Telegram Web Link
#ኢድ_ሙባረክ !

🌙🌙🌙🌙🌙

ዉድ የቻናላችን የእስልምና እምነት ተከታይ ቤተሰቦች እንኳን ለ 1441ኛዉ የኢድ_አል_ፈጥር በዐል በሰላም አደረሳቹ!!!

መልካም በአል እንመኛለን

🔰አስከፊ ጊዜ ላይ ነዉ እና ያለነዉ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማረግ በአሉን እናሳልፍ !!!!!
😰😰😰ቀልድ አይደለም😰😰😰

ዛሬ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 88 ሆኗል🙏🙏🙏 የፈራነው እንዳይወርሰን #እንጠንቀቅ እንጸልይ 🙏የዚህን ጊዜ ማለፍ ብቻ መናፈቅ መፍትሔ አይሆንም አንተ አንቺ እኔ ካልተጠነቀቅን በሩቁ ያየነው በእኛ ላይ ይደርሳል እናም እንጠንቀቅ🙏🙏🙏
╔══❖•ღڿڰۣ🇪🇹ڿڰۣღ •❖══╗​​​
💖 ክርስቶቤል ♥️
​​╚══❖•ღڿڰۣ💝ڿڰ ۣღ•❖══╝​​​​
.
••●🍃🌹🍃●•

፨፨፨፨፨፨፨፨ምዕራፍ ሁለት፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ክፍል ስምንት ፰
😊ደራሲ ቤዛዊት የሴት ልጅ😊


ፈተና እንዳለፈኝ የታወሰኝ እነ ናታን ስለተፈጠረው ነገር በስልክ መልዕክት ሲጠይቁኝ ነበር። ተበሳጨሁ ግን ደግሞ ኤዲ ቀርታ በደንብ መስራቴ አጠራጠረኝ። የተፈጠረውን ለጓደኞቼ ስነግራቸው አዘኑ። የስሜቴ ተከፋይ የሰማይ ስጦታዎቼ ናቸው ጓደኛ ከሺህ በላይ ቢሆንም የልብህን ከልብ የሚረዱት ጥቂቶች ናቸውና እድለኛም ደስተኛም ነኝ።....ሰአቱ ረፈድፈድ ብሏል ስለአለመለጠኝ የትላንትናው ፈተና ለማናገር የአስተማሪውን ቢሮ አንኳኳሁኝ መልሱ ግን ዝምታ ሆነብኝ። ደገምኩ ግን ምንም የለም አስተማሪው የለም ብዬ ልመለስ ስል ከውስጥ የቆለፉትን በር ሲከፈቱ ሰማው ቆምኩኝ "አንተ ነህ?" መምህሬ ነበር።"አዎ ቲቸር እኔ ነኝ" አልኩኝ እያየኋተቸው። "ና ግባ" ብለው በሩን ገርበብ አድርገው ገቡ እኔም ተከትያቸው ወደ ቢሮአቸው ዘለኩኝ እና በሩን ዘጋሁት። "ምን እንደሆንክ ሳስብ ሊገባኝ አልቻለም ከትምህርትህ እኩል የምታስኪደው ጉዳይ አልገጠመህም መሰለኝ" አሉ ፊታቸው የተዘበራረቀውን ወረቀት እያስተካከሉ። "ጓደኛዬ ታማ ነው አቋርጬ የሄድኩት" አንገቴን አቀርቅሬ መለስኩኝ። "እኔ የምኮራብህ ተማሪዬ ነህ ነገ የኔን ቦታ መውረስ እና ማስተማር አለብህ" ለምን እንደሚመክሩኝ ጭራሽ አልገባኝም። "እሺ ቲቸር አሁን እኔና ጓደኛዬን አትፈትነንም" ጥያቄዬን ወረወርኩባቸው። "ለእሷ የሚሆን እንኳን ጊዜ...." የለኝም ለማለት እንደሆነ ግልፅ ስለሆነልኝ "ከእኔ ጋር ትፈተን ቲቸር" ተማፀንኩት ከብዙ ልመና በኋላ አስተማሪው ለነገ ከሰአት ብሎኝ ሸሸኝ። እኔም ጓደኞቼን አግኝቼ ኤዲን ልንጠይቃት ወደ ቤቷ አቀናን። ስንደርስ ግን ኤዲ ከሆኑ ጎስቋላ አባት ጋር እየተመገበች ነበር። "ኤዲ" ናታን ጠራት። "እንዴ ናትዬ" ወደ እኛ በፈገግታ መጣች። "ኤዲ ግን አሞሻል እኮ እንዴት ይሄን ትበያለሽ" አልኳት ጣቷን ስትልስ ተፀይፌ። "አኝኬው ነው የምበላው" ፈገግታዋ በዝቶብኛል። ሰላም ብለናት ወደ ቤታቸው ገባን። እናቷ አልነበሩም እና እሳቸው እስኪመጡ ጨዋታ ጀመረን። ዘኪም "ኤዲና እየመሸ ነው ማዘርን ሰላም በያቸው እኛ እንሂድ" አለ የእጁን ሰአት እየተመለከተ። የሚገርመኝ ከእሷ ጋር ስውል በምን ቅፅበት ሰአቱ እንደሚነጉድ ነው። "እሺ በቃ ልሸኛችሁ" ብላ ይዛን ወጣች። እጄን ኪሴ ውስጥ ከትቼ እየሄድኩ ነበር እጇን በእጄ መሀል አጠላልፋ ያዘቸኝ። ፈገግ አልኩኝ። "ኧረ ግን ፎቶ ተነስተን አናውቅም" ናታን ነበር። አብረን ተነሳን እና ቀለበቱ ጋር አድርሳን ተመለሰች። እኔም ጓደኞቼን ተሰናብቼ በታክሲ ወደቤቴ ተመለስኩኝ። መቼም ሰለቸኸኝ የማትለኝ ሰፊዋ ክፍሌ ውስጥ ተኝቼ የተነሳነውን ፎቶ ማየት ጀመርኩ አንዴ ሳተልቅ አንዴም እያሳነስኩ ኤዲን እና ኤዲን ብቻ አየሁኝ። ፎቶ ላይ እንኳን ፈገግታዋ ያሸብራል። መሳቅ....መሳቅ....ደግሞ ማኩረፍ....ከዛ ...መርሳት.....ማልቀስ....ተመልሶ ....መሳቅ የኤዲ መገለጫዋ ነው። እማዬ በሩን ከፍታ ገባች ስልኬን ገልብጬ በድንጋጤ አስቀመጥኩት። "ምነው አስደነገጥኩህ?" አለችኝ መልሳ በሩን እየዘጋችው። "ኧረ አልደነገጥኩም" አልኳት ትንፋሼን ዋጥ አድርጌ። "ምን እያየህ ነበር" ስልኬን ልታነሳው ስትል ተቀበልኳት። "ምንድነው አቡሻ" አለችኝ። እኔም "የትምህርት ውጤቶቼ ናቸው አላሳይሽም ማም አታስጨንቂኝ" አልኳት ፎቶውን አይታ የምትጠይቀኝ ጥያቄ ውልብ ብሎብኝ። "የሴት ፎቶ ነው?" ደነገጥኩኝ። "ውይ ማም አይደለም" እናቴ ግን ልትተወኝ አልፈለገችም "አሳየኝ እስኪ" ብላ ሞገተችኝ እኔም " በቃ የሴት ፎቶ ነው ብዬ አሳየኋት አተኩራ ተመለከተቻት እና "ፈገግታዋ ሲያምር" አለችኝ። የሚያስደነግጠኝን ስሜቴን ተጋርታ።"ግን የሆነ ቦታ አውቃታለሁ ግን ጠፋኝ...."አለችኝ። "የት ኧረ አታውቂያትም " ብዬ ተከራከርኳት። "ፍቅረኛህ ናት?" አለችኝ ለማወቅ እየጓጓች እኔም በሃፍረት ጉሮሮዬን እየጠረኩ አቀረቀርኩ "አቡሻ መቼም እኔ ቅርብ አድርጌ ነው ያሳደኳቹ እና....." " አላውቅም ትውደደኝ አትውደደኝ አላውቅም እኔ ግን የሷ ነኝ " ተነስቼ ከክፍሌ ወጣሁኝ። ምክንያቱም ከዚህ በላይ ጥያቄ መመለስ አልችልምና እናቴም ስሜቴ ስለገባት ከክፍሌ ምንም ሳትል ወጣች። ምግብ በልቼ ክፍሌ ውስጥ ቁጭ ብዬ መፅሐፍ እያነበብኩ ነበር። የስልኬ ድምፅ ያቃጨለው ከቻርጀር ላይ ነቅዬ የይለፍ ቁጥሩን ሞላቼ ከፈትኩት ኤዲ ነበረች "ደህና ነህ" ብላ ነበር የላከችልኝ። "ደህና ነኝ ኤዲ አንቺስ ደግሞ ነገ ፈተና አለ እና ጠዋት እቤት እመጣለሁ" ብዬ መለስኩላት እና ማንበቤን ቀጠልኩኝ።
ሻወር ወስጄ ስወጣ እናቴ ተመልክታ "እሷ ጋር ነው" አለችኝ። እኔም "አይደለም ፈተና ነኝ" አልኳት ትኩስ ሻይ እየጠጣሁ። "ይሁን" ብላ ወደ ኪችን ቤት ተመለሰች እኔም በልቼ ስጨርስ አባዬ ፀሎት ጨርሶ መጣ "ጎረምሳው ደህና አደርክ" አለኝ ወንበሩን ስቦ እየተቀመጠ።"እኔም እግዚአብሔር ይመስገን ደህና አደርክ ዳዲ" አልኩኝ አፌን እየጠራረኩ " ዘንጠሀል" አለኝ።እኔም "ፈተና ነኝ ዳድ ግን ማታ ላወራህ የምፈልገው ጉዳይ አለ" አልኩት ። "እሺ ደውልልኝ ስትጨርስ እኔም የሆነ ቦታ እወስድሃለሁ " አለኝና ተሰናብቻቸው ወጣሁኝ። ሹፌራችን ያዕቆብ ዛሬ መኪናውን ይዞ ስለማይመጣ ማንም የማይጠቀምበት ጥቁሩን አውቶሞቢል ይዤ ወጣሁኝ። ሰአቱ ትንሽ ስለረፈደ መንገዱ ተዘጋግቶ ነበር እና በቆምኩኝ ቁጥር በስልኬ የኤዲን ፎቶ እያየሁ ፈገግ እላለሁ። ሳቋ ከተኛሁበት አለም አንቅቶታኛል። በእሷ ውስጥ ያየሁት ማንነቴ ለሰው እንደምጠቅም አስረድቶኝ ዛሬን አስወድዶኛል ግን እሷ በእሷ ምክንያት የተለወጠ ሰው ያለ አይመስላትም። እኔም አንደበት አጥሮኝ ለመናገር ቸግሮኛል። ለምን ከተባልኩም ማስረዳት በማይችለው አንደበቴ ብዘላብድ ፍቅሬን አሳንሶ እሷን የሚያሳጣኝ መስሎኛል በቃ ዝም ብዬ አፈቅራታለሁ እጠብቃታለሁ። የሰፈሯ ቀለበት መንገድ ስደርስ መኪናዬን ከአንድ ጥግ አቁሜ ደወልኩላት። የያዘችው የጎረቤት ስልክ ነውና ሌላ ሰው እንዳያነሳው በሰቀቀን ነበር የደወልኩት። አራት ጊዜ ከጠራ በኋላ ተነሳ "መስመር ላይ ኖት" ኤዲ ነበር ያነሳችው "ተኝተሽ ነው" አልኳት የድምጿ መለወጥ ገብቶኝ።"እና ልነሳ" አለችኝ።"ሰፈር ነኝ ቶሎ ነይ ጠዋት ክላስ አለን ከሰአት ፈተና" ስልኩ ጆሮዬ ላይ ተዘጋ ደነገጥኩኝ ካርድ ነው እንዳልል በካርድ አልጠቀምም እንደተዘጋም የገባኝ ስደውል አለመነሳቱ ነው። ምን አደረኳት ደግሞ አልኩኝ መቀያየር መቀያየር ከፋኝ በጠዋት አይኗን እንደ ደጀ ሰላም ለመሳለም ብጓጓም የተሳካልኝ አልመሰለኝም እንደዚህም እየሰበረችኝ እሷን መጥላት አለመቻሌ ለራሴ ይደንቀኛል። ጭራሽ ይብስብኛል ግን ማን ያምነኛል.......? ስልኬ ጠራ ኤዲ ናት "አንተ እግዚአብሔር ይስጥህ ውሃ እኮ መቅዳት ነበረበኝ እና ሳያጠፉት ቶሎ ቀዳሁ ከአስር ደቂቃ በኋላ መጣሁ" የኔን መልስ ሳትጠብቅ ዘጋችው። የእውነት ያማታል እኔ ብቻ የገባኝ የሆነ ህመም አለባት መኖር መሄዴንም ሳታውቅ መጣሁ ማለቷ እብደቷን ግልጽ አድርጎ አሳይቶኛል። እውነትም ብዙም ሳትቆይ ስትመጣ ከሩቅ አየኋት ጥቁር ሻርፗን ነፋስ እያንገላታው ነበር። የዛሬው ደግሞ ከረር ያለ ነው ያደረገችው ጥቁር ካልሲ ጥቁር ነጠላ ጫማ የያዘችው ጥቁር ፌስታል ያስጨንቃል። ቆማ በአይኗ እያማተረች ትፈልገኝ ጀመር ስለተናደድኩባት እኔም
መኪናው ውስጥ ቁጭ ብዬ አያት ጀመር። ግን ኤዲ ጤነኛ አይደለችም ያልኩት በምክንያት ነው ገና በጠዋቱ መንጋጋውን በጫት የወጠረ ወጣት። "የት ነሽ እሙዬ" አላት በማቅ የተደበቀው ውበቷ አማልሎት "ምድር ላይ" ተኮሳትራ መለሰችለት።"ኧረ ሙድ አለሽ" ደባሪው ወጣት መለሰላት ጥቁር ፌስታል ሰጠችውና "ለአንተ ነው አባዬ የላከኝ" አለችው ይበልጥ ለመስማት ጓጓሁ ወጣቱ ደንግጦ ፌስታሉን ከፍቶ አየው በምሳ ዕቃ ምግብ ነበረ ይዞት ተሰለበ ፈገግ አለች። ያ የሚያምር ፈገግታዋ ለእኔ ባይሆንም ለኔ እንዲሆን አየሁት።ደስ አለኝ። እግሯ እያጠፈች እየዘረጋች እኔን ትፈልገኝ ጀመር መኪናዬን ወደ እሷ አስጠግቼ ክላክስ አደረኩላት አጎንብሳ አየችኝና አኩርፋ ቆመች። ይበልጥ ደስ አለኝ። ፍቅር መንከባከብ ነው ከመኪናው ወርጄ "ይቅርታ" አልኳት ሁለት ጆሮዬን ይዤ። ሳቀች። ይሄ ፈገግታ ለኔ መሆኑ ደስ አለኝ በሩን ከፍቼ አስገባኋት እና መንገድ ጀመርን። "የሀብትህን ጥግ እያሳየኸኝ ነው" አለች ተደምማ እየተመለከተችኝ። "ኧረ ኤዲ የኔ እኮ አይደለም" አልኳት ሰርቅ አድርጌ እየተመለከትኳት።ዝም አለች እና ስልኬን አንስታ መበርበር ጀመረች። ግቢ ስንደርስ መኪናዬን አቁሜ አብረን ወረድን እና ወደ ጓደኞቻችን ጋር ሄድን ሰአት እስኪደርስ ቆመን እያወራን ነበር። "አቡሻ አንዴ ላውራህ" ሜላት ቀበጧ ነበረች። "እሺ አውሪኝ" አልኳት። "እንዴ ምን ሆንሽ እኔን አውሪኝ" ኤደን እየተርበተበተች መለሰች። ከእኔ የደበቀችውን ያልሰማሁ መስሏታል። "አይ እኔ እሱን ነው የፈለኩት" አለች ሜላት "እሺ መጣሁ" አልኳት ኤዲም "እኔ ይቺን ልጅ አልወዳትም" አለች ሜላት ስትርቅ። አተኩሬ ተመለከትኳት እና "ልቅር?" አልኳት መልሷን ማወቅ ፈልጌ "አይ ከፈለክ ሂድ ግን...""ምንም ግን የለውም ካልፈለግሽ ልቅር" አልኳት። "አልፈልግም" ተነፈሰችው። ናታን እና ዘኪ ፈገግ ብለው ነበር የሚያዩኝ እኔም ቀረሁ። የቀረሁት ግን ለእሷ የምሰጣትን ቦታ እንድታውቅልኝ ነበር ካልፈለገች ሁሉም ይቀራል እሷን ግን ማስቀረት አልችልም። ተያይዘን ወደ ክፍል ገባን እነ ኤዲ ክፍል አጠገቧ ተቀምጬ አስተማሪው ሲገባ ከክፍሉ ወጣሁኝ። እኔ ወደ መማሪያ ክፍሌ ገባሁ።የከሰአቱን ፈተና ለማስታወስ ያህል እያነበብኩ አስተማሪዬ ዝናሽ "ምንተስኖት ሂድና አምጣልኝ" አለችኝ እኔ ግን ምን እንደሆነ አልሰማሁም። "ምንድነው ቲቸር" አልኩኝ ተማሪው ሁሉ ሳቀ። "በግራ በኩል ያለው ሎከር ውስጥ ማርክ ሊስት አለ አምጣልኝ" ብላ ላከችኝ እኔም ወደ መምህራን ማረፊያው አቀናሁ። ደረጃው ላይ ኤዲ ተቀምጣ አየኋት "አጅሪት ፎርፈሽ ነው" አልኳት። "እእ አይ አይደለም...ትን ብሎኝ....ማለት አስሎኝ...." ተንተባተበች። በያዝኩት ማርክሊስት ጭንቅሏትን መትቼ "በይ ግቢ" አልኳት። ኤዲም "አቡሻ ሜላትን ግን አውርተሀት ታውቃለህ ይሄን ሰሞን" ብላ የጠረጠርኩትን አረጋገጠችልኝ። "ኧረአላወራኋትም ወደ ፊትም ያለፍቃድሽ አላወራትም" ብያት ወደ ክፍሏ እንድትገባ አድርጌ ተመለስኩኝ። ከትምህርት ሰአት በኋላ እኔና ኤዲ ፈተናውን ልንፈተን መምህራችን ጋር ሄድን ሊወድቅ የደረሰውን መነፅሩን በጣቱ ወደ ኋላ እየመለሰ "አዳራሽ ግቡ" አለን እኔም "የሚሰጥሽን ወረቀት እንዳትሰጪ ከኋላዬ ተቀመጪ" ብያት ገባሁ። እሷ ግን የሆነ ሀሳብ የገባት ይመስላል። አዳራሽ ውስጥ የሌላ ዲፓርትመንት ተማሪዎች ነበሩ ከኋላ ሄደን ተቀመጥን። አስተማሪው ወረቀቱን ሰጠን። እኔ የወሰድኩት ሁለት ነበር። ሸውጄ! ፈተናው እጅግ ቀላል ነበር እና የኤድንም የኔንም ፈተና ሰርቼ ወጣን። አስተማሪው ትኩረቱን ሌሎች ተማሪዎች ላይ ስላደረገ በቀላሉ መሸወድ ችያለሁ። ስንወጣ "ሌባ ነህ" አለችኝ። "ክሰሺኝ ብያት" እጇን ይዤ እየሮጥን ወደ መኪናዬ ጋር ሄድን እነ ናታን እየጠበቁን ነበር። ኤዲን ዛሬ የሆነ ቦታ ልንወስዳት ነው እና አይኗን በጨረቅ አስረን አስገባናት እና መንገድ ጀመርን። ከልቧ እንደምትወደው አልጠራጠርም ምን አልባትም ከገባት እንዳፈቀርኳት ይገለጽላታል።.........ይቀጥላል

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ይቀጥላል፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
#ታሪኩ ቶሎ ቶሎ እንዲለቀቅ ድምፅ ይስጡ!
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
🔥 ••●◉Join us share 🔥
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
የግጥም መንደር
😍ክርስቶቤል💖
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺🌺»̶̥✽̶┉┉┄
ለአስተያየት ለሐሳብ መስጫ @yebezawit2 ይጠቀሙ!
....መኖር.....መደሰት....ደግሞ ማመስገን....በተስፋ መታጀብ.....ለመውጣት መድከም....ላለመውረድ መታገል......ለማሸነፍ መልፋት......💟💟💟💟በስተመጨረሻም ባለ ድል መሆን የኔ ምኞት ነው....በዚህ አስከፊ ሰአትም ተሰፋ አደርጋለሁ እራሴን ለሀይማኖቴ ለቤተክርስቲያን ለቤተሰቤ ለሀገሬ ለህልሜ ስል ራሴን ከኮሮና ቫይረስ እጠብቃለሁ....🙏🙏🙏 እናንተስ?? መዘናጋት ዋጋ ያስከፍለናል....መጠንቀቅ ግን ያድነናል..💝💝💝💝💝

🇪🇹🇪🇹🇪🇹አቤቱ ሐገሬን ጠብቃት ታደጋት ከማትቸለው ጋር አታታግላት🇪🇹🇪🇹🇪🇹

#የግጥም_መንደር

🙏🙏🙏
. ❤️ ከፍቅር ❤️

ስጦታ ነው → ተቀበለው
ጣፋጭ ነው → ቅመሰው
ህይወት ነው → አጣጥመው
ተራራ ነው → ውጣው
ትዝታ ነው → አስታውሰው
መከራ ነው → ቻለው
መሰናክል ነው→ እለፈው
ህልም ነው → ፍታው
ቁልቁለት ነው→ ውረደው


#የግጥም_መንደር_
❥............🍃🌹🍃......... @yebezawit2
@yebezawit2 @yebezigetmoch
@yebezigetmoch
❥............🍃🌹🍃.............
🌹🌹 #LOVE🦋🦋
ተንኮል ሞት ነው

🙆ሰው በወገኑ ከጨከነ እና በክፋት እሾህ መንገዱን ካጠረ....ከአላማው ካሰናከለው...የወደቀው እራሱ ነው....በረግረግ ውስጥ ወዳጁን የከተተ...ህሊናውን ያቆሸሸው የራሱን ነው....💝ልብ በል.....ተንኮል መስራት ጀምረህ በተንኮል ከታሰርክ እምነኝ #ሞተሀል

መኖር ማለት ለሌላው ጧፍ መሆን እንደ አህያ ታዛዥ አገልጋይ መሆን እንደ አንበሳ ጠባቂ መሆን እንደ እርግብ የዋህ እና እንደ ጉንዳን ሰራተኛ ስትሆን ነው መኖር🤷‍♀🤷‍♀🤷‍♀ ሌላ አለም የለም🤷‍♀🤷‍♀🤷‍♀

በዚህ አለም ላይ ደግ ካልሆንክ የሚጠብቅህ የሰራኸው ተንኮል ነው

ጥሩ ሁን ፍቅርን ስጥ ለሰው መልካም አስብ 💟💟💟 ደግነት አይከፈልበትም💟💟💟 መስጠት መቀበል ነው!!!

ያለዚያ *ቅናት*ክፋት*ተንኮል*ምቀኝነት* ካለብህ እውነት #ሞተሀል!!! ትንሳኤህን በደግነት ፍጠር......

"ካጠፋሁ አፉ በሉኝ"
ቤዛዊት የሴትልጅ
@yebezawit2
@yebezawit2

@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
🙏🙏🙏🙏🙏
እንዴት እንደመጣሁ እንዳትጠይቂኝ
ለምን
ስለምትናፍንቂኝ፡፡
አውቀዋለሁኛ
አንድ የበደለሽ ሰው ናፍቀሺኛል ቢልሽ
ላንቺ
ፌዝ ነው የሚመስልሽ


ግን ናፍቀሽኛል፡፡

አዎ
በድያለሁ በግፍ
ደግሞም
ናፍቀሽኛል በእጥፍ፡፡
ማርያምን የምሬን በዝቷል መናፈቄ
የትም እገኛለሁ
የትም እስቀለሁ ግን ያለቅሳል ሳቄ፡፡
ብራመድ በሀገሩ
ብክንፍ እንኳ ብበር
ተከፍቶ አያለሁ ቆለፍኩት ያልኩት በር፡፡
ቀን የከረቸምኩት
ሌት በምን ከፈትኩት?
በለሊትሽ መጣሁ
አለሜን ስላጣሁ
ከትናንት የባሰ እንደማጣሽ ሳስብ
በደሌን አየሁት እጥፍ መውደድ ሲስብ
አንቺዬዋ ወዴ
የበደለ ሁሉ አይናፍቅም እንዴ...
ማቀፍ እንኳ ባልችል ምረት ባለምንም
አትሳቂብኝ እንጂ
ግጥሙን እያነበብኩ ናፍቀሽኝ አሁንም፡፡
ፀሀይዋን ከተትኳት
አይንሽን ለማየት ከቤቴ እየወጣሁ
የበደለ አይኔን እንዳታይኝ ብዬ
በጨለማ መጣሁ፡፡
ደረስኩኝ ከደጅሽ መፍራቴ በነነ
እሰይ አገኘሁሽ ናፍቆቴ ሰው ሆነ፡፡
እከንፋለሁ ይኸው ስደርስም አልሳምሺኝ
አጃኢብ ሰው መሆን
ሳጠፋ ጊዜ ነው ጭራሽ የናፈቅሽኝ፡፡
አጥፍቻለሁ አዎ መውደዴን ቀብሬ
አትሳቂብኝ እንጂ
ልክ ስበድልሽ ጨመረብኝ ፍቅሬ፡፡
:
:
:
እየመጣሁኝ ነው፡፡
----------//////--------------
ኤልያስ ሽታሁን

ምንጭ ፍቅር እና ግጥም
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
📜ጠቃሚ አባባሎች USEFUL QUOTes📜
ቤዛዊት የሴትልጅ

1📃አንድ ሰው ""99ኙ ገንዘብ ማግኛ መንገዶች"``የሚል መጽሐፍ ጽፎ ማሳተመመያ ገንዘብ አጣ አሉ፡፡የምታቀውን መተግበር ካልቻልክ ከማያውቀው እኩል ነህ📜


2📃ትዕግስት ይኑርህ ጥሩ ነገር ጊዜ ይፈልጋል📜

3📃አንብሳ ውሻ ሲጮህ አይዞርም📜

4📃 የራሰህን ውሀ መሽከም ስትጀምር የእያንዳንዱን ጠብታ ትርጉም ታውቃለህ📜

5📃የሚወዱህ ሰዎች መቼም ቢሆን አይለዪህም፡፡ አንተን ለመለየት መቶ ምክኒያት ቢኖር እንኳን አብረውህ ለመሆን አንድ ምክኒያት አያጡም📜

6📃ሰለ ነገ የምትጨነቅ ከሆነ በዛሬ መደስት አትችልም📜

7📃 ማንኛውንም ነገር ማድረግ ከፈለክ መንገድ አይጠፈም አለማድረግ ከፈለክ ደግሞ ምክኒያት አይጠፋም📜

8📃ትሁት የሚያደርግ ውድቀት ትዕቢተኛ ከሚያደርግ ስኬት የሻላል📜

9📃ችግርህን ለማንም አትንገር ምክኒያቱም ከነገርካቸው ውስጥ 20% ስላንተ አይጨንቃቸውም የተቀሩት 80% ደግሞ አንተ ችግር ውስጥ መሆንህ ያስደስታቸዋል📜

10📃ስዎች ሁልጊዜ እንዲያስታውስሱህ አትጣጣር
ዝም በልና የአንተ አለመኖር በህይወታቸው ውስጥ የሚያመጣውን ለውጥ እስኪያስተውሉ ጠብቃቸው📜

for any comment Inbox
💌 @yebezawit2 💌
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌺🌺🌺የግጥም መንደር🌺🌺🌺
💌💌 @yebezawit2 💌💌
╔══❖•ღڿڰۣ🇪🇹ڿڰۣღ •❖══╗​​​
💖 ክርስቶቤል ♥️
​​╚══❖•ღڿڰۣ💝ڿڰ ۣღ•❖══╝​​​​
.
••●🍃🌹🍃●•

፨፨፨፨፨፨፨፨ምዕራፍ ሁለት፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ክፍል ዘጠኝ ፱
😊ደራሲ ቤዛዊት የሴት ልጅ😊


"የት ነው የምትወስዱኝ ብቻ እያገታችሁኝ አይደለም አ?" አለችን። ናታንም "አንቺን አግተን ምድር ትቃጠል እንዴ" አላት ዘኪም" ኤዲና ታገሺ ደርሰናል" አላት ናታንን እየተቆጣ። "እሺ ብቻ ግን አስደንግጡኝ እና እሞትላችኋለሁ" ብላ አስደነገጠችኝ በቀልድ የተናገረችው ልቤን ግን አሳመመኝ። "ኧረ ነፍስ ትዘሪያለሽ" አልኳት መኪናውን ማቆሚያ ቦታ ጋር እያቆምኩ።ከመኪናው አወረድናት። የሚፈጠረውን ለማወቅ የኔም ልብ በጭንቀት በሀይል እየመታች ነው። በእግራችን ትንሽ መንገድ እንደተጓዝን አንዲት ትንሽዬ ቤት ገባን እና ጥጋችንን ይዘን "አይንሽን ግልጪ" አልናት ቀስ ብላ አይኗ ላይ የታሰረውን ጨረቅ አወረደች እና በብዥታ ተመለከተች ፈገግ አለች እና ደግማ ተኮሳተረች። "ዙቤይዳ" የምትወደው የአጎቷ ሚስት ናት። ይሄን ታሪክ የነገረችኝ ከትምህርት ቤት ወደ ቤት ስሸኛት ነበር.....የዛኔ እሷን ጎብኝተው ሲመለሱ ነበር አደጋው የተፈጠረው ከዛ በኋላ ኤዲ ፍትህን ፍለጋ ስትንከራተት ነበር እና በተወሰነ ነገር ትረዳት የነበረችው ዙቤይዳ ነበረች ፍትህን ያጓደሉባት እውነቷን የሰረቁት ሰዎች ዙቤይዳን እና ኤዲን ለያዩ ኤዲም ስታፈላልጋት ከድሬዳዋ ወጥታ ወደ አዲስአበባ መምጣቷን ሰማች ባህር የሆነችዋን አዲስአበባን አካላ እንደማታገኛት ስላወቀች ነበር ተስፋ ቆርጣ የተወችው። ስትገምት ግን አቧሬ አካበቢ እህት አለቻት ብላኝ ነበር። ፎቶዋንም አሳይታኝ በስልኬ አንስቼ ነበር የወሰድኩት። እድሜ ለናታን ዘመድ አቶ ደጉ ሰፈሩን በኮሚቴ አባልነት ስለሚያገለግሉ ሳሳያቸው ወዲያ ነበር ያወቋት። ቢያንስ እንኳን ኤዲ በገንዘብ እና ሰው በማጣት ምክንያት ያቆመችውን ፍትህ ልፈልግላት የተመረጥኩ ያህል ተሰምቶኛል።በቅርቡም ለአባቴ ነግሬው እውነትን እንድታገኝ ልረዳት አስቢያለሁ። "በህይወት አለሽ" ኤዲ ዙቤይዳ ላይ በደስታ እንባ ፊቷን እያራሰች ተጠመጠመችባት። ዙቤይዳ አሁን ላይ መንቀሳቀስ አትችልም እና ኤዲ በሀዘን ልቧ ተሰበረ። "አቡሻ ግን ምን አይነት ሰው ነህ" አቅፋ ሳመችኝ። ይሄን ደስታዋን ሳይ ውስጤ ሰላም አገኘ።ኤዲ ከ ዙቤይዳ ጋር እያወራች ስለ ትላንት እያወጉ በእንባ ተጫወቱ እኛም አብረን ሀዘናቸውን ተጋራን። "ግን ምን ሆነሽ ነው በዊልቸር ላይ የዋልሽው" አለቻት ፀጉሯን እየዳበሰች። ዙቤይዳም "አንቺን ስለረዳሁ ከስራ ያለምክንያት አስባረሩኝ የማበላቸውን ለልጆቼ አጣሁኝ ኤዲ ምን ልስጣቸው የሰው ግንባር እንዳይገርፋቸው ሁሌም የሰው እጅ ላለመጠበቅ ቀን ስራ ጀመርኩኝ። ብዙ ጊዜ የማስፈራሪያ ዛቻ ይደርሰኝ ነበር እናም የቀን ጠማማ አጎደለኝ። ስውሮቹ ሰዎች በገዟት ሴት ከሚገነባው ፎቅ ላይ ገፍትራ ጥላኝ መንቀሳቀስ መናገር አቃተኝ። እህቴ ስትሰማ መጥታ ወሰደችኝ። እናም ከብዙ መከራ ስቃይ በኋላ መናገር ጀመርኩ ከዚህ በኋላ ግን መንቀሳቀስ አልችልም አጎደሉኝ አነስኩ ሮጬ ሳልጨርስ ለልጆቼ ወገቤን ታጥቄ በለፋሁ መከራ ላስኩኝ። እኔ እንዲ ስሆን ለአንቺ እና ለእታባ አሰብኩኝ። ግን እታባ እንዴት ናት?" አለቻት። እታባ ማለት የኤዲ እናት ናት። "ደህና ናት ስናጣሽ ጊዜ የህይወታችን ትንሿ ጭላንጭል መብራት ጠፋች።በቃ ደከመኝ ለፋሁ ለፋሁ ዜድዬ ግን አቃተኝ ብርታቴ አንቺ ነበርሽ አንቺንም ሳጣሽ ተውኩት በቁሜ ሞቼ ቀረሁ" አለቻት። "ማቅሽ እስከአሁን መቆየቱ ምንድነው?" አለቻት እየተመለከተቻት። "እኔም እኮ መግነዜ ያልተፈታ ያልተቀበርኩም ሟች ነኝ" አለቻት ሀዘኗን እያስታወሰች። ከእሷ ጋር ሲያወጉ ቆይተን አመሻሽ ላይ የኤዲን እናት እሁድ ይወን እንደምንመጣ ነግረናት ከቤቷ ወጣን። ሰፈሩ ለጓደኞቼ ስለሚቀርባቸው በዛው አቀኑ እኔ እና ኤዲ ደግሞ በመኪና ወደ ሰፈሯ መሄድ ጀመርን። "እንደዛሬ ነፍስ ዘርቼ ተደስቼ አላውቅም አመሰግናለሁ" አለችኝ። ውብ እያኗን እያንከባለለች። "አታመስግኚኝ ለአንቺ አለምን ብሰጥሽ እንደሚያንስሽ ነው የማውቀው ደስታሽን ነው የምፈልገው ደስታሽን ስለሰጠሽኝ አመሰግናለሁ" አልኳት። እጇን ሰነዘረችልኝ እኔም ያዝኳት በእሷ ፍቅር ስሞት ታወቀኝ "ለኔ ስጦታዬ ነህ ያውም የታሸገ በየቀኑ አዲስ ገፅታ ያለህ ብገልጥህ ብገልጥህ የማልደርስበት" አለችኝና ይባስ አሰከረችኝ። "ለእኔ እኮ ትበዢብኛለሽ" አልኳት። እጄን ለቃ በመስኮቱ አንገቷን አውጥታ "አቡሻ የኔ ወንድም የኔ ብቻ ነው" ብላ ጮኸች። ወንድሟ ብሆንም እውነት ነው የእሷ ብቻ ነኝ እያፈቀርኳት የምኖረው እሷን ነው በማግኘትም በማጣትም የማስባት የማልማት እሷን ነው። "ታውቃለህ የእማዬ ፈገግታ ገና ከአሁኑ ይታየኛል አንተ ግን ማነህ ማን ላከህ" አለችኝ። እኔም ፈገግ አልኩኝ በደስታ ስትፍነከነክ እብደቷ እና ውበቷ ይጎላል "እኔጃ ማን ይሆን የላከኝ" አልኳት ወደ ሰፈሯ ቅያስ እየገባን። መኪናውን አቁሜ "ለማዘር አትንገሪያቸው እስከ እሁድ እሺ" አልኮት ኤዲም "እሺ ግን ነገ ለአባቴ ሄጄ እነግረዋለሁ ከፈለክ አብረን እንሄዳለን" አለችኝ። ከፈለክ ማለቷ አናደደኝ ሙሉነት የሚሰማኝ በኤዲ ነው ጉድለቴን የሸፈነችው እሷ ናት ማንም ያላየውን አይቶ ያልተረዳውን ቁስለቴን የሻረች ድክመቴን ያጠነከረች የኔ ሴት ናት "ሁሌም ከጎንሽ ነኝ በቃ አሁን ግቢ" አልኳት "እሺ ነገ ክላስ ስለሌለ ከሰአት ሰፈር ስትደርስ በትርንጎ ስልክ ደውልልኝ።" አለችኝ እኔም "እሺ ማዘርን ሰላም በይልኝ እናም ጉልበት ሳሚልኝ" አልኳት። ኤዲም "እሺ ወንድምየው ስትገባ አሳውቀኝ" ብላ አቅፋ ተሰናብታኝ ከመኪናው ወረደች።......እኔም መኪናዬን አዙሬ ወደ ቤት ተመለስኩ። ቤት ስደርስ ፊልም እያዩ ነበር ቤተሰቦቼ ትንሽ ሰአት አውርቻቸው ወደ ክፍሌ ገባሁኝ። የመፅሄት ዝግጅት እየቀረበ ነው የኤዲ ልብስ እያሳሰበኝ ነው ከዛ በፊት ነገሮችን በትንሹ አስተካክዬ ማቋን ማስወጣት እና አዲስ ሰው እንድትሆን እፈልጋለሁ....ክፍሌ ገብቼ ተንጋልዬ ተኛሁና ለኤዲ መልዕክት ላኩላት ወዲያው ተመለሰልኝ "ደህና እደርልኝ ነገ እንዳትቀር......በፊቴ ዝም ብሎ ያለጥቅም ሲሮጥ የነበረውን ጊዜዬን አስቁመህ የደስታን ሽቶ ቀብተህ ስለሰጠኸኝ አመሰግናለሁ" ብላ መለሰችልኝ። ደስተኛ ነኝ ከልቧ ስትፈነድቅ ስታብድ ስትደሰት አየኋት...ተመስገን...ለሊቱ በሰላም ተገባዶ ፀሀይ ፈንጥቃለች እኔ ግን ከአልጋዬ አልወረድኩም በቃ አይኔን ከድኜ ለዘመናት ኤዲን ማሰብ እፈልጋለሁ የኔ ስትሆን እያሰብኪ መበርታት የመወደድ ፀጋዋን ማድነቅ። "አቡሻ ቁርስ አትቀርብም" እማዬ ነበረች በክፍሌ ስታልፍ የጠራችኝ እንደምንም ከራሴ ጋር ተሟግቼ ተነሳሁኝ።"ዛሬ አብረን ወደ ቢሮ እንሄዳለን" አለች እማዬ ሻዩን እየቀዳችልኝ። "ምን አለ" አልኳት "አዳዲስ ዕቃዎች መጥተዋል እና ስለ ጨረታው መወያየት አለብን አንተም ስራውን ትለምደዋለህ" አለችኝ። ከሰአት ስለሆነ የኤዲ ቀጠሮ በእናቴ ሀሳብ ተስማማሁ።

".....ስለዚህ በጨረታው ላይ እንሳተፋለን" ብለው የተሰበሰቡት ሰዎች በጭብጨባ ክፍሉን አሸበሩት እና ስብሰባው ተበተነ ሰአቴን ስመለከት ወደ ስድስት እየተቃረበ ነው። "ለስንተኛ ጊዜ ሰአትህን እንዳየህ ታውቃለህ?" አለችኝ እናቴ ታዝባኝ። "ቀጠሮ ስላለብኝ ነው" አልኳት። "ታዲያ እዚህ ጠርተህ ማግኘት ትችላለህ" አለችኝ። እኔም "እኔጃ ማም ደስ ባይላትስ"
አልኳት። "ደውልላት እና ለኔ ስጠኝ ለዛች ልጅ ነዋ" አለች "አዎ" ብያት ኤዲ ጋር ደወልኩላት ከረጅም ጥሪ በኋላ ስልኩ ተነሳ "ወዬ አቡሻ" ኤዲ ነች። "የኔ እብድ የት ነሽ" አልኳት እየጨነቀኝ "እቤት ነኝ ምነው" አለችኝ። "ወደ መገናኛ መምጣት ትችያለሽ" አልኳት። ኤዲም "እእ እሺ እችላለሁ በሰላም ነው" "አዎ በሰላም ነው ስትደርሺ ደወይልኝ" አልኳት እና ስልኩን ዘጋሁት። እናቴም "እንዳላወራት ነው" አለችኝ ተሽከርካሪ ወንበሩ ላይ ተለጥጣ እየተቀመጠች። "ውይ ማም አይደለም ከማስደነግጣት ብዬ ነው ከፈለክሽ ላስተዋውቅሽ" አልኳት። "ታፈቅራታለህ?" ደነገጥኩ አይኔን አፍጥጬ ተመለከትኳት "ምነው አቡሻ ልክ አይደለሁም" ዝም ብዬ እናቴን ተመለከትኳት ዝም.....ቃል የለኝም.....ማፍቀር ትንሽ ነው......ሙሉ እኔነቴን ተቆጣጥራኛለች......"መዓዚ ይሄን ብትሰማ በደስታ....." "ማም!" ተቆጣሁ። "ይቅርታ አቡሻዬ ልረብሽህ አይደለም" አለችኝ። እኔም ተነስቼ በመስኮቱ የሚተራመሰውን የመገናኛ ጎብኚን ማየት ጀመርኩ። "ነግረሀታል" እናቴ ሁሉም ነገር ግልፅ ሆኖላታል። "ድፍረት አጣሁ እሷን ማፍቀር ቀሎኝ መንገር እና ማስረዳት ሸክም ሆነብኝ ቋንቋ የለኝም ቃላትም አላውቅም"አልኳት። እጄን በደረቴ ላይ አጣምሬ።.....በሩ ተንኳኳ የማም ፀሀፊ ነበረች "ስብሰባ መግባት አለብሽ" ብላ ወረቀት ሰጠቻት። እናቴም "ሶሪ አቡሻ" አለችኝና ብር አስቀምጣልኝ ወጣች። ኤዲን እየጠበኩ የሀሳቤን ዳገት እየወጣሁ የፍቅሬን ቁልቁለት እየወረድኩ ከእናቴ ቢሮ ወጣሁኝ እና እዛው መገናኛ ካለ ሬስቶራንት ተቀምጬ መጠበቅ ጀመርኩ። አይኔን ሳማትር ውብ የሆኑ ጥንዶችን ተመለከትኩ። ጆፌዬን ጣልኩባቸው.....ስልኬ ጠራ "ወዬ እናት ደረሽ" አልኳት ኤዲን። "አዎ ደረስኩኝ የት አባህ ነህ" ተበሳጭታለች። "መጣሁ" ብያት የጠጣሁትን ውሃው ሂሳብ ከፍዬ ተጣድፌ ወጣሁ።
....."አንተ ግን ሴጣን ልጆቹን በሚደበድብበት ሰአት ምን ልትሆን ነው የጠራኸኝ" አለች። አቅፋ ሰላም እያለችኝ። "ከሰአት አልደርስ ሲለኝ ነዋ" ብያት እጇን ይዤ መራመድ ጀመርን። "ወይኔ ግን ለፍቅረኛህ አዘንኩላት በዚህን ሰአት ከቀጠርካት" ትራንስፖርት አጥታ ስለተቸገረች እየተነጫነጨች መሆኑ ገብቶኛል። "ደግሞ ዘንጠሀል" አለችኝ የሰጠችኝን ሀብል እያየች። "ጨረሽ ተናደሽ" አልኳት። "አልጨረስኩም" ቀጠለች "ስትጠራኝ ልብስ እያጠብኩ ነበር.....ጨርሼ እማዬን ምሳ አብልቼ እኮ ነው የወጣሁት መሀል አናቴን ነው የከፈለችው ፀሀይ አንተ ግን ቁጭ ብለህ ማኪያቶህን ስትጠጣ ነበር" "ውሃ ነው የጠጣሁት" ብዬ አረምኳት። "ያው ነው ግን ለምን ፈለከኝ?" የማልወደው ጥያቄዋ። "ይባላል" አልኳት ወደ ሆቴሉ እየገባን። "አዎ ሰው ለምን እንደተፈለገ ማወቅ አለበት" አለችኝ "በቃ ተይው" አልኳት ንዴቴ ከመጨመሩ በፊት። ጥግ ካለው ጠረጴዛ ለመመገብ ተሰየምን። "ምን ልታዘዝ" አለችን አንዲት እንስት። ኤዲም "ለኔ ቀዝቃዛ ውሃ" አለቻት እያርገበገበች። "ምግብስ ኤዲ" አልኳት። ኤዲም "ጨው እና በርበሬ የበዛበት ፍርፍር" መልሷ አስደነገጠኝ "እንዴ ኤዲ " አልኳት ።ፈገግ አለችና "እ እሺ ፖስታ ይሁንልኝ" አለችኝ። እኔም "እሺ ለሷ ፖስታ በአትክልት ለኔ ደግሞ ሳላድ አምጪልን" አልኳት። ኤዲም ፊቷ የተቀመጠውን ቢላዋ አንስታ በሀዘን ተመለከተችው "አባቴ አልፎአልፎ ሆቴል ቤት እየወሰደን ሜኑ ላይ ያሉ ምግቦችን ያሸመድደናል በዛ ላይ አበላልም ያስተምረን ነበር" ብላ እንባዋን መሬት ላይ ፈጠፈጠችው። "ኧረ ኤዲ ዛሬ ማልቀስ ብሎ ነገር የለም" አልኳት። እሷም አንባዋን አብሳ "እሺ" አለች። የቀረበልን ምግብ እየተመለከተች "ለየብቻ ነው የምንበላው?" አለችኝ። እኔም "አዎ ማለት...." "አልበላም" ሳህኑን ገፋችው። "እሺ አብረን እንበላለን"ብያት ወንበሬን ወደ እሷ አስጠጋሁት እና መብላት ጀመርን ዝምታ መሀላችን ሰፈነ እሷ ስትበላ እኔ አያታለሁ ድንገት ከተመለከተችኝ የማልወደውን ፖስታ እጎርሳለሁ። በብርጭቆ ያለውን ውሃ እየተጎነጨች "ጥግብ አልኩኝ በስመአብ" አለችኝ ወንበሩን ተደግፋ እየተቀመጠች። እኔም "በቃ ይቺናት ረሀብሽ" አልኳት ኤዲም "ባይሆን አንተ ብላ እና ከዚህ እንውጣ" አለችኝ እኔም ከእሷ ጋር የማሳልፈው ጊዜ በልጦብኝ ምሳዬን ሳልበላ ከሆቴሉ ሂሳብ ከፍዬ ወጣን። በእግራችን አቀበቱን እየወጣን የሚያምር የቬሎ መሸጫ መደብር ጋር ደረስን "ወይኔ ሲያምር" ብላ ቆማ መመልከት ጀመረች። "መለካት ትፈልጊያለሽ" አልኳት ኤዲም "ከዛስ" አለች። "ከዛ ደስ ይልሻል" አልኳት በሀሳቤ መስማማቷን ሳልጠይቅ ይዣት ገባሁ። አጋጣሚ ሆኖ የምትሸጠው ሴት ከእናቴ ጋር ወዳጅ ናት ብዙ ጨረታ ላይ አብረው ተሳትፈዋል። ሶፋው ላይ ቁጭ ብዬ ኤዲ እንድትመርጥ ዕድል ሰጠኋት። እያዟዟረች ሁሉንም መመልከት ጀመረች ሁሉም ግን የአይን አዋጅ ሆኖባታል። በዚህ አጋጣሚ ማቅ ልብሷን ስታወልቅ ማየት ወደድኩኝ። አንዱን ረጅም ቬሎ መረጠች እና መልበሻ ክፍል ውስጥ ገባች። ፊቴ ያለውን መፅሄት እያገላበጥኩ ማየት ጀመርኩ። ኤዲ የኔ ሆና ሰርጋችን ተሰርጎ......ድግስ ተዘጋጅቶ.....ወዳጅ ዘመድ ሲሰባሰብ.....ድምቀቱ ፊቴ ውልብ አለብኝ እና ከልቤ ፈገግ አልኩኝ። ትንሽ ቆይታ ኤዲ ፊቴ መጥታ ቆመች ቀና ብዬ ተመለከትኳት...........ደነገጥኩኝ። አይኖቿ እንባን እያረገፉ ከአፍንጫዋ ደም ይፈሳል ልብሷንም ቢሆን አልቀየረችም "ኤዲ ምንሆንሽ" አልኳት በድንጋጤ "እ....." ተዘርራ ወደቀች ፈጣሪ ሆይ እባክህ አልኩኝ መከራው በኔ ላይ ፀንቷል ደስታዋን አጣጥሜ ሳልጨርስ ሌላ ሰው ትሆንብኝ እና እደነግጣለሁ አሁን ይባስ እንዲህ መሆኗ አስጨነቀኝ። ከወለሉ ላይ አቅፌ አንስቻት እየሮጥኩ ወጣሁኝ እና ህንፃ ላይ ወዳለው ከፍተኛ ክሊኒክ ወስድኳት "እባካችሁ እርዱኝ" አልኳቸው ነርሶቹ በእስትሬቸር ወሰዷት እኔም ልብሴን ያራሰውን ደሟን በስፍት እየጠረኩ ዜናውን ቆሜ መጠበቅ ጀመርኩ። አንዴ ወደላይ........ከዛም ወደታች.........ተመልሼ እቀመጣለሁ........አላስችል ሲለኝ እነሳለሁ..........እጄን በአፌ ጭኜ አስባለሁ........ወለሉ ላይ እቀመጣለሁ...ይባስ ጭንቄ የበዛው ሲቆዩብኝ እና መልስ የሚሰጠኝ ሳጣ ነበር። ለእናቷ ምን እላለሁ አልኩኝ አንድ ነገር ብትሆን ሀሳቤን ሀሳቤ እንዲያሸንፈው ደግሜ ጠንካራ ናት እላለሁ "አንተ ነህ ያመጣሀት" ዶክተሩ ነበር እጁን አልኮል እየተቀባ። "አዎ እኔ ነኝ ያመጣኋት ደህና ናት?" አልኩት እየተርበተበትኩ። ዶክተሩም "አሁን ነቅታለች....ውስጥ ሆነን እናውራ ተከተለኝ" ብሎ ክፍሉ አስገባኝ። "አንተ ወንድሟ ነህ" አለኝ ዶክተሩ። "አዎ" መለስኩለት። "አሁን ላይ የሚያስጨንቃት ነገር እንዳለ ግልፅ ነው በተደጋጋሚ እንደዚህ ትሆናለች" አለኝ እኔም መለስኩኝ። "ጥሩ ትንሽ ቆይታ መውጣት ትችላለች ግን ለወደፊት በስነልቦና ሀኪም ብትታይ መልካምነው" አለኝ ወረቀቱ ላይ ዚግዛግ እየፃፈ። እኔም አመስግኜ ወጣሁኝ። ኤዲ አይኗን ገልጣ ጣርያው ላይ ተክላለች"ደህና ነሽ" አልኳት ከአጠገቧ እየተቀመጥኩ። "አስደነገጥኩህ?" ተሳቃ ነበር የጠየቀችኝ" ኧረ አልተሳቀኩም ኤዲዬ" አልኳት። "ይቅርታ" አለች እንባዋን ላለማፍሰስ እየታገለች። "ኤዲ አትበይኝ እኔን ትጎጂኛለሽ ደግሞ አንቺን መጠበቅ ግዴታዬ ነው" አልኳት እጆቿን ይዤ። "አመሰግናለሁ" አይኗን ሰበረችው። "ሜላት ቀበጧም....." ሳታስጨርሰኝ " አገኘሀት...ምን አለችህ...ነገረችህ....አመንካት...."ጥያቄዋን አከታተለችብኝ እኔም "አይ አላ
"ሜላት ቀበጧም....." ሳታስጨርሰኝ " አገኘሀት...ምን አለችህ...ነገረችህ....አመንካት...."ጥያቄዋን አከታተለችብኝ እኔም "አይ አላገኘኋትም እሷም እንደዚህ ያማት እንደነበር ልነግርሽ እኮ ነው" አልኳት ተሸማቀቀች። "የደበቅሽኝ ነገር አለ" አልኳት። ኤዲም "ጠረጠርከኝ" መለሰች። "አይ ግን ትመስያለሽ" አልኳት። ኤዲም ቀና ብላ እየተቀመጠች "እንኳን ይልቅ አስወጣኝ ቶሎ" አለችኝ። እኔም "እሺ ግን ሰምተሻል አይደል ዶክተሩ እንዳትጨነቅ ብሏል" አልኳት። ኤዲም "ላለመጨነቅ ስጨነቅ ነው ያመመኝ" ብላ ከአልጋው ወረደች። ክፍያ ጨረስን እና ስንወጣ በር ላይ ከዶክተር ዳዊት ጋር ቸገጣጠምን ኤዲ እጆቼን አጥብቃ ያዘችኝ ዶክተሩም ምንም ሳይናገር ገባ። እኔም ኤዲን ይዤ መንገዴን ቀጠልኩኝ። "ደከመኝ እንቀመጥ" አለችኝ እኔም እሺ ብያት ጥላ ስር ተቀመጥን "መኪና እንዲያመጡልኝ ልንገራቸው" አልኳት። ኤዲም"አይ ደህና ነኝ" ብላ አቀረቀረች። ስልኬን አውጥቼ የእናቴ ሰራተኛ ጋር ደውዬለት መኪና እንዲያመጣልኝ ነገርኩት። ተቀምጠን እየጠበቅን "አቡሻ ሜላትን አታግኛት" አለችኝ። እኔም "አንቺ ያልወደድሽውን መቼም አላደርገውም"አልኳት። "አመሰግናለሁ" አለችኝ "ኤዲ ግን ለኔም ተቸገሪልኝ" አልኳት። "ምን ላንተ ምንም እሆናለሁ" ትንፋሼን ሰበስብኩ እና ቃላትን አማጥኩኝ "ሙሉ ሀዘንሽን ለእኔ ስጭኝ በቃ እኔ ህመምሽን ልታመም አንቺ ስትስቂ ብቻ ልመልከትሽ ሁሌም ደህና ሆነሽልኝ" አልኳት አቀፈችኝ......"የኔ ህመም መድሀኒት የለውም እኔን እንደጎዳኝ እኔን ይጨርሰኝ እባክህ ወንድሜ ከዚህ በላይ አትሰቃይ" በእቅፏ ውስጥ ነፍሴ ሀሴትን አደረገች....

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ይቀጥላል፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ቀጣይ ክፍል #ሶስት ሰአት በልዮ ሁኔታ!!!
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
#ታሪኩ ቶሎ ቶሎ እንዲለቀቅ ድምፅ ይስጡ!
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
🔥 ••●◉Join us share 🔥
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
የግጥም መንደር
😍ክርስቶቤል💖
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺🌺»̶̥✽̶┉┉┄
ለአስተያየት ለሐሳብ መስጫ @yebezawit2 ይጠቀሙ!

#ድምፅ መስጠት አትርሱ
╔══❖•ღڿڰۣ🇪🇹ڿڰۣღ •❖══╗​​​
💖 ክርስቶቤል ♥️
​​╚══❖•ღڿڰۣ💝ڿڰ ۣღ•❖══╝​​​​
.
••●🍃🌹🍃●•

፨፨፨፨፨፨፨፨ምዕራፍ ሁለት፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ክፍል አስር ፲
😊ደራሲ ቤዛዊት የሴት ልጅ😊



"ምንም ቢፈጠር ጥለኸኝ አትሂድ እባክህ" ቀስ ብዬ ከእቅፏ ወጥቼ አይኖቿን አተኩሬ እያየሁ "አልችልም....አዎ ልርቅሽ አልችልም...በየደቂቃው በየሰአቱ ሁሌም አጠገብሽ ነኝ መለየት አልችልም" አንገቴ ስር ገብታ ተንሰቀሰቀች። የእናቴ ሰራተኛ መኪናውን ሰጥቶኝ ተመለሰ። ትንሽ ከተማውን ተዘዋውረን እየተመለስን እያለ "አቁመው አቡሻ" አለችኝ ከፊት ለፊት የሚመጡትን የሚካኤልን ፅዋ የያዙ እናቶች ተመልክታ። "ብር ስጠኝ" እጇን ዘረጋች። ከኪሴ ቀድሞ የወጣውን ሀምሳ ብር ሰጠኋት ከመኪናው ወርዳ አስቆመቻቸው እና ብሩን ሰጥታ ዝቅ ብላ ተሳለመች። ኤዲን በየቀኑ እንድወዳት የሚያደርገኝ አዲስ ነገር አላጣም። በዚህም ይበልጥ እወደዋለው በወረት ወይም ለአንድ ሰሞን ያልሆነ መልካሙን ፍቅሯን በልቤ እርሻ ላይ ዘርታለች በየቀኑ የሚያፈራ የሚያድግ የማይደርቅ ንፁህ ዘር......"ቅዱስ ሚካኤልን አባቴ ይዘክር ነበር ምን ዋጋ አለው ነጠቁኝ ሳልጠግበው" ብላ የህመም ፈገግታ ፈገግ አለች። "ከዚህ በኋላ ግን በቃ ደስተኛ ነኝ አንተ እናቴ መድሃኒቴ ናቹ ከሰማይ የወረዳችሁልኝ መና....ታውቃለህ በፊት የተላክ መስሎኝ እሰጋ ነበር ግን ተሳስቻለሁ።" አለችኝ ኤዲ ፀጉሯን በመስታወቱ እያየች። "ሁሌም እመኚኝ መቼም አልጎዳሽም" አልኳት። "ወንድሜ ለኔ ጠበቃዬ ነው" አለችኝ። ወንድምነት ለኔ ፀጋ ሆኗል የማልገፋው ከገፋውት የምጎዳው እኔ ነኝ እና ምርጫ የለኝም ይልቅ መለማመድ ነው ለዚህ ነው ልቤ የማይሰበረው።

ከቤት አድርሻት ተመለስኩኝ።ግቢ ውስጥ መኪናውን አቁሜ ስወርድ አባዬ መናፈሻው ውስጥ ነበር። "ዳዲ ላናግርህ" አልኩት። አባቴም "እሺ ትችላለህ" አለኝ "እእ ዳድ ባለፈው ያገዝናት ጓደኛዬ ፍትህ ጎድሎባት እውነቷ ተሰርቆባት ከባድ ሀዘን ውስጥ ናት መራራ ህይወትን እየኖረች ነው" ስለ ኤዲ ነበር የማወራው። "አቡሻ ስለዚህ ጉዳይ ነገ እናውራ ጥሩ ስሜት ላይ አይደለሁም ትንሽ ነገር መስሎኝ ነው" አለኝ። እኔም እሺ ብዬ ወደ ቤት ገባሁ። አባቴ የፍትህ ጉዳይ በዕርጋታ እና በአርምሞ ነው ማዳመጥ የሚፈልገው ነፍሱን ላመነበት ከመስጠት ወደ ኋላ አይልም ለዚህም ነው በገዛ ፍቃዱ ስራ ሲለቅ ብዙ ልመና የቀረበለት አባቴ ዳኛ ብቻ አልነበረም መርማሪ ፖሊስም ነው እውነት አታመልጠውም እውነትም ለእሱ ብቻ የምታዳላ ነው የሚመስለኝ።......ክፍሌ ገብቼ መፅሐፌን ማንበብ ጀመርኩ።

ዛሬ እሁድ ነው ደስ የሚል ቀን ከቤት ስወጣ "አቡሻ ይሄን ይዘህ ሂድ" ማም የጋገረችውን ኬክ ጠረጴዛ ላይ አኖረችው። ደስ አለኝ ተሰናብቼ ወጣሁኝ። የአባዬን ሌላኛውን መኪና ይዤ ወደ ኤዲ ጋር ሄድኩኝ ኤዲም እናቷን አለባብሳቸው እጅግ ውብ ሆነዋል ደርባባዋ እናቷ ሲያዩኝ በእናት ፍቅር ተቀበሉኝ። ምን እንደተፈጠረ እየጓጉ ወደ መኪናው አስገባናቸው። ኤዲም ከጎኔ ተቀመጠች። በስሱ የተከፈተው የአስቴር ሙዚቃ ኤዲን ተመችቷት ታንጎራጉራለች። የኤደን እናት ደግሞ በጉጉት ያዩናል......ምን ትለኛለህ ምን ይሻለኛል የኔ ብትሆን ያስደስተኛል... መውደድን በመውደድ ፍቅርን በፍቅር መላሽ እንዳንተ የተመቸኝ ማንም የለም ጭራሽ" ኤዲ ስትዘፍን ለኔ በሆነ ብዬ ተመኘሁኝ። ግን አይደለም የፀና ግንብ መሀላችን ታጥሯል። እነ ዙቤይዳ ቤት ስንደርስ መኪናዬን አቁሜ እናቷን አወረድናቸው እና ኬኩንም ይዘን ገባን። የተከፈተው መዝሙር ከውጪ ይሰማል።"የማን ቤት" የኤዲ እናት ጠየቁን ለማወቅ የጓጓው ልባቸው አይናቸውን አንከራተተው በዊልቸሩ ሆና ዙቤይዳ ስትወጣ በጩኸት አቀለጡት። አለቀሱ.....ተንሰቀሰቁ....በጉልበታቸው ተንበርክከው ወደ ሰማይ አንጋጠጡ....ተነስተው ግን ማቀፍ አቅም አጡ...ደስታቸው ልክ አጣ ሀዘን ከስሜት ተደበላለቀባቸው.....ኤዲም እኔን ተሸሽጋ አለቀሰች። "ዙቤይዳ እህቴ የኔ አለም ልጄ የኔ ቅርስ ማስታወሻዬ ፍቅሬን ማያዬ" በሞት የተለያቸውን የኤዲን አባት አንስተው አምርረው አለቀሱ። ዙቤይዳም መራራ እውነትን እያስታወሰች በለቅሶ ደከመች የኤዲን እናት ደግፈን አስገባናቸው። አልቅሰው ሲረጋጉ ነበር ተነስተው ያቀፏት። እኔና ኤዲም ተቀምጠን አየናቸው። ለካ መኖር ይሄ ነው ደስታ ጥልቅ ስሜት የማይጠፋ ብርሃን ከኤዲ የህይወት መሶብ ላይ ቆርሼ በላሁ። እስሬ ተሸጉጣ "እማዬ ግን የምትሞት መስሎኝ ነበር" አለችኝ አፍ ለአፍ ገጥመው ሲያወሩ እያየች። "እኔም ፈርቼ ነበር ከጠበኩት በላይ ሆኑብኝ" አልኳት የቀረበልንን ፈንዲሻ እየዘገንኩ። በቤቱ ጥግ በኩል ካለው ስዕለ አድህኖ ስር አራት ሻማ በርቷል ቄጠማ ተጎዝጉዞ ፋስኪ መስሏል የዙቤይዳ ልጆችም በደስታ ሰክረው ይገባሉ ይወጣሉ። ኤዲም ከእጄ ፈንዲሻውን እየወሰደች ነበር የምትበላው "በራስሽ እጅ አትይዥም" አልኳት። "ሁሉንም ለኔ ስጭኝ ብለኸኝ የለ እጄ ከሚቆሽሽ ብዬ ነው" አለች እያስተዋለችኝ። "ጅል" አልኳት በቦርጫሙ ቲቪ የሚተላለፈውን ዝግጅት እያየሁ። "አንተ ደግሞ ሞኝ ነህ ያውም አስር ሞኝ" ሳቋን ለቀቀችው። ሁሉም ወደ እኛ ዞረ ደነገጥኩ "አንቺ ዲንብጥ ይሄ ሳቅሽ ዛሬም አለ" ዙቤይዳ አለች። "ኧረ ብሶባታል እንደ ፀበል ዕቃ ውጪ ነው የሚውለው ደና ጥርስ እንዳለው" አሉ የኤዲ እናት። "አያምርም እንዴ ጥርሴ" ብላ ወደኔ ዞራ ጥርሷን አሳየችኝ። ችም ችም ጥርሶቿ ሲገለጡ እንደ ዳንኩኝ እና ሲሸሸጉ እንደሞትኩ ልነግራት ብዬ ድፍረት ወኔ ከየት ይምጣ ወንድነት ፍቅር ላይ የለም ፍቅር ማሸነፍ ነው ያሉት ተሳስተዋል መሸነፍ ነው የዘለዓለም እስራት ነው የማይፈቱበት። "ትንሽ ትንሽ" አልኳት። ኤዲም "ያንተም አልተባለም" አለች።........ደስ የሚል ልዩ ቀን የሚጥም ህልም ሆኖ ባልነቃ ተመኘሁ።ኬኩ ተቆረሰ......."እናትህ ጎበዝ ናቸው አታስተዋውቀኝም" ከባድ ጥያቄ ኤዲ ወረወረች። "ፀባይ ካለሽ" አልኳት። ኬኩን ቁጭ አድርጋ እጇን አጣመረች። "ይኸው ጨዋ ነኝ"ሳቀች። ከመጠን ያለፈ ያልተገደበ የማይመረመር ደማቅ ደስታ ይታይባታል። እናቷም "የኔ ጌታ አንተ መላዕክ ነህ....ባይገርምህ እሙዬ ሳታውቅ ተደብቄ አለቅሳለሁ በዚህ እድሜዬ ብቸኛ መሆኔ ያሳስበኛል አንድ ቀን እንኳን ሳላያት ብሞት ብዬ አስብና ለራሴ አለቅሳለሁ ዘመዴን ሰጠኸኝ" አሉኝ እኔም "ደስ ስላሎት ደስ ብሎኛል" አልኳቸው። ዙቤይዳም "ይህቺ በረሮ ፀባይ ቢኖራት እሰጥህ ነበር ግን አትሆንም" ብላ መብረቅ ሆና አደረቀችኝ። ለኔ ከኤዲ በላይ የሚጠቅመኝ ቀርቶ እንደ ኤዲ የሚሆንልኝ የለም። ሺህ ጊዜ እያጠፋች እየበደለችኝ ከኔ ጋር መኖሯን ነው የምሻው.....ከፈለገችም ትግደለኝ ካሻትም ታድነኝ.....ደግሞም ታሰቃየኝ ላጣት እንጂ ልሞትላት ዝግጁ ነኝ። እስከ ምሽት አብራያቸው ውዬ እነ ኤዲን ሸኝቼ ወደ ቤት ለመመለስ መንገድ ጀመርኩ። በየቀኑ የምሰማው የታምራት ዘፈንን ከፍቼ እንባዬ ከአይኔ እየፈሰሰ ነበር የምነዳው....ማፍቀር ዝም ብሎ ማፍቀር በረመጥ መንደድ ነው...ለምን እንባዬ እንደሚወርድ አልገባኝም...

"ልሂድ ደግሞ አይኗንም ልየው የደንቡን ላድርስ
እፎይ ብዬ እንዳድር የልቤም ባይደርስ
.
.
.
.
.
.
.
.
.....💗💗💗......💗💗💗........💗💗💗💗
ሽንፈቴን እንዳልገፅላት
ከአንደበቴም ጠፉ ቃላት
አማራጩ ሆኖ ማየቱ
አልሰቸኝም ደርሶ መምጣቱ ሄዶ መምጣቱ

አንድ ቀን ለ'ኔ እስኪላት
እግሬ አይነቃም
አይታክት
አለ የምለው መድኔ
መመልከቱ ነው አይኗን በአይኔ......💝💝💝💝

ነገ ሌላ ቀን ነው ፀሀይ ገብታ ትወጣለች እኔም የኔን ፀሀይ አይቼ ሞቄ እመለሳለሁ በየቀኑም እመላለሳለሁ......"የኔ ወንድም አመሰግናለሁ" መልዕክት ላከችልኝ ኤዲ። "እንዴት ነበር ቀኑ" አለችኝ እናቴ። "እጅግ ውብ ደስ የሚል ቀን ነበር ማም" አልኳት ከአባቴ ጎን እየተቀመጥኩ። "የነገ ተረካቢዬ አንተ ደጉ ልጄ ነህ እንዲህ ሆነህ በማየቴ ተደስቻለሁ ልጅቷንም አንድ ቀን እተዋወቃታለሁ" አለኝ። እናቴም "የምን አንድ ቀን ነው የልደትህ ቀን የእኛም አንቨርሰሪ ነው ስለዚህ ታመጣታለህ ከሳምንት በኋላ ነው" አለችኝ። ጊዜው እንዴት ነጉዷል። ለካ ልደቴ ደርሷል። ከኤዲ ጋር ያሳለፍኳቸው ጊዜያት ቢያንሱም በዝምታ ግን ትልቅ ትዝታን አትርፊያለሁ። ደስ የሚል ሀሳብ መጣልኝ። የልደቴ ቀን ፍቅሬን ላበስራት "አፈቅርሻለሁ " የሚለውን ቃል የግድ ማውጣት አለብኝ በቃ ግድ ነው ግን ባጣትስ?? መልሼ በስስት ተሳቀኩኝ ግን እስከመቼ በመምጣት እና በመቅረት መስቀለኛ መንገድ የምቆመው። ፍቅር ያስገድደኛል የሌላ ብትሆን የምችልበት አቅም የለኝም የመኖር ጉጉቴን የህይወት መንገዴን ከእሷ ጋር ብቻ ነው ማሳለፍ የምሻው የደከመው ስውር እኔነቴ ጠንክሮ የተገለጠው በኤዲ ነው።
ሰኞ ጠዋት ክላስ ገብቼ ወጣሁኝ እነ ኤዲ ቀድመውኝ ነበር ኤዲ ዛሬም ስለትናንቱ የእናቷ ደስታ ዛሬ ላይ ሆና ስትፍነከነክ ሳያት ደስ አለኝ። ለእናቷ ያላት ፍቅር ይለያል ዝንብ እንኳን እንድታርፍባት አትፈልግም! ሁሌም በጨዋታም በቁመነገር መሀልም የእናቷን ነገር ሳታነሳ አታልፍም። "በነገራችን ላይ ሳምንት ልደቴ ነው የእነ ማም የጋብቻ በአል ነው ስለዚህ ተጠርታችኋል" አልኳቸው ኤዲን አቅፌ በጨዋታቸው መሀል ገብቼ "እንዴ አንተም ተወልደህ ነው እንዴ እንደ እኛ" አለች። "ምነው ልዩ ሆንኩብሽ" አልኳት። ኤዲም "ያው ከእኔ ባትበልጥም ትንሽ ልዩ ትመስላለህ" አለችኝ። እውነትም ልዩ ነሽ ብላት በታደልኩኝ። "አትቀሩም አይደል?" አልኳቸው። ዘኪም "ለእኛ እኮ አዲስ አይደለም ባይሆን ኤዲና ታሳስባለች" አለ ኤዲም" ሰው ና ብላ ተብሎ እንዴት ይቀራል እማዬም ትመጣልሀለች የጋብቻ በአል የአባቴን ፍቅር ስለምታስታውስበት ደስ ይላታል" አለችኝ ገረመኝ የገረመኝ ግን መልሷ አይደለም በፊት ስለአባቷ በሀዘን ነበር የምታወራው አሁን ግን ምንም ለውጥ አጣሁባት..."ኤዲ አንዴ ላናግርሽ" የተጣላኋት የዲፕሎማ ተማሪ ናት ደነገጥኩ። "የት ለምን እዚሁ አውሪኝ" አለቻት ኤዲ ስላላወቀቻት "ኑ እንሂድ ና ሻይ እንጠጣ" አልኩኝ "ለምን እንደምታፈቅራት እንዳልነግራት ነው" ልጅቷ አፈነዳችው። የልደት ቀኔ ህልም ተጨናገፈ ኤዲ ግንባሯ ተቋጥሮ የሳቋ ፀሀይ ጠለቀች......


💗አጓጊው ቀጣይ ክፍል እንዲቀርብ ድምፅ ይስጡ!😲😲

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ይቀጥላል፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ቀጣይ ክፍል በልዮ ሁኔታ!!!
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
#ታሪኩ ቶሎ ቶሎ እንዲለቀቅ ድምፅ ይስጡ!
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
🔥 ••●◉Join us share 🔥
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
የግጥም መንደር
😍ክርስቶቤል💖
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺🌺»̶̥✽̶┉┉┄

#ድምፅ መስጠት አትርሱ የመጨረሻው ክፍል ቀርቧል💝
Tamrat Desta 07 Aynuan Lyewu
zafany com
በጠየቃችሁኝ መሰረት ይኸው #ሙዚቃው
አይኗን ልየው💗💗💗 የግጥም መንደር
💋በእርግጥ አታምኚኝ አንቺን ማሰቤን❤️
ርቀሽ ስለሄድሽ ገፍተሽኝ እኔን🏃‍♀
አልጠላሽም ስላልወደድሽኝ🕺💑
ከሀሳብ እንድድን ብቻ ጠይቅኝ😊😊🚶

የግጥም መንደር በቤዛዊት የሴት ልጅ
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
:)
…ይቅርታ…

እሚገባሽን ሳይሆን እማይገባሽን እኔ ከፈልኩሽ…ከብዙ መጥፎነቴ ውስጥ ጥቂት ጥሩነቴን ፈልጊና ስለዛ በይና ይቅር በይኝ…

🕯 @yebezigetmoch 🕯
💌 @yebezawit2 🥀
🌸ፊሊሞን የማርያም ልጅ🙆🙆
የምፈልገው አንተን ነው....እብዱ አፍቃሪዬን💗💗💗....ዝና ገንዘብ ብርሃን ላይ የቆመ የፍቅር ጥላ ነው.... ያለማጋንን
💝💝እወድሃለሁ 💝💝

ቤዚ የራጉኤል ልጅ
@yebezigetmoch
💌💌 @yebezawit2 💌💌💌
2025/07/07 03:28:42
Back to Top
HTML Embed Code: