Telegram Web Link
♥️ ፅናት ♥️...!!!
           .
           .
           .
🥀..ክፍል 6..🥀
          .
          .
          .
#Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው .!!
.
.

.
.
በደማቁ በእርሳስ በማያምር እና ምንጭርጭሩ በወጣ ፅሁፍ ወረድ ብሎ በተመሳሳይ ፅሁፍ...."ህይወት ብዙ አስመሳይ እና ከሀዲ እንዳሉዋት ግልፅ ነው። ሰው ሳያስመስል የሚኖረው ጥላቻን ፣ ውሸትን ፣ አጭበርባሪነትን፦ ብቻ ነው ጥቂት እውነተኛ ሰዎች አሉ። ግን እነሱን የምናገኛቸው አስመሳዮች ከጎዱን በኋላ ነው እኛም አናምናቸውም  ምክንያቱም አምነን ተጓድተናል እውነተኛ ሰዎችም ይከፋሉ  ምክንያቱም አስመሳዮች የሆነው ሆኖ ህይወት ቲያትር እኛ ደሞ ቲያትርኛ ነን ትወናችንን ስንጨርስ ደሞዛችንን ለመክፈል እንሄዳለን"። ፅናት ይህንን አንብባ ስትጨረስ ፈራችም ተፅናናችም ደብተሩን ልትገልፀው ስትል ከደረጃ የሚመጣ ኮቴ ሰማች ቋቋቋቋቋ ፅናት የያዘችውን ደብተር በድንጋጤ እና በፍጥነት ከደነችው።

፨የሰማችው የ ሊባኖስን ኮቴ ነበር። በፍጥነት ወደ እሷ ተጠግታ "ይህውልሽ ሻይ አምጥቼልሻለው ጠጪ" አለችና ሻይ የያዘውን እጇን ዘረጋችላት ፅናት እጇን በዝግታ ሰዳ ተቀበለቻት እና የሻዩን ብርጭቆ ጆሮ ይዛ ፈዛ ቀረች። ከመፈዘዟ ያነቃት የሊባኖስ "ጠጪ" የሚል ድምፅ ነበር።
 ፅናት "እሺ እሺ እጠጣለው" አለችና አንዴ ጎንጨት አረገች። ሊባኖስ ከለበሰችው ፎጣ ሸሽጋ የያዘችውን ፓስቲ(በዘይት የተጠበሰ ፍርኖ ዱቄት ብስኩት)  አውጥታ "እንኪ በሻዩ ብይ" አለቻት። ፅናት ፓስቲ በሻይ በጣምምም የምትወደው ምግብ ነው።  እሺ ብላ ተቀብላት ልትበላ ስትል ሊባኖስ ከፓስቲው ጋር የያዘችውን ዶቦ አውጥታ "እሱ ይደረቅብሻል በዳቦ ብይ ብዬ ነው ይህንን እኔ እበላዋለው" ብላ ከእጇ ወሰደችው።

ፅናት ዳቦ ጭራሽ የማትወደው ምግብ ነው በተለይ በሻይማ ጭራሽ አትበላም ሊባኖስን "ይህንን ምግብ ጭራሽ አልወደውም ፓስቲው ይሻለኛል" ማለትን ፈራች። እሺታዋን ገልፃ ከዳቦ በሻይ ጋር ውስጧ መታገል ጀመረ። ግባ አትግባ ፤ውጣ አትውጣ ሊባኖስ ሊባኖስን እያየች የግዷን እሩብ  ታክሏን በልታ ከዛ "በቃኝ" አለች። ሆዷ ቢርበውም ዳቦውን መብላት ግን አልቻለችም ፅናት ለመጨረሻ ጊዜ  ትናት ጠዋት ከ ትግስት ጋር ትግስት ማታ ማታ እያዞረች ከምትሸጠው የተረፈውን  ፓስቲ  በሻይ ነው።

ሊባኖስ ፅናትን አየት አድረጋ "ምነው ሚጢጢዋ? አልተመቸሽም እንዴ? አለቻት ። ፅናት በህይወቷ አንዴም ቢሆን አድረጋ ማታውቀው መዋሸትን ነውና በሚንቀጠቀጥ ድምፅ እጆቿን እያፋተገች "እእእ አአአ አዎ ዳቦ አልወድም" አለቻት። ሊባኖስ በግረምት እያየቻት "እና ለምን በላሽ?" አለቻት ቆጠት ብላ ፅናት በድጋሜ መዳፎቿን እያፋተገች በተቆራረጠ ድምፅ "ፈረቼሽ ነው" አለቻት። በሰቀቀን ቀና ብላ እያየቻት" ሊባኖስ የአግራሞት ፊት እያሳየች "ምን?እንዴት? ምኔ ያስፈራል? ምነው እንድትፈሪኝ ያረኩት ነገር አለ?" አለቻት። ፅናት አሁን የሊባኖስ ጥሩነት እየታያት የመጣ ይመስላል ፈገግ ብላ "አይ" አለች። ፍራቻዋ ለቀቅ ሲያረጋት እህቷ ትግስት ትዝ አለቻት። "ወይኔ እህቴ ብላ ብድግ" አለች። ሊባኖስ "አይዞሽ የት ናት ምን ሆና ነው እዚህ የገባችው?" አለቻት።ፅናት እየተርበተበተች የተፈጠረውን ሁሉ አንድም ሳታስቀረ   ለሊባኖስ  ነገረቻት።

ሊባኖስ ፅናት በነገረቻት የበፀሎት አወዳደቅ አዘነች። ፅናት አሳዘነቻት ውስጧ አቅፈሽ አፅናኛት አቅፈሽ አባብያት አላት። ከዛም ፅናትን በፍጥነት እና በቅልጥፍና ተጠመጠመችባት። ፅናት ደነገጠች ሊባኖስ ስታቅፋት ጠረኗ ይበልጥ ከ አፍንጮዋ ጋር ተገናኝቶ እንደጉድ ይሸታት ጀመር። ፅናት የሊባኖስ ጥሩነት እየታያት ቢመጣም ፍራቻዋ ግን ጭራሽ እየባሰባት መጥቶል። ሊባኖስ በድንገት ፅናትን ከእቅፏ አስወጥታ  ትክሻዋን ግጥም አርጋ በሁለት እጆቿ ያዘቻት። ከዛማ ወደ ፅናት ተጠጋች እና  አይን አይኗን ታያት ጀመረ። ፅናት አንገቷን ደፋች።

ሊባኖስ "ቀና በይና እኔን ፤ አይን አይኔን  እይኝ" አለቻት። ፅናት በሰቀቀን ቀና ብላ ሊባኖስን ማየት ጀመረች። ሊባኖስም ለፅናት "እኔ የምልሽን ሁሉ ትያለሽ ሰማሽኝ" አለቻት ፍጥጥ ብላ ። ፅናት በጉንጯ አዎታዋን ገለፀጭላት። በይ አይንሽን ጨፍኝ ስትላት ፅናት ደንግጣ "እ" አለቻት። "አልሰማሽኝም"? አለቻት። ፅናት "አይ ሰምቼሻለው እሺ ብላ አይኞቿን ከደነቻቸው  ከዛ ቃል በቃል እንዲህ አስባለቻት "እኔ ሁሌም የሚመጡብኝን ነገሮች ያለ ፍራቻ ያለ መደናገጥ ጠንክሬ አልፈዋለው። ፈጣሪ መቼም ቢሆን የማልችለውን ፈተና ሊጥለኝ አይሰጠኝም ውስጤ እና እምነቴ ጠንካራ ነው ፈጣሪ የመጥፎ ስሜቶች መሸጋገሪያ ድልድዬ ነው"።

ይንን አስብላት ስታበቃ "እሺ አሁን ውስጥሽን ምን ተሰማው?" አለቻት። ፅናት በረዥሙ ተንፍሳ "ነፃነት ሰላም እና ጥንካሬ" አለቻት። ሊባኖስም "በጣም በሳል ልጅ ነሽ በይ አሁን ተነሽና እህትሽ ስላለችበት የጤና ሁኔታ እንጠይቅ" አለችና የቀኝ እጇን ዘረጋችላት ፅናት አሁን ሊባኖስን ለምዳታለችና ፈገግ ብላ እጇን ያዘቻት እና ደግፋት እህቷን ቅድም ወዳስተኙበት ክፍል ሄዱ  በፀሎት ግንንንን የለችም።
ፅናት "እህቴ" አለችና ደነገጠች። ሊባኖስም "ተረጋጊ ሚጢጢዋ ኦፕራሲዮን ክፍል ነው ምትሆነው ኦፕራሲዮን ያረጓታል ብለሽኝ አደል እንዴ?" አለችና ጠቀሰቻት።ፅናት "ልክ ነሽ እሺ" አለቻት ከዛ እስቲ ነይ አረፍ በይ አለችና ወደ አንድ ብቸኛ ወንበረ ወሰደቻት። ፅናት በጣም የድካም እና የጭንቅ ስሜት እየተሰማት ነው ይህ የረሀብ እና የጭንቀቱ ምልክት ነው ሊባኖስም አውቀዋለች። "ስሚ ሚጢጢዋ አቅም አጥሮሻል እኮ ቆይ ምግብ ነገር ላምጣለሽ እዚሁ ጠብቂኝ እሺ ብላት" ሄደች።

ፅናት በጣም እርቧት ስለነበረ በፍጥነት ነው "እሺ ያለቻት። ከዛም ሊባኖስ እሮጥ እሮጥ ዱብ ዱብ እያለች ወደ ምግብ ቤቱ ሄደች። ሊባኖስ አሁንም ያንን ደብተረ ጥላው ነው የሄደችው ፅናት ሊባኖስ ከኮሊደሩ ወደ ደረጃው ስትወረድ ቀጣይ ገልፁን ለማንበብ ተጣደፈች።

እጇ በትንሹ ቢንቀጠቀጥም ከፈታ አየችው በጣም በትልልቅ ፅሁፍ ነው የተፅፈው ግን ይሄኛው የፊት ገልፁ ላይ እንደተጻፈው በሙንጭር ፅሁፍ አልተጻፈም ደብተሩን ብድግ አድረጋ ታፋዎቿ ላይ አስቀመጠችው እና አይኖቿን ወደ ደብተሩ ወረወረቻቸው።ፅሁፎቹ በጣም ተነባቢ ናቸው ነገር ግን አያምሩም ማንበብ ጀመረች።እንዲህ ይላል  ...

"ሄዋኔ የምነግርሽን አድምጪ በመጀመሪያ ሰው ተሰባሪ ነውና ሰውን ሳይሆን ዘላለማዊ የሆነውን አምላክሽን እመኚ።ለስላሳው  ልብሽን ለሸካራ ልብ ላለመስጠት የፈለግሽው አይነትን ሰው ከጎንሽ አድርገሽ ከእሱ ጋረ ትልቅ ህይወትን ለመመስረት እና ደስተኛ ለመሆን አምላክሽ ተማፃኝ ሁኚ ""

አቋምሽን ፣መልክሽን ፣አለባበስሽን በማየት የሚቀርብሽን አፍቃሪ ነኝ ባይ ሰው ቢመጣ ፈፅሞ ላለመሸወድ አሁንም ደግመሽ የፈጣሪሽ ለማኝ ሁኚ።  ውዴ እኛ ሴቶች ከወንዶች በተፈጥሮም በአስተሳሰብም እንበልጣለን ደካማ ጎናችን እምነታችን ነው። ክፉ ሲያጋጥመን ይቀየራል ማለታችን የሆነው ይሁን የቀረው ይቅር ያፈቀርሽውን ሳይሆን ያስፈቀረሽን ፈጣሪ እንዲ ብለሽ ለምኚው አምላኬ ይህ ሰው የልቤን መሻት የሚያሞላልኝ ሰው እንደሆነ ልቤ ምስክር ናት በሙሉ ልቤ እንጂ በሙሉ አይኔ አላየውትም።

.
.
🥀..ክፍል 7 ቶሎ እዲለቀቅ አንብባቹ ስጨርሱ ላይክ ሼር አርጉ ..🥀
          .
          .
👍11322🙏2
♥️ ፅናት ♥️...!!!
           .
           .
           .
🥀..ክፍል 7..🥀
          .
          .
          .
እንዳፈቅር አፍቅሬም እንድሰጥ የሰጠከኝን ልብ ለእሱ ሰጥቼዋለውና ይህን ሰው የኔ አርገው ካላረከው ልቤን መክረክ መልሰው ልቤ ፈጣሪውን ይሰማልና። ውዴ ይህን ካልሽ ኋላ ልጁ ያንቺ ታማኝ አፍቃሪ ካልሆነ ፈጣሪ ጠራርጎ ከልብሽ አውጥቶ ያንቺን እጣ ፋንታ በልብሽ ያሰፍራል። የሰፈረውም ሰው በፍቅርሽ እኩል ፍቅር ሰቶሽ ያስደስትሻል"
    
ፅናት አንብባ ስትጨረስ ሊላኛውን ገልፅ ገለጠችው ሊላኛው ገልፅ ላይ ወንድ ሆይ አደራ ሴት ልጅን አትጉዳ ሴት ማለት በአለም ላይ ትልቁን ስቃይ ፤ ትልቁን መከራ ፤ምጥን ተቋቁማ በህይወት እንድትኖር ያረገችክ  የመኖርክ ትርጉም ናት። ምጥ ሲይዛት የሰውነት ክፍሏ ያለምንም ማደንዘዣ ተፈልቅቆ እና ተላቆ በባሊ ሙሉ ደም ከሰውነቷ ፈሶ ተቀድቶ ሰውነቷ በላብ ተጠምቆ በሞት እና በህይወት መካከል ሆና  የወለደችህ ናትና።
     
ትንሽ ነገር ሰውነትህን ሲቆርጥክ ምን ያህል ህመም ነው የሚሰማክ? በጣም ትልቅ አደል? እና እሷ ግን በምጥ ሰአት ሰውነቷ ለሁለት ሲሰነጠቅ አንተን በህይወት ተሰቃይታ ካኖረችክ ሆዷ ለማውጣት ለምትጥረው ጥረትስ? ስቃይስ? በሌላ መልኩ ያገባካት ሚስትክ አንተን አባት ለማድረግ ተመሳሳይ ስቃይ ነው ምትሰቃዬው አዳሜ ሄዋኔንን አትጉዳ" ይላል።
    
ፅናት አለቀሰች ስቅስቅ ብላ አለቀሰች በጣም አለቀስች አይኖቿ እንባን አዝለው መቆየት አልቻሉም እያነበበች ያለው ደብተር እና ፊቷ በእንባ እራሱ። ደብተሩን ከድና አስቀመጠችው። ነገር ግን ያዘነ ልቧን ከድና አለማዘን አልቻለችም። በህፃን አይምኖዋ ስንቱን አሰበችው!ሰው በኖረው ኑሮ እንጂ በኖረው እድሜ አስተሳሰቡ አይለካም።
     
ፅናት እሬሬሬሬ አለች አይታት ለማታውቀው እናቷ አለቀሰች። ተደፍታ ማንባት ጀመረች። እያለቀሰች ሊባኖስ መጣች። ፅናት ግን ልብ  አላለቻትም  ምክንያቱም ያኔ ለመጀመሪያ ጊዜ ስለ እናቷ አሟሟት  ስትሰማ የሰማቻቸው ቃላቶች በጆሮዋ እየተደጋገሙ ስለነበረ ነው።" አባትሽ ነው እናትሽን የገደላት!" የጎረቤታቸው ድምፅ "ፅናቴ አባታችን እናታችንን አንገቷ ላይ ቢላ ሰክቶ ነው የገደላት"። ፅናት እራሷን አጥብቃ በእጆቿ ያዘቻቸው።
      
ሊባኖስ ብትጠራትም ልሰማት አልቻለችም። ፅናት በእራሱዋ  አለም ውስጥ ያለ ሰው ሆናለች። ልክ እንደ ስሟ ፅናተኛ ብትሆንም ይህ ግን መቋቋም እጅግ ከበዳት ከተቀመጠችበት ተነስታ ቆመች። እጆቿ አሁንም ጭንቅላቷ ላይ ናቸው።ሊባኖስ ግራ ገባት "በደቂቃዎች ውስጥ ምን ሆና ነው?"ብላ ደነገጠች።  ሊባኖስ በድንጋጤ "ፅናት፤ ሚጢጢዋ ፤ደና ነሽ? ምነው ችግረ አለ?፤ እህትሽ ደና አደለችም  ፅናት መልስ አልስጠቻችም መንገዳገድ ጀመረች። ሊባኖስ ደገፈቻት። ፅናት ከዛን በኋላ እራሷን ሳተች ሊባኖስ እረዱኝኝኝኝኝ ብላ ጮከች።




  ፨የሊባኖስን ድምፅ የሰሙ ሁሉ ተሰበሰቡ ፅናትን ወደ ህክምና ክፍል ወሰዷት።
ሊባኖስ ደንግጣለች።"የፈጣሪ ያለ አሁን ደና አልነበረች እንዴ?" አለች ድምፅ አውጥታ ለእራስዋም አልገባትም ከዛም ወዲያውኑ "ለነገሩ ተረብሻ ነበር" አለች። ሊባኖስ  በራስዋ አለም ውስጥ ሆና ፅናትን ሊረዱዋት የሚረባረቡትን ሰዎች እረስታቸዋለች። አንድ ነርስ "ነይ እህቴ እዚህ ተቀመጪ እና ተረጋጊ ምኗ ነሽ?" አለቻት።

ሊባኖስ ምኔም ናት ማለት አልፈለገችም ፤ ግን ደሞ እህቴ ናትም ብላ መዋሸት አልፈለገች፤ ከዛም "እኔም ዛሬ ነው ያወኳት" አለች። ነርሷም "እሺ እንደዛ ከሆነ በቃ ተረጋጊ" አለችና ጥላት ሄደች። ሊባኖስ ደብተሯን ካስቀመጠችበት አግዳሚ ወንበር አምጥታ ገልፃ ከ ጉያዋ እራስ አውጥታ ለመፅፍ ጣቷቾን አዘጋጀች።

ደብተሩን ገለጠችው ስትገልጠው የፃፈችው ፅሁፋ ላይ የበሰበሰ ቦታ አየች የበሰበሰው ሉክ ከእስኪብረቶ ቀለም ጋር ሆኖ አንድ ፈዛዛ ነገር ሰረቷል። ሊባኖስ ይህንን ስታይ የፅናት እንባ ደብተሩን  እንዲህ እንዳረገው መገመት አልከበዳትም። "ይህቺ  ብላቴና ለምን በእዚህ ፅሁፋ አለቀስች? ለምንስ ነው ይህ ፅሁፍ የረበሻት?" አለች። ግን ይህንን ለማወቅ የግዴታ ፅናት ወደ እራስዋ እስክትመለስ መጠበቅ አለባት።
  
ሊባኖስ ስልኳን አውጥታ ደወለች።"ሄሎ" አለች። አንድ ሰው "አቤት" አላት። "በቃ እኔ ወደ ሰላማዊያን ልሄድ ነው" አለችው። "አሁን የት ነሽ?" ሲላት አሁንም "እዚሁ ነኝ ግን በቃ ልሄድ ደክሞኛል" አለችው።  ሰውየውም "አይ ሊባኖስ በቃ ስትረበሺ እና ማሰብ ስትፈልጊ እነሱ ጋረ ነው አደል የምትሄጂው?" አላት።
ሊባኖስም'' አዎ ልክ ነክ ዛሬ የሚመጣ ሰላማዊ  የለም?" አለች።  ሰውየውም "አለ ቦታ አለ እንዴ አንቺ ጋር" አላት። ሊባኖስም "አዎ 5 የተለቀቀ ቦታ አለ" አለችው። ሰውየውም "እሺ ጥሩ በቃ እዚህ 4 አሉ አመጣቸዋለው"። አለና ተሰናብቷት ስልኩን ዘጋው።ሊባኖስም ደብተሯን ይዛ ከሆስፒታሉ ውልቅ አለች።ወደ ሰላም የምታገኝበት ቦታ ሄደች...                                                  

   ከ 2 ወር ከ15 ቀናት በኋላ...

ሁሌም በእነዚህ የህክምና  ቀናት ውስጥ ፅናት ሲርባት የምታበላት ፤ሚስጥሯን ለምትነግራት ፤እና እራስዋን ያካፈለቻት ሴት ሊባኖስ ነበረች። ፅናት ለሊባኖስ ስለ እራስዋ እና ስላሉባት ችግሮች እንዲሁም ስለምትወዳት እህቷ ለምን ያንን ወረቀት ስታነብ እንደከፋት ሁሉንም ባለፉት ሀኪም ቤት በቆዩባቸው ጊዜ ነግራታለች።
    
ሊባኖስ ግን ለጭንቅላቷ ይከብዳታል በማለት ሙሉ ህይወቷን አላካፈለቻትም አልነገረቻትም ።
ሊባኖስ ለፅናት በህይወቷ ውስጥ የሚፈጠሩት  ነገሮች ሁሉ እሷ ምንም ያህል ብትታገል መሆናቸው እና መፈፀማቸው እንደማይቀር ብርታት ያለውን ቃል እየነገረቻት ውስጧ  እንዲቀረፅ አድርጋታለች። በተጨማሪም እራሷን  ስታ ከነቃች በኋላ በነጋታው መጥታ ብዙ ምክሮችን መክራት እና ከ ተሻላት በኋላ ሙሉ በሙሉ ትምርቷን እንድትማር ወላጅ በተባለ ቁጥረ እሷ እንደምትመጣላት አስረግጣ ነግራት ነበረ።  ያኔ ፅናትም መልሷ እሺ ነበር ምክንያቱም ፅናት ያኔ ለሊባኖስ በህይወቷ ስለተፈጠረው ነገር ስትነግራት ሊባኖስ ለፅናት  ብርታት ሆናታለች እንዲህ ነበረ ያለቻት "እየውልሽ ፅናትዬ እንዳልኩሽ ትምርትሽንም ቀጥይ በፍፁም ትምህርትሽን ማቋረጥ የለብሽም እህትሽ ደካማ መሆንሽን ብትሰማ በጭራሽ ደስ አይላትም ደስ የሚላት ጠንካራ ስትሆኚ  ነው እንጂ ደካማ ስትሆኚ አደለም እህትሽ በእሷ ምክያት ትምርትሽን እንዳቋረጥሽ ብታውቅ ይፀፅታታል" ነበረ ያለቻት።

ዛሬ ይህ ሁሉ አልፎ በፀሎት  ልትመጣ ነው። 2 ወር ከ15 ቀን ፅናት ትምህረት  ቤት ስትሄድ ሊባኖስ ሆስፒታል እህቷን እየተመላለሰች እየጠበቀችላት የ15ቀን ረፍቷ ሲያልቅ  ለ ወር ትምርቷን ሳታቋርጥ ቀጥላለች። ሊባኖስ ፅናት እንድታጠና እና የእሷን እና የእህቷን ህይወት ትልቅ ደረጃ ደርሳ እንድታሻሽል ብርታት ስለሆነቻት ትምህርቷን ጥሩ አድረጋ ይዛዋለች ። በፀሎትም ከህክምና ስትወጣ ከሊባኖስ ጋር ዶክተሩ አስተዋውቋታል "እህትሽ ጎን የነበረችው ሴት ናት"ብሎ።

ዛሬ የፌሽታ ቀን ነው በፀሎት ወደ ቤቷ ልትመጣ ነው ፅናትም ቤቱን በእሷ እና በቤቱ አቅም ፏፏ አድርጋዋለች። እህቷን ቤቷ እስክታያት በጣምምምምምም ጓጉታለች።
.
.
🥀..ክፍል 8 ቶሎ እዲለቀቅ አንብባቹ ስጨርሱ ላይክ ሼር አርጉ ..🥀
          .
          .
👍12838🤬5👎2😱1
Forwarded from Hibtu store
Tommy short brand ካልሲ / socks 🧦
Price - 300*5=-1,500

Telegram- @hibtuuu
Phone- 0913285784
👍2
♥️ ፅናት ♥️...!!!
.
.
🥀..ክፍል 8..🥀
.
.
ፅናት ቤቱን አዘጋጅታ ጨርሳለች እና  ሊባኖስ እና የአላዛር አባት አቶ ኪዳኔ በፀሎትን ይዘዋት እስኪመጡ እየጠበቀች ነው። እየተቁነጠነጠች ቁጭ፣ ከዛ ብድግ፣ እቤቷ ወጥታ አየት፤ ከዛ መለስ። በጣም ጓጉታለች። በጣምምምም ፍራሿ ላይ ጋደም አለች።

ወዲያው በር ተንኳኳ ፅናት ተስፈንጥራ ተነስታ ከፈተችው...

ዊልቸረ ላይ የተቀመጠችውን የእህቷን የዊልቸር መግፊያ እጀታ አቶ ኪዳኔ ይዘውታል። ሊባኖስም የበፀሎትን ህክምና ላይ እያለች የምትገለገልበትን እቃዎች በአነስተኛ ሻንጣ ተጠቅጥቆ ይዛዋለች።

ፅናት በሩን እንደከፈተችው አይኗ እህቷ ላይ አረፈ "እህቴ" አለች።በፀሎትም "ፅናትዬ ብላ እጆቿን ለማቀፍ ዘረጋቻቸው" ፅናት ጎንበስ ብላ በፀሎት እቅፍ ውስጥ ገባች። በፀሎት ሳግ እየተናነቃት "ይህ ጠረንሽ በጣም ናፍቆኝ እንደነበረ ታውቄያለሽ?" አለቻት። ፅናትም ሲቃ ባዘለ ድምፅ "እኔ ለእራሱ በጣም ናፍቀሽኛን" አለችና ሳመቻት። ሊባኖስ ከት ብላ ስቃ "አይ ፅናቴ በቃ አንቺ ናፍቀሽኛል ለማለት ናፍቀሽኛን የምትይው የኔ ቆንጆ ቆይ መቼ ነው  ቃሉን  በስነ ስረአቱ ጠረተሽ ማረግ የምታሳያት ደሞ አልናፈኩሽም እንዴ ትናት እኮ ነው የተገናኘነው  አለችና  እጇን ዘረጋችላት ..ፅናትም ከበፀሎት  እቅፍ ወጥታ ወደ ሊባኖስ ተጠግታ እቅፍ አረገቻትና  "አንቺም ናፍቀሽኛን ያላንቺ እማ መች ይሆልኛን" አለቻት። ሊባኖስም "እውነት ነው ሚጢጢዋ" አለችና ሳመቻት። ፅናት  አቶ ኪዳኒን አየት አድረጋ እጇን ዘረጋችላት እሱም እጁን ዘረጋላት፡ተጨባበጡ ወዲያው ኑ ግቡ አለቻቸው። ከዛም ተከታትለው ገቡ። ፅናትና ሊባኖስ ምግብ ማቀራረብ ጀመሩ።  ፅናት የቆረጠችውን የቁርጥ እንጀራ ልታስይዝ ስትል ሊባኖስ "ቆይ እኔ አስይዛለው አንቺ ቡናውን አፍይው" አለቻት። ፅናትም "እሺ ሊቦዬ" አለችና ቡናውን ለማፍላት ቁጭ አለች። ፅናት በፀሎትን አየቻት በፀሎት አይኖቾን ወደ አንድ አቅጣጫ አድረጋ ታረገበግበዋለች። ፅናት ግራ ገባት ግን ዝም አለች። ምን እየተፈጠረ እንደሆነ ግራ ገባት። ሊባኖስን አየቻት አይናቸው ሲገጣጠም ሁለቱም አይናቸውን መለሱ ፅናት ምሳቸውን ከበሉ በኋላ ቡና መቁላት ጀመረች።  አሁንም በድጋሜ በፀሎትን አየቻት ካፈጠጠችበት አይኖቾን መለስም አላረገችም።  ሁሉም በልተው ጨረሰዋል ሲበሉ በፀሎትን ሊባኖስ ነበረ ያጎረሰቻት።

ፅናት ግራ ገባት ወደ ሊባኖስ ዞራ ሊባኖስን በጥያቄ አስተያየት አፋጠጠቻት ሊባኖስ ግን ዝም ብላ ከአቶ ኪዳኔ ጋር ማውራቷን ቀጠለች። ፅናት አቁነጠነጣት ቡናውን ቆልታ ስትጨረስ ልትወቅጥ ውጪ ወጣች። ቡናውን እየወቀጠች ጆሮዋን ወደ ቤት ጣለች። የሽኩሹክታ ድምፅ ይስማታል ምን እንደሚሉ ግን አልተሰማትም።  ቡናውን ወቅጣ ወደ ቤት ስትመለስ ሊባኖስ እና አቶ ኪዳኔ ዝም  አሉ።ፅናት ጨነቃት ሁለቱንም በተራ አይታቸው አይኗን መለሰች። ፅናት ጀበናው ላይ ውሀ እና የቡና ዱቄት ጨምራ ጣደችው። ቡናውን ጥዳ እስኪፈላ ፈልቶ እስኪሰክን ሁሉንም በተራ አየቻቸው። በፀሎት ምንም ቃል ቤት ከገባች በኋላ አላወጣችም። ቡናውን ቀድታ ልትስጥ ስትል ሊባኖስ  ቆይ እኔ እስጥልሻለው" ስትል። ፅናት "አይ እኔ እሰጣለው" አለች። ሊባኖስ "ቁጭ በይ አልኩሽ" አለች እና ተቆጣቻት። ፅናት ግራ ተጋብታ "እሺ" አለች።

ሊባኖስ ቡናውን በፀሎት በእጇ "እንኪ ያዢ ቡና" ብላ ስጠቻት በፀሎትም በዳበሳ መልክ ተቀበለቻት ጠጥታ ስትጨረስ ሊባኖስ ተቀብላ ለፅናት ስጠቻት።ፅናት ይበልጥ ግራ ገባት ሳታስበው "እንኪ ያዢ ቡና"አለች። አንደኛው ተፈልቶ ሁለተኛው ሊቀዳ ሲል ሊባኖስ ስልኳ ጠረቶ ወጣች።
ፅናት ቡናውን ቀድታ ለጋሽ ኪዳኔ ልትሰጣቸው ስትል  ቆይ እኔ ሰጥልሻለው  ሲሉዋት  ፅናት ብስጭት ብላ "አይ ምንድነው እኔ እስጣለው ምናምን ምትሉት" አለችና ለእሳቸው አቀብላችው ከዛም ለሊባኖስም አስቀመጠችላት። አቶ ኪዳኔ ፊት በፍራቻ ተውጧል። ፅናት ሌላኛውን የበፀሎትን ቡና አንስታ ለመስጠት በፀሎት ፊት ቆመች። ቡና የያዘውን እጇን ወደ በፀሎት ዘረጋችው በፀሎት ግን እጇን አልዘረጋችላትም። ፅናት በፀሎት ላይ ማየት የተሳነው ሰው ፊት ስታይ በእጇ የያዘችውን ቡና በቁሟ ለቀቀችው....

ፅናት በዛ ሰአት እራሷን አልነበችም ውስጧ ዝብርቅርቁ ወጥቶ ነበር። ደርቃ ቀረች በቆመችበት የያዘችውን  ትኩሱ ቡና  እግሯ ላይ ቢደፋም አልተሰማትም። በፀሎት ቡና ወደወደቀበት እጆቿን  በመዳበስ አይኖቿን  ወደ ጣሪያ ወረወረቻቸው። በፀሎት ለስለስ ባለ ድምፅ "ምንድነው ምን ተፈጠረ?" አለች። ፅናት አይሆንንንምም ብላ ጮኸች።

ያኔ ሊባኖስ በፍጥነት በሩን በርግዳ ገባች። ሁሉም ፅናትን ለማረጋጋት ቢሞክርም አልቻሉም ፅናት አንዴ ነቃ ብላ "አይ አይ ሊሆን አይችል" ትላለች ከዛም ፍዝዝ ብላ ትቆያየች። ሊባኖስ ፅናትን ደግፋ ፍራሽ ላይ ጋደም አደረገቻት። ፅናት ግን በጭራሽ ውስጧ አላረፈም ። መንቀጥቀጥ ጀመረች።  ሊባኖስ በጣም ደነገጠች አቶ ኪዳኔም እንደዛው በፀሎት ምን እንደተፉጠረ ብትጠይቅም ምላሽ አላገኘችም።  ከዛም ቀዝቀዝ ባለ ድምጿ "ፅናቴ ፅናቴ ደና ነሽ እህቴ"አለች። መልስ አልተሰጣትም ከዛም "ሊባኖስ እህቴ   ደና ነች?" አለች አሁንም ዝም ከዛም ጮክ ብላ መልሱልኝ ብላ ጮከች።

ሊባኖስ ፈጠን ብላ ወደ በፀሎት ቀርባ "ደና ናት አታስቢ እንዲ ሆነሽ ማየት ከብዷት ነው የሚወዱት ሰው በእዚህ መልኩ ተጎድቶ ማየት ያማል" አለቻት። በፀሎትም  የሊባኖስ ንግግር የገባት ትመስላለች "ልክ ነሽ"ብላ ኡፍፍፍ አለች።

ሊባኖስ ፅናትን ለማረጋጋት ወደ ፅናት ሄደች። ፅናት አሁንም አልተረጋጋችም ይህ ነገሯ ለቀናት ዘለቀባት ከዛም በሂደት እየለመደችው መጥታ እህቷን መንከባከብ እና ማገዝ ጀመረች።

በጊዜ ሂደት  በፀሎት ማየት ባለመቻልዋ ተስፍ ቆረጠች። ፅናት ግን ተስፍ እንዳትቆርጥ የሚቻላትን ሁሉ ታረጋለች ለእሷ ብላ ማየት መስማትም የማይችሉ ስዎችን ታሪክ አፈላልጋ ታነብላታለች ለምሳሌ ስለ ሄለን ኪለር። ሄለን ኪለር ለበፀሎት ብረታትን ለፅናት ደሞ ድልን ሰጥታቸዋለች። ፅናት ትምርቷን አላቋረጠችም ምክንያቱም ሊባኖስ ታግዛታለች። የፅናት የቀን ተቀን ድረጊቷ ሌሊት ተነስታ ለእሷ እና ለእህቷ ሊባኖስ ቤታቸው ካደረችም ለእሷ ቁርስ ሰረታ ቤትም አፅድታ ትምህረት ቤት ትሄዳለች ሄዳ 6:30 ትመጣለች። ከትምህርት ስትመለስ 30 ደቂቃ ያክል ተኝታ በድጋሚ ተነስታ ታጠናለች። አጥናታ ስጨረስ 9:30 ይሆናል።  ከዛም ማታ ማታ የምትሸጠውን ምግብ በሊባኖስ እርዳታ ትሰራለች። በራቸው ላይ በዳቦ የሚበሉ ቀለል ያሉ ምግቦችን እንሸጣለን ብለው እሷና ሊባኖስ ካርቶን ላይ ፅፈው ነው የለጠፉት። ፅናት የቤቱን ስራ ስትስራ ሊባኖስ እና በፀሎት ከ ሊባኖስ መኖሪያ ያመጣሉ ሊባኖስም የደረሰችበትን ታግዛታለች። አቶ ኪዳኔ በፀሎት ለህክምና የተጠየቀችውን ብር መክፍል ስላቃታቸው በሶስተኛው ወር ነበር ከነ ቤተሰቦቻቸው  ድራሻቸው የጠፋው።ገፍታሪው ልጅም ያን ቀን ነበር የተሰውረው። የሰፈሩ ሰው የቡና ቁርስ መሆናቸውም ቀጥሏል እና ደሞ ፅናት በክፍል ከፍ ባለች ቁጥር በውበቷ ያልተማረከ እና ያልጠየቃት እኩያ ወንድ የለም ውበቷ በጣም ሲጨምር ቤቷ ድረስ ዱረየውም ጨዋውም እየመጣ የአብረሽኝ ሁኚ ማመልከቻውን ያስገባል። በሌላ በኩልም ቆንጆ ቡዳ ነው ቡዳ ቆንጆ ነው እያሉ የተቀሩት የሰፈሩ ኑዋሪዎች ያበሽቋት ጀመር።

.
.
🥀..ክፍል 9 ቶሎ እዲለቀቅ አንብባቹ ስጨርሱ ላይክ ሼር አርጉ ..🥀
         
👍8939
♥️ ፅናት ♥️...!!!
           .
           .
           .
🥀..ክፍል 9..🥀
          .
          .
          .
#Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው .!!
.
.
አዘጋጅ እና አቅራቢ :-
#ከደራሲያን_አለም የቴሌግራም ቻናል✍️
.
.
ፅናት ሁሌም ይህ ነገር መስማት ሰለቻት ታለቅስ ነበር ገና ሳታድግ በቅጡ እንዲ መባልዋ ምቾት ነስቷታል በየ መንገዱ የሚስሟት አሮጊቶችም ጭምር ስለቿት። ከዛም ሊባኖስ አንድ ሀሳብ አመጣች ቤት መቀየር  በእዚህ ተስማምተው ሊባኖስ ቤት መፈለግ በጀመረች በሳምንቱ አገኘች። ይህን ዜና ለእነ ትግስት እንዲ ስትል ነገረቻቸው "ቤት አግኝቼላችዋለው ያው ሰፈሩ ከእዚህ የባሱ ሰዎች ነው ያሉበት ነው ግን ይሁን አለቻቸው ስትነግራቸው ፅናት ቡና እያፈላች ነበረ ከቡናው ተነስታ ፍራሹ ላይ የተቀመጠችውን ሊባኖስን እና ዌልቸር ላይ የተቀመጠችውን በፀሎትን ሳመቻቸው።

በነጋታው ሊባኖስ የነገረቻቸውን ሁሉ አድረገው ወደ አዲሱ ሰፈር ወደ አዲሱ ቤት ተቀላቀሉ ይህ ሲሆን ፅናት 10 ክፍል ደርሳ ነበር።

እነ ፅናት ያን ጊዜ ኑሮም በጣም ከበደባቸው ከቤታቸው ሽያጭ የተረፈውን አንድ በአንድ ለትግስት  መታከሚያ እና ለኪራይ ካደረጉት ወራት ተቆጠሩ እንኳን ብር የሰው ልጅም አካል አልቆ እና እረግፎ መንምኖ ያልቃልና እጃቸው ላይ ያለው ብር አንድ በአንድ ለቤት ኪራይ እና ለበፀሎት ህክምና ወጥቶ አለቀ። አሁን ከድሮ በበለጠ ህይወት ከበደች ፊቷንም አዞረች በይበልጥ እና ደሞ በእጥፉ ችግራቸው ልክ እንደተቦካ  እና ኩፍ እንደሚል ሊጥ ወደላይ ወጥቶ ተስፋቸው ደሞ ሊጡ ሲመለስ ያለው አይነት መመለስ በቀስታ እንደመተንፍስ በቀስታ እንደመቀነስ በቃ ኑሮም እንዳልቦካ ሊጥ እንደመቆምጠጥ ሆነ።
ታዲያ ይህንን ኑሮ መኖር ለማነው ቀላል ለትንሿ ፅናት ነው ወይስ የአይን ብረሀኗን እና የመራመድ ፀጋዋን ለተገፈፈችው በፀሎት እ እህ መልስ የለም። ፅናት ከትምህርቷ ስትመለስ እንፖቴቶ እና ፓስቲ በመስራት እና በመሽጥ ከዛም ብር በማጠራቀም ለሆዳቸው ተርፋለች። ሊባኖስ አትረዳቸው ነገር ግን እሷም እርጋፊ ሳንቲም የሊላት ደሀ ነች።

ፅናት መጀመሪያ ሰሞን ለአንድ ቀን የሊባኖስን ሰፈር አይታዋለች በመጀመሪያ ቀን ግን ሊባኖስ ፅናት እንድትገባ አልፈቀደችላትም። ሁሌም ቢሆን  የሊባኖስን ቃልን መቼም አትረሳም። ሊባኖስ ለፅናት ብረታት ሆናታለች።

ሊባኖስ  አሁን  የት እንዳለች ሳትናገር ድራሿ ጠፍቷል።ይህ ነገር ፅናት እና በፀሎትን ቢያሳስባቸውም መፍትሄ አላገኑም ፅናት ትኖራለች ብላ የምታስብበት ቦታ ሁሉ ፈለገቻት ነገር ግን ሁሉም ሊባኖስ ቋሚ መኖሪያ እንደሌላት እና ባገኘችበት እንደምታድር ከመንገር ውጪ ማንም ምንም አላለም። እንደውም ስለ ሊባኖስ ስትጠይቃቸው ፍረሀት እና ድንጋጤ ከፊታቸው ይነበባል።  ፅናት ለምን ስለ ሊባኖስ ሲነሳ እንዲህ እንደሚሆኑ ግራ ገባት።

ሊባኖስ ከጠፋች ወራት ተቆጥሯል በእነዚህ ወራት ውስጥ ግን  አንድ ስው  አግኝታ ነበር።  ሰውየው ሊባኖስን በደንምብ እንደሚያውቃት እና ሊባኖስ ማለት የመስቀል ወፍ እንደሆነች ማንም እሷን ፈልጎ ማግኘት እንደማይችል እና ተመልሳ ብትመጣ እንኳን ከእሷ  እንድትርቅ ሊባኖስን በደንብ እንደሚያውቃት እና መጀመሪያ ሰውን መላክ ሆና ቀርባ ከዛም በአይኗ ሀይል ደሞ ግባት ውስጥ ገብታ ሞትን የሚያስመኝ ስቃይ እንደምታሰቃይ ፤ ውሎዋ የመቃብር ቦታ ላይ እንደሆነ የሞቱ ሰዎችን እንደምትወድ በቁም ያለውን ሰውም ገድላ  ወደ እሪሳነት መቀየር ለእሷ በቁም ላለው ሰው ውለታ እንደሰራች እንደምትቆጥር ነገራት።  ፅናት አማተበች በጣምም ፈራች ሰውየው የሚነግራት ፊልም ይሁን እውነት ቀልድ ይሁን ውሸት ግራ ገብቷታል ግን ደሞ ጨንቋታል።

ሌላው ፅናትን ሰላም የነሳት ከድሮ ሰፈራቸው አንዲት ሴት መጥታለች ሴቲቱ የእነሱ ሰፈር ባለ ጫት ቤት ሰውዬ አያት ናት ድሮ ሰፈራቸው የሚያወሩትን  ሁሉ ለባለ ጫት ቤቱ ስትነግረው ጫት ቤቱ ለደንበኖቹ ደንበኞቹ ለሴተኛ አዳሪዎች እና ለሚስቶቻቸው ተናግረው ወሬውን ነዙት።

አንድ ቀን ፅናት በአንድ ጀንበር እራስዋን ጠንካራ ውስጧንም ጠንካራ አድርጋ ተነሳች። ጊዜው የ10ረኛ ክፍልን ፈተና ተፈትና በጥሩ ውጤት አልፋ ክረምት ላይ ነበር። ፅናት ለእራስዋ እሷን አበረታታ እህቷን ማበርታት እንጂ ማስነፍ እንደሊለባት ተረዳች። ከዛም የምትሸጣቸውን ምግቦች በብዛት እየሰራች ለቀን ሰራተኞች ለመሸጥ ወሰነች ለእህቷም አማክራት ተስማሙ።ከዛም ሄዳ የሄለን ኪለርን መፅሀፍ በቅናሽ ገዛች።

ከዛም እህቷን መጥታ እህቴ እኛ ጠንካሮች መሆን አለብን ከእኛም የባሰ አለ እኮ እየውልሽ ዛሬ ስለ ሄለን ኪለር  አነብልሻለው በቃሌ ከነገርኩሽ ይበልጥ እንድታውቂው ነው። በፀሎት  የፅናት በአንድ ጀንበር መቀየር አስገርሟታል። እሺ ፅናቴ የእኔ ፅናት አለቻት። ፅናት የበፀሎትን እጆች እየዳበሰች። እና ደሞ አሁን እረፍት  ስለሆንኩኝ ሁሌም ቤተክረስቲያን እንሄዳለን ልክ እንደ ድሮዋችን አባባና እማማንም እንጎበኛቸዋለን አሁን ምግብ የመሽጫ ሰአቴ ሳይደረስ ስለ ጠንካራዋ ሄለን ኪለር  አስታውሺ  እህቴ ይህቺ ሴት ማየትም መስማትም መናገርም ጭራሽ የማትችል ሴት ናት ግን ደሞ ጠንካራ ናት። አየሽ እህቴ ያለንን  እናመስግን የሚመጣውን ፈጣሪ ያውቃል ሊላው ደሞ መፅሀፍ ቅዱስም አነብልሻለው አይምሮዋችን ከጠነከረ ሊላው ትርፍ ነው።
  
ያቺ የጫት ቤቱ አያት ጠንቋይ ናቸው ብላ ለሰፈሩ ተናግራ ከዛም ይሄው የማይሉት ነገር የለም እህቴ ግን እንጠንክር አለቻት።በፀሎት ለፅናትን ማደግን በአንደበቷ  አስተውላ እጅግ ተደሰተች እና ነይልኝ ብላ እጇን ዘረጋችላት ፅናትም ብድግ ብላ ልታቅፋት ወደፊቷ ተጠጋች  ነገር ግን ከፊቷ የሚታየው ድንግዝግዝ የሚል ነገር ነው ሰውነቷ እንደመዛል አረጋት ፅናት እራስዋን ሳተች። በፀሎት ደንገጠች ከዊልቸሩ ልትወርድ ስትሞክር አብራት ወደቀች።
   
ማን ያንሳቸው? መራመድ የማትችለው በፀሎት ወይስ እራስዋን ስታ የወደቀችው ፅናት መንቀሳቀስ የማትችለውን በፀሎት  ማንም ማንንም ማንሳት አለቻለም። ጮሀውም  ጎረቤት መጥራት አልቻሉም ምክያቱም ፅናት ራስዋን ስታለች በፀሎትም ስትወድቅ ጭንቅላቷን የመታት ዘነዘና ጭንቅላቷን አድምቷታል በፀሎት እንደ ፅናት ራሷን ሳተች። ማን ይድረስላቸው ታዲያ..
.
.
🥀..ክፍል 10 ከ 100 ላይክ ቡሀላ ይለቀቃል..♥️

   🥀 ..ቶሎ እንዲለቀቅ ላይክ ሼር አርጉ ..🥀
         
       
👍8328😱11
90 ዲግሪ የቀኝ አንግል መቆንጠጫ
(90 Degree Right Angle Clamp)

“ስራዎት ያቅልሉ " ሳሎዳ ትሬዲንግ

☎️....    ይደውሉ ይዘዙን...  ☎️
@Salodatrading
Contact us:-📞  +251914855557

https://vm.tiktok.com/ZMB8pYAoL/

💬 ማንኛዉም የዕቃ ዋጋ ለማወቅ
@Salodatrading @Salodatrading
👍1🤩1
♥️ ፅናት ♥️...!!!
           .
           .
           .
🥀..ክፍል 10..🥀
          .
          .
          .
#Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው .!!
.
.

.
ማን ያንሳቸው  በወደቁበት ቦታ ሰአታት ተቆጠሩ ከወደቁ ከ 3 ሰአት በኋላ
ፅናት ነቃች። አይኗን ጨፈገጋት እንደምንም ተነሳች ደረቷ ላይ የበፀሎት እጅ አለ። ድንጋጤው እብደትን ደምሮባት ባነነች። በፀሎት ወድቃለች ፅናት ብድግ አለች እጇን በአፏ ጭና ቀረች። የምታደረገው ሁሉ ግራ ገባት ብቻ ግን አይኖቿ እንባ አቅረርዋል። ተንበረከከች በፀሎትን ልታነሳት ከ ጭንቅላቷ ብድግ ልታረጋት ስትሞክር የበፀሎት  የጭንቅላቷ ደም እጇን ነካት ። ፅናት ፈራች አታነሳት ነገር አትችላትም ፅናት እንደምንም ጥራ እና ተጣጥራ  ጭንቅላቷ ላይ ባስረችው ሻሽ የፅናትን ጭንቅላት አሰረችላት።ብትጮክም የሚደረስላት እንደሊለ  አውቃ የበፀሎትን መንቃት  መጠባበቅ ጀመረች። እጇን አንጠራርታ በጆግ ያለውን ውሀ ካመጣሽ በኋላ ለበፀሎት አስራላት ከጫፉ በተረፈው  ሻሽ የጆጉን ውሀ አድረጋ ጭንቅላቷ ላይ እያደረገች ማልቀስ ጀመረች።ፅናት  በፀሎትን አቀረቅራ አየቻት የፅናት የእንባ ዘለላ የበፀሎት የአይን ቆብ ላይ አረፈ በድጋሜ ጠብ አለ። የበፀሎት የእጆቿ ጣቶች መንቀሳቀስ ጀመሩ።ፅናት ግን አላስሰተዋለችም ፅናት ከወገቧ ታጥፋ በፀሎትን አቅፋት እያለቀሰች ነው። ፅናት የበፀሎት ትንፍሽ ሙሉ በሙሉ አንገቷ ላይ እያረፈ ነው። ትግስት ሹክሹክታ በሚመስል ድምፅ እና ደሞ በደከመ ድምፅ  ፅናቴ አለቻች። ፅናት እህቴ ብላ ከ አንገቷ ቀና ልትል ስትል በፀሎት የቀኝ እጇን ፅናት አንገት ላይ አሳረፋ ግጥም አድረጋ አቀፈቻት። ፅናት "እህቴ በፀሎቴ ደና ነሽልኝ" አለቻት በፀሎትም  ደና ነኝ አለቻት።
ረዥም ሰአት ተቃቅፈው ቆዩ። ከዛም በፀሎት ስትረጋጋ ፅናት ሄዳ ፍራሻቸውን እየጎተተች በፀሎት ያለችበት ጋር አደረሰችውና "በፀሎቴ ፍራሹን አምጥቼልሻለው ቆይ ትንሽ ላግዝሽና ፍራሹ ላይ ውጪ" አለቻት። በፀሎትም "እሺ ፅናቴ" አለችና ተንጠራርታ ፍራሹ ላይ ሆነች። ፅናት አመቻችታ አስተኛቻት።ፅናት "አየሽ እህቴ ብንሞትም ማንም አይደረስልንም ይህ ሁሉ የአባታችን ጥፋት ነው። እሱ ክፉ ነው በጣም" አለችና አለቀሰች  ስቅስቅ እሪሪሪሪሪ አለችና በፀሎት ደረት ላይ ተደግፋ ማልቀስ ጀመረች።በፀሎትም ድምፅ ባታወጣም  ስቅስቅ ብላ ነው ያለቀሰችው። በፀሎት ክንዷን ዘረግታ "ነይ ክንዴ ላይ ደገፍ በይ" አለችና ፅናትን አስደገፈቻት። ፅናት ሳታስበው እንቅልፍ ጣላት። ለጥጥጥ አለች። በፀሎትም በተመሳሳይ። ግን ደም መፈሰሱን ሳያቆርጥ ትራሱን ማርጠብ ጀምሯል በፀሎት አቅም እያጣች ነው። አልቻለችም ደክማለች በጣም ደክማለች።ፅናትም ተኝታለች ፅናት በእንቅልፍ በፀሎት ደሞ በሞት እና በህይወት መካከል ሆነው ደቂቃዎች ነጎዱ ሄደው ሰአታት ተተኩ በፀሎት የጣር ድምፅ አወጣች "ፅናቴቴቴቴ እህቴቴቴቴቴ ህይወቴቴቴቴቴቴ ልዩዬዬዬ" ፅናት አልሰማችም። ተኝታለች በፅናትም አቅሟ ተሟጦ እራስዋን ስታለች። ከ30 ደቂቃ በኋላ ፅናት ውሀ ጠምቷት ተነሳች። የተፈጥሮ ነገር ግን አይገርምም? ውስጣችን ያለው ስሜት ሰአቱን ጠብቆ ከሞት ታናሽ ወንድም ሲያነቃን እና ሲያባንነን ሌላ ሰው ግን ጭንቅ ላይ ሲሆን አለመንቃታችን።
ፅናት አይኑዋን ስትገልጥ ያየችውን ማመን አቃታት ህልምም መሰላት። የቤታቸው አነስተኛ ዱካ ላይ ሊባኖስ ተቀምጣ ነበር። ተፈናጥራ ተነሳች አይኖቿን  በእጆቿ አሻሽታ በድጋሜ ለማየት ሞከረች እውነት ነው ሊባኖስን በአይኗ እንጂ በምናቧ አላየቻትም። ልትጠጋት ብላ ፈራች ግን ደሞ ውጧ እቀፊያት እቀፊያት ይላታል የእዛ ሊባኖስን አውቃታለው ባይ ሰው ንግግርም ያቃጭልባታል።
ግን ሊባኖስ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ከልቧ ላትወጣ በፅናት ልብ ውስጥ ተቀርፃለች።
      
ከፍራሿ ብድግ ብላ ፈገግ ብላ ከምታያት ሊባኖስ ጋር ተጠምጥማ እንባዋ ይፈስ ጀመረ። የበፀሎትም ደም እየፈሰሰ ነው። ፅናት በፀሎትን ለመቀስቀስ ወደ እሷ ተጠጋች ፈገግ እያለች። የበፀሎትን እጆች ያዘቻቸው።"እህቴ በፀሎቴ  ማን እንደመጣ ብታይ??"አለች በፀሎት  ግን በተራዋ ፅናትን አልስማቻትም ፅናት አሁንም ፈገግ ብላ በፂ እናቴቴቴ አልስማሽኝም ሊባኖስ መጥታለች መልስ የለም።

ፅናት ግራ ገባት የበፀሎትን እጅ ብድግ አደረገችው ዝሏል የፈጣሪ ያለ ፅናት ክው አለች። እጆቿን ለቀቀቻት እጆቿ ተልፈስፈሰው ውድቅቅ አሉ። ሊባኖስ ፈጠን ብላ ወደ እነሱ ተጠጋች።

ሊባኖስ የበፀሎትን ጉንጭ እና ጉንጭ  ይዛ ከግራ ወደ ቀኝ ከቀኝ ወደ ግራ አዘዋወረችው ፅናት እና ሊባኖስ ተያዩ ደነገጡም።ፅናት በፀሎትን ከጭንቅላቷ ቀና ለማድረግ እጆቿን  ከትራሱ እና ከበፀሎት ጭንቅላት ስር ሰርስራ አስገባቻቸው  እጆቿን  እረጠበባት ደነገጠች። ፈጠን ብላ አወጣቻቸው  እጆቿ በደም ተለውሰዋል።ፅናት ምን እየተፈጠረ እንደሆነ  ግራ ገባት ሊባኖስ የፅናትን እጆች  ስታየው ጣረ ሞት ያየችም ትመስል ነበር። "ምንድነው ሚጢጢዋ" አለቻት የድንጋጤ ፊት እያሳየች። ፅናትም " እኔ ለእራሱ ምንም አላውቅም"። አለችና "ቆይ ቆይ" ብላ የተፈጠረውን ነገረቻት። ሊባኖስ በፍጥነት  ስልኳን  አንስታ ደወለች።" ሄሎ የት ነክ አሁኑኑ ዛሬ ያደረስከኝ ቤት ና" ስልኩን ዘጋችው።
 
ፅናት እየተንቀጠቀጠች ነው። በሲኮንድ ፍጥነት  ሰውየው ደርሻለው ብሎ ሊባኖስ ጋር ደወለ። ከዛም ተቀበለችውና በፀሎትን አብረዉት ከመጡት ግብራበሮቹ ጋር መጥተው  ከ እነ ሊባኖስ እና ፅናት ጋር ጭኗቸው  አንፖላንሱን እያስቦረቀ  ነዳው።"ደረሰናል" አለ ሹፌሩ  ፅናት  ግራ ገባት።  ምንም አይነት የህክምና ጣቢያ ስላላየች። ጋቢና የተቀመጠችው ፅናት ወደ ኋላ ዞራ እህቷን ማየትም አልቻለችም። ፅናት ፈራች "እንውረድ" አለና ሹፌሩ ወረደ ከዛም ሲወርዱ ፅናት ፈጠን ብላ ወደ ኋላኛው የህሙማን መጫኛ ቦታ የመኪናውን ሻተር ከፍታ ስታይ ከቦታው ላይ ሊባኖስም ሆነ እህቷ በፀሎት እንዲሁም እነዛ ሰዎች  በቦታው የሉም ።

ፅናት ያ ሊባኖስን በደንብ አውቃታለው ያለውን ሰው ንግግር አንድ በአንድ አስታወሰች። በሀዘን እና በድንጋጤ ጊዜ ጭንቅላቷ ፈፅሞ መቋቋም የማይችለው ፅናት ልክ እንድ ሁል ጊዜው እራዋን ልትስት ሲያንገዳግዳት ሹፌሩ ተሯሩጦ ደገፋት ከዛ ፅናት  የሹፌሩ ክንድ ላይ ወደቀች።
.
.
🥀..ክፍል 11 ከ 100 ላይክ ቡሀላ ይለቀቃል..

https://vm.tiktok.com/ZMBLNfsKq/
🥀 ..ቶሎ እንዲለቀቅ ላይክ ሼር አርጉ ..🥀
         
         
👍5912🙏1
Forwarded from Hibtu store
CK/ calvin klein brand boxer
Price - 450
Telegram- @hibtuuu
Phone- 0913285784
👍1
♥️ ፅናት ♥️...!!!
           .
           .
           .
🥀..ክፍል 11..🥀
          .
          .
          .
#Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው .!!
.


ሹፌሩ በጣም ተደናግጦ የሚያረገው ጠፋው መንደሩን ዞር ዞር ብሎ አየው በሰአቱ ሰው አደለም ነብስ ያለው ፍጥረትም አልታየውም ከዛም ፅናትን በጥድፊያ ያ በጣም የሚስፈራት ድባብን የተላበሰጊቢ ተሸክሞ ይዟት ገባ። ሊባኖስ ከእሩቅ አይታው በፍጥነት ሮጣ ወደ ሹፌሩ በመምጣት ተባብረው አንድ አነስ ያለች የጭቃ ቤት ውስጥ አስገቧት ቤቷ ስትታይ ልትወድቅ ያሰፈሰፈች ትመስላለች በፍጥነት አንድ የሽቦ አልጋ ላይ አስተኑዋት።

በክፍሉ ውስጥ ፅናት ከተኛችበት ትይዩ ካለው ግድግዳ አጠገብ አንድ ተጨማሪ የሽቦ አልጋ ይታያል። በእዚህ አልጋ ላይም በፀሎትን በደረቷ አስተኝተው  የጭንቅላቷን ደም ለማስቆም እየጣሩ ያሉ አንድ የእድሜ ባለ ፀጋ ይታያሉ። እኚህ ሰው ፀጉራቸው ሙሉ ሽበት ሲሆን ልክ እንደ ባህታዊ ፀጉር ተቆጣጥሮ ወገባቸው ላይ የተንዠረገገ ነው ። ጥቁረ መነፀር እና የመነቸከ ነጭ ባርኒጣ አርገዋል።  ልብሳቸውም እንደነገሩ ነው ልክ እንደ ኮፍያቸው ነጭ ሆኖ ነገረ ግን የመነቸከ ሰፋፊ ሹራብ እና ሱሪ አድረገዋል። በጣም አጭረ ቁመት እና ቀይ መልክን ተላብሰዋል።

የትግስትን የጭንቅላት ደምን በያዙት መጣጭ ጨርቅ ላይ የሆነ ፈሳሽ ውሀ መሰል ነገረ እያረጉ ካፀዱ በኋላ ደሙ ሲቆም አንድ አረጓዴ የተጨቀጨቀ ነገረ ከብልቃጥ አውጥተው የበፀሎት የተጎዳ ጭንቅት ላይ በዳበሳ አርገው ቀቡትና በፋሻ ጠቀለሉት። ከዛም ከእሳቸው የማይጠበቅ ጉልበት እና ቅልጥፋና ተጠቅመው በፀሎትን በእፍታ ፍጥነት በጀረባዋ አስተኙዋት።እኚህ ሰው አንድ ሰው እያከሙ ሳሉ የሚያወራቸን ሰው አጥብቀው የሚጠሉ ናቸው።

ልክ በፀሎትን አክመው እንደጨረሱ ሊባኖስ "አባ በሬሳ የእሷ እህትም ተጎድታለች እራስዋን ስታ ነው" አለች። ሊባኖስ ፅናት ፅናትን እያየች ምን ሆና? ለምን እንዲ ሆነች? ብለውም ሳይጠይቁ ወዲያው ከዛች ጭቃ ቤት ወጡ።ሊባኖስ ፈገግ አለች። አባ በሬሳም አፍታ ሳይቆዩ የፈላ ውሀ እየተግለበለበ ይዘው መጡ።  የፈላ ውሀውን ከመሬቱ ላይ ካስቀመጡ በኋላ በኪሳቸው የያዙትን በፌስታል የተቋጠረ ቢጫ ዱቄት ሊያረጉ እየፈቱ ሳለ ሊባኖስ ክፍሉን ለቃ ወጣች እና በሩን ዘጋችው።

አባ በሬሳ ስራቸውን ቀጠሉ። የፈላው ውሀ ላይ ቢጫ ዱቄቱን ሲጨምሩት ውሀው ይበልጥ መፍላት ጀመረ።ከዛም ቤቱ በእንፋሎት መታጠን ሲጀምረ እሳቸውም ያቺን የጭቃ ቤት ለቀው ወጡ። ፅናት እና በፀሎትም በጭቃ ቤቷ ውስጥ የሚሸታቸው ጠረን ሰአታት አስቆጥሮ  በእኩል ሰአት አስነቃቸው። ሲነቁ ደና ሆነው ነበረ። ፅናት ብድግ ብላ ወደ በፀሎት ሄደች።በፀሎት ግራ ገብቷት "ፅናቴ የት ነው ያስተኛሽኝ ፍራሻችን ዛሬ ደሞ ትንሽ ምቾት አለው። ደሞ ምንድነው የሚሸተኝ" አለቻት። ፅናት ግራ ተጋባች። በአይኑዋ የቤቱን ዙሪያ ቃኘችው። የቆመችበት መሬት ያለችበት ቤት የት እንደሆነ አታውቅም ፈጠን ብላ ወደ በሩ ሄደች በሩ ከውጪ ተቀርቅሯል። ግራ ገባት። ወደ እህቷ ሄዳ። እጇን ያዘቻት ፍርሀት ሰውነቷን በሀያሉ ወረራት። ፅናት ቤቱ ውስጥ ከ ሁለቱ አልጋዎች እና ተንጋላ ከተኛችው በፀሎት እንዲሁም ከእራሷ ውጪ ምንም ሊታያት አልቻለም ።ፈራች በፍጥነት በፀሎት የተኛችበት አልጋ ላይ ወጥታ  አቀፈቻት። አሁን በፀሎት በተራዋ ግራ ገባት። ልክ የፅናት ግራ መጋባት ወደ ፍራቻ ሲዞረ።በፀሎት ፅናትን በዳበሳ እየነካካቻት "ፅናቴ ምነው ዝም አልሽ" አለቻት። ፅናት በፀሎትን በደንብ አቅፋ እያረጋጋቻት "በፀሎቴ ፈራው" አለቻት በፀሎት በአሁንም ግራ ገብቷት "እንዴ ለምን አለቻት" ፅናት አሁን በፀሎትን ይበልጥ እያቀፈቻት። "ቤታችን አደለንም" ስትላት።  በፀሎት ፈገግ ግርም እያለች "እና የት ነን" ስትላት። አላውቅም ብላ ሊባኖስ ቤታቸው ከመጣች ጀምሮ ያለውን ሁሉ እስከምታስታውሰው እራሷን የሳተችበት ቅፅበት ነገረቻት አሁን በፀሎትም በጣም ፈራች። እርብሽብሽ አለች።

ተቃቅፈው በጭንቀት ሳሉ ያሉበት ክፍል በሩ ጉዋ ብሎ ተከፈተ ፅናት ብርግግ ብላ ተነሳችና ቁጭ አለች። በፀሎት የፅናትን እጅ አጥብቃ ያዘቻት።ፅናት አይኖቿን  ወደ በሩ  ወርውራ አየች። አባ በሬሳ ነበሩ ወደ እነ ፅናት ጠጋ  ማለት ሲጀምሩ የፅናት ልብ ምት ፈጠነ።  ጠጋ አሉ ፅናት ፈራች።  አባ በሬሳ "ተነሽ" አሉዋት ፅናትን።ፅናት በድንጋጤ በርግጋ ከበፀሎት እጇን አላቃ ከአልጋው ወርዳ ቀጥ ብላ ቆመች።

አባ በሬሳ ወደ በፀሎት  በመሄድ የበፀሎትን ሁለት እጆች በመያዝ "ተነሽ" አሉዋት ቁጣ በተሞላበት ድምፀት  በፀሎት ብድግ አለች። ፅናት ግራ ገባት ከሰአታት በፊት ከጭንቅላቷ ደም በሀያሉ እየፈሰሳት እራሷን እማታውቀው እህቷ ምንም እንዳልተፈጠረ ብድግ ብላ መነሳቷ። ፅናት የሚሆነውን በአትኩሮት ማየት ጀመረች። አባ በሬሳ በፀሎትን  አልጋው ላይ ቁጭ ካረጉዋት በኋላ በሁለቱ እጃቸው ጉንጭ እና ጉንጯን ይዘው በሀይል ካወዛወዙዋት በኋላ ልቅቅ ሲያረጉዋት በፀሎት ወደ ኋላ ወደቀች። ፅናት ጩኸቷን አቀለጠችው።

የሚመጣ ሰው ግን አልነበረም አባ በሬሳ "ዝም ብለሽ ተቀመጭ" አሉዋት። ፅናት መሬቱ ላይ ተቀምጣ የሚሆነውን ማየት ጀመረች። ከጥቂት ቆይታዎች በኋላ በፀሎት  "ፅናቴ እህቴ" ስትላት ሰማች። ፅናት ፈጠን ብላ ወደ እህቷ አመራች ጋሽ በሬሳም በግርምት በተራቸው ቆመው ሁኔታውን ማየት ጀመሩ። በፀሎት  ያለ ማንም ድጋፍ ተነስታ ቁጭ አለች። ፅናት ህልም ላይ ያለችም መሰላት ምን እየተፈጠረ እንደሆነ ባይገባትም እህቷ ስለተሻላት ግን ተደስታለች። ተቃቅፈው አለቀሱ ረዥም ደቂቃዎች አነቡ።

ጋሸ በሬሳ እርጅና ባንቀጠቀጠው ድምፃቸው "በቃ ተላቀቁ" አሉና አላቀቋቸው። ጋሽ በሬሳ በፀሎት  ጭንቅላት ላይ ያለውን ፋሻ አነሱላት። ከዛ በቃ "ከእዚህ በኋላ ህመም የለም ህክምናሽን ጨርሰሻል። አሁን ስለመሸ ተኙ ነገ ጠዋት ቤታቹ ትሄዳለቹ። ልጅ ሊባኖስ የምትመገቡትን ይዛላቹ ትመጣለች" አሉና ወደ ፅናት ዞር ብለው ልጄ እህትሽን  እንድትንቀሳቀስ እስጃት ሲሉ ፅናት "ግን እኮ እህቴ መሄድ አትችልም በዊልቸረ ነው የምትንቀሳቀሰው" አለች ። አባ በሬሳ አውቃለው አውቃለው ልጅ ሊባኖስ ነግራኛለች ግን ሰው በእግሩ ብቻ ሳይሆን በአይምሮም መጓዝ እና መንቀሳቀስ ይችላል አዝናኛት በወሬ ለማት ነው" ብለው ወጡ። ፅናት በፍጥነት በሩን ከውስጥ ሸንጉራ በፀሎት ጋር በመጠጋት የበፀሎትን ፓንክ ቁርጥ ፀጉር እና ጭንቅላቷን ዳበሰችው ምንም የለም ለምልክትም የተቀመጠ አንዳች ጠባሳም የለም።  ፅናት ግራ ገባት።  "በፀሎቴ ጭንቅላትሽ ላይ ምንም አይነት የቁስል ወይም የጠባሳ ምልክት የለም እሺ ጠባሳው ቆይቶ ነው ሚመጣው ግን ቁስሉስ" አለች።በፀሎትም "እንዴት ሆኖ ቆይ የት ነን?" ስትላት።"አላውቅም ሽማግሌው እኮ እህትሽ እንድትንቀሳቀስ እርጃት ሲሉኝ መቼም በአንድ ጊዜ እንዲ ጤነኛ ካረጉሽ መራመድም እንድትችይ ያረጉሽ መስሎኝ በጣም ልቤ በደስታ እየመታ ነበር"አለች እንዲ እያወሩ በሩ ተንኳኳ ፅናት ማነው አለች። መልስ የለም ግን የሆነ የሚያስጨንቅ እንጉረጉሮ ይሰማታል ሁለቱም ፍርሀት ወረራቸው።
.
.
🥀..ክፍል 12 ከ 100 ላይክ ቡሀላ ይለቀቃል..

.
🥀 ..ቶሎ እንዲለቀቅ ላይክ ሼር አርጉ ..🥀
         
👍12322🤬1
♥️ ፅናት ♥️...!!!
           .
           .
           .
🥀..ክፍል 12..🥀
          .
          .
          .

ፅናት ወደ በፀሎት ዞራ "ወይኔ ምን ጉድ ነው ምን ይሻናላን" አለች። በፀሎት ፀጥ አለች። ፅናት ወደ በሩ ተጠግታ አንድ ቀዳዳ አግኝታ አጮለቀች ግቢው ሙሉ በመብራት ተጥለቅልቆል ከበሩ እራቅ ብላ የምታንኳኳ ሴት አለች። ፅናት ይህቺን ሴት ከወገቧ በታች ብቻ ነው ማየት የቻለችው። በድጋሜ አንኳኳች ፅናት ደርቃ ቀረች። ለምን ፈራቻት? አታውቅም።ከዛም ወደኋላ አፈገፈገች ከቆይታዎች ቡኋላ ያ የሚያስጨንቅ ድምፅ ጠፋ ፅናት በድጋሚ እየተርበተበተች ወደ በሩ ማጮለቂያ አጎንብሳ አይኗን ወረወረች።አሁን የግቢው መብራትም ሆነ ማንም ሰው ሊታያት አልቻለም። የሚያስጨንቀው ድምፅ ግን አሁንም ይሰማ ነበር።
       
በፀሎት ስቅቅ ባለ ድምፅ "ፅናቴ ድምፁ ከየት ነው" አለቻች። ፅናት "አላውቅም፤ እኔ ምንም አላውቅም፤ እማውቀው እንደፈራሁ ብቻ ነው" አለችና በፀሎት ያለችበት አልጋ ላይ ወጥታ ቁጥጥ ብላ ቁጭ አለች። የበፀሎት እጆች እየተንቀጠቀጡ  ነው። ይህንን ያስተዋለችው ፅናት በቶሎ የበፀሎትን እጅ ጭብጥ አርጋ ያዘችው። ከዛም "በፀሎቴ እንፀልይ?" አለቻት። ከተቀመጠችበት ሳትነሳ እዛው ባለችበት ለመመቻቸት እየሞከረች። በፀሎትም "እሺ እንፀልይ አዎ መፀለይ አለብን ህልም ቢሆንም እንኳን እንዲያነቃን አምላካችንን እንማፀን  አለች።

ፅናት እና በፀሎት እጆቻቸውን ሳያላቅቁ ሁለቱም በእየፊናቸው ለፈጣሪያቸው ምልጃቸውን ላኩ ከልባቸው ነበር ፍራቻ በወረሰው የውስጥ ነውጥ ውስጥ በጭንቀት እና በእምነት ውስጥ ሁለቱም ከፈጣሪያቸው ጋር በሀሳብ ተገናኝተው እየፀለየዩ ነው።በተመስጦ በመሀል የበሩ መንኳኳት ከተመስጦ ፀሎታቸው አባነናቸው። ግን አሁንም እራሳቸውን ሰብስበው ፀሎታቸውን ጨረሱ።

በሩ መንኳኳቱን አላቋረጠም። ከዛም ሁለቱም በጋራ እና  በደከመ ድምፅ ልክ እንደተመካከረ ሰው "ማነው?" አሉ።" እኔ ነኝ ክፈቱ ምንድነው ተኝታቹ ነው እንዴ ደሞ ከሆነስ እራት  ሳትበሉ እንዴት ትተኛላቹ። በይ ክፈችልኝ ሚጢጢዋ" አለች ሊባኖስ ነበረች። ፅናት ተስፈንጥራ ተነስታ ምንም ድምፅ ሳታጣ ወደ በሩ ሄደች።  ከዛም በሩን ከፈተችው ሊባኖስ በመቋጠሪያ ሰሀን እራት ይዛ ሰሀኑን በጥቁር ዳንቴል ሸፍናው ነበር።
    
ፅናት እንድትገባ ወዲያው ከበሩ ገለል ብላ ቆመች ልትገባ ስትል በፍጥነት ተጠምጥማባት ማልቀስ ጀመረች። ሊባኖስም አቀፈቻት እና "ቆይ  ምን ተፈጠረ?" አለች። ፅናትም ሳግ በተደመረ  ድምጿ "እኔ ለእራሱ ምንም አላውቅም በጣም ጨንቆኛል ሊቦ እባክሽ ይህ ቤት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ምንድናቸው። ያ ያ ሰውዬ መተው ከሞት እና ከህይወት መካከል ያለችዋን እህቴን በሰአታት ውስጥ ወደ ጤንነቷ መለስዋት።

ሰለተሻላት እና ደና ስለሆነችልኝ ደስ ቢለኝም ግን የሰውየው ሁኔታ ያስፈራል። ከዛ ከዛ ከዛ ደሞ ምን እንደተፈጠረ ታውቂያለሽ ከጥቂት ቆይታዎች በፊት እዚህ በር ላይ ሰው ነበር ተጠጋው እና ወደ በሩ አጮለኩኝ  1ሴት ነበርች ይህቺ ሴት ደሞ አስጨናቂ እና ሞትን የሚጠራ የሚመስል ድምፅ እያወጣች ነበር።

ከዛ በድጋሜ  ቆይቼ ድምፁ ሲጠፋ ወጥቼ ሳይ ምንም ማንም የለም ግን ያ ድምፅ ነበር። ድምፁ በሩን ስዘጋው አለ በሩን ስከፍተው የለም "። አለችና ፅናት እንባዋን አዘራችው። ሊባኖስ ምንም ነገር ልትነግራት የምትፈልግ አትመስልም "በቃ አትጨቁ ነገ ወደ ቤታቹ ትመለሳላቹ በሉ ይህንን ብሉ አለችና  መሬቱ ላይ ቁጥጥ ብላ ተቀምጣ የያዘችውን ሰሀን ፈታችው  ከላይ ያለውን እንጀራ አንስታ የሰሀኑ እፊያ ላይ አረገችው። ፅናት "ምንድነው?"አለቻት። ቅፍፍ እያለች።

ሊባኖስም "ነጩ  እልበት ነው አረጓዴው ደሞ ሳማ ወጥ"አለቻት። ፅናት በህይወቷ አንዴም ነጭና አርጓዴ ሽሮ ወጥ መሳይ ምግብ አይታ ስለማታውቅ ሌላ አለም ውስጥ ያለች መሰላት። ምግብን ከበላች እምትሞት መሰላት።  ያ ስለ ሊባኖስ መጥፎ ነገር ያላት ሰውዬ አስታወሰች ።ቃል  በቃል የሰውየው ድምፅ ጆሮዋ ላይ አቃጨለባት ፅናት መፍራት ጀመረ።" ሊባኖስ ምን አይነት ሰው ናት?" አለች። ግን መልስ የሚሰጣት የለም።  ፅናት በጣም ፈርታለች።

በፀሎት ግራ በመጋባት "ምንድነው?"አለች። ሊባኖስም "ሳማ ወጥ እና እልበት" አለቻት። " ውይ እሱን ነገር ድሮ ቀምሼው ነበር። በጣም ነው ምወደው" ስትል በፀሎት ፈገግ ብላ 1 ነገር ትዝ ያላት ትመስላለች። " ሳማ ወጥ ግን አላውቅም" አለች ፅናት ወደ በፀሎት ዞራ እያየቻት "እህቴ አለቻት"።" ወዬ ፅናቴ" አለች በፀሎት።" ቆይ የት ነው የቀመሽው?" ስትላት።" ድሮ እማማ ሳይሞቱ በፊት አንቺ ትምህርት ቤት ሆነሽ ሰርተው በልተን ነበር። ግን በጣም ስለወደድኩት እማማ ላንቺ ብለው ያስቀመጡትን ቀስ እያልኩ ሳላስበው ጨረስኩት።ከዛ ለእማማ እንዳይነግሩሽ ለምኛቸው እሺ አሉ"ብላ ሳቀች። ፅናትም "ሆሆ ብላ ሳቀች" ሊባኖስም ከእነሱ ጋር ተደምራ ቤቱን የሳቅ ድግስ አስመሰሉት።
      
ከዛም በጋራ እራታቸውን በልተው ሊባኖስ ልትሄድ ስትል ፅናት ፍረሀቷ ጀመራት። "ሊቦ አትሂጂ ከእኛ ጋር እደሪ እባክሽ" አለቻት ሊባኖስም "እንዴ ፅናቴ ለምን?" አለቻት።  ትግስትም "እሺ በይ እባክሽ በጭንቀት እና በፍርሀት ከመሞታችን በፊት ስትላት እሺ ጥሩ በሉ እንተኛ እኔ እንቅልፌ በጣም መጥቷል አለች።  ፅናትም ፈገግ ብላ "እሺ እኔና አንቺ አንዱ አልጋ ላይ መተኛት እንችላለን አለቻት።ሊቦኖስም "እሺ ጥሩ የኔ ሚጢጢ" አለችና ፅናት ተኝታበት የነበረበት አልጋ ላይ ተኛች።

ፅናት ሁሌም ሊባኖስ ሩቅ ስትሆን ፈርታት አጠገብዋ ስትሆን ለምን መላክ እንደምትመስላት አይገባትም።

ፅናትም ወደ በፀሎት ሄዳ በፀሎትን አልጋ ልብሷን አልብሳት  አልጋ ላይ ወጣች። በድጋሜ ከ አልጋው በመነሳት በሩን ዘጋችው ከዛም ሊባኖስን ስላሉበት ቤት ኑዋሬዎች እድትነግራት መጨነቅ ጀመረች። ሊባኖስ ግን ምንም ነገር ልትነግራት ፍቃደኛ አደለችም። "የሰማሽው እንጉርጉሮም በምናብሽ የፈጠርሽው እንጂ በጭራሽ የእውነት አደለም ወዳላችሁበት ቤትም ማንም አልመጣም" አለቻት። ፅናት "እሺ እኔስ በምናቤ ፈጥሬው ነው ይባል ግን እህቴ በፀሎቴም ሰምታለች" ስትላት ሊባኖስ እርብሽብሽ ብላ ፅናትን ተቆጥታ እንድትተኛ ነገረቻት። በፀሎት "ምንድነው እምትንሾካሾኩት?" ስትል ፅናት አይ ምንም በቃ ተኙ እንተኛ አለች። በድጋሜ ያላስቻላት ፅናት ብዙ ከራስዋ ጋር ከተከራከረች በኋላ ወደ ሊባኖስ ጆሮ ጠጋ ብላ "ውሸት ውሸት ነው ሴቲቱንም አይቻታለው አዎ" አለች። ሊባኖስም "እንዲህ አይነት ሴት እዚህ ጊቢ እንደሊለች ደጋግሜ ነገረኩሽ ተኚ ስትላት ፅናት መከራከሩ ቢሰለቻት ፀጥ ብላ ጣራ ጣራውን ማየት ጀመረች።

ሁለት ሀሳብ ያዛት ሊባኖስ ከእነ እህቴ አንድ ነገር ብታረገንስ የሚል እና መጉዳት ብትፈልግ ለምን እህቴን አዳነቻት የሚሉ ጭንቀቶችን እያስተናገደች በእዛው ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ውስጥ ተመመች። እንቅልፍ የተባለ ደሴት ውስጥ ከተመች።በፀሎትም እንደዛው ለጥጥጥጥ አሉ።የሆነ ሰአት ላይ እኩለ ለሊት ሆኖል።

.
.
🥀..ክፍል 13 ከ 100 ላይክ ቡሀላ ይለቀቃል..

.
🥀 ..ቶሎ እንዲለቀቅ ላይክ ሼር አርጉ ..🥀
         
👍11411👏1
♥️ ፅናት ♥️...!!!
           .
           .
           .
🥀..ክፍል 13..🥀
          .
          .
          .
#Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው .!!
.
.

.
.
ፅናት ያ የሞት ጣር የሆነ እንጉርጉሮ ጆሮዋ ላይ አቃጨለባት። ብንን አለች ሊባኖስ የለችም በፀሎትም ተኝታለች። ፅናት በቀስታ ወደ በፀሎት ሄዳ "በፀሎት በፀሎቴ አለች።በፀሎትም "ምነው? ፅናቴ" አለች። "የሆነ ነገር ተፈጥሯል" አለች። በፀሎትም  ፍንጥር ብላ ተነስታ "ምን?" አለች። "ሊቦ የለችም" አለች ፅናት እጆቿን በአፏ ጭና። በፀሎትም "እና ባትኖርስ?" አለቻት "እንዴ የት ሄዳ ሊሆን ይችላል? ቆይ" አለችና ወደ በፀሎት ጆሮ ጠጋ ብላ "ግን በሩ ከ ውስጥ ማታ እንደዘጋነው ነው እሺ ወጥታ ይሆናል ግን በየት ወጣች?  በበር ከሆነስ በሩን ከውስጥ ማን ዘጋው"? አለች። አሁን በፀሎትም በጣም መፍራት ጀመርች። ምን አልባት በእንቅልፍ ልብሽ ከፈተሽላት እረስተሽው ነው ሚሆነው ፅናቴ" አለች በፀሎት ግራ ቢገባት ከውጭ አንድ ድምፅ ተሰማ ሙታን የት ናቸው የሚል "ምንድነው የምስማው" አለች በፀሎት ፅናት በተንቀጠቀጠ ድምፅ "እኔ  ስልሽ አሰማኝም እንጂ ይህ ቤት የሆነ ነገር አለው እሺ አሁን ምን ይሻለናን" አለች። በፀሎት "እኔ አላውቅም" አለች።በድጋሜ ከውጪ ሙታን የት ናቸው አለ በጣም ቀጭን ድምፅ ጮክ ባለ አንደበት።ፅናት ደርቃ በድን ሆና ቀርች። በፀሎትም "ሙታን!?" አለች ቃሉን ረገጥ አድርጋ።

ፅናትም "አዎ ሙታን ሙታን ነው ያሉት ልክ ነሽ በፀሎቴ ልቤ ሊፈነዳ ነው ምን ይሻላን ኧረ ወይኔ" አለች። በድንገት 1 ከ እንቅልፍ የነቃ ድምፅ "ምንድነው?" አለ።ፅናት በድንጋጤ ዘላ በፀሎት አልጋ ላይ ወጣች። ፅናት ተኝታበት ከነበረበት አልጋ እግርጌ ሊባኖስ ቀና አለች። ፅናት ደነገጠች "እንዴ ሊቦ አንቺ አንቺ አንቺ ቆይ የት ነበርሽ? "አለቻት።  በፀሎትም ግራ ተጋብታ "እንዴ ቆይ ምን እየተፈጠረ ነው?" አለች። ሊባኖስ በፅናት ሁኒታ ግራ ተጋብታ "ሚጢጢዋ  ምንድነው የሆንሽው? እየተንቀጠቀጥሽ እና በፍረሀት አይን እያየሽኝ ያለሽው ቆይ ለምድነው?" አለቻት።
      
በፀሎት የፅናትን እጅ ጥብቅ አድርጋ ይዛዋለች። ሊባኖስ አሁን ይበልጥ ግራ በተጋባ አስተያየት እያየቻት "በፀሎት አንቺስ ለምንድነው ቆይ የፅናትን እጅ እንዲ አጥብቀሽ የያሽው?" አለቻት ። በፀሎትም ምንም ሳትል በቶሎ የፅናትን እጅ ለቀቀችው። ሊባኖስ አሁን ደሞ ወደ ፅናት እያፈጠጠች "ሚጢጢዋ ቆይ ምን ተፈጥሮ ነው?አለቻት ቀዝቀዝ ለማለት እየሞከረች። ፅናት በሚንቀጠቀጥ ድምፅ  " አይ ከእንቅልፌ ስነሳ አንቺ አጠገቤ አልነበርሽም ከዛ ከዛ..." እያለች የተሰማትን ስሜት ከፈጠረባት ጭንቀት ጋር ደምራ ነገርቻት ፅናት ንግግሯን ያቆመችው  ሊባኖስን ሙታን ማን እንደሆኑ በመጠየቅ ነው። ሊባኖስ ግን "አይ አይ ጆሮዋቹ ነው" በሉ አሁን ተኙ እኔም ልተኛ ብላ ወደ ፅናት እግርጌ ሄዳ ተኛች።
    
ፅናትም ረዥም ደቂቃዎች በፀሎትን አቅፋ ከቆየች በኋላ ከበፀሎት አልጋ ተነስታ "ሊቦ ትራስ አለሽ?" ብላ ስትሄድ ሊባኖስ የለችም። ፅናት እየተዝለፈለፈች ወደ በፀሎት አልጋ ሄደች። በፀሎት ፈዛለች ተቃቅፈው ለሊቱን እንቅልፍ በአይናቸው ሳይከትም አሳለፉ እና ሊነጋጋ ሲል ሁለቱም እልም ያለ እንቅልፍ እንደተቃቀፉ ወሰዳቸው።

ጠዋት ቀድማ የተነሳችው በፀሎት ነበረች።የቀሰቀሳት በመስኮቱ በኩል የሚገባው ሀያል የፀሀይ ጨረር ነበር። በፀሎት ፅናትን "ፅናቴ እህቴ የኔ ንቂ ንቂ ነግቷል" አለቻት። ፅናት አይኗን እያሻሸች ስትነሳ የተኙበት ክፍል በር በረገግ( ከፈት) ብሏል። ግን ተነስታ መሬቱን መርገጥም ፈራች። አልጋው ላይ እንዳለች አይኗን ወደ ጣሪያው እጇቿን ወደ አፎቿ አድርጋ መፀለይ ጀመረች። ፅናት ስትፀልይ በትንሹም  ቢሆን ድምፅ ስለምታወጣ በፀሎት ፅናት ፀሎት ላይ እንዳለች ተረዳች። በፀሎትም መፀለይ ጀመረች። ሁለቱም ፀልየው ጨርሰው በዝምታ ቆዩ።

በድንገት በሩ ጓ ብሎ ተከፈተ በፀሎትን ያዳንዋት ሰውዬ አባ በሬሳ ነበሩ። ፅናት ከአልጋው ላይ ተነሳች። በፀሎት ግራ ገብቷት "ፅናቴ ማነው" አለች። ፅናትም ሀኪምሽ ናቸው አለቻት።" ደና አደራቹ  ፍጥረታት?"አሉ። ማንም መልስ አልስጣቸውም። ይህንን ያስተዋሉት አባ በሬሳም "ምነው ልሳናቹ ጠፋ ልክ እንደ ሙታን?" አሉና በፀሎትን ከጭንቅላቷ ብድግ አድርገው ከኪሳቸው የሚቀባ ነገር አውጥተው ቀብተዋት ወጡ። ፅናትና ትግስት በድንጋጤ ፈዘዋል።

የአቶ በሬሳ እግር ከክፍሉ እንደወጣ  ሊባኖስ መጣች። ደና አደራቹ አለች ለእሷም መልስ የሰጣት የለም።ፅናት ቅድም ከቆመችበት አልተነቃነቀችም በፀሎትም አልጋዋ ላይ ፈዛ እና ደንዝዛ ነው ያለችው። ሊባኖስ " እናተ ልጆች" ስትል ሁለቱም ደንግጠው ከፍዘታቸው ነቁ። "ሚጢጢዋ በሉ ቶሎ በሉ ወደ ቤታቹ የመሄጃ ስአት ደረሷል ቁርስ ቤታቹ ትበላላቹ" ብላ ወጣች። ቆየት ብላ ከአንድ ፈርጣማ ወጣት ጋር የበፀሎትን ዊልቸር ይዘው መጡና በፀሎት ዊልቸሯ ላይ እንድትሆን እረድተዋት አስቀመጡዋት። ከዛ ሊባኖስ የበፀሎትን ዊልቸር እየገፋች ከክፍሉ ወጣችና "ሚጢጢዋ በይ ነይ" አለችና ወደ ፈስጣማው ሰውዬ ዞራ "ጎረምሳው በል ቶሎ መኪናውን አዘጋጅ" አለችው። እሱም እሺታውን ገልፆላት ወጣ።

ልጁ እንደወጣ እነሱም ተከተሉት ፅናት ጊቢውን ቃኘችው አስፈሪ ድባብ አለው። ብዙ ዛፎች መሬት ላይ ደሞ በየመጠኑ ኤሊ እና ግዙፍ የፎቅ ቤት አለ። ከዛ ጊቢ ሲወጡ ፅናት እና በፀሎት እፎይይይይይ እስይይይይይ ተመስገን አሉ።

ከዛማ ፅናት እና በፀሎት  ወደ ቤታቸው ከሊባኖስ እና ከሹፌሩ ጋር ሄዱ። ቤታቸው ሲደርሱ ነፃነት ተሰማቸው። ሊባኖስ ነበረች በፀሎትን እየገፋች ያስገባቻት።ቤት ከገቡ በኋላ ሊባኖስ ሹፌሩን "ማርቆስ በል ቅድም መኪና ውስጥ ያስቀመጥኩትን አምጣው" አለችው። ሹፌሩም ምንም መልስ ሳይሰጣት ወጣ። ወዲያው በፌስታል  ያለ ነገር ይዞ መጣ። ሊባኖስ ቁጭ በል ማርቆስ  አለችው። እሱ አሁንም መልስ ሳይሰጣት ቁጭ አለ። የሹፌሩ ማረቆስ አለመናገር በፀሎት እና ፅናትን ግራ አጋብቷቸዋል።
     
    ፨በእዛች ቤት ውስጥ ሊባኖስ ፣ ፅናት እና በፀሎት ሆነው በሳቅ እና በወሬ ድምቅ አረጉት። ማርቆስም አለ ግን ይስቃል እንጂ አያወራም ፅናት ማርቆስን ሳታቋርጥ እያየችው ነው። አንዴም እንኳን ሊያወራ አልቻለም። ፅናት ግራ ተጋብታ ወደ ሊባኖስ ጠጋ ብላ "ሊቦ ቆይ ሹፌሩ ለምንድነው ምንም ሳያወራ የሚስቀው?" አለች። ሊባኖስም " ዝም በይ አንቺ ልጅ በኋላ እነግረሻለው አለቻት። "እሺ ሊቦ አትናደጂ ይቅርታ" አለች ፅናት ፈገግ ብላ ሊባኖስም "ምንም አደል በቃ እኔ አሁን ልሂድ ማርቆስ በል ተነስ እንሂድ ፅናቴ ያን ቋጠሮ ያመጣውት ለእናንተ ነው ሙዝ ብርቱካን እና ብዙ ፍራፍሬ" አለው። ስትላት ፅናት "ውይ ሊቦ ብትነግሬኝ ጥሩ ነበር እኮ ቀምሳቹ ትሄዱ ነበር" ስትል በፀሎትም "አዎ በቃ ፅናቴ ቢያስ የሆነ እየሄዱ እሚበሉትን ነገር ስጫቸው" ስትል ሊባኖስ "አይ አይሆንም በሉ በሉ ደና ዋሉ" ብላ ከማርቆስ ጋር ሄዱ።
.
.
🥀..ክፍል 14 ከ 150 ላይክ ቡሀላ ይለቀቃል..
.
.
🥀 ..ቶሎ እንዲለቀቅ ላይክ ሼር አርጉ ..🥀
          .
          .
83👍50😱7👎5
♥️ ፅናት ♥️...!!!
           .
           .
           .
🥀..ክፍል 14..🥀
          .
          .
          .
#Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው .!!
.
.
አዘጋጅ እና አቅራቢ :- #ከደራሲያን_አለም የቴሌግራም ቻናል
.
.
ፅናት ማርቆስን እና ሊባኖስን እስከበር በእግሯ መኪና ውስጥ ከገቡ በኋላ ደሞ በአይኗ ሸኝታቸው ወደ ደሳሳ ጎጆቸው ተመለሰች።ቤት ከገባች በኋላ ፅናት ወደ በፀሎት ሄዳ "የእኔ ውድ እህት እየውልሽ አሁን ሁለታችንም እንቅልፍ ያስፈልገናል በቃ እንተኛ ለሊቱን ሙሉ ያሳለፍነው በቃ ቆይ ፍራሹ ላይ እንደትሆኒ ላግዝሽና ፍራሹ ላይ ሁኔ ከዛ እቅፍቅፍ ብለን እንተኛለን" አለች ፅናት። በፀሎትም "እሺ የእኔ ልዩ ልክ ነሽ በሩን ዝጊውና በቃ እረፍት እናግ" አለች።ፅናት "እሺ" አለችና በፀሎትን ወደ ፍራሽዋ እንድትወጣ ከረዳቻት በኋላ አደላድላ አስተኛቻት ከዛም በሩን ዘግታ መጣችና።
    
ፅናት  ፍራሹ ዳር ላይ ቁጭ ብላ "እህቴ በቃ አሁን ሁሉንም እንርሳውና ጥሩ እንቅልፍ እንተኛ ከባድ ጊዜ ነበር ያሳለፍነው" አለቻት።በፀሎትም "ልክ ነሽ እህቴ በጣም አስቀያሚ እና አስፈሪ ነበር በቃ እንተኛ ነይ" አለችና ክንዷን ዘርጋችላት።ፅናት ፈጠን ብላ የበፀሎትን ክንድ ተንተረሳ ፊቷን ወደ በፀሎት አዙራ  ተኛች። ብድግ ብላ በድጋሜ በፀሎትን አንገቷን ሳመቻት። በፀሎት ፈገግ ብላ የፅናትን ጭንቅላት ሳመችው  ከዛም ፀጉሯን እያሻሸች ቆየች ከደቂቃዎች በኋላ እልም ያለ እንቅልፍ ወሰዳቸው።

ጠራራ ፀሀይ አልፎ ጎረምሳው ፀሀይ ለጎልማሳው ዳመና ቦታውን ለቋል። ጎረምሳው ፀሀይ ጉልበቱን በምድር ፍጥረት ላይ አሳይቶ አልፏል ልክ ነገረኛ   ሰው የሰውን ልብ አቃጥሎ ልብን እንደሚሰውረው ሁሉ ዳመናም በተራው የተንገበገቡ ሰዎችን ቀዝቀዝ እንደሚያረግ ሽማግሌ በፀሀይ ሲተካ እሱ ቀዝቀዝ ብሎ በፀሀይ የተቃጠሉትን ረገብ እንዲሉ አርጓል።  የሆነው ሆኖ ፀሀይ ለ ዳመና ቦታዋን ስትለቅ ዳመና ደሞ ለ ዝናብ አስረክቧል። ፅናትና በፀሎት ሀገር  ሰላም ብለው እንደተኙ ናቸው።

የነቁት ሀይለኛው ዝናብ የእዛች ደሳሳ ቤታቸውን ጣራ በሀያሉ ሲወቅረው ነው። ፅናት እና በፀሎት በእኩል የነቁት። ፅናት ፈጠን ብላ ውጪ ያለውን ጫማ አስገብታ የዝናቡ ውሀ ከቤታቸው እንዳይገባ ደሞ ጨርቅ ወተፈችው። በፀሎት ድምፅ ባጀበው መልኩ እየተንጠራራች "ፅናቴ ስንት ሰአት ነው?" አለች። ፅናትም የእጅ ሰአቷን አይታ  "10 ሰአት ነው እህቴ ለምን ፈለግሽው አለች" በፀሎትም "አይ እህቴ ያ የምትወጅው ደራሲ ዛሬ ቃለ መጠየቅ አለው ባለፈው ሳምንት ሲተዋወቅ ሰምቼ ነበር" ስትላት ፅናት "የምርሽን ነው ወይኔ ስንት ሰአት"? አለቻት። በፀሎትም ከ 11 ሰአት እስከ 12:30" አለቻት። ፅናት ደስስ ብሏት "እሺ ጥሩ በቃ እናዳምጠዋለን አሁን ዝናቡ ሲያባራ ሊባኖስ ከፍራፍሬው ጋር ያስቀመጠችልን ብር አለ። የሆነ ነገር ገዝቼ እመጣና ወይ ሰርቼ እንበላለን" አለች። በፀሎትም "እሺ እህቴ ነይ ዝናብ እስኪያባራ እንዳይበርድሽ" ስትላት።"እሺ እህቴ"ብላ ብርድ ልብስ ከ እህቷ በፀሎት ጋር ለብሳ በፀሎት ክንድ ላይ ደገፍ አለች።

እንቅልፍ ሳይወስዳቸው ዝናቡ አባራ ፅናት ብድግ ብላ "እህቴ በቃ እኔ ያልኩሽን ገዛዝቼ ልምጣ" አለች በፀሎት ፈገግ ብላ "እሺ ፅናቴ" አለቻት ፅናት ሹራብ ደርባ  ሻርፗን በፊቷ ላይ ጠምጥማ ልትገዛዛ ወጣች። በፀሎት ሀሳብ ላይ ናት። "እንዴት እንዲ በጥቂት ሰአት ልድን ቻልኩኝ? ሊባኖስስ ትናት በለሊት የት ሄዳ ነበር?። እነዛ ያዳኑን ሰውዬስ? ከፅናቴ ጋር የሰማነው አስጨናቂ እንጉርጉሮሰ? ሙታንስ ማን ናቸው?"። እያለች እራስዋን ብትጠይቀውም መልስ ግን አላገኘችም።መላሽም እንደዛው።

ፅናት ለእሷ እና ለእህቷ በአስቸኳይ ሰርታ የሚበሉት ነበር እያሰበች ጉዞዋን አርጋ በስተመጨረሻ ከ እራሷ ጋር ተመካክራ እህቷ በጣም እምትወደውን እንቁላል ፍርፍር ለመስራት ወሰና እንቁላል ገዛች። ከዛም እሷ ዳቦ ስለማትወድ 1 እንጀራ እና 2 ዳቦ ገዛታ ወደ ቤቷ ጉዞዋን ቀጠለች።
 
በመንገዱ ላይ እነዛ ሴተኛ አዳሪዎችም ሆነ ዱርዬዎች አልያም ሾካካ የሰፈር ነዋሪዎች በዝናቡ ምክንያት ከተሸሸጉበት አልወጡም ሰፈሩ ጭር ብሏል ፅናት ጭቃ በጭቃ እንዳትሆን ድንጋይ ድንጋዩን እየመረጠች እየሄደች ነው። ከኋላዋ የሰው ኮቴ ተሰማት ጀርባዋን ሸከካት። ቀስ ብላ ዞር ልትል አሰበች።  ከዛም በጣም ፈራች። መዞርን  ከኋላዋ የሚከተላትን ማየት ከበዳት ፈራች። ፈጠን ፈጠን እያለች ስትሄድ ኮቴውም ፈጠን ፈጠን ይላል ቀስ እያለች ስትሄድ ኮቴውም ቀስ ይላል ፈራች። ጭር ባለ ሰፈር ውስጥ የማታውቀው ኮቴ የሚከተላት ፅናት በጭንቀት ልትሞት ደረሰች የመጀመሪያ የቤቷን መታጠፊያ መንገድ ታጠፈች። አሁንም ግን የሚከተላት ኮቴው አለ።  እግሮቿ መራመድን ገቱ ፤ አቆሙ ቀጥ ብላ ቆመች እና ቁጢጥ ብላ ተቀመጠች።
 
ወዲያ የሩጫ ኮቴ ተሰማት ትንሽ ከቆየች በኋላ ዞር ስትል ምንም አይነት ሰው ከ ኋላዋ የለም። ቀስ ብላ ወደታጠፈችበት ቦታ ተጠጋች ምንም አይነት ሰው የለም።
የፅናት ልብ  በሀያሉ መምታት ከጀመር ቆይቷል። ፅናት በብርሀን ፍጥነት ከ አከባቢው ተሰውራ ቤቷ በር ላይ እንዴት እንደደረሰች እምታውቀው ነገር የለም። የቤቷን በር ከፋታ ገባች። በፀሎት "ፅናቴ መጣሽ ቆየሽብኝ እኮ" አለቻት። ፅናትም እየተንተባተበች በተቆራረጠ ድምፅ "እእእ  አአአአ አይይይ እህቴ እንቁላል ገዝቼ እኮ ከዛ ከዛ ደሞ እዚህ በር ላይ ስደርስ ዳቦ እና እንጀራ ልገዛ ሄጄ እኮ ነው"አለችና ኡፍፍፍፍ አለች።በፀሎት ግራ ገብቷት "እንዴ ፅናቴ ምን ሆነሻል ለምንድነው አነጋገርሽ ትክክል ያልሆነው " ስትላት "አይ አይ ደና ነኝ እኮ ግራ የተጋባው መስሎሽ ይሆናን በቃ እህቴ እንቁላሉን ልስራና እንብላ" አለችና ለመስራት መንጎዳጎድ ጀመረች። ፅናት አሁንም ፍርሀቷ አለቀቃትም የምታረገው ሁሉ ጠፍቷታል።

በፀሎትም ግራ ተጋብታለች የፅናት የውስጥ የመረበሽ ተሰምቷታል ግን ደሞ ዝምታን መርጣለች የሆነው ሆኖ ፅናት  እንቁላሉን ለመስራት እሳት ማቀጣጠል ጀመረች። እሳት እያቀጣጠለች በሀሳብ ተውጣለች በድንገት ሳታሰበው የጫረችው ክርቢት ከሀሳቧ እና ከፍዘቷ አንቅቷታል  ፅናት ነቃ ብላ ትንሽዬ እና ብቸኛ ድስታቸውን አምጥታ ትንሽዬ ዘይት ጨመረችበት እና እሳቱ ላይ ጣደችውና በከሰል ማንደጃው ቀዳዳ በኩል ማረገብገቢያውን በመጠቀም ማራገብ ጀመረች። እሳቱ በሀይል ተቀጣጥሎ ድስቱን አግሎታል። በፀሎት አሁንም ከሀሳብ መንገዷ አልተመለሰችም ከሀሳብ መንገዷ የተመለሰችው ፅናት የጋለ ዘይቱ ላይ በጎድጓዳ ሰሀን የመታችውን እንቁላል ዘይቱ ላይ ሰጨምረው ባወጣው ድምፅ ነበር።
.
.
https://vm.tiktok.com/ZMBhGVJ2W/

🥀..ከ 150 Like ቡሀላ ክፍል 15 ይቀጥላል ..
         
👍12616👎5
♥️ ፅናት ♥️...!!!
           .
           .
           .
🥀..ክፍል 15..🥀
          .
          .
          .
#Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው .!!
.

.
ወዲያው በፀሎት ክትክት ብላ መሳቅ ጀመረች።ፅናት በጣም ገርሟት "እህቴቴ ምነው ምን ተገኘ እንዲ በድንገት ያሳቀሽስ ምንድነው?"አለቻት። በፀሎት "አይ በፀሎቴ  እንዲ በሆነው ባልሆነው ነገር መደንገጤ ለእራሴ ገርሞኝ ነው" አለቻት ፅናት ግራ በመጋባት ስሜት "እሺ እህቴ ዋናው መሳቅሽ ነው" አለችና በአነስተኛ ሰርቢስ ሰሀን የገዛችውን እንጀራ አንጥፋ እንቁላሉን አረገችው ከጎኑ ደሞ ዳቦ አርጋ ፍራሽ ላይ ተንጋላ ያለችው እህቷ ጋር ወሰደችው። ከዛም "እህቴ በይ ነይ እንብላ ቆይ የእጅ ውሀ ላምጣልሽ" አለችና አምጥታ አሰታጥባት ሰታበቃ ከሰል ማንደጃው ላይ በማንቆረቆሪያው ውሀ አርጋ ውስጡ ሻይ ቅጠል ጨምራ ጣደችው። በፀሎት "ፅናቴ ኧረ ነይ ባክሽ" አለቻት። ፅናትም "መጣው እህቴ ሻይ ልጣድ ብዬ እኮ ነው" አለችና ፍራሹ ጠርዝ ላይ ተቀመጠችና ልክ ሁሌም እንደሚያረጉት ተጎራረሰው መብላት ጀመሩ።

በልተው ሲጨረሱ ፅናት ሻይ አቅርባ ጠጡ። ፅናት የበሉበትን እና የጠጡበትን እቃ አነሳስታ ለማጠብ ውጪ አወጣችው። የሚያስፈልጓትን ነገሮች አውጥታ እቃ ማጠብ ጀመረች።
እቃ እያጠበች ከውጪ ሀይለኛ ጩከት ሰማች የሰማችው አንድ መኪና ከሊላ መኪና ጋር ሲጋጭ የሚፈጥረው አሰቃቄ ድምፅ ከ ሊባኖስ ድምፅ ጋር ተደምሮ ነበር። ፅናት "ሊቦዬ" ብላ ሮጣ ወጣች። በፀሎት "ፅናት ፅናቴ እህቴ ምንድነው?" አለች ግን መልስ አላገኘችም። ተጣራች ተጣራች አሁንም አቤት ባይ የለም።

በፀሎት መልስ አጣች ፅናትን ጉሮሮዋ እስኪሰነጠቅ ጠራቻት ግን አሁንም አቤት ባይ የለም። ግራ ቢገባት ዝም ብላ ቁጭ አለች። ሀሳብ ገባት "የት ሄዳ ይሆን?፤ ምን ሆና ይሆን ፤ ውጭ የምን ጩከት ነው?" አይምሮዋን ብዙ ጠየቀችው ግን ያላየውን እና ያልሰማውን ከየት ያመጣዋል። የውጪ ጩከት ረገብ አለ። ወዲያው የፅናትን እና የሊባኖስን ድምፅ እያወሩ ሰማቻቸው።"ለበፀሎቴ ምንም እዳትያት ትጨነቅብኛለች" እያለች ፅናት ለሊባኖስ ስትነግራት በፀሎት ሰማቻቸው
በፀሎት እንዳልሰማች እንደውም እንቅልፍ እንደወሰዳት ሆና ዝም አለች።

ሊባኖስ እና ፅናት እቤት ገብታ ፅናት ድምጿን ቀንሳ "ውይ እህቴ ተኝታለች እንዴት ተኛች አሁን እኮ ነው ከ እንቅልፋችን የተነሳነው" ስትል በፀሎት የፊቷን የሸፈነችውን ብርድ ልብስ ገለጥ አድረጋ "አይ አለው አልተኛውም እህቴ" አለቻት። ፅናት "እሺ በሉ አሁን ሬዲዮኑን ልክፈተው እህቴ አምልጦናል" አለችና የእጅ ሰአቷን አይታ "20 ደቂቃ አልፎናል" አለችና ሬዲዮኑ እንዲሰራ እንደተለመደው መታ አረገችው መስራቱን ቀጠለ።

ደራሲው መሀመድ ሳላዲን እያወራ ነው። ሊባኖስ፣ ፅናት እና  በፀሎት  ጆሮዋቸውን ሰጥተው ማዳመጥ ጀመሩ። ይህ ደራሲ ሰለተመረቀው መፅሀፉ  እያወራ ነው። ጉሮሮውን ከጠራረገ በኋላ "ያው እንዳልኩሽ በድርሰት አለም ውስጥ ደራስያን በተለያዮ መንገዶች ሀሳባቸውን ወደ ህዝቡ ያደርሳሉ ለምሳሌ ያክል  አንድ ደራሲ ድርሰቱን ወደ ህዝብ ሲያቀርብ እራሱን ባለቤት አርጎ ይፅፋል ማለትም እኔ ተፈቅሬ ፣ አፍቅሬ ፣ አልቅሼ ፣ ተበሳጭቼ....  እያለ ማለት ነው።

በሊላ መልኩ ደሞ የእሩቅ ታዛቢ ሆነው እነሱ ደስተኞች ነበሩ ፤ እነሱ ቤተሰብ ነበሩ ፤ ተበደሉ፣ ሞቱ... እያሉ ማስተላለፍ የሚፈለጉትን ነገር ያስተላልፋሉ እኔ በእዚህ ከተማ ደራሲ እና የዩንቨርስቲ የድርስት እና ኪነጥበብ አስተማሪ ነኝ። በተጨማሪም ሂስም ነኝ ያው ደራሲያን ድርሰታቸው ለህዝብ ከመድረሱ በፊት እገመግማለው እና በእዛን ሰአት የታዘብኩት ነገር ቢኖር ተፈቃሪዎች ሁሌም ቆንጆ ፀባይ ሰናይ እና ማራኪ ናቸው።
     
በፊልሙ አለም ውስጥም እንደዛው እና እኔ አሁን የፃፍኩት አንቺን ለእኔ የተሰኘው ድርስቴ ላይ ተፈቃሪዋ ውብ አደለችም!  እእእእ አይነ በጎ ሽንጠ ሎጋም በጭራሽ አደለችም! ወንዶች የሚተራመሱላት ሴትም አደለችም! አፍቃሪው ግን ግርማ ፣ ሞገስ ፣ የሴት ፍቅር እና ብዙ ነገሮች አሉት። ታዲያ ይህ አፍቃሪ ይህቺን ተፈቃሪ እንዴት ከልቡ እንደገባች እንዴት እንዳፈቀራት እና እንዴት ልቡ ሲያያት እንደደነገጠ ቢጠየቅም መልስ የለውም።

ይህቺ ተፈቃሪ ሴት ስሟ ሂሩት ይባላል አፍቃሪው ደሞ ጌታሁን ፍቅሩ  ወደ በሽታነት ተቀይሮ ደስስ የሚል ስቃይ ሲሰቃይ ሂሩት ግን ፍቅር የለም ብላ የምታስብ ሴት  በመሆኗ ፍቅሩን ልትቀበለው አልቻለችም ጌታሁን በእዚህ ሁኔታ ሲሰቃይ የሚያሳይ ታሪክ ነው የሂሩት እራስዋን መጣል እና መቆሸሽዋ እንዲሁም አስቀያሚና ትህትና የጎደለው ፀባይዋ መልክ የላትም እንጂ ቢኖራትም በጭራሽ እንኳንስ መፈቀር እያስወድዳትም ግን በቃ ፍቅር ያለ ምላሽ እና ያለ ምክንያት ወዶ መገኘት ነው።

የሚለው ጌታሁን  ብዙ ብዙ ቆነጃጂት እና ፀባየ ሰናይ ሴቶች ይፈልጉታል። ብቻ ከታሪኩ በጥቂቱ ይህን ይመስላል ይህ ከፃፋኩት  ውስጥ አንዱ ታሪክ ነው መፅሀፍ አንቺን ለእኔ ተብሎ ይሰየም እንጂ በውስጡ የተለያዩ 10 አጫጭር ልቦለዶች ይገኙበታል።" አለና ዝም አለ። ጠያቂዋ "ዋውውውው በጣም ደስስስ የሚል መፅሀፍ ነው ግን አንድ የመጨረሻ  ጥያቄ አለኝ አለች ጠያቂ ጋዜጠኛዋ ደራሲው እንድትቀጥል ነገራት እሷም ቀጠለች።

ብዙ ደራሲያን ድርሰታቸው በተመረቀ በ 9 ኛው ቀን ስለ መፅሀፋቸው ምንም አይነት ቃል አይተነፍሱም ያው አንብባቹ ተረዱት ነው የሚሉት ግን አንተ እንዴት ስለ መፅሀፍክ ማለትም ስለ ድርሰትክ ፍሬ ሀሳብ ልትናገር ቻልክ ?" አለችው። ደራሲው ክትክት ብሎ ከሳቀ በኋላ "የደራሲያን ችግር ይህ ነው!አለ ሞቅ ባለ ድምፅ  ግን መሆን የለበትም ምክንያቱም ደራሲ መሆን   ያለበት ሀሳብ ወደ ህዝብ እንዲገባ እንጂ ገንዘብ  ኪሱ እንዲገባ መስራት የለበትም " አለ። ጠያቂዋ ጥያቄዋን ከምስጋና ጋር እንዳጠናቀቀች እና ለደራሲው ማመስገን እሚፈልገውን እንዲያመሰግን እድሉን ሰታው አመስግኖ ፕሮግራሙ በመሰናበቻ  ሙዚቃ አድርጋ ዘጋችው። ፅናት ሊባኖሰ እና በፀሎት ለደራሲው ሳላዲን በመገረም አጨበጨቡ።

ሊባኖስ "እንዴ ቆይ ምን አይነት አእምሮ ነው" አለች በመገረም ፅናት ፈገግ ብላ ውይይይ ሊቦዬዬ "እኔ ለእራሱ በጣም ነው የማደንቀው ታያለሸ በእዚህ ሰው ሁሉም ይደነቃል ደሞ እውነት ነው።" አለች በፀሎትም በተራዋ "አዎ አዎ ልክ ነሽ ሁሌም ቢሆን እኛ ማየት የተሳነን ሰዎች አለምን በጆሮ እና በልባችን ነው የምናያት በጆሮ ማየት ይለያል በጆሮ መስማትም ይለያል በቃ አለም ጆሮአችን እና በልባችን ውስጥ ናት።ጆሮአችንን ለብዙ ነገር እንጠቀመዋለን አይንን ጨፍኖ ማሰብን እና አይንን ገልጦ ማሰብ ይለያል ለማለት የፈለኩት ምን መሰላቹ አለም ምን እየመሰለች እንዳለች ያሳየናል ለምሳሌ እኔ ፅናቴ ካነበበችልኝ መፅሀፋ ውስጥ ሰለምንኖረባት  አለም ውበት በግልፅ ያሳያል እእ ለምሳሌ ስለ ፎቆቹ ውበት ትልቀት ስላረጁ ሰፈሮች ስለ ሰዎች የአኗኗር ዘይቤ ይህን እምናቀው በመፅሀፍ ነው" አለች በፀሎት።
.

https://vm.tiktok.com/ZMBU6CUJD/

🥀..ከ 100 Like ቡሀላ ክፍል 16 ይቀጥላል ..
         
👍8912👎2
♥️ ፅናት ♥️...!!!
           .
           .
           .
🥀..ክፍል 16..🥀
          .
          .
          .
         .
         .
በፀሎት በፍቅር ስታወራ በፍቅር አይን ስታያት የቆየችውን እህቷ በፀሎትን ሄዳ ጥምጥም ብላ አቀፈቻት ከዛም " አዎ ልክ ነሽ እህቴ ልክ ነሽ አንቺ ሁሌም ልክ ነሽ የእኔ አዋቂ የእኔ አስተዋይ ፣የእኔ ሁሉ ነገር አለችና አይኖችዋን ፣ሁለቱ ጉንጮችዋን ፣ግንባርዋን እጆቿን አንገቷን ቀስ እያለች በእርጋታ ሳመቻቸው።


ሊባኖስ "አቤት ስታስቀኑ አቤት ፍቅራቹ አቤት መተሳሰብና መዋደዳችው ድንቅ ነው" አለችና አቀፈቻቸው፤እነሱም አቀፏት።

ተቃቅፈውም ሳለ የውጪ በር ተንኳኳ ፅናት ከ እቅፋቸው ወጥታ አንገቷ ላይ ያረገችውን ሻርፕ ፊቷ ላይ ጠምጥማ በሩን ለመክፈት ሄደች።በር ላይ ያለውን ሲሊፕር ጫማዋን እያረገች ማነውው አለች። በሩ ዝም ብሎ ይንኳኳል እንጂ እኔ ነኝ የሚል አንደበት የለም። ፅናት ሮጥ ብላ ከፈተችው በሩን ስትከፈት ግን በሩ ላይ ማንም የለም። ሊባኖስ ድምጿን ከፈ አድርጋ "ፅናቴ ማነው?" አለች። ፅናት መልስ አልሰጠቻትም  "የቅድሙ ኮቴ አዎ እሱ መሆን አለበት!" አለች ፅናት ሊባኖስ ፅናት ዝም ስትላት የቤታቸው በር ላይ ቆማ የግቢ በሩን ከፍታ ወደ ውጪ የምታየውን ፅናት ጠራቻት። ፅናት "ግን አቤት" አላለችም። ሊባኖስ ግራ በመጋባት ሚጢጢዋ አለች ድምፅዋን ከፍ አርጋ ያኔ ፅናት በሊባኖስ ድምፅ ደንግጣ ዞር አለች።

ሊባኖስ በሁኔታዋ ግራ ገብቷት እሷም ጫማዋን አድርጋ ወደ ፅናት ሄደች እና "ምንድን ነው ሚጢጢዬ ችግር አለ?" አለቻት። ፅናትም "አይ ሊቦዬ ምንም የለም" አለችና አንገቷን አቀረቀረች ሊባኖስ በአመልካች ጣትዋ ፅናትን ከ አገጯ ቀና እያረገቻት በይ አሁኑኑ የተፈጠረውን ንገሪኝ በይ በፍጥነት እያዳመጥኩሽ ነው። ስትላት ፅናት "ኡፍፍፍፍፍ ሊቦዬ እኔ ለእራሱ ግራ ገብቶኛል ምን አልባት በጭንቅላቴ የፈጠርኩት ነገር ሊሆንም ይችላን" አለች።
 
ሊባኖስ ግራ በመጋባት ስሜት እያየቻት "ቆይ ቆይ አንቺ ልጅ ምን እያለሽ ነው" ስትላት ፅናት "እኔ ለእራሱ ምንም የምለውን ነገር አላውቅም በቃ ተይው እርሽው" አለቻት። ሊባኖስ ፊቷ በንዴት እየተንቦገቦገ "ቆይ ምን እያልሽ ነው በይ አሁን ምንም ሳታስቀሪ ለእኔ እና ለእህትሽ ስጋትሽን ትነግሪናለሽ" አለቻት።
ፅናት "ምን ምን ምን ብዬ ሊቦዬ ማለቴ በእኔ የማይረባ ሀሳብ ያውም ባልተረጋገጠ ነገር እንዴት ምንስ ብዬ ነው የምነግራችሁ በእውነት ሊቦዬ ምንም ነገር የለም" አለች። ሊባኖስም "አይ አይ በባዶ እማ እንዲ አትሆኒም ስጋትሽን ትነግሪናለሽ ከዛ መፍትሔ እንፈልጋለን አለቀ" ብላ እቤት ጎትታ አስገባቻት እና በሩን ከውጪ ጓ አርጋው ገባች።

በፀሎት ደንግጣ "እንዴ ምንድነው ምን ምን ተፈጥሮ ነው ቆይ" አለች። ሊባኖስም" ቆይ በፀሎት ሁሉንም ነገር ከ ሚጢጢዬ እንሰማለን በይ ሚጢጢዬ ቁጭ በይ ከዛ የተፈጠረውን ሁሉ ንገሪን" አለችና እንድትቀመጥ ፍራሹ ላይ ጋበዘቻት ፅናት "እሺ በቃ ያው እኔ ማለቴ እኔ ኡፍፍፍፍፍ እኔ" ሰትል። በፀሎት በመሀል ገብታ "አንቺ ምን? እህቴ አንቺ ምን? አንቺ ምን ሆነሽ ነው?" አለች። ፅናት እየተርበተበተች ለእሷ እና ለበፀሎት እንቁላል ልትገዛ ስትሄድ ያጋጠማትን ሁሉ ነገረቻቸው የአሁኑን ስጋትዋን ጨምሯል። "ሊላው ደሞ ያው... " ብላ ምላስዋን ነክሳ ዋጥ አረገችው። ሊባኖስም አብራት ነበር የደነገጠችው።

በፀሎት "በያ እህቴ ጨረሽው!" አለች። አሁን ሊባኖስ በወሬው ጣልቃ ገብታ "በቃ አትጨናነቂ ምንም የሚያሳብ ነገር የለም" አለች። በፀሎትም "ሀሳብዋን ሳትጨርስ ለምን ታስቆሚያታለሽ በይ እህቴ ጨርሽው!" አለች። ፅናት ከእነዚህ በላይ ከ እህቷ ምንም መደበቅ ስላልቻለች። የበፀሎትን እጅ ጥብቅ አርጋ ይዛ "እይውልሽ እህቴ ዛሬ የበላንበትን እቃ እያጠብኩ" አለችና ወሬዋን አቋርጣ የሊባኖስን ፊት አየችው። ሊባኖስ ቀጥይ በቃ የሚል ምልክት በእጇ አሳየቻት። በፀሎትም እሺታዋን በአገጭዋ ገልፃ ወሬዋን ቀጠለች።

የሚጮህ ድምፅ ሰምቼ ስወጣ...." አለች ስቅቅ ብላ በፀሎት "የማንን?" አለች ፅናት "እእእ ሊቦ ከ አንድ ሰው ጋር እየተጣላች ነበር።ያ ሰውዬ ደሞ ሁሌም ማታ ማታ ምግብ ስሸጥ ያስቸግረኝ ነበር" ብላ ኡፍፍፍ አለች።በፀሎት "ምን ምን ምን እሺ ከዛስ" አለቻት። "ከዛማ አንድ ቀን መጣና ነይ መኪና ውስጥ ግቢ ከዛ ምነግርሽ ነገር አለ አለኝ" ብላ ወሬዋን ሳትጨረስ "ቆይ ምን እያለ ነው የሚያስቸግረሽ?"  አለቻት በፀሎት "ነይና መኪና ውስጥ ገብተን እናውራ እያለ" አለች።
      
የያዘችውን የበፀሎት እጅ ጥብቅ አድርጋ ይዛ። በፀሎት "ወይ ጉድ ወይ ፈተና እሺ ቀጥይ" አለቻት። ፅናት "ከዛማ.." አለችና በፀሎት ታፋ ላይ ጋድም አለች። በፀሎትም" እሺ  በይ ቀጥይ እህቴ" አለቻት ከዛ አንድ ቀን የያዝሽውን ምግብ ሁሉ እኔ እገዛሻለው አንቺ ደሞ ጊዜሽን ስጭኝ አለኝ። እሺ አልኩና መኪና ውስጥ ገባው" ስትል ሊባኖስ ከመቀመጨዋ ብድግ ብላ "ምን በይ ቀጥይ አሁን" አለቻት። ከዛ መኪና ውስጥ ከገባው ቡኋላ ሰውየው ረዘም ያሉ ደቂቃዎች ዝም ካለ ቡኋላ ማውራት ጀመረ።

በፀሎትም " ፅናት እህቴ እና ምን አለሽ?። አለች ፅናትም እሱ እማ ያለኝ ልጅ እንዳለው እና ልጁን ቀርቤ እንድቀይርለት ነገረኝ ለምን እንዴት እኔን መረጥክ እንዳትይኝ አለኝ።ግራ ገባኝና ዝም ብዬ መስማቴን ቀጠልኩ በእረግጥ ሰውየው 50 ወይ ደሞ 48 አመት ይሆናል ፊቱ በጣም ያስፈራል ልጄ መንገድ ላይ ነው አብዷል ስለእዚህ እርጅው አንቺን የመረጥኩሽ ዝም ብዬ አደለም ግራ ቢገባኝ እንጂ እና ደሞ ሳይሽ ሁሉም የእዚህ መንደረ ነዋሪ ገላቸውን በመሸጥ ነው የሚተዳደሩት በአንቺ ሙያ ያሉትም ቢሆኑ ባገኙት አጋጣሚ  አንቺ በእርግጥ ልጅ ነሽ ታስታውቂያለሽ ግን ይህ መርከስ አልፈግም ሲለኝ በንዴት "ወድያው አደለም እንዲማ አይባልም" አልኩት።

ሰውየው "እሺ ይቅር በይኝ ለማንኛውም መውጫ መግቢያሽን አጣርቻለው ልጄን ለማዳን ፍቃደኛ ካልሆንሽ እኔ ደሞ አንቺን እገልሻለው አለኝ ደንገጭኤ ፈዝዤ ቀረው።በእዛ መሀል ሊቦ ወደ እኛ ቤት ስትመጣ መኪና ውስጥ አየችኝና ወደ መኪናው መጥታ ጎትታ አውርዳኝ ሰውየውንም በእዚህ እድሜክ ለምን ትረክሳክ ብላ ሰድባው ወደ ቤት እየጎተተች ይዛኝ" ገባች።

ከዛ ቀን በኋላ ሊቦ ባገኘችው አጋጣሚ ሰውየውን ጮክ ብላ ትሰድበዋለች"። ስትል ሊባኖስ "በቃ ይበቃል" አለች በፀሎት ግን ፅናትን እንድትቀጥል ነገረቻት። ፅናትም ወሬዋን ቀጠለች ከዛ በቃ አንቺ ፀባችንን እንዳታቂ ሊቦ ለ3 ቀን ቤት አልመጣችም ካስታወሽ። ከዛ በ4ተኛው ቀን እኛ ቤት ስትመጣ ለሊቦ ይህንን ነገረኳት ከዛ በኋላ በቃ ሊቦ ሰውየውን ባየችው ቁጥር እንዴት የእኔን ሚጢጢዬ ትዝትባታለክ ብላ ትጮሀለች" አለችና ብድግ ብላ የበፀሎትን እጅ አስለቅቃ ወደ ሊባኖስ ሄዳ ሊባኖስን እቅፍ አረገቻት።

"ሊቦዬ የእኔ አሳቢ" እያለች።በፀሎት የመናደድ እና ግራ የመጋባብ ስሜት ከፊቷ እየተነበበ "ቆይ እንዴት ለእኔ አልነገረሽኝም" አለች። ሊባኖስም "አይ
.
.
https://vm.tiktok.com/ZMBaPD1wj/
🥀..ከ 150 Like ቡሀላ ክፍል 17 ይቀጥላል ..
         
👍8823🙏6
...♥️ ፅናት ♥️...!!!
          .
          .
          .
🥀..ክፍል 17..🥀
           .
           .
           .
Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው .!!

በፀሎትዬ እኔ ነኝ እንዳነግሪያት ያልኳት  ምክንያቱም ይህ አባቱ እርጅው ያለው ልጅ" ብላ ፀጥጥጥጥ አለች። "እ ጨርሽዋ" አለች ሊባኖስም "እየውልሽ በፀሎት ልጁን እንደምንረዳው እኔና ፅናቴ ቃል ተገባብተን ሰውየው ልጁን ለሚጢጢ ከማስተዋቁ በፊት ስለ ልጁ በአባቱ አማካኝነት ማለትም ሰውየውን በመከታተል ማወቅ ፈለግን እና ሰውየውን በሚስጥር መከታተል ጀመርን።ምክንያቱም ሁኔታው ምንም ስላላማረኝ ምክንያቱም ሰውየው እራሱ ሲታይ በጣምም ደም የጠማው አጋስስ ስለሆነ" አለች ሊባኖስ።

በፀሎት ግራ ገባት "እኔ ለእህቴ በጣም እየፈራው ነው በጣም  ቆይ ምን እየተፈጠረ ነው ልጄን ካረዳሽው እገልሻለው አለ ኧረ የፈጣሪ ያለ ቆይ ምን ጉድ ነው እሺ አሁን ምን ልናረግ ነው ቆይ ልጁን ለምን አትረዱትም " አለች። ሊባኖስም "እሱስ እሺ ግን ሊላ ነገር አለ እየውልሽ በፀሎትዬ እኔ ሰውየውን እየተከታተልኩት ነበር እና አንድ ቀን ሰውየው ከሆነ እብድ ጋር ሆኖ አየውት ልጁ ያው እሱ እንደሆነ አውኩ ማለት ነው ከዛ እርቆ ወደሚገኘው ሱቅ ሄጄ ባለ ሱቋን ጠጋ ብዬ እኔ ምልሽ እህት አልኳት እንዲ ስላት አይኔን ከ እብዱ ልጅ እና ከ አባቱ ስላልነቀልኩ ስለእነሱ ልጠይቃት እንደሆነ ገባት እና ስሚኝ እነዛን ሰዎች ታውቂያቸዋለሽ ብላ ጠየቀችን አይ ማናቸው? ስላት እሷ እንዴት አንድ የዘነጠ በሱፍ እና በከረባት ታስሮ በብራንድ ጫማ እና ልብስ ተሸቆጥቁጦ እንዲ እራሱን ከጣለ እብድ ጋር ተቀመጠ እያልሽ እራስሽን እየጠየቅሽ ነው ? አለችኝ እኔም አዎ ልክ ነሽ አልኳት እሷ ሳትገረፍ የምትለፈልፍ አይነት ሰው ናትና ስለ ሰውየው እና ስለ እብዱ ነገችኝ" ስትል በፀሎት "ምን ምን ብላ ነው የነገረችሽ" አለቻት። ሊባኖስም "ሰውየው የእብዱ አባት እንደሆነ እና ደሞ እብዱ ካልተኛ በስተቀር አባቱም እንደማይጠጉት  የተጠጋውን ሰው ሁሉ ከእጁ በማይጠፋው ጩቤ እንደሚወጋ ነገረችኝ" ስትል  በፀሎት ሰውነቷ መንቀጥቀጥ እና ፍርሀት ይበልጥ ሰውነቷን መውረስ ጀመራት።

ግን እስከመጨረሻው ለማወቅ ባላት ፍላጎት "እሺ ቀጥይ" አለች። ፅናት ወደ በፀሎት በመሄድ የበፀሎትን እጅ አጥብቃ ያዘችው። ሊባኖስም ንግግሯን ቀጠለች። "እየውልሽ ባለ ሱቋ እንደነገችኝ ከሆነ እብዱ የሆነ የእንቅልፍ ሰአት አለው እና አባትየም ያን ሰአት ተጠቅሞ ነው ልጁ ጋር የሚጠጋው  እና ያ ሰአት ደሞ እኔ እዛ የነበረኩበት ሰአት ነው።  ያንን ሰአት ተጠቅመው አባት ለእብዱ ልጁ መርፌ ይወጉታል። የሚወጉት መርፌ ደሞ ልጁን እንቅልፍ ይበልጥ እንዲወስደው እና እንዲሻለው ያረጋል። ከዛ መርፌውን ከወጉት በኋላ ነው ጠባቂዎቻቸውን ጠርተው ወደ ቤታቸው የሚወስዱት። አለችኝ ለምን ስላት የሰጠችኝ መልስ እጅክ ገራሚ ነበር" አለች ሊባኖስ።  በፀሎትም ቀጣዩን ለመስማት ጓጓች እና "ማለት ምንድነው ያለችሽ" አለቻት።

ሊባኖስ የጭንቀት ፊቷን ለማረጋጋት እየሞከረች " መልሱ ምን መሰለሽ እየውልሽ በፀሎትእዬ ባለ ሱቋ ያለችኝ አባትየው ልጁን ቤታቸው ይዘውት ይሄዱና ግቢያቸው  ውስጥ ከመኖሪያ ቤታቸው እራቅ ብላ ትንሽዬ ቤት አለች ከመውጫ በሩ አጠገብ  ይህቺን  ቤት
ያሰሩት ለልጃቸው ነው ቤቱ በጣም ትንሽ ነው እና በግቢውም ተገብቶ በር አለው እና ደሞ ሊላ ከውጪም ልክ እንደ ውጪ በር መውጫ አለው አባትየው ልጁ ከመነሳቱ በፊት ለሊት ላይ ወጥተው የልጁን በር ከውጭ ይከፍቱለታል ግዙፍ ቤት ነው ያላቸው አለችኝ።
         
እንዴት ይህንን አንቺ ልታውቃ ቻልሽ ስላት ባለሱቋ ክትክት ብላ ሳቀች ለምን እንደምትስቅ ፊቴን ወደ እሷ ሳዞር ምክንያቱም  እኔ የእብዱ ልጅ እናት ስለሆንኩ እና ደሞ ሰውየው የቀድሞ ባሌ ስለነበር አለችኝ ፊቷን ዞር ብዬ አየውት አይንዋ በርበሬ መስልዋል ደነገጥኩኝ እና በቃ በቃ አታልቅሽ ብዬ ሊላ ቀን መጥቼ ሙሉ ህይወቷን እንድትነግረኝ ጠየኳት ተስማማች። ሴትየዋ እየተርበተበተች  አሁን ይህ አውሬ ሳያይሽ ከእዚህ ጥፊ አለች ኮስተር ብላ።
      
እኔ ደንግጭኤ እሺ በቃ ለማንኛውም  ሲመችሽ እንገናኝ ስላት እሺ ጥሩ ከማታ ውጪ ይመቸኛል አለችኝ በቃ ከዛን አላገኘዋትም ስትል ፅናትም ግራ ገባት ምክንያቱም ፅናት ሊባኖስ ሰውየውን ተከታትላ እዚህ ደረጃ ላይ እንደደረሰች አላወቀችም ነበር። ፅናት ግራ በገባው አሰተያየት ሊባኖስን እያየቻት እንዴ ልቦዬ "ቆይ ይህንን እንዴት አልነገርሽኝም?" ስትላት "እይ ሚጢጢዬ እንዳትጨነቂ ብዬ እኮነው ለማንኛውም የእብዱን እናት ማለትም ባለ ሱቋን ሄደን ስለሁኔታው እንጠይቃታለን" አለች።

ፅናት "እሺ ሊቦዬ እንዳልሽ" አለች እና  ወደ በፀሎት ዞር ብላ "እህቴ አትጨነቂብኝ እሺ በቃ" ብላ ሳመቻት። በፀሎትም "እሺ እህቴ" አለች። ሊባኖስ ወደ ሚያወራው ሬዲዮ ሄዳ ድምፁን እየጨመረች "ቆይ ቆይ ስሙ" አለች። ሬዲዩኑ ስለ 10ኛ ክፍል ፈተና ውጤት መለቀቅ እያወራ ነው። ፅናት "ውይይ ደስ ሲል  በቃ ሊቦ ዛሬ መሽቷል ግን ነገ ስትመጪ እንሄዳለን ኢንተርኔት ቤት  አሁን በቃ ወደ ቤት ሄጂ 2 ሰአት ሊሆን ነው መሸብሽ" አለቻት ሊባኖስም "እሺ የእኔ ሚጢጢዬ በቃ እንቀሳቀስ በፀሎትዬ በይ አንቺም ደና እደሪ" ብላ የበፀሎትን ግንባር ስማት ወጣች ፅናትም ሊባኖስን ለመሸኘት ተከትላት ወጣች።
     
ፅናት ሊባኖስን ሸኝታት ከመጣች ጀምሮ እስከ ለሊቱ 8 ሰአት ድርስ ፅናት ለእህቷ የአና ማስታወሻን ስታነብላት እና ሲያወሩ ሲቀላለዱ በመሀል አንዳቸው ሲፈዙ ቆይተው ተኙ። ጠዋት በራቸው ተንኳኳ በፀሎት ተኝታ አልሰማችም ፅናት ግን ስለሰማች ተነስታ ሻርፕ ፊቷ ላይ ጠምጥማ የውጩን በር ከፈተችው በሩን በጠዋት ያንኳኩት በፀሎት ያን ጊዜ ቤታቸውን የሸጠችላቸው ባልና ሚስት ነበሩ።

ፅናት ስታያቸው ደነገጠች ለምን እንደሆነ ግን አታውቅም ሴቲቷ "ሰላም እኛ  እህትሽን ለማውራት ፈልጌ ነበር የመጣውት" ስትላት ፅናት እህቴ ተኝታለች ልቀስቅሳት?" አለቻት። ሴቲቱ "አይ በቃ ትተኛ ችግር የለም እኛም እምንሄድበት ጉዳይ ስላለን ስንመለስ እንመጣለን " አለቻት። ሰውየው ምንም ቃል ትንፍሽ አላለም። ፅናት "እሺ እነግራታለው ደና ሁኑ በቃ በኋላ እንደምትመጡ ለእህቴ እነግራታለው" ብላ አሰናብታቸው በሩን ዘጋችው።

ሰአቱ ከጠዋቱ 2 ሰአት ነበርና ፅናት በራቸው ላይ ከሰል አቀጣጥላ ቁርስ ሰርታ ስትጨርስ ሻይ ጥዳ በፀሎትን ቀስቅሳ ፊቷን አስታጠበቻት ከዛ ዊልቸር ላይ እንድትሆን እረድታት አስቀመጠቻት ፤ የተኙበትን ፍራሽም አንጥፋ ቁርስ አቀረበች ሻዩ ፈላ ሻዩንም አቅርባ ቁርስ እየበሉ በሩ ተንኳኳ ሄዳ ከፈተችው ሊባኖስ ነበረች። ፅናት ሊባኖስን እንዳየቻት "እንዴ ሊቦዬ እንኳን ደና መጣሽልኝ አዳር እንዴት ነበር አለቻት" ሊባኖስ ኧር ፅናቴ ጥያቄሽን በተራ አርጊው" ብላ ከት ብላ ከሳቀች በኋላ አንዱን ጉንጩዋን ሳም አርጋ አዳር ጥሩ ነበር አለቻት በመቀጠል ሊላኛውን ጉንጯንም ሳም አርጋ እንኳን ደና ቆያችሁኝ አለች" ፅናት በሩን ዘግታ ከሊባኖስ ጋር ተቃቅፈው እቤት ገቡ።
.
.
https://vm.tiktok.com/ZMBXpRexu/

🥀..ከ 150 Like ቡሀላ ክፍል 18 ይቀጥላል ..
         
👍12017
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📌 በኮንፕረሰር (ንፋስ) የሚሰራ መላጫ


“ስራዎት ያቅልሉ " ሳሎዳ ትሬዲንግ

☎️....    ይደውሉ ይዘዙን...  ☎️
@Salodatrading
Contact us:-📞  +251914855557

https://vm.tiktok.com/ZMBGnqBqs/

💬 ማንኛዉም የዕቃ ዋጋ ለማወቅ
@Salodatrading @Salodatrading
4👍3🤬1
.
.
..... 𝐋𝐈𝐊𝐄 𝐒𝐇𝐄𝐑 እያረጋቹቹቹቹ🙏
.
.
 ♥️ ፅናት ♥️...!!!
           .
           .
           .
🥀..ክፍል 18..🥀
          .
          .
          .
#Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው .!!
.
.
አዘጋጅ እና አቅራቢ :- #ከደራሲያን_አለም የቴሌግራም ቻናል
.
.
ሊባኖስም የቤቱን መፅዳት አይታ ኦኦኦኦ ቤቱን ፏ አርገሽዋል የእኔ ሚጢጢዬ አለችና ፍራሹ ላይ ተቀመጠች በፀሎት እንዴት አደርሽ ሊቦትዬ አለች። ፅናት ከት ብላ ስቃ ውይይይ እህቴ ሊቦን እኮ ሊባቲዬ ስትያት ሳቄነው የሚመጣው አለቻት።

ፅናትም ፈገግ ብላ "ኧረ እህቴ ይህን ያክል " አለችና ፈገግ አለች።ሊባኖስም በይ ፅናቴ ቁርስሽን ቶሎ ብይና ውጤትሽን ሄደን እንየው አለቻት። ፅናትም እየተፍለቀለቀች ከሊባኖስ እቅፍ እየወጣች "እሺ ሊቦዬ አንቺ አትበይም?" አለቻት የጠቀለለችውን ጉርሻ ወደ ሊባኖስ እየወሰደች ሊባኖስ "አይ አይ ይቅርብኝ  በልቼ ነው የመጣውት" ስትላት "እሺ ኢቺን ጉረሽና አንድ ስለሚያጣላ እደግምሻለው" ስትል ሊባኖስ "አይ አይ ፅናቴ አንጣላም ግን ስለጣመኝ ድገሚኝ" አለቻት እህቴ በፀሎት በይ በይ ሊቦ ደሞ 3ተኛ ድገሚኝ ብለሽ እዳትደባደቡ " ብላ ሳቀች። ሊባኖስ "አይ  አንቺ ልጅ  በሉ ቶሎ ብሉ እና ሚጢጢዬ እንሂድ አለች።ፅናት ለሁለተኛ ጊዜ ያጎረሰቻትን ምግብ እያኘከች።

ቁርስ በልተው እንደጨረሱ ፅናት ፊቷ ላይ ሻርፕ ጠምጥማ "በቃ ሊቦዬ እንሄድ" አለች።ከዛ ወደ በፀሎት ሄዳ ጉንጮቹዋን ከሳመቻት በኋላ ሻርፕ ፊቷ ላይ እየጠመጠመችላት "እህቴ በቃ እነዛ የቤታችን ገዢዎች ሊያናግሩሽ ይመጣሉ ምን አልባት ካልደረስንባቸው ምን እንዳሉሸ ትነግሪናለሽ" ብላ ከሊባኖስ ጋር ተያይዘው ወጡ።ልክ ፅናት እና ሊባኖስ በር ላይ ሲደርሱ። "ሚስትየው ወዴት ነው?" አለች። ሊባኖስም "መጣን ቅርብ ነን ግቡ በፀሎት አለች" ብላቸው ከፅናት ጋር በጋራ ተያይዘው ወጡ።

የቤቱ ገዢዎች ባልና ሚስትየው "ሰላም ለእዚህ ቤት" ብለው ገቡ። በፀሎትም "ሰላም ኑ ግቡ እንኳን ደህና መጣቹ" አለች።በፀሎት ምን ሊሉኝ ነው ብላ ፈርታለች።ውስጧ ብዙ ነገር ይመላለሳል "ቆይ ቤታችሁን አንፈልግም ብሩን አምጡ ሊሉን ነው እንዴ ብላ አሰበችና ቆይ እንደዛ ቢሉኝ ብር ከየት ላመጣ ነው አይ ጣጣዬ በቃ የራሳቸው ጉዳይ በቃ የፈለጉትን ይበሉ" አለች በውስጧ ካለችበት ሀሳብ የቤቱ ገዢ አባውራ "በፀሎት በፀሎት" እያለ ደጋግሞ ሲጠራት ነው የነቃችው።አአአአቤት አለች። ሰውየው ንግግሩን ቀጠለ እየውልሽ በፀሎት እኛ የእናንተን ቤት ስንገዛ ቤቱ በጣም ያስፈልገን ነበር። አሁን ግን" መልሰው ዝም አለ። በፀሎት ጩከት በተሞላው መልኩ "አሁን ግን ምን አሁን ግን ቤቱ ሰለማያስፈልገን የኖረንበትን አስልተሸ ብሩን ስጭኝ እና ቤታችሁን ውሰዱ ልትሉኝ ነው?እ በሉዋ ተናገሩ" አለች። ሰውየው ፈገግ ብሎ ባለቤቱን አያት ባለቤቱም ፈገግ አለች። በፀሎት ዝምታቸው አስፈራት።

ፅናት እና ሊባኖስ የፅናትን ውጤት ለማየት ኢንተርኔት ቤት ፍለጋ ላይ ናቸው። በመከራ እና በስንት ፍለጋ የሚሰራ ኢንተርኔት ቤት አገኙ። ሁሉም ኢንተርኔት ቤቶች መስራት አልቻሉም ነበር። ሁለቱም  በጣም ጓጉተዋል በጣም ሊባኖስ ወደ ኢንተርኔት ቤቱገብታ "ሰላም የ10ርኛ ክፍል ፈተና ውጤት ለማየት ፈልገን ነበር" አለች።ባለ ኢንተርኔት ቤቱም "እሺ ኑ ቁጭ በሉ"አላቸው። ሊባኖስ ወንበሩን ስባ ተቀመጠችና "በይ የእኔ ሚጢጢ ኮድሽን ንገሪኝ" አለቻት። በፀሎት ግራ ተጋብታ እንዴ ሊቦዬ ስለ ኮንፒውተር ታውቂያለሽ" አለቻት።ሊባኖስም መጠርጠሩስ "በያ ስጭኝ" አለቻት።

በፀሎት  ፈገግ ብላ ሰጠቻት። ሊባኖስም ኮዱን አስገብታ መጠባበቅ ጀመረች ውጤቱ ተዘረገፈ።  ሊባኖስ የፅናትን ውጤት ስታይ ደነገጠች። ወደ በፅናት ስትዞር ፅናት የኢንተርኔት ቤቱ በር ላይ ቆሞ እጆቿን በአፍዋ ጭብጥ አርጋ ሊባኖስን በጭንቀት እና በጉጉት እያየቻት ነው። ፅናት የሊባኖስ የፊት ሁኔታ አስፈራት ሊባኖስ ብድግ ብላ ወደ ፅናት ተጠጋች የሊባኖስ አይኖች በእንባ ተሞልተው ደፍርሰዋል።

ፅናት ልቧ በሀያሉ መምታት ጀምረዋል። ሊባኖስ በነፋስ ፍጥነት ፅናትን አቅፋ  "የእኔ ቆንጆ፤ የእኔ ጠንካራ፤ የኔ ጀግና" አለቻት። ፅናት ግራ ገባት ሊባኖስ የፅናትን እጅ ጨብጣ ከለጠፈችው አፍዋ አላቃ እየጎተተች ወደ ኮምፒውተሩ ወስዳ "ተመልከች ተመልከች ውጤትሽን"  ብላ ወደ ፅናት ስትዞር ፅናት አይኗን ጨፍናላች ሊባኖሰ "እይ የኔ ሚጢጢ" አለቻት ። ፅናት የጨፈነችውን አይኗን ገልጣ ውጤቷን አየችው ፈገግ ብላ የደስታ እንባ እያፈሰሰች  "እ እ እ እ እስስስትሬት ኤ" አለች። ሊባኖስም "አዎ አዎ እስትሬት ኤ ነው ያመጣሽው" አለች አይኗን ከ ኮምፒውተሩ ሳትነቅል ሊባኖስ ወደ ፅናት ጠጋ ብላ ፅናትን አቅፋ "የኔ የሚጢጢ የኔጀግና ጎበዝ እውነት ለመናገር እንደምታልፊም ተስፋ አላረኩም ነበር ማለቴ አለ አደል ባለብሽ ጭንቀቶች በዛ ላይ ሰርተፍኬትሽን እንድወስድልሽ ፈተናዎችሽን እንዳይልሽ ስላልፈቀድሽልኝ አሁን በጣም ጠንካራ እንደሆንሽ አውቄያለው በይ አሁን ወደ እህትሽ እንሂድ እና የምስራቹን እንገራት" አለች። ፅናትም " እሺ ሊቦዬ በቃ እንሄድ" አለች።

ሊባኖስ ኮምፒውተሩ ኪቦርድ ላይ የተቀመጠውን የፅናትን አይዲ ይዛ ለባለ ኮንፒውተሩ ብር ከፈላው  ወደ ቤት መሄዳቸውን ቀጠሉ መንገዱ ረዘመባቸው  በጣም ረዘመባቸው ፅናት እህቷ ፊት ላይ ፈገግታ ማየት ያውም በእራሷ ምክንያት ማየት በጣም  ያስደስታታል ሊባኖስም እንደ ነብሷ የምትወዳቸውን የፅናት እና የበፀሎትን ፈገግታ ከፊታቸው ማየት አለምዋ ነው። በስንት ጉጉት እና ጥድፊያ ቤት ደረሱ ፅናት ሊባኖስን ጥላት  የግቢውን በረ በርግዳ በፍጥነት  ገባች  ከዛም እሮጥ ብላ ጓ ብሎ ከተከፈተው ቤታቸው ስትገባ  ፊት ለፊት ዊልቸር ላይ ተቀምጣ እየተንሰቀሰች የምታለቅስውን እህቷን አየቻት።ደነገጠች ሊባኖስም ደንግጣ ከቆመችው ፅናት እና የፅናት አይን ካረፉባት በፀሎት ፊት  ደረሰች።ሊባኖስ " በፀሎቴ ብላ ከፅናት ኋላ ስትመጣ በፀሎትን ስታይ" ደነገጠች። የቤቱ ገዢዎችም ነበሩ።ሚስትየው ፅናትን በዝምታ እያየቻት ነው። ባለቤቷ ደሞ መሬት መሬቱ አቀረቅሮ እያየ ነው። በፀሎት ዘላ እህቷ ላይ ተጠምጥማ  ወደ ቤቱ ገዢዎች እያፈጠጠች "እህቴን ምን ብላችዋት ነው?"።አለች ዝም አሉዋት ከዛ ሊባኖስም ተደርባ "በሉ መልሱላት እንጂ"እና አፈጠጠችባቸው ።

የሊባኖሰሰ ድምፅ አስበርግጓቸው የባልና ሚስት ትኩረት ሙሉ ለሙሉ ወደ ሊባኖስ ሆነ። በፀሎት "ተይ ተይ ሊባቲዬ አትጩሂባቸው እኔ እማለቅሰው በደስታ  ነው" አለች። ፅናትም አይ አይ እህቴ አትዋሽኝ" አለች። ሊባኖስ ቁጣዋ ሳይበርድ "እየውልሽ አንቺ ልጅ እውነቱን ተናገሪ ብዬሻለው" አለች እና ወደ ሰዎቹ ዙራ "ቆይ ምን ብላቹሀት ነው አትናገሩም እንዴ ቆይ አፋችሁን ምን ያዛቹ" አለች።በጸሎትም "በቃ ሊቦዬ ቤቱን ሰጥተውን ነው በነፃ" አለች።
.
..ክፍል 19 ከ 150 ላይክ ቡሀላ ይለቀቃል..
.
.
🥀 ..ቶሎ እንዲለቀቅ ላይክ ሼር አርጉ ..🥀
         
       
👍22367🤬6
2025/10/28 06:48:23
Back to Top
HTML Embed Code: