Telegram Web Link
የክርስቲያኖ ሮናልዶ ልጅ ለፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን እንዲጫወት ጥሪ ቀረበለት

የክርስቲያኖ ሮናልዶ ልጅ ክርስቲያኖ ጁኒየር በፖርቹጋል ከ15 ዓመት በታች አዳጊዎች ብሔራዊ ቡድን እንዲጫወት ለመጀመሪያ ጊዜ ተጠርቷል።

የሮናልዶ የበኩር ልጅ፣ የ14 ዓመቱ ክርስቲያኖ ጁኒየር በአሁኑ ሰዓት በሳዑዲ ዓረቢያ ለአል ናስር ክለብ አካዳሚ በመጫወት ላይ ይገኛል።

የፖርቹጋል ከ15 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በዚህ ወር በክሮሽያ በሚካሄደው የቭላትኮ ማሬኮቪች ዓለም አቀፍ ውድድር የሚሳተፍ ሲሆን በውድድሩ ከጃፓን፣ እንግሊዝ እና ግሪክ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍4884👎4👀3
“40 በመቶ የሚሆነው የትግራይ ግዛት በወራሪዎች ስር ነው የሚገኘው፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ዋነኛ ተልዕኮ የክልሉን የግዛት ወሰን ማረጋገጥ ነው” - ፕሬዝዳንት ታደሰ

“የትግራይ ክልል 40 በመቶ የሚሆነው ግዛት በወራሪዎች ቁጥጥር ስር ነው የሚገኘው” ሲሉ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ ገለጹ፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ዋነኛ ተልዕኮ የክልሉን የግዛት ወሰን ማረጋገጥ እና የተፈናቀሉትን ወደ ቀያቸው መመለስ ነው” ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ ይህንን የገለጹት በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር የሆኑትን ጄነስ ሃኒፈልድ ዛሬ ሚያዚያ 28 ቀን 2017 ዓ.ም በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው።

ፕሬዝደንት ታደሰ “40 በመቶ የሚሆነው የትግራይ ክልል ግዛት በወራሪዎች ቁጥጥር ስር ነው የሚገኘው፣ ከሁሉም ነገር በፊት እና ከምንም ነገር በላይ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ተልዕኮ በህገመንግስቱ የተከለለውን የክልሉን የግዛት ወሰን ማረጋገጥ እና የተፈናቀሉትን ወደ ቀያቸው መመለስ ነው” ሲሉ ለአምባሳደሩ መናገራቸውን ከጽህፈት ቤታቸው ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በተጨማሪም ፕሬዝዳንቱ ከአምባሳደሩ ጋር በነበራቸው ውይይት “የመጀመሪያው ዙር 75ሺ ታጣቂዎችን ወደ ማህበረሰቡ የመቀላቀል ተግባር እስከ መስከረም ይጠናቀቃል፣ ሁለተኛው ዙር ግን ከክልሉ ግዛት መከበር ጎን ለጎን የሚፈጸም ነው” ሲሉ መናገራቸውን ጽህፈት ቤታቸው አስታውቋል።

Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
👍16👎94😁3
YeneTube
Photo
አስገኘው አሽኮ ሴቶችን በተመለከተ በሰጠው  አስተያየት ላይ ከኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር የተሰጠ መግለጫ

እንደሚታወቀው በሀገራችን የሴቶችና የሴት ህፃናት ጥቃት ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ፣ አይነቱን እየቀያየረና በአፈፃፀሙም እየረቀቀ የመጣ እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ነው። ይህንንም ለመከላከል የተለያዩ የሚመለከታቸው አካላት እንዲሁም መላው የህብረተሰብ ክፍል የራሱን አስተዋፅዖ ማድረግ እንዳለበት እሙን ነው። አብዛኛው የማህበረሰብ ክፍል ጥቃት ምን ማለት እንደሆነ በቂ ግንዛቤ የሌለው ከመሆኑም በተጨማሪ በአንዳንድ ግለሰቦች የሚሰነዘሩ ሴቶችን የተመለከቱ አስተያየቶች ለጥቃት መባባስ ጉልህ ሚና አላቸው።

ከዚህ ጋር  ተያይዞ ሰሞኑን በአንድ ታዋቂ ግለሰብ ማለትም በድምፃዊ አስገኘው አሽኮ ሴቶችን በተመከተ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተደረገው ንግግር ሴቶች በአካላዊ፣ በኢኮኖሚያዊ እንዲሁም በጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች እየደረሰባቸው ካለው ጥቃት በተጨማሪ በጠቅላላው በመፈረጅ የስነልቦናዊ ጥቃት እንዲደርስባቸው ያደረገ እና ብዙ ሴቶችንም ያስቆጣ ተግባር ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ጉዳዩን ብዙ ሰዎች እንዲቀባበሉት እና የበለጠ ሴቶች ላይ እንዲዘባበቱ ያነሳሳም ጭምር ነው።

ድምፃዊው ከዚህ ቀደም "የሀገር ካስማ" በተሰኘው ሴቶችን ለማበረታታት ታልሞ በተሰራ ህብረዝማሬ ላይ በመሳተፍ የሴቶች አጋር መሆኑን በማሳየቱ እንደተቋም እውቅና ሰጥተን የነበረ ሲሆን አሁን ባደረገው ንግግር ግን ሴቶች ላይ የጥላቻ ዘመቻ እንዲከፈት በማድረጉ ማኅበራችን እጅግ ያዘነ መሆኑን ለመግለፅ ይወዳል።

ድምፃዊው በንግግሩ "በፍቅር ያበደች ሴት ካሳየኸኝ የማይሞት ሰው አሳይሀለው" በማለት ሴቶችን ሁሉ በአንድ በመፈረጅ በአጠቃላይ የሴቶችን ስብዕና የሚነካና ሴቶች በህገመንግስቱ የተሰጣቸውን ክብራቸው ተጠብቆ የመኖር  መብት የጣሰ አስተያየትን ሰጥቷል። ይህ ንግግሩም በሀገራችን የጥላቻ ንግግር እና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1185/2012 አንቀፅ 2(2)፣ 4 እና 7ን የጣሰ እና የወንጀል ተጠያቂነትን የሚያመጣ ተግባር ነው።

በመሆኑም ማኅበራችን ግለሰቡ በተገቢው መልኩ በህግ ተጠያቂ እንዲሆን የሚሰራ መሆኑን እየገለፅን የተፈፀመውን ድርጊት አጥብቀን እናወግዛለን። ዛሬ ላይ ያለተጠያቂነት የምትታለፍ አንዲት ጥላቻ ነገ ላይ በሴቶች ላይ ለሚፈፀም ከባድ ዘመቻ በር ከፋች በመሆኗ ይህንን ንግግር የምታሰራጩ የማህበራዊ ሚዲያዎችም ይህን ከማድረግ እንድትቆጠቡ እናሳስባለን።

በሴቶች ላይ የሚፈፀም ጥቃትን መከላከል የሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ሀላፊነት ነው።
በሴቶች ላይ የሚፈፀም የጥላቻ ንግግርን አጥብቀን እንቃወማለን!!

የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር  (ሚያዝያ  28 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ)
😁79👍42👎145
ብሄራዊ ባንክ በነገው ዕለት ሌላ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ እንደሚያካሂድ አስታውቋል።

ባንኩ ለነገው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ 60 ሚሊዮን ዶላር መመደቡን ገልጧል።

ባንኩበየሁለት ሳምንቱ መደበኛ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ማውጣት ከጀመረ ወዲህ፣ የነገው ጨረታ ሦስተኛው የውጭ ምንዛሬ ጨረታው ይኾናል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍23😭73
🚀 ትልቅ እድል በLinkedIn! 🚀

የLinkedIn መለያዎን ይከራዩ፡ በየሳምንቱ ተገብሮ ገቢ ያግኙ!

🔑 እንዴት?
LinkedIn መሆን አለበት። 1 አመት እና ከዚያ በላይ መለያው ይኖርበታል።

💰 የገንዘብ አማራጮች:

300+ ግንኙነቶች - 13$ በየሳምንቱ

500+ ግንኙነቶች - 15$ በየሳምንቱ

800+ ግንኙነቶች - 17$ በየሳምንቱ

1000+ ግንኙነቶች - 20$ በየሳምንቱ

2000+ ግንኙነቶች - 25$ በየሳምንቱ

👉 ፈጣን ክፍያ - በ24 ውስጥ ይክፈሉ።

🔔 መልካም ዕድል!

1 ዓመት ዕድሜ ወይም ከዚያ በላይ

300+ - 13$ በሳምንት

500+ - 15$ በሳምንት

800+ - 17$ በሳምንት

1000+ - 20$ በሳምንት

2000+ - 25$ በሳምንት

🚫 መግለጫ:
መለያዎን ሊከራዩ፣ መለያዎች ሳምንታዊ ገደቦች መድረስ የለበትም።

ይህ እውነት ነው

ምንም አደጋ የለም

ወንጀል የለም።

📱 ቴሌግራם: @rwslimiited
👍63😁3
YeneTube pinned a photo
በ490,000 ቅድመ ክፍያ  በመሀል ካዛንቺስ  የቤት ባለቤት ይሁኑ ‼️

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው አያት ካዛንቺስ መንደር

እጅግ ውብ ዕይታ ያላቸው ቤቶች

ከ 1 መኝታ እስከ ባለ 4 መኝታ
👉ባለ አንድ መኝታ 45, 55 ,60 ካ.ሜ
👉ባለ ሁለት መኝታ  80,ካ.ሜ
👉ባለ ሶስት መኝታ  95,105,115 ካ.ሜ
👉ባለ አራት መኝታ  140  ,160 ካ.ሜ

✍️ ቅድመ ክፍያ 10%
📹 (ከ490,000ብር ቅድመ ክፍያ  ጀምሮ)

❇️  በ 18 ወራት የሚረከቡት ቤት💁

      

       📍በግቢው ዙሪያ

   ➾ፓርኮች ና የወንዝ ዳር ልማት
    ➾አለማቀፍ ት/ቤትና ሆስፒታል
    ➾የእምነት ተቋማ

       📍የቤቶቹ እይታ

    ➤ ወደ ቤተ መንግስት ( ጊቢ ገብርኤል )
    ➤ ወደ ያካ ተራራ ጫካ
    ➤ ወደ ወንዝ ዳር ልማት
    ➤ ወደ ወዳጅነት ፓርክ

👉 ቀድሞ ለመጣ ቅድሚያ ይስተናገዳል

❇️  ከሀገር ውጭ ያላችሁ ደንበኞች በወኪል መግዛት እንደምትችሉ እናሳውቃለን ።

ለምዝገባ 📲 0950123353 ወይም
በ whatsapp :-https://wa.me/251950123353
አሁኑ ይደውሉ
👍21
ትራምፕ በፍቃደኝነት አሜሪካን ለቀው ለሚወጡ ህገ-ወጥ ስደተኞች የ1ሺ ዶላር ማበረታቻ አቀረቡ

የአሜሪካ መንግስት በህገ ወጥ መንገድ በሀገሪቱ ውስጥ የሚገኙ ስደተኞች አሜሪካን ለቀው ለመውጣት ከወሰኑ 1,000 የአሜሪካ ዶላር እንደሚሰጥ እና የጉዞ ክፍያቸውን እንደሚሸፍን አስታውቋል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ስለ ጉዳዩ ለጋዜጠኞች ሲያብራሩ ህገወጥ ስደተኞች የቀረበላቸውን አማራጭ የሚቀበሉ ከሆነ አንድ ቀን ወደ አሜሪካ የሚመለሱበት ህጋዊ መንገድ ሊሰጣቸው እንደሚችል ተናግረዋል።

እንዲሁም የአሜሪካ የሀገር ውስጥ ደህንነት ዲፓርትመንት (ዲ.ኤች.ኤስ) ፀሃፊ ክሪስቲ ኖም፤ ከአሜሪካ በራስ ፈቃድ መውጣት ከእስር ለመዳን፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ወጪ ቆጣቢው መንገድ ነው ብለዋል።

የሀገር ውስጥ ደህንነት ዲፓርትመንት አክሎም፤ እቅዱ የገንዘብ ወጪን እንደሚቀንስ እና እስካሁን ስደተኞችን ለመያዝ፣ ለማሰር እና ከሀገር ለማስወጣት በአማካይ ከ17,000 ዶላር በላይ ወጪ እንደተደረገ አስታውቋል።

ዲፓርትመንቱ አክሎም የመጀመሪያው ሕገወጥ ስደተኛ ከቺካጎ ወደ ሆንዱራስ ለመብረር አማራጩን እንደተቀበለ መግለፁን ቢቢሲ ዘግቧል።

@Yenetube @Fikerassefa
😁17👍162🔥1
🚀 ቡስትግራም: ተመልካቾች እና ፎሎወሮች ያግኙ።

📣🔥👀📹👍


📹የቲክቶክ : ቪዲዮዎችዎ ብዙ ቪውስ፣ ላይኮች፣ ፎሎወሮች እና ኮመንቶች ያግኙ።

📷የኢንስታግራም: ፎሎወሮች፣ ላይኮች፣ ቪውስ እና ኮመንቶች ያግኙ።

📹የዩቲዩብ: ሰብስክራይበሮች እና ቪዲዮ ቪውስ በፍጥነት ያግኙ።

✈️ቴሌግራም: ቻነል መምበሮች፣ ፖስት ቪውስ፣ ላይኮች እና ሪአክሽኖች ይጨምሩ።

ቡስትግራም - የሶሻል ሚዲያ ገፅታዎን መገንባት አሁን በጣም ቀላል ሆኗል!`

📹 📷 📹 ✈️

LINK - 🔗 👉 https://www.tg-me.com/boostgramPromoBot/boostgram 🕯📈
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍52🔥1
Asgegnew Ashko የጣሰው/የተላለፈው ህግ የለም!

የሴት ጠበቆች ማህበር ግን ሀገራችን ውስጥ በሴቶች ላይ በሚፈፀሙ አሰቃቂ ወንጀሎች ጉዳይ መግለጫ ሲያወጣ እና ሲታገል አይታችሁ ታውቃላችሁ?

ይህ ማህበር አስጌን እከሳለው ማለቱን ስሰማ ገረመኝ (እውነት ከሆነ)

የአስጌ የሰሞኑን በፍቅና ሴቶች ላይ የሰጠው ግላዊ አስተያየት ከኢትዮጵያ ህግጋቶች አንፃር የጥላቻ ንግግር እና የሀሰት መረጃ ስርጭትን ለመከላከል የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1185/2012 እና የኢትዮጵያ የወንጀል ህግን ጨምሮ የጣሰው ህግ የለም። አስጌ በምንም ሁኔታ ሊጠየቅ አይችልም!

አስጌ በሰጠው ግላዊ አስተያየት በአዋጅ ቁጥር 1185/2012 አንቀጽ 4(1) ላይ እንደተገለጸው የጥላቻ ንግግር በአንድ ሰው ወይም ቡድን ላይ እንደ ጾታ ባሉ የማንነት ጉዳዮች ላይ የተመሰረተ ጥላቻን፣ አድልዎ ወይም ጥቃትን ማነሳሳት ድርጊት አልፈፀመም።

ሆኖም ግን፣ አስጌ በፖስቱ ህገመንግስታዊ ሀሳብን የመግለፅ መብቱን በመጠቀም ሀሳቡን ገለፀ እንጂ ምንም አይነት ስድብ፣ ማንቋሸሽ እና ምንም አይነት ጎጂ እርምጃ አላነሳሳም፤ የጥላቻ ንግግርም አላደረገም።

ከዚህም በተጨማሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 613 ስድብ እና ስም ማጥፋትን ይወነጅላል። በዚህ ሁኔታ አንድም የተለየ ሰው ወይም ቡድን አልተሰደበም ወይም አልተዋረድም። ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት በህገ መንግስቱ አንቀጽ 29 እንደተጠበቀው ግለሰቦች በህግ ወሰን ውስጥ የግል አመለካከቶችን እንዲገልጹ ያስችላል።

So, እውነት ከሆነ ማህበሩ በእንዲህ ባለው ጉዳይ ጊዜውን ከሚያጠፋ በርካታ እህቶቻችን ላይ እየደረሱ ያሉ ግፍና ወንጀሎችን ለመከላከል ለእህቶቻችን ዘብ ይቁም።
ከዛም በዘለለ በየቲክቶኩ የሴቶችን ክብር የሚያዋርዱ እና የሚሳደቡ በዚህም እውቅና እያገኙ የሚገኙ ወጣቶች ላይ ይስራ!

በዳዊትካሳ
👍954👎3🔥1😁1
የሙያ ብቃት ምዘና ማረጋገጫ ያልያዘ አሽከርካሪ ማሽከርከር አይችልም- ሚኒስቴሩ

ከያዝነው ዓመት ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ የአሽከርካሪዎች የሙያ ብቃት ምዘና እንደሚጀመር የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የብቃት ምዘናውን መስጠት ያስፈለገው 83 በመቶ በሀገሪቱ እየደረሰ የሚገኘው የትራፊክ አደጋ ከአሽከርካሪዎች እና ተሽከርካሪዎች ጋር የሚያያዝ በመሆኑ ነው ተብሏል፡፡

ይህን ተከትሎም በዚህ ዓመት ምዘናው ሥራ ላይ ባሉ አሽከርካሪዎች እንደሚጀመር የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴዔታ አማካሪ አሰፋ ሀዲስ አረጋግጠዋል፡፡

በዚሁ መሠረት በሕዝብ እና ደረቅ ጭነት ከ1 እስከ 3 ባሉ ደረጃዎች እንዲሁም ለፈሳሽ 1 እና 2 አሽከርካሪዎች የሙያ ብቃት ምዘና እንደሚሰጥ አብራርተዋል፡፡

የሙያ ብቃት ምዘና ከመሰጠቱ በፊት ለአሽከርካሪዎቹ የሙያ ስልጠና እንደሚሰጥም አስታውቀዋል፡፡

ከስልጠናው በኋላ የሙያ ብቃት ምዘና (ሲኦሲ) እንደሚወስዱ እና ፈተናውን ያለፉት መንጃ ፈቃዳቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት እንደሚኖረው ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል የሙያ ብቃት ምዘና ፈተናውን ወስደው ያላለፉ አሽከርካሪዎች እንደገና ስልጠና ወስደው ድጋሚ ይፈተናሉ ብለዋል፡፡

የሙያ ብቃት ምዘና ማረጋገጫ ያልያዘ አሽከርካሪ ማሽከርከር እንደማይችልም ነው ያሳሰቡት፡፡

በቀጣይም የሙያ ብቃት ምዘናው ታክሲን ጨምሮ በሌሎቹም አሽከርካሪዎች ላይ እንደሚተገበር ጠቁመዋል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
👍31😁133👎1
መንግሥት ጤና ባለሙያዎች ለሚያነሷቸውን ጥያቄዎች አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥ የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማህበር ጠየቀ!

መንግሥት ጤና ባለሙያዎች የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች ችላ ከማለት ወጥቶ ጉዳዩ በሀገር ላይ ችግር ከማስከተሉ በፊት ለጥያቄዎቹ ተገቢውን ቦታ እና ምላሽ እንዲሰጥ የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማህበር ጠይቋል።ማህበሩ ወቅታዊ የጤና ባለሙያዎች ጉዳይ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ "ጤና ባለሙያዎች እያነሷቸው ያሉ ጥያቄዎች ተገቢ በመሆናቸው መንግሥት አስቸኳይ መፍትሔ ሊሰጥ ይገባል" ብሏል።

የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማህበር በተለያየ ጊዜ ጤና ባለሙያዎች የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች ሕጋዊ አግባብን ተከትሎ ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጤና ሚኒስቴርን ጨምሮ ለሀገሪቱ ከፍተኛ የመንግሥት መስርያ ቤቶች ማቅረቡን ገልጿል፡፡ነገር ግን ጤና ባለሙያዎቹ የሚያነሷቸው ጥያቄዎች በወቅቱ እና በተገቢ ሁኔታ ባለመመለሳቸው ጤና ባለሙያዎች አሁንም በተለያዩ መንገዶች መብታቸውን በመጠየቅ ላይ መሆናቸውን አስታውቋል።

በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ በርካታ አካባቢዎች የሚገኙና ከከፍተኛ የጤና ባለሙያ ስፔሻሊስቶች ጀምሮ ዶክተሮች፣ ነርሶች፣ እና የቀዶ ጥገና ባለሙያ የሆኑ የጤና ባለሙያዎች በተለያዩ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴ መተግበሪያዎች፤ "ሕይወትን ስናድን ኖረናል አሁን ግን የራሳችንን ሕይወት ማዳን ይኖርብናል" በሚል መፈክር እያሰሙ መሆኑ ይታወቃል፡፡በዚህም የጤና ባለሙያዎቹ የደመወዝ እና ሌሎች የጥቅማጥቅም ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጣቸው በሚሰሩበት ሆስፒታል/ጤና ተቋም ላይ የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ ጥያቄያቸውን በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።

ከመፈክሮቻቸው መካከልም "እርካታ የቤት ኪራይ አይሆንም"፣ "እርካታ ዳቦ አይሆንም"፣ "ላልተኖረው ልጅነታችን ስንል እስከጥግ እንሄዳለን" "ዝምታ ይበቃል! ችግሮቻችንን ስሙ"፣ "እስካሁን የሌሎችን ሕይወት ስናድን ኖረናል አሁን ግን የራሳችን ሕይወት ማዳን ይኖርብናል"፣ "አስቸኳይ መፍትሄ እንሻለን" እንዲሁም "አሁን ወይም መቼም" የሚሉ ይገኙበታል፡፡

የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማህበር ጉዳዩን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫም፤ ጤና ባለሙያዎች መብታቸዉን ለማስከበር የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ እንደሚደግፍና እውቅና እንደሚሰጥ የገለጸ ሲሆን፤ ጥያቄው ግን ሀገርን እና ማህበረሰብን በማይጎዳ መልኩ መሆን እንዳለበት አሳስቧል።መንግሥትም ለሚያነሱ ጥያቄዎች ተገቢውን ቦታ በመስጠት አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥ ጠይቋል።

Via Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa
👍543
ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ባካሄደው ጨረታ አንድ የአሜሪካ ዶላር በአማካኝ በ132 ብር ተሸጠ!

በጨረታው ለተሳኩ ሁሉም የዋጋ ጥያቄዎች የተመዘነ አማካይ ዋጋ በአንድ የአሜሪካ ዶላር 132.9643 ብር ደርሷል። በአጠቃላይ 16 ባንኮች በጨረታው የጠየቁትን የውጭ ምንዛሬ ድልድል ማግኘት ችለዋል።

ባንኩ ከ15 ቀናት በፊት ባካሄደው ተመሳሳይ ጨረታ አንድ የአሜሪካ ዶላር በአማካኝ በ131.70 ብር መሸጡ ይታወሳል።

ብሔራዊ ባንክ በየ15 ቀናት የውጭ ምንዛሬ በጨረታ መሸጡን እንደሚቀጥል የገለጸ ሲሆን፣ ለዛሬው ጨረታ 50 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለባንኮች እንዲገዙ ቀርቦ ነበር። ቀጣዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ከሁለት ሳምንታት በኋላ የሚካሄድ ሲሆን ዝርዝር መረጃዎች ከጨረታው ቀን በፊት ይፋ ይደረጋሉ።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
👍19👎5
ኤርሚያስ አመልጋን ጨምሮ ህገወጥ የገንዘብ ማሰባሰብ ላይ ምርመራ ተጀመረ - የካፒታል ገበያ ባለስልጣን

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ታዋቂውን ስራ ፈጣሪ አቶ ኤርሚያስ አመልጋን እና "ጀነሲስ ኢንቨስትመንት ሰርቪስ" የተባለ ኩባንያን ጨምሮ ህገወጥ በሆነ መንገድ ሰነደ መዋዕለ ንዋዮችን ለህዝብ በመሸጥ ገንዘብ ሲያሰባስቡ በነበሩ ግለሰቦችና ድርጅቶች ላይ የቀረቡ ቅሬታዎችን ተቀብሎ ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል።

ባለስልጣኑ በሰጠው መግለጫ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ግለሰቦችና ድርጅቶች ላይ ህገወጥ የሰነድ ሽያጭን በመጠቀም ከህዝብ ገንዘብ በማሰባሰብ ተግባር ላይ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን ገልጿል።

በተለይም በአቶ ኤርሚያስ አመልጋ እና በ"ጀነሲስ ኢንቨስትመንት ሰርቪስ" ኩባንያ ላይ እየተካሄዱ ያሉት ምርመራዎች በህገ መንግስት የተረጋገጠ የመሰማት እና የመከላከል ሙሉ መብታቸው በተጠበቀ ሁኔታ እንደሚከናወኑ ባለስልጣኑ አረጋግጧል።

በተጨማሪም ባለስልጣኑ ህብረተሰቡ ከካፒታል ገበያ ጋር በተያያዙ እንቅስቃሴዎች ላይ ሲሳተፍ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል።

በተለይም በንግድ ድርጅቶች ምስረታ ላይ ሲሳተፉ የንግድ ምዝገባ እና ምስረታ ሰነዶችን ከሚመለከተው አካል እንዲያረጋግጡ እንዲሁም ገንዘብ ከመክፈላቸው በፊት በባለስልጣኑ ፈቃድ ከተሰጣቸው የኢንቨስትመንት አማካሪዎች ብቻ ምክር እንዲፈልጉ ጠቁሟል።

ባለስልጣኑ ፈቃድ ሳይኖራቸው የካፒታል ገበያ አገልግሎት የሚሰጡ ወይም ለማቅረብ የሚሞክሩ አካላት ካሉ ለባለስልጣኑ ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን፣ በእንደዚህ አይነት ህገ-ወጥ ድርጊቶች ላይ ተገቢውን እርምጃ እንደሚወስድ አረጋግጧል።
Via Capital Newspaper
👍31😁106👀6👎3
Forwarded from YeneTube
በ490,000 ቅድመ ክፍያ  በመሀል ካዛንቺስ  የቤት ባለቤት ይሁኑ ‼️

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው አያት ካዛንቺስ መንደር

እጅግ ውብ ዕይታ ያላቸው ቤቶች

ከ 1 መኝታ እስከ ባለ 4 መኝታ
👉ባለ አንድ መኝታ 45, 55 ,60 ካ.ሜ
👉ባለ ሁለት መኝታ  80,ካ.ሜ
👉ባለ ሶስት መኝታ  95,105,115 ካ.ሜ
👉ባለ አራት መኝታ  140  ,160 ካ.ሜ

✍️ ቅድመ ክፍያ 10%
📹 (ከ490,000ብር ቅድመ ክፍያ  ጀምሮ)

❇️  በ 18 ወራት የሚረከቡት ቤት💁

      

       📍በግቢው ዙሪያ

   ➾ፓርኮች ና የወንዝ ዳር ልማት
    ➾አለማቀፍ ት/ቤትና ሆስፒታል
    ➾የእምነት ተቋማ

       📍የቤቶቹ እይታ

    ➤ ወደ ቤተ መንግስት ( ጊቢ ገብርኤል )
    ➤ ወደ ያካ ተራራ ጫካ
    ➤ ወደ ወንዝ ዳር ልማት
    ➤ ወደ ወዳጅነት ፓርክ

👉 ቀድሞ ለመጣ ቅድሚያ ይስተናገዳል

❇️  ከሀገር ውጭ ያላችሁ ደንበኞች በወኪል መግዛት እንደምትችሉ እናሳውቃለን ።

ለምዝገባ 📲 0950123353 ወይም
በ whatsapp :-https://wa.me/251950123353
አሁኑ ይደውሉ
👍6
ያለ ረዳት የሚያሽከረክሩ የከተማ ታክሲ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገለጸ!

በአዲስ አበባ ከተማ በብዛት የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡት "ሚኒባስ" ታክሲዎች ያለ ረዳት መንቀሰቀሳቸው ሕገ-ወጥ እንደሆነ እና ደንቡን ተላልፈው በተገኙ አሽከርካሪዎች ላይ የቅጣት እርምጃ እንደሚወሰድ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

በከተማዋ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያለረዳት የሚያሽከረክሩ የከተማ ታክሲዎችን ቁጥር መጨመር አስመልክቶ አሐዱ ያነጋገራቸው ተሳፋሪዎች ባሰሙት ቅሬታ፤ "አሽከርካሪዎች እያሽከረከሩ አገልግሎት የሰጡበትን ሒሳብ በሚቀበሉበት ጊዜ አደጋ ሊያደርሱ የሚችሉበት ዕድል ከፍተኛ በመሆኑ ሊታሰብበት ይገባል" ብለዋል።

"ማሽከርከር ሙሉ ትኩረትን የሚፈልግ ነው!" ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ፤ "አሽከርካሪዎቹ የረዳትን ሥራ ደርበው ለመስራት በሚያደርጉት ጥረት ከፍተኛ ስጋት የሚፈጥር በመሆኑ ሊታረም ይገባል" ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።    

አሐዱ የቀረበውን የተገልጋዮች ቅሬታ ይዞ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ጠይቋል።በኮሚሽኑ የትራፊክ አደጋ ምርመራ የግድያና አደጋዎች መርማሪ ኢንስፔክተር ተመስገን ደሳለኝ በሰጡት ምላሽ፤ "የከተማ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አሽከርካሪዎች ያለ ረዳት ማሽከርከራቸው በሕግ የተከለከለ ነው" ብለዋል።

"መሰል ድርጊቶች ለመንገድ ላይ አደጋዎች መፈጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አላቸው" ያሉት ኢንስፔተክተር ተመስገን፤ አሽከርካሪዎች ሙሉ ትኩረታቸውን በማሽከርከር ሥራቸው ላይ አለማድረጋቸው የመንገድ ላይ ክስተቶችን ለመቆጣጠር እንዳይችሉ እና አደጋ እንዲፈጠር የሚያደርግ በመሆኑ የተከለከለ መሆኑን ተናግረዋል።

"ይህንን ደምብ ተላልፈው በተገኙ አሽከርካሪዎች ላይም ቅጣት ይጣላል" ሲሉ አሳስበዋል።መርማሪው፤ አሽከርካሪዎች የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ከመሰል ድርጊት መቆጠብ እንዳለባቸው በማሳሰብ፤ ነዋሪዎችም መሰል የደንብ ጥሰቶች በሚያጋጥሙበት ወቅት ለቁጥጥር ባለሞያዎች ጥቆማ በመሰጠት እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርበዋል።

Via Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa
👍49👎3👀1
በፀጥታ ችግር ምክንያት የነዳጅ አቅርቦት እጥረት መከሰቱን የአማራ ክልል ንግድ ቢሮ ገለፀ።

በክልሉ በባለፉት ሁለት ወዲህ እየተፈጠረ ያለዉ አለመረጋጋት ለእጥረቱ መከሰት እንደምክንያት ተቀምጧል።በአማራ ክልል ንግድና ገቢያ ልማት ቢሮ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ታፈረ ይመር ለጣቢያችን እንዳሉት በባለፉት ሁለት አመታት በክልሉ ተፈጥሮ በነበረዉ ግጭት ምክንያት መንገድ ላይ ያለዉ የፀጥታ ችግር መግጠሙን ተናግረዋል።

ቦቴዎች በነፃነት ነዳጅ ጭነዉ ለመግባትና ለመዉጣት ግዴታ በመንግስት አካል ካልታጀቡ ሹፌሮች እንደሚገደሉና እንደሚታገዱ የገለፁት አቶ ታፈረ ይህም አቅርቦቱ ላይ ተፅእኖ እያሳደረ እንደሆነ ገልፅዋል።

አሁን ላይ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ከፌደራል ነዳጅና ንግድና ቀጣናዊ ጋር በመነጋገር ያለዉን አቅርቦት በሁሉም አካባቢዎች ለማድረስ እየተሰራ እንደሚገኝና ይህ ሲባል ግን ችግሩ ሙሉ ለሙሉ አለመቀረፉን ተናግረዋል።ምርቶችን ቸርቻሪዎች ለህብረተሰቡ በተገቢዉ ሁኔታ ባለማድረሳቸዉና ምርቱን ከመጠቅም ይልቅ በጥቁር ገቢያ የመሸጥ ሁኔታዎች ስላሉ ክትትል በማድረግ ምርትን በመዉረስ ለመንግስት ገቢ እየሆነ እንዳለ ገልፅዋል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
👍154😁1
🚀 ትልቅ እድል በLinkedIn! 🚀

የLinkedIn መለያዎን ይከራዩ፡ በየሳምንቱ ተገብሮ ገቢ ያግኙ!

🔑 እንዴት?
LinkedIn መሆን አለበት። 1 አመት እና ከዚያ በላይ መለያው ይኖርበታል።

💰 የገንዘብ አማራጮች:

300+ ግንኙነቶች - 13$ በየሳምንቱ

500+ ግንኙነቶች - 15$ በየሳምንቱ

800+ ግንኙነቶች - 17$ በየሳምንቱ

1000+ ግንኙነቶች - 20$ በየሳምንቱ

2000+ ግንኙነቶች - 25$ በየሳምንቱ

👉 ፈጣን ክፍያ - በ24 ውስጥ ይክፈሉ።

🔔 መልካም ዕድል!

1 ዓመት ዕድሜ ወይም ከዚያ በላይ

300+ - 13$ በሳምንት

500+ - 15$ በሳምንት

800+ - 17$ በሳምንት

1000+ - 20$ በሳምንት

2000+ - 25$ በሳምንት

🚫 መግለጫ:
መለያዎን ሊከራዩ፣ መለያዎች ሳምንታዊ ገደቦች መድረስ የለበትም።

ይህ እውነት ነው

ምንም አደጋ የለም

ወንጀል የለም።

📱 ቴሌግራם: @rwslimiited
👍6👎6
የዲኤችኤል #DHL ኢትዮጵያ ሰራተኞች ዛሬ የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸው ተሰማ፡፡

የሰራተኛ ማህበር በማቋቋማችን ከአስተዳደሩ ጋር አለመግባባት ተፈጥሮ ቆይቷል ያሉት ሰራተኞቹ አሁን ያለውን የኑሮ ውድነት ለመቋቋም የሚያስችል የደሞዝ ጭማሪም ተከልክለናል ይላሉ፡፡

ጉዳዩን በመሀል ሲያሸማግል የቆየው የትራንስፖርትና መገናኛ ሰራተኛ ማህበር ፌዴሬሽን ጉዳዩን ለአለም አቀፍ የትራንስፖርት ፌዴሬሽን አሳውቂያለሁ ብሏል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
👍12😁3
2025/07/12 15:43:53
Back to Top
HTML Embed Code: