Forwarded from Jafer Books 📚
♻️ ጠበኛ እውነቶች ♻️
በሜሪ ፈለቀ
ይህ መፅሐፍ በ4 ክፍሎች የተከፈለ ልብወለድ ሲሆን የተለያዩ ማህበራዊ እና ግላዊ ሕይወትን የሚዳስስ መፅሐፍ ነው።
❶ ቅዳሴና ቀረርቶ
'' እውነታው ሰዎች ሊያወድሱህ ከፈለጉ ከፈጣሪ ታናሽ
ያደርጉሃል። ሊዘልፉህ ከፈለጉ ደግሞ ሳጥናኤል የሚቀናበት ክፍ ያደርጉሀል። ከሰማሃቸው ደግሞ ራስህን የመሆን እድል አይሰጡህም። ሁሉም በፈለጉት
መንገድ ሊቀርፁህ መጥረቢያ ይስላሉ። ልብህን ከከፈትክላቸው የየድርሻቸውን ጠርበውህ ቅርፅ አልባ ያደርጉሃል።''
❷ ቀላውጦ ማስመለስ
''ሲገባኝ ሁሉም ሰው የሆነች የለውጥ ኩርባአላቸው''።
አስተሳሰቡ ወደ ስሜቱ ወደ ድርጊቱ የሚቀየርበት። ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚታጠፍበት ወይም
ከወደቀበት መቀመቅ የሚስፈነጠርበት ወይም ለዛለው ጉልበቱ የሚያገኝበት።''
❸ ''እናቴን ተመኘኋት
በተለያየ መኝታ በተለያዩ እንቅልፍ ውስጥ አንድ አይነት ህልም እንዴት ይታለማል? የሆነ ሰው ያለፈበት መንገድ እና የደረሰበት ስኬት እንዴት የሌሎች ብዙዎች መንገድና መድረሻ ይሆናል? የሌሎች ብዙዎች ደስታ በአንድ ሰው መድረሻ እንዴት ይፈጠራል?"
❹ ምርጫ አልባ ምርጫ
''ሁሌም ዛሬ ላይ ቆመህ ሁለት ምርጫ አለህ። ትናንት ወይም ነገ፤ትዝታ ወይም ተስፋ!''
''ብሩህ ነገ የሚባል ቀን የለም። ማንም ቢሆን ነገን ኖሮ የሚያውቅ የለም። ምክንያቱም ነገን ለመኖር ስንጀምር ዛሬ ተብሏል። ብዙዎቻችን ግን ሁሌም ብሩህ ነገን ለመኖር ስንናፍቅ ብዙ ዛሬያችን ያልፈናል። እኛም ብሩህ የሚባል ቀን ሳይኖረን እናልፍለን። ብሩህ ቀን በእጃችን ያለው ዛሬ ነው።''
🎀 ሜሪየ የእውነት የስነ ፅሁፍ አተራረክሽንና ችሎታሽን አይቼ ባላየ ባልፍ ንፉግነት ስለመሰለኝ ከወንበሬ ብድግ ብየ አመስግኜሻለሁ ። “

👍12😁1
ልንጋባ ሁለት ሳምንት ሲቀረን እጮኛዬ ጤነኛ እንዳልሆነ አወቅኩ (ክፍል ስድስት)
"በፍፁም እኔ አይኔ እያየ የሀብትህ ተካፋይ አታደርጋትም!" ብላ ያዙኝ ልቀቁኝ አለች እህትየው።
"ለምን?" አላት ኮስተር ብሎ
"ይሄን እንዴት ማየት ያቅትሃል? አትወድህም!" ብላ ተንጨረጨረች። ቀና ብሎ ትርጉሙ ያልገባኝ አስተያየት አይቶኝ
"ንብረቱ የኔ አይደል? እኔ ልወስንበት! አይሻልም እህቴ? " ብሏት
ምንም የሚቆረፍድ ነገር እንዳልተወራ እኔም እንዳልሰማሁ አስመስሎ የበረዶ ሸርተቴ ልንጫወት እኔና እሱ ልብሳችንን ደራርበን እቃዎቹን መጫን ጀመርን።
ልንጋባ ቀን ቀጥረን ነው። የጋብቻ ውህደቱ ላይ እኔን ከማግባቱ በፊት ያፈራው ንብረት ተካፋይ እንዳልሆን እህትየው ወጥራ የምትሟገተው።
እውነት ለማውራት ይሄን ጉዳይ አላሰብኩትም ነበር። ከሀገሬ ስመጣም የመኖሪያ ፈቃድ ማግኘት ከዛ ልጄን ማምጣት ከዛም ለዓመታት ስቋምጥ የነበረውን ትምህርት መማር ከዛ ቤተሰቤን መርዳት በእርሱ ሀብት ከእርሱና ከልጄ ጋር በድሎት ስለመኖር እንጂ ብፋታው ወይ እሱ የሆነ ነገር ቢሆን ስለሚለው አስቤ አላውቅም። ቢሞትስ ብዬም ያሰብኩ ጊዜ ስለ መኖሪያ ፈቃዴ እንጂ ስለሀብቱ ሽውም አላለኝ:: ሳልዋሽ ግን የእህትየው መንገብገብ እልህ አስያዘኝ።
"እህትህ አትወደኝም!" አልኩት የበረዶ መናሸራተቻውን ጫማው ላይ እየሰካን። መናሸራተቱን ከዚህ በፊት ሁለቴ ሞክሬው ሁለቴም ወድቄ እግሬን ተጎድቻለሁ። ዛሬ ለኔ ብዬ ሳይሆን እርሱን ደስ እንዲለው ነው አብሬው የወጣሁት። ሰሞኑን ብዙ ነገር ለእርሱ ብዬ እያደረግኩ ነበር:: አላውቅም:: ብቻ ደህና እንዲሆን እፈልጋለሁ::
"አንቺን ስለማትወድሽ አይደለም እኔን ካንቺ በላይ ስለምትወደኝ የተጠነቀቀችልኝ መስሏት ነው!" አለኝና አወሳሰበብኝ።
"እኔ ስለንብረትህ አስቤ አላውቅም ታምነኛለህ? እሷ እንዳለችው ብታደርግም ቅር አይለኝም" አልኩት።
"አምንሻለሁ። እውነቱን ሳወራሽ እሷ ጉዳዩን እስካነሳችበት ሰዓት ድረስ እኔም ብንለያይ ወይም ብሞት የሚለውን አስቤው አላውቅም!" አለኝ
መንሻራተቱን ጀምረነው ስለነበር መደነቃቀፌን ጀመርኩ። ቁልቁላቱ ላይ ልንደርስ ስንቃረብ ከነመንሸራተቻዬ አዝሎኝ ቁልቁለቱን ተምዘገዘገ። እጮሃለሁ .....ይስቃል ...... እስቃለሁ ደግሞ እጮሃለሁ። የሚያየን ሰው ፈገግ እያለ .... የሚያውቁት ደግሞ ሰላም እያሉት እንተላለፋለን። ቁልቁለቱን ስንጨርስ ተያይዘን በረዶው ላይ ወደቅን።
ከብዙ ቀናት በኋላ ጥርሱ እየታየ ሳቀ:: ክፉ ደግ እንደማያውቅ ህፃን ፍልቅልቅ ብሎ ሳቀ!! ኩርምት ብሎ አራት ሳምንት ጉልበቱን አቅፎ እንዳልተኛ ሰው ሳቀ ........ ከአራት ሳምንት በፊት ራሱን ሊያጠፋ እንዳልነበረ ሰው ሳቀ .........
ድንገት ሳቁን አቁሞ ደንግጦ እያየኝ "ምነው ምንሆነሻል?" ሲለኝ ነው ሳቁን እያየሁ እንባዬ ሳያስፈቅደኝ ጉንጬ ላይ እየተንከባለለ እንደሆነ ያወቅኩት
"ምንም አልሆንኩም ደስ ብሎኝ ነው። የደስታ እንባ ነው አልኩት::" እንባዬን እየጠረግኩ።
ገብቶታል። ፈገግ እያለ እጄን ተቀብሎኝ ውስጥ እጄን ሳመልኝ።
"አፈቅርሻለሁ!" አለኝ እጄን ደጋግሞ እየሳመ። ዝም አልኩት። ከዚህ በፊትም እንዲህ ሲለኝ ምንም መልሼለት አላውቅም። እንድመልስለትም ጠብቆ አያውቅም። ዛሬ ታዲያ ለምን ጨነቀኝ? ለምን የበደለኝነት ስሜት ይሰማኛል? ልቤ ላይ አየር ያጠረኝ አይነት የማፈን ስሜት .... ልነግረው ነበር .... ምን እንደሚሰማኝ አላውቅም ልለው ..... እህትህ ያለችው እውነቷን ነው ልለው ..... አላፈቅርህም ነበር አሁን ግን ላፍቅርህ አላፍቅርህ አላውቅም ልለው ነበር ....... አፌን ስከፍት ቶሎ ብሎ በሌባ ጣቱ ከንፈሬን ከደነው
"ተይ እንዳትይኝ!" አለኝ ዝም አልኩትና ከንፈሬ ላይ የጫነውን ጣቱን ስሜው
"እሺ እንነሳ!" አልኩት። ተመልሰን መኪናችንጋ እስክንደርስ ምንም ሳናወራ እሱ በመንሸራተቻው እኔ በጫማዬ ተጓዝን። እቤት ደርሰን ሻወር ሊወስድ ሲገባ እህቱ ሳሎን ተቀምጣ መፅሃፍ እያነበበች ነበር። አጠገቧ ተቀመጥኩ። ምን እንደምላት አስቀድሜ ያሰብኩት ነገር አልነበረም።
"ቃል እገባልሻለሁ እሱን የሚጎዳ ምንም ነገር አላደርግም!" አልኳት። የሆነ ከአፌ እስኪወጣ እየጠበቀችው ያለ ነገር ይመስል ስግብግብ ብላ ተጠመጠመችብኝ።
"አመሰግናለሁ። አመሰግናለሁ ። አመሰግናለሁ" ብዙ ጊዜ አለችኝ ጭምቅ አድርጋ ይዛኝ።
ቤተክርስቲያን ፀሎት አድርሶ አንደሚመለስ ሰው ያለ ስሜት ...... ለካህን ሀጢያቱን ተናዞ እንደሚመለስ ሰው ያለ ስሜት ..... ተቀበለኝ። ወደ መኝታ ቤት እየሄድኩ ለእሷ ያልኳትን ለራሴ ደጋግሜ እያልኩ ነበር
"ምንም ቢሆን የሚጎዳው ነገር አላደርግም!!" ከኋላዬ ገብቶ የመኝታ ቤቱን በር ሲዘጋው ወደርሱ ዞርኩ። ፎጣውን ወገቡ ላይ አሸርጦ የረጠበ ፀጉሩን ወደ ኋላ እየላገ በስድ አይን እያየኝ ነበር። እንዲህ ካየኝ መቼ ነበር? ወር? ስድስት ሳምንት? እኔንጃ ..... ዘልዬ እጄን አንገቱ ላይ ጠምጥሜ በእግሬ ወገቡን ዞርኩት። "
ምንም ቢሆን የሚጎዳህ ነገር አላደርግም እሺ!" እያልኩት አንገቱን .... ትከሻውን .... ጸጉሩን ... ጆሮውን ያገኘሁትን ቦታ እስመዋለሁ! ያልኩበት ስሜት ገብቶት ይሁን አላውቅም እየደጋገመ
"አውቃለሁ! አውቃለሁኮ" ይለኛል። መልሼ ነግረዋለሁ መልሶ "አውቃለሁ" ይለኛል።
ያሸረጠው ፎጣ ተፈታ (አይበቃችሁም እንዴ ምንድነው?) ለፍተን በጀርባችን እንደተጋደምን።
"ፔሬድሽ መምጣት አልነበረበትም?" አለኝ:: ቆጠርኩ .....ከተጋደምኩበት ብንን እንዳለ ሰው ተስፈንጥሬ ተነሳሁ
"ኦህ ኖ !" አልኩኝ። ተስፈንጥሮ ተነሳ
"በፍፁም! በፍፁም አይሆንም! በፍፁም እንደእኔ አይነት ልጅ እንዲወለድ አልፈልግም።" እንዲህ ጮሆብኝ አያውቅም። ሁኔታው አስደነገጠኝ!!
ህመሙ በዘር እንደሚተላለፍ ያነበብኩት ትዝ አለኝ።
እህእ አልጨረስንማ ታዲያ

👍20
እኔን የሆነው ማነው?
መፅሃፌ የወጣ ጊዜ ሰይፉ ፍንታሁን ሾው ላይ ሊያቀርበኝ ጠርቶኝ ነበር:: ለምን እንቢ እንዳልኩት አስረዳችኃለሁ .... በሰዓቱ እንደምታውቁት 'እንተዋወቃለን ወይ' ራሱ ሃና ጠርታኝ ገፀባህርያቶቹ የመጀመሪያ ቀን ምን አደረጉ ብትለኝ ደስታዬ ነበር 🤣🤣
(የመጀመሪያ መፅሃፉን ያሳተመ ደራሲ አለም በሱ መፅሃፍ ዛቢያ እንደምትዞር ማመኑ በኔ አልተጀመረም 🤪🤣🤣🤣🤣ጠበኛ እውነቶች ... የአለም ዋልታ ነውሃሃ ... ወይኔ ሜዬ ይሄን እያነበበ ራሱ መፃፍ ፃፊ ደብዳቤ የማያቅ እንዳለ ብታውቂ .... አንተ ሶዬ ተጣላኝ)
የሆነው ሆኖ አዘግጁ አብርሃም ደውሎልኝ ሀሙስ ቀረፃ ትገቢያለሽ ምናምን ሲለኝ ... ባሊሄሌሌም ... ሳልሳም ደንሼ ነበር:: ብዙ ለማስታወቂያ ያሰብናቸውን እቅዶች ሰርዘን በቃ ሰይፉጋ ከቀረብኩ ብዬ ከአለም አንደኛ ቀደዳ ተዘጋጅቼ: ከዛ ልብስ ራሱ ያው የሜመሮች አይን ውስጥ የማያስገባ 🤪 ምን አለፋችሁ ስንቴ እእእ ብዬ ጉሮሮዬን እንደምጠርግ ሁላ ተዘጋጅቼ ... ፖ ግነት
እንቢ አልኩት እንድላችሁ እየጠበቃችሁ አይደለምኣ? አላልኩትም !!! ... ስቆላ ከርሜ ለተወሰነ ሳምንት በራሱ ምክንያት ሾውን አቆመና ትዝታ ማቅረብ ጀመረ:: ደውዬ ለአብርሃም የሚቆጨኝ 'አብርሽ' ምናምን ብዬ ማቆላጰሴ ... ስጠይቀው 'ጣጣ የለውም ከ4 ሳምንት በኃላ እንጀምራለን:: ያኔ የመጀመሪያ ነሽ አለኝ!' ደጋግሜ አረጋግጬ ትኬቴን አስረዝሜ ስጠብቀው አራተኛው ሳምንት ላይ ዘጋኝ ዘጋኝ!! ብደውል አያነሳ ... ቴክስት ብፅፍ አይመልስ ... ደሞኮ በመሃል ታዲያስ አዲስ ላይ ከሰይፉ ጋር በሬዲዮ ላይቭ ስቀደድ ነበር:: ሰይፍሻ ምናምን ብዬ አቆላምጬው ..... ወየው ሜዬ ...
(ለምን ዛሬ መፃፍ ፈለግሽ የሚል ከኔ የባሰ እርጉም አይጠፋም!! ዋናው ምክንያት ይህቺ ልጅ ጨዋ ናት ብሎ አንጀቱ ቢራራና ድጋሚ ቢጠራኝ ከሚል ሀሳብ ነው🤣🤣🤣🤣🤣🤣)
ከዛማ በኔ ቦታ ቬሮኒካ አዳነ ሲንግል ለቃ ነበር እሷን አቀረባት!! ዋናው ነጥቤ ይሄ ቢሆንም ኮመንት ላይ ሰይፉን ብትረግሙልኝም ደስ ይለኛል!!
ልጅቷን ሰፋኃት!! የትም ሳያት ደሜ ይፈላ ጀመር:: ደሞኮ ከዛ በፊት እወዳት ነበር:: 'አማረብኝ ብላ ይሄን የለበሰችው?' 'ምን የሚሉት ቅብጠት ነው' ጠመድኳት በቃ!! የሆነ ሰው ስለሷ ነቅፎ ከፃፈ ወይ ከሰማሁ 'ህእ' ማለቴስ? ጌታን ሀሜት አይደለም ከፈለጋችሁ መንሽኗት...
እኔ ወይዘሮ ሜሪ ፈለቀ ከብዙ ክፉ ሰዎች መለስተኛ ክፉ የሚያደርገኝ አንደኛ ክፋቴን አምናለሁ ሁለተኛ ወደ ቀልቤ እመለሳለሁ:: እና የሆነ ቀን ከራሴ ጋር ስብሰባ ገባሁና "ሜዬ ልጅቷ ምን ታድርግሽ? እሷኮ ከነመፈጠርሽ ነው የማታውቅሽ? ምን ልሁን ባይ ነሽ?" አልኳት ክፉዋን ....
ክፉዋ ምን አለች ..."እኔ ልቀመጥ ያለምኩት ቦታ ነው እሷ የተቀመጠችው!"
ያው ኃላ ላይ ተስማምተው (ሁለቱ ሜሪዎች) ልጅቷን እንደበፊቱ መውደድ ቀጠሉ...
እና እዚህ መንደር የሆነ ፐብሊክ አይን ውስጥ ያለ ሰው ምንም ሳያደርጋቸው ሙልጭ ሲያደርጉት
"እኔን የሆነው ማነው?" እላለሁ

👍16🤣3🥰2❤1
ልንጋባ ሁለት ሳምንት ሲቀረን እጮኛዬ ጤነኛ እንዳልሆነ አውቅኩ
(የመጨረሻ ክፍል)
ልጄን ወይ እወልደዋለሁ ወይ አስወርደዋለሁ። ምርጫ ነው። ህይወት ራሱ የምርጫችን ውጤት አይደል? ልክ እሱን ማግባት አለማግባት ራሱ ምርጫዬ እንደሚሆነው?
"ተገላገልሽ!" ትለኛለች ያቺ ታይላንዳዊቱ ወዳጄ ጠርታኝ። ሁለታችንም የምናውቀው አንድ ምግብ ቤት ባለቤት የሆነ ሰውዬ ያለሁበትን ሁኔታ ነግራው ሊያገባኝ እና ሊረዳኝ እንደሚፈልግ እየነገረችኝ።
"ለምን ሊረዳኝ ፈለገ?"
"ምክንያቱ ምን ያደርግልሻል? የመኖርያ ፈቃድሽን አይደል የምትፈልጊው? ደሞ አሪፍ እድል ነው። ካልፈለገች አብራኝ አለመኖር ትችላለች ብሏል። ቅረቢውና ከወደድሽው አብረሽ ትሆኛለሽ። ካለበለዚያ በቃ ለመኖርያ ፈቃድሽ ሲባል የውሸት ጋብቻ ይሆናል ማለት ነው።"
(እዩት እድሌን ግን ... ይሄ እድል ስፈልገው የት ነበር? ዛሬ ስለፔር ማሰብ ስጀምር .... ራሴን የማልመልሰው ርቀት ያህል ከሄድኩ በኃላ ነው የሚረዳኝ ሰው የሚገኘው? የት ነበር? )
"አልፈልግም" አልኳት ሳስብ ቆይቼ
"እና ከእብድ እጮኛሽ ጋር መጋባቱ ይሻልሻል?"
"ሁለተኛ እብድ እንዳትዪው!" ብዬ ዘልዬ ተነሳሁ
"ኦ ማይ ጋድ ፍቅር ይዞሻል" አለችኝ በጣም የተገረመች መስላ
አልመለስኩላትም። ትቻት እየሄድኩ የወሰንኩት ውሳኔ ይቆጨኝ እንደሆነ አስባለሁ። ህይወት ራሱ የምርጫችን ውጤት አይደል? እሱን መረጥኩ። ምርጫዬ የሚያፈራው ፍሬ መራራም ይሁን ጣፋጭ ..... እሱን መረጥኩ::
"ማውራት አለብን!" አልኩት እቤት እንደገባን
"እሺ" አለኝ።
"ልጃችን የባይፖላር ተጠቂ ላይሆን የሚችልበት እድልምኮ አለው" አልኩት::
"ሊሆን የሚችልበት እድልም ሰፊ ነው።"
"እሺ ባይሆንስ?"
"ዜሮ ምናምን ነጥብ ቢሆን እንኳን የመሆን እድሉ በፍፁም በፍፁም ልጄን እኔ የማልፈውን ስቃይ እንዲያልፍ አልፈቅድም።"
"እሺ እኔ ልጄን ማስወረድ ባልፈልግስ?"
"እባክሽ እዚህ አጣብቂኝ ውስጥ አትክተቺኝ። እባክሽ?" አለኝ
ዝም አልኩ። ወሬውን ከዛ በላይ መቀጠል አልፈለግኩም። ተጨማሪ ጥያቄ ብጠይቀው የሚመልሰውን መልስ ፈራሁት። ወይ ልጄን ወይ እሱን መምረጥ አለብኝ:: ልጄን መውለድ እፈልጋለሁ ብለው መጋባቱ ይቅርብኝ እንደሚል እንኳን ልቤ እያወቀው .... እሱ የምርጫው አጣብቂኝ ውስጥ ላለመግባት እኔን እንድመርጥ እያስገደደኝ እንደሆነ እንኳን እያወቅኩ እሱን መረጥኩ!! .... ደግሞም ልጄስ እሱ እንደፈራው አባቱ የሚያልፈውን ሰቀቀን የሚደግም ቢሆንብኝስ? ከአንድ ልጄ ውጪ ሌላ ልጅ መውለድ ብፈልግም አልወልድም።
እሱን ማግባት የሚያስከፍለኝን በሙሉ አሰብኩት። አለማግባቱም የሚያስከፍለኝን አሰላሁት። ከእርሱ ጋር መሆን ብዙ ያስከፍለኛል። እንደዛም ሆኖ ማድረግ የምፈልገው ከእርሱ ጋር መሆኑን ነው።
"እሺ!" አልኩት በመጨረሻ
"እሺ ምን?" አለኝ ከአፌ የሚወጣውን ለመስማት እየጓጓ
"እሺ ልጅ አይኖረንም ግን አንድ ነገር ቃል እንድትገባልኝ እፈልጋለሁ!"
"ምንም ይሁን ምንም!.... ምንም ነገር!!" አለኝ በደስታ እያቀፈኝ
"መድሃኒትህን መቼም ቢሆን ሳታቋርጥ እንደምትወስድ ቃል ግባልኝ።"
"ቃሌ ነው።"
ሰርጋችን በቤተክርስቲያን እንዲሆን የመረጥኩት እኔ ነኝ። ቄሱ ፊት ቆሜ አይን አይኑን እያየሁት
"በህመሙም በጤናውም በድህነቱም በሃብቱም ........" ብዬ እየማልኩ እህቱን አያታለሁ ለሚያያት ሰው ግድ ሳይላት እንባዋን ትነዳዋለች።
ጨርሰናል!!!!!

👍10❤6
ላመንኩበት ነገር ገገማ ነኝ 🤣🤣
(ፖ ወሳኝ ገገማ ርእስ ይልሃል ይሄ ነው)
ከብዙ አመታት በፊት ጀምሮ ነው Dhar Mann እና Jay Shetty የሚባሉ ምርጥዬዎች መከታተል የጀመርኩት ... ለራሴ አንድ ቀን ልክ እንደነሱ በአጭር ደቂቃ አንድን ሀሳብ የሚያስተላልፍ ድራማ እንደምሰራ አውቅሁ ... (We are not just telling stories, we are changing life እንዲል dhar Mann .... ቢያንስ ለአንድ ሰው መነሳት ወይም መበርታት ምክንያት የሚሆን ሀሳብ ካስተላለፍኩ መነሻው ያ ነው:: ...
(ልቤን እኮ ሳስበው እንዴት እንደምኮራ ... የምን ቁጥ ቁጥ ነው ካለሙ አይቀር ተራራ ነው እንጂ ሃሃሃ)
እናም በዩቱዩብ ጀመርኩት ... በሳምንት አንድ ቀን (ሀሙስ እለት) አጫጭር ድራማዎችን በቋሚነት ፎቷቸውን ከስር ከምታዩት ቤተሰብ ጋር እንሰራለን:: የኔ ስራ ፅሁፉን መፃፍ ነው:: (አንዳንዴ የሌላም ሰው ይሆናል:: ባለፈው እንኳን የአጭር ድራማ ፅሁፍ አወዳድሬ አልነበር?ልክ እንደዛ) እና ምን አልኩት "የሜሪ ሃሳቦች" (ገገማ ነኝ አልኳችሁኮ )
Mintesnot Melaku
"ሜዬ እንድች ብለሽ እንዳታስቢ" ብሎ ይቀበለኝና ዳይሬክት አድርጎ ለተመልካች ያሰናዳል::
በብዛት ከ10 ደቂቃ የማይበልጡ ድራማዎችን ነው የምንሰራው ... ቢያንስ ለአንድ ሰው የሆነ መልእክት አደርሳለሁ ብዬ አምናለሁ:: ... ለሚመለከተው 100 ሰውም ይሁን 10000 ... ለምስሉም ሆነ ለድምፁ ... ለሀሳቡም ሆነ ለትወናው ግድ ሰጥቶን እንጨነቃለን:: 'ለዩቱብ አይደል?' ብለን የምናልፈው የለም:: .... (አንጎርርም ብለን ነው እንጂ ህእ ድሮን ሁላ ተጠቅመን የምንቀርፅ ሰዎች ነው ...)
ከዚህ በተጨማሪ ስቱዲዮ ገንብተናል:: ትረካዎችን የምንቀርፅበት:: ... በሙያው አንተና አንቺ የተባሉ (አንቱ ላለማለት ነው) በብዛት ቃና ቲቪ ላይ የሚሰሩትን ልጆች ነው በቋሚነት በድምፅ የምናሰራው.... ይሄን ፕሮግራም "ከገፅ ወደ ጆሮ" ብለነዋል::
ስቱዲዮ ከገነባን: ቋሚ ቤተሰብ ከመሰረትኩ: ወላ አልበላ አልጠጣ ብዬ 5D mark 4 ካሜራ ከገዛሁ .... ሀሳቡ በእጄ ከሆነ dhar mann ን ለመሆን ምንድነው የሚቀረኝ? 39 ሚ ፎሎወር ብቻ 🤣🤣🤣🤣🤣
ማነው ቀላል ነው ያለው? ህይወት ለቀሽሞች አትሆንም ..... ለበረቱ እንጂ....
እውነት ስናወራ ያላነሰ ወጪ አውጥተን ... ሰዓት ባክኖ ... ወላ አንዳንዴ ተደጋግሞ ተቀርፆ ... ያየው ሰው 1000 ሳይሞላ ሲቀር ... ለምንድነው የማልተወው ብዬ አስቤ የማላውቅ መስሏችሁ? አውቃለሁ .... ግንሳ ?.... የሆነ ሰው ይመጣና "ሜሪዬ የዛሬውን ድራማኮ አየሁት ... የምታውቂኝ... ያለሁበትን የነገርኩሽ መሰለኝ" ሲልሳ ..... ለሌላ አንድ ሰው መነሳት ደግሞ እንበረታለን!!!!
አፉን የሚከፍት ከንቱስ ሳይገጥም ቀርቶ መሰላችሁ? .... አላመናችሁኝም? ገገማ ነኝ .... ...
እና ይሄን ታሪክ ከኔ ጋር ምን ያገናኘዋል?
ሰብስክራይብ አድርጉ ለማለት ነዋ .... 👇🏼👇🏼
https://youtu.be/X2DubJh0UEo

YouTube
ለፍቅር ሲባል ራስን መክፈል ልክ ነው?
ውድ ተመልካቾቼ ይህ ሀሙስ ሀሙስ በተለያየ ሀሳብ ዙሪያ ለውይይት መነሻ የሚሆን አጭር ድራማ ይዘንላችሁ የምንቀርብበት «የሜሪ ሀሳቦች» የተሰኘ ፕሮግራማችን ነው። እንደምን ከረማችሁ!!
ሁሌም እንደምንለው ሁላችንም በተለያየ ሃሳብ ዙሪያ የተለያየ አይነት እይታ ይኖረናል። ቤተሰብ በመሆን የናንተንም ሀሳብ ብታጋሩን ደስታችን እጅግ የበዛ ነው።
በዚህ ቻናል ቢያንስ ለአንድ ሰው መነሳት ምክንያት ይሆናል ብለን…

👍9
"ሚስትህን ምን ያህል እንደምትወዳት የሚገባህ ቺት ያደረግክባት ቀን ነው:: አቤት መንገብገቡ .. አቤት ፀፀቱ .." እያለ በቁምነገር ፀፀቱን ያስረዳዋል
"ኦህ ... ምን ያህል እንደምወዳት ለማረጋገጥ ቺት ላድርግባታ?" አላለውም ?
🙆🏻♀️🙆🏻♀️🙆🏻♀️🙆🏻♀️🙆🏻♀️🙆🏻♀️🙆🏻♀️🙆🏻♀️
(ሰው ግን መስማት የፈለገውን እየመረጠማ ነው የሚሰማው)

❤4👍1🥰1
ውዶቼ መቼም በቀን ከ2000 በላይ ሰው በኮሮና በመያዝ የቀይ መስመሯን መሻገራችንን ሰምተናል::
ብዙ ወዳጆቻችን በፌቡ ተይዘው ማገገማቸውን ፅፈው አንብበናል:: ያ ማለት ያልፃፉ ብዙዎች አሉ ... ከነአካቴው መዳን ሳይችሉ የሞቱም አሉ ማለት ነው::
እውነት ነው በቀን ውስጥ በኮረና ከሚሞተው በትራፊክ አደጋ የሚሞተው ሊበልጥ ይችላል::
እውነት ነው በቀን በኮረና ምክንያት ከሚሞተው በብሄር ምክንያትና ለማይረባ የፖለቲካ ጨዋታ በየክልሉ ሬሳው የሚቆጠረው ብዙ ነው::
እውነት ነው ከኮረና የባሰ ርሃብ ... እጅግ ብዙ ሰቆቃ ያለብን ህዝቦች ነን
.
.
.
.
ይሄ ሁሉ ላለመጠንቀቅ ምክንያት አይሆንም:: ምክንያቱም ክፋቱ ብቻችንን አይደለም የምንሞተው ...
እባካችሁ የምንችለውን ሁሉ እያደረግን እንጠንቀቅ ....
ብዙ ሰዎች እየሞቱ ነው...

👍4❤1
"ባሌ እንዳመነዘረብኝ ባወቅሁ ጊዜ እጅጉን ደስ አለኝ" በሚል ርእስ ለተከታታይ ሰባት ክፍል በፅሁፍ ከወር በፊት ለጥፈነው የነበረውን ፅሁፍ አስታወሳችሁት?
አሁን ደግሞ ውብ ተደርጎ በባለሙያዎች ዋና ዋና ገፀባህሪ የሆኑትን ሶስቱንም በተለያየ ድምፅ በትረካ ደግሞ በሁለት ክፍል ተዘጋጅቶ "ከገፅ ወደ ጆሮ" በሚለው ፕሮግራማችን ቀርቦላችኃል::
ፅሁፉን ላላነበባችሁም እንዲሁም ፅሁፉንም አንብባችሁ በድምፅ መድገም ለምትፈልጉ ክፍል 1 ሊንኩን አስቀምጬላችኃለሁ:: የተራኪዎቹን ድምፅ እና አተራረክ በፍቅር ነው የወደድኩላቸው ... የሆነ ቦታማ እኔኑ ሴትየዋን እንባዬን አስመጣችው ..

👍2
አንዳንዴ ተስፋ መቁረጥ ጥሩ ነው::
በተስፋ አለመቁረጥና በትእግስት ብዙ ነገር እንደሚሳካ አምናለሁ:: አንዳንዱ ነገር ግን በቃ አይሆንም .... ከብርትኳን ዛፍ ላይ በየዓመቱ እያፈጠጥክ ማንጎ መጠበቅ ... አይሆንማ!!!...
ወይ ማንጎ ተክለህ ጥበቃህን ትክክለኛ ቦታው ላይ አድርግ ወይ አርፈህ ብርትኳንህን እየቀጠፍክ አጣጥም..... ወይ በእምነት መንጎ ነህ ብያለሁ መንጎ ነህ ብለህ ግግም 🤣🤣🤣🤣
የተዋበ ቀን ዋሉማ❤️❤️

ወይ የሴት ልጅ አበሳ 🤣🤣🤣
ብዙ ጊዜ አነቃቂ ንግግር የሚናገሩ ሰዎችና ፍቅረኞቻቸውን ማፅናናት የፈለጉ ወንዶች ... በማህበረሰብ የውበት መስፈርት "ቆንጆ" ያይደለችን ሴት
"ዋናው የውስጥ ውበት ነው:: የላይኛው ጠፊ ነው .. ረጋፊ" ሲሉ ይደመጣሉ::
እህህህ ይሄ ነገር በግርድፉ
"ፊትሽንማ ለመድሃንያለም ትቼው እንጂ ይገፋ ነበር?" የሚል መልእክት አይደለም ያለው?
ይሁን የላዩ በውስጡ ይካካሳል አይነት?
......
......
.....
በገደምዳሜ ላይኛው የሊማሊሞ ጥምዝምዝ ነው ...
"ምኗን ነው የወደድክላት?" እለዋለሁ
"ውስጧን ልቧን .. አንጎል ... ትርፍ አንጀቷን ..." ብሎ የሆድቃዋን ሁላ ሲጠራ ቆይቶ
"ከሚታይ ነገር ጥቀስ!" እለዋለሁ ...
አይኑን ጨፍኖ ሲያስብ ቆየና "ቤቢ ሄሯ" አይለኝም?
🙆🏻♀️🙆🏻♀️🙆🏻♀️🙆🏻♀️🙆🏻♀️
ውብ ቀን ውብኛ አዋዋል ዋሉማ❤️❤️❤️

👍4😁4
ሳምሶን ከሚስቱና ከሚስቱ እናት ጋር እየኖረ... ሁሌ ከሚስቱጋ ይጣላና እንዲያስታርቀው ያገባ ጏደኛውጋ ይመጣል
ሳምሶን፡- "ሰው የገዛ ባሉን እንዴት ሰ….ቀጫን! ብሎ ይሰድባል?" ይላል ብክንክን ብሎ
ጏደኛው ፡- "ሰቀጫን?.... ምን ማለቷ ነው?"
ሳምሶን፡- "እሱማ ስግብግብ፣ ቆንቋና እንደማለት ነው፡፡"
የጏደኛው ሚስት፡- "ሆ!! ....ምን ብታደርጋት ነው ቆይ ሰ…ቀጫን ያለችህ?"
ሳምሶን ፡- "እሱማ እ…. እንትን … እንጀራ ስቆጥር እናቷ አይተው ነገሯትና …"
ጏደኛው ፡- "በስመአብ !! ......ቱ !!!!......አንተ?"
ሚስትው፡- "አበስኩ ገበርኩ!!!"
ሳምሶን ፍጥን ብሎ ፡- "ለጥቂት እኮ ነው ... እንጀራው ትኩስ ሆኖ እየተደራረበ አልሄድ ብሎኝ (የደብተር ገፅ እንደመግለጥ በእጁ እየቆጠረ )እንጂ እኮ ለጥቂት ልጨርስ ነበር::"
ጏደኛው ፡- "ሂድ!!.... ሂድ አንተ!!!!!......... ሰ…ቀጫን!!!.............. አሁን እንጀራ ስትቆጥር ተይዘህ አስታረቅኩህ በኋላ ስኳር ስትቆጥርስ?"
ሳምሶን(ከአፉ ቀበል አድርጎ)፡- "ማን ?....እኔ?....... ኸረ አይለመደኝም!!!! ሁለተኛ……….. በእርሳቸው ፊት ልቆጥር ?.......አላደርገውም!!"🤣🤣🤣🤣
*ትዳር ሲታጠን

👍16😁5🤣2
ኢትዮዽያ መኪና ነድቼ አላውቅማ ... ራሴ ነዳለሁ ብዬ መኪናውን ልከራይ የቀጠርኩት ሰውዬ ...
"አይከብድሽም? እርግጠኛ ነሽ? ረዥም አመት እንኳን ውጪ የነዱትኮ እዚህ ይፈራሉ .... (ሲያስፈራራኝ ከቆየ በኃላ ) ለማንኛውም እስኪ አብረን ሆነን ልይሽ" ብሎ ከኃላ ተቀምጦ ስንዳ ... ሲኖትራክ ሲንቀለቀል መጣ ...
"ውይይ ይለፍ ቆይ ያስፈራል" አልኩት ...
"ገና እሩቅ ነውኮ .."
"አይ ቢሆንም አመጣጡን እየው ያስፈራል::" እለዋለሁ:: ምን ቢለኝ ጥሩ ነው?
"በዚህ አያያዝሽ ሹፌሩ ወርዶ ሁላ እለፊ ቢልሽ...'በማርያም ሞተሩንም አጥፋውና ነው የማልፈው' ትያለሽ::"
ወዮዮዮዮዮዮዮ 🙆🏻♀️🙆🏻♀️🙆🏻♀️🙆🏻♀️🙆🏻♀️🙆🏻♀️🙆🏻♀️🙆🏻♀️
ውብ ቀን ውብኛ አዋዋል ዋሉማ❤️❤️❤️❤️

😁7
አውሮራ / የሰሜኑ ብርሃን
ዙረት ነፍሴ እንደሆነ ታውቃላችሁኣ? ይሄ ኮረና አፈር ይብላና አላላውስ ብሎኝ ... እንጂ አዞራችሁ ነበር::
ከወራት በፊት እዛው ኖርዌይ ሰሜን ጫፍ የምትገኝ ትሮምሶ የምትባል ከተማ ይሄን ተአምረኛ የሰሜን ብርሃን ላይ ሄጄ ነበር:: ተፈጥሮ አጃኢብ ያስብላል:: ... የሆነ ምርጥ ሰዓሊ የሳለው ስእል ነው የሚመስለው ...
የተወሰኑ ቪዲዮዎች ላስቀር ሞክሬ ነበር:: እና ስንድት አድርጌ በቪዲዮ አቅርቤላችኃለሁ::
👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼
https://youtu.be/7L7KvFBfudc

ዙረት የሰሜን ምትሃታዊ ብርሃንን ለማየት #northernlight #nordlys #norway
ውድ የቻናሌ ቤተሰቦች ሰላማችሁ እንደሰማይ ከዋክብት እንደማይቆጠር የምድር አሸዋ እጅጉን የበዛ ይሁን። ይህ ዙረት የተሰኝ የተለያየ ቦታዎችን የምንዞርበት አዲስ ፕሮግራማችን ነው። በዛሬው ዙረታችን ሀገረ ኖርዌይ ሰሜን ጫፍ ትሮምሶ የተባለ ከተማ ተጉዘን ተአምረኛውን የሰሜን ብርሃን ወይም አውሮራ እኔ በአካል እናንተ በዓይን እንጎበኛለን። እያካበድኩ አለመሆኑን ስታዩ ትፈርዱኛላችሁ የምር ምትሃተኛ ውበት ነው።…
👍5
ቤተሰብ እንዴት ከረምን? ተጠፋፋንኣ? ተመልሻለሁ...
የመታወቂያ ስሜ ሜሪ ፈለቀ እንዳልሆነ መቼም ታውቃላችሁኣ?
በቀደም ኤርፖርት ልጅቷ ግራ ተጋብታ እያየችኝ .. ፖስፖርቴን እያገላበጠች ... እህቷ ናት ብላ አስባ መሰለኝ 🤣🤣
'ከሰው ጋር ተመሳስለሽብኝ .... እ.... ሜሪ ፈለቀ?' ትለኛለች 'Never mind እሷ ፀጉሯ እንዳንቺ አይደለም" ብላኝ ወደ ስራዋ ተመለሰች .... ትዝ ሲለኝ ለካ ፀጉሬን ወደ ላይ አስይዤዋለሁ ....
" እ? ፀጉሬን ሳይቸግረኝ ለጏደኛዬ ሰርግ ተሰርቼው ቅድም ሙቀት ሊያፈነዳኝ ሲል ሰብስቤው ነው ... የማስርበት አጥቼ በጫማ ክሬ ነው ያሰርኩት ሁላ" ብዬ አንድ እግሩ የጫማ ክር የሌለበትን ጫማዬን ሳሳያት በሳቅ እየፈረሰች
"ራሷ ነሽ በቃ ! ... " ብላኝ እስክሄድላት እያየችኝ ትነፍራለች...
ዛሬ ደግሞ (በነገራችን ጎን ከእናት ሀገር ወደ አባት ሀገር ተመልሼ አስር ቀን ሆቴል ውስጥ እየኳረየንትኩ🤣 ነው) ምግብም ቡናም ራሳቸው ክፍል ድረስ ነው የሚያመጡት ... ዛሬ ተጨማሪ ቡና ፈልጌ ስወርድ ... ከፍሪዝና ከእብደት መሃል ባለ ፀጉር ... (አስቡት ማክሰኞ የገባሁ ዛሬ ነው ወደ ሪሴፕሽን ሁላ የወረድኩት... ቡና ለማምጣት ሊፍት ውስጥ ለመግባት ፀጉሬን ላስተካክል? )
በዛ ላይ ምንም ክፍት ጫማ የለኝም ... ስለዚህ በካልሲ ወረድኩ ... ሪሴፕሽኑ አይኑን በልቅጦ ሲያየኝ
"ለ2 ደቂቃ ቡና ማምጣት ሜካፕና ሂል ጫማ ለብሼ እንድመጣ አትጠብቅብኝምኣ?" ስለው እየፈረሰ ቡናዬን ሰጠኝ ... ሊፍት ውስጥ እስክገባ እያየኝ ይደክማል.....
.......
የሆነ ያልተፃፈ dressing code አለ:: ማንም የነገረህ የለም ... ስታበላሽ ግን ብዙ ሰው በግርምት ያይሃል .... የሰው reaction እንዴት እንደሚያዝናናኝ...
መዘነጥ ደስ ይለኛል:: ... ስዝረከረክ ደግሞ ቆንጆ እዝረከረካለሁ:: ... አንዳንዴ ደግሞ ከላይ ዝብጥ ያለ ሙሉ ልብስ ለብሼ ከስር ነጩን ሲሊፐር አድርጌ ወጣለሁ .... ሂል ጫማዬ ወይ መኪና ውስጥ ነው ወይ ደግሞ እቤት ገብቼ ልብስ ለመቀየር ሰንፌ ነው....... በተለይ እኚህ 'ትልልቅ ቦታዎች' የሚባሉ ቦታዎች ጋር የሰው ሪአክሽን ያስቀኛል....
......
ህይወት 24 ሰዓት ሸሚዝ በከረቫት ዓይነት አይደለችም ... ብዙ ጊዜ እኛ ጭራሽ የሚያስጨንቀን ... ለሌላው ጥንቅቅ ብለን መታየት ነው:: ... ለምሳሌ ብዙ ሰው ሀብታም ከመሆን ይልቅ ሀብታም ለመምሰል ሲጋጋጥ ይታያል:: ...... (በተለይ የኛ ሰው ከውጭ ሀገር ሲመለስ .... ቡፍ🤣🤣🤣 ... እውነት ነው ሽሮ ወጥ ያምራል ... ግን come on... ከኤርፖርት ቀጥታ አዝመራ ሽሮ ቤት? )
ማይ ፒፕል ..... ህይወቱ ያንተ ነው .... ሌሎች ሲያዩህ ስለሚሰማቸው ስሜት ሳይሆን አንተ ስለሚሰማህ ስሜት ተጨነቅ..... ህይወትህን ሳትደሰትበት ብታረጅ 'ቆይ ይሄ ምስኪን ያልኖራችው ቀናት አሉ" ብሎ አዝኖ 1 ቀን ከራሱ እድሜ የሚያበድርህ የለም ... ዘንድሮ እንኳን እድሜ ብር ራሱ የሚያበድር የለም 🤣
የለበስሽው ልብስ... ያደረግሽው ሜካፕ ... የምትኖሪው ዘይቤ አንቺን ተመችቶሻል? ... ደስተኛ ነሽ? (I mean ማታ ከራስሽ ጋር ብቻሽን ሆነሽ ራስሽን በመስታወት ያለሜካፕ ስታዪው ... ቅድም በሜካፕ ስታዪው ከተሰማሽ ውብነት ጋር እኩል ስሜት ተሰምቶሽ ትተኛለሽ? ወይስ ...'መድሃንያለም ድረስልኝ ... ይህቺ ማነት?' ብለሽ ከራስሽ ትሸሺያለሽ?)
~ ደግነትህ ለራስህ ለሚሰማህ ጥሩ ስሜት ነው? ወይስ ሌሎች ጭንቅላት ውስጥ ስለምትስለው ለጋስነትህ?
~ የገዛሽው መፅሃፍ ለፎቶ ነው ወይስ ታነቢዋለሽ?
~ ያነበብከው መፅሃፍ ያውቃል ለመባል የምትሸመድደው ነው ወይስ ጠብ ያለልህ ነገር አለ?
.
.
.
ለሰዎች 'ልክ' መስለን ለመታየት ከመጋጋጥ ልክ ለመሆን ራሳችንን ማስለመዱ አይቀልም ... ?
ማለቴ ነገሩን ነው እንጂ ... ምንም ብትሆን በሁሉም ሰው ፊት ልክ ልትሆን አትችልም .. ምን አደከመህ? ዝም ብለህ ራስህን ሁን (አይሆኑ አኳኃን ለመሆን አትመርጥም መቼም ... እንደ አክቲቪስት ያለ... እተማመንብሃለሁ🤣🤣🤣)
.....
ውብ ቀን ውብኛ አዋዋል ዋሉልኝማ❤️❤️❤️❤️❤️

👍20🥰2❤1
አልወዳትም እንጂ አልጠላትም...
ሞታ የለቅሶ ድንኳኗ ውስጥ የተነጠፈው ፍራሽ ላይ ተቀምጬ ሊቀብሯት በሳጥን አሽገው ጥጉ ላይ አስቀምጠዋት ሲላቀሱ የማስበው
'አልወዳትም እንጂ አልጠላትም' .... የሚለውን ነው... በሃሳቤ መሃል ከቤተሰብ ወይ ከወዳጅ አንዱ ሲያፈጥብኝ
"ወይኔ እህቴን .. ወይኔ እህቴን ... ትተሺኝ አትሂጂ .." እሪታዬን አቀልጠዋለሁ ... እንባዬ ይተባበረኛል::
እህቴ ናት ... አዎ የሞተችው እህቴ ናት ... ብዙ መለስተኛ ክፉ ነገሮች አድርጌባት አውቃለሁ ...
ለምሳሌ ለሰርጏ ሰዓታት ሲቀሯት የሙሽራ ልብሷን በእስኪሪብቶ ቀለም ቡራቡሬ እንዳደረግኩባት አይነት ትንንሽዬ ክፋቶች ...... ግን አልጠላትም!!!
ባሏን ከማባለግና ሰርጏን ከማበላሸት የትኛው ትልቅ ክፋት ነው?
"ካላንቺ እንዴት ልኑረው?" እያለ ወገቡን ተደግፎ ድንኳን ውስጥ ይዝረከረካል ባሏ ... እኔ ሰልችቶኝ እስካቆምኩበት ቀን ድረስ እኮ ከሚስቱጋ ከተኛበት ቀስቅሼ የማባልገው ሰውዬ ነበር!! .. እሺ ከኔና ከሱ ማናችን የባሰ ክፉ ነበርን ለሷ?
አያችሁ አልወዳትም እንጂ አልጠላትምኮ ...
ኦው የምርቃቷ ቀን የጫማ ሂሏን የሰበርኩባትን መቼም እንደክፋት አትቆጥሩብኝም ... ምርቃት የምታክል ክፋት !
ያስቃምኳት... ያሰከርኳት ... ያስጨስኳት .... ያጣበስኳት ... ይሄ መቼም ከውለታ እንጂ ከተንኮል ከተቆጠረ ... ደግ ነገር የለም ማለት እኮ ነው...ሆ!!
"እህቴ መካሪዬ ... " ... እናቴ አየችኛ ... ለቀስተኛውን ተቀላቅዬ የፈረደበት ዓይኔን ላስጨንቀው ...
እህቴ ክፉ ሴት ሆና አይደለም!! በተቃራኒው ከማውቃቸው ሰዎች ለፍፅምና የቀረበች መልካም ሴት ናት .... የማልጠላት ለዛ ነው ...
የማልወዳት በዚህ ፍፅምናዋ እሷ በፍሬም የተቀመጠች ሞዴል ሆና ቤተሰቦቼ እኔን በሷ አምሳል ጠፍጥፈው ሊሰሩኝ እያቦኩ የሚጠፈጥፉኝ ሁሌም በጅምር ያለሁ ቡኮ የሸክላ ጭቃ መሆኔ ነው ....
እሷ በትምህርቷ አንደኛ ስትወጣ 'እህትሽን አየሻት?' ያቦኩኛል .. ጎበዝ ተማሪ አድርገው ሊቀርፁኝ ሲጀምሩ እሷ በሆነኛው እስፖርት አሸንፋ ዋንጫ ይዛ ትመጣለች .....
ደሞ የጀመሩትን አፍርሰው ያቦኩኛል ... እስፖርተኛ እንድሆን ሊቀርፁኝ ይጀምራሉ ... ገና ቅርፅ ሳልይዝ እሷ በሆነኛው በጎ አድራጎት ተሳትፋ ስሟ ይወደሳል ... ደሞ ያፈርሱኛል ... ይጠፈጥፉኛል ..
'እህትሽን አየሻት?'
በተሳሳተ መንገድ አትረዱኝ 🤷🏽 ክፉ መስራት ፈልጌ አይደለም .... እኔ እሷን መሆን ብዙ ሞክሬ ያልተሳካልኝ ነገር ስለነበር ... የክፋት ሙከራዬ እሷን ወደ እኔ ማውረድ ነበር::.... ትዳር ባይኖራት ..... ባትመረቅ ... የክፋት ክፋቱ እሷ ማምለጫ አታጣም ነበር!! ....
ከሞት ማምለጫ የለውም እንጂ ህምምም... አሁንም በተሳሳተ መንገድ አትረዱኝ በመሞቷ አልተደሰትኩም:: በመሞቷ ከማንም በላይ የምጎዳው እኔ ነኝ...
ግማሹን ዘመኔን እኔ እሷን ለመምሰል ስጋጋጥ ... የቀረውን እሷ እኔን እንድትሆን ስጋጋጥ ነው በመሃል አየር ላይ በትናኝ የሞተችው .... እና አሁን ምን ልስራ? ማንን ልምሰል?
በሞቷም ልከተላት? ራሷን ብቻ ሳይሆን ያቺ በፍሬም የተቀመጠችልኝን ሞዴሌን ይዛት ነው የተቀበረችውኮ ..... ከኔ በላይ ማን ሊያለቅስላት ይችላል?
"እህቴ ... ምሳሌዬ ..... ወዮዮዮዮዮዮ ኡኡኡኡኡኡኡኡ" .... አብርዶ የነበረው ለቀስተኛ ማርሹን ጨምሮ እርርርርሪሪሪሪሪሪሪሪሪሪ.....
"አይዞሽ! አይዞሽ ኤድዬ" ... ጀርባዬን ቸብ ቸብ ያደርጉኛል ...
እሷ ራሷን ሆና .. የምትፈልገውን አድርጋ ... የራሷን የህይወት መንገድ ሮጣ በ30 ዓመቷ ሞተች ... ቢያንስ ኖራለችኣ?
እኔ እሷን ስመስል ... እሷ እኔን እንድትመስል ተንኮል ስፅፍ 30 ዓመት .... ኖርኩ ነው የሚባለው?
ማነው የሞተው? እኔ ወይስ እሷ?
"ኤድዬ እህትሽን ትሰናበቻታለሽ?" ወደ ቀብር ሊንቀሳቀሱ ነው ... እናቴን አየኃት በተከፈተው ሳጥን ጠርዝ ላይ ድግፍ ብላ እህህህህ ትላለች ...
እሷን ነው የምሰናበተው ራሴን?
"ቆይ ትንሽ ደቂቃ" አልኩኝ ...... ፊቷን የማይበት ጉልበት እያሰባሰብኩ ... (ነፍስም ባይኖረውም... ባታየኝም) ጥፋተኝነት ሲሰማኝ ፊቷን እፈራዋለሁ
.....
"ጫማዬን የሰበርሽው አንቺ ነሽኣ?"
"አዎ... በምን አወቅሽ?" አላያትም.... በግድ አጠገቤ መጥታ እንዳያት ታስገድደኛለች
"ለምን? "
"እኔ እንጃ I guess ቀንቼ ነው" (ትስቅብኛለች)
"We talked about this አይደል እንዴ? Remember? አንቺ ዶክተር መሆን አትፈልጊም.. እኔ ነኝ የምፈልገው... እኔ ዘፋኝ መሆን አልፈልግም አንቺ ነሽ የምትፈልጊው... መሆን በማትፈልጊው ነገር ለምን ትቀኚብኛለሽ? እነ ማሚ እንዲበጠብጡሽ ለምን ትፈቅጅላቸዋለሽ?"
"አላውቅም!" (ታቅፈኛለች ... ጭንቅላቴን ያጣበበውን ብስጭት ... ቅናት ... ተንኳል .. ሀዘን ... ስብራት ... ታሪክ ... ባወራላት ደስ ይለኛል.... እየመጣ ያንቀኛል .... ለምን እንደሆነ በማይገባኝ ምክንያት ሽንፈቴን አምኖ መቀበል ይመስለኛል)
"በደም እህትሽ እንዳልሆንኩ ታውቂያለሽ? አንቺም እንደነሱ እያወቅሽ ነው ወይስ አታውቂም?" ይሄን ያልኳት እሷን መጉዳት ፈልጌ ይሁን መልሱን ፈልጌው አላውቅም::
ፊቷ ላይ መልሱን አገኘሁት:: አታውቅም!! በደቂቃዎች ቀድማኝ የተወለደች መንታ እህቷ መሆኔን ነው የምታውቀው::
"ኤድዬ እህትሽን መሰናበት ከፈለግሽ እየጠበቅንሽ ነው::"
"እሺ"
...... አልጨረስንም...........

👍19❤2
አልወዳትም እንጂ አልጠላትም ....#2
"ከእኔና ከርሷ ምረጥ ብትባል?"
"ደሞ ጀመረሽ .... ተይ ኤዱ እረፊ.... "
"ንገረኝ... ምን መስማት እንደምፈልግ ታውቃለህ!! ... ንገረኝ!!" እጮሃለሁ ... በጥፍሬ ቆዳውን እጫነዋለሁ .... ሚስቱ(እህቴ) ሰውነቱ ላይ ምንም ምልክት እንድታገኝበት አይፈልግምኣ ...
"አንቺ!!.. አንቺ ትበልጫታለሽ!" ይለኛል:: ከሚስቱ ንፁህ ልብ እና ከእኔ እብድ ጭን መሃል እየዋለለ ... ቃላቶቹ አፉን ለቀው ሲወጡ ይጎመዝዙታል..... ያስታውቅበታል:: .....
ፍቅር ይሁን ተንኮል አልጋው ላይ የምሰራው አይገባኝም ..... ፍቅር የያዘኝ በውጊያችን መሃል ከሚነግረኝ ቃላቶች ነው .... የሰውነታችን ግብ ግብ ብዙም አይስበኝም ....
እሱ ከህሊናው ይልቅ ግለቱ ያሾረዋል!! ... እኔ ከህሊናዬ ይልቅ ቅናቴ ያነደኛል:: ... ሁለታችንም ፀፀት አለብንኮ .... እንደ vampire diaries ቫምፓየሮች ... let us shut it down! ብለን የምንዘጋው የህሊና ማስቀመጫ ሳጥን የለንም ...
ነገሩ አንደኛው ስሜት ሌላኛውን የመደፍጠጥ ጉልበቱ ነው .... እሱ ፀፀቱን በደምስሩ የሚንቀለቀል ግለቱ ይበልጥበታል:: እኔ ቅናቴና እሷን ለመብለጥ ያለኝ ፉክክር ፀፀቴን በብዙ እጥፍ ያስከነዳል:: ... ወጥረን እንዋጋለን!!
እኔ እሷ መሳተፏን እንኳን በማታውቀው ውግያ ማሸነፌ ሲነገረኝ ..... የምን ፀፀት ... የምን ህሊና... የምን ሲኦል .....
"ለእሷ እንዲህ አድርገህላት ታውቃለህ?"
"አዎ"
"አልፈልግም በቃ አቁም!! .... አልፈልግም አልኩ እኮ " እጮሃለሁ ....
"እሷ ግን እንዳንቺ አትጣፍጠኝም!" (ውሸቱን እንደሆነ አውቃለሁ .... ቢሆንም ደስ ይላል)
"እሺ አታቁም .... ቀጥል" እላለሁ ፈገግ ብዬ
.....
.....
....
አንድ ቀን ሀቅ አመለጠው ..."እውነቱን ልንገርሽ ... አልጋ ላይ ትበልጫታለሽ .... ልቧ ግን ይበልጥሻል:: ንፁህ ሴት ናት እሷ!"
"ውረድልኝ ወደዛ .... እላዬ ላይ ዘጥ ዘጥ እያልክ ስለንፁህነት በሙሉ አፍህ ታወራኛለህ?"
አስጠላኝ ..... ሲደውል አላነሳለትም .... በየቀኑ የሚፀፀትበትን ውጊያ ለመዋጋት ለምን እንደሚለምነኝም አይገባኝም ..... !!!
.....
.....
...
"አይዞሽ ኤዱ አይዞሽ.." ይለኛል የእህቴን ሬሳ ልሰናበት በቆምኩበት የሚንዠቀዠቅ እንባዬን እያየ
'የምርህን ነው ግን እንዲህ እየተንፈራፈርክ የምታለቅስላት?' ልለው ያምረኝና ... እኔስ የምሬን ነው? ለምንድነው የማለቅሰውስ? ... ምናልባት እሱም ከቅንዝራምነቱ አስበልጦ አይወዳት ይሆናል እንጂ ይወዳታልኮ .... እኔም ከቅናቴ አያይልም እንጂ.... እህቴኮ ናት!!
አለቀስኩ ..... ምርር ብዬ እየተንገፈገፍኩ አለቀስኩ ... ለሷ ይሁን ... ለራሴ... ለሀጢያቴ ... ለፀፀቴ ..... ብቻ ድንኳኑ ገና አሁን ሞቷን የተረዳ ይመስል በለቅሶ ግልብጥብጡ እስኪወጣ እሪሪሪሪሪሪሪ አልኩ .....
"ገደልሽ ..... ገደልሽኝ ...... ገደልሽኝ" ደጋግሜ የምለው ይሄን ነው ...... ያደረግኳትን ሁሉ በሞቷ ተበቀለችኝ ....
......
የሙሽራ ቀሚሷን ካበላሸሁባት በኃላ ... ለወራት አኩርፋኝ ነበር .... ሌላ የተገኘውን ቀሚስ ሚዜዎቿ ተከራይተው ተሞሽራ አለፈ:: ....
"ትጠይኛለሽ?" አለችኝ ከወራት በኃላ እቤት መጥታ ...
"አልጠላሽም!" አልኳት
"ታዲያ ለምንድነው ሀዘኔን ማየት የምትፈልጊው? እኔ ምንድነው የበደልኩሽ?"
"ምንም! ...... አላውቅም!! ምናልባት አንቺን ከምወድሽ በላይ ራሴን እጠላዋለሁ መሰለኝ .... አላውቅም!!"
"ኤዱዬ በስመአብ ወልድ .... !!(አማተበች) እሺ ለምን አታወሪኝም? ልስማሽ ንገሪኝ!"
"መናገር እንደማይሆንልኝ ታውቂያለሽ!"
አቅፋኝ ብዙ ቆየችና "እሺ እኔ ምን ላድርግልሽ? ኤድዬ ለኔኮ ያው መንታ እህቴ ነሽ.... ከአንድ ማህፀን አለመውጣታችን it doesn’t matter at all... እንዲህ አድርጊ በይኝ ላንቺ ጥሩ ስሜት ከሰጠሽ አደርጋለሁ::"
"ማሸነፍሽን ተይኝ!!" አልኳት ሳላስበው .... ግራ ገባት .... "አየሽ .... የሰርግ ቀንሽን አበላሽቼብሽ እንኳን ምንም እንዳላደረግኩኝ .... ጭራሽ ታዝኚልኛለሽ .... እኔ ልጥልሽ እታገላለሁ .... አንቺ ሳትታገዪ ሁሌም ታሸንፊኛለሽ .... ተይ በቃ .... እንደ እኔ ክፉ መሆን ባትችዪ እንኳን መልካም አትሁኚልኝ!!"...
በጣም ግራ ተጋብታ ስታየኝ ቆይታ
"ኤዱዬ እባክሽ ሳይካትሪስትጋ ሂጂ .... ቢያንስ ስትተነፍሺ ይወጣልሻል:: ቁጣሽ ይበርዳል!!" አለችኝ ...... አልሰማችኝም ..... ያልኳት አንዱም አልገባትም ..... አሁንም በለጠችኝ!!! ለዛ ነው የማላወራው .... ለማንም አይገባም ....
......
.....
....
"ገደልሽኝ .... ገደልሽኝ ..... " እሪታዬን ማቆም አቃተኝ ..... ድምፄ እየተዘጋ መጣ ..... አባቴ መጥቶ ከወደቅኩበት አነሳኝ .....
"ልቀቀኝ .... ልቀቀኝ!" ብዬ የጮህኩት ምንም የማክበር ለዛ በሌለው ቁጣ ነው .... ደንግጦ እጁን አሸሸ.... ራሴን ፈራሁት ... እሱም የፈራኝ ይመስላል ...... እንዳልፈነዳ እና እንዳልፈጀው ....
......
.....
.....
ለመጨረሻ ጊዜ 'አባ' ብዬ የጠራሁት ቀን 17 ዓመቴ ነበር ..... እንባ እና ንፍጤ ፊቴ ላይ ተለዋውሰው .... እንደ አባት መከታ እንዲሆነኝ ዓይን ዓይኑን እያየሁ ... ባለፈው እህቴ ከትምህርት ቤት ስትመለስ መንገድ ላይ ጎረምሳ በጥፊ መቷት ... እያለቀሰች ስትነግረው ደም ስሩ ተገታትሮ እየፈላ ሄዶ ልጁን አሩን እንዳበላው .... 'እኔ አባትሽ እያለሁ' እንዲለኝ .....የእኔማ ይብሳል .... ይገድላቸዋል.... የገዛ ቤቱ ... ልጁ ተደፍራ ... አለቀላቸው ....
"አባ ..." መናገር አቅቶኝ እንሰቀሰቃለሁ .... ሲጨነቅ ቆይቶ
"ይሄን ጉድ ለማንም እንዳትናገሪ የኔ ልጅ !!" አለኝ ... የቱን ጉድ እንደሆነም በደንብ አልገባኝም ... እኔ በአራት ጎረምሳ መደፈሬ? ወይስ ከደፋሪዎቹ አንዱ አብሮን የሚኖረው የሱ ወንድም ልጅ መሆኑ? እቤቱ መሆኑ? ....
"የኔ መደፈር ነው የሚያሳስብህ ስምህ?" አልኩት ተናግሬው በማላውቀው ቁጣ
"መደፈር ብለሽ ጭራሽ ነገሩን አታጋኚው .... ድንግል የነበርሽ ነው የሚመስለው:: ሲጀመር ክፍልሽ ድረስ አራት ጎረምሳ ምን ስታደርጊ አስገባሽ?"
እንባዬ ደረቀ ..."ቤቱ ነውኮ .... ወንድሜ ነውኮ .... እህቴ ናት ብሎ ነው ለጏደኞቹ ያስተዋወቀኝ....ሰላም ልንልሽ ነው ብለው ነው የገቡት ... ውጡ ልበላቸው? ይሄ ይሆናል ብዬ አስባለሁ?" ማስረዳት ቸገረኝ.....
"ወንድምሽ አይደለም:: ልጄ ... ነገሩን የባሰ አፀያፊ እያስመሰልሽው ነው:: ... በደም እንደማትዛመዱ ታውቂያለሽ!! ቀድሞውኑ እንደ እህትሽ ስብስብ ብለሽ ብትቀመጪ ......"
ከዛ በኃላ ያወራውን ብዙም አልሰማሁትም ....
"እሱ ወንድሜ ካልሆነ ... እሷስ በምን በኩል እህቴ ሆነች? አይደለችም!" አልኩት .....
........ አልጨረስንም ..........