Telegram Web Link
....በማርያም ስም ተጠይቄ መጨከን አልችልም እና ታሪኩን እነሆ.....😘😘

ታዲያ ቀጣይ እንዲደርሳችሁ ድምፅ ስጡ
💖🌿💖🌿💖🌿💖💐

⇣⇣ 💖ክርስቶቤል💖
⇣⇣
🍃🌹🍃.........
ምዕራፍ ሁለት

🔥ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ፨🔥

💥 💔😭ክፍል አስራ ዘጠኝ🙏


........"ኤዲ" የመኪናውን በር ከፍቼ ወረድኩኝ። ዝናቡ ልብሷን አበስብሶት ተጣብቆባታል። የአለም ውበት ስትርቀኝ ደብዝዞብኝ ነበር ልክ አይኖቿን ስመለከት ግን የአለም ውበት ደግሞ ተገለጠልኝ። "አትሂድ" ብርዱ እያንዘፈዘፋት ተናገረች። "ኤዲ ብቀር ደስ ባለኝ ግን...." አባዬ ጣልቃ ገባ" ጥጋችሁን ያዙ ብሎ ከመሀል አስፖልት አስወጣን።"ረፈደ አትበለኝ....አትወደኝም?." "አንቺን አልጠላሽም" "እና አትሂድ እያልኩህ እኮ ነው በቃ ሁሌም አብረኸኝ ሁን የነፍሴ ቅኝቷ አንተ እኮ ነህ ሲከፋኝ እና ሲጨንቀኝ የሚያደምጠኝ የለም አንተ ብቻ ነህ የኔን ስሜት የምትረዳው ከዝምታዬም ጋር የምትግባባው አንተ ነህ" ከዝናቡ እኩል እንባዋ ፊቷን እያጠበ ይወርዳል። "ኤዲ ብመለስ ደስ ይለኛል ግን አልችልም ጠልቼሽ አይደለም ከምታስቢው በላይ እወድሻለሁ ነገር ግን እኔ አንቺ ጋር ቦታ የለኝም።የአባትሽ ገዳይ ተባባሪ ልጅ ነኝ ለህመምሽ ምክንያት ነኝ " ከነበረው ፍቅሯ ሲጨመር ይታወቀኛል ግን ምን ላድርግ ሀዘኗን እኔን ባየች ቁጥር ታስታውሳለች እናም በሽታዋ መሆንን ስለማልፈልግ መራራ ውሳኔ መወሰን አለብኝ።"ጠልተኸኛል ተናደህብኛል" ብስጭቷ መጣ እንደ አራስ ነብር ተቆጥታ መናገር ጀመረች "አዎ አዝኜብህ ነበር አንተንም ቤተሰብህንም ማጥፋት ተመኝቼ ነበር ግን በቂ ምክንያት አለኝ የሞተው አባቴ እኮ ነው እህቶቼ ወንድሞቼ ያደኩት በፍቅር ተቀማጥዬ ነው ድሎቴን እኮ ነው ያጣሁት በዛ ላይ ለእውነት ስቆም ደግሜ ሰው እንዳልሆን ተደርጌ ነው ከርክመው የጣሉኝ ሰባብረው የወረወሩኝ። አንተ እናትህን ተጠምታ አይተሀታል?! አንተ አባትህን በረሀብ ብዛት የሊጥ እርሾ ሲለምን አይተኸዋል?! ንገረኝ! አላየህም እኔ ግን አይቻለሁ ምንም ማድረግ አቅቶኝ አልቅሻለሁ እብድ ሆኜ ብቻዬን አውርቻለሁ መፍትሄ አጥቼ የሰው ቤት ተንበርክኬ ለምኛለሁ የቱ ይበልጣል...አንተ የልጅነት ህይወትህ ያማረ ነው። የእኔ ግን መንገዱ አሜኬላ የወረሰው ነበር ያውም የእሳት እሺ ምን አጠፋሁ ከአንተ ብሩን ስወስድ እንኳን ከልቤ እንድትወጣልኝ ነበር ግን አልቻልኩም በየቀኑ አስብሃለሁ በቃ ራሴን መሆን አቃተኝ ታዲያ ለምን እንዳፈቅርህ አደረክ ለምን ፍቅርን አሳየኸኝ ለምን??" ተንሰቅስቃ አለቀሰች። "አባዬ እባክህ እንሂድ" አልኩኝ። ልቤ ግን እያነባ ነበር። "ቂም ይዘህ ነው አስከፍቼህ ለምን ለኔ ስትል ትሄዳለህ ካልወደድከኝ" በብስጭት ጠየቀችኝ። ስትናደድ ሌላው የውበት ገጿ ወለል ብሎ ይታያል። "ኤዲ ይቅርታ በቃ አልሆንሽም ስለይሽ የምጎዳው እኔ ነኝ ግን...." "አንዴ አድምጠኝ እና ትሄዳለህ.....በአንድ ወቅት ነው አንድ ንጉስ የታሰሩ ሰዎች ላይ ፍርድ ሊሰጥ ከሹማምንቶች ጋር ይቀርባል። እናም ወታደሮቹ አንድ አንድ ወጣት ይዘው ቀረቡ። ከወጣቱ ላይ የመንፈስ ጥንካሬ እና ፅናት ይነበብበታል ንጉሱም ምን ፈፅሞ ነው ብሎ ጠየቀ ወታደሮቹም ትናንት በአካባቢያችን በሚገኙት መንደሮች ውስጥ አስፈላጊ የሆነ ተልዕኮ ይፈፅም የነበረን አንድ የአሚሩን መኮንን አንገት ቆርጦ ጥሏል ሲያዝም እጁ ላይ ጎራዴው ነበር ብለው ለአሚሩ ነገሩት። እጅጉን ተናዶ ሰውየውን ወደ ጨለማው እስር ቤት መልሳችሁ ውሰዱት ና በወፍራም ሰንሰለት እሰሩት። ሲነጋም በራሱ ጎራዴ አንገቱን ቆርጣችሁ አውሬዎች ስጋውን እንዲበሉትና አየሩ እሱን የሚያስታውሳቸውን ጠረኑን ወደ ቤተሰቡና ወዳጆቹ አፍንጫዎች እንዲያደርሰው ሬሳውን ጫካ ውስጥ ጣሉት አላቸው። ከዛም ወታደሮቹ ሌላኛዋን ሴት አመጧት የተፈጥሮ ውበት ያላት አንዲት ወጣት ሴትን አቀረቡ። ንጉሱም"ይህች ከሬሳ አጠገብ እንደሚቆም የሞት መንፈስ የመሰለች ሴት ምን አጥፍታ ነው ብሎ ጠየቀ አንዱ ወታደርም ዘማዊ ናት ትናንት ማታ ባሏ ከሌላ ወንድ እቅፍ ውስጥ አግኝቷት ነው ለፍርድ ያቀረባት አለ። አሚሩም ወደ ጨለማ ክፍል ደግማችሁ ውሰዷት በፈፀመችው ከባድ ስህተት የተነሳ የበከለችው አልጋዋን እንድታስታውስ በእሾህ አልጋ ላይ አስተኝታችሁ እሰሯት በተሳመች ጊዜ የተሰማትን ጣፋጭ ስሜት እንድታስታውስ ሀሞት የተቀላቀለበት ኮምጣጤ አጠጧት።ጠዋት ደግሞ ሲነጋ ከከተማው እርቃኗን መሬት ለመሬት እየጎተታችሁ በድንጋይ ውገሯት ለስላሳውን ሰውነቷን ስጋ ተኩላዎች ይደሰቱበት አጥንቶቿንም ትሎች ይበሳሷቸው ብለው በየኑበት እንዲህ እንዲህ ብለው ፍርዱ አልቆ ንጉሱ ከፍርዱ ወጡ። እዛ ሁኔታዋን የተመለከተ ሰው በቀጣይ ቀን ሬሳዎች ከሚጣሉበት እርሻ ቦታ ሄደ። ከዛም አንዲት ሴት መጥታ በጎራዴ ተቀላውን ወጣት ሬሳ ቀበረችው ለምን ብሎ ሰውየው ጠየቃት።መኮንን ገድለሀል የተባለው ወጣት እውነትም ገድሏል ግን የገደለው ይህች የቀበረችውን ሴት ከመኮንኑ መጥፎ ስራ ነፃ ሊያወጣት ብሎ ነበር ለመልካም!! እሷም እንደ ሄደች አንድ ወጣት መጣ እና ዘማዊ ናት ተብላ በስቃይ የሞተችውን እንስት አፈር ቆፍሮ ቀበራት እና አበባ በተነላት። እናም ዘማዊ ናት ለምን ቀበርካት ሲለው

ለፍቅሩ ስትል በድንጋይ ተወግራ የሞተችለት ዕድለ ቢሱ ሰው እኔ ነኝ ከልጅነታችን ጀምሮ አፈቅራታለሁ እሷም ታፍቀረኝ ነበር። ያደግነው አብረን ነው እናከብረውና እናገለግለው የነበረው ፍቅራችን የልቦቻችን ጌታ ነበር። ሁለታችንንም ፍቅር አገናኘንና ነፍሶቻችንን አቆራኛቸው አንድ ቀን ከከተማ ወጣ ብዬ ዋልኩ። ስመለስ አባቷ የማታፈቅረውን ሰው እንድታገባ እንዳስገደዷት አወቅሁ ከዚያ በኋላ ህይወቴ የማያቋርጥ ትግል ሆነ ተስፋዬም ጨለመ። ልቤን አደብ ላስገዛው ብሞክርም ሊረጋጋልኝ አልቻለም። በመጨረሻም ቢያንስ በሚስጥር አይኗን ለማየት ወሰንኩ። ብቸኛው አላማዬ ውብ ዓይኖችዋን ለማየትና ለስላሳውን ድምጿን ለመስማት ነበር። ቤቷ ስደርስ ብቻዋን ሆና በእደለ ቢስነቷ ታነባለች።አጠገቧ ተቀመጥኩ.....ፀጥታ አነጋገረን.....ቅንነትም ወዳጃችን ሆነ። በዝምታ እየተግባባን ለአንድ ሰአት ያህል ከቆየን በኋላ ባሏ መጣ። ስሜቱን እንዲቆጣጠር ባስጠነቅቀውም እሱ ግን ሁለት እጆቿን እየጎተተ ወደ መንገድ አውጥቶ ዘማዊቷና ፍቅረኛዋ እነዚውላችሁ ብሎ ጮኸ ወታደሮች እሷን ወሰዷት። ደንቆረው ህግና የበሰበሰው ልማድ በአባቷ ጥፋት ሴቲቱን ቀጥተው ወንዱን ይቅርታ አደረጉለት።

ብሎት ጥሎት ሄደ።አየህ አማሩ ባላወቁት ፈረዱ። እኔም በማታውቀው ፈርጄብህ አሳዘንኩህ ይቅርታም እያልኩህ ነው አንተ ግን ደግመህ እየገፋኸኝ ነው። እኔ ስፈርድብህ ጥፋተኛ ሆንኩ አሁን አንተስ ጥፋተኛ አይደለኸም እያራከኝ ልክ ነህ?? ሰው መግደል ወንጀል ነው አሚሩ ግን ሲግድል ልክ ነው ....ዘማዊነት ነውር ብልግና ነው አሚሩ ግን እርቃኗን በመንገድ ሲያስጎትቷት ጎሽ ቆንጆ ፍርድ ይባላሉ። እኔና አንተስ? እኔ ከአንተ ስለይ ልክ አይደለሁም?? አንተ ግን እጎዳሻለሁ በሚል ሰበብ ስትለየኝ ልክ ነህ ያለህ ማነው....? ማንም......" አለች። "ኤዲ ይሄ ታሪክ ለእኔ ምን ይጠቅመኛል እኔ በስህተት አልወሰንኩም አልፈረድኩም ደግሞ አንድ ቀን ትረጂኛለሽ.." አልኳት ለመሄድ ሰአቴን እየተመለከትኩ። ኤዲም እንባዋን ዘረገፈችው "ሂድ....ሂድ ክርስቶቤል....እራቀኝ ሸሽተህ ተሰወር......ደስ ካለህ ደስ የማይለኝ ምክንያት አይኖርም.....ደስ ይበልህ.......ጎዳናው እንደ ጨርቅ ተጠቅልሎ አጥሮልህ ያስብክበት ቦታ በሰላም ድረስ......አብረን የታየንበት መንገድ አንተን እንድሸኝህ ሆኗል.....አሮጌ ቢመስልም ቃሉ ለሚሄድ
ሰው አዲስ ስለሆነ...ቻው የኔ ክርስቶቤል....." የኔን መልስ ሳትጠብቅ ፊቷን አዙራ በዝግታ መራመድ ጀመረች ቤተሰብ ጓደኞቼ በእንባ ዝናብ ውስጥ ቆመው እያዩን ነበር። የሀዘን ምሬት ከልቤ ውስጥ ወጥቶ መንገዱ ላይ እንደ ምንጣፍ ተነጠጸ።ሰአቱም እየቆጠረ ምሽቱም በፀጥታ እየተዋጠ ነው። "ኤደንንንንንን" በሀይል ጮኬ ተጣራሁኝ እና ተመለከትኳት እሷ ግን መራመዷን ቀጠለች። መንገዱን ልታቋርጥ ግራ ቀኟን ሳትመለከት መሀል መንገዱ ላይ ገባች። ጥቁር የቤት መኪና ከላይ ክፍ እንዳለው መልአክ እየተክለፈለፈ ይመጣል።"ኤደንንን" ናታን በሩጫ ወደ ኤዲ ሮጠ እግሮቼ ሽምድምድ ብለው ተወርውሬ ተቀመጥኩኝ እጆቼም ሽባ ሆነውብኝ ድምፄም ባዳ ሆነኝ ልቤ እየጮኸ አፌ ግን ተለጎመ። ከአይኖቼ ጥቁር እንባ መፍሰስ ጀመሩ። የሀዘን ሸማ ለበስኩ። ጆሮዬ የጩኸት መአት እያስተጋቡ ያሰሙኛል ጭንቃላቴ ውስጥ የምን እንደሆነ የማላውቀው ድምፅ ያቃጭላል ድምፁም ከፍ እያለ መጣ።....ጨለማው ላይ የሀዘን ድር እያደራ ዝናቡም ማካፋት ጀመረ ደመናው ግን በነፋስም አልተበተነም። የኤዲ እጆች ወደ ግራ እና ቀኝ ተዘርግተው ከሰውነቷ የሚፈሰው ደም ከውሃው ጋር ተደባልቆ እንደ አባይ ወንዝ ቁልቁለቱን ይወርዳል።......ይቀጥላል!!!

የመጨረሻው ክፍሎች

💝ክርስቶቤል💟 ደራሲ ቤዛዊት የሴት ልጅ

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ይቀጥላል፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
#ታሪኩ ቶሎ ቶሎ እንዲለቀቅ ድምፅ ይስጡ!
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
🔥 ••●◉Join us share 🔥
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
የግጥም መንደር
😍ክርስቶቤል💖
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺🌺»̶̥✽̶┉┉┄

💝ውድ አንባቢያን @yebezawit2 ላይ ስለ ታሪኩ የማሰማቹን አጋሩኝ መልሼ ወደ እናንተ አቀርባለሁ😍 አመሰግናለሁ 🙏🙏🙏
💌ከተሰጡኝ አስተያየቶች የተወሰነው ነው..
ሁላችሁንም ከልብ አመሰግናለሁ 🙏
እግዚአብሔር ያክብርልኝ። @yebezawit2 ላይ አሁንም አድርሱኝ።💌

🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
እርጉዝ ሆኜ እኔ መቆየት አልችልም" አለችኝ። "እና ታፈርጪዋለሽ ሰለቸኝ ጠላ ቤት ልሂድ ብሎ ነገር የለም" አልኳት ዶክተሩ ያጠራጠረውን እያብሰለሰልኩ። "ግን እስኪ ንገረኝ ምን አይነት አባት ነው የምትሆነው?" አለችኝ የበልጥ ልቤን እያጓጓችው። ጉሮሮዬን ጠረግ ጠረግ አድርጌ እነግራት ጀመር "ልክ ከስራ አብረን ወደ ቤት እንገባለን ያው ነፍሰጡር ስለሆነሽ እኔ ምግብ አበስላለው አንቺ ደግሞ ቡና አቀራርበሽ ታፈያለሽ ቤቱን ሞቅ ታደርጊዋለሽ ከዛ ምግብ በልተን ቡናችንን ጠጥተን እኔ ዕቃ አጥባለሁ ከዛ ጌማችንሰ እናጫወት እና እግርሽን አጥቤሽ በጊዜ ትተኛለሽ።" በረጅሙ ስቃ ወሬዬን አቋረጠችኝ። "ህልመኛው ልጄን እንዲሁማ አልሰጥህም" የኤዲ እናት ነበሩ። ደነገጥኩኝ "ከእኔ ጋር አትኖሪም እማዬ" ኤዲ ጉዳዩን አምርራ እናቷን ጠየቀቻቸው "ከአንቺ ከልጄ የት እሄዳለሁ" አሏት። ዙቤይዳ ገርበብ ባለው በር ገባች። ለቤተሰቦቿ ትቻት በሩን ዘግቼ ወጣሁኝ። የእውነት ለኤዲ ስነግራት እጅጉን ልቤ በደስታ ብርሃን ይሰወር ነበር። ደስተኛ ህይወትን ከኤዲ ጋር......"አባዬ ኤዲን ላገባት ነው ማለቴ" አባዬ ተጠመጠመብኝ። "ግሩማችን በስተመጨረሻ" ጓደኞቼም አቀፉኝ። "መቼ ነው የምትጋቡት" እማዬ በደስታ ጠየቀችኝ።" ከዚህ ስትወጣ" አልኳቸው ሁሉም ደነገጡ። "ምን ተይዞ" አባዬ ነበር።"ኤዲ ውርሱን ተቀብላለች" አልኳቸው። ሁሉም የደስታን እንባን አነባ። ከረጅም ጊዜያት የልፋት እና የመከራ ቀን ለሊቶች በኋላ አይኔ መልካሙን ተመለከተ ልቤም ማፍቀር ቻለ.......አዲስ ህይወት አዲስ አለም........እሌኒ ኤዲን ተክታልኝ ነው የሄደችው። ከእሷ ጋር የህይወት ዳገት ልወጣ ልቧ መርጦኛል የለመንኩት ሆኖልኛል የእሷ ሊያደርገኝ በዘላለም ቃል በቅዱስ ጋብቻ ሊያፀናኝ ነው። ታግሼ አፍቅሪያታለሁ ስትርቀኝ ከጎኗ ቆሚያለሁ ስታጠፋ አልፊያታለሁ ሳጠፋ ምራኛለች እሷ እብድ ናት እኔ ደግሞ የእሷ አብሮ አብድ ሆኜ ልኖር ነው። የማላውቀው የደስታ ስሜት ወሮኛል። "እሄዳለሁ ስትል ጎርረህ" ዘኪ ሳቀብኝ። "እኮ ለነገሩ ከዚህ በኋላ አቶ ነው የሚባለው" አለ ናታን። ያ የህመም ልጅነቴ በኤዲ ዕድሜ አገግሟል አሁንም ጉዞዬ በኤዲ ደም ለዘለዓለም ተሽሯል።"ቀለበት ባስርላትስ?" አልኳቸው። እማዬም ፈገግ ብላ አየችኝና "ታውቃለህ እኔ በእነዛ እህቶችህ ለምን እንደምበሳጭ ስለዚህ አድርግላት ደግም ቆንጆ ናት ስትወጣ ሰዎቹ በዝተው እንዳይሰርቁህ የኔ ናት ብለህ አውጅ" አለችኝ በደስታ የአባዬን እጅ ያዝ አድርጋ። የእነ አባዬን ፍቅርን ተመኘሁ። ዳድ እና ማሚ ሲጣሉ እንኳን በፍቅር ነው እናቴ እጅጉን ተናዳ ስትናገር ዳድ ግን ቃል አይወጣውም የሚገርመኝ ግን እራሱ ሄዶ ነው ይቅርታ የሚላት እናቴም ብትሆን ከአባቴ ጋር ከተጣላች ምግብ አትበላም ስታለቅስ ትውላለች እንጂ ይቅርታ አጠይቀውም አባዬም ስለሚረዳት ይቅርታዋን ሳይጠብቅ ነው ይቅርታ የሚጠይቃት የእማዬ ጉድለት ይቅርታ አለመጠየቅ እና ብስጭት ነው። ይሄን ጉድለቷን አባዬ ይቅርታ በመጠየቅ እና በዝምታ ያሸንፈዋል። የአባዬ ጉድለት ደግሞ ሲከፋው በመጠጥ መደበቅ ነበር እናቴም ሸፍናለታለች ሲከፋውም ሲጨነቅ ከፊቱ አንብባ ከመጠጥ ይልቅ ቤት ውስጥ ምግብ አብስላ ቡና አፍልታ ታሸንፈዋለች። ደስ የሚል የምወደው ቤተሰብ አለኝ። እኔም ቤተሰብ ልመሰርት ነው ልክ እንደ እነ አባዬ።
"ቀለበቱን ገዝተን እንምጣ" ብዬ ከጓደኞቼ ጋር ወጣን በር ላይ ያዕቆብ የመኪና በሩን ተደግፎ ቆሟል። "እንዴት መጣህ" አልኩት በማየቴ ተደንቄ። "ፋዘር ናቸው ቅድም የጠሩኝ ደህና ናት ፍቅርህ" አለኝ። ያዕቆብ እጅግ የተረጋጋ ማንነት ያለው ሰው ነው። አባዬ እንደ ልጁ ነው የሚመለከተው የእውነትም የሚወደድ ሰው ልክ ካልሆንን ከስራ ቢባረርም ሳይጨንቀው ስህተታችንን ይነግረናል። ቅድምም በፍጥነት እኩል ሆስፒታል ሲደርሱ ገምቼ ነበር የያዕቆብ ቤት እዛው አካባቢ ስለሆነ።...."ወርቅ ቤት ውሰደን ደህና ናት" አልኩት ተጣድፌ ወደ መኪናው እየገባሁ ያዕቆብም ደስታዬን ከፊቴ አንብቦ "እንኳን ደስ አለህ..." አለኝ። "ላገባ ነው የማፈቅራትን ሴት ሁሌም አይኗን ላይ ነው ከጎኔ ቆማ ሰው ሁሉ ሊያያት ነው" የደስታ ውሃ በራሴ ላይ ፈሰሰ። "ይቅርታ በል መጀመሪያ" አለኝ ያዕቆብ። "ለምን ላገባ ነው እኮ ነው ያልኩህ" አልኩትኝ የሚለኝ ግራ ገብቶኝ እሱ ግን ይቅርታ እንድጠይቀው አጥብቆ ሞገተኝ። እኔም ክርክሩን ለመቋጨት "ይቅርታ" አልኩት። ፈገግ ብሎ "አየህ ያለምክንያት ያለጥፋትህ ይቅርታ ጠየከኝ ትዳርም ውስጥ ያለበደለህ ይቅርታ መጠየቅ አለብህ እና ይቅርታ መጠየቅን መለማመድ አለብህ.....ይኸው ወርቅ ቤቱ ግን ዝግ ነው ገና11:00 ነው" አለኝ ያዕቆብ ሁሌም ያስደንቀኛል። ወርቅ ቤቱ እስከሚከፈት ድረስ አዛው ተቀምጠን መጠበቅ ጀመርን። ያዕቆብ በመኪናው የከፈተው ሙዚቃ እያዳመጥን ሰአቱን መጠበቅ ጀመርን....ሙዚቃው በጆሮአችን ይንፎሎፎላል። አንዲት ቀይ ወፍራም ሴት መጥታ ወርቅ ቤቱን ከፈተችው እኔና ጓደኞቼ በሩን እንኳን በደንብ ሳትከፍት ፊቷ ቆምን ደንግጣ ነበር የተመለከተችን። "የሚያምር በጣም ለውብ ሴት የሚሆን ቀለበት ስጭን" አልናት። መቸኮላችን ገርሟታል የወረቅ አይነቶችን ፊታችን ደረደረቻቸው። ሁሉም የአይን አዋጅ ነበር። ዘኪ "ይሄ ነው የሚያምረው" ብሎ እኔ ናታን ያላየነው ውብ ቀለበት አሳየን ብሩን ካርድ ከፍለናት ወጣን ናታንም " ለምን ኬክ አንገዛም ደስ ይላታል አንተም ልብስህን ቀይር" አለኝ። ሰርጌ ሆነ የኔ አለም!! የዚህ ሁሉ ውክባ የዚህ ሁሉ ደስታ ምክንያቷ የኔ ሴት ኤዲ ናት ልብስ ቤት ስናካልል ቆይተን እዛው ቦሌ አካባቢ ካለ ዜድ ፋሽን ቡቲክ ገዛን። ነጭ ቲሸርት በጥቁር ሱሪ ለበስኩኝ እና እላዬ ላይ የደረቀውን ልብስ ፌስታል ውስጥ ከተትኩት። ገና እየከፈቱ ካሉት ኬክ ቤት ገብተን ተጨማሪ ክፍያ ከፍለን ሰው ያዘዘውን ኬክ ይዘን ወጣን። የጓደኞቼ ልፋት ደስታ የእውነት የፈጣሪ ስጦታዎቼ ናቸው።"ለእናቷም የሆነ ነገር ስጧቸው አበባም ያዝ።" አለኝ ያዕቆቤ። "ብቻ ግን ኤዲ እንደ ድሮ ተለውጣ አላገባህም ብትል እንዴት እንደማለቅስ" አለኝ ናታን ለእናቷ የሚሆን ስጦታ ከመደብሩ እየፈለግን። "ሞርተኛ አንተ ቆመህ ስለቀረህ ነው" ብሎ ዘኪ ሰደበው። ከመደብሩ የሚሆን ዕቃ አጥተን በእግራችን እየተዘዋወርን የከበሮ ድምፅ ከሩቁ ተሰማኝ። "የት ነው?" አልኩት ለያዕቆብ ሰፈሩን በደንብ ስለሚያውቅ። "መድሀኒአለም ነው ምነው" አለኝ። ለእናቷ የምገዛውን ዕቃ አገኘሁ።.........

ኬክ ወይን አበባ እና ለእናቷ ስጦታ ይዘን ወደ ሆስፒታሉ ተመለስን። በእግራችን ህንፃ ለህንፃ ስንዋከብ ላየን የጠፋ ዶሮ የምንፈልግ ነበር የምንመስለው ስንበተን ከዛ የሚረባ ነገር አጥተን ስንሰባሰብ.......ሆስፒታሉ ግቢ ውስጥ ስንደርስ ከመኪናው ወርደን ከያዕቆብ እና ከጎደኞቼ ጋር ወደ ውስጥ ገባን የኤዲ እናት እና ቤተሰቦቼ አብረው ተቀምጠው በሳቅ እያወጉ ነበር። ይሄ ሳቅ ሊሰፋ መሆኑን ሳውቅ እኔም በደስታ አበራሁ። "ለምን ወጣችሁ?" አልኳቸው። "ዶክተሮቹ ኤዲን ለሁለተኛ ጊዜ እየተመለከቷት ነው" አሉኝ ዶክተሩ ያለኝ ትዝ ብሎኝ ደስታዬ ግማሽ ጨረቃን መሰለ።...........


.....ዶክተሮቹ እያወሩ ተክተልትለው ወጡ እኔም የእነሱን መውጣት ተከትዬ ወደ ውስጥ ገባሁ ኤዲ ደገፍ ብላ ተቀምጣ ነበር ከኋላ የቀረችው ነርስ አልጋ ልብሱን አልብሳት ወጣች። "አባት የት ጠፍተህ ነው?" አለችኝ እንደ እናት እየተመለከተችኝ። እኔም አይኗን ስሜ "እዚሁ የበርኩ ቁርስ በላሽ"
አልኳት ውስጤ የተጫረው ጥርጣሬ ለማስወገድ። "አዎ በላሁ" አለችኝ። እኔም አጠገቧ ያለውን ሻርፕ አንስቼ አይኗ ላይ አሰርኩት"አንተ ክርስቶቤል ምንድነው ልታስጮኸኝ ነው" አለችኝ።......እነ አባዬ ወደ ውስጥ ገቡ ኬኩን ከፍቼ ምግብ የምትበላበት ጠረጼዛው ላይ አስቀመጥኩት። አበባውንም ከጎኑ። ሁሉም ከቧት ይመለከታታል። እሺ እንደምትለኝ ልቤ አምኖ እንዳልሰከረ አፌ ተሳሰረ ምን ብዬ እንደምጀምር ጠፋኝ። ናታን ተመለከትኩት ወደ ጆሮዬ ተጠግቶ "የሚሰማህን ንገራት" አለኝ። የሚሰማኝን ካወራሁ ቀለበቱ በእጇ ላይ አይኖርም ምክንያቱም ለእሷ ያለኝ ፍቅር በዘመን ብዛትም ተገልፆ አያልቅም። እማዬ በደስታ እያነባች ስልኳን አውጥታ እየቀረፀች ነው። ማን እንደነገራቸው ያላወኩት ነርሶች እና ዶክተሮችም በሩ ላይ ቆመዋል። ጉሮሮዬን ጠርጌ ከፊቷ ተንበረከኩ "እናት....ስለ አንቺ ምን እንደሚሰማኝ....." ኤዲ ሻርፖን ከአይኗ ላይ አወረደች። "ምንድነው?" በድንጋጤ መሳቅ ጀመረች። "ጠዋት ከእንቅልፌ ስነሳ ከጎኔ ላይሽ እፈልጋለሁ። ማታ ወደ ቤቴም ስገባ አንቺን ማየት እፈልጋለሁ በምውልባቸው ቦታዎችም አንቺን ይዤ መታየት እፈልጋለሁ በቃ ሙሉ ህይወቴን ከአንቺ ጋር መኖር እፈልጋለሁ.....አንቺ ለእኔ ህዝቡን እንዳሻገረው ሙሴ ነሽ ከትላንት ህይወቴ በፍቅር አሻግረሽኛል። እወድሻለሁ ኤዲ አግቢኝ....." በመከራ ቃሉን ቋጨሁት። ሳቅ ለቅሶ ሁሉም ተደበላለቀባት........."ያንቺ ክርስቶቤል ብቻ ልሁን" አልኳት። ይበልጥ ሳቀች እናቷም ያለቅሳሉ ጓደኞቼም ያነባሉ። እኔና ኤዲ ያለፍናቸው የስቃይ መንገዶች መጨረሻቸው ይሄ ሆኗል። "የኔ ክርስቶቤል ነህ አፈቅርሃለሁ" በደስታ ዘለልኩኝ። "ኧረ ቀለበቱን" ሲሉኝ ነው መዝለሌን ያቆምኩት። በውብ ቀለበቷ ላይ ቀለበቱን አጠለኩላት። ልክክ አለባት። ግምታችን ልክ ነበር። አቅፌ ሳምኳት። ያዕቆብ በስልኩ ሙዚቃ ከፈተ ትክክል የሆነ ለኔ ስሜት የተዘፈነ የሚመስል ሙዚቃ......


በደስታ እንዲኖር ሰው በዚህ አለም ላይ
ፍቅር እንደሆነ ከምንም በላይ
ውስጤን ያሳመነው
አንቺን ማግኘቴ ነው።
💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕
ሲተረክ ሲወራለት በሰው አፍ ሲነገር
የማውቀው እስከዛሬ ፍቅርን በስም ነበር።
ዛሬ ግን ከነፍስሽ ጋር ነፍሴ ስትዋሀድ
አንቺው ውስጥ ይኸው ፍቅርን አየሁት በገሀድ።
🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
ላንቺ ምንስ ቢባል ቃላት መች ይበቃል
እንኳንም ተፈጠረሽ ልበልሽ በአጭር ቃል
🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇
እንድኖር ያደረገኝ ደስታን አጣጥሜ
ፍቅርሽ ነው ሌላ አይደለም ልንገርሽ ደግሜ
ኧረ እንዴት ልግለፅልሽ ቃላት አጣ አንደበቴ
መውደዴ አቅሜ ነው በየዕለት ህይወቴ
💐🏡🏠🏡💐😘😘💐🏡🏠🏠🏠🏠🏡🏡
ለአንቺ ምንስ ቢባል ቃላት መች ይበቃል
እንኳንም ተፈጠረሽ ልበልሽ በአጭር ቃል
🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟

ኬኩን ቆረስነው እና ለእናቷም ስጦታ ሰጠኋቸው የአማኑኤልን ምስለ ስዕል ነው።.......የአማኑኤል ስጦታዬን በእሳቸው በኩል ስላገኘው ነው።.....ኬኩን በልተን በደስታ እየተሳሳቅን ሰአቱም ነጉዶ አመሻሽ ላይ ደርሷል። ኤዲ ስለደከማት ተኛች። እኛም ከክፍሉ ወጥተን እንግዳ መቀበያው ጋር ተቀምጠን እያወጋን ነበር። "እንኳን ደስ አላችሁ" አለንዶክተሩ ። "እናመሰግናለን" አልኩት። ወዲያው ግን ፊቱን አጠቆረው ሁላችንም ደነገጥን.......

🌟🌟🌟የመጨረሻው ክፍል ሶስት ሰአት🌟🌟🌟

💝ክርስቶቤል💟 ደራሲ ቤዛዊት የሴት ልጅ

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ይቀጥላል፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
#የመጨረሻ ክፍል እንዲለቀቅ ድምፅ ስጡ!
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
🔥 ••●◉Join us share 🔥
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
የግጥም መንደር
😍ክርስቶቤል💖
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺🌺»̶̥✽̶┉┉┄

💝ውድ አንባቢያን @yebezawit2 ላይ ስለ ታሪኩ የማሰማቹን አጋሩኝ መልሼ ወደ እናንተ አቀርባለሁ😍 አመሰግናለሁ 🙏🙏🙏
😰😰😰ክርስቶቤል የመጨረሻው ገፅ😰😰😰
💖🌿💖🌿💖🌿💖💐

⇣⇣ 💖ክርስቶቤል💖
⇣⇣
🍃🌹🍃.........
ምዕራፍ ሁለት

🔥ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ፨🔥

💥 💔😭የመጨረሻ ክፍል 😭💔


ኬኩን ቆረስነው እና ለእናቷም ስጦታ ሰጠኋቸው የአማኑኤልን ምስለ ስዕል ነው።.......የአማኑኤል ስጦታዬን በእሳቸው በኩል ስላገኘው ነው።.....ኬኩን በልተን በደስታ እየተሳሳቅን ሰአቱም ነጉዶ አመሻሽ ላይ ደርሷል። ኤዲ ስለደከማት ተኛች። እኛም ከክፍሉ ወጥተን እንግዳ መቀበያው ጋር ተቀምጠን እያወጋን ነበር። "እንኳን ደስ አላችሁ" አለንዶክተሩ ። "እናመሰግናለን" አልኩት። ወዲያው ግን ፊቱን አጠቆረው ሁላችንም ደነገጥን "እእ ይሄን ስላችሁ እያዘንኩ ነው....የኤደን ጭንቅላት ውስጥ መውጣት ያለበጥ ኢጢ አለባት" ብሎ የደስታዬ እሳት ላይ ቀዝቃዛ ውሃ ቸለሰበት።"ይሄን በምርመራ አረጋግጠናል ካልወጣ ግን ለእሷ ጤና አሳሳቢ ነው ይሄን ስላችሁ ግን እያዘንኩ ነው" አለን። "እሺ ምን እናድርግ ልጄ ብትሞትብኝስ" አሉ እናቷ በድንጋጤ።"እማማ ያው ለማዳን የሚደረግ ነውና መልካሙን ማሰቡ ይበጃል።" አላቸው። "በዛ ላይ ለህክምናው ተጨማሪ ክፍያ...." "ምንድነው የምትለው ዶክተር እንዴትም አድርጋቹ አውጡት የልጄ ሚስት እኮ ናት" አለ አባዬ ቱግ ብሎ። "ምን ትጠብቃለህ መደረግ ያለበትን አድርግ እኛም እንከፍላለን ልጅቷም ባለሀብታም ናት" አለ ዘኪ። ዶክተሩም "ፊርማችሁ ያስፈልገናል ነገ ቀዶ ህክምናውን ማከናወን እንችላለን። ጎበዝ ዶክተሮች ይመጣሉ....ያው ፊርማው የግድ ስለሆነ ነው" አለን። "ፕሮፌሰር ከበደ የሉም እንዴ?" አልኩት። ዶክተሩም "እሳቸው መቼ እንደሚመጡ ስለማይታወቅ በሌሎች ዶክተሮች ይደረግላታል።" አለኝ። ፕሮፌሰር የእኛ ወዳጅ ናቸው አባዬ ደጋግሞ ሲደውል ስልካቸው ዝግ ነው። የሚያውቃቸው ዶክተሮችን ደውሎ አማከራቸው እና የቀረበውን ውል ፈረምን። ኤዲ ቀዶ ህክምናውን እንድታደርግ። አይኖቼ ግን የሚያጧት ይመስል እንባን ያፈሳሉ።ጓደኞቼ ነገ እንደሚመጡ ነግረውኝ ከእማዬ ጋር ወደ ቤት ሄዱ እኔ አባዬ እና የኤዲ እናት ቀረን። ክፍሏ ገብተን ምግብ አብልተናት እኔ ሶፋው ላይ ተኮራምቼ ተቀመጥኩኝ። የፊታችንን መለዋወጥ ኤዲ ተመልክታ የሆነ ነገር እንደተፈጠረ አውቃለች ግን ማወቅ ስላልወደደች ተጠቅልላ ተኛች። እናቷም በዝምታ እንባቸውን ይዘረግፋሉ። ወደ ሰማይ ያንጋጥጣሉ።እኔም ፈርቻለሁ እየታገልኩ ይሁን እየተሰቃየሁ ግራ ገብቶኛል። ሁለት ወዶ አይሆንም መኖር የፈለገ ሰው ግድ መታከምን ይመርጣል እና እኛም መርጠናል......አላውቅም ግማሽ ልቤ ጎበዝ ዶክተሮችን እና እግዚአብሔርን አስቦ ይበረታል ግማሽ ልቤ ግን የብርሃን ፋኖሴ ብትጠፋስ እያለ ነፍሴን ያውካታል......ተሰባስበን እንዳልተደሰትን ተለያይተናል ተራርቀናል.....ያ ፍቅር የሀዘን ጥላ አጥልቶበት የሌለ መስሏል....

........ፀሀይ ከተሰወረችበት ብቅ ብላለች እኛ ግን ሳንተኛ ነው ያነጋነው። ኤዲ ግን ተኝታለች። ከሶፋው ላይ ተነስቼ ልወጣ ስል ሁለት ነርሶች መጡ "ምንድነው የተፈጠረው አሁን ንገሩኝ" አለች ኤዲ ነርሶቹን ተመልክታ። ፊቷ ጭር ብሏል ውበቷ ደብዝዟል ሳቋ ተሸሽጓል ለሊትም ስታቃስት ነበር ያደረችው.........
"አትጨነቂ እናት ትንሽ...." እንባዬ ቀደመኝ። "ምንድነው?" ደግማ ጠየቀችኝ። "የቀዶ ህክምና ስለሚያስፈልግሽ ነው ቀላል ነው" አልኳት ህመሜን ዋጥ አድርጌ። "ወደ ቤት ውሰዱኝ" አስደነገጠችኝ።" ለምን ቀላል ነው አትፍሪ እግዚአብሔር አለ የኔ ልጅ" አሏት እናቷ "አይ ውሰዱኝ ምግብም አብሉኝ እርቦኛል የዶክተሮቹን ወሬ አትስሙ" አለች አይኖቿ እንባን አቅረው።" ምንም አያሳስብም ተጨማሪ መረጃ ይሰጡሻል ከዛ ስትወጪ ትበያለሽ" አላት አባዬ። እያረጋጋት። ኤዲ ግን አሻፈረኝ አለች።ነርሶቹ እና ዶክተሩ አስረዷት።"ኤደን በጭንቅላትሽ ያለው ኢጢ መውጣት አለበት። አሁን የሚመጡት ዶክተሮች ለመጀመሪያ ጊዜ ተሰባስበው የሚሰሩት እድለኛ ነሽ እናም አጋጣሚውን ተጠቀሚ ደግሞ ከዚህ ስትወጪ የወደድሽውን የናፈቅሽውን ሰርግሽን ታደርጊያለሽ። ለዚህ ደግሞ ጤናሽ ዋስትናሽ ነው እና አስቢበት" አሏት እሷም "የኔ ጤና ቤተሰቦቼ ናቸው አትቅደዱኝ አባዬም እንኮን ይፈራል እንኳን እኔ ስለዚህ ተዉኝ" አለች። ዶክተሩም "ኤደን ቤተሰብሽን ተመልከቺ አንቺን ላለማጣት እኮነው እየደከሙ ያሉት" ብሎ ወጥሮ ሞገታት። እሷም ለእኛ ስትል በተስፋ ማጣት ተስማማች።እኔን እያየች "ምንም ብሆን እናቴን አደራ እንዳትሰለችህ።" አለችኝ። "እናት እንደዚህ አትበይ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው አማኑኤል ያውቃል" አልኳት የነገሮች መጣደፍ እየደነቀኝ። የሆነ ደራሲ እንደፈለገ እያዘዘ የሚፅፍ እና የሚመራን መሰለኝ ግን አይደለም ይሄ የኔ ህይወት ነው።....ኤዲ ቀኑ ሙሉ ምግብ ውሃ እያለች ቆየች..."አባት ግን የመጀመሪያ ልጄን ማን እንደምላት ታውቃለህ?" አለችኝ። እኔም "ንገሪኝ" አልኳት። "በእምነት ነው የምላት ብቻ ድኜ ልውጣ" አለችኝ..."ማያዬ ትድኛለሽ አንቺ አይኔ ነሽ አትጎጂም አታስቢ" አልኳት ፀጓሯን አየዳበስኩ። ጠጋ ብላ ከንፈሬን ሳመችኝ ተመለከትኳት በቀኝ አይኗ ብቻ እንባን አፈሰሰች.....ነርሶቹ ሊወስዷት መጡ..................ኤዲም እጄን አጥብቃ ይዛ "እባክህ አስወጣኝ እኔ የምፈልገው መኖር ነው አልተርፍም ከገባሁ......ጥቁር መጋረጃ ሲጋረድ አይቻለሁ" አለችኝ በፍርሃት እያነባች በሌላኛው እጇ የእናቷን ፊት ዳበስ አድርጋ "የኔ እናት እወድሻለሁ ራስሽን ጠብቂ" አለቻት። ቃላቶች የማትመለስ ይመስሉ ነበር። የቅድሙ እመለሳለሁ ብላ የጀገነችበት ወኔዋ የለም.....እንደማትመለስ ብቻ ታወራለች......ባስቀራት ተመኘሁ.....ግን ለዘለዓለም ከማጣት ለሰአታት መታመምን መረጥኩኝ.....ወደ ቀዶ ህክምናው ክፍል አስገቧት አንድ ሁለት እያለ መቆጠር ተጀመረ እማዬ ጓደኞቼ ያለማቋረጥ ይደውላሉ። ዶክተሮቹ ገብተው ቆዩ የሚወጣም የሚገባም የለም እንቆራጠጣለን። ሰአቱ ይነጉዳል.....ይከንፋል....ይበራል....ለምን እንደሆነ ሳይገባኝ ልቤ በትዝታ ይጎትተኛል።...... እማዬም ባያስችላት ጓደኞቼም ቢጨንቃቸው መጡ። ግን ምንም የሚነግረን ሰው የለም። እማዬ እየተርበተበተች የኤዲን እናት ታፅናናለች። ድንገት በሩ ተከፍቶ አንድ ነርስ ወጣ "ኤዲስ ኤዲ" አልኩት ነርሱ ደንግጧል። ከፊታችን የሚመጡትን ነጭ ጋውን የለበሱ ሰውዬ ተመልክቶ ወደ ሰውየው ሮጠ ፕሮፌሰር ከበደ ናቸው። "ፕሮፌሰር ችግር ተፈጥሯል" ነርሱ ሲነግራቸው ሰማሁ። ፕሮፌሰሩ በዝምታ ራመድ ራመድ ብለው ወደ ቀዶ ህክምናው ክፍል ገቡ ነርሱም ተከተላቸው። ፀጥታ ሰፈነ....ዝም....ረጭ......ፀጥ.....ጭጭ


.......ፕሮፌሰሩ አንገታቸውን አቀርቅረው ወጡ። አባዬ ያዛቸው "እንዴ ከየት ተገኘህ ትልቅ ሰው" አለው አባዬን። አባዬም "የልጄ እጮኛ ናት ውስጥ ያለችው እንዴት ሆነች..?" አባዬ ጠየቃቸው። "ያንተ ቤተሰብ ናት። አዝናለሁ..." አንገታቸውን አቀረቀሩ። በሩን በርግቼ ወደ ውስጥ ዘልዬ ገባሁ ሁለት ወንዶች ይዘው አስወጡኝ። ዶክተሩ መነፅሩን እያስተካከለ ወጣ። "ንገረን ዶክተር...." "አዝናለሁ ማትረፍ አልቻልንም" ብሎ እንደ ቀልድ አረዳን ዘልዬ አንቄ ያዝኩት "ገደልካት አይደል አድናታለሁ አውቃለሁ ብለህ ገደልካት እናትን ቀማኸኝ።....." አስለቀቁኝ። የኔዋ ኤዲ እራበኝ አብሉኝ ጠማኝ አጠጡኝ እያለች በለቀሶ ተማፅናን ጥላን ሄደች።እያየኋት የኔ ፀሀይ ተሰወረች። ሙሉ ሰውነቷን አንሶላ አልብሰው አስወጧት። አስቆምናቸው።
እንዳያሳዩኝ ለመንኳቸው እነሱ ግን አይሆንም አሉኝ። የኤዲ እናትም ሆስፒታሉን በጩኸት አቀለጠቱት በዋይታ በጩኸት ልመልሳት ተጣራሁ ህልሟን በህልሜ ላይ አጣምራ ደስታን ሸምና አልብሳኝ ሄደች። ራቀችኝ....."እናት ተነሺ እባክሽ ባለዕዳ አታድርጊኝ የምትወጂውን ምግብ እንበላለን ጠላ ቤት እንሄዳለን.....እሺ በቃ እቤት ስንስቅ እንውላለን....ኤዲ አትጨክኚ......ያለአንቺ ምን ኖሮኝ ነው.......ሰብስበሽ አትበትኚን......ተነሺ....አትሂጂ ህይወቴን ያለአንቺ አልግፋ እባክሽ ንቂ....." ዝምታ ብቻ ነው መልሱ። "አድባሬ ነይ ቡና ላፍላልሽ....አባትሽ እኮ አይጠቅምሽም....ሀብት ያለ አንቺ ምን ሊረባኝ የእኔን ህይወት ለማሳመር እየጣርሽ በሽታሽን ሳታውቂ ኖርሽ አይደል...." እናቷ ይለምኗታል።"እኔ ነኝ በደለኛው እኔ ልሙት እኔን ምረሽ አንቺ እንዴት አስቻለሽ" አባዬ ይንሰቀሰቃል ነርሶቹ። ወሰዷት......የኔን ፍልቅልቅ ከእኔ አራቋት.......የኔዋን አኩራፊ ወሰዷት......የኔ እብድ የህይወቴን ኮከብ ሸፈኗት.........

በቃ አላውቅም ህመም ብቻ ነው የሚሰማኝ የምኖርበት ነገር አይጥመኝም። የኤዲን ሰውነት በጠባብ ሳጥን ወስነው ሰጡን እንደማትጨክን ስለማውቅ ሳጥኑን ደበደብኩት ግን ዝም አለችኝ ራበኝ ጠማኝ እያለች የኔ ከርታታ ነጠቁኝ ወሰዷት። ሰማይ ደርሼ ምድር ብፈርጥም ልመልሳት አልቻልኩም።......... ጥቁር የለበሰ ሰው መካነ መቃብሩን ከቦታል ኤዲን ከአባቷ አጠገብ አሳረፏት......እሷ ከአፈሩ....እኔ ከአፈሩ በላይ......ጠጋ ብዬ ቀዩን አፈር ዘገንኩኝ። "እናት አልቻልኩም ለማን እንደተውሽኝ አላውቅም ሳቄም ደስታዬም ሀዘኔም ድሎቴም ከአንቺ ጋር አብሮ ይቀበር። በቃ በሰላም እረፊ እኔም
እመጣለሁ።ግን እንዴት ልሁን ትናፍቂኛለሽ.....ምን ላድርግ.....ወዴት ልሽሽ.....ያየኝ አይንሽ ተከደነ....ያሳቀኝ ጥርስሽ ተደበቀ.......የሰማኝ ጆሮሽ ተዘጋ.....የመራኝ እግርሽ ደረቀ.....ያቀፈኝ ክድንሽ የዳበሰኝ ጣትሽ ተዘርግቶ ቀረ........









ያንቺ ብቻ ክርስቶቤል ነኝ። አፈሩን በተንኩባት። መቃብሩም አፈር ለብሶ ተዘጋ.......ህልሜ ቅዠት ሆኖ ቀረ።ሁሉም ከቤቱ ተከቷል እኔ ግን አልቀርም ጨለማ ከምትፈራው ኤዲ ጋር መቅረት አልችልም። ከመቅፅበት ነገር ተለውጧል ተገነባ የመሰለው ፈርሷል......በቃ አክትሟል.....እሷን ማፍቀር እና መጠበቄ ግን አይቅርም......የኤዲ እናትም ታመው ከአልጋ ሆነዋል....የኔም ልብ ታሞ ሞቷል.....የሙታን ኑሮ መግፋት ተገደናል....ትዝታም ቤቱን ሰርቶብናል....ናፍቆትም ድሩን አድርቷል....ማያዬ ሄዳለች ጨለማ ነው የሚታየኝ....በቃ የእሷ ክርስቶቤል ነኝ...እሷ የለችም እኔ ግን አለሁ....ፍቅር ይቀጥላል.....


💔💔💔ተፈፀመ💔💔💔
ክርስቶቤል 🌟ደራሲ ቤዛዊት የሴት ልጅ🌟
🏡🏡🏠🏡🏡🏠🏡🏡🏡🏠🏠🏠🏠🏠
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch


ምን ተሰማቹ?? 😭💔🙏
@yebezawit2 ላይም 💌 ፃፉልኝ
ነገሮች በአንዴ ይለወጣሉ ፍቅር ግን በነገሮች ይፀናል....ከፍቅር ጀርባ አሳዛኝ ገፆች አሉ....ግን ይሄም ፍቅር ነው ለኤዲ መታመን ለእሷ መሞት...ፍቅር ነው መቸኮሌ ይፀፅተኛል....ግን በፍቅር ከትባ ያኖርችልኝ ትዝታዋ አለኝ እንደ ክንዷ የሚያሞቀኝ እስካርፕ አለኝ በሌለችበት ሞገስ የሚሆነኝ ውበት የሚሰጠኝ #ሀብሏ አለኝ........
አቡሻ(ክርስቶቤል)
ከእናንተው የመጡ........

ዘረሰናይ..ቤዚ ኤዲ ለምን ሞተች አልልሽም አቡሻ ግን ለምን ስቃይ በዛበት አመመኝ የእውነት እንደዚህ ያስለቀሰኝ ታሪክ የለም ጀግና መሆንሽን ግን አረጋግጠሻል...

ሂዊ የእውነት ምን እንደሚሰማኝ አላውቅም ኤዲን ለምጃት ነበር በየሰአቱ ደጋግሜ አነበው ነበር አላውቅም ቃላቶችሽም ልቤን ይዘውት ይሆናል ከፍቶኛል..😭

ሶስና...መጀመሪያ ሳላደንቅሽ አላልፍም ትችያለሽ። ግን መጨረሻው ልቤን ሰበረው ቀለበት አሰረላት ስትይ ልጅ እንደምትወልድለት ስትነግረው በጣም ደስ ብሎኝ ነበር ግን አልሆነም አዝኛለሁ እንደዚህም ሆኖ ግን ያምራል ጀግና ነሽ።


አማን የቦሌ....ጨካኝ ሰው ነሽ በአቡሻ ላይ እንዴት ጨከንሽ ታሪክሽን በጣም እወዳቸዋለው #ያልተረኩት_ታሪክ እንደሚለው ድርሰትሽ ነበር መጨረሻውን የጠበኩት ለቤተሰቦቼ አነብላቸው ነበር የዛሬው ግን አስለቀሰን...ጨከንሽ በጣም

ሃዊ...ሳለቅስ ነበር የማነበው ምን አይነት ችሎታ እንደተሰጠሽ አላውቅም...እህቴን ኤዲ ውስጥ አያት ነበር እህቴ ከሞተች ሰባት አመት አልፏታል ዛሬ ኤዲ ስትሞት በቃ ያወቅሽኝ ያህል ተሰማኝ እህቴም የሰርጓ መዳረሻ ሰሞን ነው በልብ ድካም የሞተችው እና ያንን ጊዜ አስታውሰሽኛል አመሰግናለሁ...

ኪራ...የኔ ታሪክ ነው ቤዚ በእርግጥ የማፈቅራት ሴት ባትሞት ጥላኝ ሄዳለች ህመሜን የታጋራሽኝ ያህል ተሰምቶኛል ቀጣይ ቶሎ ታሪክ ጀምሪ

ልዩ...ቤዚ የራጉኤል ልጅ አናደድሽኝ አበሳጨሽኝ አስለቀሺኝ ጭራሽ ምን ተሰማችሁ አልሽን እኔ እራሴን ጠላሁት የምወዳቸው ሰዎች ሲሞቱ አያሳየኝ ግን አዘንኩብሽ በአንቺ ሰርግ አሳስበሽኝ ተስካር አበላሽኝ ቤዚ አስለቀሺኝ...ሌላ ታሪክ ጀምሪ አፍጥኚው...


💔ይሄን እና ሌሎች አስተያየቶች ደርሰውኛል💔 ታሪኩን አንብባችሁ ስለጨረሳችሁ አመሰግናለሁ 🙏🙏🙏

ብዙዎቻችሁ ያንቺ ታሪክ ነው ወይ ብላችሁ እየጠየቃችሁኝ ነው #አይደለም ነው መልሴ....
ቀጣይ ታሪክ እንድጀምር አስተያየታቹን አድርሱኝ🙏
@yebezawit2
💌💌💌💌💌💌💌🥀🥀🥀

@yebezigetmoch
🌷🌷🌷ማስታወቂያ🌷🌷🌷
@yebezigetmoch

#ሰባራ_ልቦች
ውድ ቤተሰቦቼ እንዴት ከርማችኋል? እነሆ በሰጣችሁኝ ሀሳብ አስተያየት መሰረት አዲስ ታሪክ ይዤ ተመልሻለሁ #ሰባራ_ልቦች በቅርብ ቀን 🌟 በሳምንት ሶስት ቀናት ብቻ(ለጊዜው) የማቀርብ መሆኑን አሳውቃለሁ።

💔 ሰባራ ልቦች💔
ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ
በቅርብ ቀን!!!
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
💔💔ሰባራ ልቦች💔💔
ደራሲ ቤዛዊት የሴት ልጅ

🌟 በግጥም መንደር ብቻ!!🌟
💕በቅርብ ቀን💕
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
#ሳትነቃ 🤷‍♀
እኔ የዋህ አንተ በዳይ ፣
አውቀህ አጥፊ ሁሌ አታላይ፣
እኔ አወጋሽ አንተ ወቃሽ፣
ባመንኩህ ልክ የምትዋሽ፣
እኔ ከፍቶኝ አንተ ሳቂ ፣
ልቅረብህ ስል ደርሶ ራቂ፣
እኔ ፍቅር አንተ ፀብ ፀብ፣
አብሮነትን የምታጠብ••
እኔ መውደድ አንተ መጥላት፣
የሚቀልህ አጉል መኩራት••
እኔ ናፍቆት አንተ ኩርፊያ
ልዩነቶች
አንዱ አንደ ዶፍ ሌላው ካፊያ፣
ሁነን ኗሪ ብንከርምም
እየቻልኩህ እንደምንም
አልገባህ ሲል ሴትነቴ
•• አለቀና ያ ትግስቴ ••
ሳልነግርህ ሄድኩ ይሄው በቃ
እንደተኛህ ሳትነቃ •••
#ሼን
እጅግ አመሰግናለሁ 🙏❤️
አዲሱ ድርሰቴም በቅርብ ቀን #ሰባራ_ልቦች ይቀጥላል...💕🌟
🌟ውድ ቤተሰቦቼ....አዲሱ ታሪክ እንዲጀመር እና ሜንበሮች እንዲጨምሩ
#ሼር በማድረግ አብሮነታችሁን አሳዩኝ🙏💕🙏
💔ሰባራ ልቦች💔
ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
የማስመሰል ቅኔ
.
.
ከገደቡ ያልፋል
አዳኝ ጠበል ይሻል
መረን ያጣ ዝቅጠት ቅዱሱን ያረክሳል
ታላቅነት ሲ'ናድ
°°°
አልፋውን ዘንግቶ በውድቀት ሲደቃ
በመለዋወጥ ሀቅ
የኮከቦች አጀብ ሰርክ ይናፍቃታል ለፈካች ጨረቃ
ልብ በይ አለሜ...
ባልመዘነው ዛሬ በትናንት እየኖርን ቆልፈን በነገ
በውሸት ስንኳትን
የሰነቅነው ተስፋ ጥሎን እያረገ
በመጣጣር ፋንታ ያልፋል ካስቀደምን
ስንጓዝ አይደለም ቀድመን ነው የወደቅን
ልብ በይ አለሜ...
ጥል ቤት አይገነባም ፀብ አይሆንም ቋንቋ
በስሜት ብንጓዝ አንወጣም ካረንቋ
በሌቱ ያሰረን የኋልዮሽ ጉዞ ካቴናን ለመስበር
የእሾህ አጥርን ነቅሎ በእውነታ መታጠር
ይበጃል ለዘመን የጎደለን ማከም
የተመታን ትውልድ በቅጡ ማስታመም
ታላቅነት ሲ'ናድ
°°°
አጉል ሽቅብ መካብ ያልተገራን ፍጡር
የገደለን ማግዘፍ ክቡርነትን መቸር
የሸሁን ቃል መጣስ ካህናትን መዝለፍ
ከርሞ ጥሬ መሆን እያደሩ ማደፍ
እንደ እርግብ ለስልሶ እንደ እባብ መናደፍ
ታላቅነት ሲ'ናድ
°°°
አምሳሉን ሲቀጣ ከሰውነት ሲወርድ እምነትን ሲያጎድል
አጋም ነው ትራሱ ቀንጠፋ ነው ልብሱ ተብሎ ይሞገሳል
ጮራ መሆን ሲችል ለጥፋት ደምኖ ለውድቀት ይዘንባል።
እናም በዚህ ክፍተት...
ቤታችንን ትተን ላፍታ ቢያስጎመጀን የጎረቤት አለም
መሆን ያዳግታል እውነት ይሸሸጋል በማስመሰል ቀለም።

አማኑኤል ደርበው(አማን)

@yebezigetmoch

@yebezigetmoch
🌟 #ሐሙስ በቀን ቅዱስ 🙏💕🙏
💔ሰባራ ልቦች💔
ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ
🌟🌟ይጀምራል!!🌟🌟
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
Forwarded from Deleted Account
2025/07/05 23:42:10
Back to Top
HTML Embed Code: