Telegram Web Link
ርዕስ የቲም አይደለንም

ግጠም ሲለኝ ደርሶ ሰአት አልጠብቅም
እናንተን ለመምታት እውቀት ባላረቅም
መረጃ የላችሁ የጃሂል ጥርቅም
ዝቅ ብለህ ቅራ ካላወክ አታቅም

እንደ ሱፍይ የለም ለሀቅ የሚታመን
ለድኑ የቆሙ ባለንበት ዘመን
ቅረብና እያቸው እንድንተማመን
              ጃል
ይመልሱላሀል ጠይቅ ተጠግተህ
ፊትና ማራገቡን ማጭበርበሩን ትተህ
ውሸት አታሰራጭ ፌስቡክ ላይ ተኝተህ
የጥመት ቀስት ነሁ የዘመኑ አንበሳ
ኢኽዋን ያቃዠዋል ስማቸው ሲነሳ
     ሸህ አቡበክር ሰለይማን   
መረጃ ቢነግሩት ላኪን አይረዳም
ንፁህ ከሀይቅ እንጂ ከኩሬ አይቀዳም
       ሙሸቢሁ ሁላ       
እረቢዕ ሲደርስ አትነጫነጩ
መረጃ አልባ ተረት ሁሌ አታሰራጩ
ኢብሊስ ጋር ሂዱና ፀጉር ተነ ጫጩ
              እና ለዚ
ስወዱም ስጠሉም ይኑራችሁ ሚዛን
የነብዩ መውሊድ ቢሸጥ እንገዛን
ቀነስነው ስትሉ የበለጠ በዛን
              ሀየ ሀየ
እርግጥ ከናንተ ጋር ይበዛል ውዳቂው
አጨብ ጫቢ ሁላ የገንዘብ ደማቂው
የሷለሆች መንገድ አሏህ ነው ጠባቂው
            ብትለፉም
ፊትና ለመቀስቀስ ምንም ብትለፉም
ውሸትን ቅጥፈትን ብታቀላጥፉም
ከሚዲያ ጩኸት ከፌስቡክ አታልፉም
             ሀሀሀሀሀሀ
ዊላዳው አብቧል ፈፅሞ አልተነካም
ተስፋ ቁረጡ እንጂ ፊትናው አልተሳካም
ሁሌ የሚውጥ ሰው የጥመትን ክኒን
በርዘንጅ ሲሰማ ይሆናል መጃኒን
           ሀበሻ
የሊቃውንት ሀገር የውቀት መናገሻ
ዳሩል ሒጅረተይኒ ነችና ሀበሻ
የነዚያ ሶሀቦች መጠጊያ መሸሻ
የተቀበለችው ሆና መዳረሻ

የእውቀት ጠበብቶች የአሊሞች ሀገር
የፅናት ተምሳሌት ግርግዳና ማገር
ብዙ ሊቆች አሉን ሁሉን ብንናገር
         እንግዳሳ
ሀቅን ያስተማሩ አረብ ከሀበሻ
አጧዕ ኢብኑ ረባህ የኢልሙ ወጌሻ
እወቀቱ ባህር ነው የለው መዳረሻ
የጥመትን ህንፃ ደማሚት ማፍረሻ
              ናቸው
መጠኑን በዝርዝር ጠንቅቄ ባላውቅም
ስንት አሊም አሉ አያጠያይቅም

እነማንስ ናቸው አይንህን ገልጠህ እይ
ኢትዮጲያዊ ናቸው ኢማሙ ዘይለዕይ
ሙፍቲ የነበረው ኢማሙ አጣኢይ
ኸረ ሌላም አሉ ኢማሙ አድ ረዕይ
         ውዶቼ
የሀበሻ አሪፍ ስማቸው ሲነሳ
እነ አህመዱ ዳንይ የቃጥበሬው ኢሳ
እነ ዓሊ ጎንደር አልጀበርቲ ሙሳ
የቲም አይደለንም ፈፅሞ እንዳትረሳ

   በሙሂቡ ቀለም
https://www.tg-me.com/byetiLhadorat
እደዚ ያሉ ምርጥ ምርጥ ግጥሞችን ለማገኘት
ይቀላቀሉን ሼር ማድረግም አይርሱ
ረቢዕ አንድ አለ

ለነብዩ መውሊድ ዛሬ እንተሳሰብ
በየ መሳጂዱ ሀያ እንሰባሰብ
አሽቀን ይመልከት ይሄ ህብረተሰብ
         
እየተነዛነዝን ያለ እድሜ ከማርጀት
አንድ ሶስት ሆነን ቡድን ከማበጀት
ለማይረባ ነገር ወጭን ከመበጀት
እስኪ ለረቢዑ እንሰብስብ ባጄት
ሐያ እንሳፈረው ያንን የገራም ጀት
   እናንተን አይጠቅስም
በሙጀሲማ ስም የተወሸቃችሁ
የምትበጠብጡ እውነቱን አውቃችሁ
እየሸተተን ነው  የሀሳብ ጭቃችሁ

ምንድን ነው ማንንም በነገር መሸኘት
ሰው ሀቅ እንድረዳ ነው እንጂ መመኘት
የምን መድረቅረቅ ነው ሹህራ ለማግኘት
         ስንት አለ መሰለህ……
የሙጀሲም ጋሪ ሳይሰራ አንድ ፋይዳ
በየሽርኩቻው ስር ነገር እየነዳ
ማንንም መቃወም እውቀት የሚመስለው
ቀርበው ሲጠይቁት መረጃ የሌለው
         ስንት አለ መሰለህ……
በሱ አስተሳሰብ ዱዓት የሚሰፍር
ለመሀይምነት ፈፅሞ እማያፍር
         ስንት አለ መሰለህ…
እውቅና እሚመስለው ፊትና ማቀጣጠል
ጀመዓ እሚበትን ቆርጦ በመቀጠል
አህባሾች እያለ ምቾት ለመዘንጠል
ፓርቲ የሚያቋቁም ውስጡን በተናጠል
ጀግንነት ነው ለሱ ዑለማን ማብጠልጠል
        ስንት አለ መሰለህ………
የትላንቱ ፊትና ያላስተማራቸው
ከነሱ ሀሳብ ውጭ ሌላ እማይገዛቸው
          ስንት ሰው አየሁኝ…
ማታ ሚቀየሩ ጧት ከኛ ጋር መጥተው
ሳምንት የማይቆዩ ባቋማቸው ፀንተው
ለገንዘብ ነው እንጂ ለህዝብ የማያዝኑ
ሰውን ባለባበስ ብቻ እሚመዝኑ

እሬትና ማርን የሚቀላቅሉ
ሙዝ ተከልን ብለው እሾህ የሚያበቅሉ
አቋመ ብልሹ ብዙ ሰወች አሉ
            ይልቅ……
ቂል ከሚሆን ምርቱ ስሜት እየዘራህ
ሐያ ከኛጋ ሁን መውሊዳቸው ይምራህ

በሙሂቡ ቀለም💚❤️💚 ١٤٤٦ حجرا
ሼር ሼር ሼር
https://www.tg-me.com/byetiLhadorat
በፓኪስታን ውስጥ ያሉ ሁሉም የመንግስት እና የግል ትምህርት ቤቶች ለነብያችን ሙሀመድ መውሊድ እንዲደሰቱ ለሶስት ቀናት ትምህርት ቤቶች ዝግ ይደረጋሉ በማለት አስታዉቋል።

#ረቢዕ   #ሚላድ   #ነብዩሰዐወ   #ደስታ
https://www.tg-me.com/byetiLhadorat
ላንቱ የፃፍኩቱ………

በትንሽ መዳፌ በቁንፅል መፃፌ
ማቅለም ጀምሪያለው ቃላትን ሰልፌ

የውበቱን ረጋ በባዕድ እሚያትቱ
የዛን የደግ ሰው  አንደበተ ሩቱ
     መፃፍ ጀምሪያለው………
ማውጫ የለው መግቢያ ሽፋን የለው ጥራዝ
ሉል ንግግሮቹ ተወዳጅ ከአልማዝ
ብራናው ኹሙል ነው ማለቂያ የለው ገፅ
በሙሂቡ ዳኒ ታሪኩ ሲገለ'ፅ
   መፃፍ ጀምሪያለው………
ስላንቱ እየገጠምኩ ቃላት ባላረቅም
ከበያኑ ይልቅ ድልዙ ቢደምቅም
ጃሂል ነኝ አቃለሁ ምንም አወ አላቀም
መግጠም ሱሴ ሆኗል እሱን ደግሞ አለቅም
   መፃፍ ጀምሪያለው……………
የመልክሁ ቁንጅና ኢንታሃው እርቋል
የፀጉርሁ ዘለላ ሀሩ ተንጠቅ ጥቋል
ጨረቃ ለሁለት ሰማን ተሰንጥቋል
የዊላዳሁ ብርሀን እስከ ሻም ፈንጥቋል
ሳዋ ያለው ባህርም ባለበቱ ደርቋል
የቴምሩ ዛፍም ናፍቆት ተሰቅ ስቋል
    መፃፍ ጀምሪያለው………
ሲገጥሙ አይቼ ስንኝን መደርደር
ራሴን ሳላጠና ሳልቆም በመንደርደር

በሸውቅ ጋልቤ ካለሁበት ጓዳ
መግባትን ተመኘሁ ያመናረል ሁዳ
ወዳጅሁ ሙሂቡ

ስነጫነጭ መዋል አመሌ ገርሽቶ
ምን ሆነሀል?  ሲሉኝ
በመጤው ባሀሪየ ሰዉ ተመልክቶ
አላውቅም ምንድነው?
ልገልፀው አልቻልኩም የፊቶትን ቀመር
ሸፍጥ ሆኖብኛል መስማት ብቻ ኸበር

ላንቱ ገብቻለሁ ሁሉንም ከድቼ
እንቅልፍ ትቻለው ዳግም ብየ ዝቼ
ለተመልካች ሁሉ
እኔ አንቱን በመውደድ አሳበቀ ልቤ
ካንቱጋ አድራለው በሩሄ ተስቤ
ሙሂቡ
አብልጨ ልወደድሁ ከሰላማን ከቢላል
ላንቱ ይድረስልኝ ግጥሜ ይቀጥላል

እስኪ ሼር አድርጉት ነቢን የምትወዱ
እንዲ ዳረስልኝ ግጥም ለሚወዱ

በሙሂቡ ቀለም

https://www.tg-me.com/byetiLhadorat
Join
ዳና

መኪና ባታገኝ ተስበህ እንደ እባብ
በነቢ ውደታ በሚደንቅ ድባብ
በራችን ክፍት ነው ግባ ባሰኘህ ባብ
ዳና እንገናኝ ተዘጋጅ ያሸባብ


በmuhib ቀለም
https://www.tg-me.com/byetiLhadorat
1
እዳላስተምር

ቀርቼማ ነበር
በገጠር ዑለሞች ተጉዤ በእግሬ
ዳገቱን ሜዳውን ወንዙን ተሻግሬ
ሁሉን ቻል አድርጌ አንጀቴን አስሬ

       ቀርቼማ ነበር
ያውም እየተራብኩ በብዙ ሀሪማ
በራያ በየጁ አቦ ተውኝማ
በቃሉ አውራጃ በኮቻ ከተማ

አለሁኝ እንደ አለሁ በነገ በዛሬ
አስተምራለሁ ስል አቂዳን ተምሬ
ይሄው እገኛለሁ ሰንፌ ጠንክሬ

ግን ምን አደርጋለሁ

የማይታገሉት ባላንጣ ጥሎብኝ
ሁሌ በአዕምሮ እየተደፋብኝ
ንፁሁ ሀሳቤን እያፈረሰብኝ
የመከራ ናዳ የህይወት ውርጅብኝ
ቂራአት መውደዴ ዕድሜየን ፈጀብኝ

መፍትሄው የራቀ አስቸጋሪ ነገር
    አይጋፉት ድንበር
    አይሰርዙት መስመር
እምቢኝ ብሎኝ ቀረ ለማቆም ሲጀመር
ተጣብቆ አለቅ አለኝ ደሜ ሲመረመር

ስተቴን እንደ ቅርስ እያስተረጎመ
እምቢኝ ባይ ልሳኔ እንደተለጎመ
እንደ ደረቅ ቅጠል ከቀን ዛፍ ይረግፋል
ባየሩ ሽውታ በቅፅበት ይጠፋል
ሌላ መሻይኽ ሳይ ባድስ ይጠለፋል

እንደ ባህር አረግ የስቃየ ክምር እየተሰደደ
የግጥሞቼን ማማ የተስፋየ ፍሬ ነገን እየናደ
ሁሉም እረገጠው ሁሉም ጠቀጠቀው
የማይረባ እያለ አልፎ ሂያጁም ናቀው
      ነፋሴ ብቻ ነው
ምንድነህ" እያለ ደፍሮ ያልጠየቀው

ይገርመኛል የኔ ጀህልን አለማለፍ
እራመዳለሁ ስል ሁሌም ስጠላለፍ
          
ለሰው የማይገባ በርቀቱ የሚያምር
#ሙሂቡ_ተብየ_ቀለሜን ስቀምር
ወደ መልካም ነገር ጉዞየን ስጀምር
እንቅፋት የሆነኝ ሀቅ እንዳላስተምር
     እርሱ ነው ጠላቴ
የዱንያ ውደታ የመከራ ክምር

       

@yedanawecuchannnneel@
👍2
የታላቁ የዳና ሀሪማ መስራች የወኑት ዳንይ ዳንይል ዓወል ኸልዋ ግንባታ ላይ
2025/07/10 08:52:50
Back to Top
HTML Embed Code: