Telegram Web Link
መዝሙር 15
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ አቤቱ፥ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል? በተቀደሰውም ተራራህ ማን ይኖራል?
² በቅንነት የሚሄድ፥ ጽድቅንም የሚያደርግ፥ በልቡም እውነትን የሚናገር።
³ በአንደበቱ የማይሸነግል፥ በባልንጀራው ላይ ክፋትን የማያደርግ፥ ዘመዶቹንም የማይሰድብ።
⁴ ኃጢአተኛ በፊቱ የተናቀ፥ እግዚአብሔርንም የሚፈሩትን የሚያከብር፥ ለባልንጀራው የሚምል የማይከዳም።
⁵ ገንዘቡን በአራጣ የማያበድር፥ በንጹሑ ላይ መማለጃን የማይቀበል። እንዲህ የሚያደርግ ለዘላለም አይታወክም።
“አቤቱ ጕልበቴ ሆይ፥ እወድድሃለሁ።”
— መዝሙር 18፥1
የጌታችን መወለድ
የነፃነት ድምፅ
የህይወት ተስፋ
የእረፍት ምልክት ነው።

እንኳን ለብርሀነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ!! ❤️❤️❤️
ተግባራዊ ክርስትና

ፀሎት ብቻ አይደለም
ስግደትና ፆም ብቻ አይደለም

ተግባራዊ ክርስትና ከሰዎች ጋር ያለን ግንኙነትና ህይወትም ጭምር ነው። ብዙዎቻችን በውስጣችን ቂም አዝለን ከሰው ተጣልተንና ለሰው ፍቅር ሳይኖረን በፀሎትና ፆም ብቻ ክርስትናችንን የተገበርን ይመስለናል።

እግዚአብሔር አምላክ ይህንን አይወድም ቅዱስ ዮሀንስም በመልእክቱ "የሚታየውን ወንድምህን ሳትወድ የማይታየውን እግዚአብሔር እወዳለሁ ትላለህን? ይለናል።

ጌታችንም እንዲሆናችሁ "መፅሀፍትን ትመረምራላችሁ እነሱም ስለኔ ይናገራሉ ግን ህይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ወደኔ ልትመጡ አትወዱም።" ይለናል ይህ ቃል ምንድን ነው?

ጠቢብ ነን ምሁር ነን ብዙ አንብበናል ብዙም ነገር አውቀናል ክርስትና ገብቶናል ምዕመኖቻችንን ከመናፍቃንና ከአህዛብ እንጠብቃለን የሚሉ ክርስቲያኖች ህይወታቸው እንዴት ነው?

ከወንድማቸው ከክርስቲያኑ ጋር ያላቸው ግንኙነትስ? እውቀታቸው ትምክህት ሆኖባቸው ፀጋቸው መታበያ ሆኖባቸው እግዚአብሔር ፀጋና እውቀቱን የነጠቃቸው ሰዎች ቀላል አይደሉም።

እግዚአብሔር የልብን መታደስ የሚፈልግ አምላክ ነው ልብና ኩላሊትም ሚመረምረው ጌታ ከኛ ትህትናን ራስን ዝቅ ማድረግንና እንደ ቃሉ መመላለስን ይፈልግል።

ይሄን ስናደርግ ፀሎታችንም ፆማችንም ዝማሬያችንም ይሰማል መላእክትም ከበፊቱ በበለጠ መልኩ ያግዙናል ይራዱናል።🙏🙏
የአዳዲስ የተዋህዶ መዝሙሮችን በየእለቱ የሚለቅላችሁ የተዋህዶ ቻናል

የተዋህዶ መዝሙሮች ቤት
ይቀላቀሉን

@eotcholysong
“ከቃልህ የተነሣ ትጸድቃለህና ከቃልህም የተነሣ ትኰነናለህ።”
— ማቴዎስ 12፥37
መዝሙር 20
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በመከራ ቀን እግዚአብሔር ይስማህ፤ የያዕቆብ አምላክ ስም ያቁምህ።
² ከመቅደሱ ረድኤትን ይላክልህ፥ ከጽዮንም ያጥናህ።
³ ቍርባንህን ሁሉ ያስብልህ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትህን ያለምልምልህ።
⁴ እንደ ልብህ ይስጥህ፤ ፈቃድህንም ሁሉ ይፈጽምልህ።
⁵ በማዳንህ ደስ ይለናል፤ በአምላካችን ስም ከፍ ከፍ እንላለን፤ ልመናህን ሁሉ እግዚአብሔር ይፈጽምልህ።
⁶ እግዚአብሔር የቀባውን እንዳዳነው ዛሬ አወቅሁ፤ ከሰማይ መቅደሱ ይመልስለታል በቀኙ ብርታት ማዳን።
⁷ እነዚያ በሰረገላ እነዚያም በፈረስ ይታመናሉ፤ እኛ ግን በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም ከፍ ከፍ እንላለን።
⁸ እነርሱ ተሰነካክለው ወደቁ፤ እኛ ግን ተነሣን፥ ጸንተንም ቆምን።
⁹ አቤቱ፥ ንጉሥን አድነው፥ በጠራንህም ቀን ስማን።
“ፍቅራችሁ ያለ ግብዝነት ይሁን። ክፉውን ነገር ተጸየፉት፤ ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ፤”
— ሮሜ 12፥9
የድንግል ማርያም እረፍት
ኢትዮጵያዊው ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ አርጋኖን ድርሰቱ ከሚያሰጥመው ባሕር ሞገድ የተነሣ የማትነቀነቅ፥ መልኅቆቿም በሦስቱ ሥላሴ ገመድ የተሸረቡ ናቸው ይህቺ ደግሞ ከነፋሳት ኃይል የተነሣ የማትናወጥ በጭንጫ ላይ ያለች የዕንቈ ባሕርይ ምሰሶ ናት፤ እርሷን የተጠጋ መውደቅ መሰናከል የለበትም” የሚላት እመቤታችን ሞት አይቀርምና እርሷም እንደሰው የምትሞትበት ጊዜ ደረሰ፡፡ እግዚአብሔር አያዳላምና፡፡ /ሮሜ.፪፥፲፩/2፥11/ ቅድስት ድንግል ማርያም የኃያሉ እግዚአብሔር እናቱ፥ መቅደሱ፥ ታቦቱ፥ መንበሩ ሆና እያለ ሞትን መቅመሷ በራሱ የሚያስገርም ምሥጢር ነው፡፡ ከቤተ ክርስትያን ወገን ሞትን እንዳያዩ የተወሰዱ ቅዱሳን ሄኖክ፥ ኤልያስ፥ ሌሎችም እንዳሉ የቅዱሳት መጻሕፍት ምስክርነት አለ፡፡ ይህ ከኅሊናት ሁሉ በላይ የሆነው ምሥጢር ርቀቱ በመጽሐፈ ዚቅ እንዲህ ተብሏል፡፡ “ለምንት ይዜኃር ኃያል በኃይሉ ወባዕል በብዝኃ ብዕሉ ኢያድለወ  ሞት ክርስቶስ ለሥጋ አባሉ ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ፡፡ ኃይለኛ በኃይሉ ለምን ይታጀራል? ባለ ጸጋም በሀብቱ ብዛት፡፡ ክርስቶስ ለአካሉ አላዳላም፤ ሞትስ ለሟች ይገባዋል የእመቤታችን የቅድስት ማርያም ሞት ግን አስደናቂ ነው”
እመቤታችን ያረፈችው በጥር ሃያ አንድ ቀን ነው፤ በአባት በእናቷ ቤት ሦስት ዓመት ኖረች፤ ዐሠራ ሁለት ዓመት በቤተ መቅደስ ኖረች፤ ከልጇ ጋር ሠላሣ ሦስት ዓመት ከሦስት ወራት፤ ከጌታ ስቅለት በኋላ ዐሥራ አምስት ዓመታት ኖረች፤ ጌታን የጸነሰችበትን ወራት ስንጨምር በዚህ ዓለም በሥጋ የቆየችበት ጊዜ ስድሳ አራት ዓመት ይሆናል፡፡
የቤተ ክርስቲያን ትውፊት የድንግል ማርያም ሞት በሚከተሉት ምክንያቶች እንደሆነ ያስረዳል፤ የመጀመሪያው “ለመለኮት ማደርያ ለመሆን የበቃችው ኃይል አርያማዊት ብትሆን ነው እንዷ ምድራዊት ሴትማ እንደምን ሰማይና ምድር የማይችለውን ልትሸከመው ይቻላታል?” የሚሉ ወገኖች ነበሩና በርግጥም እግዚአብሔር ወልድ የተዋሐደው የሰው ልጆችን ሥጋ እንጂ የመላእክትን አለመሆኑን ለማጠየቅ ነው፡፡ ይህንን ሁኔታ ቅዱስ ጳውሎስ ሲያስረዳ “እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥በሕይወታቸው ሁሉ ስለሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ፡፡ የአብርሃምን ዘር ይዟል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም” አለ፡፡ /ዕብ.፪፥፲፬-፲፭/2፥14-15/ በዚህም ድንግል ማርያም የአዳም ዘር መሆኗ ታወቀ፡፡ ሁለተኛው ቅዱስ ያሬድ እንዳለው ጌታችን በፍርዱ አድልዎ የሌለበት መሆኑ ይታወቅ ዘንድ ነው፡፡ ሥጋ የለበሰ ሁሉ በለበሰው ሥጋ ሞትን ይቀምስ ዘንድ የግድ ነውና፡፡ ይህን በማስመልከት ጥር 21 አንድ ቀንን የእመቤታችንን እረፍት እናከብራለን።

ወስባሐት ለእግዚአብሔር..
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
🌺🌺 እንኳን አደረሳችሁ !! 🌺🌺
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
1ኛ ዮሐንስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁸ ልጆቼ ሆይ፥ በሥራና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት አንዋደድ።
¹⁹-²⁰ ልባችንም በእኛ ላይ በሚፈርድበት ሁሉ፥ ከእውነት እንደ ሆንን በዚህ እናውቃለን በፊቱም ልባችንን እናሳርፋለን፥ እግዚአብሔር ከልባችን ይልቅ ታላቅ ነውና ሁሉንም ያውቃል።
²¹ ወዳጆች ሆይ፥ ልባችንስ ባይፈርድብን በእግዚአብሔር ዘንድ ድፍረት አለን፥
²² ትእዛዙንም የምንጠብቅና በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን የምናደርግ ስለሆንን የምንለምነውን ሁሉ ከእርሱ እናገኛለን።
²³ ትእዛዚቱም ይህች ናት፥ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናምን ዘንድ፥ ትእዛዝንም እንደ ሰጠን እርስ በርሳችን እንዋደድ ዘንድ።
²⁴ ትእዛዙንም የሚጠብቅ በእርሱ ይኖራል እርሱም ይኖርበታል፤ በዚህም በእኛ እንዲኖር ከሰጠን ከመንፈሱ እናውቃለን።
“ልጆቼ ሆይ፥ በሥራና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት አንዋደድ።”
— 1ኛ ዮሐንስ 3፥18
#ልብ ያለው #ልብ ብሎ ያስተውል"!!!

#አትማኝ፦ እንደ አዳም የዲያቢሎስ ባርያ ትሆናለህ፡፡ #ዘፍጥ 3፥1-8
#አትቅና፦እንደ ቃኤል ወንድምህን ትገላለህ፡፡ #ዘፍጥ 4÷1-8
#አትስከር፦አእምሮ አሳጥቶ የማይገባ ስራ ትሰራለህ፡፡
#ዘፍጥ 19÷30-38
#አለምን አትመልከት፦እንደ ሎጥ ሚስት የጨው ዐምድ ሆነህ ትቀራለህ፡፡ #ዘፍጥ 19÷22-23
#በአባትህ አትሳቅ፦እንደ ካም ትረገማለህ፡፡ #ዘፍጥ 9÷20
#እልከኛ አትሁን፦ እንደ ፈርፆን ትሰጥማለህ፡፡ #ዘፀ 14÷28
#በሀሰት አትመስክር፦እንደ ሐማ ባዘጋጀኸው ጉርጓድ ትገባለህ፡፡
#መጽ አስቴ 7÷1
#ትዕቢተኛ አትሁን፦እንደ ሰናክሬም ትወድቃለህ፡፡ #2ነገ 19÷35
#ክፉ ባልንጀራን አትያዝ፦ እንደ እንደ ሳምሶን በጠላትህ እጅ ትወድቃለህ፡፡ መጽ.#መሳ 16÷15
#አትዘሙት፦እንደ ሰሎሞን አምላክህን አስረስቶ ጣፆትን እንድታመልክ ያደርግሀል፡፡
#1ነገ 11÷1-8
#ስልጣንን አትውደድ፦ እንደ አቤሴሎም በአባትህ ላይ ትነሳለህ፡፡
#2ነገ ሳሙ 15÷13-17
#ገንዘብን አትውደድ፦እንደ ይሁዳ ጌታን ያስክድሀል ፡፡ #ማቴ 26÷ 14÷16
ሁላችሁም የተዋህዶ ልጆች ይህንን ምስል ፕሮፋይላችሁ በማድረግ የቤተክርስቲያንን ሀዘንና ስብራት እንግለፅ።

በፆመ ነነዌም ሙሉ ጥቁር ልብስ በመልበስ በፆም በፀሎት ስለ ቤተክርስቲያናችን ወደ እግዚአብሔር እንጩህ። 🙏🙏😔
2025/07/01 14:45:39
Back to Top
HTML Embed Code: