Telegram Web Link
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋሕዶ🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
መታዘዝ

"አቤቱ ጌታ ሆይ:- አንተ ወደዚህ ዓለም መጥተሃል::ለእናትህ ለቅድስት ድንግል ማርያምና ለቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ ትታዘዝላቸው ነበር:: አንተ ራስህ ፈጣሪ ሆነህ ሳለህ ለፈጠርሃቸው ሰዎች በፍቅር ትታዘዝላቸው ነበር:: አንተ እኮ ሰማይና ምድር የሚታዘዙልህ አምላክ ነህ! መታዘዝህ ሥልጣንህን አያጠፋውም:: መታዘዝን በእኔ ውስጥ ቀድስ  ከመታዘዝ ሩጬ እንዳላመልጥ ከአንተ ጋር እሰረኝ:: እኔ በአንተ መታዘዝ ውስጥ ተካፋይ መሆኔ ይታወቀኝ ዘንድ ትእዛዝህን እቀበላለሁ:: በእኔ ዐይኖች ፊት እንደመገረፍ ስለሚቆጠር መታዘዝ ለእኔ መራራ ነው:: ከአንተ ጋር ከሆንኩኝ ግን እጅግ ጣፋጭ ነው:: የአንተን የመታዘዝ ልምድ ለእኔ አስተምረኝ፣አለማምደኝ አድለኝም:: ይህን ካደረግህልኝ እውነተኛ ትዛዥ የሆንኸው አንተን በእኔ ውስጥ ስትሰራ እመለከታለሁ::ጽድቅን ለመፈፀም ታዛዥ የሆንኸው አንተ ለእኛ ምሳሌ ነህ::" /ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ

@dmse_tewado
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋሕዶ🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለታሪክ ይቀመጥ በልጆቹ ሞት በቤተ ክርሰቲያን ስደት መከራ የሚቀልድ አባት።

https://www.tg-me.com/dmse_tewado
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋሕዶ🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
ቅዱሳን አንተን ባወቁበት መጠን አውቅህ ዘንድ እሻለሁ የቅዱሳኑ ንፅህና ግን በእኔ ዘንድ የለም። እጠጋለው ኀጢአቴም ዳግመኛ ታርቀኛለች እጠጋለው ኀጢአቴም ዳግመኛ ታርቀኛለች።አቤቱ ጌታዬ ሆይ አደከመቺኝ አንተን በፍፁም ንፅህና አፈልግህ ዘንድ ከለከለቺኝ።ደክሞኝም ፈፅሜ እንዳልተውህ ያቀመስከኝ የፍቅርህ ጣዕም ትዝ ይለኛል። አቤቱ ተጨነኩ አንተስ እስከመቼ ዝም ትላለህ? እስከመቼስ ለፈቃዴ ትተወኛለህ?...

አቤቱ አንተን እንደወደዱህ እንደ ቅዱሳንህ ከፈቃዴ እንድሰዋልህ ቅድስት የምትሆን በጎ ጭካኔንን አስጨክነኝ።

“ከፈቃዴ እሠዋልሃለሁ”
  — መዝሙር 54፥6


https://www.tg-me.com/dmse_tewado
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋሕዶ🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
"ሁሉን የያዘውን ያዙት፤ ሁሉን የሚገዛውን አሠሩት፤ የህያውን አምላክ ልጅ አሠሩት፤ በቁጣ ጎተቱት፤ በፍቅር ተከተላቸው። በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንደ የዋህ በግ በኋላቸው እየተከተለ ወሰዱት፤ ሊቃነ መላእክት በመፍራት እና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት፤

ኃጢአትን ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት፥ በመኳንንት የሚፈርደውንም በእርሱ ፈረዱበት፤ ለሱራፌል ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን የሾህ ዘውድ አቀዳጁት፤ ለኪሩቤል የገርማ ልብስ የሚያለብሳቸውን ለመዘበት ቀይ ግምጃ አለበሱት፤ ኪሩቤል በእሳት ክንፍ ተሸፍነው በፊቱ የሚሰወሩለትን እርሱን ክፉ ባሪያ አሥሮ ፊቱን ጸፋው፤ የመላእክት ሠራዊት በፍጹም መደንገጥ የሚሰግዱለት እየዘበቱበት በፊቱ ተንበረከኩ፡፡

ይህን ያህል ትህትና እንደምን ያለ ትህትና ነው? ይህን ያህል ትእግስት እንደምን ያለ ትእግስት ነው? ይህን ያህል ዝምታ እንደምን ያለ ዝምታ ነው? ይህን ያህል ቸርነት እንደምን ያለ ቸርነት ነው? ኃያል ወልድን ፍቅር ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው በደል የሌለበትን እንደበደለኛ ሰቀሉት፡፡ ህይወትን የሠራውን ከበደለኞች ጋር ቆጠሩት፤ አዳምን የሠሩ እጆች በመስቀል ቀኖዎት ተቸነከሩ፤  ወዮ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ተቸነከሩ፡፡

ወዮ በአዳም ፊት የህይወት እስትንፋስን እፍ ያለ አፍ ከሃሞት ጋር የተቀላቀለ የኮመጠጠ መፃፃን ጠጣ፤... ወዮ የወልድን መከራውን የሚናገር ምን አፍ ነው? ምን ከንፈር ነው? ምንስ አንደበት ነው? የፍቁሩ የጌታ ህማማት በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል፤ ህሊናም ይመታል፤ ነፍስም ትንቀጠቀጣለች፤ ሥጋም ይደክማል የማይሞተው ሞተ፤ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ፤ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ። የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡"

/ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ/

https://www.tg-me.com/dmse_tewado
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋሕዶ🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
#ለሰይጣን_ጊዜ_የለኝም

መምህሩ ተማሪዎችን ሊፈትን በአንድ ሰዓት ውስጥ የሚመለሱ ሁለት ጥያቄዎችን አዘጋጀ። ተማሪዎች ራሳቸውን አዘጋጅተው ወደ ፈተና ክፍል ገበተው ወንበር ወንበራቸውን ይዘው ይጠብቃሉ። መምህሩ የፈተና ወረቀቱን ይዞ ገባ። የፈተናውን መመሪያ ተናግሮ የፈተና ወረቀቱን አደለና ሰዓት ይዞ "መጀመር ትችላላችሁ" አላቸው።

የመጀመሪያው ጥያቄ ስለ እግዚአብሔር የምታውቀውን ጻፍ የሚል ነው። ሁለተኛው ጥያቄ ደግሞ ስለ ሰይጣን የምታውቀውን ጻፍ ይላል፡፡ "ለአንዱ ጥያቄ 30 ደቂቃ ነው የተሰጠው ማለት ነው" ብለው ሰዓት ሳያልቅባቸው ሁለቱንም ጥያቄዎች ለመጨረስ ተሎ ተሎ ይጽፋሉ። ፈተና ከተጀመረ 30 ደቂቃ መሙላቱ ሰዓት ያዩ ተማሪዎች ከአንደኛው ጥያቄ ወደ ሁለተኛው አልፈው መስራት ጀምረዋል፡፡ በአእምሮአቸው የመጣላቸውን ሐሳብ በቻሉት ፍጥነት ይጽፋሉ፡፡ መምህሩም ሁሉም ተማሪ የየራሱ መስራቱን እየዞረ ይከታተላል።

"ለማጠናቀቅ አስር ደቂቃ ይቀራችኋል" አለ መምህሩ። መልሰን ጨርሰናል ብለው ያሰቡ ተማሪዎች ግማሾቹ ፈተና ወረቀቱን ለመምህሩ ሰጥተው ሲወጡ፥ ሌሎቹም የመለሱትን ደግመው ያነባሉ፡፡ ያልጨረሱም የቀረችውን ደቂቃ ለመጠቀም ይጣደፋሉ። ከአስር ደቂቃ በኋላ "ሰዓት አልቋል ሁላችሁም መስራት አቁሙ" አለ መምህሩ፡፡ እየዞረም ፈተና ወረቀቱን መሰብሰብ ጀመረ፡፡ አንድ ተማሪ ጋር ሲደርስ ግን አሁንም መልስ እየጻፈ ያገኘውና "ሰዓት አልቋል ሲባል አትሰማም እንዴ?" ብሎ ወረቁትን ተቀበለው፡፡

ሁሉም ተማሪዎች ለሁለቱም ጥያቄ የሚያውቁትን የመለሱ ሲሆን አንዱ ተማሪ ግን ለጥያቄ ቍጥር አንድ (ስለ እግዚአብሔር የምታውቁትን ጻፉ ለሚለው) ብቻ ነው መልስ የሰጠው። መምህሩ በዚህ ተማሪ መልስ ተገርሞ "ለምንድ ነው ለሁለቱንም ጥያቄዎች መልስ ያልጻፍከው?" ብሎ ጠየቀው። እርሱም "#ለሰይጣን_ጊዜ_የለኝም" ስለ እግዚአብሔር ራሱ የማያልቅ ቢሆን እኮ ነው የተሰጠን ሰዓት አልቆ ገና እየጻፍኩ ያስቆምከኝ" አለው ይባላል፡፡

እውነት ነው ነገረ እግዚአብሔር ቢጽፉት፣ ቢናገሩት፣ ቢሰሙትና ቢያዜሙት የማያልቅና የማይሰለች ጥልቅ ምሥጢር ነው። የፈለግነው ያህል ጊዜ ብንሰጠው እንኳን በጅምር እያለን ጊዜው ያልቃል። በቃሉ ፍቅር፥ በምሥጢሩ ተመስጦ ውስጥ ሆነን ወደማያልፈው ዓለም እንሻገራለን፡፡

ይህንን ገንዘብ ለማድረግ ግን ለሰይጣንና ለጉዳዮቹ የሚሆን ጊዜ የለኝም ማለት ይገባል፡፡ ከጊዜ ውጭ የሚሰራ ነገር የለምና ለሰይጣን የሚሆን ጊዜ ከሌለን ከኃጢአት ሁሉ መራቃችን አይደል? ለሰይጣን ጊዜ ላለመስጠት ደግሞ ከእርሱ ጋር መጣላት ነው። መቼም ሰው ለጠላው ነገር የሚሆን ጊዜ አይኖረውም። ምንም ስራ ባይኖረውም እንኳ ከጠላው ጋር ላለመገናኘት ምክንያት ፈጥሮ ይርቅ የለ? ስለዚህ ለሰይጣን ጊዜ እንዳይኖርህ ከእርሱ ጋር ተጣላ። የሚገርመው ከሰይጣን ጋር ስትጣላ ደግሞ ከሰው እና ከእግዚአብሔር ጋር በፍቅር መኖር ትችላለህ፡፡ ከ24ቱ ሰዓት ለሰይጣን የሚሆን ጊዜ ከሌለን መቼም ቢሆን ኃጢአት ሊያሰራን የሚችልበት ዕድል ወይም አጋጣሚ አይኖርም። የተሰጠን ጊዜ ለሰጪው አምላክ መልሰን እንሰጠው ዘንድ ማስተዋሉን ያድለን።
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋሕዶ🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋሕዶ🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
                         †                         

[    የዐቢይ ጾም አምስተኛ ሳምንት     ]

             [    ደብረ ዘይት   ]

ሊፈርድ የሚመጣውን ዳኛ - አማላጅ አትበል !

- በዓለ ደብረ ዘይት በሰቂለ ሕሊና በተመስጦ ልቡና የሚከበር ታላቅ በዓለ እግዚእ ነው። በግርማ መለኮት በክበበ ትስብእት ይመጣል። የሚመጣውም ሊፈርድ ነው። ያማልዳል የምትል ሁሉ መጽሐፍኽን ፈልግ።

----------------------------------------------

ቅዱስ ዳዊት ይመጣል ያለን እግዚአብሔርን ነው። "ከክብሩ ውበት ከጽዮን እግዚአብሔር ግልጥ ኾኖ ይመጣል" እንዲል። [መዝ ፵፱፡፪]

ደግሞም "ይመጣልና በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣል ፤ እርሱም ዓለምን በጽድቅ አሕዛብንም በቅንነት ይፈርዳል" ይላል። [መዝ ፺፭፡ ፲፫]

ሲሠልስም  "ወንዞች በአንድነት በእጅ ያጨብጭቡ፣ ተራሮች ደስ ይበላቸው፤ በምድር ሊፈርድ ይመጣልና" ብሏል። [መዝ ፺፯፡ ፰]

ነቢየ ልዑል ኢሳይያስም "እነሆ እግዚአብሔር መዓቱን በቁጣ ዘለፋውንም በእሳት ነበልባል ይመልስ ዘንድ ከእሳት ጋር ይመጣል፤ ሠረገሎቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ ይኾናሉ" ሲል ተናግሯል። [ኢሳ ፷፮፡ ፲፭]

ቅዱሳን መላእክትም "ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ [ክርስቶስ] ወደ ሰማይ ሲሔድ እንዳያችሁት እንዲሁ ይመጣል እሏቸው" ተብሎ ተጽፏል። [ሥራ ፩፡ ፲፩]

የመጀመሪያው መጽሐፍ ጸሐፊ ነቢዩ ሔኖክም "እነሆ ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ . . . ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቷል" በማለት ተናግሯል። [ሔኖ ፩፡ ] ሐዋርያው ይሁዳም አጽንቶታል። ይሁዳ ቁ ፲፬።

ከሁሉም በላይ የራሱ የጌታችን ምስክርነት ወደር አይገኝለትም።

"ከዚያች ወራትም መከራ በኋላ ወዲያው ፀሐይ ይጨልማል፥ ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም፥ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፥የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ። በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፥ በዚያን ጊዜም የምድር ወገኖች ሁሉ ዋይ ዋይ ይላሉ፥ የሰው ልጅንም በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል፤  መላእክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፥ ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከዐራቱ ነፋሳት ለእርሱ የተመረጡትን ይሰበስባሉ" በማለት በማያወላዳ ቃል ነግሮናል። ማቴ ፳፬፡ ፳፱-፴፩፡፡

"የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል፤ አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል፥ በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል። የንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ። . . .
በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል፦ እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘለዓለም እሳት ከእኔ ሒዱ" ይላቸዋል። ማቴ ፳፭፡ ፴፩-፵፩።

ይህንን ጌታ አማላጅ እያልህ መጠበቁ በየት እንደሚያቆምህ ዐውቀኽ ከአሁኑ ተመለስ።

እንኳን ለበዓለ ደብረ ዘይት አደረሳችሁ !

[  ዲ/ን ዓባይነህ ካሤ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
https://www.tg-me.com/dmse_tewado
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋሕዶ🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
🎤ድምፀ ተዋህዶ🎤:
ድንግል ሆይ !
ወላዲተ አምላክ !!
የምህረት እናታ  አንች ነሽና
ከልጅሽ አስታሪቅን በሀጢአታችን
ብዛት ነውና ፈተናችን የበዛው
በይቅርታው ብዛት ይምረን ዘንድ
ለምኚልን !!! የአስራት አገርሽን ኢትዮጲያን ሰላም አድርጊልን
ምእልተ ፀጋ  ላንቺ የሚሳንሽ የለምና ከልጅሽ አስታርቂን ።

#ድምፀ_ተዋህዶ

#shere_👇join_👇shere
https://www.tg-me.com/dmse_tewado
Audio
🌷የልደታ ማርያም እናቴ ነይ ከልጅሽ ጋር
ሁሌም በሕይወቴ ×(2)❤️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን አደረሰነ!

☞ወርኀ ግንቦት ቡሩክ፤ አመ ፲ወ፫፦

ተዝካረ በዓሉ ለእግዚአብሔር አብ (ወሀቤ ብርሃን)

ወበዓለ ቅዱሳን አበው፦

✿ዐቢይ ወክቡር አርሳንዮስ ጻድቅ (ጠቢብ ወመስተጋድል)
✿ዳንኤል ገዳማዊ (ረድኡ)
✿፳፻ ሰማዕታት ዘደብረ ሊባኖስ (ዘቀተሎሙ ፋሽስት)

❖ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤
ኪያነኒ ይምሐረነ በጸሎቶሙ።
ወበረከቶሙ ይብጽሐነ፤ ለዓለመ ዓለም አሜን፡፡

╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
        @zkre_kdusan21                    
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋሕዶ🎤 (🙏ኦርቶዶክሳዊ ዝማሬ🙏)
ሰበር ዜና
--
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ባደረገው ስብሰባ የሚከተለውን ውሳኔ አስተላልፏል፦

1. ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆርስን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፤
2. ብፁዕ አቡነ  ሳዊሮስን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ 
3. ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስን የሐዲያ ሀ/ስብከትን እንደያዙ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
4. ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ዘኮሎራዶን የቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ገዳማት ሊቀ ጳጳስ፤
5. ብፁዕ አቡነ ናትናኤልን ሚኒሶታን እንደያዙ የኮሎራዶ ሀ/ስብከትን እንዲመሩ፤
6. ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የደቡብ አፍሪካ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳ ጳስ፤
7. ብፁዕ አቡነ ዕንባቆምን የገዳማት መምሪያ ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲመሩ፤
8. ብፁዕ አቡነ ሙሴ አውስትራልያን እንደያዙ የግቢ ቅዱስ ገብርኤልና የበዐታ ለማርያም ገዳም ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲመሩ ወስኗል።

ምንጭ፦ የኢ/ኦ/ቤ/ክ ሕዝብ ግንኙነት

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
       @News_Tewahdo
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯
"እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዕርገት በዓል አደረሳችሁ!"

በዚችም ዕለት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእኛ በነሣው ሥጋ ከአባቱና ክመንፈስ ቅዱስ ጋራ ወደአለው የአንድነት አኗኗሩ ከሰማያት በላይ ያረገበት ሆነ።

እርሱም በረቀቀ ጥበቡ በመከራው በሞቱና በመነሣቱ ሥራውን ከፈጸመ በኋላ አርባው ቀን ሲፈጸም በነፋሳት ክንፍ ላይ ሁኖ ዐረገ። ያን ጊዜ በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ ወጣ በነፋሳትም ክንፎች ላይ ሁኖ ወጣ ያለው የዳዊት ትንቢት ተፈጸመ።

በዚህም ዕርገቱ ለሚያምኑበት በልዕልና ወደሚኖሩበት የሚዐርጉ መሆናቸው ተረዳ ተረጋገጠ ራስ በአለበት ሕዋሳት ሊኖሩ ይገባልና።

አዳም አስቀድሞ በምድራዊ ርስቶች በሲኦልም እንደኖረ መኖርንም እንደ ቀደመ እንዲሁ ዳግማዊ አዳም ጌታ በመንግሥተ ሰማያት ርስት መኖርን ቀደመ።

የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ዕርገቱን ከትንሣኤው አከታትሎ ወዲያውኑ አላደረገም መናፍቃን ዕርገቱ ምትሐት ናት ብለው እንዳያስቡ።

ጌታችንም በረቀቀ ጥበቡ የደቀ መዛሙርቱን ተሸብሮ የነበረ ልቡናቸውን እያጽናና መነሣቱንም እያስረዳቸው ከትንሣኤው በኋላ አርባ ቀን ኖረ።

በጌታችንም ዕርገት የዳንኤል ትንቢት ተፈጸመ እንዲህ የሚል ሌሊት በራእይ አየሁ እነሆ ታላቅ እንደ ሰው ልጅ የሆነ መጣ ዘመናትን ወደ ሚያስረጃቸው ደረሰ ከፊቱም አቀረቡት።

የዘላለም አገዛዝ ጌትነት መንግሥት የዘላለም ሥልጣን ተሰጠው ሕዝቡና አሕዛቡ ሁሉ መንደር መንድረው የሚኖሩትና ነገዱም ነገሥታቱም ሁሉ ይገዙለታል አገዛዙም የዘላለም አገዛዝ ነው መንግሥቱም የማያልፍ የማይጠፋ ነዋሪ ነው።

ለእርሱም ምስጋና ይሁን ከቸር አባቱ ሕይወት ከሆነ መንፈስ ቅዱስም ጋር ለዘላለሙ አሜን።

ምንጭ፡- መጽሐፈ ስንክሳር ዘወርኃ ግንቦት

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
       @News_Tewahdo
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯
ፓስተር ትዝታው ሳሙኤል ወደ ኢትዮጵያ ገብቷል። የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የሕግ ክፍል በሕይወት ካለ በሕግ አግባብ ትዝታውን ይጠይቅልን። ተጠያቂም ያድሥግልን።

አፉ እንዳመጣለት ሲከፈት የኖረ፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሲያጥላላና የከበረ ስሟን እያነሣ ሲያክፋፋ የኖረ፣ የሕፃንነት ቅርሻቱ ያለቀቀው፣ ፓስተር ትዝታው ሕግ ዐዋቂም ሕግም ካለ መጠየቅ/መከሰስ አለበት። እሱን ለቅጣት የሚያበቁ በርካታ ማስረጃዎች አሉ። ዳሩ ግን ቤተ ክህነቱ እንቅፍ ላይ ነው።

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
       @News_Tewahdo
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋሕዶ🎤 (Name)
እውነተኛ የመረጃ ምንጭ ፈልገው ያውቃሉ⁉️

ከዚህ በፊት ያልተሰሙና ያልተነገሩ መረጃዎችን፣ ያለምንም ወገንተኝነት፣ ስለ ህዝብ ጥቅም ብቻ የሚያቀርብ ቻናል ተከፍቷል። ወቅታዊና አስተማማኝ መረጃዎችን ለማግኘት ይቀላቀሉ።

https://www.tg-me.com/+T4nCtrKz_-DWg9aJ
https://www.tg-me.com/+T4nCtrKz_-DWg9aJ
እጅህ ላይ ባለው ነገር ከታመንህ እግዚአብሔር አምላክ በእጁ ውስጥ ያለውን ነገር ይሰጥሃል።

በውስጥህ ያለውን አቅም መጠቀም ከቻልህ እግዚአብሔር የአንተ ያልሆነ ተጨማሪ አቅም ይሰጥሃል።

ከእግረኞች ጋር ሳትደክም እኩል መራመድና መቅደም ከቻልህ እግዚአብሔር ፈረስን ለውድድር ይሰጥሃል። ኤር. 12፥5

የሚታዩ ኃጢአቶችን ለመዋጋት ታምነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር የተሸሸጉና የማይታዩ ኃጢአቶችን ድል እንድትነሣ ይሾምሃል።

በሕፃንነትህ በልጅነትህ ለእግዚአብሔር የታመንህ ሆነህ ከተገኘህ እርሱ በወጣትነትህ በምታደርገው ውጊያ ውስጥ ታማኝነትን ያድልሃል።

ልያን ለመቀበል ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር ራሔልን ሚስት አድርገህ ታገባት ዘንድ ይሰጥሃል። ዘፍ. 29፥27

በሲና ምድረ በዳ ለመቀመጥ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር አምላክ የተስፋይቱን ምድር ከንዓንን ያወርስሃል።

በዚህ በተወሰነና አጭር ሕይወት ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር መጨረሻ የሌለውን ዘላለማዊ ሕይወት ያድልሃል።

ትልቁ ቁም ነገር በእጅህ ውስጥ የገባው ነገር ትንሽም ይሁን ጥቂት በእርሱ መታመን መቻልህ ነው።

ስለሆነም ባለህ አንድ መክሊት ታምነህ ስትገኝ እግዚአብሔር አምስት መክሊቶችን በአደራ ይሰጥሃል።

አንተ በሚታዩት ነገሮች ላይ ታማኝ ሆነህ ስትገኝ እርሱ በማይታዩት ነገሮች ላይ ይሾምሃል።

በመሆኑም ዓይን ያላየችውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልብ ያልታሰበውን መንግሥቱን ያወርስሃል። 1ኛ ቆሮ 2፥9

(አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ - መንፈሳዊው መንገድ መጽሐፍ አያሌው ዘኢየሱስ እንደተረጎመው።)

የሕይወት ፡ እናቱ ፡ ሆይ፤ ተቀዳሚ ፡ ተከታይ ፡ በሌለው ፡ በአንድ ፡ ልጅሽና ፡ በእኛ ፡ መካከል ፡ አስታርቂን።

╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╮
     @ORTHODOX_LIFE19      
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯
2025/06/28 10:27:23
Back to Top
HTML Embed Code: