Telegram Web Link
ወደ ትግራይ ይጓዙ የነበሩ እና በአፋር ክልል ቆመው የሚገኙ የጭነት መኪኖች እንዲለቀቁ የክልሉ መንግስት ጠየቀ!

የሸቀጥ ጭነት ይዘው በአፋር ክልል በኩል ወደ ትግራይ ይጓዙ የነበሩ መኪኖች ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በአፋር ክልል እንዳይንቀሳቀሱ መደረጋቸውን የትግራይ ክልል መንግስት አስታወቀ፤ የፌደራል መንግስት መፍትሔ እንዲሰጠው ጠይቋል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የንግድ እና ሰነድ ኤጀንሲ ለንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስቴር ለዶ/ር ካሳሁን ጎፌ በጻፈው ደበዳቤ ወደ ትግራይ ክልል ጭነት ይዘው የሚጓጓዙ ተሽከርካሪዎች መከልከላቸውን አስታውቆ ማብራሪያ ጠይቋል።

የክልሉ ቴሌቪዥን በበኩሉ ሁሉም የጭነት መኪኖች ህጋዊ መሆናቸውን የሚገልጽ ሰነድ ያላቸው ቢሆንም እንዳይጓዙ የተደረገበት ምክንያት እንዳልተገለጸላቸው አስታውቋል፤ በጭነት መኪኖቹ ክልከላ ዙሪያ ከፌደራል መንግስቱም ይሁን ከአፋር ክልል በኩል የተባለ ነገር አለመኖሩን አመላክቷል።

በአፋር ክልል ወደ ትግራይ በሚወስደው መንገድ ብቻ ሳይሆን በአማራ ክልል በወልድያ በኩል ወደ መቀለ የሚወስደው መንገድ ላይ የጭነት መኪኖቹ እንዳያልፉ መከላከልቸውን ቢቢሲ ምንጮቹን ዋቢ በማድረግ አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
አይ ኤም ኤፍ ለኢትዮጵያ ከሚሰጠው ብድር ውስጥ 260 ሚሊዮን ዶላር ሊለቅ ነው!

ኢትዮጵያ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) ባለሙያዎች፤ በተራዘመ የብድር አቅርቦት ሶስተኛ ግምገማ ላይ ከስምምነት ደረሱ። ግምገማው በአይ ኤም ኤፍ ስራ አስፈጻሚ ቦርድ ሲጸድቅ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ከዓለም አቀፉ ተቋም ከሚበደረው 3.4 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ 260 ሚሊዮን ዶላር ይለቀቅለታል።

የአይ ኤም ኤፍ ቦርድ ግምገማውን ከማጽደቁ በፊት፤ የኢትዮጵያ መንግስት ከይፋዊ አበዳሪዎች ጋር የመግባቢያ ስምምነት ላይ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። ይህንን ዛሬ አርብ ግንቦት 22፤ 2017 ይፋ ያደረጉት፤ ከሁለት ወር ገደማ በፊት ወደ አዲስ አበባ መጥቶ የነበረውን የአይ ኤም ኤፍ የባለሙያዎች ቡድን የመሩት አልቫሮ ፒሪስ ናቸው።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
የገንዘብ ሚኒስቴር አዲስ የታክስ ኦዲት መመሪያ አወጣ!

የገንዘብ ሚኒስቴር የታክስ ኦዲት አፈጻጸምን እና የታክስ ስሌት ማስታወቂያ አወጣጥን የሚመራ አዲስ መመሪያ ቁጥር 1063/2017 አውጥቷል። መመሪያው በትላንትናው ዕለት ግንቦት 21 ቀን 2017 ዓ.ም. የወጣ ሲሆን፣ የታክስ አስተዳደር ሥርዓቱን ውጤታማ፣ ቀልጣፋና ግልጽ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።

ይህ አዲስ መመሪያ የታክስ ባለሥልጣን ባለሙያዎችንና ታክስ ከፋዮችን ኃላፊነት የሚደነግግ ሲሆን፣ በተለያዩ የታክስ ኦዲት ዓይነቶች ላይ፣ እንደ የተመላሽ ኦዲት፣ የዴስክ ኦዲት፣ ጭብጥ ተኮር ኦዲት፣ አጠቃላይ ኦዲት እና የማጭበርበር ምርመራን ጨምሮ ተፈጻሚ እንደሚሆን ይደነግጋል።

መመሪያው የፌዴራል መንግስትን የታክስ አዋጅ ድንጋጌዎች ተግባራዊ ለማድረግ የተሟላ ማዕቀፍ እንደሚሰጥ፣ እንዲሁም የኦዲት ሂደቱ ወጥነት ያለው፣ ግልጽነት የሰፈነበት እና የታክስ ከፋዮች መብት የሚጠበቅበት መሆኑን እንደሚያረጋግጥ ተመላክቷል።

የታክስ ስሌት ማስታወቂያ የሚላከው ታክስ ባልተከፈለበት፣ ተጨማሪ ታክስ እንዳለ ሲረጋገጥ፣ ወይም ታክስ ማጭበርበር ጥርጣሬ ሲኖር የተባለ ሲሆን የመስክ ኦዲት ከመጀመሩ አስር የስራ ቀናት በፊት ለታክስ ከፋዩ የጽሁፍ ማስታወቂያ መሰጠት እንዳለበት ካፒታል ከመመሪያው ለመረዳት ችሏል።

ኦዲት በሚደረግበት ጊዜ ታክስ ከፋዮች ለኦዲተሮች ምቹ ሁኔታዎችን የማመቻቸትና የሚጠየቁ ሰነዶችን የማቅረብ ግዴታ እንዳለባቸው ያሳስባል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
#ከቴምር ሪልስቴት
‼️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ መሀል ሣር ቤት አፓርትመንት እና ሱቅ ፒያሳ ለሽያጭ ያወጣነው 

🎯የክፍያ አማራጮች 40/60 ለሚከፍል

👉1መኝታ 75ካሬ 4,815,000ብር ሙሉ ክፍያ
👉2መኝታ 94ካሬ 6,034,800ብር ሙሉ ክፍያ
👉2መኝታ 103ካሬ 6,612,600ብርሙሉክፍያ
👉3መኝታ 132ካሬ 8,474,400ብር ሙሉ ክፍያ
👉3መኝታ 146ካሬ 9,373,200ብር ሙሉ ክፍያ 9,373,000ብር 

‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ 
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
       👇👇👇👇👇👇
     +251939770177
     +251996856273
https://www.tg-me.com/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
Ethiopian Building Codes Standards
Private Sector Engagement in Building Code Revision


The Ethiopian Construction Authority, in collaboration with the College of Technology and Built Environment (formerly AAiT) and The Urban Center, is organizing a series of technical sessions in June 2025 to support the ongoing revision of the Ethiopian Building Code Standards.

Designed for professionals in the construction industry, the 14 expert-led sessions of EBCS will address key themes such as structural design, fire and earthquake safety, mechanical and electrical systems, and emerging building technologies. These sessions aim to highlight the building codes and gather input from the private sector, ensuring that industry experience is reflected in the revised codes, making them both inclusive and grounded in practice.

📍Venue: The Urban Center
📅 Participation by registration only
🔗 Register here

#EthiopianBuildingCodeStandards
Open to professionals, engineers, architects, and others in the construction sector
83 በመቶ የሚሆነው የትራፊክ አደጋ የሚከሰተው በአሽከርካሪዎችና በተሽከርካሪ የቴክኒክ ብቃት ችግር ምክንያት መሆኑ ተገለጸ!

በከፍተኛ ደረጃ እየተከሰተ ካለው የትራፊክ አደጋ ውስጥ 69 በመቶ ገደማ የሚሆነው በአሽከርካሪዎች እና 14 በመቶ የሚሆነው ደግሞ በተሽከርካሪ የቴክኒክ ብቃት ምክንያት የሚከሰት መሆኑን የመንገድ ደህንነት እና መድህን ፈንድ አገልግሎት ለአሐዱ ገልጿል።

በሀገሪቱ ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ የመጣው የትራፊክ አደጋ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የገለጹት በአገልግሎቱ የመንገድ ደህንነት ትምህርትና ግንባታ መሪ ሥራ አስፈፃሚ ዮሐንስ ለማ፤ ለአደጋው መጨመር ምክንያቱ ብዙ ቢሆንም በዋናነት የአሽከርካሪዎች ቸልተኝነት ተጠቃሽ መሆኑን ተናግረዋል።መሪ ሥራ አስፈፃሚው አክለውም የእግረኞች የመንገድ አጠቃቀም ችግር፣ የመንገድ ሁኔታ እና በተለይ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከልክ በላይ ፍጥነት ማሽከርከር ለአደጋው ተጋላጭ የሚያደረጉ መንስኤዎች መሆናቸውን ተናግረዋል።

"አደጋው የሰው ሕይወት ከማጥፋቱ በተለይም አምራች የሚባለውን የሀገሪቱን ወጣት እያሳጣን ነው" ያሉት አቶ ዮሐንስ፤ በንብረት ውድመት ላይ እየደረሰ ያለው ምጣኔ ሃብታዊ ኪሳራ ቀላል የሚባል አለመሆኑን አንስተዋል።የትራፊክ አደጋው በአብዛኛው ከ5 እስከ 30 የእድሜ ክልል ውስጥ ባሉ ሰዎች ላይ የሚከሰት ሲሆን፤ አደጋውን የሚያደርሱት ደግሞ ከ18 እስከ 30 እድሜ ያሉ አሽከርካሪዎች እንደሆኑም አቶ ዮሐንስ ጠቁመዋል።

በ2016 ዓ.ም በንብረት ላይ በደረሰ አደጋ ብቻ ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙን አስታውሰዋል።የትራፊክ አደጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ አደጋው በትራፊክ ፓሊስና የሚመለከተው ባለድረሻ አካል ቁጥጥር ብቻ መቀነስ ስለማይቻል ሁሉም በጋራ ሊሰራ እንደሚገባ መሪ ሥራ አስፈፃሚው አሳስበዋል።

Via Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa
የእነ አቶ ጌታቸው ረዳ ፓርቲ በአንድ ወር ከአጋማሽ ውስጥ “በትግራይ መስራች ጉባኤዬን አካሄዳለሁ” አለ 

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጊዜያዊ ፍቃድ ያገኘው ዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ ፓርቲ (ስምረት)፤ እስከ አንድ ወር ተኩል ባለው ጊዜ ውስጥ መስራች ጉባኤውን እንደሚያካሄድ ገለጸ። ፓርቲው ከመጪው ሰኞ ጀምሮ የአባላት ምልመላ እና ከክልል እስከ ቀበሌ ያሉ አደረጃጀቶችን የመፍጠር ስራዎችን እንደሚያከናውን አስታውቋል። 

ስምረት ፓርቲ ይህን የገለጸው፤ ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 23፤ 2017 በአዲስ አበባው ሸራተን ሆቴል በሰጠው የመጀመሪያው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው። ጋዜጣዊ መግለጫውን ከፓርቲው መስራቾች አንዱ የሆኑት የቀድሞው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት በነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ ይሰጡታል ተብሎ ቢጠበቅም፤ ባጋጠማቸው “የጤና እክል” ምክንያት በመግለጫው ሳይሳተፉ ቀርተዋል።

እርሳቸውን በመተካት መግለጫውን የሰጡት የአዲሱ ፓርቲ የሚዲያ እና የኮሚዩኒኬሽን ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ረዳኢ ሓለፎም፤ ፓርቲው በሚቀጥለው አንድ ወር ውስጥ ሁለት መሰረታዊ ስራዎችን እንደሚያከናውን ተናግረዋል። መቶ አባላትን በመያዝ ጊዜያዊ ፍቃዱን ከምርጫ ቦርድ ያገኘው ስምረት፤ በዚህ ጊዜ ውስጥ ከትግራይ እና ከሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች አባላትን የመልመል ስራዎች እንደሚሰራ አቶ ረዳኢ ተናግረዋል።

🔴 ዝርዝሩን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16063/

🔴 ሙሉ መግለጫውን በቪዲዮ ለመመልከት ➡️  https://youtu.be/B-oc3qLdRIg
ሳውዲ አረቢያ ኢትዮጵያን ጨምሮ በ14 ሀገራት ላይ የቪዛ እገዳ ጣለች!

ሳውዲ አረቢያ በድምሩ በ14 ሀገራት ዜጎች ላይ የብሎክ ቪዛ ማውጣትን በጊዜያዊነት ማገዷን አስታውቃለች።ከነዚህ ሀገራት መካከል ኢትዮጵያን ጨምሮ ሰባት የአፍሪካ ሀገራት ይገኙበታል።

ይህ የቪዛ እገዳ አዲስ የጊዜያዊ የሥራ ቪዛ ማመልከቻዎችን እና በመጠባበቅ ላይ ያሉትንም የሚመለከት ነው የተባለ ሲሆን በውጭ ዜጎች የሥራ ኃይል ላይ የተመሰረቱ የሳውዲ አረቢያ ዘርፎችን እንደሚጎዳ ተገልጿል።

በእገዳው ሰለባ ሆነዋል ከተባሉት የአፍሪካ ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ ፣ ግብፅ፣ ናይጄሪያ፣ አልጄሪያ፣ ሱዳን፣ ቱኒዚያ እና ሞሮኮ ይገኙበታል። ከዚህ በተጨማሪ ኢንዶኔዥያ፣ ኢራቅ፣ ዮርዳኖስ፣ የመን፣ ህንድ፣ ፓኪስታን እና ባንግላዲሽ ተካትተዋል።እነዚህ ሀገራት ከሳውዲ አረቢያ ከፍተኛ የሰው ኃይል ፍልሰትና የገንዘብ ዝውውር ስለሚያገኙ፣ እገዳው ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጫና ሊያስከትል እንደሚችል ተዘግቧል።

የብሎክ ቪዛ የሳውዲ አረቢያ ቀጣሪዎች ቀድሞ በተፈቀደላቸው ኮታ የውጭ ሠራተኞችን እንዲቀጥሩ የሚያስችል ነው። የሳውዲ አረቢያ መንግስት የቪዛ እገዳውን የጣለበትን ዝርዝር ምክንያት ባይገልጽም፣ ይህ እርምጃ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰራተኞችን ዕጣ ፈንታ አጣብቂኝ ውስጥ ሊጥል እንደሚችል ካፒታል ለመረዳት ችሏል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ አሸማጋይ ድርጅት መሥራች አባል ሆነች

በቻይና የሆንግ ኮንግ ልዩ አስተዳዳር በትናንትናው ዕለት በተካሄደ የፊርማ ሥነ-ሥርዓት የዓለም አቀፍ አሸማጋይ ድርጅት በይነ መንግሥታዊ ተቋም መመሥረቱ ይፋ ሆኗል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኢትዮጵያ መሥራች አባል ሆና መፈረሟ በመንግሥታት መካከል የሚፈጠሩ ግጭቶችና አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ በሽምግልና ለመፍታት ያላትን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ መሆኑን ገልጸዋል።

አክለውም፤ ተቋሙ በመንግሥታት፣ በመንግሥታትና በግሉ ዘርፍ መካከል የሚፈጠሩ ከኢንቨስትመንት ጋር የተያያዙ አለመግባባቶችን በሠላማዊ መንገድ በሽምግልና ለመፍታት ያቀደ መሆኑን መጠቆማቸውን  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመልክቷል

@Yenetube @Fikerassefa
የፒኤስጂ ደጋፊዎች በፓሪስ ደስታቸውን ሲገልፁ በተነሳ ግርግር 2 ሰዎች ሞተው፣ 192 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል

ፒኤስጂ ትናንት የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግን ማሸነፉን ተከትሎ የክለቡ ደጋፊዎች በፈረንሳይ ዋና ከተማ በፓሪስ ጎዳናዎች ላይ ደስታቸውን ሲገልጹ አምሽተዋል።

በዚሁ ወቅት በተነሳ ግርግር 2 ሰዎች ሞተው 192 ደግሞ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፤ ከ500 በላይ ሰዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል።

ይህ እንዳይመጣ ተፈርቶ ከ5 ሺህ 400 በላይ ፖሊሶች በደንብ ማስከበር ሥራ ላይ ተሰማርተው የነበረ ቢሆንም፤ ደስታቸው ከቁጥጥር ውጪ የሆነባቸው ድጋፊዎች ግን በተለያዩ ቦታዎች እሳት አስነስተዋል።

በዚህም 200 ያህል መኪኖች እንደተቃጠሉ እንዲሁም የአውቶቡስ ፌርማታዎችና ሌሎች መሰረተ ልማቶች እንደተሰባበሩ ታውቋል።

ደጋፊዎቹ ከፖሊስ ጋርም ተጋጭተው የነበረ በመሆኑ፤ ፖሊስ ውሃ በመርጨት እና አስለቃሽ ጭስ በመተኮስ ለመበተን ሞክሯል።

በተነሳው ግርግር 22 ፖሊሶች እና 9 የእሳት አደጋ ሰራተኞችም ጉዳት ደርሶባቸውል።

በትናንትናው ዕለት ፓሪስ ሴንት ዠርሜን የጣሊያኑን ኢንተር ሚላን በሰፊ የጎል ልዩነት በማሸነፍ የመጀመርያውን የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ያነሳ ሲሆን፤ በዚህም በፓሪስ የሚገኙ ድጋፊዎቹም ደስታቸው ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ አምሽተዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
የቻናል ጥቆማ!

የonline ስራዎችን ታገኙበታላችሁ!
🚀 Upwork Profile Mastery 
Standout & land high-paying Upwork gigs!
Profile Tips 
Proposal Templates 
Niche Strategies 
📂 Free Tools + Examples 
👉 Join: https://www.tg-me.com/UpworkProfilePro 
መረጃዎችን ለመላክ @honelegn19
🎯 For Beginners:
• Profile Setup & Review 
• Proposal Writing Help 
• First Job & Rate Strategy 
• Client Communication Tips 
• Niche & Rules Guidance 
• Contract & Tool Support 
• Q&A Mentorship
🌟 Empowering freelancers with real strategies. 
መልካም እድል ለሁላችሁም!
🗝️  እጅግ አመቺ በሆነ አከፋፈል የቤት ባለቤት ይሁኑ

60% የባንክ ብድር የተመቻቸላቸውን ቤቶች በልዮ ቅናሽ

❇️  በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው DMC Real Estate የመጨረሻው መንደር ወቅቱን ባገናዘበ  ቅናሽ ዋጋ በተለያዩ ካሬ አማራጮች አቅርቦሎታል : :

⭐️ከሀያ አምስት ዓመታት በላይ ግንባታ ላይ ከቆየ አንጋፋ ድርጅት

📍አድራሻ - በመሀል ከተማ ለቡ መብራት-ሀይል

💸ቅድመ ክፍያ
   
    💎ባለ 1 መኝታ  በ 431 ሺ ብር
    💎ባለ 2 መኝታ  በ 619 ሺ ብር
    💎ባለ 3 መኝታ  በ 751 ሺ ብር
    💎ባለ 4 መኝታ  በ 1,051,626 ብር 

🛍️🛒ሱቆች ከ 43 ካሬ ጀምሮ

🏦60% የባንክ ብድር የተመቻቸላቸው (እየኖሩበት ወይም አከራይተውት እስከ 20 አመት ቀስ ብለው የሚከፍሉት)

➡️በ 8% ቅድመ ክፍያ

➡️እስከ 30% በሚደርስ ቅናሽ ዋጋ (ለ20 ቤቶች) በመጠቀም የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ


➡️☎️ 09 31 14 82 42

➡️@Novi_03 (telegram)

➡️Whatsapp Link-
https://wa.me/251931148242
ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ5 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ሬሚታንስ ወደ ሀገር ውስጥ መላኩን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍጹም አረጋ ለኢዜአ እንደተናገሩት በ2016 ዓ.ም አጠቃላይ የተላከው ሬሚታንስ 4 ነጥብ 4 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ሲሆን በ2017 ዓም ዘጠኝ ወራት ብቻ 5 ነጥብ 1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወደ ኢትዮጵያ ተልኳል ፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
#ከቴምር ሪልስቴት
7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ መሀል ሣር ቤት አፓርትመንት እና ሱቅ ፒያሳ ለሽያጭ ያወጣነው 

🎯የክፍያ አማራጮች 40/60 ለሚከፍል

👉1መኝታ 75ካሬ 4,815,000ብር ሙሉ ክፍያ
👉2መኝታ 94ካሬ 6,034,800ብር ሙሉ ክፍያ
👉2መኝታ 103ካሬ 6,612,600ብርሙሉክፍያ
👉3መኝታ 132ካሬ 8,474,400ብር ሙሉ ክፍያ
👉3መኝታ 146ካሬ 9,373,200ብር ሙሉ ክፍያ 9,373,000ብር 

‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ 
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
       👇👇👇👇👇👇
     +251939770177
     +251996856273
https://www.tg-me.com/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
Ethiopian Building Codes Standards
Private Sector Engagement in Building Code Revision


The Ethiopian Construction Authority, in collaboration with the College of Technology and Built Environment (formerly AAiT) and The Urban Center, is organizing a series of technical sessions in June 2025 to support the ongoing revision of the Ethiopian Building Code Standards.

Designed for professionals in the construction industry, the 14 expert-led sessions of EBCS will address key themes such as structural design, fire and earthquake safety, mechanical and electrical systems, and emerging building technologies. These sessions aim to highlight the building codes and gather input from the private sector, ensuring that industry experience is reflected in the revised codes, making them both inclusive and grounded in practice.

📍Venue: The Urban Center
📅 Participation by registration only
🔗 Register here

#EthiopianBuildingCodeStandards
Open to professionals, engineers, architects, and others in the construction sector
2025/07/06 16:03:56
Back to Top
HTML Embed Code: