አልወዳትም እንጂ አልጠላትም .....#3
እንድትሞት በጭራሽ አልፈልግም ነበር:: ስለምወዳት አይደለም !!!.... በቁሟ ልበልጣት .... ላሸንፋት ነበር ትግሌ ..... ሞቷማ ኪሳራዬ ነው::
የሞቷ ቀን ማታ በሬን አንኳኳች ........ ደፈራርሰው ያበጡ ዓይኖቿ .... የተንጨባረረው ፀጉሯ ....የሚንቀጠቀጡ እግሮቿ ... የሆነ ነገር እንደተፈጠረ ገባኝ::
"ትዳሬን? ኤዱዬ ፍቅሬን? እንዴት እንደምወደው እያወቅሽ? ምን ብበድልሽ ነው እንዲህ የከፋሽብኝ? እስኪ ንገሪኝ እኔ ምንድነው ያደረግኩሽ?" ከንፈሯ ይንቀጠቀጣል..... እንባዋ ይከታተላል ..... አሳዘነችኝ .... ማታ አልጋቸው ላይ ሲዋደቁ የእኔን ስም እንደጠራባት ነገረችኝ ... ፈገግታዬ አመለጠኝ::
"ይሄን ነው prove ማድረግ የፈለግሽው? ከኔ የተሻልሽ መሆንሽን ከባሌ ጋር ተኝተሽ ነው ማረጋገጥ የምትፈልጊው?" እየተናደደች መጣች ..." .... ጤነኛ አይደለሽም ..... ይሄ በሽታ ነው!..... " ደሞ ምልስ ትልና አሳዛኝ ትሆናለች ... "እንዴት ክፉ ነሽ ግን በማሪያም?...." ኩርምት ብላ ትንሰቀሰቃለች ........
ዝም ብዬ እሰማታለሁ:: .... ስታለቅስ... ምን ያህል ክፉ ሴት እንደሆንኩ ቃላት እየቀያየረች ስትነግረኝ... ስትናደድ ... አንድ ሰዓት ያህል ዝም ብዬ ሰማኃት ...
ለምንድነው የመሸነፍ እንጂ የድል ስሜት የማይሰማኝ ታዲያ? ..... በክፋት መብለጥ የለም ይሆናል....
"ታውቂያለሽ ወንድምሽ ከደፈረኝ በኃላ አብሬው የተኛሁት ወንድ ባልሽ ነው!!" አልኳት .... (አታውቅም... እንደማታውቅም አውቃለሁ:: .... ፊቷ የሆነ ነገር የፈነዳበት ይመስል ተመሰቃቀለ::)
"ቤተሰቦችሽ እኔ ለተደፈርኩት ... እህትሽ ከሰማች ትጎዳለች ... እንዳትሰማ ብለው ተጠነቀቁልሽ:: ... አስበሽዋል? እኔ እሳት ውስጥ ሆኜ እየነደድኩ .... ሙቀቱ አንቺን እንዳይነካሽ እየከሰልኩ ዝምም ጭጭጭጭ ብዬ ስነድ?"
ዝም አለች:: ክው ብላ ደርቃ ከአፌ የሚወጡት ቃላት የሆኑ የሞት ፍላፃዎች ይመስሉ እየተንቀጠቀጠች ትጠብቃቸዋለች .....
ሁሌም እንደዛ ነበር ... የሆነ የተረገመ ቀን እቤታችን የመጣች እንግዳ
"በስመአብ ቁልጭ እናትሽ አይደል እንዴ? ነፍሷን ይማረው ፀጉሯን እንዲህ ማስያዝ ትወድ ነበር እሷም!" ብላ የማውቅ የመሰላትን ቦንብ ከማፈንዳቷ ቀን በፊት
'ውይ ልጄ ደረቅ ዳቦ አትወድምኮ' ተብሎ እኔ ደረቅ ዳቦ ስበላ ለእህቴ እንቁላል መሰራቱን በክፉ ተርጉሜው አላውቅም ነበር::
'እሷ ጎበዝ ተማሪ ስለሆነች' ተብሎ እሷ የግል ትምህርት ቤት ስትማር እኔ የመንግስት መማሬን ጉብዝናዋ የሰጣት ሽልማት ነው ብዬ ከማሰብ ዘልዬ አላውቅም....
'እሷ ቆንጆ ስለሆነች ጎረምሳ አያስኬዳትም' በሚል የሚያመላልሳት መኪና ሲከራዩላት ... እኔ ጥፍጥፍ መሆኔን አምኜ ከሷ ትምህርት ቤት የሚርቅ ትምህርት ቤቴን መንገድ በእግሬ እየፈጨሁ ለእህቴ ጥበቃ ከመደሰት ያለፈ የተሰማኝ አልነበረም::
እህቴ ናታ.... በመልክም በባህሪም በጭራሽ የማንመሳሰል መንታ እህቴ ....
"እናቴ ማናት?" ብዬ ጎፈላሁ እንግዳዋ ከሄደች በኃላ ..... 13 ዓመቴ ነው:: እናቴ(አሳዳጊዬ) እህቴ እንዳትሰማ እሽሽሽሽ አስብላኝ
"ይሄን ነገር ግን በፍፁም እህትሽ እንዳትሰማ... እንዴት እንደምትወድሽ ታውቂያለሽ አይደል? ቃል ግቢልኝ በፍፁም ለእህትሽ እንዳትነግርያት .... " ብላ መርዶዬን ነገረችኝ .... እናቴ የኛን ቤት ተከራይታ የምትኖር የቡና ቤት ሴት እንደነበረችና እኔን ስትወልድ እንደሞተች ነገረችኝ .....
አሳዳጊዎቼ ልጅ የመውለድ ተስፋቸው ባዶ መሆኑን በዶክተርም በጥበቃ ብዛትም ባረጋገጡበት ወቅት የእኔ እናት እንደ ተዓምር ከማን እንዳረገዘች የማታውቀውን ልጅ ልታስወርድ ዱብ ዱብ ስትል ነው አሳዳጊዎቼ በደስታ እኔን ሊያሳድጉኝ ቃል ገብተውላት እናቴ የወለደችኝ .... ቆይ ....!!!! እህቴ ከእኔ ጋር ግብ ግብ የጀመረችው ገና ሳላውቃት
ሳታውቀኝ ... በእናቴ ሆድ ሆኜ ነው...
ለዓመታት ልጅ አልሸከም ያለው የአሳዳጊዬ ማህፀን ልክ እናቴ ሆድ እኔ መደላደል ስጀምር እህቴን ቋጠረ:: .... ውድድሩ ተጀመረ....
"በቃ አሁን የራሳችንን ልጅ ስላገኘን ልጅሽን የማሳደግ ፍላጎታችንን ትተነዋል" ብለዋት እንደነበር አድጌ ያቺ እንግዳ ናት የምትነግረኝ ... እናቴ በማላውቀው ምክንያት ልትወልደኝ ወሰነች.... ስትወልደኝ ሞተች:: አሳዝኛቸው.... ወይም ልውሰዳት ያለ ዘመድ ስለጠፋ... አልያም እግዜሩን ፈርተው ለፅድቅ ትሆነናለች ብለው ... አላውቅም:: ወሰዱኝ...... በወሩ እህቴ .... መንታዬ ተወለደች::
ቤተሰብ ያጣሁት እኔ .... የኖርኩት ህይወት ሁሉ እንክትክት ብሎ የውሸት ካብ ሆኖ የተናደብኝ እኔ .... የተዋሸሁት እኔ .... "እሷ ከሰማች ይከፋታል..." ተብሎ የምትጠበቀው እሷ ....
"ለምን አልነገርሽኝም? እንዲህ ሁሉ ስትሆኚ ምናለ ብትነግሪኝ? ይሄ ጅብ እንዴት እህቱ ላይ እንዲህ ያደርጋል?" አለችኝ መልሳ ወንድሜ የምትለው የአጎቷ ልጅ ከጏደኞቹጋ ያደረገኝን ስነግራት ... ባሏን እንዳባለግኩባት ረስታው አቅፋኝ ለእኔ መንገብገብ ጀመረች .....
"ቤተሰቦችሽ ሁሉም ነገር በደም ካልተገመደ ዋጋው አይታያቸውም ..... በደም ስለማንገናኝ እህቱ አልነበርኩም ..... ደም ስላልፈሰሰኝ ደፈረኝ እንዳልል ዝም አስባሉኝ .... ስህተት ነው ተባለለት .... ድሮም የጀመረችው ነው ተባለና የሱን አውሬነት በእኔ ጥፋት ከደኑለት ..... እሽሽሽሽሽሽ ዝም በይ ተባልኩ::"
አሁንም ልክ እንደ ቅድሙ መንሰቅሰቅ ጀመረች .....
"በህይወቴ አንድ ነገር ይሁንልሽ ብሎ ፈጣሪ ቢጠይቀኝ ምን እንደምሻ ታውቂያለሽ?" አልኳት ....
"ምንድነው?" አለችኝ ማድረግ የምትችለው ነገር ቢሆን አሁኑኑ የምታሳካልኝ በሚመስል ጉጉት
"አንቺን እንዲያደርገኝ .... አንቺን መሆን"
ዝምምምምም አለች::..... አሳዘንኳት .... ዝምምምም አለች .....
"እሺ እኔ ምን ላድርግ? እነአባቢን ልጣላቸው? ያ ደስ ይልሻል? ወይም እኔን እንደሚወዱኝ እንዲወዱሽ ልንገራቸው? ስራ ልተው? ስራ ባይኖረኝ ደስ ይልሻል? አብርሽን ብቻ ተይልኝ አትበይኝ .... እሱን አልችልም.... ኤዱዬ እሱን ከራሴ በላይ እወደዋለሁ:: ሌላ የፈለግሽውን ላድርግልሽ እንዳሸነፍሽኝ ከተሰማሽ..." አለችኝ ..........
አዎ በክፋት አይበለጥም ......... ይኸው አሁንም በዝረራ አሸነፈችኝ ....
"ውጪልኝ!!" አልኳት በቀስታ ..... "ውጪልኝ .... ከህይወቴም ከቤቴም ውጪልኝ ... " እያልኳት ለራሴ 'በቃኝ' እላለሁ ..... ርቄ እሄዳለሁ ... ሁላቸውንም የማላይበት .... ሁሉንም ከኃላዬ ጥዬ ብንንንንንን ብዬ እሄዳለሁ ....
......... አልጨረስንም ..........

👍15❤2👎1
አልወዳትም እንጂ አልጠላትም.....#4
'ከቤቴ ውጪልኝ' የሚለውን ዘላ 'ከህይወቴ ውጪልኝ' ያልኳትን ሰምታኝ መሰለኝ....... የሞተችው......
"ኤዱዬ የኔ ከህይወትሽም ከቤትሽም መውጣት አንቺን አያስተካክልሽም!! Let us make this right!! ላግዝሽ?" አለችኝ ....
"የቱን? የቱን ነው የምናስተካክለው?" አልኳት "ያንቺ እህት አለመሆኔን? ንገሪኝ ከየት እንጀምር? ገና ሳልወለድ ቤተሰቦችሽ ከከዱኝ? ወይስ ለ13 ዓመት እማ አባ ያልኳቸው ቤተሰቦቼ ሳይሆኑ የወለደችኝ ሌላ ሴት መሆኗን እንዴት ነው የምናርመው? ከየት እንጀምር ንገሪኝ? .... ጥፋት ሳጠፋ 'ዘር ከግንዱ ይመዘዛል' እየተባልኩ .... በራሴ መንገድ ስጏዝ 'እንደእህትሽ ብትሆኚ ምናለ?' እየተባልኩ ማደጌን ምኑጋ እናቅናው ?" ......
እንዲህ ለማንም አውርቼ አላውቅም.... የተሰማኝን ህመም ሁሉ መዋጥ እንዳለብኝ ተነግሮኝ ነው ያደግኩት.... ጭጭ... እሽሽሽሽሽ ተብዬ ... እየታመሙ መሳቅ ለምጄ ነው ያደግኩት ....
"ወንድሜ ስለው ያደግኩት ወንድ ከጏደኞቹ ጋር የደፈረኝን ምኑጋ እናቅናው እህቴ? ንገሪኝ ?.... እኔ .... እኔ መቃናት አልችልም!! .... የእኔ ህይወት የቱምጋ አይቃናም!! .. "
"ወደኃላ ተመልሶ ቢቃና .... ሀ ብዬ ሌላ ሰው ሆኜ መፈጠር ነው የምፈልገው.... ያንቺ እህት ሳልባል... አንቺ በምታገኚው ፍቅር ሳልቀና ... ባንቺ ጉብዝና ራሴን ሳልለካ.... እንዳንቺ ቆንጆ ለመሆን ሳልመኝ.... ባጠቃላይ ካንቺ ሳያወዳድሩኝ 'እኔን' የሚወዱኝ ቤተሰቦች ልጅ ሆኜ መፈጠር ነው የምፈልገው ..... ክፉ ... ቀናተኛ ... ሳልሆን ...."
ከተቀመጠችበት ሳትነሳ ብዙ ቆየች.... እኔ ህመሜን ብዙ አወራሁ .... ከቤቴ ስትወጣ ....
የኔን ሸክም ሲደመር የጥፋተኝነት ስሜት ሲደመር ባሏ ከእህቷጋ የባለገባት ሚስት የልብ ስብራት ... ይሄን ሁሉ ተሸክማ ከአንገቷ አቀርቅራ .... የጎበጠች መሰለኝ ...
"ኤድዬ ህመምሽን ስላልታመምኩልሽ ይቅርታ!!" ብላኝ ወጣች .... እኔ 30 ዓመት ቀስ በቀስ የጠጣሁትን ጎምዛዛ ክፋትና በደል ... በአንድ ቀን ጋትኳት .... ከበዳት!!
....
.....
...
የቀብር ቦታው ላይ ሬሳዋን ወደ ጉድጏዱ ሲነዱት እያየሁ ...ምናለ አቅፌያት ቢሆን? 'ያንቺ ጥፋት አይደለም' ብያት ቢሆን? ምናለ ዝም ብዬስ ቢሆን? .... ምናለ..... ምናለ.... እያልኩ እንሰቀሰቃለሁ:: .....
.....
.....
ከቤቴ ከወጣች በኃላ ለሰዓታት ከተቀመጥኩበት ሳልነሳ ስልኬ ጠራ!!
"እህትሽ አርፋለች!"
ምንም አልጠየቅኩም:: እስከአሁንም ድረስ የደወለልኝ ማን እንደሆነ አላውቅም:: ... ስልኩንም ከዘጋሁ በኃላ ለሰዓታት እዛው ተቀመጥኩ:: ድጋሚ ስልኬ ጠራ:: ጏደኛዋ ናት::
"ኤዱ የት ነሽ?" አለችኝ በማልቀስ በሻከረ ድምፅ .... 'እንዴት እህትሽ ሞታ ለቅሶ ቦታ የለሽም' የሚል ድምፀት ባለው ቃና
"ምን ሆና ነው?" የሚል ጥያቄ ነው ከአፌ የወጣው....
"ወየው ጉዴ አልሰማሽም? (ለቅሶ አስከትላ) ምን እንዳጋጠማት ምን አውቄ? ራሷን ነው ያጠፋችው::" አለችኝ ...... ስልኩን ዘጋሁት .... እስኪነጋ ከተቀመጥኩበት አልተነሳሁም:: ..... ፀሀይዋ ብቅ ስትል ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ለቅሶዋ ላይ ተገኘሁ:: ስገባ ነጠላ ትከሻዬ ላይ አደረጉልኝ.... ምፅ ምፅ እያሉ ደግፈው ወንበር ላይ አስቀመጡኝ ...... ግራ ገባኝ ....
ሲያፈጡብኝ አለቅሳለሁ .... እንባዬ ይተባበረኛል ..... እስከቀብሯ ቀን ድረስ ሲያለቅሱ ከማልቀስ .... ሲያፈጡብኝ 'ጨካኝ' ላለመባል አይኔን ከማስጨነቅ ያለፈ የሚሰማኝንም ስሜት ለይቼ አላወቅኩትም::
አፈሩን ሲያለብሷት ልቤን ሞት ተጫነው:: ዝም ጭጭ .... ያለ ስሜት ተሰማኝ:: አብሬያት ጉድጏድ ውስጥ የገባሁ ስሜት .... አፈሩ እኔ ላይ የሚጫን ስሜት .... ራሴን ልስት አይነት ስሜት ይሰማኝና ተስተካክዬ ለመቆም እሞክራለሁ .. .... የሚሰማኝ ዝምታ ብቻ ሆነ ... ከዛ .... ጨለማ!!!!
እንደሞት ያለ ጨለማ ........
"ምን ሆኜ ነው?" አልኩኝ አይኖቼን ስገልጥ ሆስፒታል እንዳለሁ ገብቶኝ:: ...... አጠገቤ የእህቴ ጏደኛ እና እናቴ (አሳዳጊዬ) ነበሩ:;
"ቀብር ቦታ ራስሽን ስተሽ ነው" አለችኝ ጏደኛዋ .... ፊታቸው ላይ የሆነ የጉጉት ስሜት አየሁ..... ስለነቃሁ የመደሰት ግን ያስደሰታቸው መንቃቴ ብቻ ሳይሆን ሌላ ነገር እንዳለ ገባኝ
"ምንድነው?" አልኩኝ ወደ እናቴ ዞሬ ..... ከአፌ
እስኪወጣ ስትጠብቀው የቆየ ቃል ይመስል ቅብል አድርጋ
"ምን ማለቷ ነው? ምንድነው?" ብላ የሆነ ፖስታ ሰጠችኝ
"ምንድነው?" አልኩ እየተቀበልኩኝ
"እህትሽ ከመሞቷ በፊት ያስቀመጠችልሽ ደብዳቤ ነው! ምን ማለቷ ነው? ከሁላችን መርጣ ለምንድነው ላንቺ የፃፈችው? የፃፈችው ምኑን አልገባኝም!" አለችኝ
"ለእኔ ከሆነ የተፃፈው ለምን አነበባችሁት?" አልኩኝ ፖስታው ላይ ለኤደን ብቻ የሚል ፅሁፍ እያየሁ .,,......
.......... አልጨረስንም............

👍13❤2🤮1
አልወዳትም እንጂ አልጠላትም ....#5
(የመጨረሻ ክፍል)
"ኤደን ምን ይሰማሻል?"
"ምንም"
(ዝም ተባብለን ሰዓቴ አልቆ እመለሳለሁ::)
በሌላኛው ቀንም ........
"ኤደን ዛሬስ ለማውራት ዝግጁ ነሽ?"
"አይደለሁም!! ማውራት አልፈልግም!"
(ዝምምምምም..... ሰዓቱ ያልቃል)
ደግሞ በሌላኛውም ቀን
"ኤደን ዛሬስ ለመጀመር ዝግጁ ነሽ?"
"ምኑን?"
" ማውራት ትፈልጊያለሽ?"
"እኔ ምንም የማድረግ ፍላጎት የለኝም!!"
(የምፈልገው አንድና አንድ ነገር .... የቀብሯ ቀን ጭልጥ አድርጎ የወሰደኝ ጨለማ ለዘለዓለሙ እንዲወስደኝ ነው)
በሌላኛው ቀን አልጠየቀኝም:: ገብቼ ስቀመጥ ሰላምታ ሰጥቶኝ ዝም አለ::
"ዛሬ አትጠይቀኝም እንዴ?"
"ምኑን?"
"ዝግጁ መሆን አለመሆኔን?"
"ነሽ?"
"አይደለሁም!"
"ጥሩ!! ዝግጁ እስክትሆኚ ድረስ የሚሰማሽ እዚህ መጥቶ መቀመጡ ከሆነ ዝም በይ... ማውራት ሲሰማሽ አውሪ.... ማልቀስ ሲሰማሽ አልቅሺ.... መጮህ ሲሰማሽ ጩሂ ..... ሰዎች ሀዘናቸውን በተለያያየ መንገድ ነው የሚያስተናግዱት.... የተለያየ ጊዜ ይወስድባቸዋል::"
"ሀዘን አይደለም የሚሰማኝ!!"
"እሺ!! ምንድነው የሚሰማሽ?"
"ምንም!!! ዝም ... ፀጥ .... ያለ ስሜት!!"
ለብዙ ቀናት ተመላለስኩ .... እሄዳለሁ:: እቀመጣለሁ:: ሰዓቴ ያልቃል:: እመለሳለሁ::
"ዛሬ አሻንጉሊትሽን የት ትተሻት መጣሽ?" አለኝ
"ሰጥቻት መጣሁ:: ..... 'ያውልሽ' ብዬ መቃብሯ ላይ ወርውሬላት መጣሁ:: ትውሰደው .... " እንባዬ ከወራት በኃላ ላስቆመው እንዳልችል ሆኖ ይንጠኝ ገባ ...... ማልቀስ ማቆም እፈልጋለሁ:: .. አቃተኝ.... የቀብሯ ቀን እንደሆነው ራሴን የምስት መሰለኝ .... ጨለማው ናፈቀኝ... ግን አልመጣም... አልወሰደኝም.... ደብዳቤዋን ከኪሴ አውጥቼ ሰጠሁት::
"አየህ በዝህች ሁለት መስመር ደብዳቤ እንዳልሞትም እንዳልኖርም አስራኝ ሞተች:: አንብበውማ! ጮክ ብለህ አንብበው!!"
" አንቺ ደግሞ በተራሽ የእኔንም ደርበሽ ኑሪልኝ:: የከፈልኩትን ዋጋ እንዳታከስሪኝ .... ደስ ተሰኝተሽ ኑሪና ዋጋዬን ክፈዪ!! .... ፖኒን ትቼልሻለሁ::" ጮክ ብሎ አነበበው .... ቤተሰቦቻችን እንዳልገባቸው ሁሉ እሱም አልገባውም..... የሆነው ሳይገባቸው ነው 'ጭንቅላቷ ተቃውሷል' ብለው ሳይካትሪስት የቀጠሩልኝ....
"ፖኒ ያቺ አሻንጉሊት ናት!" እንደገባው ራሱን ነቀነቀ.... "በጣም ልጅ ሆነን ለሁለት አንድ አሻንጉሊት ተገዛልን:: እሷ ስም አወጣችላት:: አልተቃወምኩም:: .... የሆነ ቀን እኔ ስጫወት ደርሳ ካልወሰድኩ አለች ... ተደባደብን ... አባታችን መጥቶ አሻንጉሊቷን ከእኔ ቀምቶ ለሷ ሰጣት ... ቀን ቀን በአሻንጉሊቷ መጫወት የምትችለው እሷ መሆኗን አወጀ:: ከፈለግኩ ማታ እሷ ስትተኛ መጫወት እንደምትችል... ያውም እሷ ከፈቀደችልኝ..... ነገረኝ:: ምርርርርርር ብዬ አለቀስኩ::...... ያስለቀሰኝ ከአባታችን ለሷ ማገዝ በላይ የሷ መደሰት ነበር:: እንዳለመታደል ሆኖ ሁሌም እሷ ስትተኛ ጠብቄ ለመጫወት እቀመጥና እንቅልፍ ቀድሞ ስለሚጥለኝ ያልፈኛል::.... ምን ማለቷ ነው? ስትሞት ትታልኝ የምትሞተው?"
"ምን ማለቷ ይመስልሻል አንቺ?"
"እኔ ምን አውቅላታለሁ? ህይወትሽን የቀማሁሽ እዛጋ ነው ... ከዛ ጀምሪ ማለቷ? ያውልሽ ይስፋሽ ማለቷ? እኔ ምን አውቅላታለሁ ምን አድርጊ እንደምትለኝ? ቆይ እሷ ራሷን እንደክርስቶስ ነው የምታየው? ማነኝ ብላ ነው የምታስበው ህይወቷን ስትሰጠኝ ..... በቃ ሞተችልኝ ብዬ በደስታ የምኖር ነው የመሰላት? ደሞ ቆይ ክርስቶስኮ ለአንድ ሰው አልሞተም .... ለዓለም ህዝብ ነው የሞተው... ክርስቶስ ለአንተ እንደሞተልህ ብታውቅም ስላላመንከው እኔ አሁን የሚሰማኝ አይነት ሸክም አይሰማህም .... ሌላ የሆነ ሰው አምኖ እንደሚያገለግለው ታውቃለህ ... እሷ ምን አስባ ነው ለአንድ ለእኔ ህይወት ከፍላ ... ከዛ በደስታ እንድኖርላት የምትፈልገው? ቆይ የቱጋ ሀ ብዬ መኖር እንድጀምርላት ነው? ቆይ አንተ ስታስበው ጤነኛ ሆኜ ራሱ መኖር የምችል ይመስልሃል?"
"አዎ ይመስለኛል!!"
"እኮ እንዴት?" ..... እስከዛሬ ያላወራሁበትን ሰዓታት ጨምሬ ለፈለፍኩ::
"ራስሽን ይቅር በማለት ትጀምሪያለሽ!!"
"ሌላ 30 ዓመት መኖር ቢሰጥሽም መኖር አትጀምሪም አትለኝም ታዲያ?"
"ሳይኖሩ ከመሞት መኖር ጀምሮ መሞቱ አይሻልም ታዲያ? ...... "
......
.....
"ለራሴ ስል መኖር አልፈልግም..... ለሷ ስል ደግሞ መሞት አልፈልግም"
.....
"ሁለቱን ለማስታረቅ ነው ከራስሽ መታረቅ ያለብሽ..... "
................. ጨርሰናል................
(አላለቀም ብትሉም አልቋል..... አልቋል ብትሉም እንደዛው)

👍16💯3❤2
ውድ የዚህ ቻናል ቤተሰብ ...👆🏼👆🏼 ከላይ የፃፍኩላችሁን 'አልወዳትም እንጂ አልጠላትም' የሚለውን ፅሁፍ በፌስቡክ ገፄም እያጋራሁት ነበር:: የመጨረሻውን ክፍል ስለጠፍ የአብዛኛው ሰው አስተያያየት ታሪኩኮ አላለቀም የሚል ነበርና አንድ ሀሳብ አመጣሁ!! ታሪኩን በሚፈልጉት መንገድ እንዲጨርሱትና አሳማኝ አድርጎ ለጨረሰ ሽልማት ለመስጠት ... በመሆኑም የሚከተለው ፅሁፍ ከ53 ፅሁፍ አንደኛ በመውጣት የ4000 ብር ተሸላሚ ሆኗል:: እንደ ክፍል 6 እንድታነቡት ጋበዝኳችሁ!!
👍2
አልወዳትም እንጂ አልጠላትም… [6]
[ ከ Meri Feleke የቀጠለ]
እሱ ወደ በረንዳው ሲወጣ ክፍሉን ለቆ መሄድም መቆየትም በማይፈልገው የባዶነት ስሜቴ ውስጥ ሆኜ አስተዋልኩት። በመስኮቱ በኩል በረንዳው ላይ ጀርባውን ላለሁበት ክፍል ሰጥቶ ቆሞ ይታየኛል። አቋቋሙን ሳልፈልግ ማጤን ያዝኩ። ልቡናዬ ስራ ያገኘ ስለመሰለኝ ለቅፅበትም ቢሆን ከግሌ ዓለም በመውጣቴ ደስ ሳይለኝ አልቀረም።
አቋቋሙን ደግሜ አስተዋልኩት። በአንድእጁ የበረንዳውን ብረት ይዟል። ከወገቡ በታች አስተዋልኩት ቀኝ እግሩ ሸብረክ ብሏል። ግራ እግሩ ተወጥሮ ሰውነቱን ተሸክሞታል።
በእጁ ጣቶች ሙዚቃ በሚመስል ሥልተ–ምት ባለው ነገር የበረንዳውን ብረት ይጠበጥባል። ሙዚቃውን መገመት አማረኝ…
ጥቂት ቆይቶ ወደኔ ሲመለስ አየሁት። ሳላስበው ጥያቄ አመለጠኝ። "ሙዚቃ እያንጎራጎርክ ነበር?"
ፊት ለፊቴ ተቀመጠ። "ለዘፈን የሚሆን ድምፅ የለኝም። ሃሳቤ ውስጥ ጠዋት የሰማሁት የ Ray LaMontagne "Trouble" የሚል ሙዚቃ እየተመላለሰብኝ ነበር።" ፈገግ አለ። ጥቂት ብልጭ ብሎ በጠፋ ፈገግታው ውስጥ ጥርሶቹን አየኋቸው። አልተበላሹም።
"የምትነግሪኝ ነገር ያለ ይመስላል፤ ልክ ነኝ? " አለኝ። መረጋጋቱ ውስጥ ጥንካሬው ያረጋው መናወጥ ያለ ለምን መሰለኝ?? እንዳፈጠጥኩበት ሲገባኝ አይኔን ሰበርኩ። መልሼ ሳየው "ንገሪኝ" የሚል አይነት እይታ ገፁ ላይ አነበብኩ።
"ታካሚህ ባልሆን የምታጋራኝ እውነት ወይም የሆነ የምትነግረኝ ነገር አለህ?" ጠየኩት።
ትከሻውን ሰበቀ። "ማወቅ የምትመኚው ነገር ካለ…" በሚል።
በዝምታ ቆየን።
"የምንጠላው ደግ ማንነት ሲሰዋ መታወክ ካጋጠመን፣ በውስጣችን የሚሞተው ክፉ ማንነት ስለመሆኑ እያሰብኩ ነበር።" አልተረዳሁትም። አውቆታል መሰለኝ… ቀጠለ። እሱን በስራ የጠመድኩት ስለመሰለኝ ተዝናናሁ።
" ጠቅላላ ሐኪም የነበረ ወዳጅ ነበረኝ። በወጣትነቱ ነበር ያገባው። ብዙዎች በማይደፍሩት እድሜ። ትዳሩ የሰመረ የሚባል አልነበረም። እጅግ የከፋ ማንነትን አዳበረ። ባለቤቱ የተሸከመችው ሰው በጊዜ ሂደት ጥላቻ፣ ቅናት፣ መሰላቸትና፣ ውስልትና ደራርቦ የተቀባ ማንነት ነበር። ከበዳት። እናም ለከባድ ድባቴ ተጋለጠች። የእንቅልፍ ክኒኖች ቀለቧ ሆኑ። አንድ ቀን ምሽት ወደ ቤቱ ሲመለስ የተለመደ ድባቴዋ ውስጥ ሆኗ ያገኛታል። አልፏት ገብቶ ተኛ። ማለዳ ላይ ሲነቃ ባለቤቱ እስከመጨረሻው አሸልባለች። አንቺ ባለፍሽበት የሃዘን ጥግ ሆኖ ጊዜያትን በፀፀት ውስጥ አለፋቸው። ስለሞተው፣ መቃብር ስለወረደው ደግነቷ በፀፀት ነደደ። ለወራት መስታወት ፊት ይገተራል። ራሱን መመልከት በጀመረ ቀን አምርሮ ጠላው።"
ወሬውን ሲገታ የሰውዬውን ምስል በአይነህሌናዬ ስዬ ጨርሻለሁ። ሰአታችን ማብቃቱ ገብቶኛል። ከወትሮው ቆይቻለሁ። "ሙዚቃ ማድመጥ ስሜቱ አለሽ? " ጠየቀኝ። መልሴን ሳይጠብቅ አንድ ዲስክ አቀበለኝ። ክፍሉን ለቅቄ ወጣሁ። በተደበላለቀ የሃሳብ ማዕበል ውስጥ ሆኜ…
----
🎵Trouble
Trouble been doggin' my soul
Since the day I was born
🎵Worry
Worry just will not seem to leave
My mind alone... ሙዚቃው ውስጥ ያሉ የመጀመሪያ ስንኞችን ስሰማ ለኔ፣ ለሴትነቴ የተፃፈ መሰለኝ።
🎶 Well, I've been saved by a woman ... እያለ ይዘልቃል— ሙዚቃው።
" ሐሳብ ይመጣልኛል፣ እልፍ ሃሳብ። ማዛመጃና መቋጠሪያ እያጡ እንደጉም ሲተኑም ይሰማኛል።
ወዲያው የጀመረልኝ ታሪክ ሰቅዞ ይይዘኛል። ራሱን የጠላው ሃኪም ያሳዝነኝ ይጀምራል። መጨረሻውን በማሰብ ብቻ ስቃዩ ነፍሴን ይቧጥጣታል። Why am i still thinking of that damn Doc while i got alot on my plate?
መፃፍ አሰኘኝ። የሆነ ነገር መፃፍ፣ ጥቂት ሞከርኩ። እሱን አቁሜ ለእህቴ ላለቅስላት ፈለግኩ። ሰበብ አጣሁ። በየትኛው ገፅዋ ላልቅስላት? ከወትሮው በተለየ ዛሬ ለምን በህይወት ያለች ያህል መሰለኝ?? "ብትኖር" የሚለው ሃሳብ በራሱ ለምን እንደወትሮው ልቤን በቅናት ፍም አልጠበሰውም?? እንቅልፍ አሰኘኝ። ሰውነቴ ያለልማዱ እንቅልፍ ተመኘ።
—★★★—
ማስታወሻ ደብተሩን አልያዘም። ተረጋግቶ ተቀምጦ አገኘሁት። የተለመደ ጥልቅ አስተያየት ከፈገግታ ጋር። እንድቀመጥ ጋበዘኝ። ጥቂት "እዚ ግባ" የማይባሉ ነገሮች ተለዋወጥን። ስለ አየሩ፣ ስለ መንገዱና ወዘተ…
"ጥሩ እንቅልፍ ከቀናት በኋላ ተኛሁ" አልኩት። መልካም ዜና መሆኑን ነግሮኝ ስለ እንቅልፍ ጥቅም ጥቂት ቃላት ወረወረ። ሐተታ አለማብዛቱን ወድጄዋለሁ።
" ዛሬ ምን ይሰማሻል? " በማለት ጠየቀኝ። ምን እንደሚሰማኝ በቃላት ማስፈር አልችልም እልፍ ስሜቶች በአዕምሮዬ አቋርጠው አሁን አሁንም ያልፋሉ። ምን ልበል?
" ሐኪሙ ወዳጅህ ምን ሆነ? እሱን ሳስብ ነበር።"
"ለምን አሰብሺው? "
"አላውቅም! ከሃሳቤ አልጠፋ ስላለኝ፣ ወይ ሐዘናችን መንታ ሆኖ ስለታየኝ? ወይ ክፉ ስለሆንኩ፣ ወይም I developed a crush which would be another madness... እንጃ! "
ዘና ብሎ ተቀመጠ። ጥቂትም ፈገግታ አላሳየኝም። በተረጋጋ ድባብ ውስጥ ሆኖ ቀጠለ።
" ራሱን ለማጥፋት በወሰነበት አንደኛው ምሽት ላይ ከሆስፒታል ለድንገተኛ እርዳታ ተደውሎለት በመሰላቸት ውስጥ ሆኖ በፍጥነት ወደ ስራው ያመራል። ከሱስ መላቀቅ ያልቻለች ነፍሰጠር ያለጊዜዋ ምጧ ደርሶ ትሰቃያለች። ከፍተኛ የደም መፍሰስ ነበራት። ልጇን ብቻ እንዲያድን ትማፀነው ነበር። ልጇን አተረፈው። እናትን ለማትፍ የሚበቃ ደም አልነበረም። በዚህም ካለፈው የባሰ ህመም ውስጥ ነበር።
"ለምን? " አልኩት ድምፄ ስስት እንዳለበት ለራሴም ታውቆኛል።
" በሆስፒታሉ ደም በመለገስ ከሚታወቁ ጥቂቶች ዋነኛዋ ሚስቱ ነበረች! ያም ከመሞቷ በፊት ድባቴ ውስጥ በመግባቷ ተቋርጧል።"
እንባዬ ሳላስበው ሲፈስ ተሰማኝ። ከዚህ ባለታሪክ ጋር ከህይወት የፀፀት ፅዋ አብረን የቀመስን ያህል አጋሬ መሰለኝ።
" በዚህ ምክኒያት ነው ራሱን ያጠፋው? " ጥያቄ ገፍቶኝ ወጣ።
" ልክ ነው በዚህ ምክኒያት ነው። ነገር ግን ያጠፋው የገዛ ነፍሱን አልነበረም፤ ክፉ ማንነቱን እንጂ።"
ግራ አጋባኝ። " ምን ማለት ነው? አልሞተም?? በህይወት አለ?" ጉጉቴ በጥፍር የመቆም ያህል ነበር።
" ትናንት ያልኩሽ ያን ነበር። ሐኪሙ ህይወቱን የቀየረበት አጋጣሚ ነበር ያ ምሽት። በክፉ ማንነቱ የተደበቀ መልካም ገፁ ነፍስ የዘራው ባለቤቱ ስትጎድል ነው። በሷ መጉደል መስዕዋትነት ውስጥ ከል የለበሰ ደግ ማንነቱ ነፍስ ሲዘራ ክፉነቱ ደግሞ ውስጡ ሞቷል!"
" ደግ ማንነትን ለምን አሳደድነው? " በድጋሚ ጠየኩት። ራሴን ከባለታሪኩ ጋር አዳብዬ ነበር። እኔም እስከመቃብር ያሳደድኳት ቀናነት ነበረች።
" አየሽ ደጋግ ማንነቶች ላይ የሚያስቀናን የገዛ ልቡናችን ጥላ ነው። የምናሳድደው ነገር በሙሉ የገዛ ራሳችን ማንነት ነው። ደግነቱም ቢሆን የራሳችን ምስል ነው ነገር ግን በሁነትና በገጠመኞች ከል እናለብሰዋለን። አሳደን በማስወገዳችን ውስጥ የሚፈጠር የመንፈስ እርጋታ መታወክ ካለ ያ ትልቁ ህይወት የምትቸረን ዕድል እንጂ ቀውስ አይደለም። ምክኒያቱም "መታወካችን" በደረሰብን ጫና የሸሸግነውን ማንነት ነፍስ የሚዘራበት ማርከሻችኝ ነው። በሽታ የሚጀምረው መታወካችንን መካድ ከቀጠልን ነው"

👍30❤2
"ስለ ሐኪሙ ንገረኝ?" አልኩት ታሪኩን እንዲቋጭልኝ ተጣድፌ።
"በሳምንታት ውስጥ ብቻ በመቶ ሊትሮች የሚቆጠር ደም ማሰባሰብ ችሎ ነበር። ወደፊት መራመድ ሲጀምር ህይወቱ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተቀየረ። ስፔሻላይዝ ያደረግነው አብረን ነበር። አሁን በቅንነቱ የሚታወቅ የሥነአዕምሮ ባለሞያ ነው።" በተለመደ እርጋታ ተነስቶ ሻይ እፈልግ እንደሆን ጠየቀኝ።
ፍላጎት አልነበረኝም። መሄድ ብቻ ነበር የፈለኩት። ድጋሚ ወደዚህ ቦታ ለመምጣት ፍላጎት አጣሁ።
" ደግሞ…ሙዚቃውን ወድጄዋለሁ!" አልኩት። ፈገግ አለ። ከወንበሬ እስክነሳ ድረስ ፈገግ እንዳለ ነበር።
" ሙዚቀኛ መሆን እንደምፈልግ ነግሬህ ነበር? … ኣህ አልነገርኩህም። ጥቂት ግጥሞች ከመተኛቴ በፊት ለመፃፍ ሞክሬኣለሁ ደግሞ… ምናልባት መቋጫ አጥቼ የተውኩት ሃሳብ ዛሬ ከመጣልኝ እጨርሰዋለሁ…"
"መልካም እድል እመኝልሻለሁ" አለኝ ትከሻዬን መታ መታ አድርጎ። " ሠሞኑን ተደራራቢ ነገሮች ስላሉብኝ ላንቺም ፋታ ለመስጠት፤ ቀጣይ ቀጠሮኣችንን በሳምንት እናስረዝም። ማስታወሻ እልክልሻለሁ አለኝ። አልከፋኝም። ፍላጎቴ ነበር። ጥያቄዎች እየመጡ ይጠፉብኛል። ተሰናብቼው ወደ ውጪ መራመድ ጀመርኩ። በሩ ላይ የተለጠፈ ፅሁፍ ሃሳቤን ያዘው።
" ደም በመለገስ ህይወት እንደሚያተርፉ ልብ ብለዋል? 12 ተኛ ዙር ዘመቻችንን ይቀላቀሉ!" ይላል። የሆነ ግፊት ወደ ኋላ እንዳይ አደረገኝ። እጁን በኪሱ ከቶ ሲያስተውለኝ አይን ለአይን ተጋጠምን። መራመድ ቀጠልኩ። በገዛ ስጋዬ ውስጥ የሚመላለሰው ማንነቴ እንግዳ ሆነብኝ። "አዲስ ማንነት" የሚሉት ይሄን ይሆን?
🎶"Well, I've been saved by a woman.... " ሙዚቃው አፌ ላይ ይላወሳል።
————————
በሱራፌል አየለ

👍19❤3
ሌሎች አሸናፊ ፅሁፎችን እና ለውድድር የቀረቡትን ማየት ከፈለጋችሁ የፌቡ ገፄን መጎብኘት ትችላላችሁ
https://www.facebook.com/meri.feleke.9
https://www.facebook.com/meri.feleke.9
Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
የቀይ ልክፍት
(ሜሪ ፈለቀ)
"ጥሬ ስጋ በቀይ ወይን ምሳ ልጋብዝሽ" ብሎ ነው የጀመረኝ።
"በደስታ" አልኩኝ። ጥሬ ስጋ ነፍሴ እንደሆነ ማንም ያውቃል።……
"ምሳ በልቼ አሁን መጣሁ" ብዬ ከቤት ወጥቼ የሚቀጥለውን ቀን ምሳ በልቼ ተመለስኩ።
በቁርጥ ሰበብ ስንቋረጥ ዓመት ሆነ።……
"ሜዬ ገብቶልሻል ይሄ ልጅ! "ይሉኛል ጓደኞቼ……
በፍፁም! በጠዋት ደውሎ ካላሳቀኝ ደህና ዋዪልኝ ካላለኝ ደህና አልውልም እንጂ ፍቅር አልያዘኝም። ደሞ ምሳ ሰዓት ላይ ደውሎ "የት ነሽ? እ? ልይሽ? " ካላለኝ እህሉን እንደቀሙት ህፃን እነጫነጫለሁ እንጂ ፍቅር አልያዘኝም። ማታ ደውሎ ደህና እደሪ ካላለኝም አድራለሁ እንቅልፍ በዓይኔ አይዞርም እንጂ……
"ኸረ ሜዬ ገብቶልሻል! " ይሉኛል ጓደኞቼ ለወትሮው ስንገናኝ አዲስ ስለወጣ መፅሃፍ በመጨቃጨቅ የምናጠፋውን ቅዳሜ ከሰዓት እኔ አዲስ ስለሆነው የኔ ታሪክ፣ የነገረኝን ቀልድ ፣ የሄድንበትን ቦታ…… እያጎረሰኝ የበላነውን ምግብ… ስቀድላቸው ማታ 2 ሰዓት ሆኖ ስለተለያየን እኮ ነው። እኔ ልጅት በፍፁም!
"ኤጭ አሁንስ ተጃጃልሽ! "ይሉኛል ደግሞ። አዲስ ጫማ ልጦኝ ከአራት ኪሎ ፒያሳ በለሊት ቼቼ አድርጎ እንዳደረሰኝ ልነግራቸው የትከሻውን ስፋት… የአንገቱን ስር ጠረን… ላስረዳቸው አንድ ሰዓት ከ59 ደቂቃ ስለወሰደብኝ።
"ማፍቀርስ እንዳንቺ ከሆነ አይፈቀር! " ይሉኛል። እሱ እወዳለሁ ያለውን ቀይ ጥፍርቀለም ፍለጋ 16 ተኛ ቀይ ጥፍርቀለሜን እያጋዙኝ በቀደም ለት የእግሬን ጥፍሮች ሊቀባልኝ ብሎ እንዴት እንዳበለሻሸው ስነግራቸው ብቻዬን እየሳቅኩ ስሽኮረመም እኮ ነው። እስኪ አሁን ይሄ ማፍቀር ነው? እነሱ ሳያዩ የገዛሁትን 10 ቀይ ጥፍር ቀለም ቢያውቁ ምን ሊሉ ነው?
"አይ እንግዲህ በቃሽ አንቺ ከሰሙሽ እንዴት እንዳደረገኝ አድርጌ ላሳያችሁ ትያለሽ! " ይሉኛል ደግሞ። እሱ የሚወደውን ቀይ ፒኪኒና ጡት ማስያዣ ቁጥሩን ለማላውቀው ጊዜኛ ለመግዛት ቡቲክ ባየሁ ቁጥር እያስቆምኳቸው በቀደም ለት እንዴት እንዳገላበጠኝ ስነግራቸው።
(እህእ ቺኮች ከልጁ ፎንቃ ሊይዛችሁ ነው እንዴ? ኸረ ተበተኑ አግብቷል)
"አዎን አፍቅሬዋለሁ! "
በሁለተኛው ዓመት የሆነ ቀን እቤቴን ከሳሎን መኝታ ቤት፤ ከጓዳ ሳሎን እየተዘዋወርኩ እያየሁት እኔ የምወደው ሳይሆን እሱ የሚወደው ቤት እንደሆነ ሳይ…… ሶፋዬ እሱ በሚወደው ግራጫማ ቀለም ሶፋ ተቀይሯል። ምንጣፉ እሱ የሚወደው ብርማ ቀለም… የቤቱ ግድግዳ ቀለም… ሌላው ቀርቶ የጓዳ እቃዎቼ…… ሁሉም እሱ እወዳቸዋለሁ ያላቸው ናቸው። አንድ ሎከር ሙሉ ቀይ ፒኪኒና ጡት ማስያዣ.… ሺቲ የምትለብስ ሴት አልወድም ማለቱን ተከትሎ የነበሩኝን 6 ሺቲዎች የሰፈራችን ልብስ ሰፊጋ ቁምጣና ቦላሌ ማስደረጌን ታዝቤ……
"አዎን አፍቅሬዋለሁ።" አመንኩ።
በምንም ምክንያት የማይሰረዘውን ለዓመታት የኖረ የጓደኞቼን የቅዳሜ ከሰዓት ስብስብ ከሱ ጋር ለመሆን ስሰርዝ፤ የቤቴን አንድ ቁልፍ ስሰጠው……
"አዎ ተጃጅያለሁ።" አመንኩ
ይህችኛዋ ሰራተኛሽ ወጧ አይጣፍጥም ቀይሪያት ሲለኝ የምወዳትን ልጅ ደመወዟን ሰጥቼ ሳሰናብታት፤ ይሄ ጓደኛሽ አይነውሃው አላማረኝም ሲለኝ ጓዴን የአይንህን ቀለም ካልቀየርክ ብዬ ስተጋተግ……
"አዎ ነፍዣለሁ።" አመንኩ።
በሶስተኛው ዓመት የሆነ ቀን ላይ……
"ቀይ ሴት በጣም ነው የምወደው! " አለኝ…… ቀይ ሚስቱን ፍለጋ ከቤቴ ወጣ… የሚወደውን ነገር እየፈለግኩ ሳደርግለት አይደል ሶስት ዓመት ያለፈው? ልቤ ሌላ ስራም ልምድም አልነበረውም አይደል? ልቤ ተከትሎት ቀይዋን ሚስቱን ሊያፋልገው እንደወጣ አልተመለሰም ። ቀይ ወንድ ላግባለት ይሆን?
"አሁን ጅልም እብድም ነው የሆንሽው! "አሉኝ ጓደኞቼ
፠፠. ፠፠. ፠፠፡፡

👍23🤣4❤2🥰2
እንደምንድናችሁ ቤተሰብ??? ከፅሁፎቻችን ባልተያያዘ ሁናቴ "ጠበኛ እውነቶች" አራተኛው እትም ገበያ ላይ መሆኑን ሰምታችኃል ወይ?????
ውድ የዚህ ቻናል ቤተሰቦችና ባለድርሻ አካላት 😜 ቤተሰብ ስለሆንን እና ልታነቡኝ ስለፈቀዳችሁ ፈጣሪ ያክብርልኝ። በዚህ ቻናላችን አጫጭር ልብወለዶች… ተከታታይ ክፍል ያላቸው ልብወለዶች አንዳንዴ ወግ…… ኤጭ ቁምነገር በዛ ስትሉ ደግሞ ፍተላ… እፅፍላችኋለሁ።…… በተጨማሪም እናንተን ሊያሳትፍ የሚችሉ የተለዩ ውድድሮችን አዘጋጃለሁ:: አብራችሁኝ ስላላችሁ አመሰግናለሁ። የምፅፈውን ከወደዳችሁ ሼር በማድረግ ለሌሎች አጋሩልኝ። አይይይ አልወደድኩትም ካላችሁም ያልወደድኩት ፅሁፍ ነው ብላችሁ ሼር አድርጉትማ!! 😁😁😁
የበዛዛዛዛዛ ክብርና ነፍፍፍፍፍፍፍፍ ፍቅር ❤️❤️❤️❤️
የበዛዛዛዛዛ ክብርና ነፍፍፍፍፍፍፍፍ ፍቅር ❤️❤️❤️❤️
👍4
“ባሌ ቺት እያደረገብኝ ነው:: ከእርሱም ብሶ ሳፋጥጠው ቤቱን ጥሎ ወጣ!" አለችኝ
"እርግጠኛ ነሽ?" አልኳት ሲታዩ ፊልም ላይ ያሉ የፍቅር ጥንዶች ስለሚመስሉ በነገሩ ደንግጬ
"አየሽ" ብላ ስልኳን መዥረጥ አድርጋ የሆነ አፕ እያሳየችኝ ... "በዚህ አፕ የባልሽን ስልክ ቁጥር ታስገቢና በስልኩ ባልሽ የት እንዳለ መከታተል ትችያለች ... ከሳምንት በፊት የሆነ ሆቴል ገብቶ ነበር:: ሳፋጠው ... ደክሞኝ ናፕ ላደርግ ነው አለኝ ... አስቢው ቤቱ የ7 ደቂቃ መንገድ ሆኖ ..."
የምለው ግራ ገብቶኝ ሳለ ደግሞ ሌላ አፕ ከፈተች .. "አየሽ ይሄ ደግሞ ከመኪናው ጋር የተገናኘ ነው:: መኪናው ሲንቀሳቀስ በስልኬ እከታተለዋለሁ ..."
"ይሄን ሁላ ስለላ ከምታካሂጂበት እንድትጠራጠሪው ያደረገሽ ነገር ካለ ብታወሪው አይሻልም ነበር? ይሄ ነገርኮ አንቺኑ ነው በሽተኛ የሚያደርግሽ!" አልኳት
"ሳልጠይቀው ቀርቼ መሰለሽ? ሁሌም የሆነ ሰበብ አያጣም!"
"እሺ ቆይ ቀድሞ ነገር እዚህ ደረጃ ላይ ያደረሰሽ ጥርጣሬ ምንድነው??"
"ስልክ አጠቃቀሙ ነው:: ስልክ ስደውልልለት ስብሰባ ነኝ ብሎ ይፅፋል ወይም አያነሳም:: ... ከዛ ከሆነ ደቂቃ በኃላ ይደውላል:: ያ ማለት ከሰው ጋር ነበር ማለት ነው:: ዞር ብሎ ነው የሚደውልልኝ ....ማለት ነው:: በተለይ ደግሞ ከሰዓት ነው ይሄን የሚያደርገው ... እቤት ሲሆን ብዙ ጊዜ ስልኩ ሳይለንት ነው:: በዛ ላይ ፓስዋርድ አድርጎበታል .... ሌላው .. ሌላው... ሁሉንም ኖትፊኬሽኖች ኦፍ አድርጏል ... ድንገት ፊት ለፊት መጥቶኮ እንዳላየው ነው ...."
እንደትንግርት ፈዝዤ እያየኃት ከቆየሁ በኃላ
"አንቺ ብትሆኚ ምን ታደርጊ ነበር?" አለችኝ
"አልዋሽሽም እኔም ብሆን ጥዬሽ እጠፋ ነበር::" አልኳት
ለካ እሷ 'አንቺ በኔ ቦታ ብትሆኚ ምን ታደርጊ ነበር?' ማለቷ ነው ምፅ 🤷🏽🤷🏽.... በግልምጫ አፍርጣኝ ወጣች ....
ሜዬ ከቀልብሽ ለምን አትሆኚም 🏃🏽♀️🏃🏽♀️🏃🏽♀️🏃🏽♀️
ውብ ምሽት ውብኛ አምሹልኝማ❤️❤️❤️❤️

😁13👍7🥰2
እንደምን ከረማችሁልኝማ?? ተጠፋፋንኣ??
ከጀርባዬ የተቀመጡ ባልና ሚስት ወይም ፍቅረኛሞች
እሷ :- ይሄኛው አይሻልም?
እሱ:- ይሄ ብዙ ኪሎ ሜትር ተነድቷል:: ሌላ ምረጪ...
(አንድ የሆነ ያገለገለ መኪና የሚገዛበት ሳይት ውስጥ መኪና ሊገዛላት ይመስለኛል እየመረጡ ነው::)
እሷ:- እሺ የቱ ይሁን?
እሱ:- ደስ ያለሽን...
"ደስ ያለሽን" ይላታል እንጂኮ ያሳይችውን ሁሉ በሆነ ሰበብ ይጥልባታል:: .. ተወደደ... ቀለሙ ደስ አይልም.... መልሶ ደግሞ "ደስ ያለሽን" ... ይላታል ....
የሆነ ካፌ ምናምን ተቀምጣችሁ የሚቀጥለው ወንበር ላይ ያሉ ሰዎች የሚያወሩትን ልቅም አድርጋችሁ ከመስማታችሁ የተነሳ ከእነርሱ ጋር የመጣችሁ ምናምን ወይም የምታውቋቸው ነገር መስሏችሁ አያውቅም??
ዞር ብዬ "አንቺ አይገባሽም እንዴ በቃ ብሩ የሚቀንሰውን ምረጪ !" ልላት ሁላ ምንም አልቀረኝም::
መዓት ካሳየችው በኃላ የሆነኛውን "አዎ ይሄ አሪፍ ነው!! ይሄን እንገዛለን" ሲላት ወሬውን በጣም ከመሳተፌ የተነሳ
"እስኪ እስኪ??" ልል ነበር🤣🤣🤣🤣
ውብ ምሽት ውብኛ አመሻሽ አምሹልኝማ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
መጥቻለሁ ለማለት ነው::

🤣14👍9😁3❤2🥰1
በጣም ከፍቶኛል ብላኝ በሰንበቱ ስንጦለጦል ሄድኩላት
"አይገርምሽም ሚስት አለኝ ብሎኝ break up አደረግን" ብላ ትነፋረቃለች ... ስትረግመው ቆይታ
"ፒተር ግን ምን ነክቶት ነው? እንዲህ የሚያደርግ ሰው አይመስልም ነበር::" ብዬ ሳባብላት ንቅት ብላ
"እሱ አይደለምኮ... ከእርሱጋማ ባለፈው ሳምንትኮ ተለያየን.... አልነገርኩሽም እንዴ? ይሄ እንትና ይባላል ... ሳምንታችን ነው ከተዋወቅን::" (ፒተር ተብዬው ራሱኩ ሶስት ወሩ ነበር😜)
ፓ ሳምንቱን ሙሉ ሚስት እንዳለው ሳይነግርሽ እንዴት በድሎሻል? ልላት ነበር አለቃቀሷኮ እናቷ የሞተችባት ነበር የሚመስለው... ስልኳ ጠራና
"የኔ ፍቅር እባክህ እንገናኝ ደብሮኛል" አላለችም?? ፒተርየውን መሆኑ ነው.... ድንግርግር ብሎኝ ነገሩ
"ምን ልትይው ነው? በቀደም እንደተጣላን የጠበስኩት ሰውዬኮ ሚስት እንዳለው ነግሮኝ ልቤን ሰበረው ልትዪው ነው?" አልኳት ከዛ ደረቱ ላይ ድግፍ ብላ ንፍርቅ ብላ አልቅሳ ልትታረቅ 🤣🤣🤪
"አንቺ አይገባሽም!" አላለችኝም ጭራሽ ከቤቴ ጠርታ ተነፋርቃብኝ ስታበቃ 🙄🙄🙄🙄🙄🤔🤔🤔🤔🤔
በቀደም አንዱ ኢንስታግራም ላይ የሰራው ቀልድ ትዝ አለኝ:: አንዷ ለጏደኛዋ ደውላላት
"ስሚ ፍቅረኛሽ ከእገሊት ጋር ቺት እያደረገብሽ እንደሆነ ታውቂያለሽ?" ብትላት
"ማ? ሰለሞን ነው?"
"ኸረ ሀይሉ ነው እንጂ."
"ወንዶች ግን አይገርሙም? ቱ ወንድ ግን አይታመንም!!" 🤪🤣🤣🤣🤣
የሆነማ የተደበላለቀ ነገር አለ🙄🙄🙄
'ምን ላይ ቆሜ ነው ማንን የማማው' ማለት ቀረ በቃ??
ለማንኛውም ቱ ወንዶች ግን ትገርማላችሁ🤣🤣
ውብ ቀን ውብኛ ዋሉልኝማ❤️❤️❤️❤️❤️

👍18❤2🥰1
እናንተ ሌላ ሰው ላይ ተጠቅማችሁ የምታውቋትን ተንኮል ሰው እናንተ ላይ ሲተገብረው ሳቃችሁ አይመጣም? (መንግስተ ሰማያት ገቢዎችን አይመለከትም!)
እንቢም እሺም ለማለት የቸገረ ፌቨር ስትጠየቂ «በሚቀጥለው ሳምንት የእናቴ መቀነት ያደናቅፈኛል፣ ከዛ ቀጥሎ ባለው ሳምንት ደግሞ የአባቴ የጫማ ክር ይጠልፈኛል። ከዛ በኋላ መልሱን ልንገርህ?» ግግም ብሎ ከዛ በኋላ ሲደውል ከራስሽ ውጪ ከማንም ጋር ስብሰባ አድርገሽ የማታውቂ ልጅ «ስብሰባ ላይ ነኝ በኋላ ደውላለሁ።» መቼም አትደውዪም እኮ....
ከለሊቱ 9 ሰዓት በፊት እንቅልፍ በዓይኗ ዞሮ የማያውቅ ልጅ እየተንጠራራች ነገር ከምትደዋወሉበት ሰዓት በፊት ትደውልልህና «ውይ ሀኒ እንቅልፌ ሊደፋኝ ሲልኮ ድምፅህን ሳልሰማ አልተኛም ብዬ ነው ».......... ይገባህ የለ? ወይ ሌላ ስልክ ላይ ልትጣድ ነው። ወይም እነዛ አንተ የጠመድካቸው ጀለሶቿ እንውጣ ብለዋታል።🤷🏽🤷🏽
አስቀድሞ ገና ስልኩን እንዳነሳ « ልክ ልተኛ ስል እኮ፣ ልክ ስብሰባ ልገባ ስል፣ ልክ ስራ ቦታ ስደርስ .......... ደወልሽ»....... ይገባሽ የለ? ቶሎ ተፋቺኝ ነገር......🤣
ስልኳና እጇ የማይለያዩ ልጅ በቀን ዘጠኜ ትደውልልህ የነበረ ፣ አስራ ዘጠኜ ቴክስት ትፅፍ የነበረ «የአጎቴ ልጅ እኮ መጥቶ ከእርሱ ጋር እራት ልንበላ ወጥቼ ስትደውል አላየሁትም። ማሚን እቤት እያገዝኳት ስልኬ አጠገቤ አልነበረም።» ይገባህ የለ? Sophia Zewdu እንዳለችው ወደ አጎቷ ልጅ ስልታዊ ማፈግፈግ ላይ ናት!😀😀
ለወትሮው ጭራሽ ተለማመጪኝ የሚልሽ ባል ያለቅጥ ወሬ ሲያበዛ፣ አውርቶልሽ ስለማያውቃቸው ነገሮች ሲያወራሽ ፣ በፊት እንደማይመለከትሽ የሚቆጥራቸው ፖለቲካና ኳስ ሁላ ላይ ሀሳብ ስጪኝ ብሎ ግግም ሲል.......... አብሲቱን ብቻሽን አትጥዪውም! ቁሌቱን ብቻሽን አታማስዪውም ሲልሽ.............. ይገባሽ የለ? የሆነች ፋውል ሰርቶልሻል። ፈንጅ ረግጧል።
ለወትሮው ሽንት ቤት ካላጀብሽኝ፣ ቆዳዬን ገልብጬ ካላሳየሁሽ፣ ልቤን በትሪ ካላቀረብኩልሽ ................የምትልሽ ጓደኛሽ የሆነ ነገር ሆና «ንገሪኝ ምን ሆንሽ?» ስትያት «አይ የቤተሰብ ጉዳይ ነው፣ ለማንም የማወራው አይደለም» ስትልሽ ይገባሽ የለ? ከዚህ በፊት ያወራችልሽን የሆነ ቦታ ቦረቅ ብሎብሽ ተቀደሻል።
ብቻ ብዙ ነገር ይገባንልኮ ፣ ይገባሽል፣ ይገባሃልኣ? ራስህ አድርገህ የምታውቀውን ሌላ ሰው አንተ ላይ ሲያደርገው ግን ያስቃል የምር።
አንድ ፌቨር የጠየቅኩት ወዳጄ ሳይገረፍ እሺ ብሎኝ ከእኔ ጋር ላለመገጣጠም አሳሩን ይጨልጣል። ከሶሻል ሚዲያዎቹ ሁላ ዲአክቲቬት ሊያደርግ ትንሽ ነበር የቀረው። ስደውልለት ምን ሊለኝ እንደሚችል ገምታለሁ። ጌታ ምስክሬን ተቀራራቢ ነው የሚሆነው። ከ30 ደቂቃ በኋላ እደውላለሁ ይለኝና እገምታለሁ ወይ ስልኩ ዝግ ነው ወይ አይነሳም ። ሲደውል የሚለኝን እገምታለሁ ። ባትሪዬኮ አልቆ፣ እንግዳ መጥቶብኝ፣አጣዳፊ ስራ ገጥሞኝ።
ቅድም በጣም ገርሞኝ። «ትቼዋለሁ በቃ!! አንተ ስትቆይብኝ እንትናኮ ሰራልኝ።» እለዋለሁ። «ሜዬ ሙች ልክ ልደውልልሽ ስል። ውይይ ዋናው እንኳን ተሳካልሽ እንጂ እኔማ ዛሬ ልጀምርልሽ ነበር።»
ኸረ ተው!! እኛም እድሜ ገፍቶ ቀጥተኛ መሆንን አስተምሮን እንጂ ይህቺ ይህቺ ትገባናለች!!
እርግጥ እኔ ተንከሲስ ነኝ። አምናለሁ!! ግን ሁላችንም አንዳንዴ አውቀን እንበለጣለን እንጂ እናውቀው የለ?
«ምናለ ደስ እንዲለኝ እንኳን አንዳንዴ አውቀሽ የተሸወድሽልኝ ብታስመስዪ?» ይላል ፍቅር የሰራውን ነገር ሳውቅበት።
ውብ ቀን ውብኛ ዋሉልኝማ❤️❤️❤️❤️❤️❤️

👍25❤4🥰2🐳1
ቤተሰብ ❤️ እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሰንማ!!
2014 ለሁላችንም የእውነቱን አዲስ ይሁንልን!!
ለሀገራችን ሰላሙን ያምጣልን❤️❤️❤️
ከምትወዷቸው ሁሉ ጋር ውብ በዓል ውብኛ አዋዋል ዋሉልኝ❤️❤️❤️
ከብዙ ክብርና ከነፍፍፍፍፍፍፍፍ ፍቅር ጋር❤️❤️❤️❤️❤️

👍1