Telegram Web Link
ሪፖርተር ጋዜጣ ፓርላማ ገብቶ እንዳይዘግብ መከልከሉን አስታወቀ!

ላለፉት 30 ዓመታት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) ተገኝቶ ዘገባዎችን ሲሠራ የቆየው ሪፖርተር ጋዜጣ፣ ፓርላማ ገብቶ እንዳይዘግብ መከልከሉን አስታወቀ።ሪፖርተር ክልከለው የተጠለበት “ግልጽ ባልሆነ እና ባልታወቀ” ምክንያት መሆኑን ገልጿል። ከሚያዝያ 6 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ 'ምንም ዓይነት ምክንያት ሳይኖር ወይም በፓርላማው በይፋ ሳይገለጽ' ከበር ላይ በጥበቃ ሠራተኞች "ሪፖርተር እንዳይገባ ተብሏል” በሚል ዘጋቢዎቹ እንዳይገቡ መከልከላቸውን አስታውቋል፡፡

ሪፖርተር ለምን ፓርላማ ገብቶ እንዳይዘግብ እንደተከለከለ ጥያቄ የቀረበላቸው የፓርላማው የጥበቃ ሠራተኞች ‹‹እንዳይገባ ተብለን በቃል ተነግሮናል›› ከማለት ባለፈ፣ ለመከልከል የሚያበቃ ማስረጃ ማግኘት አለምቻሉን ገልጿል።ጋዜጣው ለፓርላማው ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ምሥራቅ መኮንን (ዶ/ር) ለምን ሪፖርተር ፓርላማ እንዳይገባ እንደተከለከለ ጠይቆ፣ “እኔ አልከለከልኩም፣ በሕመም ምክንያት ቢሮ አልገባሁም፣ እንደገባሁ አሳውቃችኋለሁ” ማለታቸውንና ከገቡም በኋላ ምላሽ አለመስጠታቸውን ገልጿል፡፡

የሪፖርተር ዘጋቢዎች እንዳይገቡ የቃል ትዕዛዝ የሰጡት የፓርላማ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ንጉሤ መሸሻ (ዶ/ር) መሆናቸው በመነገሩ፣ ለእሳቸውም ሪፖርተር ተመሳሳይ ጥያቄ አቅርቦ፤ በአጭር የጽሑፍ መልዕክት “እኔ ያገድኩትም ሆነ የከለከልኩት ነገር የለም” በማለት ምላሽ ሰጥተዋል ብሏል፡፡ፓርላማው በይፋ ዕግድ እንደጣለ ወይም ትዕዛዝ እንደሰጠ ሳይታወቅ ክልከላ መደረጉ "ከሕግም ሆነ ከሞራል አንፃር ተገቢ አለመሆኑን" የገለጸው ሪፖርተር፣ የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት (ሕግ አውጪው፣ ሕግ ተርጓሚውና አስፈጻሚው) መፍትሔ እንዲሰጡ በመጠየቅ ላይ መሆኑን ገልጿል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የኢንሹራንስ ዘርፉ ለዉጪ ባለሃብቶች ክፍት እንዲሆን የሚያስችል አዲስ አዋጅ በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ተነገረ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሀገሪቱን የኢንሹራንስ ዘርፍ ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት የሚያደርግ አዲስ አዋጅ በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታውቋል።ውሳኔው የኢትዮጵያን የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ለማዘመን እየተደረገ ካለው ሰፊ ጥረት አንዱ አካል ነው ተብሏል።

ይህ የተገለጸው 51ኛው የአፍሪካ ኢንሹራንስ ተቋም ዓመታዊ ኮንፈረንስ እና አጠቃላይ ስብሰባ በአዲስ አበባ በተጀመረበት ወቅት ነው።

የብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ እንደተናገሩት፣ የባንኩን ዘርፍ ለውጭ ባንኮች ክፍት ያደረገው አዲሱ አዋጅ "የፋይናንስ ዘርፋችንን ለማዘመን በተደረገው ጥረት ትልቅ ምዕራፍ" እንደሆነ ተደርጎ ይታያል። በዚህ ስኬት ላይ በመመስረት፣ ባንኩ አሁን ደግሞ ትኩረቱን የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪውን በማሻሻል ላይ አድርጓል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
የደቡብ ሱዳን የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች በፈጸሙት “የደፈጣ ተኩስ ጥቃት” ስድስት ሰዎች ተገደሉ 

ከደቡብ ሱዳን የመጡ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች፤ በጋምቤላ ክልል፣ በአኙዋሃ ዞን፣ ዲማ ወረዳ በሚገኝ ቦታ ላይ በከፈቱት “የደፈጣ ተኩስ ጥቃት” ስድስት ሰዎች መገደላቸውን የወረዳው የአስተዳደር እና የፖሊስ ኃላፊዎች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። በትላንትናው ዕለት ጠዋት በተፈጸመው በዚህ ጥቃት፤ በዘጠኝ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን መመልከታቸውን በአካባቢው የሚገኙ የህክምና ባለሙያ ገልጸዋል።
የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ጥቃቱን የሰነዘሩት፤ ከዲማ ወረዳ 39 ሰዎች አሳፍሮ ወደ ጎግ ወረዳ ሲጓዝ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ላይ እንደሆነ የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኢንስፔክተር ኡታክ ሜዶ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሱ የደፈጣ ጥቃት የተሰነዘረበት፤ ከዲማ ከተማ 45 ኪሎ ሜትር ርቀት ተጉዞ አቻኛ እና 45 በተባሉ ቀበሌዎች መካከል በደረሰበት ወቅት እንደሆነ የፖሊስ አዛዡ አስረድተዋል።
ታጣቂዎቹ በአውቶብሱ ላይ ተኩስ በከፈቱበት ወቅት “መሳሪያ የያዘ ተሳፋሪ” መልሶ በመተኮስ አጸፋውን መመለሱን ረዳት ኢንስፔክተር ኡታክ አመልክተዋል። በተኩስ ልውውጡ አንድ ታጣቂ መገደሉንም የፖሊስ አዛዡ ጠቁመዋል። በታጣቂዎቹ የደፈጣ ጥቃት የአውቶብሱን ሹፌር ጨምሮ የስድስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በስድስት ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱንም ጨምረው ገልጸዋል። 

🔴 ዝርዝሩን ለማንበብ ➡️  https://ethiopiainsider.com/2025/16005/
YeneTube
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ከፍተኛ ጥቃት መሰንዘሯን ተከትሎ ትራምፕ ፑቲንን 'እብድ ነው' ሲሉ ተናገሩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሞስኮ በዩክሬን ላይ ያደረሰችውን ከባድ የአየር ላይ ጥቃትን ተከትሎ በሩሲያ አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ደስተኛ እንዳልሆኑ ተናግረዋል። ትራምፕ ባልተለመደ ተግሳጽ “ምን ነካው? ብዙ ሰዎችን እየገደለ ነው” ያሉ ሲሆን አክለውም ፑቲንን "ፍፁም እብድ ነው" ሲሉ ተደምጠዋል።…
ሩስያ በአንድ ቀን ውስጥ 110 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች መጣሏን አስታወቀች

የሩስያ ዩክሬን ጦርነት ከጀመረ 2000 ቀናት ሊሞላው በጣት የሚቆጠሩ ጊዜያት ቀርተዋል። ጦርነቱ አሁንም አውዳሚ ሆኖ የቀጠለ ሲሆን ባለፉት ቅዳሜና እሁድ አስከፊው ጦርነት ተባብሶ ቀጥላል።

የዩክሬን ባለስልጣናት በተፈጸመባቸው ትልቁ የሩሲያ የአየር ላይ ጥቃት የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ12 ወደ 13 ከፍ ማለቱን እና ቢያንስ 60 ሰዎች መቁሰላቸውን አስታውቀዋል። ተጎጂዎቹ በሰሜን ምዕራብ ዞይቶሚር ክልል ውስጥ መገኛቸውን ያደረጉ የ8፣ የ12 እና የ17 አመት እድሜ ያላቸው ሶስት ታዳጊ ህጻናት እንደሚገኙበት ተነግሯል።

የዩክሬን አየር ሃይል ሩሲያ በአንድ ሌሊት 298 ሰው አልባ አውሮፕላኖችን እና 69 ሚሳኤሎችን ማስወንጨፏን ገልጾ 266 ሰው አልባ አውሮፕላኖችን እና 45 ሚሳኤሎችን ማውደም መቻሉንም አስታውቋል። ከዚህ በተጨማሪ የሩስያ የመከላከያ ሚኒስቴር ወታደሮቹ በዩክሬን ምስራቃዊ ዶኔትስክ ግዛት ውስጥ የምትገኘውን የሮማኒቪካ መንደር መቆጣጠራቸውንም አስታውቋል።

በተጨማሪም የሩሲያ አየር መከላከያዎች እሁድ እለት 110 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በመጥለፍ ያከሸፈ ሲሆን 13ቱ በሞስኮ እና በቴቨር የአየር ክልል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ መሆናቸውን አክሏል።

በሚሊዮን ሙሴ
@Yenetube @Fikerassefa
ህወሓትን ይተካል የተባለው ተገዳዳሪ ፓርቲ የምዝገባ ፈቃድ አገኘ

"ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ" ጊዜያዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባ ፈቃድ ተሰጠው

በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011ዓ.ም.ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲ ጊዜያዊ የምዝገባ ፈቃድ ለዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) ዛሬ ግንቦት 18 ቀን 2017 ዓ.ም መሰጠቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
ፖስት ፒል በተደጋጋሚ ሲወሰድ ከማህጸን ውጪ እርግዝና ሊፈጠር እንደሚችል ተነገረ

በርካቶች ለድንገተኛ ግንኙነት የሚወሰደውን ፖስት ፒል የእርግዝና መከላከያ  በየቀኑ እየወሰዱ መሆኑ ተነግሯል


በአሁን ሰዓት በኢትየጵያ በርካታ ወጣቶች  ለድንገተኛ ጊዜ የሚወሰደው የወሊድ መቆጣጠሪ የሆነውን ፓስትፒል አግባብ ባልሆነ መልኩ እየተጠቀሙ  እንደሆነ ተገልጿል ።

ፖስት ፒል በድንገት ለሚፈጠር ግንኙነት የሚወሰድ ቢሆንም በየጊዜው እና በቋሚነት የሚወስዱ ወጣቶች ቁጥር ቀላል አለመሆኑን እና የጎንዮሽ ጉዳት ሊያስከትል የሚችል እንደሆነ በፕላን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ  የኮሙኒኬሽን ክፍል ሃላፊ የሆኑት ዶክተር ምስክር ጌታሁን ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

መድኃኒቱ በተደጋጋሚ ሲወሰድ ከማህጸን ውጪ እርግዝና የሚከሰት መሆኑ በመግለጽ በተጨማሪም ረጅም ጊዜ በቆየ የፍቅር ግንኙነት  ውስጥ ኮንዶም መጠቀም ማቆምም በተመሳሳይ ከእርግዝና ውጪ  ለተለያዩ በሽታዎች ተጋላጭ እንደሚያደርግ ተነግሯል። በዚህም ፌስቱላ ህመም ቀዳሚውን ስፍራ እንደሚይዝ ተጠቁሟል።

በኢትዮጵያ  ከእርግዝና እና ከወሊድ ጋር በተያያዘ መከላከል በሚቻልም ሆነ ከባድ በሆኑ ምክንያቶች  ህይወታቸው  የሚያልፉ እናቶች ቁጥር አሁም ቀላል የማይባል እንደሆነ በመግለጽ ይህንንም ለመከላከል  ፕላን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ የተለያዩ ከተሞች የጤና ተቋማትን በመገንባት እና ቀጣይነት ያለው ክትትል እንዲያገኙ የማድረግ ስራ እየሰራ መሆኑ  የፕላን ኢትዮጵያ የኮሙኒኬሽን ክፍል ሃላፊ የሆኑት ዶክተር ምስክር ጌታሁን  ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።


Via:- ዳጉ ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa
Forwarded from YeneTube
#ቴምር ሪልስቴት
⚠️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ ለሽያጭ ያወጣናቸው ቤቶቾ እና ሱቆች
‼️ፒያሳ (ሊሴ ገ/ማርያም ትምህርት ቤት) ጀርባ
         👉1 መኝታ 66ካሬ=
         10% ቅድመ ክፍያ 693,000ብር
         ሙሉ ክፍያ 6,930,000 ብር
         👉2መኝታ 71ካሬ
        10%ቅድመ ክፍያ 745,500ብር
        ሙሉ ክፍያ 7,455,000ብር
         👉2መኝታ 93ካሬ=
       10% ቅድመ ክፍያ 976,500ብር
       ሙሉ ክፍያ 9,765,000ብር
        👉3መኝታ 130ካሬ
      10%ቅድመ ክፍያ 1,365,000ብር
      ሙሉ ክፍያ 13,650,000ብር
        👉ቀሪውን 90% በ17ዙር ከፍለው         የሚጨርሱት
        👉30% እና ከዛ በላይ ለሚከፍል ከከፈሉት ላይ 25% ደረስ የሚደርስ ቅናሽ አዘጋጅተናል
‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ 
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
       👇👇👇👇👇👇
     +251939770177
     +251996856273
https://www.tg-me.com/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
Forwarded from YeneTube
🟥📣የመጨረሻ ዲያስፓራ ቁ3 ብሎክ 

🏫ከስቱድዮ እስከ ባለ 4 መኝታ ከተጨማሪ የሰራተኛ፣ ላውንደሪ ክፍል እና የዕቃ ክፍል ያካተቱ ቤቶች

💸ቅድመ ክፍያ
   
    💎ባለ 1 መኝታ  በ 431 ሺ ብር
    💎ባለ 2 መኝታ  በ 619 ሺ ብር
    💎ባለ 3 መኝታ  በ 751 ሺ ብር
    💎ባለ 4 መኝታ  በ 1,051,626 ብር 

🛍️🛒ሱቆች ከ 43 ካሬ ጀምሮ

🏦60% የባንክ ብድር የተመቻቸላቸው (እየኖሩበት ወይም አከራይተውት እስከ 20 አመት ቀስ ብለው የሚከፍሉት)

➡️በ 8% ቅድመ ክፍያ

➡️እስከ 30% በሚደርስ ቅናሽ ዋጋ (ለውስን ቤቶች) በመጠቀም
የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ


➡️☎️ 09 72 42 75 95     

➡️@Tirsit9 (telegram)

➡️Whatsapp Link-
https://whatsapp.com/dl/code=gsXOc8ttJB?mode=tac
ስለጥፊው የማክሮን ምላሽ

እኔና ባለቤቴ እየተከራከርን ነበር፣ ወይም ይልቁንም እየተቀላለድን ነበር - ማክሮን ባለቤታቸው ፊታቸው ላይ ስላሳረፉት ሳሳ ያለ ጥፊ ተናገሩ

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ይህ ክስተት "ዓለም አቀፍ አደጋ  የሆነ" መሆኑ አስገርሟቸዋል።
"ሰዎች ብዙ ከንቱ ነገር ያወራሉ። ሁሉም ሰው መረጋጋት አለበት" ብለዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
የኡጋንዳ ጦር ከጀርመን ጋር ያለውን ግንኙነት በአምባሳደሩ አፍራሽ ተግባራት የተነሳ ማቋረጡን አስታወቀ

የኡጋንዳ ጦር በካምፓላ የበርሊን አምባሳደርን በምስራቅ አፍሪቃዊቷ ሀገር በማፍረስ ተግባር ላይ እጃቸው አለበት ብሎ ከከሰሰ በኋላ ከጀርመን ጋር ያለውን ወታደራዊ ትብብር ማቋረጡን ቃል አቀባዩ አስታውቋል።የዩጋንዳ ህዝብ መከላከያ ሰራዊት ከጀርመን ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ ጋር እየተካሄደ ያለውን የመከላከያ እና ወታደራዊ ትብብር እንቅስቃሴዎችን በሙሉ ወዲያውኑ አግዷል ሲል የጦሩ ቃል አቀባይ ክሪስ ማጌዚ በኤክስ ላይ በለጠፉት መግለጫ ተናግረዋል ።

ውሳኔው "በኡጋንዳ የወቅቱ የጀርመን አምባሳደር ማቲያስ ሹዌር በሀገሪቱ የዉስጥ ጉዳይ በንቃት እየተሳተፉ ነው የሚል ታማኝ መረጃ " እንዳላቸዉ ማጌዚ አክለዋል።በኡጋንዳ እና በጀርመን መካከል ስላለው ወታደራዊ ትብብር ሆነ እንቅስቃሴ ግን ዝርዝር መግለጫ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

በካምፓላ የሚገኘው የጀርመን ኤምባሲ አስተያየት ለመስጠት ከሮይተርስ ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽ ለመስተት ፍቃደኛ አልሆነም፡፡ዩጋንዳ ወታደሮቿን በሶማሊያ የአፍሪቃ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ኃይል ኦኤስሶም ውስጥ ያሳተፈች ሲሆን ከፊሉ በአውሮፓ ኅብረት ድጋፍ የሚደረግለት እና ጀርመን አባል የሆነችበት ነዉ።


Via:- ዳጉ_ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa
በኢትዮጵያ የክፍያ ስርዓት ኦፕሬተር ፍቃድ ለማግኘት የሚጠይቀው የተከፈለ ካፒታል ወደ 100 ሚሊዮን ብር ከፍ ተደረገ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የዲጂታል ክፍያዎችን እና የፋይናንስ ተደራሽነትን ለማሳደግ የክፍያ ስርዓት መመሪያውን ማሻሻሉን አስታዉቋል።

ማዕከላዊ ባንኩ “የክፍያ መፈጸሚያ ሰነድ አውጪዎች ፈቃድ እና እውቅና አሰጣጥ መመሪያውን” ያሻሻለ ሲሆን በዘርፉ ፍቃድ ለመዉሰድ ይጠይቅ የነበረዉ 50 ሚሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል አሁን ወደ 100 ሚሊዮን ብር ከፍ ብሏል።

በሥራ ላይ የዋለው አዲሱ መመሪያ ቁጥር ONPS/10/2025፣ አሁን ፈቃድ ያላቸው የክፍያ ሥርዓት ኦፐሬተሮች ካፒታላቸው ከዚህ መጠን በታች ከሆነ እኤአ እስከ ሰኔ 2027 መጨረሻ ድረስ ይህንን መስፈርት እንዲያሟሉ ተጠይቀዋል።

በፈቃድ አሰጣጥ ሂደት ላይ ያሉ ደግሞ ፈቃዳቸውን ከተቀበሉ በሁለት ዓመት ውስጥ አዲሱን የካፒታል እና የአክሲዮን ድርሻ መስፈርቶች ማሟላት እንደሚጠበቅባቸው ካፒታል ለመረዳት ችሏል።

@Yenetube @Fikerassefa
በበረራ መሃል የአውሮፕላን በር ለመክፈት የሞከረው ግለሰብ

በኦል ኒፖን ኤርዌይስ በረራ ዉስጥ የነበረ አንድ ተሳፋሪ በጉዞ መሃል የአውሮፕላኑን የመውጫ በር ለመክፈት መሞከሩ ተገልጿል።

በረራው ከቶኪዮ ሃኔዳ አውሮፕላን ማረፊያ በሰላም ተነስቶ በጉዞ ላይ ባለበት ወቅት ነበር ይህ ግለሰብ የአውሮፕላኑን በር ለመክፈት ግብ ግብ ዉስጥ የገባው፡፡

ታድያ በዚህ ምክንያት ከቶኪዮ ተነስቶ መዳረሻውን ሂውስተን ለማድረግ ያለመው አውሮፕላን በሲያትል አየር መንገድ ሊያርፍ ግድ ብሎታል።

በሁኔታው የተደናገጡ የበረራ ሰራተኞች እና ተሳፋሪዎችም ግለሰቡን የህግ አስከባሪዎች ከመድረሳቸው በፊት ማስቆም ችለዋል።

የሲያትል ወደብ ፖሊስ ተሳፋሪው የመውጫ በሮችን በበራ መሃል ለመክፈት ሞክሮ እንደነበር ማረጋገጡን ኤን.ቢ.ሲ ነውስ ዘግቧል።

እናም በኋላ ላይ ባለስልጣናት ተሳፋሪው የህክምና ችግር እንዳለበት ወስነው በአቅራቢያው ወደሚገኝ ሆስፒታል ወሰደውታል።

አውሮፕላኑም ግለሰቡን አውርዶ ጉዞውን በመቀጠል ወደ መዳረሻው ሂውስተን በሰላም አርፏል።

@Yenetube @Fikerassefa
ከ4 ሺህ በላይ የኮሌራ ታማሚዎች ተመዝግበው 42 ሰዎች ህይወታቸው አጥተዋል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ!

የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ዛሬ ባወጣው አዲስ ሪፖርት መሰረት፣ ከጥር እስከ ሚያዝያ 2017 ዓ.ም. ባሉት አራት ወራት ውስጥ በኢትዮጵያ ጋምቤላና አማራ ክልሎች ከ4,056 በላይ የኮሌራ በሽታዎች የተመዘገቡ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 42 ሰዎች በበሽታው ህይወታቸውን አጥተዋል። ይህ ማለት የሞት ምጣኔው 1.04 በመቶ መድረሱን ያመላክታል።

ሪፖርቱ እንደሚያሳየው፣ ከጠቅላላው የኮሌራ ታማሚዎች መካከል 2,016 የሚሆኑት ከጋምቤላ ክልል ሲሆኑ 32 ሰዎች ሞተዋል። በአንጻሩ በአማራ ክልል 2,040 የኮሌራ ታማሚዎች ተመዝግበው 10 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።

በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ 83 አዳዲስ የኮሌራ በሽታዎች ተመዝግበው የነበረ ቢሆንም፣ ከእነዚህ አዲስ ጉዳዮች ጋር ተያይዞ ምንም አይነት ሞት አለመከሰቱ ተገልጿል።

የኮሌራ ወረርሽኝ አሁንም ንቁ ሆኖ በሁለቱም ክልሎች በሚገኙ 32 ወረዳዎችና 5 የስደተኞች ካምፖች ውስጥ መስፋፋቱን ቀጥሏል። ከእነዚህ ውስጥ 27 ወረዳዎች በአማራ ክልል ሲሆኑ 5 ወረዳዎች ደግሞ በጋምቤላ ክልል ይገኛሉ። ባለፉት ሰባት ቀናት ውስጥ በአማራ ክልል ተጨማሪ ሁለት ወረዳዎች አዳዲስ የኮሌራ ታማሚዎችን ሪፖርት አድርገዋል።

ካፒታል ያገኘዉ መረጃ እንደሚያሳየዉ አብዛኛው የበሽታው ወረርሽኝ በአማራ ክልል ውስጥ በእጅጉ የተጠናከረ ሲሆን፣ ሪፖርት ከተደረጉት አጠቃላይ ጉዳዮች ውስጥ 89.9 በመቶ የሚሆኑት ከአራት ወረዳዎች ብቻ የመጡ ናቸዉ።

የዓለም ጤና ድርጅት ይህንን ወረርሽኝ ለመግታትና ተጨማሪ የሰው ህይወት እንዳይጠፋ ለመከላከል ፈጣንና የተቀናጀ ምላሽ እንደሚያስፈልግ አሳስቧል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
ከሁለት ሺ በላይ ኤክስፖርተሮች የቻይናን መስፈርት አሟልተው የግብርና ምርት መላክ መጀመራቸው ተገለጸ!

ከሁለት ሺ በላይ ኤክስፖርተሮች የቻይናን መስፈርት በማሟላት የግብርና ምርቶችን እንዲልኩ ማድረግ መቻሉን የግብርና ባለሥልጣን አስታወቀ። ወደ አውሮፓ እና ወደ ተለያዩ የዓለም ሀገራት ሰሊጥ፣ ቦለቄ እና ቡና የሚልኩ ኤክስፖርተሮችም በመመዝገብ የመላክ ሂደቱን ባለስለጣኑ እንደሚከታተልም ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ድሪባ ኩማ ገልጸዋል፤ ተቋሙ ምርቶች ላይ ክፍተቶች ሲገኙ ኢትዮጵያን ወክሎ የሚከራከር መሆኑንም ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የቻይናን ትልቅ የስጋ ምርት ገበያ ለመጠቀም ዝግጅቷን ማጠናቀቋን ያመላከቱት ዋና ዳይሬክተሩ ኢትዮጵያ የስጋ ምርቷን ቻይና መላክ ከጀመረች ከቻይና የገበያ መስፈርት ጋር ተመሳሳይ ለሆኑት የአውሮፓና ኤዥያ ገበያ ማቅረብ እንደምትችልም ገልጸዋል።

በቻይና ሀገር የምርት ጥራትና ደህንነት በሚቆጣጠረው ተቋም ለኢትዮጵያ የላከው ከአንድ ሺህ በላይ ገጽ ያለው ዶክመንት በኢትዮጵያ ባለሙያዎች ተሞልቶ መላኩን ገልጸዋል። በቅርቡ ምላሽ ይልካሉ ተብሎ ይጠበቃልም ብለዋል።ከበሽታ ነጻ የሆነ የእንስሳት አረባብ ሂደትን ለመከተል እየተሠራ መሆኑን አመልክተው፤ የቻይና ገበያ በስፋት ያለው በመሆኑ አሁን ባሉት ቄራዎች ብቻ ፍላጎትን ማዳረስ እንደማይቻል እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ቄራዎችን መገንባት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

ወደ ዓለም ገበያዎች የሚላኩ ምርቶች ከበሽታ ነጻ እንደሆኑ እና የተቀባይ ሀገራት መስፈርቶችን እንደሚያሟሉ የማረጋገጥ ሥራ እየተሠራ ነው ማለታቸውን ከፕሬስ ያገኘነው መረጃ ጠቁሟል።

Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
#ቴምር ሪልስቴት
⚠️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ ለሽያጭ ያወጣናቸው ቤቶቾ እና ሱቆች
‼️ፒያሳ (ሊሴ ገ/ማርያም ትምህርት ቤት) ጀርባ
         👉1 መኝታ 66ካሬ=
         10% ቅድመ ክፍያ 693,000ብር
         ሙሉ ክፍያ 6,930,000 ብር
         👉2መኝታ 71ካሬ
        10%ቅድመ ክፍያ 745,500ብር
        ሙሉ ክፍያ 7,455,000ብር
         👉2መኝታ 93ካሬ=
       10% ቅድመ ክፍያ 976,500ብር
       ሙሉ ክፍያ 9,765,000ብር
        👉3መኝታ 130ካሬ
      10%ቅድመ ክፍያ 1,365,000ብር
      ሙሉ ክፍያ 13,650,000ብር
        👉ቀሪውን 90% በ17ዙር ከፍለው         የሚጨርሱት
        👉30% እና ከዛ በላይ ለሚከፍል ከከፈሉት ላይ 25% ደረስ የሚደርስ ቅናሽ አዘጋጅተናል
‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ 
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
       👇👇👇👇👇👇
     +251939770177
     +251996856273
https://www.tg-me.com/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
Forwarded from YeneTube
🟥📣የመጨረሻ ዲያስፓራ ቁ3 ብሎክ 

🏫ከስቱድዮ እስከ ባለ 4 መኝታ ከተጨማሪ የሰራተኛ፣ ላውንደሪ ክፍል እና የዕቃ ክፍል ያካተቱ ቤቶች

💸ቅድመ ክፍያ
   
    💎ባለ 1 መኝታ  በ 431 ሺ ብር
    💎ባለ 2 መኝታ  በ 619 ሺ ብር
    💎ባለ 3 መኝታ  በ 751 ሺ ብር
    💎ባለ 4 መኝታ  በ 1,051,626 ብር 

🛍️🛒ሱቆች ከ 43 ካሬ ጀምሮ

🏦60% የባንክ ብድር የተመቻቸላቸው (እየኖሩበት ወይም አከራይተውት እስከ 20 አመት ቀስ ብለው የሚከፍሉት)

➡️በ 8% ቅድመ ክፍያ

➡️እስከ 30% በሚደርስ ቅናሽ ዋጋ (ለውስን ቤቶች) በመጠቀም
የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ


➡️☎️ 09 72 42 75 95     

➡️@Tirsit9 (telegram)

➡️Whatsapp Link-
https://whatsapp.com/dl/code=gsXOc8ttJB?mode=tac
በትግራይ ክልል ግንቦት 20 በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ይገኛል።

በአንፃሩ በተቀሩት የኢትዮጵያን ክልሎች ግንቦት 20 እየተከበረ አለመሆኑን ተመልክተናል።

@Yenetube @Fikerassefa
አሜሪካ ኤምባሲዎቿ የተማሪዎች የቪዛ ቀጠሮ እንዳይሰጡ አዘዘች!

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በውጭ አገሮች የሚገኙ ኤምባሲዎቹ የተማሪዎች የቪዛ ቀጠሮ እንዳይሰጡ አዘዘ።የአመልካቾችን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የማጣራት ሂደት ለማስፋት በዝግጅት ላይ እንዳለ ያስተዋወቀው አስተዳደሩ፤ ለተማሪዎች የቪዛ ቀጠሮ እንዳይሰጥ በጊዜያዊነት አግዷል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርኮ ሩቢዮ መልዕክት በሰፈረበት ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ በተላከ ማስታወሻ ላይ እገዳው "ተጨማሪ መመሪያ እስኪወጣ ድረስ" ይቆያል ተብሏል።አስተዳደሩ የተማሪዎች አመልካቾች የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችን የማጣራት ስራ አጠናክሮ የሚሰራ ሲሆን ይህም በኤምባሲዎች እና በቆንስላ ጽ/ቤቶች ላይ ትልቅ አንድምታ እንደሚኖረው ተገልጿል።

ትራምፕ የግራውን ርዕዮተዓለም እየተከተሉ ናቸው ካሏቸው ታዋቂ የአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች ጋር ውዝግብ ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ የተወሰነ ውሳኔ ነው።አንዳንዶቹ የአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች በግቢያቸው ውስጥ በሚደረገው የፍልስጤም ድጋፎች ለጸረ-ሴማዊነት በር ከፍተዋል ሲል ዋይት ሃውስ ከሷቸዋል።

ዩኒቨርስቲዎች በበኩላቸው የትራምፕ አስተዳደር በነጻነት ሃሳብን የመግለጽ መብቶችን ለመጣስ እየሞከረ ነው ሲሉ ይወቅሳሉ።ፕሬዚዳንት ትራምፕ ታዋቂው ዩኒቨርስቲ ሐርቫርድ የውጭ አገር ተማሪዎችን እንዲሁም ተመራማሪዎችን እንዳይቀበል በሚል ፈቃዱን ቢሰርዙም ይህ ፖሊሲያቸው በፌደራል ዳኛ ታግዷል።ይህ በሐርቫርድ ላይ የጣሉት ውሳኔ ተግባራዊ የሚሆን ከሆነ ሩብ የሚሆኑት ተማሪዎቹ ከውጭ አገር የሆኑት ተቋሙ በከፍተኛ ሁኔታ ሊጎዳ ይችላል ተብሏል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
2025/07/07 15:18:44
Back to Top
HTML Embed Code: