Telegram Web Link
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
"ታማሚው ስለማይድን የተሰበሰበውን ብር ሰይጣን አሳስቶን አጠፋነው. . ."

ይህንን ያለው 9,000 ሰው ተሰብስቦ በሚመለከተው የቲክቶክ ሽምግልና ላይ ነው።

ከሞተር ወድቆ ከወገብ በታች ለማይንቀሳቀሰው አለሙ ቢጫ የተባለ ታማሚ ግለሰብ የተለያዩ ታዋቂ ቲክቶከሮች የእርዳታ ገንዘብ ቢሰበስቡም ለታማሚው ብር ሳይደርስ ቀርቶ ታማሚው ባቀረበው ተማፅኖ ብሩን የሰበሰቡት ቲክቶከሮች የተወሰነ ብር ቢመልሱም ዋነኛው ወጣት ግን 350,000 ሺህ ብር አካባቢ ለመመለስ ፈቃደኛ አልሆነም። ለዚህም የቀረበው ምክንያት " ታማሚው ስለማይድን ብሩን አጥፍቼዋለሁ . . . ቲክቶክ አካውንቴን ሸጬ እከፍላለሁ" ብሏል።

Via: ስንታየሁ ኃይሉ
@Yenetube @Fikerassefa
የአሜሪካው ም/ቤት የ95 ቢሊዮን ዶላር የውጪ ዕርዳታ አጸደቀ!

በአሜሪካ የተወካዮች ም/ቤት ለዩክሬን እና ለእስራኤል የሚሰጥን የ95 ቢሊዮን ዶላር የዕርዳታ ጥቅል ሕግ ከወራት ሙግት በኋላ ትናንት ቅዳሜ አጽድቋል።በኮንግረስ ያሉ መሪዎች ከቀኝ ዘመም ወግ አጥባቂዎች የደረሰባቸውን ተቃውሞ ወደ ጎን በማለት፣ ብዙም ባልተለመደ ሁኔታ ቅዳሜ ዕለት በተገናኘው ም/ቤት ሕጉን እንዲጸድቅ አድርገዋል።

አሁን የቀረው ሕጉን ወደ ሕግ አውጪው ሸንጎ ወይም ሴኔቱ መላክ ሲሆን፣ በዲሞክራቶቹ ቁጥጥር ስር ያለው ሴኔት እስከ ማክሰኞ ድረስ እንደሚያጸድቀው ይጠበቃል።

ከፓርቲያቸው ከፍተኛ ግፊት ያላባቸው ሪፐብሊካኑ የም/ቤቱ አፈጉባኤ ማይክ ጆንሰን፣ ወንበራቸውን እንደሚያጡ በፓርቲያቸው አባላት ዛቻ እየደረሰባቸው ሲሆን፣ ሕጉን ለማጽደቅ በተደረገው እያንዳንዱ እርምጃ የዲሞክራቶቹን ዕገዛ አግኝተዋል ተብሏል።

አራት ክፍሎች ያሉት ሕግ፣ ለዩክሬን፣ እስራኤል እና በኢንዶ ፓሲፊክ ለሚገኙ የአሜሪካ አጋሮች ገንዘብ የሚመድብ ሲሆን፣ ቲክ ቶክ በአሜሪካ ማኅበረሰብ ዘንድ ፈጥሯል የሚባለውንም ችግር የሚመለከት ነው።ሕጉ በም/ቤቱ የሚጸድቅ ከሆነ፣ በፊርማቸው እንደሚያጸኑት ፕሬዝደንት ባይደን ሲያስታውቁ ቆይተዋል።

[VoA]
@YeneTube @FikerAssefa
የመስተንግዶ ባለሙያዎች የአለባበስ ኮድ መመሪያ ዝግጅት በመጠናቀቁ በቅርቡ ፀድቆ ተግባራዊ ይሆናል ተባለ፡፡

በሆቴሎች የሚሠሩ ሴት የመስተንግዶ ባለሙያዎች ከሀገሪቱ ባሕል ውጪ የሆነውን አለባበሳቸውን ለማስተካከል የሚያስችል የአለባበስ ኮድ መመሪያ ዝግጅቱ በመጠናቀቁ በቅርቡ ፀድቆ ተግባራዊ እንደሚደረግ የአዲስ አበባ ባሕል፣ ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ገለጸ።

የአዲስ አበባ ባሕል፣ ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሂሩት ካሣው (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በአንዳንድ ሆቴሎች የሴት መስተንግዶ ሠራተኞች አለባበስ ከሀገሪቱ ባሕል ወጣ ያለ ነው።

ይህን ለማስተካከል የሚረዳ የመስተንግዶ ባለሙያዎች የአለባበስ ኮድ መመሪያ ዝግጅቱ ተጠናቆ ለከንቲባ ጽሕፈት ቤት እንዲፀድቅ በመላኩ መመሪያው በከተማዋ ካቢኔ በቅርቡ ፀድቆ ተግባራዊ እንደሚደረግ ይጠበቃል ብለዋል።

ለቱሪስቶች መስተንግዶ ሲሰጥ የሀገራችንን ባሕልና እሴት በጠበቀ መልኩ መሆን አለበት ያሉት ኃላፊዋ፤ በሆቴሎች ያለው የመስተንግዶ ባለሙያዎች አለባበስ ሥነ-ሥርዓቱን የጠበቀ መሆን እንዳለበት ተናግረዋል።

ሂሩት (ዶ/ር)እንዳመላከቱት፤ አሁን ላይ የመስተንግዶ ባለሙያዎች በተለይም ሴቶች በአንዳንድ ሆቴሎች አማካኝነት ሥነ-ሥርዓቱን ያልጠበቀ አለባበስ እንዲለብሱ ይገደዳሉ። ድርጊቱ ከሴት ልጅ መብት አኳያ ክብርን ያልጠበቀ እና አሳፋሪ ነው ብለዋል።

መመሪያው ፀድቆ ሥራ ላይ ሲውል በሆቴሎች የሚሠሩ የመስተንግዶ ባለሙያዎች ወጥ የሆነ ዓለማቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የአለባበስ ኮድ እንዲከተሉ ይደረጋል ያሉት ኃላፊዋ፤ ይህም የኢትዮጵያን ባሕልና ወግ ያልጠበቀ የአለባበስ ሥነ ሥርዓትን ለመቆጣጠር እንደሚያስችል አስረድተዋል።

አሁን ላይ በአንዳንድ ሆቴሎች የሚታየውን ከባሕል ያፈነገጠ የመስተንግዶ ባለሙያዎች አለባበስ መስተካከል እንዳለበት የከተማው ነዋሪዎች ጥያቄ እንደሚያቀርቡ ገልጸው፤ መመሪያው ሲፀድቅ የሁሉንም ጥያቄ እንደሚመልስ አብራርተዋል። ሕጉ ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣትም ጭምር ያለው በመሆኑ መመሪያውን በሚተላለፉ ላይ ቅጣት እንደሚጣል ጠቁመዋል።

የአለባበስ መመሪያውን ለማውጣት ቢሮው ሁለት ዓመት ሲሠራ መቆየቱን ተናግረው፤ ሕጉ ከፀደቀ በኋላ ወደ ርምጃ እንደሚገባ አመላክተዋል። ሕጉ እስኪፀድቅ የቁጥጥር ሥራ የሚሠራ ሲሆን በሚደረገው ክትትልና ድጋፍም አሁን ላይ ለውጦች መኖራቸውን ተናግረዋል።

በቱሪዝም ዘርፉ ውድድር በዓለም አቀፍ ይዘት ያለው በመሆኑ ደረጃውን ያልጠበቀ መስተንግዶ የሚሰጥ ከሆነ ቱሪስቶች ተመልሰው እንደማይመጡ የሚገልጹት ሂሩት (ዶ/ር)፤ በሆቴሎች መልካም መስተንግዶ እንዲሰጥ ለማስቻል ቢሮው በየዓመቱ ሁለት ሺህ ለሚደርሱ በሥራ ላይ ላሉ መስተንግዶ ሰጪ ባለሙያዎች ሥልጠና እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።

በከተማዋ ያሉ ዓለም አቀፍ ሆቴሎች የመስተንግዶ ባለሙያዎቻቸው አለባበስ ጥሩ መሆኑን ጠቅሰው፤ በመጠኑ ከሴት የመስተንግዶ ባለሙያዎች የፀጉር አያያዝ ሥነ-ሥርዓት ጋር በተያያዘ የማይፈቀዱ ነገሮች በአንዳንድ ሆቴሎች የሚታዩ በመሆኑ እንዲሻሻሉ ክትትል ይደረጋል ብለዋል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ክልል መንግሥት ለሕዝቡ ጥሪ አቀረበ።

የሕወሓት ታጣቂ ቡድን የሰላም አማራጮችን ወደ ጎን በመተው የማንነት ጥያቄ ያለባቸውን የራያ አላማጣ፣ የራያ ባላ፣ ኦፍላ፣ ኮረም እና ዛታ አካባቢዎችን በወረራ ይዟል::

ይህንን ተከትሎ የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ የአማራ ሕዝብ ዛሬም እንደትላንቱ ከሀሰት ፕሮፓጋንዳ እና ከሰርጎ ገቦች ራሱን እና አካባቢውን እንዲጠብቅ ጥሪ አስተላልፏል::

ሕዝቡ ከክልሉ መንግሥት እና በየአካባቢው ከሚገኙ አስተዳደሮች ጋር የጠበቀ ቁርኝት በመፍጠር ጠላቶቹ የከፈቱበትን ጥቃት ለመመከት በሚደረገው ጥረት የድርሻውን እንዲወጣ ነው ጥሪ ያደረገው::

የክልሉ መንግሥት ከአማራ ሕዝብ በተጨማሪ ለፌደራል መንግሥት እና ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ጥሪ አቅርቧል፤ ለፌደራል መንግሥት ባስተላለፈው ጥሪ የሕወሓት ታጣቂ ቡድን በወረራ ከያዛቸው ቦታዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ለቆ እንዲወጣ እና ሕዝቡን ከጥፋት መታደግ እና የሀገሪቱን ሉዓላዊነት መታደግ እንደሚገባ ጠቁሟል::

ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ደግሞ ሕወሓት በክልሉ ሕዝብ ላይ የፈጸመውን ወረራ በጥብቅ እንዲያወግዝ እና ከክልሉ ሕዝብ ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርቧል።

@Yenetube @Fikerassefa
በፒያሳ ለኮሪደር ልማት የፈረሱ ሰፈሮችን ጨምሮ በከተማው በርካታ ቦታዎች የሊዝ ጨረታ ወጣ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ፣ በአራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ ከአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየም ፊት ለፊት ለኮሪደር ልማት በሚል የፈረሱ ሰፈሮችን ጨምሮ ከ250 በላይ በሚሆኑ ቦታዎች ላይ የሊዝ ጨረታ ማውጣቱን ዋዜማ ከተመለከተችው የጨረታው ሰነድ ተረድታለች።

የሊዝ ጨረታው ከለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ውጭ በተቀሩት የከተማው አስር ክፍለ ከተሞች ባሉ ቦታዎች ላይ ወጥቷል። የሊዝ ጨረታው ለአመታት ከተቋረጠ በኋላ ሲወጣ የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።የጨረታው ሰነድም ከረቡዕ ሚያዝያ 9 2016 አ.ም ጀምሮ መሸጥ የተጀመረ ሲሆን ፣ የሰነድ ሽያጩ እስከ ሚያዝያ 24 ቀን 2016 አ.ም ድረስ እንደሚቀጥል ተነግሯል።

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎንደር ዞን ውስጥ በሚገኘው የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ከሦስት ቀናት በፊት የተነሳው እሳት መቆጣጠር አለመቻሉ ተገልጿል።

ሚያዚያ 10፣ 2016 ዓ.ም. በስፍራው የተነሳው እሳት በቁጥጥር ሥር አለማዋሉን የክልሉ ባለሥልጣን ገለጹ።የክልሉ የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ የሆኑት አባይ መንግሥቴ ለቢቢሲ እንደተናገሩት እሳቱ ከተነሳበት ቀን ጀምሮ የአካባቢው ማኅበረሰብ እና አመራሮች ለማጥፋት ጥረት ቢያደርጉም እሳቱን መቆጣጠር አልተቻለም።

“የቦታው አቀማመጥ አስቸጋሪ በመሆኑ ጠፋ ሲባል እንደገና እየተነሳ በቁጥጥር ሥር ማዋል አልተቻለም” ብለዋል።ሆኖም እሳቱ ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይስፋፋ የአሰሳ እና የጥበቃ ሥራ እየተሠራ ነው ያሉት ኃላፊው፣ እሳቱ ከቁጥጥር ውጪ አለመውጣቱን ተናግረዋል።

በፓርኩ የእሳት አደጋ ሲከሰት ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ አይደለም።
ከአምስት ዓመታት በፊት በፓርኩ ከፍተኛ እሳት ተነስቶ ከክልሉ እና ከፌደራል አቅም በላይ ሆኖ የእስራኤል እና የኬንያ እሳት ማጥፊያ ሄሊኮፕተርን ድጋፍ እስከ መጠየቅ ተደርሶ ነበር።

@YeneTube @FikerAssefa
መልዕክት ወደ ክልል ከተሞች ይላኩ ይቀበሉ።
#ፈጥን #ቀላል እና #አስተማማኝ
ቁ.1 አዲስ አበባ ከጎላጎል ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ኳሊቲ ህንፃ
0962627762 -ሀዋሳ
0980526262 - ወላይታ ሶዶ
0988627762 - አርባምንጭ
0925636333 - ቦረና
0980526262 - አዳማ
በኮሬ ዞን በቀጠለው ጥቃት አራት አርሶ አደሮች በታጣቂዎች መገደላቸው ተገለፀ!

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ፣ አራት ወጣት አርሶ አደሮች፣ ከምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና ወረዳ በተነሱ ታጣቂዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ።በእርሻ ሥራ ላይ እንደነበሩ የተገለጹት አርሶ አደሮች የተገደሉት፣ “ኦነግ ሸኔ” ባሏቸው ታጣቂዎች እንደኾነ፣ የኮሬ ዞን የሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ተፈራ ቦንዶራ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ ቆቦ ቀበሌ ትላንት ሚያዚያ 13 ተገደሉ ከተባሉ አራት ወጣት አርሶ አደሮች ውስጥ ሁለቱ የወንድማቸው ልጆች እንደኾኑ አቶ ምትኩ ሽብሩ በስልክ ለአሜሪካ ድምፅ በስልክ ገልፀዋል።

አራቱም የሁለት ቤተሰብ አባላት መኾናቸውን፣ የሟቾቹን ስም በመዘርዘር የገለፁት አቶ ምትኩ እርስ በርሳቸውም ዘመዳማቾች መኾናቸውን አክለዋል። ለጥቃቱ ጉጂ ዞን ውስጥ ይንቀሳቀሳሉ ያሏቸውን ታጣቂዎችን ተጠያቂ ያደረጉት አቶ ምትኩ፣ ይህን የሚያስቆም ኃይል ባለመኖሩ ሕዝቡ ስጋት ላይ መውደቁን ገልፀዋል።

አቶ አጋፋሪ መንገሻ የተባሉ የቆቦ ቀበሌ ነዋሪ የእርሻ ማሳቸውን አረም በሚያርሙበት እና ከብቶቻቸውን በሚጠብቁበት ወቅት እንደተገደሉ ተናግረዋል።

አቶ አጋፋሪ ተዘርፈዋል የተባሉ ከብቶች እና ሌሎች ንብረቶች ወደ ገላን ወረዳ እንደተወሰዱባቸው ገልፀው ክስ አሰምተዋል። ባለፈው ሳምንት የ13 ዓመት አዳጊ እና ሌላ አርሶ ከቆቦ ቀበሌ መገደላቸውን አቶ አጋፋሪ አስታውሰዋል።

የኮሬ ዞን ሰላም እና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ተፈራ ቦንዶራ በግብርና ሥራቸው ላይ የነበሩ አራት አርሶ አደሮች የተገደሉት ሸኔ ሲሉ በጠሯቸው የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ታጣቂዎች መኾኑን ተናግረዋል።አቶ ተፈራ አክለው ካለፈው ሚያዚያ 8/2016 ዓ.ም ጀምሮ፣ በአንድ ሳምንት ውስጥ ሰባት አርሶ አደሮች ዳኖ ፣ መቅሬዲ እና ቆቦ ከተሰኙ ቀበሌዎች ያልታጠቁ ሲቪሎች በታጣቂዎች መገደላቸውን አክለው ገልጸዋል::

ስለ ጉዳዩ ከአፋን ኦሮሞ ክፍል ባልደረባ ነሞ ዳንዲ የተጠየቁት፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትም፣ በዓለም አቀፍ ቃል አቀባዩ አቶ ኦዳ ተርቢ ክሱን አስተባብለዋል። ከምዕራብ ጉጂ ዞን ባለሥልጣናት አስተያየትና ምላሽ ለማካተት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም::ይሁን እንጂ ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ጉዳይ የተጠየቁት የአካባቢው ባለሥልጣናት፣ ቀበሌዎቹ በሸማቂዎች በሚደርሰው ጥቃት የተነሳ ከቁጥጥር ውጭ መኾኑና ለኅብረተሰቡ መግሥታዊ አገልግሎት መስጠት እንዳልተቻለ መናገራቸው ይታወሳል።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ በግማሽ አመት ብቻ 1ሺህ 358 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው እንዳለፈ ተነገረ።

በ2016 አመት በባለፊት ስድስት ወራቶች በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች ምክንያት 1ሺህ 358 ዜጎች ለሞት መዳረጋቸው ተነግሯል።በደረሱ አደጋዎች ምክንያትም ከ 1 ቢሊዮን ብር በላይ የሚሆን ንብረት እንደወደመ ነው የተገለጸው።

ባለፉት 6 ወራት ከ2.5 ሚሊዮን በላይ ህግ የተላለፉ ተሽከርካሪዎችን በመቅጣት ከ 1.8 ቢሊዮን ብር በላይ ለመንግስት ገቢ መደረጉም ተጠቁሟል፡፡የመንገድ ደህንነትና መድህን ፍንድ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አባሶ የመንገድ ትራፊክ አደጋን ለመከላከልና ሕግ ተላልፈው የሚገኙ አሽከርካሪዎች ላይ ተገቢውን የቅጣት ዕርምት ለመውስድ ቴክኖሎጅን በመጠቀም ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ሃላፊው አክለው እንደተናገሩት ከ 1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች የመንገድ ደኀንነት ትምህርቶች በካሪኩለም ውስጥ ለማካተት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ እና የተሽከርካሪዎች ቴክኒክ ብቃት ማረጋገጫ ተቋማት ያልተገቡ ማስረጃዎችን እንደሚሰጡ የገለፁት ሥራ አስፈጻሚው ተገቢውን ክትትል በማድረግ ላይ እንገኛለ ብለዋል።

ለአደጋ አጋልጭ የሆኑ መንገዶች ተለይተው የማሻሻያ ሥራዎች መከናወናቸውና የሞተር አልባ ትራንስፖርትንም ለማስፋፋት በ13 ከተሞች የመንገድና መሰል መሰረተ ልማቶችን የማልማት ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ገልጸዋል።ተደጋጋሚ ጥፋት የሚያጠፉ አሽከርካሪዎች ላይ መንጃ ፈቃድ እስከመንጠቅ የሚያደርስ እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ የገለጹት ሃላፊው አገልግሎቱ በአዲስ አበባና ሸገር ከተሞች ተግባራዊ በመደረግ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
ከጅቡቲ የባሕር ወደብ አቅራቢያ ስደተኞችን የጫነች ጀልባ ሰጥማ በደረሰው አደጋ 16 ተሰዳጆች መሞታቸው ተገለጸ።

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ድርጅት IOM ዛሬ እንዳስታወቀው 28ቱ የጀልባዋ ተሳፋሪዎች እስካሁን አልተገኙም። ጀልባዋ 77 ተሰዳጆችን አሳፍራ እንደነበር ነው IOM በኤክስ ገጹ ይፋ ባደረገው አጭር መረጃ ያመለከተው።ከተሳፋሪዎቹ ውስጥም ልጆች እንደሚገኙበትም አስታውቋል። የጅቡቲ መንግሥት የአደጋ ጊዜ ሕይወት አድን ሠራተኞች ባሕር ላይ በደረሰው አደጋ የተጎዱትን ለማዳን ጥረት እያደረጉ እንደሆነም ገልጸዋል።

እንዲህ ያለ አደጋ በተሰዳጆች ላይ በተጠቀሰው አካባቢ በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ሲደርስ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። የዛሬ ሁለት ሳምንት በጅቡቲ የባሕር ጠረፍ አቅራቢያ በደረሰው ተመሳሳይ የጀልባ አደጋ ልጆች ጨምሮ 38 ስተደኞች ሕይወታቸውን አጥተዋል። በተያያዘ ዜና ከፈረንሳይዋ ካሌ ደሴት ወደ ብሪታንያ ለመሻገር ሲሞክሩ አምስት ስደተኞች ባሕር ላይ በደረሰ አደጋ መሞታቸው ተሰምቷል።

ሟቾቹን ጨምሮ ከመቶ በላይ ስደተኞችን ጭና የነበረች መርከብ የገጠማትን አደጋ ተከትሎ የፈረንሳይ የባሕር ኃይል መርከቦች በስፍራው ደርሰው ተሳፋሪዎቹን ለማውጣት መቻላቸው ነው የተገለጸው። ተሰዳጆቹ ወደ ብሪታንያ ለመሻገር በሞከሩበት ምሽቱን የብሪታኒያ መንግሥት በሀገሪቱ የሚገኙ ሕገወጥ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ ለማሻገር የሚያስችለውን ሕግ አጽድቋል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from እድል SPORT
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የተከሰተው እሳት በቁጥጥር ስር መዋሉን የሰሜን ጎንደር አስተዳደር አስታወቀ

በአማራ ክልል ሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የተከሰተው እሳት በቁጥጥር ስር መዋሉን የሰሜን ጎንደር አስተዳደር አስታወቀ። ሚያዝያ 10 ቀን 2016 ዓ ም ከምሽቱ ሦስት ሰዓት መንስኤው እስካሁን ባልታወቀ ምክንያት በፓርኩ የተለያዩ አካባቢዎች የእሳት ቃጠሎ መነሳቱ ነው የተገለጸው።

እሳቱ በአካባቢው ሕዝብ ርብርብ በቁጥጥር ስር መዋሉን ዛሬ ለዶይቼ ቬሌ የተናገሩት የሰሜን ጎንደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ቢምረው ካሣ በድርጊቱ የተጠረጠሩ ሦስት ሰዎች መያዛቸውን አመልክተዋል።

በተጠርጣሪዎቹ ላይ በሕግ አግባብ ምርመራ ተደርጎ ጉዳዩ የሚጣራ መሆኑን፤ ቃጠሎው ያደረሰው የጉዳት መጠንም ተጣርቶ ይፋ እንደሚደረግም ተመልክቷል። የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የሚገኝበት አካባቢ ሦስት ዓይነት የአየር ጠባይ እንዳለና በየዓመቱም ተመሳሳይ የእሳት አደጋ በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ እንደሚከሰት ነው ባለሥልጣኑ የገለጹት።

ከቀናት በፊት የተነሳው እሳት በፓርኩ የተለያዩ ክፍሎች ላይ እንደነበር በማመልከትም ፓርኩ ጓሳ እንደመሆኑ የተዳፈነ እሳት ንፋስ አቀጣጥሎት እንዳይነሳ ክትትል የማድረግ ጥረት መኖሩንም ተናግረዋል። የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በጎርጎሪዮስ የዘመን ቀመር በ1978 በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና ባህል ድርጅት ዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት ተመዝግቧል።

@Yenetube @Fikerassefa
YeneTube
Photo
🇪🇹 ውድ ኢትዮጲያውያን አሜሪካ ሀገር የሚገኝ ዪኒቨርስቲ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ነፃ የትምህርት እድል ለአፍሪካውያን አቅርቧል፣ የዚህ እድል ተካፋይ ሁኑ ወይም ለእህት/ወንድም/ጓደኛ ላኩላቸው እና እድላቸውን ይሞክሩ፣ Application የሚያበቃው ሚያዚያ 28 ነው ፈጥነው ይመዝገቡ
__________
🇺🇸 Are you passionate about Artificial Intelligence and Business? Do you want to become an Al leader and tackle global challenges?

Arizona State University , in partnership with the Mastercard Foundation, is offering 5 scholarships for the 2024/2025 academic year! These scholarships will cover:

- Full tuition fees
- Accommodation expenses
- Comprehensive support
- Visa application costs
- English language test costs
- Airfare to and from Phoenix, Arizona
- Participation in Scholarship programming
To be eligible, you must:
- Be a citizen of an African country
- Be between 18 and 33 years old
-Demonstrate leadership, academic excellence, and community engagement
- Have earned an undergraduate degree with a minimum 4 years of study
- Not have started or completed another graduate or master's degree before August 2024
- Be able to live in Phoenix, Arizona for the duration of the program

Apply here: https://lnkd.in/eFbEMfQt

Official Link: https://asu.co1.qualtrics.com/jfe/form/SV_07WFFri1Y0P5LWm

Women, refugees, displaced persons, and people with disabilities are strongly encouraged to apply!

#scholarship #africa #ethiopia #free #ethiopia
ህ.ወ.ሓ.ት ከብልጽግና ፓርቲ ጋር ለመቀላቀል ውይይት አላደረግኩም፤ መሰረታዊ ልዩነቶችም አሉን ሲል ገለጸ

የህወሓት እና የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች እያደረጉ የሚገኙት ውይይት "ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኋላ የተፈጠረውን አንፃራዊ ሰላም ለማስፋት እና ለማጠናከር ያለመ ነው" ሲል ድርጅቱ ትላንት እና ዛሬ እየወጡ የሚገኙ ዘገባዎችን ዛሬ ባሰራጨው መግለጫ ማስተባበሉን አዲስ ማለዳ ተመልክታለች።

ህወሓት እና ብልጽግና ፓርቲ ለመዋሀድ ተከታታይ ውይይትና ድርድር እያደረጉ ይገኛሉ የሚሉ ዘገባዎች መውጣታቸው ይታወሳል።

አዲስ ማለዳ ከህወሓት አጭር መረጃ እንደተመለከተችው "ህወሓት እና ብልጽግና መሰረታዊ የዓላማ እና የአስተሳሰብ ልዩነት ያላቸው ፓርቲዎች ናቸው" በማለት በይፋዊ ገጹ ሰፍሯል።

ይኹን እንጁ ልዩነቶቹ እንዳሉ ሆኖ ሁለቱ ፓርቲዎች ሊወያዩባቸው የሚገቡ ብዙ አጀንዳዎች በመኖራቸው ተከታታይ ውይይት ተጀምሯል ተብሏል።

"ከዚህ ባለፈ ግን ህወሓት ከብልጽግና ጋር ለመቀላቀል ንግግሮች ተጀምረዋል የሚለው መረጃ ሙሉ በሙሉ ከእውነት የራቀ ነው" ሲል ድርጅቱ ማስታወቁን አዲስ ማለዳ ተመልክታለች።

ሕወሓት ገዥውን ፓርቲ ብልፅግና ለመቀላቀል ተከታታይ ድርድሮች እያደረገ ነው በሚሉት ዘገባዎች የሕወሓት ሊቀ መንበር ደብረፅዮን ገብረሚካዔል በአዲስ አበባ ተገኝተው ይህን ድርድር መጀመራቸው እና ከሁለት ሳምንታት በኋላ የብልፅግና ምክትል ሊቀ መንበር አደም ፋራህ ወደ መቀሌ ተጉዘው ድርድሩን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

እነዚሁ ዘገባዎች በህወሓት ውስጥ ብልፅግናን መቀላቀል “ስህተት ነው" በሚሉ እና "ውህደቱ ለትግራይ ችግሮች መፍትሄ ለማምጣት ጠቀሜታ አለው" በሚሉት ሃሳቦች መከፋፈል መኖሩን የጠቆሙ ቢሆንም ህወሓት ጉዳዩን ሙሉ በሙሉ አስተባብሏል።

@Yenetube @Fikerassefa
⚽️ እድል SPORT


🎮 በጽሑፍ ቀጥታ የጨዋታ ስርጭት
🚨 የዝውውር ዜናዎች
📊 ስታትሰቲክስ
🧐 ትንተና

🔍 የእግር ኳሱ ዓለም እንዴት ሰነበተ? ማን ምርጥ ጨዋታን አሳለፈ? የላቀ የጨዋታ እቅድ ማን ይዞ ገባ?

📌 ለመሳሰሉ ጥያቄዎች መልስ የሚያገኙበት ቻናል

https://www.tg-me.com/edilsport
አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ በፀጥታ ሀይሎች ተያዘ

አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ በዛሬው እለት አመሻሹን ሚያዚያ 15ቀን 2016ዓ.ም ወደ እስራኤል ሊያቀና በነበረበት ወቅት ላይ በፀጥታ ሀይሎች መያዙን የአርቲስቱ የቅርብ ምንጮች ገልፀዋል።

ጉዳዩን አስመልክቶ የአርቲስቱ የቅርብ ወዳጅ በማህበራዊ ትስስር ገፁ "ያያ ዘልደታ" ጉዳዩን አስመልክቶ ተከታዩን አስፍሯል።

" ዛሬ ከመሽ ዕብደት በሕብረት የተሰኘውን አዲሱን ትያትር ለማሳየት ወደ ሃገረ እስራኤል ለመሄድ ዝግጅቱን ጨርሶ እነሆ አሁን ከመሸ ከኤርፖርት ተይዞ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ተወስዷል::" ሲል አስታውቋል።

እስከ አሁን ባለው ሂደት ከመንግስት አካላት ስለ ጉዳዩ የተሰጠ ምላሽም ሆነ ማብራሪያ የለም።

ዳጉ_ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa
2024/05/16 10:39:41
Back to Top
HTML Embed Code: