Telegram Web Link
#አዲስ አበባ ከተማ ላለፉት 14ዓመታት ያህል በስራ ላይ የነበሩ የታክሲ ተራ አስከባሪዎች ማህበራት ከስራ ውጪ ከሆኑ ዛሬ ስድስተኛ ቀናቸውን እንደያዙ የደረሰኝ መረጃ ያመላክታል፡፡

ላለፉት 14 ዓመታት በአዲስ አበባ በሁሉም አከባቢዎች የታክሲ ተራ ማስከበር ስራ ላይ የነበሩ እስከ 9ሺ የሚደርሱ ተራ አስከባሪዎች ካሳለፍነው ሳምንት ረቡዕ እለት ጀምሮ ከስራ ውጪ መሆናቸውን ምንጮች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል፡፡
እነዚህ የታክሲ አስከባሪ ማህበራት ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ በየወረዳቸው በጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፍ ተደራጅተው በዚህ ስራ ላይ ቆይተዋል፡፡

ማህበራቱ ስራ ያቆሙት በከተማዋ በሁሉም አካባቢዎች ያሉ የታክሲ ተራ አስከባሪዎች በአዲስ ሊተኩ እንደሆነ ከተነገረ ከአንድ ወር በኋላ ነው፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
YeneTube
Photo
በአዋጅ የሚቀየር ነገር ካለመጣ 7ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ በተያዘለት ግዜ ይካሄዳል" ምርጫ ቦርድ

በአዋጁ ላይ በተቀመጠው ሁኔታ መሠረት 7ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ በተያዘለት ግዜ ይካሄዳል ሲል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዛሬው ዕለት በምርጫ ቅደመ ሁኔታዎች ዙሪያ በቦርዱ ዋና ስብሳቢ ሜላተወርቅ ሐይሉ በኩል መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫውም፤ በ2013 ዓ.ም ከተደረገው ምርጫ ማግሥት ጀምሮ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የውይይት እና ጥናቶች መቅረባቸውን ዋና ስብሳቢዋ ገልጸዋል።

በጥናቱ መሠረትም ቦርዱ ማሻሻል ያለበትን ሁኔታ በመገምገም የአምስት ዓመት ስትራቴጂ በማውጣት ወደ ሥራ መገባቱን አንስተዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ካለፈው ምርጫ ማግሥት የምርጫ ጉዳይ የሚመለከተው አዋጅ ቁጥር 1162 ላይ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይትት በማድርግ፤ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረቡን ወይዘሮ ሜላተወርቅ ሐይሉ ተናግረዋል።

አሐዱም "ለመሆኑ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጉባኤ በጊዜው የማያደርግ ከሆነ ምርጫው ጊዜው ሊቀየር ይችል እንደሆነ" ለቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ጥያቄ አቅርቧል።

ዋና ሰብሳቢ ሜላተወርቅ ሐይሉ ሲመልሱም፤ "ሀገራዊ ምክክር እየተካሄደ ስለሆነ እራሳችን ቆጥበን አንቀመጥም" ሲሉ ተናግረዋል።

በአዋጅ ማሻሻያ ተደርጎ የሚመጣ አዲስ ነገር ካልመጣ በስተቀር 7ኛው ሀገራዊ  ምርጫን በተያዘለት ግዜ እንደሚያከናውንም ጨምረው ገልጸዋል።

በተጨማሪም ከፀጥታ አንፃር አስቻይ ሁኔታ ባለባቸው ቦታዎች ሁሉ ምርጫው ይካሄዳል የተባለ ሲሆን፤ አስቻይ ሁኔታ በሌሉባቻው ቦታዎች ደግሞ ጊዜዉን እየጠበቀ የሚካሄድ ነው የሚሆነው ተብሏል።

በዚህ ቅድመ ዝግጅት ሥራም ከእጅ ንክኪ የሆነ የምርጫ ስርዓት ለመፍጠር እንደሚሰራ የተናገሩ ሲሆን፤ በተለይም የምርጫ ምዝገባውንና አጠቃላይ ሂደቱን በዲጂታል መንገድ እንደሚሰራም ተገልጿል።

በምርጫው ላይ የመራጮች ምዝገባ በከፊል እንዲሁም የእጩዎች ምዝገባ ሙሉ ለሙሉ በዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) እንደሚከናወንም ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ ከ50 ሺሕ በላይ የምርጫ ጣቢያዎች መኖራቸውን የተናገሩት ዋና ሰብሳቢዋ፤ "እነዚህን የምርጫ ጣቢያዎች እንደገና መመልከት ያስፈልጋል" ብለዋል።

በዚህም በተሰራ ሥራ እስካሁን 12 ሺሕ የምርጫ ጣቢያዎችን የመለየት ሥራ መሠራቱንም የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ አስረድተዋል።

የሀገር ወሰስጥ ተፈናቃዮች ወደ ምርጫ እንዲሳተፍ እና እንዲመረጡ ጭምር ጥናት ተደርጎ የሕግ ማዕቀፍ መሻሻያ እንደተደረገበትም ገልጸዋል።

በቀጣይ ዘርዘር ያለ የምርጫ ቅደመ ዝግጅት ሥራዎችን በመስራት ለመገናኛ ብዙሃን ይፋ እንደሚደረግ ተገልጿል።

@Yenetube @Fikerassefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የዩክሬን ድሮኖች በሩሲያ የጦር ጄቶች ላይ ከባድ የተባለ ጥቃት ፈፀሙ!

ዩክሬን በአራት የሩሲያ ወታደራዊ ካምፖች የሚገኙ 40 የጦር አውሮፕላኖች ላይ ተከታታይ ከባድ ጥቃቶችን መፈጸሟን አስታወቀች።ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ በጥቃቱ 117 ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቅም ላይ መዋላቸውን ገልፀው "34 በመቶ [የሩሲያ] ስትራቴጂክ ክሩዝ ሚሳዔል ተሸካሚዎችን" መምታታቸውን ተናግረዋል።

የዩክሬን ደኅንነት ተቋም ጥቃቱን ለመፈጸም ለአንድ ዓመት ከግማሽ ያህል ሲያቅድ መቆየቱንም ገልጸዋል።ሩሲያ በአምስት ግዛቶቿ ላይ "የሽብር ተግባር" መፈፀሟን አስታውቃለች።ጥቃቱ የተፈጸመው የሩሲያ እና የዩክሬን ተደራዳሪዎች ዛሬ ሰኞ ለሁለተኛ ዙር ድርድር ቱርክ ኢስታንቡል ከመገናኘታቸው በፊት ነው።

ሁለቱ አገራት ጦርቱን ለማጠናቀቅ ያስቀመጧቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ተከትሎ በሁለተኛ ዙር ድርድር ውጤት ይመጣል ተብሎ እንደማይገመት ታዛቢዎች ተናግረዋል።የዩክሬን ባለሥልጣናት በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ከባድ የሆነ የሚሳዔል ጥቃት እና የድሮን ጥቃት መፈጸሙን ተናግረዋል።የሩሲያ ብሔራዊ መገናኛ ብዙኃን ኤጀንሲ፣ ሪያ በበኩሉ የአገሪቱ የደኅንነት መሥርያ ቤት በአገሪቱ ምሥራቃዊ ክፍል ታቅዶ የነበረን ጥቃት ማክሸፉን ዘግቧል።

ሁለት ግለሰቦች በፕሪሞሪ ግዛት በባቡር ሀዲድ ላይ አሻጥር ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ዘግቧል።የሩሲያ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር የካቲት 2022 ዩክሬን ላይ ወረራ ከፍተው እስካሁን ጦርነት እየተካሄደ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ኢስታንቡል ላይ ከመደራደሯ በፊት 160 የዩክሬን ሰው አልባ አይሮፕላን አወደመች

ሩሲያ ለዛሬ ሰኞ አጥቢያ ከ160 በላይ የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ማውደሟን አስታወቀች። እንደ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ሩሲያ ገለፃ የአየር መከላከያ ኃይሏ 162 የዩክሬን ድሮኖችን መትቶ አውድሟል። አብዛኛዎቹ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ተመተው የከሸፉት በሁለቱ ሃገራት የድንበር አካባቢዎች ነው። 57 በኩርስክ ክልል እና ሌሎች 31 በቤልጎሮድ ክልል መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቃል። ሰው አልባ ጥቃቱ የተፈፀመው ከሩሲያ እና ከዩክሬን የተውጣጡ ልዑካን ዛሬ በቱርክ ሊያደርጉት ከታቀደው ስብሰባ ሰዓታት በፊት ነው። የስብሰባው አላማ ከሦስት ዓመታት በላይ በዘለቀው የዩክሬን ግጭት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመደራደር ነው። ልኡካኗን ወደ ኢስታምቡል እንደምትልክ ያስታወቀችው ዩክሬን ትናንት የስለላ መሥሪያ ቤቷ በአራት የሩሲያ ወታደራዊ የአየር ማረፊያ ላይ በፈጸማቸው ጥቃቶች ከ40 በላይ የሩሲያ የጦር እና የስለላ አውሮፕላኖች ማውደሙን ይፋ አድርጋ ነበር። ሁለቱ ሃገራት ከድርድሩ በፊት በየፊናቸው የወሰዱት ጠንካራ ውጊያ በድርድሩ ላይ የሚኖረውት ሚና እየተጠበቀ ነው።

ፎቶ፤  በኢስታንቡል ሩሲያ እና ዩክሬን የሚደረደሩበት የቺራጋን ቤተ መንግሥት

@Yenetube @Fikerassefa
🌺🌸  #ግእዝን_በርቀት 🌺🌸


የግእዝን ቋንቋ በ፲፬ ዙሮች እስካኹን ለብዙ ሺሕ ተማሪዎች በቀላል መንገድ ማስተማር ተችሏል። አኹን ደግሞ በ፲፭ኛ ዙር በቴሌግራም ለኹለት ወራት ( ከሐምሌ ፩ እስከ ነሐሴ ፴፥ ፳፻፲፯ ዓ.ም. በተመጣጣኝ ክፍያ ለጀማሪ ተማሪዎች የሚኾን ትምህርት ለመስጠት ስለታሰበ ባሉበት ኾነው በቀላሉ መማር ከፈለጉ አኹኑኑ
                  
@geezdistance15


የሚለውን የቴሌግራም የመጠቀሚያ ስም በመጫን ወደ ትምህርት መስጫ ቻናሉ መግባት ይችላሉ።



🌺🌸  #ግእዝን_በርቀት 🌺🌸
አቶ ታዬ ደንደአ በፀጥታ ኃይሎች ተይዘው መወሰዳቸውን ባለቤታቸው ተናገሩ!

የቀድሞው የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣን የነበሩት አቶ ታዬ ደንደአ በዛሬው ዕለት በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ባለቤታቸው ተናገሩ።ከሥልጣናቸው ተነስተው ለረጅም ጊዜ በእስር ላይ ከቆዩ በኋላ በዋስትና ተለቀው ጉዳያቸውን ከውጪ ሲከታተሉ የነበሩት አቶ ታዬ ዛሬ በቁጥጥር ስር ከመዋላቸው በፊት በቀጠሯቸው መሠረት ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር።

በዛሬው ጠዋቱ የፍርድ ቤት ውሎ ነጻ ተብለው በነበሩባቸው ሁለት ክሶች በድጋሚ እንዲታዩ የተወሰነ ሲሆን ከችሎት መልስ ከሰዓት በኋላ እንደታሰሩና የት እንዳሉ እስካሁን እንደማይታወቅ ቤተሰቦቻቸው ለቢቢሲ ገልጸዋል።ባለቤታቸው ወ/ሮ ስንታየሁ አለማየሁ ዛሬ ሰኞ ግንቦት 25/2017 ዓ.ም. ከሰዓት 10 ሰዓት በኋላ በፖሊሶች ለጥያቄ እንደሚፈለጉ በመግለጽ ከመኖሪያ ቤታቸው ተይዘው መወሰዳቸውን አረጋግጠዋል።

የቀድሞው የሰላም ሚኒስትር ዲኤታ፣ የገዢው ብልጽግና ፓርቲ እንዲሁም የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት አባል የነበሩት አቶ ታዬ ደንደአ ባለፈው ኅዳር ከእስር ከተለቀቁ በኋላ ጉዳያቸውን በፍርድ ቤት ሲከታተሉ ቆይተዋል።ባለቤታቸው ለቢቢሲ እንደተናገሩት ወደ መኖሪያ ቤታቸው የመጡት የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በር አንኳኩተው ለጥያቄ በፌደራል ፖሊስ እንደሚፈልጉ በመግለጽ ወስደዋቸዋል።

ከፀጥታ ኃይሎቹ ውስጥ የታጠቁ እንደነበሩ የጠቀሱት ባለቤታቸው ወደ ቤት በመግባት አቶ ታዬን ይዘው እንደወጡ እና በዚህ ጊዜም የጨፌ (የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት) አባል መሆናቸውን እና የሕዝብ ተወካይ መሆናቸውን በተደጋጋሚ ሲናገሩ ነበር ብለዋል።ከአስር በላይ የሚሆኑ የፖሊስ አባላት አቶ ታዬን ለመያዝ ታዘው መምጣታቸውን እንደተናገሩ እና ተወሰዱ ወደተባለበት መሃል አዲስ አበባ ወደ ሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ጽሕፈት ቤት እንደሚሄዱ ቤተሰቦቻቸው ገልጸዋል።

ነገር ግን የቀድሞው የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ እና የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት አባል አቶ ታዬ ደንደአ በፀጥታ ኃይሎች ከቤታቸው ተይዘው ከተወሰዱ በኋላ እስከ ሰኞ ምሽት ድረስ የታሰሩበትን ማወቅ እንዳልቻሉ ባለቤታቸው ወ/ር ስንታየሁ ዓለማየሁ ለቢቢሲ ገልጸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የቻናል ጥቆማ!

የonline ስራዎችን ታገኙበታላችሁ!
🚀 Upwork Profile Mastery 
Standout & land high-paying Upwork gigs!
Profile Tips 
Proposal Templates 
Niche Strategies 
📂 Free Tools + Examples 
👉 Join: https://www.tg-me.com/UpworkProfilePro 
መረጃዎችን ለመላክ @honelegn19
🎯 For Beginners:
• Profile Setup & Review 
• Proposal Writing Help 
• First Job & Rate Strategy 
• Client Communication Tips 
• Niche & Rules Guidance 
• Contract & Tool Support 
• Q&A Mentorship
🌟 Empowering freelancers with real strategies. 
መልካም እድል ለሁላችሁም!
🗝️  እጅግ አመቺ በሆነ አከፋፈል የቤት ባለቤት ይሁኑ

60% የባንክ ብድር የተመቻቸላቸውን ቤቶች በልዮ ቅናሽ

❇️  በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው DMC Real Estate የመጨረሻው መንደር ወቅቱን ባገናዘበ  ቅናሽ ዋጋ በተለያዩ ካሬ አማራጮች አቅርቦሎታል : :

⭐️ከሀያ አምስት ዓመታት በላይ ግንባታ ላይ ከቆየ አንጋፋ ድርጅት

📍አድራሻ - በመሀል ከተማ ለቡ መብራት-ሀይል

💸ቅድመ ክፍያ
   
    💎ባለ 1 መኝታ  በ 431 ሺ ብር
    💎ባለ 2 መኝታ  በ 619 ሺ ብር
    💎ባለ 3 መኝታ  በ 751 ሺ ብር
    💎ባለ 4 መኝታ  በ 1,051,626 ብር 

🛍️🛒ሱቆች ከ 43 ካሬ ጀምሮ

🏦60% የባንክ ብድር የተመቻቸላቸው (እየኖሩበት ወይም አከራይተውት እስከ 20 አመት ቀስ ብለው የሚከፍሉት)

➡️በ 8% ቅድመ ክፍያ

➡️እስከ 30% በሚደርስ ቅናሽ ዋጋ (ለ20 ቤቶች) በመጠቀም የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ


➡️☎️ 09 31 14 82 42

➡️@Novi_03 (telegram)

➡️Whatsapp Link-
https://wa.me/251931148242
#ከቴምር ሪልስቴት
7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ መሀል ሣር ቤት አፓርትመንት እና ሱቅ ፒያሳ ለሽያጭ ያወጣነው 

🎯የክፍያ አማራጮች 40/60 ለሚከፍል

👉1መኝታ 75ካሬ 4,815,000ብር ሙሉ ክፍያ
👉2መኝታ 94ካሬ 6,034,800ብር ሙሉ ክፍያ
👉2መኝታ 103ካሬ 6,612,600ብርሙሉክፍያ
👉3መኝታ 132ካሬ 8,474,400ብር ሙሉ ክፍያ
👉3መኝታ 146ካሬ 9,373,200ብር ሙሉ ክፍያ 9,373,000ብር 

‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ 
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
       👇👇👇👇👇👇
     +251939770177
     +251996856273
https://www.tg-me.com/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
Ethiopian Building Codes Standards
Private Sector Engagement in Building Code Revision


The Ethiopian Construction Authority, in collaboration with the College of Technology and Built Environment (formerly AAiT) and The Urban Center, is organizing a series of technical sessions in June 2025 to support the ongoing revision of the Ethiopian Building Code Standards.

Designed for professionals in the construction industry, the 14 expert-led sessions of EBCS will address key themes such as structural design, fire and earthquake safety, mechanical and electrical systems, and emerging building technologies. These sessions aim to highlight the building codes and gather input from the private sector, ensuring that industry experience is reflected in the revised codes, making them both inclusive and grounded in practice.

📍Venue: The Urban Center
📅 Participation by registration only
🔗 Register here

#EthiopianBuildingCodeStandards
Open to professionals, engineers, architects, and others in the construction sector
ቢል ጌትስ ካለው 200 ቢሊዮን ዶላር ሀብት ውስጥ አብዛኛውን ለአፍሪካ ሊሰጥ መሆኑን በአዲስ አበባ ቆይታው ተናገረ!

የማይክሮሶፍት መስራች ቢልጌትስ፤ በቀጣዮቹ 20 ዓመታት ካለው ሀብት ውስጥ አብዛኛውን በአፍሪካ የጤና እና ትምህርት አገልግሎቶችን ለማሻሻል እንደሚያውል ተናገረ።የ69 ዓመቱ ባለጸጋ፤"በጤና እና ትምህርት የሰው ልጅን በማውጣት፤ አፍሪካ ውስጥ እያንዳንዱ ሀገር በብልጽግና ጎዳና ላይ መሆን አለበት" ብሏል።

ቢል ጌትስ ባለፈው ሳምንት እሁድ ግንቦት 24/2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በብሔራዊ ቤተመንግሥት በተካሄደ ሥነሥርዓት የሀገሪቱን ታላቅ የክብር ኒሻን ሽልማት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተሸልሟል።ዐቢይ፤ ይህንን ሽልማት ለጌትስ ያበረከቱት በባለሀብቱ የመሰረተው ቢል ኤንድ ሚሊንዳ ጌትስ "ባለፉት 25 ዓመታት በኢትዮጵያ ላበረከታቸው አሻጋሪ ሥራዎች እና ታላላቅ ዘመን ተሻጋሪ በጎ ተፅዕኖዎችን" እውቅና ለመስጠት እንደሆነ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

ቢል ጌትስ በአዲስ አበባ ከተማ ባደረገው ንግግር አፍሪካውያን ወጣት ፈጣሪዎች ሰው ሰራሽ አስተውህሎትን በምን አይነት መንገድ በመጠቀም በአህጉራቸው የጤና አገልግሎትን ማሻሻል እንደሚችሉ እንዲያስቡ አሳስቧል።ቤልጌትስ ከ20 ዓመት በኋላ 200 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሎ ከሚጠበቀው ሀብቱ ውስጥ 99 በመቶውን ለመስጠት ማቀዱን ያስታወቀው ባለፈው ወር ነበር። የባለሀብቱ ቢል ኤንድ ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በ2045 ስራውን ያጠናቅቃል።በአፍሪካ ህብረት ዋና መስሪያ ቤት በተዘጋጀው ስነ ስርዓት ላይ "በቀጣዮቹ 20 ዓመታት ውስጥ ያለኝን ሀብት እንደሚከፋፈል በቅርቡ ቃል ገብቻለሁ። አብዛኛው ገንዘብ አፍሪካ ውስጥ ያሉ ተግዳሮቶችን እንድትፈቱ ለማገዝ ይውላል" በማለት ተናግሯል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
ሲኖዶሱ በማይጨው ሀገረ ስብከት ሲተዳደሩ የነበሩ ስድስት ወረዳዎች እራሳቸውን ችለው በሀገረ ስብከት ደረጃ እንዲተዳደሩ መወሰኑ ህገወጥ ነው” - የትግራይ ኦርቶዶክስ አባቶች

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሲኖዶሱ በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን የማይጨው ሀገረ ስብከት ሲተዳደሩ የነበሩ ስድስት ወረዳዎች በልዩ አደረጃጀት እራሳቸውን ችለው አንድ ሀገረ ስብከት ሆነው እንዲተዳደሩ ማድረጉ ከትግራይ ክልል ኦርቶዶክስ አባቶች በኩል ተቃውሞ ቀረበበት።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከግንቦት 6 እስከ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ባካሄደው ጉባኤ (አመታዊው ርክበ ካህናት) በደቡባዊ የትግራይ ዞን የሚተዳደሩ ስድስት ወረዳዎች ማለትም የአላማጣ ከተማ፣ አላማጣ፣ የኮረም ከተማ፣ ኦፍላ፣ ባታ፣ ጨርጨር እራሳቸውን ችለው ሀገረ ስብከት እንዲቋቋምላቸው ውሳኔ አሳልፏል ሲል የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጽሕፈት ቤት ግንቦት 24 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

“ሀገረ ስብከት የሚቋቋመው መንግስት ዞን አደርጎ ሲያዋቅር መሆኑ እየታወቀ በጉባኤው ላይ አጀንዳ ተደርጎ እንዲያዝ በማድረግ እና ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ተነጋግረናል፣ ተረዳድተናል የሚል አሳሳች መረጃ በማቅረብ እንዲወሰን ተደርጓል” ብሏል።

Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
🌺🌸  #ግእዝን_በርቀት 🌺🌸


የግእዝን ቋንቋ በ፲፬ ዙሮች እስካኹን ለብዙ ሺሕ ተማሪዎች በቀላል መንገድ ማስተማር ተችሏል። አኹን ደግሞ በ፲፭ኛ ዙር በቴሌግራም ለኹለት ወራት ( ከሐምሌ ፩ እስከ ነሐሴ ፴፥ ፳፻፲፯ ዓ.ም. በተመጣጣኝ ክፍያ ለጀማሪ ተማሪዎች የሚኾን ትምህርት ለመስጠት ስለታሰበ ባሉበት ኾነው በቀላሉ መማር ከፈለጉ አኹኑኑ
                  
@geezdistance15


የሚለውን የቴሌግራም የመጠቀሚያ ስም በመጫን ወደ ትምህርት መስጫ ቻናሉ መግባት ይችላሉ።



🌺🌸  #ግእዝን_በርቀት 🌺🌸
YeneTube
Photo
ስስ ፌስታል ይዞ የተገኘን ሰዉ እስከ 5 ሺህ ብር እንዲቀጣ የሚያዘዉ አዋጅ ጸደቀ!

ማንኛውም ሰው አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውል የፕላስቲክ ከረጢት ይዞ ከተገኘ ከ2000 እስከ 5000 ብር የሚያስቀጣው አዋጅ፤ ዜጎችን በማያውቁት ጉዳይ ለቅጣት የሚዳርግ ነው የሚል ትችት ከምክር ቤት አባላት ቀርቦበታል፡፡

የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ዛሬ የጸደቀው የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ አዋጅ ፤ ማንኛውም ሰው አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውል የፕላስቲክ ከረጢት ይዞ ከተገኝ ከ2000 እስከ 5000 ብር እንዲቀጣ ይደነግጋል፡፡ያመረተ ወይም ወደ ሀገር ውስጥ ያስገባ፣ ለገበያ ያቀረበ ወይም የሸጠ፣ ለንግድ ዓላማ ያከማቸ ወይም ይዞ የተገኘ ከ50,000 ብር በማያንስና ከ200,000 ብር በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ እና ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት እንዲቀጣ አዋጁ ያዝዛል፡፡

የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አወቀ አምዛዬ(ዶ/ር) የአዋጁን ይዘት በንባብ ባቀረቡበት ወቅት፤ የምክር ቤት አባሉ አለሙ ጎንፋ (ዶ/ር) ህዝባችን በፕላስቲክ እቃ ይዞ ወደ ቤቱ ከገባ ይጣለው? ወይስ መልሶ ለአካባቢ ጥበቃ ያስረክበው? የሚል ጥያቄ ከጠየቁ ብኋላ የምናመርተው የፕላስቲክ ውጤት ዳግም እንድንጠቀምበት የሚያደርግ ቢሆን አይሻልም ወይ? ምክንያቱም 10 ጊዜ የምጠቀምበትን ፕላስቲክ አንድ ጊዜ ብቻ ተጠቀም ማለት ተገቢ አይደለም፣ አዋጁ ፕላስቲኩን ከተጠቀምኩበት ወዲያ የት ማስቀመጥ እንዳለበት አላስቀመጠም ብለዋል፡፡

አዋጁ ይዞ የተገኝ እንዲቀጣ ይደነግጋል ህዝባችን የዚህ ግንዛቤ ይኖረዋል ወይ? የትኛው ፕላስቲክ እንደሆነ የመለየት ግንዛቤስ አለው ወይ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ሌላ አንድ የምክር ቤት አባል በበኩላቸው ማንኛውም ሰው ፕላስቲክ ይዞ ከተገኘ ከሁለት እስከ አምስት ሺህ ብር እንዲቀጣ ይደነግጋል፤ ይህ ከእኛ ነባራዊ ሁኔታ ጋር እንዴት ታየ? በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ያለው የማህበረሰብ ክፍል ሊጠቀመው ስለሚችል ጫና አይፈጥርም ወይ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ለጥያቄዎቹ ምላሽ የሰጡት የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አወቀ አምዛዬ(ዶ/ር) ለአንድ ጊዜ ብቻ አገልግሎት ላይ የሚውሉ ፌስታሎችን ዝቅተኛው የማህበረሰብ ክፍልም ስለሚጠቀማቸው ቅጣቱ ያን ግንዛቤ ውስጥ ያስገባ ነው ብለዋል፡፡ለምሳሌ «አንዲት አሮጊት ወይም ሽማግሌ የሁለት ብር ዳቦ ወይም የአስር ብር ስኳር ገዝተው ሲሄዱ 5 ሺህ ብር ክፍሉ ቢባሉ ላይኖራቸው ስለሚችል ቅጣቱ ከ5 ሺህ ወደ 2 ሺህ ዝቅ እንዲል ተደርጓል ይህም የህብረተሰቡን የመክፈልም አቅም ከግንዛቤ ያስገባ ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡

የፕላስቲክ ከረጢቶች ከቅጣቱ በላይ ሀገርን የሚጎዱ ናቸው እስከ መቶ ዓመት ድረስም አይበሰብሱም ያሉት ምክትል ሰብሳቢው፤ ከዚህ አንጻር ቅጣቱ ሃያም ሰላሰም ሺህ ቢሆን ሀገርን ለማትረፍ ነው ብለዋል፡፡ለህዝቡ ግንዛቤ ለመስጠትም ከመጪው ሃሙስ ጀምሮ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ይካሄዳል ሲሉ አወቀ አምዛዬ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

አዋጁ የፕላስቲክ ጫማዎችን፣ የውሃ ኮዳዎችን እና ወፍራም የፕላስቲክ ውጤቶችን አይጨምርም መባሉን ሰምተናል፡፡አዋጁ ማንኛውም ሰው ከመኖሪያ ቤቱ ድንበር አንስቶ ከሃያ ሜትር በላይ አካባቢውን የማጽዳት ግዴታን ያስቀምጣል፡፡አዋጁ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

Via Sheger
@YeneTube @FikerAssefa
አቶ ታዬ ደንደአ ጉዳያቸውን ማረሚያ ወርደው እንዲከታተሉ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ!

የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ አቶ ታዬ ደንደአ የዋስትና መብታቸው ተነስቶ ጉዳያቸውን ማረሚያ ሆነው እንዲከታተሉ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጥቷል።አቃቤ ህግ በታዬ ደንደአ ላይ ከዚህ ቀደም አቋርጦት የነበሩ ሁለት ክሶችን ዳግም አንቀሳቅሷል።

ተከሳሹ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 251/ሐ ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ክስ ቀርቦባቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡አቶ ታዬ የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ በነበሩበት ወቅት የሀገርን፣ የመንግስትንና የህዝብን ደህንነት ማረጋገጥ ሲገባቸው ይህን ወደ ጎን በመተው በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ወንጀል ሕግ አንቀፅ 257 ንዑስ አንቀጽ (ሠ) በመተላለፍ ሲንቀሳቀሱ እንደነበር በክሱ ላይ ተመልክቷል፡፡

በዚህም በአሽባሪነት የተሰየመው ኦነግ ሸኔ በኦሮሚያ ክልል እንዲሁም የታጠቁ ፀረሰላም ኃይሎች በአማራ ክልል ከመንግስት ጋር ጦርነት ላይ ባሉበት ጊዜ የእነዚህን ፀረሰላም ኃይሎች ፕሮፖጋንዳ ተቀባይነት እንዲያገኝ በማሰብ በራሳቸው ስም በተከፈተ ማህበራዊ ሚዲያዎች የፕሮፖጋንዳ መልክቶችን ያስተላለፉ በመሆኑ ክስ ቀርቦባቸዋል።

በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሐምሌ 30 ቀን 2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት ቀርቦባቸው በነበረው ሁለት ክሶች መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ ተሰናብተው እንደነበር ይታወሳል።ተከሳሹ ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ ትዕዛዝ በመስጠት የመከላከያ ምስክርን ለመስማት ለሰኔ 30 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ሲል ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
«የህወሓት አመራሮች ትግራይን ወደሌላ ጥፋት ከሚያስገባ አካሄድ ይቆጠቡ» ሲል ሳልሳይ ወያነ ትግራይ አሳሰበ!

የህወሓት አመራሮች ካለፈ ጦርነት ያላገገመች ትግራይ ዳግም ወደሌላ ጥፋት ከሚያስገባ አካሄድ ይቆጠቡ ሲል ተቃዋሚው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ገለፀ።በሌላ በኩል በክልሉ ተደቅኖ ያለ ፖለቲካዊ እና የፀጥታ አደጋ የሚያስቀር እውነተኛ ፖለቲካዊ ውይይ እንዲደረግ ፓርቲው ጥሪ አቅርቧል። 

በትግራይ በተቃዋሚነት የሚንቀሳቀሰው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ትላንት ባሰራጨው መግለጫ እንዳለው ከኢትዮጵያና ኤርትራ መንግስታት ባህሪ እንዲሁም እያካሄዱት ካለ የሚድያ ዘመቻ በመነሳት ሲታይ ወደ ጦርነት እያመሩ መሆኑ መረዳት ይቻላል ያለ ሲሆን፥ እነዚህ በጋራ በትግራይ ላይ ጦርነት ከፍተው የነበሩ ሐይሎች ዳግም ትግራይ የጦርነት አውድማ እንዳያደርጓት ስጋቱ ከፍተኛ መሆኑ አመልክቷል። 

የትግራይ ጉዳይ አጀንዳዎች ያለሆኑ የህወሓት መሪዎች፣ ትግራይ ካለፈው ጦርነት ጠባሳ ሳታገግም ወደ ሌላ ጦርነት የምትገባበት ፖለቲካዊ አካሄድ ከጀመሩ ቆይተዋል በማለት የከሰሰው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ፥ በተለያየ አቅጣጫ ተሰልፈው ትግራይን ወደጦርነት እየገፉ ያሉ ቡድኖች ከድርጊታቸው ይቆጠቡ ብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
የቻናል ጥቆማ!

የonline ስራዎችን ታገኙበታላችሁ!
🚀 Upwork Profile Mastery 
Standout & land high-paying Upwork gigs!
Profile Tips 
Proposal Templates 
Niche Strategies 
📂 Free Tools + Examples 
👉 Join: https://www.tg-me.com/UpworkProfilePro 
መረጃዎችን ለመላክ @honelegn19
🎯 For Beginners:
• Profile Setup & Review 
• Proposal Writing Help 
• First Job & Rate Strategy 
• Client Communication Tips 
• Niche & Rules Guidance 
• Contract & Tool Support 
• Q&A Mentorship
🌟 Empowering freelancers with real strategies. 
መልካም እድል ለሁላችሁም!
Forwarded from YeneTube
🗝️  እጅግ አመቺ በሆነ አከፋፈል የቤት ባለቤት ይሁኑ

60% የባንክ ብድር የተመቻቸላቸውን ቤቶች በልዮ ቅናሽ

❇️  በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው DMC Real Estate የመጨረሻው መንደር ወቅቱን ባገናዘበ  ቅናሽ ዋጋ በተለያዩ ካሬ አማራጮች አቅርቦሎታል : :

⭐️ከሀያ አምስት ዓመታት በላይ ግንባታ ላይ ከቆየ አንጋፋ ድርጅት

📍አድራሻ - በመሀል ከተማ ለቡ መብራት-ሀይል

💸ቅድመ ክፍያ
   
    💎ባለ 1 መኝታ  በ 431 ሺ ብር
    💎ባለ 2 መኝታ  በ 619 ሺ ብር
    💎ባለ 3 መኝታ  በ 751 ሺ ብር
    💎ባለ 4 መኝታ  በ 1,051,626 ብር 

🛍️🛒ሱቆች ከ 43 ካሬ ጀምሮ

🏦60% የባንክ ብድር የተመቻቸላቸው (እየኖሩበት ወይም አከራይተውት እስከ 20 አመት ቀስ ብለው የሚከፍሉት)

➡️በ 8% ቅድመ ክፍያ

➡️እስከ 30% በሚደርስ ቅናሽ ዋጋ (ለ20 ቤቶች) በመጠቀም የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ


➡️☎️ 09 31 14 82 42

➡️@Novi_03 (telegram)

➡️Whatsapp Link-
https://wa.me/251931148242
2025/07/06 22:08:32
Back to Top
HTML Embed Code: