙💙 @yebezawit2 💜💜💜
💓ድምፅ መስጠታችሁን አትርሱ!💓💓
💜💜አስወቅስሻለሁ💜💜

ልረሳሽ እያሰብኩ ሳስብሽ እውላለሁ
ልተውሽ እያልኩ እጨነቅልሻለሁ
አንቺ ደህና እኔ ደግሞ ታማሚ
ራሴን ትቼ አንቺን አላሚ...
የተሰጠሽ ባይገባኝ ቢሆንብኝ ቅኔ
ያንቺ ፍቅር መራቅ አልወደደም ከእኔ
በልክ አድርጊው ተይ እጎዳለሁ
ብሞትም አልጠቅምሽ አስወቅስሻለሁ!!
ቤዛዊት የሴትልጅ በ21/10/12 20:25
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
😰😰😰 ስለምን መግደል?😰😰😰

ፈጣሪ በአምሳሉ ፈጥሮ እስትንፋሱን እፍ ብሎ በህይወት ያቆመውን ሰው #በጥላቻ #በግፍ መግደል አሸናፊነት #ጀግንነት አይደለም

ሰውን በአመለካከቱ እና በአስተሳሰቡ ልትቃረን ትችል ይሆናል😢😢😢 ግን መግደል #አትችልም!!!!

🙏አባት ሆይ ማረን ማለት ይከብዳል!
ወንድም ወንድሙን እየገደለ እንዴት ትታረቀን?🙌
😢😢😢 በግፍ የተገደሉ ሁሉ በሰዎች እጅ ነፍሳቸውን ለተነጠቁ ውድ የእግዚአብሔር ፍጥረት የሆኑ #የሰው ልጆች በጠቅላላ ነፍሳችሁ በሰላም ትረፍ😢😢😢
ቤዛዊት የሴትልጅ
23/10/2012
🇪🇹🇪🇹🇪🇹ኢትዮጵያ ሰላምሽ ይብዛ🇪🇹🇪🇹🇪🇹
💔💔ሰባራ ልቦች💔💔
ክፍል #አራት 💔💔💔💔🇪🇹
🇪🇹ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ 🇪🇹
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐

....አሊ እንደዚህ ሆኖብኝ አያውቅምና ጭንቀቴ አየለ።ንፁህ ማንነቷን ይዛ ዕድል ወደ እኔ ክፍል መጣች ሳያት ይበልጡን በራሴ አዘንኩኝ ተከራክሬ ላድናት አልቻልኩም ወንድሜን አሳዘንኩኝ።"ሰው አይከፋውም" አለችኝ ደርቀው የገረጡትን እጆቿን እየፈተለች።"እንዴት?" በማውራቷ ተደንቄ ነበር የጠየኳት እሷ ግን ዝም አለች....በቃ ዝም...."እኔ የምልሽ ዕድል ቤተሰብ...." ንግግሬን ለማድመጥ አልፈቀደችም ተነስታ ወጣች። ኤጭ! ዛሬ የማላበላሸው ነገር የለም እንዴ ብዬ ከወንበሬ ተነስቼ ልወጣ ስል ከዶክተር አዛርያስ ጋር ተገጣጠምን "ዶክ ወዴት እየወጣህ ነው" አለኝ ነጭ ጋውኑ ውስጥ እጁን እየከተተ።"እዚሁ ዞር ዞር ልበል ብዬ" አልኩት አመጣጡን ለመገመት እየሞከርኩ።" ምነው ፈልገኸኝ ነው?" አልኩት ቀጠል አድርጌ።"ምን የዕድልን ወረቀት ፅፈህ እንድትሰጠኝ ብዬ ያው ልትወጣም አይደል" ብሎ ስጋ እንዳየ ውሻ ተንሰፈሰፈ። ሰው ግን እንዴት ነው በበሽተኛ እንደዚህ የሚመቀኘው ብዬ በልቤ አስቤ ጥርሴን ብልጭ አደረኩኝ። በቃ መወሰን አለብኝ ወንድሜንም ህሊናዬንም ማጣት አልሻም እና "ወደ እኔ ቤት ስለምወስዳት ችግር የለውም" ብዬ የወረቀት አምሮቱን ገደልኩበት።"እውነት..ከምርህን ነው ማለት ልጅቷ እኮ ከአንተ personality ጋር አትመጣጠንም" አለኝ እራሱን አዋዶ። "ማለት የኔ personality ምንድነው?" አልኩት እሳት ልሼ። "አይ ያው አንተ እንደማይህ ከፔሸንቶች ጋር መግባባት አቅቶሀል እና እሷ ደግሞ.." ቀጣዩን ወሬ ላለማድመጥ አቋረጥኩት እና "የመውጫ ሰአቴ ስለደረሰ ላዘጋጃት ስለተጨነክልኝ አመሰግናለሁ" ብዬው ወደ ዕድል ክፍል አቀናሁኝ። እድል በተዘበራረቀ አልጋው ላይ ተቀምጣ በእግሮቿ መሀል አንገቷን ቀብራ በዝምታ ውቅያኖስ ውስጥ ሰጥማለች።"ዕድል" አልኩኝ እየተሸበርኩ።እሷም ቀና ብላ አየችኝ።እኔም ከአጠገቧ ካለው ወንበር ላይ ተቀመጥኩኝ።በዝምታ ማየት ጀመረች ፈራኋት...ልቤ ተሸበረ ግን ልነግራት ይገባልና ምራቄን ዋጥ አድርጌ ጉሮሮዬን ጠርጌ አወራት ጀመር።"ዕድልዬ እእ ያው እንደምታውቂው አሁን ጤንነትሽ እየተስተካከለ ስለሆነ መውጣት እንዳለብሽ ቦርዱ ወስኗል ስለዚህ .." መንታ እንባዋ ዶፍ ሆኖ ይወርዳል ሲቃዋ ደግሞ መብረቅ መስሎ ያሸብራል።እጆቿን አምጥታ እጆቼን ላይ አሳረፈቻቸውና በአይኗ ትማፀነኝ ጀመር።አይኖቿ ውስጥ "እባክህ አታስወጣኝ እባክህን ታደገኝ መሄጃ የለኝም ተረዳኝ" የሚል ይመስላል። አይኖቿ ላይ ያሉትን እንባዎች በመዳፌ ዳበስኩላት እና "አታስቢ እኔቤት እንድንሄድ እና እንድትዘጋጂ ነው የመጣሁት" አልኳት። በጥያቄ እና በምርመራ አይን ተመለከተችኝ።"የምሬን ነው አንቺን ለመንከባከብ ቤተሰቦቼ አያንሱም" አልኳት እና ቀና አደረኳት እሷም በዝምታ አይኗን መሬቱ ላይ ተክላ ቀረች።"እድልዬ ምንም ሀሳብ አይግባሽ ከስራ መልስ ከእኔ ጋር ትሆኛለች ቀን ላይ ግን እናቴም አባቴም ስላሉ አትጨነቂ ደግሞ አታስቸግሪም አንቺ" ብዬ ከሀሳቧ እንድትወጣ ትከሻዋን ሰበቅ አድርጌ ያዝኳት እሷም በሹራቧ እጀታ ፊቷን ጠራርጋ በአውንታ ፊቷን አበራችልኝ እና ድብቅ ጥርሶቿን ብልጭ አደረገቻቸው። ልቤ አረፈ አሊ ይሄን ቢሰማ ምን ይል ይሆን እያሰብኩ ነርሷ እንድታሰዳልኝ ጠይቄ ከክፍሏ በዝግታ ወጣሁኝ።ግን ሌላም ሀሳብ ይዞኛል የኔን መለወጥ የሚናፍቁት ቤተሰቦቼ የእድል ወደ ቤት መምጣት በለሌላ እንዳይተረጉሙት ውስጤን ጨንቆኛል።ግን ምን ምርጫ አለኝ...ምንም💔


..💔💔💔....... ይቀጥላል.......💔💔💔
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
💐የግጥም መንደር💐በቤዛዊት የሴት ልጅ💐
🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ፍርዱ እኛን ቢነካስ?
*
*
*
ድንገት ሲቃ ገርፎን ላፍታ ስናማርር
ለሚያልፈው መከራ በደል ስንደረድር
ሀቁ ሳይታየን
ውረድ ወይ ፍረድ ስንል ቁመን መቅደስ
ጩኸታችን ከስሞ ፍርዱ እኛን ቢነካስ?
--------------------------
አማኑኤል ደርበው(አማን)
@kene_tobeya
@kene_tobeya
💔💔ሰባራ ልቦች💔💔
ክፍል #አምስት 💔💔💔💔🇪🇹
🇪🇹ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ 🇪🇹
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐

እጇን በእጆቼ አጥብቄ ይዤ ወደ ቤት አብረን ማዝገም ጀመርን። እድል ግን ቃል አልወጣትም የቤቱን በር ከኪሴ ባለው ቁልፍ ከፍቼ እንድትገባ ጋበዝኳት እሷም ገባች በረንዳው ላይ ያለችው እናቴ ተአምር እንዳየሰው ከተቀመጠችበት ወንበር ላይ ተስፈንጥራ ተነሳች።እኔም ወደሌላ እንዳይተረጉሙት "እ እናት እድል ትባላለች ይቅርታ ሳልነግራችሁ...." እናቴ አቋረጠችኝ እና "ተወው ጎሳዬ የኔ ቆንጆ ልጅ" ብላ አገላብጣ በፍቅር ሳመቻት ዕድል የሚያምር ፈገግታዋን አነፀባረቀች። እኔም ሳላስበው ፈገግ አልኩኝ። "ነይ ግቢ" ብላ ወደ ቤት እየተጣደፈች አስገባች እኔም እናቴን በአይኔ ጠርቻት "እናት ልጅቷ ማውራት አትፈልግም እና ስሜቷን የምትገልፀው በፊቷ መሄጃ ስለሌላት ነው ያመጣኋት" አልኳት ፀጉሬን እያከኩ።"አይ የኔ እናት ምን ሆና ነው...ይሁን ለነገሩ ማን ያውቃል" ጥላኝ ወደ ውስጥ ገባች። እኔም በረንዳው ላይ እንደተቀመጥኩ በሀሳብ ጠፋሁኝ።

.....ቀን ቀንን እየወለደ እድል ቤታችን ከመጣችን ዛሬ አራተኛ ሳምንቷ ነው።እስከዛሬ ግን ቃል ወጧት አያውቅም። ሁሌም ግን ከእናቴ ጋር ምጥን ፈገግታዋን እያሳየች ተግባብታ እየኖረች ነው።እኔም ሀሳቤ ረግቷል አሊም ቢሆን ደስ ብሎታል። ነገን ማን ያውቃል....ዛሬ ለየት ያለ ቀን ነው እድልን ፀጉሯን አብጥሬ አስዤላት ወደ ውጭ ተያይዘን ወጣን እና በእግራችን መራመድ ጀመርን። ፀሀይ ወደቤቷ ገብታለች ጨረቃም ብርሃኗን ፈንጥቃ ጨለማን ለመርታት ትታገላለች "እድልዬ ተመችቶሻል አይደል?" አልኳት። ወሬዬን አጠንክሬ ፈገግ ብላ አየችኝ እና በአውንታ ነቀነቀች።"እድልዬ ዛሬ በጣም ከፍቶኛል አላውቅም ምን ማድረግ እንዳለብኝ ቤተሰቤን አላማክር ነገር እንደምታይው ነው..." አልኳት። እና ከመንገዱ ጥግ ባለው ወንበር ላይ አብረን ተቀመጥን እሷም መላ ሰውነቷን ጆሮ አድርጋ ልትሰማኝ ጓጓች።አይኖቼን አሻግሬ የተደረደሩት ላዳ ታክሲዎች ላይ ጥዬ "እድል ታውቂያለሽ ሰዎች ባለኝ እውቀት እና የገንዘብ መጠን ደስተኛ እመስላቸዋለው ግን ሰባራ ነው ልቤ ያፈቀርኳት ልጅ ዛሬ ባትኖርም ግን አሁንም ትናፍቀኛለች እኮ ምን ልሁን እድል እስኪ መርሻ መድሃኒት ስጭኝ" አልኳት። ለምን እንደዚህ እንደምነግራት አላወኩም ብቻ ስለበፊት የፍቅር ታሪኬ ስተርክላት ቆይቼ አይኖቼን ወደ እሷ መለስ አድርጌ ስመለከታት እያነባች ነው።"እንዴ እድል ምን ሆንሽ" አልኳት ደንግጬ እሷም በሹራቧ ፊቷን ጠርጋ የአንገቷን ሀብል አውጥታ አሳየችኝ እና ፈገግ ብላ ከቆየች በኋላ "ያማል በጣም" አለችኝ እጇን በደረቷ ያዝ አድርጋ መለሰችልኝ።"አውሪኝ እድል አወሪኝ እባክሽን ሰባራ ልቤን መጠገን እሻለሁ አንቺ ስትመጪ ነው ሳሎን መቀመጥ የጀመርኩት ምግብም የምበላው እና እባክሽ አውሪ እና ታሪኬን ቀይሪው በቃ ሰባራ ልቤን ይዤ ልመንን" አልኳት እሷም ተንሰቅስቃ ማልቀስ ጀመረች ደነገጥኩኝ "ስለኔ ምን የሚወራ አለኝ ኖረች እና አበደች በቂ ነው" ጣቷን እየፈተለች ትነግረኝ ጀመር።
.......💔💔💔....... ይቀጥላል.......💔💔💔
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
💐የግጥም መንደር💐በቤዛዊት የሴት ልጅ💐
🇪🇹🇪🇹🇪🇹
2025/07/05 04:27:09
Back to Top
HTML Embed Code: