💕ሰባራ ልቦች💕
🍃🍃የመጨረሻ ክፍል መዳረሻ🌿🌿
❤ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ 💕
@yebezawit2
🌹🌹ሰባራ ልቦች💔💔💔
....የሰማሁት ድምፅ የሰምሃል ነበር ፊቴን ሳላዞር ቆምኩኝ።"አትሂድ በቃ እውነቱ ያየኸው ሳይሆን በልብህ ያለው ነው" እንባ ባነቀው ድምፀት አወራች እኔ ግን ከቆምኩበት ወደ ፊት መንገዴን ቀጠልኩኝ። ሲሞላ አላየሁም የልቤ ሲሆንልኝ እናም በቀጠሮ ሳይሆን አሁን ዛሬ ኋላዬን ሳላይ መሄድን ፈለኩኝ መራቅ ከእድል አይን ስር መሸሽ አውቃለሁ ለእኔ ባለ ሰባራ ልብ ከባድ ነው ግን ግድ ነው መሄድ መምጣት ነው አሉ እንጂ መሄድ መሞት ነው የሚወዱትን ማጣት ከቃል በታች መውደቅ ስቃይ ነው። እግሬን እየተከተልኩ ሜዳውን መቋራጥ ስጀምር ከፊቴ ነጭ ኩታ የደረቡ ሁለት አባቶች እና አንድ ደርባባ ሴት ተመለከትኩ ቆምኩኝ ወደ ኋላ ላለማየት ራሴን ገዝቻለሁ ከወንድነት ወኔዬ እና ጉልበቴ አልፎ የሚዘረገፈውን እንባዬን በእጄ እየዳበስኩ አተኩሬ አየኋቸው "ልጅ ልዑል" አሉ በስተቀኝ ያሉት ባለ ነጭ ሽበት አዛውንት። አንገቴን አቀረቀርኩ እና ዝም አልኩ ። "ስጠራህ አቤት አትልም" አሉ መልሰው እኔ ግን ቃል አላወጣሁም ለምን? ምን ማለት እችላለሁ ዝም ብቻ ነው የኔ ድርሻ። "እስኪ ዘወር ብለህ ተመልከት" አሉ ደርባባዋ እናት ቀና ብዬ ደም በመሰለው አይኔ ተመለከትኳቸው እና " ልሄድ ነው አላይም...ይቅር በሉኝ" መንገዴን ልቀጥል ስል። "ታዛዥ አልነበርክም እንዴ" መሃል ላይ ያሉት አባት ጠየቁኝ።እኔ ግን ሰውነት ናፍቆኝ ሰው አድርጋኝ የራቀችኝን እድልን ላለማየት ነበር ራሴን የገዘትኩት ግን አባቶቹ ለምን እንደፈለጉ አልገባኝም እና በሰባራ ልቤ እያነባሁ ወደ ኋላ ዘወር አልኩኝ እና ተመለከትኩ። አይኖቼ ያጭበረበሩኝ መስሎኝ ጨፍኜ ዳግም ገለጥኩ ግን እውነት ነው ውሸት የለውም ፈገግ አልኩኝ እና ማልቀሴን ጀመርኩ።ሜዳው ላይ እግሬን ዘርግቼ ተቀመጥኩኝ እና እናቱን እንዳጣ ጨካኝ ወታደር በእግሮቼ መሃል አንገቴን ቀብሬ መራራ ለቅሶን አለቀስኩ።ሰምሃል ከዊልቸሩ ተነስታ ነበር የተመለከትኳት ይሄ ለእኔ የቀን ቅዥት ነበር የሆነብኝ ግን እውነት ነው። "እድል" ሰምሃል ወደ እኔ እየመጣች ተጣራች "ምን አሁን ምን ቀረሽ" እድል እየተመናጨቀች ስትወጣ እሷም እንደ እኔ ካለችበት ደርቃ ቀረች። "ልዑሌ ይቅርታ ለማለት የሚበቃ ሞራል የለኝም" ብላ እጇን ዘረጋችልኝ እና ይዣት ከተቀመጥኩበት ተነሳሁ። ከአዛውንቶቹ ጋር ወደ ቤት ገብተን ተቀመጥን እና የሆነው ሁሉ ሊተረክልኝ እንግዶች ይጠሩ ተባለ።እኔ ግን ሰምሃል ከወዲያ ከወዲህ ስትል ማየቱ እንግዳ ነገር ሆኖብኝ በስስት አያታለሁ እድልም በእናቷ እግር ላይ ተኝታ ገጿን በእንባ በዝምታ ታርሳለች። "ግቡ ግቡ " ሰምሃል ከውጪ የሚገቡትን ሰዎች በሚያምር ትህትና ጋበዘቻቸው። የኔው ጉዶች ነበሩ እናቴ አባቴ ወንድሜ እና አሊሾ ከእነሱ ውጪ ቂም ይዤበት የማዝንበት የድሮ ፍቅሬን የቀማኝ ዶክተር ማርቆስ ነበር።የሚሆነው ነገር ስላልገባኝ ዝም ብዬ መመልከት ጀመርኩ ሰምሃልም ከትንሿ ኩርሲ ላይ ተቀምጣ ታወጋን ጀመር። "ልዑሌ አንተን ትቼህ ስሄድ ልክ ላልመስልህ እችላለሁ ግን ልክ ነበርኩ የምወደው ሰው ነበር እስሱም ማርክ ነበር ማርክን ለማግኘት ነው አንተን የቀረብኩህ በእርግጥ አንተ የግቢው ታዋቂ ብትሆንም እኔ ግን ያለ ምክንያት የምወደው ማርክን ነበር ሳየው ሁሉ በፊቱ ፈገግታ እጠግባለሁ ብቻ ትቼህ ሄጄ ረስቼህ ነበር ግን ማርክ ሁሌም ስለአንተ ያስብ ነበር ስፈልግህ አጣሁህ እናም እርጉዝ እያለሁ በገጠመኝ የጤና እክል ሁለት ልጅ አጣሁኝ ብቻ ህይወት ጨልማ ጎስቋላ ሆንኩኝ እናም በደሌን ተናዝዤ ንስሃ ልገባ አሰብኩ ግን ይቅርታችሁን ፈልጌ እየናፈኩ አዲስአበባ መጣሁ እና ልደታ ቤተክርስቲያን መጥቼ ስሳለም አጋጣሚ እናትህን አገኘኋቸው ሳያቸው ነበር ወዲያው ያወኳቸው የሆነው ሁሉ አጫወቱኝ እናም ከእኔ ከተለየህ ጀምሮ የጊዜ መቁጠሪያህ መቆሙን ስትነግረኝ ወልጄ አለመሳሜ ምክንያቱ ገባኝ። አታምኑኝ ይሆናል ግን በየቀኑ እየመጣሁ አይህ ጀመር ቤተሰቦቼ አዲስአበባ መሆኔን አያውቁም እና እንደምንም አሊሾን አውርቸው ካሳመንኩት በኋላ ያንተን ጉዳይ ጨርሴ እድል እህቴን አሰብኳት እሷም በእኔ ግፍ ተጎድታለች።በእርግጥ መኖር አላቆመችም በእግዚአብሔር ጸንታ ታግላ ለበደሌ ጸልያ ለጥላቻዬ ፍቅርን ሰጥታኝ አክብራኝ አሸንፋኛለች እና ደካማ ጎኗን ስለማውቅ ነበር ጉዳት ደርሶብኛል ብዬ የመጣሁት እሷም አንተን ፍለጋ ወጣች በየቀኑ ግን አሊሾ ይከታተላት ነበር" አለችኝ።
የምታወራልኝ ሁሉ የሆነ ልብወለድ መሰለኝ ግን ደግሞ በሁለት አይኖቼ እየተመለከትኩ ነውና ውሸት ነው ብዬ መኬድ ከበደኝ። "እና ልዑሌ እድልዬ እግዚአብሔር በእናንተ ከካሰኝ ብዬ እንድትተዋወቁ ድራማ ሰራንባችሁ ያንቺ ሙላት እሱን ሞላው ያንተ መጥቆር እና ማዘን እሷን አበርትቶ አንተን ደገፈችህ እና ላትለያዮ እጅ ለእጅ ተያያዛችሁ።ስደተኛ እና ሰባራ ልብህ በእድል ልብ አረፎ ሲፅናና አየሁት የእውነት ልዑሌ ስትስቅ ሳይህ ደስታ ምድሬን ሞላችው እናም በቃ ይሄን ሰራንላችሁ" አለች እድልን እያየች እድልም በዝምታ ካደመጠች በኋላ "በቃ ይሄ ነው" አለች። ሁሉም ደንግጦ ይመለከታት ጀመር። "አንተስ የሰራኸው ድራማ የለም" አለችኝ ወደ እኔ አይኗን አፍጥጣ።ደነገጥኩ "አድል እኔ አላውቅም እንደ አንቺ እንግዳ ነኝ።" በጩኸት ንግግሬን አቋረጠችው። መሃል ላይ እየተንጣጣ የሚነደው እሳት ቤቱን አሞቆታል። "ተንኮል ነው ታውቅ ነበር አውቃለሁ እኔ ላይ መጫወት አይሰለቻችሁም ግን ቆይ ምን አረኩህ እስኪ አንተ ንገረኝ ህመም አይተህ አታውቅም እና ነው እኔን እንደዚህ አይኔ ስር የተጫወትከው እስኪ አሁን ታምነኛለች ብለህ ነው እንደዚህ የምታወራው።" ከተቀመጠችበት ከመነሳቷ ከእሳቱ ዳር እራሷን ስታ ተዘርራ ወደቀች። ሁሉም በጩኸት ጎጆ ቤቷን አተረማመሰው......
🌹🌹🌹ይቀጥላል🌹🌹🌹
❤ፍቅር የሚያወሩት ሳይሆን የሚኖሩት እውነት ነው! ማጭበርበር ውሸት የሌለበት ንፁህ ለሚወዱት ብቻ የሚሰጡት በስስት የሚያኖሩት ልዩ በረከት ነው💚የሚታደሉትም ጥቂቶች ናቸው😍 ያገኙት ጥለውት ያገኙት ሲያከብሩት የሚጎዱ ብዙዎች አሉ💕ያ ህመምም በፍቅር ይታከማል🌹 ውበት እና ሃብት ፍቅር የሚያመጣው እንጂ ፍቅርን የሚያመጡ አይደሉም❤❤❤😘😘😘
ይቀጥላል...ብጫቂ ገፆች
ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ
@yebezigetmoch

💝💝ሰባራ ልቦች💝💝
🌹🌹የመጨረሻ ክፍል🌹🌹
🍃ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ🍃
የጎጆ ቤቱን በር በርግደን እድልን አቅፌ ወደ ጤና ጣቢያው አቀናን ግን እንደ ሰማይ እርቆ አደከመኝ በበረሃ ውሃ እንደተጠማ ውሻ አለክልኬ እድልን እንዳቀፍኳት ሜዳው ላይ ተንበረከኩ ወንድነት እና አቅም ከእኔ ራቁ የሰምሃል ለቅሶ ሰፈሩን አቀለጠው።"እኔ ደግሞ ልያዛት" ማንነቱን የማላውቀው ሰው ነበር ከእኔ ተቀብሎ ሲከንፍ ከጤና ጣቢያው ያደረሳት።ልበ ቀናዋ ትሁቷን እድልን ወደ ውስጥ አስገብተው እኛን ከውጪ አቆሙን።"እህቴ በላኋት እኔ ነኝ ጠላቷ ምህረት የማይገባኝ" ሰምሃል ወገቧን ይዛ እያወራች ተንጎባደዳለች።እኔ ግን ላንቃዬ ላይ ምላሴ ተጣብቃ ማውራት ተስኖኛል።
ምን አልባት ይሄን ስል ማንም አይረዳኝ ይሆናል ካፈቀረ ሰው ውጪ ያለ ባይረዳኝ አይገረመኝም ምክንያቱም ለመረዳት ገና ሰው ሆኖ ሰውነቱ አልገባውም።ሔዋን ያቺን እፀ በለስ በልታ የአለምን አንድ አይን እንዳጠፋች እና አለም በጨለማ እንደተዋጠች ሁሉ እኔም ሰምሃል ያንን የመለያየት በለስ ቀጥፋ ስታበለኝ ምድራዊ ሲኦል ከቦኝ እና ወርሶኝ ነበር።ነገርግን ለእኔ የሚጨነቅ አምላክ መስጠት እንጂ መቀበል የማታውቀው ሰው የማይጠግብ የሚመስላት መሳቅ እንጂ ክፋት የማይገባት ገር እና ትሁት የሆነች ለሰዎች የተፈጠረች የምትመስላቸውን የሴት ሚዛን የሆነች የሰውነት ተምሳሌት የሆነችን እመቤት እድልን በመንገዴ አመጣት ከዚህ በላይ ምን አለም አለ? መንገዴን የምታስተካከል እሷን ልኮ የተሰበረውን ጠገነልኝ የጎደለውን ሞላልኝ።ለእድል ይሄ የሚገባት አልመሰለኝም እኔ ይሄን ድራማ ከቶ አላውቀውም ነገርግን ደስ ብሎኛል እንኳን አገኘኋት በውሸት ታሪክ እውነቷን እደልን አገኝቻታለሁ።የምፀየፈውን የቀድሞ ማንነቴን እንድወደው እንኳን ተበደልኩ እንድል አድርጋ በልቤ የሰራሁትን የሀዘን ጎጆ አፍርሼ የደስታ ሀገር እንድመሰረት አቅም እና ብርታት ሆናኛለች። ግን ታውቅ እና ትረዳኝ ይሆን? ስትነቃስ እኔን ትፈልገኝ ይሆን?
ዶክተሩ ከክፍሉ ሲወጣ አይተን ሮጠን ከበብነው።"አይዞአችሁ ደህና ናት ከአንድ ለሊት እንቅልፍ በኋላ ይሻላት።እንደዚህ ሆናችሁ ብትመለከት ታዝናለች እና ጠንከር በሉ" ብሎ ብዙ ሳያብራራ ወደክፍሉ ገብቶ ቀረ።እኔም ተከትየው ወደ ክፍሉ ገብቼ ፊቱ ካለው ወንበር ተቀመጥኩ"ዶክተር እኔም ዶክተር ነኝ እና ያለውን ነገር ብታሳውቀኝ" አልኩ አቅም እንዳለው ሰው ግንባሬን ቋጠር አድርጌ "ደህና ናት አሁን ላይ የሚያስጨንቃት ነገሮችን እናንተ አርቁላት ባለቤትህ ናት?" ጥያቄው ክው አደረገኝ። ምን ልበለው እውነት ነው ባለቤቴ ሳይሆን ባለቤቷ ብሆን ለእኔ ተድላ ነው ህይወቴ ከህይወቷ ጋር እንዲዋሃድ ምኞቴ ነው ግን እንዴት መግለፅ እና መንገር እንዳለብኝ አላውቅም ፈገግ አልኩኝ እና "በሀሳቤ ባለቤቴ ናት በእውኔ ግን ባለቤቷ ነኝ" አልኳት አጉል እየተፈላሰፍኩ።ዶክተሩ ለፈገግታዬ ፈገግ ብሎ "ገባኝ ነገሮች ላይ ተስፋ አትቁረጥ ሴቶች እንደዚህ ናቸው ቢወዱህም እንኳን እስካላመኑህ ድረስ ፍቅራቸውን አያሳዩህም እና ታገስ" አለኝ የደረሰበት ይመሰል እየመከረኝ። እኔም አመስግኜ ከክፍሉ ወጥቼ ወደ እድል ጋር ሄድኩኝ በሩ ገርበብ ብሏል እነ ሰምሃል ከበዋታል ቀስ ብዬ በሩን ከፈትኩት መቼም ስሜቴን አላብራራም ግን መልሷም አውቄ መንገዴን እጀምራለሁ። "ግባ" እንባዋ በሹራቧ እየሞዠቀች ሰምሃል ቦታ ለቀቀችልኝ እድል ቀስ ብላ አየችኝና አይኖቿን ሰበር አደረገች።"እንድሄድ ትፈልጊያለሽ " አልኳት። አለመፈለጓ መስሎኝ አይኗን መስበሯ። ቀና አለች እና "ይ ቅ ር ታ ታደርግልኛለህ" በቀስታ አወራች አይኖቼ እንባን አቅረው ተመለከትኳት "እኔን ይ ቅ ር በይኝ" አልኳት።ቀስ ብላ ጉልኮስ ያልተቀጠለበትን ቀኝ እጇን ዘረጋችልኝ አጠገቧ ተንበርክኬ ያዝኩት።"የእውነት ማ ረ ኝ የዋሸኸኝ መስሎኝ ነበር ግን እውነታው እኔ እና አንተ በሌሎች ሳይሆን በእግዚአብሔር መንገድ የተገናኘን ነን" ንግግሯ እንባዬን እንዳፈስ አስገደደኝ።ላጣ ፍቅር ለተራበ ነፍስ ማልቀስ ያንሰዋል።"ግማሽ ሰው ነኝ አንተ ጋር ግን ሞልቻለሁ ደስተኛ ነኝ አንተ ጋር ደምቂያለሁ ሴት ነኝ አንተ ጋር ልዩ ሆኛለሁ ልቤ ሰበራ ነው አንተ እጅ ላይ ግን ተጠግኗል ከልብህ ትወደኛለህ?" አለችኝ።ሰምሃል በሲቃ እና በእንባ ወለሉ ላይ ተዘርግታ ማንባቷን ቀጠለች።"ከምታስቢው በላይ እወድሻለሁ በአይኖችሽ ውስጥ ያየሁትን ልዑል ላጣው አልፈልግም እጅሽ እጄን እንደያዘ ዘመናት አልፈው በደስታ እንኖራለን" አልኳት በእንባ ፈገግ አለች። ልቤ ከልቧ አረፈ ሀሳቤ በሀሳቧ ተከበረ ነፍሴ ከነፍሷ አንድሆነ እሷ ጋር መጥቼ እሷ ጋር ቀረሁ ሁላችንም በደስታ ተቃቀፍን።አንድ ሆንን በፍቅር የተሰበረ በፍቅር ተጠገነ።ዛሬ ደስተኛ ነኝ የደስታዬ መፍሰሻ እድል ናት የኔ ደስታ ቤተሰቤንም አኩሩቶ ጮቤ አስረግጧል አሊሾ ውለታው ከወንድምነት ከጓደኝነት አልፏል።በጥሩ ድራማ እውነተኛ ፍቅርን ሰጥተውኛል።ፍቀሬን እድሌን የሚቀማኝ የለም ፍቅር ያጣመረው ፍቅር ያኖረዋል! ጤና ጣቢያውን በደስታ ሳቅ አናጋሁት.......ተፈፀመ!!ፍቅር ግን ይቀጥላል❤
💙💙💙የምትወዱትን ፈጣሪ ይስጣችሁ💙💙💙
💛ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ💛
🌹የግጥም መንደር🌹
😍ሰባራልቦች❤❤❤💚💚💚💚

ዛሬ ደስ😊 አለኝም ከፋኝ😭😭
ከሃዘኔ ስጀመር😭
ከትላንት ወዲያ በ10/03/2013 ነበር ስራ የለም እና ዕረፍት አድርጌ ቤቴ ውስጥ ቁጭ ብዬ ድርስቴን እየፃፍኩ ስልኬ ጠራ "ማኪ" ነበር ፈገግ አልኩኝ።"ሄሎ ማኪ" አልኩኝ "ወዬ በረሮዬ እንዴት ነሽ?" ደህንነቴ ከልቡ የሚያሳስበው ሰው ነው።"ደህና ነኝ እግዚአብሔር ይመስገን እንዴት ነህ" መልሼ ጠየኩት።"አለሁልሽ ይመሰገን ስሚኝ ውዴ እማማ ጋር ነኝ" አለኝ። ለካ እማማን አታውቋትም ማኪንም😊
ማኪ አምና ነው ቤተክርስቲያን ቁጭ ብዬ ከአምላኬ ጋር ሳወራ እሱ ደግሞ ከእኔ ትይዩ ተቀምጦ እጅግ የምወደውን መዝሙር በክራር ይጫወታል።ልክ ሲጨረስ ተናደድኩ ድፍረት የለኝ ነገር ድገመው አልለውም አንገቴን አቀርቅሬ ዝም አልኩ። ግን እሱ ከፊቴ ተርድቷል መሰለኝ ደገመው "ባለውለታዬ ባለውለታዬ ከአመድ ያነሳኸኝ ከትቢያ ተጥዬ"...አይኖቼን ተክዬ ዝም ብዬ አየሁት ተነስቶ ወደ እኔ መጣ እና ተቀመጠ ሰላምም አለኝ ደስ አለኝ ሌላ መዝሙር ዘምርልኝ አልኩት። ዘመረልኝ❤ ድምፁ እርጋታው😊 ከዝማሬው በኋላ "ሁሌ ትመጫለሽ?" አለኝ።"አዎ ሁሌ ማለት እችላለሁ ውሎዬ እዚህ ነው" አልኩት። "ደስ ይላል ግን አውቅሻለሁ ልበል" አለኝ። ውይ አልኩኝ በልቤ "እኔጃ" አልኩት። "አውቅሻለሁ"ብሎ ደረቀ🙄 ይሁና! ከዛላችሁ በመዝሙር ተዋውቀን ቤተክርስቲያን ስሄድ አላጣውም።ይዘመርልኛልም💚 ስልክ ተቀያየርን አወጋን ቤተሰብ ሆንን ማኪ እጅግ መንፈሳዊ ሰው ነው የተረጋጋ የሚኖረው ከእናቱ ጋር ነው እናቱ ፋርማሲስት ስትሆን እሱ ደግሞ ማኔጅመንት ነው ያጠናው ግን አይሰራበትም(የደላው😂) የሚሰራው የራሱን ንግድ ነው በህይወቱ የማይረሳው እና መርሳት ያልቻለው ሀዘን የአባቱ ሞትን ነው።ስለ አባቱ አውርቶ አይጠግብም እኔም ሳላውቃቸው ወድጃቸዋለው እና ከማኪ ጋር ሁሌ የምንጣላው ይሄን ማቅህን አውልቅ በሚል ነው ግን ተሳክቶልኛል😊🙏 በብዙ ንትርክ (የተወበትን መንገድ እመለስበታለሁ) እና ለ'ኔ ወንድሜ ነው ያውም ል ዩ💚
❤❤እማማ ደግሞ ባስ ውስጥ ከሜክሲኮ ጋርመንት ስመጣ ያወኳቸው ደግ እናት ናቸው በችግር ውስጥ የሚታገሉ እጅ የማይሰጡ ጠንካራ እናት ናቸው። ብቻ ስለ እሳቸው ብዙ ማውራት አልፈልግም ትውውቃችን ብቻ አጋጣሚ ነው ❤❤ እኚህ እናት ለእኔ እናት ሆነውኝ ነበር ልመና ሳይሆን ስራን የሚወዱ ሰው ናቸው።😊
ታዲያ ማኪ እማማ ጋር ነኝ ብሎኝ አገናኘኝ።ማኪን ያስተዋወኳቸው እኔ ነኝ። ማኪ ሀዘኔ በረታ በሚል ተልካሻ በሚል ምክንያት ሰላም ሲያጣ እማማ ጋር ወስጄ ታሪካቸውን ሰምቶ ምክር (ሰድብም🙄 ቁጣ) አግኝቶ ከልቡ ወደ ልቡ ተመልሷል። እማማ ጋር በቻልኩት ሁሉ እሄዳለሁ ምርቃቴን አፍሼ እመለሳለሁ😋 ከዛ ግን እማማ ህመማቸው በርትቶ አልጋ ያዙ ጉልበታቸው ተፈተነ😣 በ10 በስልክ ሳወራቸው እንዲህ አሉኝ
"ተባረኪ በሁለት እጇ እመአምላክ ትስጥሽ መቼስ እኔ የምሰጥሽ የለም" አሉኝ😭 (የሰጡኝ እናትነት አንሶብኝ) "ልጄ ቢኖር ኖሮ አንቺን ነበር የምድርለት"(😂ያን ሳቃቸውን እያጀቡ) እኔም "ታዲያ ምን ችግር መርጠው ይድሩኛል" አልኳቸው።....
በ13 እሁድ ከቤተክርስቲያን ስመለስ እንደማያቸው ቃል ገብቼ ተመርቄ ስልኩን ዘጋሁት ማኪም እዛው አድሮ እኔ ስመጣ ወደቤቱ ሊገባ ተነጋግረን ስልኩን ዘጋሁት። ዛሬ ግን ከመሸ ተደወለልኝ የእማማ የእህታቸው ልጅ እታጉ ናት ልቤ ሳላውቅ ተተረከከ 😭 "እማማ አረፉ" ብላ አረዳችኝ። እጄን በስስት አይተው የሚስሙት መዳፌ ላይ እንትፍ እያሉ የሚመርቁኝ በልቼ የማልጠግብ የማይመስላቸው በትዕግስት ማጣት ጮክ ብዬ ሳወራ በመቋሚያቸው ቋ! የሚያድርጉኝ ቤተክርስቲያን ስጋ ወደሙን ሲወስዱ ከጎናቸው የሚያደርጉኝ የሚያሞግሱኝ ስጠፋ አንቺ ሲሚብሮ የት ጠፋሽ የሚሉኝ ስቆጣቸው የሚፈሩኝ 😯 ሲያመኝ የሚጨነቁ የቢዚነስ ስራዬ ሲበላሽ የሚጨነቁልኝ😣😣 የተሻለ ሰው እንድሆን ስራዬን አጣጥለው ወደፊት የሚገፈትሩኝ😭 እማማ ሄዱ መርቀውኝ በመቁጠሪያቸው እንትፍ ብለው ዳብሰው ሳልጠግባቸው ብዙ ከእሳቸው ሳልማር እሳቸው ሄዱ....ወደ አገናኘን አባታቸው ተጓዙ...😭😣😣 የማዝነው ለራሴ ነው ግን ደግሞ መፅናናት ግድ ይልኛል! ሀዘኔን አይወዱምና ተመስገን ብዬ ቀና እላለሁ🙏🙏🙏 እግዚአብሔር ሆይ ነፍሳቸውን ማርልኝ😣 ከሁሉም አንድ ነገር ይናፍቀኛል ቁጣቸው!😭😭😭😭
🙏🙏🙏ነፍስ ይማር🙏🙏🙏
ቤዛዊት የሴትልጅ
@yebezawit2 😭

Forwarded from መቃን ዲጂታል መጽሔት (✏️ⓐⓜⓐⓝ)
ብራና የግጥም ውድድር
@aman0777 ይመዝገቡ።
➬አማኑኤል ደርበው
➬ዳግም ደጀኔ
➬አቅሌሲያ ጌታቸው
➬ቤዚ የራጉኤል ልጅ
➬ስንታየሁ ማሚቴ ከ60% ሲዳኙ
ህዝብ 40% ይዳኛል።
www.tg-me.com/kene_tobeya
ቀድማችሁ ተመዝገቡ
የኢንተርኔት ባኬጅ በስጦታ ይበረከታል።
@aman0777 ይመዝገቡ።
➬አማኑኤል ደርበው
➬ዳግም ደጀኔ
➬አቅሌሲያ ጌታቸው
➬ቤዚ የራጉኤል ልጅ
➬ስንታየሁ ማሚቴ ከ60% ሲዳኙ
ህዝብ 40% ይዳኛል።
www.tg-me.com/kene_tobeya
ቀድማችሁ ተመዝገቡ
የኢንተርኔት ባኬጅ በስጦታ ይበረከታል።
❤❤❤አልናገርም💙💙💙
ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ
🌹🌹🍃🍃🍃☀☀☀☀
ክፍል አንድ😍
....አይኔን ከግራ ወደ ቀኝ እያማተርኩ ከሚመላለሱት የግቢው ተማሪዎች ውስጥ በአይኔ እፈልጋታለሁ።ግን የለችም።"ማርኮን አይበቃህም" የጓደኞቼ ንትርክ እና እንሂድ የሚል ጭቅጭቃቸው ከተቀመጥንበት ተነስተን ወደ ክፍል ገባን።ክፍሉ በተማሪዎች ጫጫታ በአንድ እግሩ ቆሟል ወንበሬ ላይ ተቀመጥኩ።"ቆይ ግን ለምን አትነግራትም" ከግራዬ የተቀመጠው ዘላለም ጠየቀኝ።"አንተ ደግሞ የእሷን ነገር ከክፍል በኋላ ዱካዋን ታጠፋለች ማንን ቀርባ ነው እሱን ቆማ የምታወራ" ሌላኛው ወዳጄ ኪሮስ መለሰለት።እውነት ነው አንድም ቀን ከሰው ጋር አይቻት አላውቅም ብቻዋን ነው የምትመጣው ስታወራ እና ስትስቅ የማያት በስልክ ነው የሆነ ሰዓት አላት አስተማሪ በወጣ በሁለት ደቂቃ ውስጥ ይደወልላት እና እየተፍነከነከች እቃዋን ሰብስባ ትወጣለች።በቃ እሷ ማለት በዝምታ መጥታ በዝምታ ትሄዳለች።አስተማሪዎቻችን እንኳን በየቀኑ ነው "የእዚህ ክፍል ተማሪ ነሽ" የሚሏት።እሷም በአውንቷ ጭንቅላቷን ከመነቅነቅ በቀር ሌላ መልስ የላትም።እኔ ደግሞ የክፍሉ አሸባሪ መሆኔ ይታወቃል።ህይወትን ለማሸነፍ በምሽት ቤቶች በዲጄነት እሰራለሁ ቀን ደግሞ እማራለሁ።ስቀር አስተማሪዎቼም ሳይቀሩ ደውለው ይፈልጉኛል።ኩራተኛ እና ነገረኛም መሆኔ ይታወቃል።በግቢው ያሉ ሰዎች ውበቴን ሲያደንቁ አይጠግቡም እና ያኮሩኝ እነሱ ራሳቸው ናቸው።የሚገርመኝ የእኔን ወሬ ናፍቆት ያለክፍላቸው ገብተው የሚማሩ መኖራቸው ነው።የአስተማሪ ስህተት ማለፍ አልወድም ሰቃይ ባልሆንም ወዳቂ ግን አይደለሁም ከአስተማሪ ጋር መከራከር ቁርሴ እና ምሳዬ ነው።በእረፍት ሰዓት ሙዚቃ አዳምጣለሁ እናም ቀኑ ሙሉ በሴቶች ተከብቤ እውላለሁ ቢሆንልኝ እና ዘፋኝ ብሆን በታደልኩ ግን ገንዘብ የለም።የእሷ እኔን አለማስተዋል አልገረመኝም ከእነጭራሹ የማያውቁኝም አሉ።ነገር ግን ቢያንስ አንድ የምትቀርበው ሰው አለመኖሩ ደንቆኛል።አሳይመንት እንኳን ሲሰጥ አታወራም ገንዘብ አዋጥታ ዞር ነው የምትለው።የማይናደድባት ሰው የለም እሷ ግን መስሚያ ያላት አትመስልም።እንዴት እንደሆነ ባይገባኝም ስትቀር ስታረፍድ እጅጉን ይጨንቀኛል አይኖቼን ሳንከራትት ነው የምለው።ፍቅር ያዘኝ እንዳልል የሚፈቀር ነገር አላየሁባትም ጥላቻ ነው እንዳልል ይሄ ምን አይነት ነው ያስብለኛል።ሰው እንዴት እንደዚህ ለሰው ይጨነቃል።ሆ! ብቻ ተመስገን ነው የሚባለው።የክፍሉ የጫጫታ ማዕበል በመምህራችን መምጣት በፀጥታ ተዋጠ።ሁሉም አይኑን የሚወደደው አስተማሪ ላይ ተክሏል።መምህር አወቀ ይባላል።ስሙ ከሰውነቱ ጋር የተዋሀደ ብቸኛ ሰው ነው። ተማሪዎቹ ጓደኞቹ ናቸው ከእኔ ጋር ደግሞ ቤተሰብ ነን በተለይ ከባለቤቱ ጋር ለመዝናናት የስራ ቦታዬ ሲመጣ የሚወርድልኝ ሳቢ ምሽቴን ነው የሚያደምቀው ታዲያ እኔም የሚወደውን የኤፍሬም ታምሩን መከረኛ ሙዚቃ እከፍት እና ጥርስበጥርስ አደርገዋለሁ።ባለቤቱ እጅግ ውብ እና እርጋታ የተላበሰች ደርባባ ሴት ናትና ትመቸኛለች።አስታውሳለሁ ከመምህሬ ጋር በእረፍት ካፌ ቤት ተገናኝተን ቡና እየጠጣን ስለባለቤቱ ያለኝን ክብር እና አድናቆት ስነግረው ቅናቱን እየሸሸገ "በል ሰውዬ አርፈህ ተማር ልጅነህ" ብሎኝ ነበር ተነስቶ የሄደው ይወዳታል ማለት አልችልም ይሞትላታል እውነትም ይገባታል።አጋነንኳት አይደል ያውም የሰው ሚስት።"በቀጣይ አንድ አሳይመንት ይኖረናል" መምህራችን ተናገረ።በሩም ተንኳኳ "ይግቡ" ሲጢጥ ብሎ ተከፈተ "ምነው በጊዜ መጣሽ" ተረበኛው መምህር የመጣችውን ተማሪ ጠየቀ።አንገቷን አቀረቀረች።እኔ ግን ደስ አለኝ።"በይ ግቢ እና አንድ ትወና አሳይተሽ ተቀመጪ" አላት እሷም በሩን ዘግታ ከፊት ለፊታችን ቆማ ሁላችንንም አየችን ክፍሉ የሞላው ተማሪ በጉጉት ነው የሚጠብቀው።እውነት ለመናገር በመምህር ክፍለ ጊዜ እንደሚያረፍድ ተማሪ ተወዳጅ የለም ምክንያቱም ሁሉም ተማሪ ስለሚስቅ በመምህር ክፍለጊዜ ያረፈደ ከቻለ ይዘፍናል አልያም ይተውናል ግዴታ ነው ሁለቱንም አልፈልግም ካለ ቀልድ መናገር አለበት።አቤት ግን ቀልድ የሚቀልዱ ተማሪዎችን ማሰቃየት የኔ ተንኮል ነው።"ታዲያ ምን ይሁን" እያልኩ አሸማቅቃቸዋለው ግን አይቀየሙኝም እኔም እረሳዋለው እሱም አልሆን ያለው ተማሪ በተማሪ ትዕዛዝ ይቀጣል እና ሁሉም ዞሮ እኔን ነው የሚያየኝ ያው ተንኮል በድግሪ ነኝና። ዛሬ ደግሞ በይበልጥ እየጠበኩ ነው። እሷም በዝምታ አይታን አቀረቀረች አሁንም መምህራችን እንድትዘፍን እድል ሰጣት ዝም ሆነ መልሷ ቀልድም አልወደደችም።"ልትቀጪ ነው" ብሎ አይኑን ወደ ተማሪዎቹ ያዞረው መምህር አስደሰተኝ።እጄን አወጣሁ ሁሉም እየሳቀ ነበር የሚያየኝ።"እንድትተውን ነው የምንፈልገው አፍቅራ የምትለምን ሴትሆና ትስራልን" አልኩኝ።ቀና ብላ ስታየኝ የአይኖቿ ብርሃን እንደ መብራቅ ልቤን ሲተረክክ ተሰማኝ "በይ ቶሎ ስሪ አርፍደሽም ሰዓታችንን አትስረቂ" አላት።እንባዋ መውረድ ጀመረ እየሳቀ እና እየተንሾካሾከ የሚጠብቀው ተማሪ ቀዝቃዛ ውሃ ተቸለሰበት አቅፋ የያዘችውን ትልቅ መፅሀፍ በቁሟ ለቃ አፏን አፍና እየሮጠች ከክፍሉ ወጣች ደነገጥኩ።ተማሪው በአንድ ላይ ሳቀ እኔ ግን ደርቂያለሁ።"እርኩስ" "ወይኔ ግፍህ" "አሯሯጥካት" "የምር ገባላት እንዴ" የተማሪው ወሬ በጆሮዬ ይንፎለፎላል። አስተማሪውም "በሉ ስትመጣ ስጧት" ብሎ መፅሃፉን ከጠረጴዛው ላይ አኑሮት ሰዓቱን ተመልክቶ ከክፍሉ ለቆ ወጣ እኔም እየሮጥኩ ተከትዬ ወጣሁ እና ልጅቷን መፈለግ ጀመርኩ።የግቢውን ዙሪያ ገባውን አስሼ ወገቤን ይዤ ቆምኩኝ አወጣቷ ወደክፍል የምትመለስ አትመስልም። ከአንድ ዛፍ ስር ቁጭ ከማለቴ ከጀርባዬ የሲቃ ድምፅ ተሰማኝ።ዘወር ብዬ ተመለከትኩ ልጅቷ ናት።ወደ እሷ ጋር ተጠግቼ ቆምኩኝ።ተሰፈንጣራ ተነሳች"ይ ቅ ር ታ እህት ያው ቀልድ ስለሆነ ነው" አልኳት ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ሁኔታ ይቅርታ እየጠየኩ።"አራዳ ነህ" ብላኝ ምንም ሳትል ጥላኝ ሄደች መፅሃፏን የምትወስድ ቢመስለኝም ተሳስቻለሁ ከግቢው ወጥታ ነው ርቃ የሄደችው።እኔም መፅሃፏን ይዤ ወደ ቤቴ ተመለስኩ።ለምሽት የማጫውተውን ሙዚቃ እየመረጥኩ መፅሃፏን ማገላበጥ ጀመርኩ።አንዲት ብጫቂ ወረቀት ተመለከትኩ።
📖ይቀጥላል📖 💙💙
@yebezawit2
🍃🍃☀☀☀አልናገርም🍃🍃☀☀

💙💙አልናገርም💙💙
ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ
🌹ክፍል ሁለት❤
😲😲😲😲😲😲
አንዲት ብጫቂ ወረቀት ተመለከትኩ።ወረቀቱ ላይ "ሟች ነኝ" የሚል ፅሁፍ ሰፍሮበታል።አሁን ማን ይሙት ይህች ልጅ አፈር ይበላታል? አልኩኝ።
ሰዓቴ ደርሷል እና ስበር ወደ ምሽት ቤቴ አቀናሁ።ጠባቧ አዳራሽ በሰው ተጨናንቃ የሞቀ ገብያ መስላለች ሙዚቃው ከፍ ብሎ ቀጠለ መምህር አወቀን ተመለከትኩት ደስ አለኝ ወዲያው ሙዚቃውን ቀይሬ ኤፍሬም ማጫወት ቀጠልኩ።አጉረምራሚ ቢኖርም መስሚያ የለኝምና ቦታ ልሰጠኋቸውም ነበር።"አንተ አመፀኛ" መምህሬ በሞቅታ ጮክ ብሎ ጠራኝ። "ያቺን ልጅ አገኘሀት" አለኝ ክፍል ያለ መስሎት ይሁን ባይገባኝም ስለ ልጅቷ ጠየቀኝ።"ሟቿን ነው" አልኩት የምሳፈጠውን መምህሬን የጎሪጥ እያየሁት።ሁኔታዬ ያልገባው መምህሬም "በል ነገ እናወራለን" ብሎኝ ደርባባዋን ሚስቱን ይዞ ከጭፈራ ቤቱ ሹክክ ብሎ ወጣ። "አይ መምህሬ" አልኩኝ በእሱ ሁሌም እደነቃለሁ። ለሊቱን ዳንኪራ ላይ አሳልፌ ንጋት ላይ ወደ ቤት ከወፎች ዜማ ቀድሜ ማቅናት ጀመርኩ የሰፈራችንን ግማሽ እንደጨረስኩ አንድ ሰው ተመለከትኩ ከሆነች ጀርባዋን እኔ ላለሁበት መንገድ ከሰጠች ልጅ ጋር በእንባ እየራሰ ያወራል።እሷም እጇን ትከሻው ላይ ጣል አድርጋ "ይሄ አንተን ወደ ኋላ ሊጎትትህ አይገባም መውደቅ መሞት አይደለም እና አታስብ ሁሉን የሚያስብ የማይዘነጋ አምላክ አለ...እ ይህቺን ያዛት ኖሮኝ ባደርግልህ ደስ ባለኝ ግን የለኝም" አለችው።በእጁ የሆነ ነገር እየሰጠችው ከሁኔታው ስረዳ ገንዘብ ነው።'ምኑ ችጋራም ነው በጠዋቱ የሚለምነው' አልኩኝ በውስጤ ልጅቷም ሹራቧን ዝቅ አድርጋ ተሰናብታው ቀልቁለቱን መውረድ ጀመረች ሰውየውም የምርቃት ዶፍ እያወረደ ወደ እኔ ጋር መምጣት ጀመረ።ከአጠገቤ ሲያልፍ አንድ ምርቃት ውልብ ብሎ ከጆሮዬ ዘው አለ "በክፉ የሚያይሽ አይኑን ጨለማ ጉልበቱን ቄጤማ ያደርገው" አሉ። የእውነት እኔ ለልጅቷ አሜን አልኩኝ።
መንገዴን ጨርሼ ወደ ቤቴ ገባሁ እና በቁሜ ደቃቃ አልጋዬ ላይ ተዘረርኩ እና ሬሳ መሰልኩ።
ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ገብቼ ከጓደኞቼ ጋር ዞር ዞር እያልን ያቺ ደንብራ ከክፍል የወጣችዋን "ሟች ነኝ" ብላ እራሷን እንደ ተዋናይ የቆጠረችዋን ልጅ አየኋት። ጓደኞቼን ጥዬ ወደ እሷ ጋር እሮጥኩ።"ሰላም" አልኳት ከጎኗ አብሬ እየተራመድኩ ዝም አለች ዝምታ ውበቷ የሆናት ሴት።"ኧረ በፃድቁ" አልኳት ተመለከተችኝ ቀና ስትል ግን ያቺ ልጅ ካየኋት ከነበራት ውበት ተወልጣለች ፊቷ አብጧል አይኖቿ ቀልጠው ተነርተዋል። እጇን ያዝኳት "እባክሽን ምን ሁነሽ ነው አልኳት" "ለምን ጠየከኝ" ጥያቄዋ ደረቅነቷን ያሳያል። "የእውነት ከልቤ ነው ልቀልድብሽ አይደለም" አልኳት። "እጄን ልቀቀኝ እኔ ጊዜ የለኝም" አለች እጇ ላይ ያለውን ወረቀት እያየች የዊዝድሮ መሙያ ቅፅ ነበር ደነገጥኩ።"ምን ሁነሽ ነው?" ደገምኩላት። "እስኪ ተወኝ መተው አታውቅም" ተቆጣች።"የምተውሽ ስትነግሪኝ ነው" አልኩ "እሺ እንደዛ ከሆነ ጥሩ እንደምታየው ዊዝድሮ ልሞላ ነው በቃ" አለች እጇን ከእጄ ልታስለቀቅ እየታገለች።"ምክንያቱስ?" ሌላ ጥያቄ። "ሁፍ ጅል ነህ እንዴ" ስድቧ ደስ ሲል። ፈገግ አልኩና "ልሁን ችግር የለውም አሁን በይ ተናገሪ" አልኳት። እሷም አንገቷን እንደማቀርቀር አድርጋ "ስራ መስራት ስላለብኝ ነው" መለሰችልኝ። ወረቀቱን ከእጇ መንጭቄ እጇን ለቀኳት።"አምጣው እስኪ አትቀልድ" አለች። "መቼስ እኛ እያለን ስታቆሚ ማየት አንፈልግም ሶስተኛ ዓመታችን ነው ለአንድ ዓመት ብለሽ" ፊቷ ወረቀቱን ቀደድኩት እና "ስራ የምትፈልጊ ከሆነ እኔ አስገባሻለሁ" ስልኬን በወረቀት ፅፌ ሰጠኋት "ደውይልኝ የእውነት ትምህርት ካቆምሽ ራስሽን ይቅር አትይውም" ብዬ ጥያት ሄድኩ። አስተያየቷን መቼም ሳስበው አይኗ ፈጦ አፏ ተከፍቶ ቅንድቧ ተሰቅሎ ነው የሚሆነው። ጓደኞቼን ፈልጌ እነሱ ጋር ተቀላቀልኩ። ስራ አስገባሻለሁ ያልኳት ግን ከልቤ ነበር ያው መስተንግዶ ነገር መች ይጠፋል። ከትምህርት መልስ ስልኳን ብጠብቅም አልጠራም መሸ ስራ ገባሁ ከስራ ወጣሁ ግን አልደወለችም ደነቀኝ ስራውን አልፈለገች ይሆን ወይስ እኔ አልታመንም ብዬ ማሰብ ጀመርኩ። ከከሰዓት ትምህርት አለኝና ፀጉሬን ታጥቤ ልብሴን ቀይሬ ሽቶዬን እየተቀባሁ ስልኬ ጠራ አዲስ ቁጥር ነው።"አቤት" አልኩኝ በአንድ እጄ ፀጉሬን እያስተካከልኩ "እእ ወረቀቴን የቀደድክብኝ ልጅ ነኝ" ልጅቷ ናት። ፈገግ አልኩ እና "እሺ ልጂት በሃሳቤ ተስማማሽ" አልኳት።"እ አዎ የት ነው ስራው" ጠየቀችኝ።"እሱን እንገናኝ ና እነግርሻለሁ" አልኳት።"እ እሺ ከክፍል ስንወጣ በሩ ላይ እንገናኝ ስልክ አልይዝም ነገ" አለችኝ። እንደዛ ሰው ሁሉ ለጉድ እያያት ስልክ የምታወራው ልጅ ከእጇና ከጆሮዋ የማይለየው ሴትዮ አልይዝም ማለቷ ደንቆኛል ምን አልባት ደብሯት ይሆናል ብዬ ብቻዬን ሳይመለከተኝ እና ሳያገባኝ በሷ ጉዳይ ገብቼ ፈተፈትኩ አቦኳሁ ።"እሺ ችግር የለውም" ስልኩን ልዘጋው ስል "ስምህን ግን...." አለች።"ወረቀቴ በይኝ" አልኳትና ዘጋሁት። የእውነት ደስ አለኝ ከባድ ቀጠሮ መስሎ ተሰማኝ ወዲያው የለበስኩትን ልብስ ቀየርኩ። ጥቁር ቲሸርቴን በጥቁር ሱሪ በምወደው ሸራ ጫማዬ ለብሼ ሰአቴን አጥልቄ ከቤቴ ወጣሁኝ። ግቢ ስደርስ ጓደኞቼን አግኝቼ ክፍል ገባን መምህሩ ቢዘገይም አልቀረም እና እስከ አስራአንድ ሰዓት ተምረን ወጣን። ዛሬ ጓደኞቼንም ቻው ሳልል ሮጬ ወደ በሩ አቀናሁ እሷ ቀድማኝ ነበር። "ሰላም" አልኳት።"ሰላም ስራው...." ችኮላዋ ገርሞኛል። "የምን መጣደፍ ነው ቡና እየጠጣን እናወራለን አልኳት።"አይ አልችልም እባክህን ስራውን በቶሎ ንገረኝ" ብላ በተማፅኖ አየችኝ። አቤት አስተያየት አቤት የአይኖቿ ውበት።"እሺ እነደዛ ከሆነ እየተራመድን ማውራት እንችላለን" ብያት መንገዱን አብረን መጓዝ ጀመርን። "ስራው ያው የምሽት መስተንግዶ ነው" አልኳት። ቆመች "ምነው" አልኳት።"እኔ እኮ በማታ መስራት አልችልም ሰካራሞችስ" አለች።"ለእሱ አታስቢ እኔ የምሰራበት ቤት ስለሆነ እኔ እጠብቅሻለሁ ትምህርትሽን ከማቆም ይሄ ይሻላል" አልኳት።ፍርሃቷ እህቴን አስታውሶኝ እህቴ ከማግባቷ በፊት የምሽት ስራዎችን ትሰራ ነበር። ነገርግን ብዙ ስቃይ አይታለች ጤናዋን አጥታለች ተደብድባለች በገዛ ጓደኛዋ ተሽጣ ከአውሬ ድናለች በመጨረሻም ግን እግዚአብሔር መልካም ባል ሰጥቷት አሁን ላይ በችርችሮ ሱቅ ውስጥ እየሰራች ነው።ህይወቷን በሰላም እየመራች ነው።ለዚህች ልጅም ይህ ስራ ያስፈልጋታል ግን የማታ ወንዶች አውሬ ናቸው እና ከተመለከቷት አልፈዋት አይሄዱም እሷ ማለት በመንገድ ላይ የበቀለች ፍሬ ሳትሆን የተሸሸገች ፅጌረዳ ናትና እንዳትቀጠፍ ልጠብቃት ግድ ይለኛል። ልጅቷ አመነታች።"የእውነት አትፍሪ ስራው ያስፈልግሻል ያልተፈጠረ ተራራ ፈጥረሽ አትጨነቂ" አልኳት። ብዙ ካመነታች በኋላ "እሺ ግን ክፍያቸውስ" አለች። "ከክፍያው በፊት ግን አንድ ነገር ማወቅ አለብሽ ቤቱ ሀብታሞች ናቸውና የሚመጡት መዘነጥ እና ማማር አለብሽ ያው ቆንጆ ብትሆኚም ተጨማሪ ድምቀት ልትጠቀሚ ይገባል።" አልኳት የቤቱን መተዳደሪያ። "እሺ ክፍያውን...."አለችኝ። "ክፍያውን እርግጠኛ አይደለሁም እና ማታ አብረን ሄደን ማናጀሩን ማውራት እንችላለን።"ብዬ ከመመለሴ "እሺ በቃ እእ ወረቀቴ ቻው አመሰግናለሁ እደውላለሁ ማታ" እየሮጠች ከአጠገቤ ርቃ ተጓዘች።ጠፋች....የተጨነኩት ቀጠሮ በሩጫ ተገናቀቀ አጃሂብ አልኩኝ። ግን ደግሞ ምሽትም አለ ውበቷን በጨረቃ ብርሃን ለማየት ጓጉቻለሁ።

ትመጣ ይሆን እያልኩ እያመነታሁ ወደ ቤቴ የሚወሰደው መንገድ ብቻዬን እያወራሁ መንገዴን ጀመርኩ።
❤❤ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ 🌹🌹
💙አልናገርም💛
በግጥም መንደር ብቻ!!
@yebezawit2
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
✔✔✔ድምፅ መስጠት አትርሱ✔✔✔
💚💚ይቀጥላል💚💚
❤❤ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ 🌹🌹
💙አልናገርም💛
በግጥም መንደር ብቻ!!
@yebezawit2
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
✔✔✔ድምፅ መስጠት አትርሱ✔✔✔
💚💚ይቀጥላል💚💚
📖📖የተወደዳችሁ አንባብያን
ከዛሬ ጀምሮ የዝግጀት ማስተካከያ አድርጊያለሁ❤❤❤
በዚህም መሰረት
🕊አልናገርም😍ተከታታይ ድርሰት ሰኞ ዕረቡ ዓርብ ቅዳሜ እሁድ
❤የእናንተ አስተያየት❤ ማክሰኞ
❤እውነተኛ ታሪክ(በቅርቤ ካሉ ሰዎች) እሁድ
❤የግጥም ግብዣ ቅዳሜ
😍😍የማቀርብ መሆኑን በትህትና እገልፃለሁ 🙏🙏🙏
እወዳችኋለሁ ❤❤❤❤
ከዛሬ ጀምሮ የዝግጀት ማስተካከያ አድርጊያለሁ❤❤❤
በዚህም መሰረት
🕊አልናገርም😍ተከታታይ ድርሰት ሰኞ ዕረቡ ዓርብ ቅዳሜ እሁድ
❤የእናንተ አስተያየት❤ ማክሰኞ
❤እውነተኛ ታሪክ(በቅርቤ ካሉ ሰዎች) እሁድ
❤የግጥም ግብዣ ቅዳሜ
😍😍የማቀርብ መሆኑን በትህትና እገልፃለሁ 🙏🙏🙏
እወዳችኋለሁ ❤❤❤❤
Forwarded from መቃን ዲጂታል መጽሔት (✏️ⓐⓜⓐⓝ)
የብራና የግጥም ውድድር ተወዳዳሪወች
-ያፌት ኮድ 04
-አረብ ኮድ 10
-anaf ኮድ 02
-ሉኡል ዘ ማሪያም ኮድ 01
-ኤርሚያስ ዘ ደብረ ቁስቋም ኮድ 13
-በፍቃዱ መላኩ ኮድ 05
-አስናቀ ሞገስ ኮድ 06
-ሳሙኤል ኮድ 03
-ሒሻም ሙነወር ኮድ 08
የመወዳደሪያ ግጥም አስገብተዋል።
@kene_tobeya
-ያፌት ኮድ 04
-አረብ ኮድ 10
-anaf ኮድ 02
-ሉኡል ዘ ማሪያም ኮድ 01
-ኤርሚያስ ዘ ደብረ ቁስቋም ኮድ 13
-በፍቃዱ መላኩ ኮድ 05
-አስናቀ ሞገስ ኮድ 06
-ሳሙኤል ኮድ 03
-ሒሻም ሙነወር ኮድ 08
የመወዳደሪያ ግጥም አስገብተዋል።
@kene_tobeya