Telegram Web Link
የግጥም መንደር
የጥበብ መጀመሪያ ......

getem bech@
https://www.tg-me.com/yebezigetmoch
💋ክርስቶቤል💋
አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ ወደውታል❤️ ወይስ ይቋረጥ 👎 ያላችሁን አስተየያት @yebezawit2 ላይ አድርሱኝ!
🌸 ፍቅር ማለት እውነት ነው 🌸
🌺 ሰናይ ምሽት🌺
🔥🔥🔥🔥🔥🔥
ከብዙዎቹ በጥቂቱ
አሁንም ስለምትሰጡኝ አስተያየት አመሰግናለሁ ❤️❤️❤️🙏🙏🙏
@yebezawit2 ላይ ያድርሱኝ🍟
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
🍃🌹🍃.......


❤️እውነተኛ ፍቅር ሁሌም ቃሉ ትክክል ነው ሽንገላን አያውቅም፤ችግር አይበግረውም፤ስህተትህን በትግስት እያለፈ መልካም ነገርን ያስተምራል።መሆን ምን ማለት እንደሆነ እየኖረ ያሳየሀል።።።።😘



ከወደዱት ሼር ያድርጉት

🌹 @yebezigetmoch
🌹 @yebezigetmoch
🌹 @yebezigetmoch


🌹🌹______
Joine_and_share
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
➮በምን ይለያያል ውዴታና ፍቅር?

➦ውዴታ በጊዜ የተገደበ ነገር ነው እናም የወደድከውን ነገር(ሰው) ከጊዚያት ቡኃላ ልትጠላው ትችላለህ።

➦ፍቅር ግን በጊዜ የማይገደብ የጠለቀ ስሜት ነው፤ ያፈቀርከው ሰው ፍፁም አትጠላውም ፤ እስከህይወትህ ፍፃሜ ድረስ በልብህ ውስጥ ይኖራል።

,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,
❤️❤️❤️ከፍቅር❤️❤️❤️
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
ያለአንቺ እኔ ማለት.......በቁሙ የሞተ ነኝ....አንቺ ነሻ የሞት መድሃኒቴ
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
❤️ፍቅር ማለት ይቅር ማለት ነው!ፍቅር እውነት ነው
JOIN US @yebezigetmoch
@yebezigetmoch
❤️ከእናንተው የተሰጡኝ አስተያየቶች🙏


#አናንያ ክርስቶቤልን በጣም ነው የምወደው በየቀኑ ስለ አቡሻ እጨነቃለሁ እናም በቶሎ አድርሽን እባክሽን

#king z ቻናልሽን በቅርቡ ነው የተቀላቀሉት ግን ደስ የሚል እና የማይሰለች ነው ከዚህ የተሻለ ነገር እጠብቃለሁ

#ye_enatua_lij ቤዚዬ በጣም ነው የማከብርሽ

#amani ቤዚዬ ጥሩ ነገር ስለምትፅፊልን ደስ ይለኛል ግን ደግሞ ታሪኩን ለቀሽልን ሌሎች ፅሁፎችን ባትደርቢባቸው ሌላው ግን ደስ ይላል በርቺልኝ

#የማርያም ነኝ ጥሩ ነገር ነው የምትለቂው በተለይ ክርስቶቤልን እወደዋለው እና ቀጥይበት እንደ ሀሳብ ግን ትረካ ብትጀምሪልን ደስ ይለኛል!

ለሰጣችሁኝ ፍቅር አክብሮት አስተያየት እጅጉን አመሰግናለሁ 🙏
አሁንም የምክር የድጋፍ አገልገሎት ከፈለጋችሁ አስተያየት መስጠት ከወደዳችሁ @yebezawit2 ላይ ያስቀምጡልኝ🙏🙏🙏💋💋💋
🔥🔥መልካም ቀን🔥🔥
🍟 @yebezigetmoch
🍟 @yebezigetmoch
❤️❤️❤️እየጠበኩህ ነው❤️❤️❤️

መዘግየትህ ሀሳብ ቢገባኝም
አስባለሁ ብዬ አታረፍድም
የልቤን ለልብህ እስክትነግረው
በተስፋ እየጠበኩህ ነው!!!

ቤዛዊት የሴት ልጅ
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
😰😰😰መቼ ተለየሁሽ❤️❤️❤️

የራኩኝ ልምሰል እንጂ ቅርብ ነኝ
ሳታይኝ እኔ ከጎንሽ ነኝ
ከትላንት ትውስታ እየጨለፍኩኝ
የዛሬ ኩርፊያሽን እሽራለሁኝ።
አታርፍድ አትበይኝ አትቅር
መች ይወጣልኝና ያንቺ ፍቅር
ከትላንት ብሷል ጨምሮ መውደዴ
ሟች ነኝ ካጣሁሽ ከመንገዴ
እንድኖር አትፍቀጂ የሙታንን ኑሮ
በዝምታሽም አለ ልቤ ተሰብሮ።
አታርቂኝ መቼ ትመጣለህ ብለሽ
ከጅምሩ እኔ መች ተለየሁሽ!😍

በቤዛዊት የሴት ልጅ
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
👌👌😘😘እጅግ ስለወደድኩት❤️🙈
ለላክሽልኝ #ሄዋን አመሰግናለሁ
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
╔══❖•ღڿڰۣ🇪🇹ڿڰۣღ •❖══╗​​​
💖 ክርስቶቤል ♥️
​​╚══❖•ღڿڰۣ💝ڿڰ ۣღ•❖══╝​​​​
.
••●🍃🌹🍃●•

፨፨፨፨፨፨፨፨ምዕራፍ ሁለት፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ክፍል አምስት ፭
😊ደራሲ ቤዛዊት የሴት ልጅ😊

አሁን አውርታኝ አሁን የምትናፍቀኝ ኤዲ ከእኔ እየራቀች መሆኗን ሳስብ ልቤ ይደክማል። በሀዘን ተጠቅልዬ ተኛሁኝ።......ቀኑ ግን በሀሳብ ሊገፋልኝ አልቻለም እንኳን እኔ ህልሜም የእሷ ሆኗል አይኖቼ ከመከደናቸው ከመቅፅበት ትመጣለች። አይ ኤዲ ምን ያህል እንዳፈቀርኳት ምን አለ ልቤን ከፍታ ባየችልኝ ጉዳቴን። እነ ናታን መጎዳቴን ሰምተው ነበር እቤት የመጡት ክፍሌ ውስጥ ቁጭ ብለን ማውጋት ጀመረን "አንተ ግን መቼ ነው የምትነግራት" ናታን ጠየቀኝ። "አላውቅም በቃ የኔ አይደለችም በዚህ ሰአት ነግሪያት ልቧን መስበር አልፈልግም ደስተኛ ናት ከዛ ዳዊት ጋር" አልኳቸው ብሽቅ ብዬ። "ሳታውቀው እንዴት ልትመጣ እና ልትቀርብህ ትችላለች ንገራት በቃ ውሳኔው የራሷ ነው" አለኝ ዘኪ። እኔም በሀሳብ ተከዝኩኝ በዶክተሩ ምንም ቢሆን ምንም ደስተኛ ሆናለች ባይታወቃትም እየራቀችኝ ነው። ከዚህ በላይ መጓዜን ሳስብ ደግሞ ህመሙ ወደ ኋላ ይጎትተኛል። "እ ምን አሰብክ ወይ እኛ እንንገራት" አለኝ ናታን። "አይ እራሴ እነግራታለሁ አትጨነቁ" ብያቸው ተነስቼ ልብሴን መቀየር ጀመርኩ። "አንተ አሁን ልትነግራት ባልሆነ" አለኝ ናታን። "ኧረ ደብሮኛል ፑል እንጫወት ኤዲን ቢያንስ ለመርሳት ልሞክር" ብያቸው ተያይዘን ከቤት ወጣን ሁልጊዜ የምንጫወትበት ፑል ቤት ገብተን መጫወት ጀመርን። ግን በምንም ልረሳት አልቻልኩም ለአፍታ እንኳን ልቤ እሷን አለማሰብ አይችልም። ጥዬ ወጣሁኝ ጓደኞቼንም ትቼ እጄን ኪሴ ውስጥ ከትቼ መንገዴን በዝግታ ቀጠልኩኝ። "አቡሻ አቡሻ" ቀበጧ ሜላት ነበር አይቼ እንዳላየ ሰምቼ እንዳልሰማ መራመዴን ቀጠልኩ እሮጣ መጥታ መንገዴን አስቆመችኝ። "ዛሬም ትጠላኛለህ አይደል" አለችኝ። የለበሰችው አጓጉል ቀሚስ አሳምራዋለች መከረኛ ልቤ ግን ለኤዲ ተመኘላት።"አልጠላሽም ግን አልፈልግሽም" አልኳት። "እሺ አውቃለሁ አስጨንቄሀለሁ ግን በጣም ይቅርታ በቃ ጓደኛ ብቻ እንሁን ደግሞ ኤደንን እንደምትወዳት አውቃለሁ" ብላ አብራኝ መራመድ ቀጠለች። የተረጋጋ ነገር ባይባትም ቀበጥነቷ አልቀቃትም። "በምን አወቅሽ" አልኳት። "ያስታውቃል ስትገባ ስትወጣ ከእሷ ጋር ነህ ብቻዋን እንድትሆን እንኳን እድል አትሰጣትም ደግሞ አንተ ከሴት ጋር ታይተህ አይታወቅም" አለችኝ። ፈገግ አልኩና "ኤዲ የምትገርም ልጅ ናት ብታውቂያት ትወጃታለሽ" አልኳት። ሜላትም "ኧረ እኔ አልወዳትም" መልሷ አስደነገጠኝ "እንዴ ምን አደረገችሽ" አልኳት። "እንደዛ እየወደደችህ ስታስመስል ታናደኛለች" ጭራሽ አወዛገበችኝ። "ምንድነው የምትዘላብጂው የሰከረ ወሬሽ ደግሞ ጀመረሽ" አልኳት። "እውነቴን ነው እኮ አቡሻ የሆነ ቀን ከአንተ ጋር ሆና እየሳቀች ስትላፉ አይቼ በቅናት አብጄ ነበር እና ክፍል ስትገባ ላወራት ሲሄድ በሆነ በቀይ ክር በተሰፋ ብዙ ወረቀት ባለበት ደብተር ላይ እየፃፈች አገኘኋት" ቀና ብዬ ተመለከትኳት። "በደብተሯ ልስቅ ወሰድኩባት እሷ ግን ውስጡ ያለውን ፅሁፍ እንዳላነብ ለመነችኝ እኔም ስገልጠው የሆነ ስም ፅፋ እወደዋለው አይወደኝም ስለእሱ አስባለው አያስበኝም ምናምን ብላ ፅፋ ነበር" "ማነው የሚለው ስሙ ደግሞ ከእኔ ጋር ምን ያገናኘዋል" ብዬ አፈጠጥኩባት። "እውነቴን አቡሻ ስለ አንተ ነው የፃፈችው ከአነበብኩት በኋላም እንዳልነግርህ ለመነችኝ ካመንከኝ እመነኝ" መራመዴን አቁሜ ተጠግቼ አይኗን እየተመለከትኩ "ቀልድ አልወድም ሜላት" "እንዴ እኔ አልቀለድኩም የነገርኩህ ያ ጊዜ ያሳበድኩህ ጊዜ ስለሚቆጨኝ ነው እንጂ አያገባኝም ስሙን ደግሞ ሳስታውስ እነግርሃለሁ" ብላኝ ጥላኝ ሄደች።

መንገዱን አያጎተመተምኩ ገፋሁ። ካቀረቀርኩበት ቀና ስል ግን ኤዲን ከዳዊት ጋር አየኋት እሷም ስትመለከተኝ ደንግጣ ቆመች እኔም ቆሜ ተመለከትኳት ቁና ተንፍሳ "አቡሻ" ብላ ምንም እንዳልመሰለው ሰላም አለችኝ። "እዚህ ምን እየሰራቹ ነው" አልኩኝ። ዳዊት ኤዲን አቅፎ ወደ ራሱ እያስጠጋት "ፍቅር ወክ አማረኝ ብላ ነው" አለኝ። አይኖቼ ደም ለበሱ። "አሪፍ በቃ ተዝናኑ" አልኩኝ "ጉዳት እንደ ደረሰብክ ነገረችኝ ሳይህ ግን ደህና ነህ" አለኝ "ያው የወደቀ ሁሉ አይሰበረም የታመመም ሁሉ በሽተኛ አይመስልም" ጥያቸው መንገዴን ቀጠልኩኝ። ስልኬ አቃጨለ ቀበጧ ሜሪ ናት "አንተ አሁን ትዝ አለኝ ክርስቶቤል ነው የሚለው" አለችኝ። እኔም ስልኩን ዘጋሁት ክርስቶቤል ማነው እኔ አይደለሁም ደግሞ ለምን ስለ እሱ ለኔ መናገር አልፈለገችም እንደ ማፈቅራት ስለምታውቅ ነው ወይስ ምንድነው......የሀሳብ ጋጋታ አዕምሮዬን አጨናነቀው።.....ዛሬ ክላስ ስላለኝ ቁርሴን በልቼ ወደ ግቢ ሄድኩኝ። ውስጤ በኤዲ ሳላውቅ አዝኖባት ተበሴጭቻለሁ። ለምን እንደሆነ እኔም ግራ ገብቶኛል። ከመኪናው ወርጄ ወደ ግቢ ስገባ ኤዲ ጥቁር ሻርፗን ጭንቅላቷ ላይ ጣል አድርጋ አቀርቅራ ጣቶቿን እየፈተለች ነበር። ቆሜ አተኩሬ ተመለከትኳት ቀና ብላ ስታየኝ አልፊያት ሄድኩኝ። "ጠብቀኝ አቡሻ" ብላ ራመድ ብላ አስቆመችኝ። "አዝነህብኛል" አለችኝ። "ለምን አዝንብሻለሁ" አልኳት ግንባሬን ቋጥሬ። "አድምጠኝ ዳዊት እኮ......" ንግግሯን እንድትጨርስ እድል ሳልሰጣት "መብትሽ ነው እኔ እኮ ወንድምሽ ነኝ በዛ ላይ በስጋ ያልተዛመድን ከፈለግሽም አትንገሪኝ" አልኳት። የእውነት የኔን ጉዳት መረዳት የሚችለው ልክ እንደ እኔ የመፈቀር ሳይሆን የማፍቀር እጣ ወጥቶለት የተገፋ ሰው ነው። ፍቅር ሲገባኝ መድሃኒት ነው እኔ ግን በኤዲ በያንዳንዱ ስራዋ እና ውሳኔዋ እየታመምኩ ነው። አድናኝ ትገለኛለች መጣች ስል ሄዳለች። ዥዋዥዌ! ውስጤ ተስፋ ቆርጦባት ይሁን ፍቅሯ ቆርጦልኝ አይኔ አይኗን ማየት እንኳን ከበደው። "አልገባኝም እሺ ይቅርታ ከፈለክ ልቀጣ" አለችኝ አይኔን በምርመራ አይን እየተመለከተች። "አሁን የምሰራው ስራ አለኝ ደህና ዋይ" ጥያት ሄድኩኝ። ምን አልባት እንዲህ ስሆን ለተመለከተኝ ባለጌ ሊለኝ ይችል ይሆናል የታመምኩት ግን እኔ ነኝ ፍቅሬን አሳልፌ መስጠቴ ሳያንስ ከሌላ ሰው ታሪክ የምሰማ እኔ ማለት ቅርብ ሆኜ የራኩኝ ሆኛለሁ። ላይብረሪ የምሰራው ስራ ሳይኖር ቁጭ ብዬ በሞባይሌ ፌስቡክ እየተጠቀምኩ ነበር ናታን ቴክስት የላከልኝ። "ኤደን ወድቃለች የግቢው መውጫው ጋር" ላይብረሪ ያሉት ተማሪዎች እስኪረበሹ ክፍሉን አተረማምሼ እየሮጥኩ ወጣሁኝ። ስደርስ ግን ነቅታ ነበር። የከበቧትን ገፍትሬ ከአጠገቧ በርከክ አልኩኝ። "ሂድ የምትሰራው ስራ አለብህ" አለችኝ በደከመ ድምጿ እኔን ጥፋተኛ ልታደርገኝ ነው። የሰማሁትን ብነግራት ምን አገባህ እንዳትለኝ ፈራሁኝ። "እንደዚህ ሆነሽ ነው የምገባው ይልቅ ምግብ በልተሻል" እጆቼን ይዛ እንደምንም ተነሳች እና ልብሷን በዝምታ ማራገፍ ጀመረች። የመኪና ክላክስ ተደረገለን ሁሉም የቆመው ተማሪ ዞረ ዶክተር ዳዊት ነበር ጥላኝ ወደ እሱ ገብታ ሄደች እኔም በቆምኩበት ቦታ ተመልሼ ተቀመጥኩኝ። ተማሪው አንድ በአንድ ተበተነ እኔ ግን እዚያው ነኝ ገፍታኝ አርቃኝ ከሄደችበት። ዝምታዬ ህመሜን ሊነግራት ቀርቶ ይባስ አሳጣኝ። "ይቅርታ አቡሻ አንተ ጋራ እንዳልደውል ነግራኝ ለእሱ ደውላ ጠራችው አዝናለሁ" ዘኪ ነበር እንባዬን መቆጣጠር አቃተኝ። የምወደው እሷነቷ የለም። ራቀችኝ.....በቃ እኔንም አራቀችኝ........ጭንቅላቴን በእግሮቼ መሀል ደብቄ ተንሰቀሰኩኝ። አሁንም
እንዲህም ሆና አፈቅራታለሁ። አንዳንዴ እንዴት ነው ሰው አንቺ ስጠይኝ እኔ የምወድሽ ክርስቶስ አይደለሁም የሚለው እላለሁ። ይኸው እኔ በደከመው ሰውነቴ እሷን እላለሁ በዛለው እግሬ ወደ እሷ ለመቅረብ እራመዳለሁ። ግን ዝያለሁ......እንባዬን ጠርጌ ተመልሼ ወደ ግቢ ገባሁኝ። አንድም ቃል ሳይወጣኝ ቀኑ ሙሉ ውዬ ወደ እናቴ ቤት ተመለስኩኝ እና ጥናቴን ቀጠልኩኝ። መደበቂያዬ እሱ ነው ግን በደብተሬም በመፀሐፌም ሳይቀር ከትቢያት ይዣታለው። የጀመርኩትን ፅሁፍ አቁሜ ወደ አልጋዬ ሄድኩኝ እና ግድግዳውን ተደግፌ ስለ ደበቀችኝ ስለ ክርስቶቤል ማሰብ ጀመርኩኝ። እናቷን ለመጠየቅ አሰብኩ ግን ደግሞ እሳቸው ባያውቁትስ እያልኩ ሀሳቤን በሀሳቤ ሻርኩት።.........

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ይቀጥላል፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
#ታሪኩ ቶሎ ቶሎ እንዲለቀቅ ድምፅ ይስጡ!
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
🔥 ••●◉Join us share 🔥
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
የግጥም መንደር
😍ክርስቶቤል💖
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺🌺»̶̥✽̶┉┉┄
ለአስተያየት ለሐሳብ መስጫ @yebezawit2 ይጠቀሙ!
╔══❖•ღڿڰۣ🇪🇹ڿڰۣღ •❖══╗​​​
💖 ክርስቶቤል ♥️
​​╚══❖•ღڿڰۣ💝ڿڰ ۣღ•❖══╝​​​​
.
••●🍃🌹🍃●•

፨፨፨፨፨፨፨፨ምዕራፍ ሁለት፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ክፍል ስድስት ፮
😊ደራሲ ቤዛዊት የሴት ልጅ😊

እንቅልፌን ተቼ የስልኬ ድምፅ አቃጨለ እንደምንም አይኔን ገልጬ አየሁት አዲስ ቁጥር ነው። ዘግቼው መልሼ ተኛሁኝ ድጋሜ ተደወለ በሶስተኛው አነሳሁት "አንተ ግን ክፉ ሰው ነህ ያውም መጥፎ" ኤዲ ነበረች ዛሬም ሰክራለች። "የት ነሽ" አልኳት ሰአቴን እያየሁ።"ምን አገባህ ምንም አያገባህም የትስ ብሆን" አለችኝ። "ኤደን የት ነሽ" ደገምኩላት። ስልኩን ለሌላ ሰው ሰጠች "ሄሎ ወንድሜ" አለኝ ከስልኩ ውስጥ ያለው ድምፅ "እባክህ ናና ውሰዳት ወደ መሳለሚያ ነን" አለኝ ደግሞ የማላውቀው ሰው እኔም በእሷ ለመጨከን ብቃቱም ሀሳቡም የለኝም እና ለኤዲ ብዬ በሹራቤ ላይ ሹራብ ደርቤ የክፍሌን በር ቀስ ብዬ ዘግቼ የእናቴን መኪና ይዤ ወጣሁኝ ወጣቱ ያለኝ ቦታ ስደር ግን ማንም ሰው አልነበረም ብደውልም የሚያነሳው የለም። ጨዋታ ነው?! አልኩኝ በብስጭት። "ማነህ?" የአንድ ሰው ድምፅ ተሰማኝ ዞሬ ተመለከትኩት የህንፃው ጠባቂ ነገር ነው። "እእ እዚህ የሆነች ልጅ ነበረች ደውለውልኝ ነው" አልኩት ምን አልባት ካያቸው። "አንተ ነህ እንዴ ልጁ ምነው ቆየህ ላስቀምጣት ስላልቻልኩ ሰደድኳት" አለኝ የሄደችበትን አቅጣጫ ጠቁሞኝ እኔም መኪናዬን አስነስቼ ቁልቁለቱን መውረድ ጀመርኩኝ ብዙም ሳልርቅ ግን ኤዲን አየኋት። መኪናውን አቁሜ ወረድኩኝ እና ከወደቀችበት አነሳኋት እሷ ግን እያስመለሰች ነበር። እንደዚህ መሆኗ ግራ ገብቶኛል። "አንተም ያው ነህ" አለችኝ አፏን እየጠረገች። "ነይ እሺ ተነሺ" ብዬ ወደ መኪናው አቅፌ አስገባኋት እና "ያምሻል ከመቼ ጀምሮ ነው መስከር የጀመርሽው" አልኳት እሷም እጇን በአፏ ጭና ማልቀስ ጀመረች። "ምን ሁነሽ" አልኳት እሷ ግን ቃል ሳይወጣት ነበር የምታለቅሰው። "ወደቤት አድርሰኝ" አለች ዞራ ሳትመለከተኝ። "እንደዚህ ሆነሽ" "እናቴ አትገፋኝም" አለችና ተመለከተችኝ። በእኔ ወይም በዳዊት እንዳዘነች ግልፅ ነው።......ሰፈሯ አድርሻት እኔም ወደ ቤቴ ተመለስኩኝ። ፀሀይ ብትወጣም እኔ ግን ትላንት ላይ ነኝ። ከቤት ምንም ሳልል ነበር ወደ ግቢ የሄድኩት ስደርስ ግን ጓደኞቼ እንጂ ኤዲ የለችም። "አልመጣችም" አልኳቸው። ናታንም "እናንተ ግን ለምን እንደ ሰለጠነ ሰው አታወሩም" አለኝ። እኔም "ምን ብዬ ላውራት እስኪ ነገረኝ በራሷ ጥፋት ዘጋችኝ ምን ያህል እንደምወዳት አይገባትም" ተበሳጨሁ። "አትወዳትም" የዘኪ መልስ አበገነኝ "የእውነቴን ነው ፍቅር እኮ ልክነት አይደለም እስኪ የኛን ጓደኝነት ተመልከት እንጣላለን እንታረቃለን እናጠፋለን እናለማለን እንደባበራለን እንነፋፈቃለን ፍቅር ይሄ ነው ከወደድካት መልሳት" ብሎኝ ጥሎኝ ወደ ክፍል ገባ እኔ ግን ከተቀመጥኩበት ሆኜ እየጠበኳት ነበር ልክ ተማሪው ሁሉ ገብቶ ከግማሽ ሰአት በኋላ ኤዲ እየተጣደፈች ወደ ግቢ ገባች። "ኤዲ ደህና አደርሽ" አልኳት አብሪያት እየተራመድኩ። "እግዚአብሔር ይመስገን" መሀላችን ዝምታ ሰፈነ። ደረጃውን እየሮጠች ስትወጣ እጇን ያዝኳት "ምንድነው" ግንባሯ እንደተጨማደደ ነው። "እጠብቅሻለሁ እስክትወጪ ጥለሺኝ እንዳትሄጂ" ብያት ተመልሼ ወደ ውጪ ወጣሁኝ። ለመጀመሪያ ጊዜ ትምህርት እያለኝ ሳልገባ። ለእኔ ትምህርቱን እናቱ አባቱ ጓደኛው ላደረገ ሰው ከባድውሳኔ ነው።ግን ይሄ ሁሉ በእሷ በኤዲ ነው የሆነው። ክላስ ጨርሳ ስትወጣ አየኋት። ቦርሳዬን ይዤ አብሪያት ከግቢ ወጣሁኝ። "እሺ እየሰማሁህ ነው" አለችኝ። ረጅም ቀሚሷን ሰብሰብ አድርጋ ይዛ። "ምን ሁነሽ ነው ኤዲ እስኪ እንደ ትልቅ ሰው እናውራ" አልኳት። ልቤ እየተሰበረ። "እኔ ህፃን ሆንኩኝ እንዴ" ወደ ፀብ ተረጎመችው። "ኤዲ በፈጠረሽ ፊት አትንሺኝ ተቀምጠን እናውራ" አልኳት። "የምሰራው ስራ አለኝ" "እጠብቅሻለሁ" "በጣም እቆያለሁ" "ችግር የለም እስካወራሽ እጠብቅሻለሁ" ቆመን ተከራከርን። "በቃ ማወቅ የፈለከው ለምን እንደሰከረኩ ነዋ....አልቻልኩም እኔ ለዳዊት ቅምጡ ነበርኩ ሚስቱ መጥታ አዋረደችው ያውም ነፍሰጡር ነች የሰው ትዳር በተንኩኝ አሁን ሁሉም ኤደን ኤደን ይላል በቃ ከዚህ አለም ወስዶ የሚያጠፋኝ በቃ ሌላ አለም የሚያሰየኝ ሰው ስፈልግ ጭራሽ ሌላ ማቅ ተጨመረበኝ የሚወለደው ልጅ እኮ የለ አባት ሊያድግ ነው አንተም እራቀኝ ብዙ ነገርህ ይበላሻል እኔን ለእኔ ተወኝ" እንባዋ ጅረት ሆኖ ይወርዳል። በአንድ በኩል ውስጤ በደስታ አበራ ሀዘኗ ግን አሳዘነኝ። "ኤዲ ይቅርታ ግን እኔ ልተውሽ አልችልም" አልኳት። ቆሞን ስንጨቃጨቅ የሚመለከተንን ሰው አስተውላ። "የላከህ ሰው አለ እንዴ በቃ ተወኝ" ብላ መንገዷን ቀጠለች።እኔም እየተከተልኳት "አታምኚኝም ማለት ነው" ጠየኳት። "እንደፈለክ አስበው እኔ ግን የራሴ ችግሮች ይበቁኛል" አለች። "እሺ በቃ ስትረጋጊ ደውይልኝ" ብያት ለመንገር የቋመጥኩትን ፍቅሬን ዛሬም ሸሽጌ ተመለስኩኝ። ግን አዲስ የተስፋ ብርሃን ተለኩሶልኛል ዳዊት ከዚህ በኋላ የለም።ተመስገን አልኩኝ። ግን ደግሞ መከፋቷ የማይደርቀው እንባዋ የልቤን ህመም ቀስቆሶታል። በዚህ ጉዳቷ ውስጥም ደግነቷን ነው የተመለከትኩት ለልጁ ለፈረሰው ትዳር ጭንቀቷ አስደንቆኛል። ኤዲ በየቀኑ እንድወዳት የሚያደርገኝ ነገሯ ንፁህ ደግነቷ ነው።ከቤቴ ደርሼ ወደ ክፍሌ ገብቼ ለጓደኞቼ የተፈጠረውን አሳውቂያቸው ኤዲን እየናፈኩ አልጋዬ ላይ ጋደም አልኩኝ።

"አቡሻ ምግብ ቀርቧል" እናቴ ነበረች። "መጣሁ ማም" ብዬ ከክፍሌ ስልኬን ይዤ ስወጣ መልዕክት ገባልኝ። ኤዲ ነበረች "አቡሻ ስለጮውኩብህ ይቅርታ ነገሮች በቶሎ ስለሚያስከፉኝ ነው ወንድሜ" ብላ ነበር የላከችልኝ። ወንድሜ ማለቷን ግን ልቤ ሳይለምደው አልቀረም እና እንደ በፊቱ ግድ አልሰጠኝም። የምግብ ጠረጴዛው ላይ ከቤተሰቦቼ ጋር ተሰየምኩኝ። "ቶሎ ታረጃለሽ ለኔ አትጨነቂ ግን እመኚኝ እኔ ማንም አላከኝም" ብዬ መለስኩላት ምግቡን እየጎረስኩ ስልኬን ነበር የማየው አባዬ በአግራሞት እየተመለከተኝ "ከማን ጋር የምትፃፃፈው" አለኝ። እኔም "አይ ከማንም ጋር አይደለም ከሰው ጋር ነው" አልኩኝ ደንግጬ እማዬም ፈገግ ብላ "መቼስ አውሬ አታወራም አይደል ወይስ መታፈሩ ነው" አለችኝ። አፍሬ ግን አልነበረም ኤዲ ለ'ኔ የምወዳት ልጅ ለእሷ እኔ ደግሞ እኔጃ አላውቅም። የኤዲ መልዕክት ገባልኝ "እንዳውም ጥሩ ነው ትንከባከበኛለህ ከእማዬ ጋር ትዘፍንልኛለህ..ደግሞ ከራስህ በላይ አምንሀለሁ ሀብሉን ረሳኸው" ይላል። ታወሰኝ በቃል ያፀናችው ወንድምነቴ አሳመመኝ ደግሞ ልጎረሰው ያዘጋጀሁትን ወደ ሳህኑ መለስኩት። እና መልሼ ልፅፍላት ስል ሌላ መልዕክት ጨመረች ሌላ ቁስል ሌላ ስብራት ሌላ ፅልመት "ዴቭ እኮ ይቅርታ አንቺን ነው የምፈልገው እያለኝ ነው ጨነቀኝ" ብላ ነበር የላከችልኝ። ውሃውን ተጎንጭቼ ወደ ክፍሌ በለቅሶ ተመለስኩኝ እናቴም ተከትላኝ መጥታ በሬን ብታንኳኳ ግን መልሴ ዝምታ ሆነ። ብሶቴን አይታ ለማታወራው ስብራቴን ለምታውቀው ለመኝታ ክፍሌ በለቅሶ መንገር ጀመርኩ። ሂጂ አግቢው ብላት ልታገባው ነው። እኔ በቃ የምወደድ አይደለሁም ማለት ነው ምንድነኝ ለእሷ የድብርቷ መጫወቻ ወይስ ምን.....ብጮህ የማላወጣው ብናገር ማንም የማያምነው ባለቅስ አንጄቴን የማይቆረጠው በቃ የመረር ሀዘን ስቃይ የሆነ ፍቅርን መታቀፌ ለራሴ አዘንኩኝ።.............
ሌላ ተጨማሪ መልዕክት ደረሰኝ እየተንቀጠቀጥኩ ከፈትኩት "እኔ ግን
በጣም ጠልቼዋለው....ከቻልክ ከእኔ አርቅልኝ ወንድሜ ተከላከልልኝ ደስተኛ የምሆን መስሎኝ ነበር ግን አልሆነም ከዚህ ሰው ገላግለኝ" ይል ነበር። ቀንበሬ ዳግም ተሰበረ። ደስታ ከሀዘን የደባለቀው ስሜት ውስጤን አናወጠው "አንቺን ማንም አያስከፋሽም መቼም እኔ እስካለሁ አትፍሪ" ብዬ ላኩላት እና ፊቴን በመዳፌ አብሼ አልጋዬ ውስጥ ገባሁኝ። ግን ኤዲ መልዕክቴን አልመለሰችልኝም። ሰአቱ ቢሄድም እኔ ግን መልሷን ስልኬ ላይ አፍጥቼ እየጠበኩ ነው ለተመለከተኝ የለየልኝ እመስላለሁ ግን እብድ ሆና ያሳበደችኝ እራሷ ኤዲ ናት። የወፎችን ዜማ ስሰማ ተአምር ሆነብኝ የአይኖቼ ሸፋሽፍት ለአፍታም አልተከደኑም ነበር። ፈተና ስላለኝ ሻወር ለመውሰድ ከክፍሌ ወጣሁኝ። እናቴ ግን ቆሜ ስትመለከተኝ የያዘችውን ብርጭቆ ለቃ አቀፈችኝ። ሳይገባኝ ለካ እነሱንም የዚህ ገፈት ተቃማሽ አድርጊያቸዋለው እናቴን አቅፊያት "ይቅርታ ማም አስጨነኳቹ" አልኳት። "ሁሌም ራስህን ጠብቅ እወድሃለሁ" አለችኝ። እኔም ይቅርታ ጠይቄ ሻወር ወስጄ ምግብ በልቼ ወጣሁኝ።ፈተናው የሚሰጠን ከኤዲ ክፍል ጋር ተደባልቀን ነበር እና ደስ ብሎኛል ፈተናው ሊጀመር ሁላችንም የፈተና አዳራሽ ተገኝተናል። የኮርሱ የመጨረሻ ፈተና ነውና በትንሹም ቢሆን አንብቢያለሁ። ያሳሰበኝ ግን ፈተናው አይደለም ኤዲ ናት መንገድ መንገድ ባይም ኤዲ ግን አልመጣችም ደጋግሜ ስደውልም ስልኩ ዝግ ነው ውስጤም አንዳች ነገር እየረበሸው ፊት ለፊት ካለው ወንበር ተቀመጥኩኝ።ፈተኙ ወረቁትን ሰጥቶን እንድንጀምር አዘዘን እና በሩን ዘጋው። አይኔን አንገታቸውን ደፍተው በሚሰሩት ተማሪዎች እየወረወርኩ ፈለኳት ግን አልመጣችም። አስማሪው "መኮራረጅ አይቻልም ድምፅ ቀንሱ" አለ ሊወድቅ የደረሰውን መነፅር እየመለሰ። በሩ በሀይል ተንኳኳ የኔ ልብ በሀይል መምታት ጀመረ አስተማሪው በብስጭት "የማነው ጋጥወጥ" ብሎ በረገደው። የኤደን እናት ሲታመሙ የጠራቻት ልጅ ነበረች። ትንፋሿን ሰብስባ "አቡሻን ፈልጌ ነው" አለችው። "ፈተና እኮ..... " "አቤት ምንድነው" አልኳት። አስተማሪውን አቋርጬ "ኤዲ ልትሞት ነው ልትሞት ነው" መንታ እንባዋን ዘረገፈችው።.............ይቀጥላል!

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ይቀጥላል፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
#ታሪኩ ቶሎ ቶሎ እንዲለቀቅ ድምፅ ይስጡ!
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
🔥 ••●◉Join us share 🔥
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
የግጥም መንደር
😍ክርስቶቤል💖
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺🌺»̶̥✽̶┉┉┄
ለአስተያየት ለሐሳብ መስጫ @yebezawit2 ይጠቀሙ!
.ከፍቅር


በዙሪያህ ሶስት አይነት ሰዎች ቢኖሩ ጥሩ ነው።

የሚበልጥህ ሰው… ልትማርበት።

ከአንተ ተመጣጣኝ እኩል የሆነ ሰው… እግር በእግር አብረሀው ልትሄድ።

የምትበልጠው ሰው… የነበርክበትን ልታስታውስበትና ልታስተምረው አንተ ጋር ልታደርሰው።
@yebezigetmoch
.... ግን በሚበልጥህ ከቀናህ… በእኩያህ ከተመቀኘህ… በምትበልጠው ከተኮፈስክ… አንተ ሰው ወደፊት ለመሄድ የሆነ ነገር አጉድለሃል።

#ሰናይ_ምሽት

የግጥም መንደር

📩 @yebezawit2
❤️…ናፍቀህኛል በይኝ…የውሸትሽንም ቢሆን…❤️
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
╔══❖•ღڿڰۣ🇪🇹ڿڰۣღ •❖══╗​​​
💖 ክርስቶቤል ♥️
​​╚══❖•ღڿڰۣ💝ڿڰ ۣღ•❖══╝​​​​
.
••●🍃🌹🍃●•

፨፨፨፨፨፨፨፨ምዕራፍ ሁለት፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ክፍል ሰባት ፯
😊ደራሲ ቤዛዊት የሴት ልጅ😊


በቆምኩበት ጉልበቴ ሲከዳኝ ታወቀኝ። ኤዲ ላይ ተስፋ መቁረጥ አልችልም። እኔ ያለ እሷ ምንም ነኝ ብኮሳተርም ባኮርፋት ያለ እሷ ግን ህይወቴ ጣዕም እንደማይኖራት አውቃለሁ። ዛሬ ላይ ግንኙነታችን እየሻከረ ቢለሰልስም የምፈልገው ነገር ቢኖር ከእሷ ጋር ማርጀት ከእሷ ጋር መፋቀር ደግሞ መጣላት ደግመን መታረቅ መነፋፈቅ ከእሷ ጋር መሰለቻቸት በቃ የህይወትን ከፍታ እና ዝቅታ አብሪያት ማሳለፍን እጓጓለሁ። "እባክህን አድናት" ልጅቷ እያለቀሰች ተማፀነችኝ። አስተማሪው በድንጋጤ ነበር የሚመለከተን። ምንም ቃል ሳይወጣኝ በሩጫ ከግቢው ወጣሁኝ። ወደ እሷ ጋር.......ወደ ኤዲ ጋር.....ወደ ምወዳት ሴት.......እየገደለች ወደ ምታድነኝ....ወደ ጉድለቴ ሙላት.......የህይወቴ ፋኖስ.....አለሜ ጋር......የመኖሬ ጉጉት...... እሷን እያሰብኩ በፍጥነት ነበር የምሮጠው። የኤዲ ሰፈር ጋር ስደርስ የግቢያቸው በር ተከፍቶ ሰው ይገባል ይወጣል። አንዲት ቀጠን ያለች ሴት ነጠላዋን አዘቅዝቃ ስትገባ ተመለከትኩ። አይሆንም አምላኬ ከእሷ በፊት እኔ ልቅደም.......በዝግታ እየተራመድኩ ወደ ግቢው ገባው ሰው ቆሞ ከንፈሩን ይመጣል ከአንዱ ጥግ ደግሞ አንገታቸውን ደፍተው ያለቅሳሉ። ወደ ሰዎቹ በቀረብኩ ቁጥር የልቤ ምት ሲጨምር ይታወቀኛል። "የኔ ልጅ ጉድ ልትሰራኝ" የኤዲ እናት ነበሩ። ወደ እኔ መጥተው አቅፈውኝ አለቀሱ። እኔ ግን እጄን አንስቼ ለማቀፍ የሚሆን ጉልበት አጣሁኝ። እንባዬ ያለማቋረጥ መውረድ ጀመረ። ኤዲ አታደርጊውም ብዙ የሚቀረን ብዙ ማድረግ ያለብን ነገር አትሂጂ ኤዲ በፈጠረሽ አትሂጂ....በልቤ ማውራት ጀመርኩ። የቤታቸው በር ሲከፈት የተሰበሰበው ሰው አይኑን ተክሎ መልካም ዜና ሲጠብቅ ዶክተር ዳዊት ነበር። ተናደድኩ "ደህና ናት አሁን" አለ በኩራት ደረቱን ገልብጦ እናቷ ሮጠው ገቡ ጎረቤቶቻቸውም ወደ ውስጥ ዘለቁ። ዶክተሩ እንደጠበኩት ወደ እኔ መጣ።"እዚህ ምን ትሰራለህ አንተ ቆሻሻ" አልኩት ይበልጥ ተጠግቼው። "የማፈቅራት ሴት ለመምጣት አንተን ማስፈቀድ ያለብኝ" የለበጣ ሳቀ። "ስማ አፈቅራታለሁ ስትል አታፍርም እንደዛ ሆና ጥለሀት ሄድክ ማስከር ነው ፍቅር" በበስጭት አፈጠጥኩበት። "ያው ደሀ እኮ መስከር ነው የሚያውቀው" "ሀብታምም ማስከር ነው አላማው" ኤዲ ነበረች በሁለት እናቶች ተደግፋ ትከሻዋ ላይ ጋቢ ተደርጎላት ፀጉሯ ሁለት ቦታ ተጎንጉኗል። "ሶሪ ኤዲ ታውቂያለሽ...." ዶክተሩ ማውራቱን አላቆመም። "በቃህ ተወኝ ተወኝ አቡሻ ደግሞ ጥለኸው ግባ" ብላ ወደ መፅዳጃ ቤቱ ወሰዷት። "ስማ ከዚህ በኋላ አጠገቧ ብትደርስ ቆሻሻ ስራህን ነው ለሙያ አጋሮችህ ለሚሽቆጠቆጡልህ ነግሬልህ የማስረክስህ" መልሱን ሳልጠብቅ ጥየው ገባው።........የተሰበሰበው ሰው ወጥቶ እኔና ኤዲ እናቷ ቀርተናል የኤዲ እናትም "መጣሁ ትርንጎ ጋር ነኝ" ብለው ጣል አድርገው ወጡ። ኤዲም ቡላ የመሰለው ጋቢ ከትከሻዋ እንዳለ እያስተካከለች "ለምን መጣህ " አለችኝ። ይህቺ ልጅ ያማታል እንዴ? አልኩኝ። "ኧረ ኤዲ ለምን መጣህ አይባልም" አልኳት ። ፈገግ ብላ "አዘንክብኝ" አለችኝ።የሆነውን ያወኩኝ መስሏት እኔ ግን የተፈጠረውን አልሰማውም። "ለምን አዝንብሻለሁ አላዝንም በአንቺ መቼም" አልኳት።

"አቡሻ ምን ላድርግ በቃ የእናቴን ነገር ሳስብ እበረታለሁ ግን የማደርገው ሁሉ ወደ ጥፋት እየወሰደኝ ነው። ለ'ኔ ደስታ የተፈጠረ አይመስለኝም ማታ ሁሉንም ነገር ሳስብ የምኖርበት አላማዬ ከምሞትም ምክንያት ጋር ሊመጣጠን አልቻለም በቃ እማዬ ስትወጣ መድሃኒቷን አብዝቼ ወሰድኩኝ ምን ዋጋ አለው አተረፉኝ። አቃተኝ ለምን እኔ ያለምክንያት ተፈጠርኩ" ማቆሚያ የሌለው እንባዋ የልቧን ስብራት ያወራል። "ኤዲ ለምን እንደዚህ አደረግሽ አልልሽም ግን ቢያንስ ከፍቶኛል ብትይኝ እመጣ ነበር። ደስታሽን አብሬሽ እፈልገው ነበር። አንቺ በመሄድሽ የእናትሽ ስብራት መቼም አትጠግኚውም አንቺ ሰባተኛ ሀዘኗ ልትሆኚ ነው" የእውነት ከፍቶኝ ነበር የተናገርኳት። የብርታት ጀንበሬ ያዘቀዘቀች መሰለኝ። "ይቅርታ" "ይቅርታ አትበይኝ ይልቅ በአንድ ነገር ልቅጣሽ" አልኳት። ኤዲ ከኔ ጋር ለእኔ ሆና ሺህ ብዙ ሺህ ስህተቶችን ትስራ ጥፋትም ታጥፋ ለእሷ የማደርገው ይቅርታ የኔን ህይወት ከእሷ በላይ ስለሚያሳምር አይለቅብኝም። "ደስ ይለኛል ምን ልቀጣ" አለች ፈገግ ብላ ተስተካክላ እየተቀመጠች። ......"በጣም ጮክ ብለሽ የምልሽን ትያለሽ" አልኳት። ኤዲም የምላትን ሳታውቅ ከልቧ ሳቀች። "እእ አትይም" አልኳት ኤዲም "ለመጮህ ችግር የለውም ንገረኝ" አለችኝ። "ከዚህ በኋላ አልሞትም አላማ አለኝ ብለሽ ተናገሪ" አልኳት። የእውነትም እብድ ናት ድምጿን ከጠበኩት በላይ ከፍ አድርጋ ተናገረች። "በዚህ ድምፅ አንድ ዘፈን"አልኳት። "ወደ ኋላ አልልም ከእንግዲህ ስለአየሁህ ፊቴ ተስለህ ከተገለጥክልኝ ህያው ተድላ አልሻም በጭራሽ ከአንተ ሌላ......ከሰለሞን እፅ የሚበልጠው የክብር ጌታ ከእኔ ጋር ነው ሁሉም የሚያስተው ሁሉን የሚያስንቅ አለ በልቤ የእግዚአብሔር ፅድቅ......" አይኗን ጨፍና ስትዘምር እናቷም በር ላይ ቆመው በአግራሞት እየተመለከቷት ነበር። "ወደ ኋላ አልልም አልሞትም......የሚወዱኝ አያዝኑም" አይኗን ገለጠች። "አንቺ እብድ አብደሽ ልታሳብጅን ነው" አሏት እናቷ ነጠላቸውን እያጣጠፉ "እናቴ ይቅርታ" አለቻቸው። "አይ የኔ ልጅ ተይው እስኪ ይልቅ ልጁን አታስጨንቂው" አሏት በቀዘቀዘ ድምፃቸው። ኤዲ እያወራችኝ ቆይታ ጋደም ባለችበት እንቅልፍ ወሰዳት። እኔም ትንሽ ሰአት ከእናቷ ጋር አውርቼ ወደ ቤቴ ተመለስኩኝ።.....

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ይቀጥላል፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
#ታሪኩ ቶሎ ቶሎ እንዲለቀቅ ድምፅ ይስጡ!
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
🔥 ••●◉Join us share 🔥
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
የግጥም መንደር
😍ክርስቶቤል💖
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺🌺»̶̥✽̶┉┉┄
ለአስተያየት ለሐሳብ መስጫ @yebezawit2 ይጠቀሙ!
Forwarded from Learn English Language (Bezi Ye Raguel Lij)
በክርስቶስ ክርስቲያን የሆናቹ ውድ የእግዚአብሔር ልጆች እንደምን አመሻችሁ.....እንደሚታወቀው ይህ መንፈሳዊ ቻናል ፅሁፎችን ማድረስ አቋርጦ ነበር አሁን ግን ወደ ትምህርቱ ተመልሰናል እና #በቅርብ_ቀን በልዩ ሁኔታ ስለ #ጸሎት እናቀርባለን...
🙏ጸሎት መቼ ላድርግ?
🙏ጸሎት የት ልፀልይ?
🙏ጸሎት እንዴት ልጸልይ?
ለሚሉ ጥያቄዎች መልስ ይዘን እንመለሳለን።
መልካም አዳር

@gerahite_slusi
@gerahite_slusi

#መምህር_ዘበነ_ለማ
ይህ በቤተ ክርስቲያን መምህር በሆነው በዘበነ ለማ የተከፈተው ቻናል በአድናቂዎቹ እና በወዳጆቹ የተከፈተ እንጂ በመምህር ዘበነ ለማ የተከፈተ አይደለም ቻናሉ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፅሁፎች ይቀርቡበታል።
https://www.tg-me.com/Gerahite_Slusi
2025/07/07 18:17:46
Back to Top
HTML Embed Code: