ሳታውቅ በስህተት
.
.
ካፌ ተቀምጣ ፥ ጥንዶቹን እያየች
አንተን እያሰበች ፥ ደግሞም እየቀናች
አንዳንድ ጊዜ ጸጉሯን
እነደገና ሀብሏን ፥ በእጇ እየፈተለች
ምናለ በኖረ
ምናለ ባቀፈኝ ፥ ብላ እየተመኘች
ባለችበት ቅጽበት ፥ ባለችበት ሰዐት
አንድ ሶብይ መጥቶ ፥ ወንበሩን ጠየቃት
አንተ እንደው የለህም ፥ ምናለ ቢቀመጥ
ይሄው ተቀመጠ
ሀብል የሚያይ መስሎ
መንታ ጡቶቿ ላይ ፥ አይኑ እንደፈጠጠ
እሱ እንዳንተ አይደለም
እሳት ነው ምላሱ ፥ ወሬ ማያልቅበት
ደቂቃም አልሞላው
ከንፈሯን ሲያስከፍት ፥ ሳቅ ባሕር ሲከታት
ሳታውቀው ነው እሷ ፥ ሳታውቀው በስህተት
ቁጥሯን የሰጠችው ፥ በጠየቃት ቅጽበት
ከዛ በሆነ ቀን…
የሆነችው ሁሉ ፥ የሰራችው ስህተት
አውቃ ነው ፥ አውቃ ነው በድፍረት
ባክህ ይቅር በላት
ያንተን የጀርባ እድፍ ፥ሰይጣን ነው ሹክ ያላት።
(ሰለሞን ሳህለ)
@yegetemmender
@yegetemmender
@yegetemmender
.
.
ካፌ ተቀምጣ ፥ ጥንዶቹን እያየች
አንተን እያሰበች ፥ ደግሞም እየቀናች
አንዳንድ ጊዜ ጸጉሯን
እነደገና ሀብሏን ፥ በእጇ እየፈተለች
ምናለ በኖረ
ምናለ ባቀፈኝ ፥ ብላ እየተመኘች
ባለችበት ቅጽበት ፥ ባለችበት ሰዐት
አንድ ሶብይ መጥቶ ፥ ወንበሩን ጠየቃት
አንተ እንደው የለህም ፥ ምናለ ቢቀመጥ
ይሄው ተቀመጠ
ሀብል የሚያይ መስሎ
መንታ ጡቶቿ ላይ ፥ አይኑ እንደፈጠጠ
እሱ እንዳንተ አይደለም
እሳት ነው ምላሱ ፥ ወሬ ማያልቅበት
ደቂቃም አልሞላው
ከንፈሯን ሲያስከፍት ፥ ሳቅ ባሕር ሲከታት
ሳታውቀው ነው እሷ ፥ ሳታውቀው በስህተት
ቁጥሯን የሰጠችው ፥ በጠየቃት ቅጽበት
ከዛ በሆነ ቀን…
የሆነችው ሁሉ ፥ የሰራችው ስህተት
አውቃ ነው ፥ አውቃ ነው በድፍረት
ባክህ ይቅር በላት
ያንተን የጀርባ እድፍ ፥ሰይጣን ነው ሹክ ያላት።
(ሰለሞን ሳህለ)
@yegetemmender
@yegetemmender
@yegetemmender
Forwarded from አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ) (አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ))
ልክፍት
""""""""
መንገዴን ስራመድ
ስትስቂ አይቼሽ፥ዓይኔ ከዓይንሽ ገጥሞ፤
በግጥምጥሞሹ
"ምን ያፈጣል?" ብለሽ፥ያንቺ እሳቤ ጠሞ...
ዓይኔን ልሰብር ስል
ሲገለማምጠኝ፥ዓይንሽ ልኩን አልፎ፤
ያኔ ነው የጎላሽ
በፍቅር ልቦናዬ
ከአሳሳቅሽ ይልቅ፥ያ ግልምጫሽ ገዝፎ...
አየሽ
አንዳንዴ እንዲ ነው
ከቶ አይታወቅም
የመዋደድ ጭረት፥የመፋቀር መምጫ፤
የድንገት የድንገት
ሲቆራኝ ሲጣበቅ፥ሆኖ እንደ ሙጫ፤
ከጉያው ይከታል
መሳቅ ምንም ሆኖ፥አማሎ ግልምጫ..!
አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@Run_Viva_Run
@HAKiKA1
@HAKiKA1
@HAKiKA1
""""""""
መንገዴን ስራመድ
ስትስቂ አይቼሽ፥ዓይኔ ከዓይንሽ ገጥሞ፤
በግጥምጥሞሹ
"ምን ያፈጣል?" ብለሽ፥ያንቺ እሳቤ ጠሞ...
ዓይኔን ልሰብር ስል
ሲገለማምጠኝ፥ዓይንሽ ልኩን አልፎ፤
ያኔ ነው የጎላሽ
በፍቅር ልቦናዬ
ከአሳሳቅሽ ይልቅ፥ያ ግልምጫሽ ገዝፎ...
አየሽ
አንዳንዴ እንዲ ነው
ከቶ አይታወቅም
የመዋደድ ጭረት፥የመፋቀር መምጫ፤
የድንገት የድንገት
ሲቆራኝ ሲጣበቅ፥ሆኖ እንደ ሙጫ፤
ከጉያው ይከታል
መሳቅ ምንም ሆኖ፥አማሎ ግልምጫ..!
አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@Run_Viva_Run
@HAKiKA1
@HAKiKA1
@HAKiKA1
ስለ አስትሮሎጂ ማወቅ ይፈልጋሉ?
ከሰላሳ አመት በላይ በዚሁ ዘርፍ ላይ ምርምር ያደረጉት የዶክተር አብነት ስሜን አዲስ የ you tube channel Dr abinet sime ብላችሁ search በማድረግ subscribe ያድርጉና ቤተሰብ ይሁኑ። ዶክተር አብነት ከዚ ቀደም በበርካታ የመፅሐፍ ስራቸው ይታወቃሉ በተለይም የኢትዮጵያ ኮከብ በሚል መፅሐፋቸው።
ከሰላሳ አመት በላይ በዚሁ ዘርፍ ላይ ምርምር ያደረጉት የዶክተር አብነት ስሜን አዲስ የ you tube channel Dr abinet sime ብላችሁ search በማድረግ subscribe ያድርጉና ቤተሰብ ይሁኑ። ዶክተር አብነት ከዚ ቀደም በበርካታ የመፅሐፍ ስራቸው ይታወቃሉ በተለይም የኢትዮጵያ ኮከብ በሚል መፅሐፋቸው።
#ይሄን_ታውቂው_ይሆን
.
ኤፊ ማክ
.
የቤቴን መግቢያ በር ፣
አሽሙረኛ አናፂ ፣ ወዳንቺ አቁሞት
ስትወጪ እንደ ፀሀይ ፣
ስትገቢ እንደጀምበር ፣ አያለሁ ባግራሞት
ታውቂው ግን እኔንጃ ፣
ተፈጥሮሽ ካይን ጋር ፣ እንዳለው ቃለ ውል
በሄድሽበት መንገድ ፣
ላፍታ ያየሽ ሁሉ ፣ አብሮሽ እንደሚውል
እንኳን የዘየርሽው ፣
ያኮረፍሺው ቢኖር ፣ እንዴት ሆኖ ሊሆን
የረገጥሽው አፈር ፣
ፍቅርሽ ለደቆሰው ፣ መዳኒት እንደሆን
ይሄን ታውቂው ይሆን?
ከሳቅሽ ሚቀዳው ፣
ካዘንሽ ሚሸመን ፣ የከተማው አየር
እንኳን የቤታችን ፣
የሰፈሩ ጠረን ፣ ባንቺ እንደሚቀየር
ሰንበት አስቀድሰሽ ፣
የቅድስናሽ ልክ ፣ በሰው አፍ ሲተረክ
እንኳን ጎረቤትሽ ፣
ሀገሬው በሙላ ፣ ባንቺ እንደሚባረክ
የማይሆነው ሁሉ ፣ ባንቺ እንደሚሆን!
ይሄን ታውቂው ይሆን?
አድባር እንደሚሉሽ ፣
ጥለት ሲዘቀዘቅ ፣ ሀዘን ቤት ሲጠና
አልቃሽ እና አስለቃሽ ፣
ሀዘንተኛ ሁሉ ፣ ባንቺ እንደሚፅናና
ፍቅር እና ክብር ፣
ሰዋዊ ግብረገብ ፣ በጎደላት አለም
ቅንዝረኛ ወጣት ፣
አየኋትኝ ብሎ ፣ እንደ ሚስለመለም
ኑሮሽ ሲስተካከል ፣
የቀበሌው ኗሪ ፣ ባንቺ እንደሚሸለም
ካንድ እራስሽ አልፈሽ ፣
ከስጡኝ ተላልፈሽ ፣ ስተርፊ ለብድር
አንዴ የማይበላ ፣
የድሃው ሰፈር ሰው ፣ ጠግቦ እንደሚያድር።
የማይሆነው ሁሉ ፣ ባንቺ እንደሚሆን!
ይሄን ታውቂው ይሆን?
አያድርገውና...
ድንገት ወንድ ካየን ፣ እቤትሽ ከትሞ
እኔና መሰሌ ፣
ወር እንደምንተኛ ፣ ጨጓራችን ታሞ
ይሄን ታውቂው ሆን?
አታውቂው ይሆናል ፣ እኔ ግን አውቃለሁ
በጉርብትናዬ...
ወድጄሽ ወድጄሽ ፣ ወድጄሽ አልቃለሁ።
።።።።።።
@Am_in_love
@Am_in_love
@Am_in_love
.
ኤፊ ማክ
.
የቤቴን መግቢያ በር ፣
አሽሙረኛ አናፂ ፣ ወዳንቺ አቁሞት
ስትወጪ እንደ ፀሀይ ፣
ስትገቢ እንደጀምበር ፣ አያለሁ ባግራሞት
ታውቂው ግን እኔንጃ ፣
ተፈጥሮሽ ካይን ጋር ፣ እንዳለው ቃለ ውል
በሄድሽበት መንገድ ፣
ላፍታ ያየሽ ሁሉ ፣ አብሮሽ እንደሚውል
እንኳን የዘየርሽው ፣
ያኮረፍሺው ቢኖር ፣ እንዴት ሆኖ ሊሆን
የረገጥሽው አፈር ፣
ፍቅርሽ ለደቆሰው ፣ መዳኒት እንደሆን
ይሄን ታውቂው ይሆን?
ከሳቅሽ ሚቀዳው ፣
ካዘንሽ ሚሸመን ፣ የከተማው አየር
እንኳን የቤታችን ፣
የሰፈሩ ጠረን ፣ ባንቺ እንደሚቀየር
ሰንበት አስቀድሰሽ ፣
የቅድስናሽ ልክ ፣ በሰው አፍ ሲተረክ
እንኳን ጎረቤትሽ ፣
ሀገሬው በሙላ ፣ ባንቺ እንደሚባረክ
የማይሆነው ሁሉ ፣ ባንቺ እንደሚሆን!
ይሄን ታውቂው ይሆን?
አድባር እንደሚሉሽ ፣
ጥለት ሲዘቀዘቅ ፣ ሀዘን ቤት ሲጠና
አልቃሽ እና አስለቃሽ ፣
ሀዘንተኛ ሁሉ ፣ ባንቺ እንደሚፅናና
ፍቅር እና ክብር ፣
ሰዋዊ ግብረገብ ፣ በጎደላት አለም
ቅንዝረኛ ወጣት ፣
አየኋትኝ ብሎ ፣ እንደ ሚስለመለም
ኑሮሽ ሲስተካከል ፣
የቀበሌው ኗሪ ፣ ባንቺ እንደሚሸለም
ካንድ እራስሽ አልፈሽ ፣
ከስጡኝ ተላልፈሽ ፣ ስተርፊ ለብድር
አንዴ የማይበላ ፣
የድሃው ሰፈር ሰው ፣ ጠግቦ እንደሚያድር።
የማይሆነው ሁሉ ፣ ባንቺ እንደሚሆን!
ይሄን ታውቂው ይሆን?
አያድርገውና...
ድንገት ወንድ ካየን ፣ እቤትሽ ከትሞ
እኔና መሰሌ ፣
ወር እንደምንተኛ ፣ ጨጓራችን ታሞ
ይሄን ታውቂው ሆን?
አታውቂው ይሆናል ፣ እኔ ግን አውቃለሁ
በጉርብትናዬ...
ወድጄሽ ወድጄሽ ፣ ወድጄሽ አልቃለሁ።
።።።።።።
@Am_in_love
@Am_in_love
@Am_in_love
እምላለሁ
.
.
ይኸው ምላለው መስቀሌን ይዤ
ያፈቀረሽን ልቤን ገንዤ።
አልሄድም ካንቺ አልርቅም ከቶ
እንዲህ አይደል ወይ ከማሉ በ ቶ።
ማይክል ሰለሞን
(የቡዜ ልጅ)
@yegetemmender
@yegetemmender
@yegetemmender
.
.
ይኸው ምላለው መስቀሌን ይዤ
ያፈቀረሽን ልቤን ገንዤ።
አልሄድም ካንቺ አልርቅም ከቶ
እንዲህ አይደል ወይ ከማሉ በ ቶ።
ማይክል ሰለሞን
(የቡዜ ልጅ)
@yegetemmender
@yegetemmender
@yegetemmender
እረሳሁሽ በቃ
.
.
ማን ነበረ ስምሽ
ምን አይነት ነው መልክሽ
ከማን ጋር ነበረ
የት ነው ያገኘሁሽ?
ላስታውስ አልቻልኩም
አስሬ ስምሽን ደጋግመሽ ብጠሪም
ምልክት እንዲሆን ገላሽን ብገልጪም
ላስታውስ አልቻልኩም
ትላንትን ብዘፍኚም
ከአዕምሮዬ ቅርጫት
ትዝታ ብትከቺም
ምክንያቱም
.
ምክንያቱም
.
የተረሳ ሁሉ ሚታወስ አይደለም
አንቺዬ ተይ ይቅር
ጩኸትሽ እዚህ ይብቃ
አንቺነትሽ ሲተን
ግብረ ገብ ሲጎልሽ እረሳሁሽ በቃ!!
ተይኝ
ማይክል ሰለሞን
(የቡዜ ልጅ)
@yegetemmender
@yegetemmender
@yegetemmender
.
.
ማን ነበረ ስምሽ
ምን አይነት ነው መልክሽ
ከማን ጋር ነበረ
የት ነው ያገኘሁሽ?
ላስታውስ አልቻልኩም
አስሬ ስምሽን ደጋግመሽ ብጠሪም
ምልክት እንዲሆን ገላሽን ብገልጪም
ላስታውስ አልቻልኩም
ትላንትን ብዘፍኚም
ከአዕምሮዬ ቅርጫት
ትዝታ ብትከቺም
ምክንያቱም
.
ምክንያቱም
.
የተረሳ ሁሉ ሚታወስ አይደለም
አንቺዬ ተይ ይቅር
ጩኸትሽ እዚህ ይብቃ
አንቺነትሽ ሲተን
ግብረ ገብ ሲጎልሽ እረሳሁሽ በቃ!!
ተይኝ
ማይክል ሰለሞን
(የቡዜ ልጅ)
@yegetemmender
@yegetemmender
@yegetemmender
እንባዬን ነው የሳኩት
.
.
በስንብቱ ለት
ከተውሺኝ ቦታ ላይ በሀዘን ታንቄ
ሰላም ግቢ ብዬ ሸኘውሽ በሳቄ።
ስትሰናበቺኝ ስትሄጅ ፈገግ ያልኩት
የደስታ እንዳይመስልሽ እንባዬን ነው የሳኩት።
ሂጅ አልኩሽ
ቻው አልኩሽ
ግን ደሞ ጠበኩሽ
ቻው አልኩሽ
ሂጅ አልኩሽ
ግን ደሞ
መምጣትሽን ስጠብቅ
ሀውልት መሰልኩልሽ።
ሀውልት ትክል ድንጋይ
የማልነቃነቅ
ጊዜ እልፍ ቢል፥
የማልለዋወጥ
የአንድ ዘመን ምስል።
በትላንት የቀረ
ሚባል የነበረ
በመገተር ብቻ
አመት ያስቆጠረ።
ተመልከች እዚጋ
ይህ ነው አፍቃሪነት
እያኖሩ መሞት
ይህ ነው ወዳጅነት
ሌላውን ማካሄድ በተገተሩበት።
የትም ወድቆ መቅረት
በሌላው እንቅፋት።
እናም
ስትሰናበቺኝ
ስትሄጅ ፈገግ ያልኩት
የደስታ እንዳይመስልሽ
ሀዘኔን ነው የሳኩት።
የጤና እንዳይመስልሽ
በጥርሴ ነበረ
እብደት የጀመርኩት።
ማይክል ሰለሞን
(የቡዜ ልጅ)
@yegetemmender
@yegetemmender
@yegetemmender
.
.
በስንብቱ ለት
ከተውሺኝ ቦታ ላይ በሀዘን ታንቄ
ሰላም ግቢ ብዬ ሸኘውሽ በሳቄ።
ስትሰናበቺኝ ስትሄጅ ፈገግ ያልኩት
የደስታ እንዳይመስልሽ እንባዬን ነው የሳኩት።
ሂጅ አልኩሽ
ቻው አልኩሽ
ግን ደሞ ጠበኩሽ
ቻው አልኩሽ
ሂጅ አልኩሽ
ግን ደሞ
መምጣትሽን ስጠብቅ
ሀውልት መሰልኩልሽ።
ሀውልት ትክል ድንጋይ
የማልነቃነቅ
ጊዜ እልፍ ቢል፥
የማልለዋወጥ
የአንድ ዘመን ምስል።
በትላንት የቀረ
ሚባል የነበረ
በመገተር ብቻ
አመት ያስቆጠረ።
ተመልከች እዚጋ
ይህ ነው አፍቃሪነት
እያኖሩ መሞት
ይህ ነው ወዳጅነት
ሌላውን ማካሄድ በተገተሩበት።
የትም ወድቆ መቅረት
በሌላው እንቅፋት።
እናም
ስትሰናበቺኝ
ስትሄጅ ፈገግ ያልኩት
የደስታ እንዳይመስልሽ
ሀዘኔን ነው የሳኩት።
የጤና እንዳይመስልሽ
በጥርሴ ነበረ
እብደት የጀመርኩት።
ማይክል ሰለሞን
(የቡዜ ልጅ)
@yegetemmender
@yegetemmender
@yegetemmender
ሊያወርዱሽ ነው በቃ!!!
.
.
"እንዲህ ነሽ
እንዲያ ነሽ"
እያለ ቢክብሽ
አትስሚ ይቅርብሽ፡፡
ምን ይጎድልብሻል ቃላት ተደራርቶ
ለማርገፍ ነው ትርፉ
ለውበት ሚረገድ ሽለላ ቀርርቶ፡፡
ውሸት ነው አታምሪም ዝም በያቸው ባክሽ
ሊያወርዱሽ ነው እንጂ መች ገባቸው ልክሽ
ልሳን ያለው ሁሉ ሲጠራሽ ለውበት
አቤት ያልሽ ቀን ግን መች ይቆያል እውነት፡፡
ለጠራሽ
ለመራሽ
ለተረከሽ ሁሉ
ትሳሚያለሽ አሉ!!!
ሲሰናዳ እያየሽ
የግጥም ጉባኤ የመወድስ ጥራዝ
የሰማሻቸው ቀን
ከሰማይሽ ወርደሽ አትበልጭም ከኩራዝ
ይቅር አትስሚያቸው
ስንቱን አርገፈዋል ባማረ ቃላቸው?
ቢሉሽ ጀንበርና ኮከብ ወይንም ጨረቃ
ይቅር አትስሚያቸው
ሲክቡሽ ሲስሙሽ ሊያወርዱሽ ነው በቃ፡፡
(ኤልያስ ሽታኹን)
@yegetemmender
@yegetemmender
@yegetemmender
.
.
"እንዲህ ነሽ
እንዲያ ነሽ"
እያለ ቢክብሽ
አትስሚ ይቅርብሽ፡፡
ምን ይጎድልብሻል ቃላት ተደራርቶ
ለማርገፍ ነው ትርፉ
ለውበት ሚረገድ ሽለላ ቀርርቶ፡፡
ውሸት ነው አታምሪም ዝም በያቸው ባክሽ
ሊያወርዱሽ ነው እንጂ መች ገባቸው ልክሽ
ልሳን ያለው ሁሉ ሲጠራሽ ለውበት
አቤት ያልሽ ቀን ግን መች ይቆያል እውነት፡፡
ለጠራሽ
ለመራሽ
ለተረከሽ ሁሉ
ትሳሚያለሽ አሉ!!!
ሲሰናዳ እያየሽ
የግጥም ጉባኤ የመወድስ ጥራዝ
የሰማሻቸው ቀን
ከሰማይሽ ወርደሽ አትበልጭም ከኩራዝ
ይቅር አትስሚያቸው
ስንቱን አርገፈዋል ባማረ ቃላቸው?
ቢሉሽ ጀንበርና ኮከብ ወይንም ጨረቃ
ይቅር አትስሚያቸው
ሲክቡሽ ሲስሙሽ ሊያወርዱሽ ነው በቃ፡፡
(ኤልያስ ሽታኹን)
@yegetemmender
@yegetemmender
@yegetemmender
አዳሜን ሸኝቼ አንቺን ባስቀርለት
ልቤ ቀን ወጣለት
እፎይ
ተቃረብኩ ለሰማይ
ተቃረብኩ ለፀሀይ
በስምሽ ተነቀስኩ በሁለቱም ክንፌ ላይ።
በሁለቱም ክንፌ ላይ ስምሽን ብነቀስ
ገነት ደጃፍ መድረስ
(ገባሁ)
ተጫወትኩ
ተፏገርኩ
ከመላክ ከፃድቃን
በቀልዳችን አዳም በሳቅ እስከሚያለቅስ።
የሰው ልጅ ሲደላው ሲደሰት በነብሱ
አርያም መቅደሱ።
ገባኝ
ደላኝ
ሰፋኝ
ተወለድኩ እንዳዲስ
ከእቅፍሽ ስትከቺኝ።
(ተመስገን)
አዳሜን ሸኝቼ አንቺን ባስቀርለት
ልቤ ቀን ወጣለት።
(የቡዜ ልጅ)
@yegetemmender
@yegetemmender
@yegetemmender
ልቤ ቀን ወጣለት
እፎይ
ተቃረብኩ ለሰማይ
ተቃረብኩ ለፀሀይ
በስምሽ ተነቀስኩ በሁለቱም ክንፌ ላይ።
በሁለቱም ክንፌ ላይ ስምሽን ብነቀስ
ገነት ደጃፍ መድረስ
(ገባሁ)
ተጫወትኩ
ተፏገርኩ
ከመላክ ከፃድቃን
በቀልዳችን አዳም በሳቅ እስከሚያለቅስ።
የሰው ልጅ ሲደላው ሲደሰት በነብሱ
አርያም መቅደሱ።
ገባኝ
ደላኝ
ሰፋኝ
ተወለድኩ እንዳዲስ
ከእቅፍሽ ስትከቺኝ።
(ተመስገን)
አዳሜን ሸኝቼ አንቺን ባስቀርለት
ልቤ ቀን ወጣለት።
(የቡዜ ልጅ)
@yegetemmender
@yegetemmender
@yegetemmender
እስክትመጣ እንጂ....
.
.
የአፍ መፍቻ ቋንቋን
ተክቼበት ሳቋን
ግሱን ተውላጠ ስም
እረሳለሁ ጉንጯን ስስም
የተድፋብኝን ሰማይ
የራቀችኝን ፀሀይ
ድል እነሳታለሁ
ባንድ ቃል አሽንፋለሁ
"ትወደኛለች" እላለሁ::
ስትመጣ
ትናንቴን ጠራርጌ
ወደ ሠርጌ::
የለኝ አዲስ ቋንቋም
እቆማለሁ እንጂ የናፍቆት አቋቋም::
አዲስ ዘመን አበራልኝ
አዲስ ቤቴን አጠረልኝ
(ከየት አገኘልኝ?)
በዓይኖቿ ውበት አቆማለሁ ጊዜ
ስትስመኝ ካወራሁ እሱ ኑዛዜ::
ወይን አያርካው የናፋቂን ጥምስ
እስክትመጣ እንጂ ምን ያርጋል ግጥምስ?
(ኤልያስ ሽታኹን)
@yegetemmender
@yegetemmender
@yegetemmender
.
.
የአፍ መፍቻ ቋንቋን
ተክቼበት ሳቋን
ግሱን ተውላጠ ስም
እረሳለሁ ጉንጯን ስስም
የተድፋብኝን ሰማይ
የራቀችኝን ፀሀይ
ድል እነሳታለሁ
ባንድ ቃል አሽንፋለሁ
"ትወደኛለች" እላለሁ::
ስትመጣ
ትናንቴን ጠራርጌ
ወደ ሠርጌ::
የለኝ አዲስ ቋንቋም
እቆማለሁ እንጂ የናፍቆት አቋቋም::
አዲስ ዘመን አበራልኝ
አዲስ ቤቴን አጠረልኝ
(ከየት አገኘልኝ?)
በዓይኖቿ ውበት አቆማለሁ ጊዜ
ስትስመኝ ካወራሁ እሱ ኑዛዜ::
ወይን አያርካው የናፋቂን ጥምስ
እስክትመጣ እንጂ ምን ያርጋል ግጥምስ?
(ኤልያስ ሽታኹን)
@yegetemmender
@yegetemmender
@yegetemmender
Question of acclamation
(የአድናቆት ጥያቄ ላንቺ/ተ)
፨የቡዜ ልጅ፨
፨አምሮብሻል፦ከማን ጋር ተቀጣጥረሽ ነው ስንት አመት ሙሉ ያላየሁትን መኳኳል ያየሁብሽ?
፨የገላሽ መአዛ ዛሬ ልዩ ነው፦ጠረንሽ ከቀድሞው ተለይቶብኛል የዚህ ጠረን ባለቤት ማነው?
፨ሁሌም እንዲ ሳቂ፦ምን አጊንተሽ ነው?
፨ፀባይ ገዝተሻል እንደድሮው አትጨቃጨቂም፦ችላ ብለሺኛል
፨ስራ ላይ ጎብዘሻል፦ስደውልልሽ ወይም እንገናኝ ስልሽ busy ነኝ ማለት አብዝተሻል፣ከፊቱ የተለየ ስራ ከወዴት መጣ?
@yegetemmender
@yegetemmender
@yegetemmender
(የአድናቆት ጥያቄ ላንቺ/ተ)
፨የቡዜ ልጅ፨
፨አምሮብሻል፦ከማን ጋር ተቀጣጥረሽ ነው ስንት አመት ሙሉ ያላየሁትን መኳኳል ያየሁብሽ?
፨የገላሽ መአዛ ዛሬ ልዩ ነው፦ጠረንሽ ከቀድሞው ተለይቶብኛል የዚህ ጠረን ባለቤት ማነው?
፨ሁሌም እንዲ ሳቂ፦ምን አጊንተሽ ነው?
፨ፀባይ ገዝተሻል እንደድሮው አትጨቃጨቂም፦ችላ ብለሺኛል
፨ስራ ላይ ጎብዘሻል፦ስደውልልሽ ወይም እንገናኝ ስልሽ busy ነኝ ማለት አብዝተሻል፣ከፊቱ የተለየ ስራ ከወዴት መጣ?
@yegetemmender
@yegetemmender
@yegetemmender
እንደውም እግዜር ቢፈቅድ
በቸር በፀጋው ቢቀባኝ
በነጥብ ምልክት አርጎ
ከንፈርሽ ግርጌ ባስገባኝ!
አንቺም መስታወትሽ ፊት
ቀለም ልትቀቢ ከንፈርሽን
እሽኩርምም ፍንድቅ ስትይ
አያለሁና ማፈርሽን፤
ለወዳጅ ዘመድ በሙሉ ማርያም በተኛሽበት
በድንገት እንደሳመችሽ
አወራሽ አይደል?
ይመችሽ!
ሳቂበት የታባቱና
ድመቂ ፍ-ክት ፍክትክት
በማርያም የተመሰልኩት
እኔ ነኝ ያንቺ ምልክት!
እንኳንስ ከንፈርሽ ግርጌ ቢያኖሩኝ ተረከዝሽ ስር
ለመኖር እንዴት ይመቻል
ሳይወደው ከኖረው ህይወት
በፈቃድ የተረገጠ አፍቃሪ መች ይሰለቻል!
ለወዳጅ ዘመድ በሙሉ ማርያም በተኛሽበት
በድንገት እንደሳመችሽ
አወራሽ አይደል?
ይመችሽ!
(አስታወሰኝ ረጋሳ)
@yegetemmender
@yegetemmender
@yegetemmender
በቸር በፀጋው ቢቀባኝ
በነጥብ ምልክት አርጎ
ከንፈርሽ ግርጌ ባስገባኝ!
አንቺም መስታወትሽ ፊት
ቀለም ልትቀቢ ከንፈርሽን
እሽኩርምም ፍንድቅ ስትይ
አያለሁና ማፈርሽን፤
ለወዳጅ ዘመድ በሙሉ ማርያም በተኛሽበት
በድንገት እንደሳመችሽ
አወራሽ አይደል?
ይመችሽ!
ሳቂበት የታባቱና
ድመቂ ፍ-ክት ፍክትክት
በማርያም የተመሰልኩት
እኔ ነኝ ያንቺ ምልክት!
እንኳንስ ከንፈርሽ ግርጌ ቢያኖሩኝ ተረከዝሽ ስር
ለመኖር እንዴት ይመቻል
ሳይወደው ከኖረው ህይወት
በፈቃድ የተረገጠ አፍቃሪ መች ይሰለቻል!
ለወዳጅ ዘመድ በሙሉ ማርያም በተኛሽበት
በድንገት እንደሳመችሽ
አወራሽ አይደል?
ይመችሽ!
(አስታወሰኝ ረጋሳ)
@yegetemmender
@yegetemmender
@yegetemmender
ከቁልምጫህ ካዝና ከሚፈስ እስትንፋስ ሰርሳሪ ድርድሬ
ከነብሴ ተጋብቶ ካካል ውስጠቴ አልፎ የሆነኝ አድባሬ
ካንተነት ልብህ ውስጥ እኔነቴን ከተህ የያዝከኝ በጉያ
ነብስህ ምን ብትልህ ዘላለምን ሰተህ ያረክ ለኔ ማያ
መታደል ካንተ ጋ መጣመር ከልብህ ለኔ ካልከው ርስቴ
ቀን እየቆጠርኩኝ 80 ፍለጋ እንድትለኝ ሚስቴ
አልቆይም ጌትዬ ከልብህ ከሾምከኝ ካምላክ ከተማምልክ
እንኳንስ ዘምንን ቀናትንም አጥፈህ ንጉስ ራሴ በሆንክ
1/4/2017❤️❤️❤️
https://www.tg-me.com/Tinasview23
https://www.tg-me.com/Tinasview23
https://www.tg-me.com/Tinasview23
ከነብሴ ተጋብቶ ካካል ውስጠቴ አልፎ የሆነኝ አድባሬ
ካንተነት ልብህ ውስጥ እኔነቴን ከተህ የያዝከኝ በጉያ
ነብስህ ምን ብትልህ ዘላለምን ሰተህ ያረክ ለኔ ማያ
መታደል ካንተ ጋ መጣመር ከልብህ ለኔ ካልከው ርስቴ
ቀን እየቆጠርኩኝ 80 ፍለጋ እንድትለኝ ሚስቴ
አልቆይም ጌትዬ ከልብህ ከሾምከኝ ካምላክ ከተማምልክ
እንኳንስ ዘምንን ቀናትንም አጥፈህ ንጉስ ራሴ በሆንክ
1/4/2017❤️❤️❤️
https://www.tg-me.com/Tinasview23
https://www.tg-me.com/Tinasview23
https://www.tg-me.com/Tinasview23
Telegram
ትህትናዊ✍️እይታ📷...Tina's view
ቻናሉን ይቀላቀሉና ገቢራዊ ምስሎችን ከ ግጥሞቼ ጋር ይታደሙ
For any suggestions and comment
@onTinu
For any suggestions and comment
@onTinu
Forwarded from ትህትናዊ✍️እይታ📷...Tina's view
ጨረቃ በደመና እኔ ባንተ መንግስት ተከልለን ስኖ'ር
ደማቅ ባለህብር ስውርውር አድርጎ ካለ'ም በሚሰውር
ግና.....
መች ሊያሻን ፀሃዩ ገላ ደጅ ዘርጊ አካል የሚያሳጣ
እኔና ብርሃኔ ልብህ ይበቃናል ማየ ፍቅር ሚያጥጣ
አባይ ና' ጣና ተዛምደው ሲወርዱ በሥሥት ትስር'ስር
ሲያኖረኝ አምላኬ ከማተብ ቃህ'ጋ ካንተነትህ እቅፍ'ስር
ኑርልኝ ያ'የኔ ብዬ ልመካብህ ስወጣ ስገባ ለሚያየኝ ላርዳበት
ዘላለም ወስደኸኝ በስምህ ስጠራ ወዳጅህ ወዳጄ ልቡ እንዲቆርጥለት
🧚❤️🧚❤️🧚❤️
ለምወድህ 6/4/2017
በፍቅር የተከተበ ✍️🧚❤️
https://www.tg-me.com/Tinasview23
https://www.tg-me.com/Tinasview23
https://www.tg-me.com/Tinasview23
ደማቅ ባለህብር ስውርውር አድርጎ ካለ'ም በሚሰውር
ግና.....
መች ሊያሻን ፀሃዩ ገላ ደጅ ዘርጊ አካል የሚያሳጣ
እኔና ብርሃኔ ልብህ ይበቃናል ማየ ፍቅር ሚያጥጣ
አባይ ና' ጣና ተዛምደው ሲወርዱ በሥሥት ትስር'ስር
ሲያኖረኝ አምላኬ ከማተብ ቃህ'ጋ ካንተነትህ እቅፍ'ስር
ኑርልኝ ያ'የኔ ብዬ ልመካብህ ስወጣ ስገባ ለሚያየኝ ላርዳበት
ዘላለም ወስደኸኝ በስምህ ስጠራ ወዳጅህ ወዳጄ ልቡ እንዲቆርጥለት
🧚❤️🧚❤️🧚❤️
ለምወድህ 6/4/2017
በፍቅር የተከተበ ✍️🧚❤️
https://www.tg-me.com/Tinasview23
https://www.tg-me.com/Tinasview23
https://www.tg-me.com/Tinasview23
Forwarded from ትህትናዊ✍️እይታ📷...Tina's view
ለሃሙስ መዳረሻ ከረቡ ላይ ያለችን ጨረቃ ማፍቀር በምናብ አብሮ መንሳፈፍ የልብ ንፅህናን የስሜት መስከን ሲዋሃድ ያለው ውበት አቤት አቤት አጃኢብ ነው 😍😘😍
Forwarded from ትህትናዊ✍️እይታ📷...Tina's view
አበባየ ከልብ ስር የሰፈረች መልክ ውበቷ የሚያሳሳ
ፍቅር ሽታ መውደድ ናፍቃ ለስ'ሯ ዳስ ልትቀልስ ስትነሳ
ምድር ቀናች ሸሸት ራቅ መዋቲ ገል ምን ሊረባ
ዳና ሰሪ ነገን አፍሪ ያ ልብ ነው የልባም ሰው የሚባባ የሚያረባ
በጋሽ ቴዎድሮስ ካሳ የተነሳ የተፃፈ
9/4/17
ፍቅር ሽታ መውደድ ናፍቃ ለስ'ሯ ዳስ ልትቀልስ ስትነሳ
ምድር ቀናች ሸሸት ራቅ መዋቲ ገል ምን ሊረባ
ዳና ሰሪ ነገን አፍሪ ያ ልብ ነው የልባም ሰው የሚባባ የሚያረባ
በጋሽ ቴዎድሮስ ካሳ የተነሳ የተፃፈ
9/4/17