Forwarded from Beki Ayele
ቃል ስጠኝ
ሀና ደበበ
ተስፋን የሰነቀች አፍቃሪ ሴት ድምፅ የፍቅር ግጥም በገጣሚ ሀና ደበበ ቃል ስጠኝ ዛሬ ማታ 3/7/2016 በ #Beki_Ayele የዩቲዩብ ቸቻናል ቃል ስጠኝhttps://www.youtube.com/@Beki_Ayele
#ሰርቢያኖች ስለ ጦርነት ያላቸው ድንቅ አባባል
ጦርነት ሲጀምር.... #ፓለቲከኞች ጥይት ያቀብላሉ። #ባለጽጎችም ምግብ ይሰጣሉ። #ድሆች ግን ልጆቻችን ይለግሳሉ።
ጦርነቱም ሲያበቃ...
ፓለቲከኞች ቀሪ ጥይቱን ይሰበስባሉ። ባለጸጎችም ከጦርነቱ በተረፈው ሐብታቸው ማደግ ይጀምራሉ፤ ድሆች ግን ልጆቻቸውን በመቃብር ሥፍራ ይፈልጋሉ።
ይህ ነው የጦርነት ዶሴው
ሠላም ለኢትዮጵያ💚💛♥️
@yefkr_hiwet
ለካ 'ረፍትም ይደክማል...
ፍቅርም ህመም አለው...
ደስታም ጥቂት እንባ...

ሁሉም ነገር ከመናፈቅ ጋር በስሱ ሲሆን ነው ደስ የሚለው።



#ዝብርቅርቅ ሐሳብ።
@yefkr_hiwet
ይታዩኛል ብዙ ሰዎች፡
እራፊ አልባ ልብስ የለሾች፤

ይታዩኛል ብዙ ልብሶች፡
በውስጣቸው  የሉም
ሰዎች


@yefkr_hiwet
Forwarded from Beki Ayele
ሰላማችሁ ይብዛ እንዴት አላችሁ የሙዴ ባለሙዶች የፍቅርን በፍቅር ፍቅር የሆናችሁ ቤተሰቦች Beki ነኝ ከተገናኘን ቆይን ቢሆንም ፈጣሪ ፀሎታችንን Acsept ጠላታችንን blok አጥያታችንን Delete እያደረገ አገናኝቶናል ። እም በአንድ አሳብ ተገናኝተናል ፍቅራችን ከፍቅሩ ከራቀ ቆየ እም ይህ ሀሳብ እንደሚመልሰን አምናለው ሀሳቡም ከዚ ቀደም ሄደን የነበረ ቢሆንም የአሁኑ ግን ይለያል የአሁኑ የሚሆነው ምግብ ይዘን ዳቦ አስደፍተን ቡና ፈንድሻ እና መሰሎቹን ይዘን እዛው አብልተን አፍልተን አጠጥተን መመለስ ነው ይሄ የኔ ሀሳብ ነው እናንተስ ምን ትላላችሁ። ሀሳብ ስጡበት አሊያም መስማማታችሁን ንገሩ ጊዜን ለመጠቀም ያክል


@fkrn_be_fkr
ስለኪሳራችን ፣ ስለተሰናከለብን ፣ ስለቀለልነው ፣ ስተለበላሸብን ሆን ብለው ለሚረሱልን ፤ ሲያገኙን ፈገግታ ለሚያሳዩን ፤ ለሚያከብሩን ፣ ስናከብራቸው አክብሮታችንን እውቅና ለሚሰጡልን ።

ቺርስ ለነሱ 🙏

ጥንካሬያችንን ፈልፍለው ለሚያሳዩን ፣ ዘንበል ስንል ዝንብል ለማይሉብን ። ስንስት በቀላሉ አቋም ለማይዙብን ፣ ስንደክም ትከሻቸውን ለሚያውሱን ።

ቺርስ ለእነሱ 🙏

ሲጨንቀን ጭንቀታችንን ለሚጋሩ ፣  ለሚታመኑን ፣ ስኬታችን ለሚያስደስታቸው ፤ ችግራችን ለሚያሳስባቸው ፤ ለምንወዳቸው ለሚወዱን ።

ስንበድላቸው ለማይጨክኑብን ፤ ስናጠፋ ይቅርታ ለሚያደርጉልን ፤ ዋጋችን ለሚገባቸው ፤ ወዳጅነትን ለሚረዱ ፤ ድክመት ላይ ለማያተኩሩ

ቺርስ ለእነሱ
@yefkr_hiwet
የሆነ ጊዜ ነበር ከልቤ ስስቅ የነበረበት፣ ግን ሌላ ጊዜም ነበር በጣም ሳለቅስ የነበረበት፣ ከዛም ሳልፍ ግን በህይወት ላይ ለማዘንም ለመደሰትም ጊዜ እንዳለዉ ያመንኩበት፥

የሆነ ጊዜ ነበር ለህይወት መጓጓት የጀመርኩበት፣ ግን ሌላ ጊዜም ነበር ሁኔታዎች ማያልፉ መስሎኝ የተጨነኩበት፣ ከዛም ሳልፍ ግን ሁሉም እንደሚያልፍ ያየሁበት፣ ህይወቴ ዉስጥ ለተፈጠሩት ነገሮች ትርጉም መስጠት የጀመርኩበት

የሆነ ጊዜ ነበር ተስፋ የቆረጥኩበት፣ ግን ሌላ ጊዜም ነበር ከእንቅልፍ መንቃቴ ተአምር እንደሆነ የተረዳሁበት፣ ከዛም ሳልፍ ግን የሆነ ቀን እንደምሞት ያወኩበት

ሁላችንም ይሄን ህይወትን እየኖርን ያለነዉ ለመጀመሪያ ጊዜ ነዉ፣ ራሳቹ ላይ አትክበዱ ፣ ለራሳቹ ሌላ እድል ስጡ፣ የህይወትን ሌላ ጎን ለማየት አትስነፉ፥

@yefkr_hiwet
በእምነት_የመጣ_እምነት

ከለታት አንድ ቀን
ከማጣህ ከምሞት?” ፥ የሚል ምርጫ አቅርባ
የራሷን ጥያቄ ፥ በxእንባዋ አጅባ
ብሞት ይሻለኛል ፥ ብላ ነገረችኝ
ስትነግረኝ አመንኳት
እፈትናት ብዬ ፥ እንድትሞት ራኳት
ሳልፈልግ ሸኘኋት ፥ ሳትፈልግ አጣችኝ።

ከእለታት ሁለት ቀን
“እሷ ዋሽታ አታውቅም ፥ ለቃሏ ታማኝ ነች
እንዳጣችኝ አውቃ ፥ ይሔኔ ሞታለች።”
በማለት አስቤ
ለቀብሯ ስዘጋጅ ፥ እሷ ትኖራለች

ከእለታት ብዙ ቀን
“እንዴት አልሞተችም ?”
የሚል የእምነት እዳ ፥ መች አብሰለሰለኝ?
አጥታኝ ስትኖር ባያት
እየኖረች መሞት ፥ ምታውቅ መሠለኝ።
አምናታለሁና!
እሷ አትዋሽምና!

በላይ በቀለ
ወያ

@yefkr_hiwet
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኔ ስኬት

በ5 ደቂቃ ውስጥ የ ጂት ኩን ዶ ማርሻል አርት የ ብላክ ቤልትን ፈተና(ጋሬጣ) ተጋፍጦ የረታው ወጣት #ሙዋዝ_ጀማል ነገ ቅዳሜ 12/8/2016 ከረፋዱ 12:00 ላይ በ#Beki_Ayele የዩቲዩብ ቻናል ይጠብቁን ይጠብቁን።

        #የኔ_ስኬት
https://www.youtube.com/@Beki_Ayele
የኔ ስኬት

በ5 ደቂቃ ውስጥ የ ጂት ኩን ዶ ማርሻል አርት የ ብላክ ቤልትን ፈተና(ጋሬጣ) ተጋፍጦ የረታው ወጣት #ሙዋዝ_ጀማል ነገ ቅዳሜ 12/8/2016 ከረፋዱ 12:00 ላይ በ#Beki_Ayele የዩቲዩብ ቻናል ይጠብቁን ይጠብቁን።

        #የኔ_ስኬት
https://www.youtube.com/@Beki_Ayele
                      ጀገንኩብሽ
በረከት አየለ፣ ፋሲካ በላይ እና አብዱልሰመድ ሙሃመድ በጋራ በመሆን የሰሩት መውደቅን ለማፍራት የሚል የሚያጀግን ሀሳብ ያለው በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ አጭር ፊልም በBeki Ayele የዩቲዩብ ቻናል ዕሮብ 16/7/2016 ከአመሻሹ 12:00 ላይ ይጠብቁን።
             ጀገንኩብሽ
https://www.youtube.com/@Beki_Ayele
የመጀመሪያ ቀጠሮ
           የመጀመሪያ ግብዣ

የባጥ የቆጡን ሲያወሩ ቆዩና "ምን አይነት ሰው ነሽ?" አላት አፉ ጋር የደረሰውን ጉርሻ እየጎረሰ "ምን አይነት ሰው ነኝ መሰለህ" የጠቀለለችውን ጉርሻ ቁጭ አድርጋ ቀጠለች

"በጣም ስለወደፊታቸው የሚጨነቁ አስር እና ሀያ አመት የሚያቅዱ አይነት ነበርኩ። ከዛ ድንገት የሆነ ቅፅበት ላይ ታክሲ ላይ ያየሁት ጥቅስ አባነነኝ "ዛሬ ቢሆንስ የምትሞተው" ይላል ከዛ ያስጨንቁኝ የነበሩ ነገሮች በሙሉ ዋጋ አጡብኝ በቃ የእለቱ እለት ማታ እንደሚሞት ሰው መኖር ጀመርኩ

ራሴን የምከለክለው ነገር አልነበረም ሁሉንም አድርጌዋለሁ አሁን ምንም የቀረኝ የምለው ነገር የለም በቃ ለሁሉም ነገር ስሜት አጥቻለሁ ነው የምልህ። ነገሮች ቀስ ብለው እንዳይሆኑ አጣደፍኳቸው እና የሚያስደስቱኝ እና የሚያሳዝኑኝ ነገሮች ተመናመኑ

አንዳንዴ ከልክ በላይ ነገሮችን መገፋፋት ዋጋቸውን ያሳጣዋል።" አለችው እና መብላቷን ቀጠለች። መልዕክቷ ግልፅ ነበረ <ላንተ የሚሆን የማቀርበው ትኩረት እና ጉጉት አይኖርም> ማለቷ ነው።

እነሆ የመጀመሪያም
     የመጨረሻም ቀጠሯችን ሆነ ማለት ነው።

@yefkr_hiwet
ከገርልፍሬንዴ ጋ ስለኤክሶቻችን እያወራን  ።

ይገርምሻል ኤx እንዴት እንደምታምር ፣ ፀጉሯ እርዘመቱ ጥቁረቱ ግን ሰውነቷ የበለጠ ያምራል ከለሯም ንጣቱ እያልኩ በስሜት ከወንድ ጓደኛዬ ጋ እንደማወራ ሁሉ ብዙ ዘበዘብኩ

ሳያት ኮስተር ብላለች

አንቺ ከxሽ ጋ በምን ተለያያቹ ስላት

"አይ አልተለያየንም "
ማለት ?
"መሃላችን ላይ ትንሽ ግጭት ነገር ተፈጥሮ ነበር አሁን እንፈታዋለን
"

@yefkr_hiwet
በእርሱ ቁሰል
...........................
ተገረፈ

ተወነጀለ

ተተፋበት ተሰቀለ

እሱ ስለ እኛ ሞትን ተቀበለ

አቤት ትህትና አቤት አቤት ፍቅር

ኢየሱስ መጣ እኛን ሊያድን ወደምድር

       በእለተ አርብ መስቀል አሸከሙት

       ይህም አልበቃቸው በጅራፍ ገረፉት

        ህዝቡም በጥላቻ ምራቅ ተፉበት

        ያኔ ያመሰገኑት አሁን ሰደቡት

ይሰቀል ይሰቀል እያሉ ሲጮሁ

አላወቁም ነበር ለእኛ መሆኑን?

እሱ እኮ ንጉስ ነው የሰማይ የምድር

ዝቅ ያለው ፍቅርን ሊያስተምር

እግር ያጠበው ትህትናን ሊያሳይ

በሰው እጅ ተሰቅሎ ሆነ ለሰው ሲሳይ

ከ99 በጎቹ አንዱ ቢጠፋበት

ለፈጠረው ፍጡር በጣም ሳስቶለት

ወረደ ወደምድር ሊሆን መስዕዋት

እናቱስ ግን እንዴት ቻለች

እንባዋን ወደምድር ረጨች

ፀሀይም አኩርፋ ብርሀኗን አጠፋች

የአምላኳን ገላ አላሳይም አለች

ጨረቃም ከእሷ አቅም ደም ለበሰች

ጴጥሮስም አላውቀውም ብሎ ካደው

ዶሮ ሲጮህ ትዝ አለው አምላኩ ያለው

አዎ በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን

በእኛ ሀጥያት እሱ ተሰዋልን

በሱ ፍቅር ከሀጥያት ነፃን

መገረፍ ያለብን እኛ የተገረፈው እሱ

መሰቀል ያለብን እኛ የተሰቀለው እሱ

መከራን ተቀበለ  አስጠጋን ወደራሱ

ይህ ነው እግዜአብሄር 

ለሰው ልጆች ብሎ እራሱን ሚያዋርድ

ፍቅርን ለማስተማር ፍቅር ሆኖ የሚወርድ

ይህ ነው እግዘብሔር  ፍጥረቱን ሚወድ

.............................


@yefkr_hiwet
​ትመጣ እነደው ብዬ
     ከበርክ ቆሜ
   ደጅ ደጁን እያየው
  በፍቅርህ ታምሜ
   ልክ ስትመጣ
   ሁሉን እረስቼ
  ከንፈርህን ሳምኩት
መታመሜን ትቼ

       ለካስ
አንተን የሚያሳየኝ
የቁም ቀዠት ኖሩዋል
የሠው እያየሁኝ
  የራሴ ህልም ሆኗል

  መንቃት ባለፈልግም
  ከዚህ ውብ ቅዠቴ
   ድንገት ቀሰቀሰኝ
     የገዛ ብሶቴ


‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌...........♥️💍••●🍃🌹🍃●•............


‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ @yefkr_hiwet
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌        ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
2024/05/15 21:42:55
Back to Top
HTML Embed Code: