Telegram Web Link
የኢትዮጵያ የጨርቃ ጨርቅ ዘርፍ በፖሊሲ ክፍተትና በዝቅተኛ ደመወዝ እጦት እየተፈተነ ይገኛል ተባለ!

የኢትዮጵያ የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ዘርፍ ዕድገት በወሳኝ የፖሊሲ ጉድለቶችና በዝቅተኛ ደመወዝ ባለመኖሩ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ መውደቁ ተገለጸ።

በዘርፉ እየተባባሰ የመጣው የሰለጠነ የሰው ኃይል እጥረትና መንግስት ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረውን ዝቅተኛ ደመወዝ ተግባራዊ ለማድረግ የዘገየበት ሁኔታ በዋነኛነት ተጠቅሷል።

የኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ባለሙያዎች ማህበር ስራ አስፈፃሚ አባል ዶ/ር ቶሌራ አደሬ እንዳሉት በቅርቡ የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው ወደ ዘርፉ የሚገባው የሰለጠነ የሰው ኃይል ቁጥር በእጅጉ ቀንሷል።

ጥናቱ ይህ ማሽቆልቆል የሙያው ክብር በመሸርሸሩና አሰሪዎች አነስተኛ ክህሎት ያላቸውን ሰራተኞች በዝቅተኛ ዋጋ የመቅጠር አዝማሚያ በመኖሩ እንደሆነ አመልክቷል።

ይህ አካሄድ የሰለጠነ የሰው ኃይልን ከማደናቀፉም በላይ ዘላቂ እድገትና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል።

Vua Capital
@YeneTube @FikerAssefa
👍23
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ፣ ዛሬ ከቀትር በኋላ ከእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጌዲዮን ሳር ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውን አስታውቀዋል።

ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጌዲዮን ሳር በኢትዮጵያ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ የገቡት በዛሬው ዕለት ነበር።ውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ አዲስ አበባ የገቡት፣ በግብርና፣ ውሃ፣ ታዳሽ ኃይል፣ ጤና እና በአየር ንብረት ቴክኖሎጂ ዙሪያ የተሠማሩ የእስራኤል ኩባንያዎች ሃላፊዎችን አስከትለው እንደሆነ የእስራኤል የዜና ምንጮች ዘግበዋል። የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ፣ ባለፈው መጋቢት በቴላቪቭ ይፋዊ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት፣ ከእስራኤሉ አቻቸው ጌዲዮን ሳር ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸው አይዘነጋም።

@YeneTube @FikerAssefa
👎54👍3016🔥1😁1
ወ/ሮ ሰሃረላ አብዱላሂ ዳግም የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ተሾሙ።

ወ/ሮ ሰሃረላ ከሚያዝያ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው መሾማቸውን የጤና ሚኒስቴር አሳውቋል።

ከዚህ ቀደም በተለይም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት በጤና ሚኒስትር ደኤታነት እንዳገለገሉ የሚዘነጋ አይደለም።

አሁን ወደ ጤና ሚኒስቴር እስከተመለሱበት ጊዜ ድረስ የነዳጅና ኢነርጅ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲያገለግሉ ነበር።

@YeneTube @FikerAssefa
👍56👎13😁11
Forwarded from YeneTube
⭐️ ⭐️ እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤዉ በሰላም አደረሳችሁ።  ⭐️ ⭐️

የበዓል ስጦታ በማይታመን ዋጋ!!!

📍 ሳር ቤት ላይ አፖርትመንቶችን

በካሬ 64,200 ብር ብቻ

ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ታላቅ ቅናሽ

ባለ 2 እና ባለ 3 መኝታ አፖርትመንቶችን

ለመኖሪያ ምቹ እንዲሁም ለኢንቨስትመንት አዋጭ!!!

ታድያ ይህ እድል እንዳያመልጥዎ
ፈጥነዉ ይደዉሉ!!!

+251 950 05 56 55

ወይም በቴሌግራም

TG  @Davehomes

What’s up https://wa.me/message/KGIM2YTYQGNYO1
👍83
በ490,000 ቅድመ ክፍያ  በመሀል ካዛንቺስ  የቤት ባለቤት ይሁኑ ‼️

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው አያት ካዛንቺስ መንደር

እጅግ ውብ ዕይታ ያላቸው ቤቶች

ከ 1 መኝታ እስከ ባለ 4 መኝታ
👉ባለ አንድ መኝታ 45, 55 ,60 ካ.ሜ
👉ባለ ሁለት መኝታ  80,ካ.ሜ
👉ባለ ሶስት መኝታ  95,105,115 ካ.ሜ
👉ባለ አራት መኝታ  140  ,160 ካ.ሜ

✍️ ቅድመ ክፍያ 10%
📹 (ከ490,000ብር ቅድመ ክፍያ  ጀምሮ)

❇️  በ 18 ወራት የሚረከቡት ቤት💁

      

       📍በግቢው ዙሪያ

   ➾ፓርኮች ና የወንዝ ዳር ልማት
    ➾አለማቀፍ ት/ቤትና ሆስፒታል
    ➾የእምነት ተቋማ

       📍የቤቶቹ እይታ

    ➤ ወደ ቤተ መንግስት ( ጊቢ ገብርኤል )
    ➤ ወደ ያካ ተራራ ጫካ
    ➤ ወደ ወንዝ ዳር ልማት
    ➤ ወደ ወዳጅነት ፓርክ

👉 ቀድሞ ለመጣ ቅድሚያ ይስተናገዳል

❇️  ከሀገር ውጭ ያላችሁ ደንበኞች በወኪል መግዛት እንደምትችሉ እናሳውቃለን ።

ለምዝገባ 📲 0950123353 ወይም
በ whatsapp :-https://wa.me/251950123353
አሁኑ ይደውሉ
👍201
የትግራይ ልማት ማህበር ጉባኤ በውዝግብ ሲቋረጥ ምርጫው እንደገና እንዲካሄድ ታዘዘ!

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን በትግራይ ልማት ማህበር (ትልማ) በቅርቡ በመቀሌ ከተማ ያካሄደው 12ኛ ጠቅላላ ጉባኤ በከፍተኛ የአፈጻጸም ችግሮች ምክንያት መጠናቀቁን አስታወቀ።

በተለይም የሥራ አመራር ቦርድ አመራሮችን ለመምረጥ በተደረገው ሂደት ላይ በተፈጠረው አለመግባባት ጉባኤው ያለ ስምምነት በመቋረጡ ባለሥልጣኑ አዲስ ምርጫ እንዲካሄድ አዟል።

ባለሥልጣኑ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው፣ ጉባኤው ከመጀመሪያው ጀምሮ ተሳታፊዎችን በመምረጥ ረገድ ጉልህ የሆኑ ችግሮች የታዩበት ሲሆን ይህ ጉዳይ ለትልማ አመራሮች በተደጋጋሚ ቢገለጽም ጉባኤው በዚሁ ችግር ቀጥሏል።የጉባኤው የመጨረሻ አጀንዳ የነበረው የሥራ አመራር ቦርድ ምርጫ ላይ ተሳታፊዎች መካከል መግባባት ሳይፈጠር በመቅረቱ ጉባኤው ያለ ስምምነት የተቋረጠ ሲሆን የተወሰኑ ተሳታፊዎችም ጉባኤውን ጥለው መውጣታቸው ካፒታል ከመግለጫው ተመልክቷል።

ባለሥልጣኑ ይህ ሁኔታ ማህበሩን ወደ መከፋፈል ሊያመራና ለህብረተሰቡ የሚሰጠውን ጥቅም ሊያስተጓጉል እንደሚችል በመገንዘብ የሥራ አመራር ቦርድ ምርጫው በአስቸኳይ እንዲስተካከልና አስፈላጊ የሆኑ እርማቶች እንዲደረጉ ባለስልጣኑ አሳስቧል።ይህን ተከትሎ ከዚህ ቀደም በተካሄደው ምርጫ ጋር ተያይዘው የሚከናወኑ ማናቸውም ተግባራት በባለሥልጣኑ ዘንድ እውቅና እንደሌላቸው በግልጽ አስታውቋል።

ባለስልጣኑ:- የትልማ 12ኛ ጠቅላላ ጉባኤ የስራ አመራር ቦርድ ምርጫ በህግ ፊት እውቅና እንደሌለውና ተቀባይነት እንደሌለው አጽንኦት ሰጥቷል። ከዚህ የቦርድ ምርጫ ጋር ተያይዘው የሚከናወኑ ማንኛውም ተግባራት፣ የፋይናንስ እንቅስቃሴዎችና ሌሎች ውሳኔዎች በህግ የሚያስጠይቁ እንደሚሆኑም በጥብቅ አስጠንቅቋል።

-Capital
@YeneTube
👍12😁43
Skype ተዘጋ

ከሁለት አስር አመታት በላይ በቪዲዮ ኮሙኒኬሽን ዘርፉ ያገለገለው Skype ከትናንት ጀምሮ በ Microsoft መዘጋቱ ተሰምቷል።
Skype በወር ከ300 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች ነበሩት።

በዚህም ሁሉም የግለሰብ Skype አካውንቶች ከ December 2025 በኋላ delete ይደረጋሉ። እስከዛ ድረስ ሰዎች መረጃቸውን/
e.g.chat history.data.etc/ ማውጣት ይችለሉ።
👍13😭21
#ጅማ ዞን በድረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ

#ኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን ሸቤ ሶምቦ ወረዳ ሚርጋኖ በሶ ቀበሌ ባሳለፍነው ሳምንት መገባደጃ በጣለው ከባድ ዝናብ በድረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ።

አደጋው እሁድ ሚያዚያ 26 ቀን 2017 በሚርጋኖ ባሶ ቀበሌ ልዩ ስሙ ገሬ ኦጎደማ በተባለ ቦታ ላይ ለሌት 6 ሰዓት በጣለው ዝናብ መከሰቱን የሸቤ ሶምቦ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

ከባድ ዝናብ እና ኃይለኛ ንፋስ በቀላቀለ ዝናብ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን እና በተለያዩ ንብረቶች ላይ ጉዳት መድረሱን የሸቤ ሶምቦ ቡሳ ጎኖፋ ጽህፈት ቤቱ አክሎ ገልጿል።

የወረዳው ቡሳ ጎኖፋ ጽህፈት ቤት ኃላፊ፤ ዩሱፍ አባ ማጫ እና የሚርጋኖ በሶ ቀበሌ የብልጽግና ፓርቲ ኃላፊ ምስጋና ለታ ተጎጂዎችን በመጎብኘት ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ገልጸዋል ተብሏል።

ባሳለፍነው አመት ሀምሌ 15 ቀን በ #ደቡብ_ኢትዮጵያ ክልል #ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ ከ250 በላይ ሰዎች ህይወት መለፉም አይዘነጋም።

በተመሳሳይ ወቅት በ #ሲዳማ ክልል በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን በተከሰተ የመሬት መንሸራተት የ 11 ሰዎች ህይወት አልፏል።

በ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ቤንች ሽኮ ዞንም የአራት ሶዎች ህይወት በመሬት መንሸራተት አደጋ ማለፉም ይታወሳል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍12😭64
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፍ ስብሰባዎች ምቹ ነች- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፍ ስብሰባዎች ምቹ ነች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዲፕሎማሲያዊ ማዕከል እንደመሆኗ በአህጉራዊ ጉዳዮች ግንባር ቀደም ናት ያሉ ሲሆን፤ በዚህም ልዩ የሆነ የንግድ ሥራ ዕድል እና የባሕል ብልጽግናን የምትሰጥ ሀገር መሆኗን ጠቅሰዋል።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በብዙ ትጋት እዚህ የደረሰው የአውሮፕላን ማረፊያ የሚያበረታታ ስለመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

ዘመናዊ የመሰብሰቢያ ቦታዎች፣ ጥራታቸውን የጠበቁ ማረፊያዎች እና በፍጥነት በማደግ ላይ ያሉ መሠረተ ልማቶች ያሏት ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፍ ስብሰባዎች ምቹ መሆኗን ነው የገለጹት።

ደማቅ የሆነ ባሕል፣ የተለያዩ የምግብ አማራጮች፣ ሙዚቃዎች እና አስደማሚ የተፈጥሮ ውበት ባሉባት ሀገር የዓለም አቀፍ ስብሰባዎች፣ ኮንፈረንሶች እና ኤግዚቢሽኖች (MICE) በሚካሄዱባት መድረሻዎን ያድርጉ ሲሉ ጋብዘዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
😁33👍186👎3👀1
በብርቱካን ተመስገን ጉዳይ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የነበሩት ተጠርጣሪ የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ሰራተኞች በዋስ እንዲለቀቁ ተወሰነ

በሽብር ወንጀል ጉዳይ ተጠረጥረው በእስር ላይ የሚገኙ አራት የኢቤኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሰራተኞች፤ ዋስትና በማስያዝ እንዲለቀቁ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ።

ሁለት የጣቢያው ሰራተኞችን ጨምሮ 16 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ መመስረቱን የፌደራል ዐቃቤ ህግ ለፍርድ ቤት አስታውቋል።

Via ኢትዮጵያ ኢንሳይደር
@Yenetube @Fikerassefa
👍14👎3
ህወሓት አደራዳሪዎች “ትጥቅ ፍቱ ከማለት ውጭ ስምምነቱ በጥቅል እንዲፈጸም ያሳዩት ዝግጁነት ውስን ነው” ሲል ተቸ!

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የፕሪቶርያ ስምምነት “አደራዳሪዎች ትጥቅ ፍቱ ከማለት ውጭ ስምምነቱ በፓኬጅ [በጥቅል] እንዲፈጸም ያሳዩት ዝግጁነት ውስን ነው” ሲል ተቸ።

"ብሔራዊ አንድነታችን ሉዓላዊነታችን ለማስጠበቅ" በሚል መሪ ቃል የፓርቲው 1337 የሚሆኑ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ተሳትፈውበታል በተባለው እና ከሚያዚያ 23 እሰከ 25 ቀን 2017 ዓ.ም በተካሄደው ስብሰባ ማገባደጃ ባለ 10 የአቋም መግለጫ አውጥቷል።

አቋሙን ካንጸባረቀባቸው ጉዳዮች አንዱ የፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት አንዱ ሲሆን፤ “ሙሉ በሙሉ አልተተገበረም” ሲል በመግለጽ ላለመተግበሩም ሶስት ምክንያቶችን አስቀምጧል።

በአቶ ጌታቸው ረዳ የተመራውን የጊዜያዊ አስተዳደሩን “ተቆጣጥሮት የነበረው የፓርቲው አንዱ ቡድንን” በመጀመሪያ ምክንያትነት ያስቀመጠው መግለጫው በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ የኢትዮጵያ መንግስት በኩል ስምምነቱን ለማስፈጸም “ቁርጠኛ አለመሆኑ ነው” ሲል ገልጿል።

ሌላኛው በአቋም መግለጫው የተካተተው ነጥብ ደግሞ የፓርቲው እውቅናን የተመለከተ ሲሆን “እውቅናየ የሚወሰነው በትግራይ ህዝብ ነው ብየ ነው የማምነው” ሲል ገልጿል። በፕሪቶርያው ስምምነት መሰረት ህጋዊ ሰውነቱ ወደ ነበረበት እንዲመለስም ጥሪ አቅርቧል።

Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
👍26😁8👎4
ኢትዮጵያ እና ኢራን በመረጃ ልውወጥ ዘርፍ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከኢራን ፖሊስ ጋር በጋራና በትብብር መስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ዛሬ ሚያዚያ 28 ቀን 2017 ዓ/ም የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ።

እንደ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ መረጃ፤ ሁለቱ የፖሊስ ተቋማት የመረጃ ልውወጥ ለማድረግ፣ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ እና በትብብር ለመከላከል፣ በልምድ ልውውጥ እና በአቅም ግንባታ ሥራዎች ላይ በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

የመግባቢያ ሰነዱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል እና የኢራን የሕግ አስከባሪ ኃይሎች ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል አህመድ ረዛ ራዳን ናቸው። የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በመረጃው፤ መግባቢያ ሰነዱ በስምምነቱ መሠረት በየጊዜው ክትትል እየተደረገ ተግባራዊ እንደሚሆን አስታውቋል።

በመጋቢት ወር የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል፤ ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የዱባይ ፖሊስ የምርመራ ቡድን ኃላፊ ሌ/ኮለኔል አብደላ መሃመድ ጋር በአዲስ አበባ በወንጀል ምርመራ ዙሪያ መወያየታቸው ይታወሳል።

በሁለቱም ሀገራት ተፈላጊ የሆኑ ተጠርጣሪዎችን አሳልፎ በመስጠት በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ ስለሚቻልበት ሁኔታም መወያየታቸውንም የፌደራል ፖሊስ በወቅቱ አስታውቋል።

@Yenetube @FikerAssefa
👍37😁19👎32🔥1👀1
በጀርመን መራኄ መንግስትነት ይመርጣሉ ተብለው የሚጠበቁት ፍሪድሬሽ ሜርስ በመጀመሪያው ዙር ምርጫ አብላጫ ድምጽ ሳያገኙ ቀሩ።

ሜርስ ዛሬ በሀገሪቱ ምክር ቤት ተመርጠው ሥልጣን ይረከባሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር።ይሁንና ዛሬ ጠዋት የጀርመን የህዝብ እንደራሴዎች በሰጡት ድምጽ እርሳቸው መራኄ መንግሥት እንዲሆኑ የመረጡት 310 የምክር ቤት አባላት ብቻ በመሆናቸው ሜርስ መራኄ መንግስት ለመሆን የሚያስፈልጋቸው 6 የምክርቤት አባላት ድምጽ ጎድሏቸዋል።በዚህም ምክንያት የምክር ቤቱ ስብሰባ ተቋርጧል።

ሜርስ መራኄ መንግሥት ለመሆን ከ630 የጀርመን ምክር ቤት አባላት ቢያንስ የ316ቱን ድምጽ ማግኘት አለባቸው።ምክር ቤቱ ሜርስ ከዛሬ ጀምሮ የጀርመንን መንግሥት እንዲመሩ ከመረጠ ሥልጣኑን ከተሰናባቹ ኦላፍ ሾልስ ይረከባሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር። የሶሻል ዴሞክራት ፓርቲ አባል የሆኑት ሾልስ ላለፉት ሦስት ዓመታት ገደማ በመራኄ መንግሥትነት አገልግለዋል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
👍163
🚀 ትልቅ እድል በLinkedIn! 🚀

የLinkedIn መለያዎን ይከራዩ፡ በየሳምንቱ ተገብሮ ገቢ ያግኙ!

🔑 እንዴት?
LinkedIn መሆን አለበት። 1 አመት እና ከዚያ በላይ መለያው ይኖርበታል።

💰 የገንዘብ አማራጮች:

300+ ግንኙነቶች - 13$ በየሳምንቱ

500+ ግንኙነቶች - 15$ በየሳምንቱ

800+ ግንኙነቶች - 17$ በየሳምንቱ

1000+ ግንኙነቶች - 20$ በየሳምንቱ

2000+ ግንኙነቶች - 25$ በየሳምንቱ

👉 ፈጣን ክፍያ - በ24 ውስጥ ይክፈሉ።

🔔 መልካም ዕድል!

1 ዓመት ዕድሜ ወይም ከዚያ በላይ

300+ - 13$ በሳምንት

500+ - 15$ በሳምንት

800+ - 17$ በሳምንት

1000+ - 20$ በሳምንት

2000+ - 25$ በሳምንት

🚫 መግለጫ:
መለያዎን ሊከራዩ፣ መለያዎች ሳምንታዊ ገደቦች መድረስ የለበትም።

ይህ እውነት ነው

ምንም አደጋ የለም

ወንጀል የለም።

📱 ቴሌግራם: @rwslimited
👍41
ዜና፡ ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ #በትግራይ የተፈናቃይ መጠለያዎች በርሃብ ሳቢያ ስምንት ሰዎች ሞተዋል ተባለ

በተመሳሳይ
#በአማራ ክልል የእርዳታ መቋረጥ ችግር እየፈጠረ መሆኑም ተገልጿል

በትግራይ እና በአማራ ክልሎች ከቀያቸው ተፈናቅለው በመጠለያ ለሚገኙ ነዋሪዎች የሰብአዊ እርዳት መስጠት ከተቋረጠ ወዲህ ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸው ተገለጸ።

በትግራይ አክሱም ከተማ በሚገኙ መጠለያ ጣቢያዎች ተጠልለው ከሚገኙ ተፈናቃዮች መካከል ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ ስምንት ሰዎች በረሃብና በመድሃኒት እጦት መሞታቸውን የምዕራብ ትግራይ ዞን የአክሱም ክላስተር ተፈናቃዮች አስተባባሪ አቶ ካህሳይ አሳየሀኝ አስታውቀዋል።

በተያያዘ ዜና በአማራ ክልል አዲሱ የአሜሪካ አስተዳደር ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ በአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (USAID) ይሰጥ የነበረ እርዳታ መቀነስና በአንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ መቋረጥ በክልሉ በሚገኙ ተፈናቃዮች ዘንድ ከፍተኛ ተፅዕኖ እያሳደረ እንደሆነ ተፈናቃዮች ገልጸዋል።

ተፈናቃዮቹ ምግብ የለም፣ የመጠለያ ድንኳኖች ፈርሰዋል፣ የህክምና ባለሙያዎች ከመጠለያዎች ወጥተዋል፤ “ይደረጉ የነበሩ የዱቄት፣ የዘይትና አልባሳት ድጋፎች የሉም” ማለታቸውም ታውቋል።

@Yenetube @Fikerassefa
😭21👍102😁2
የጤና ባለሙያዎች ጥያቄ

"እርካታ ቤት ኪራይ አይከፍልም" - በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሰልፍ የወጡ የጤና ባለሞያዎች።

የጤና ባለሙያዎች የደመወዝ እና ሌሎች የጥቅማጥቅም ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጣቸው በሚሰሩበት ሆስፒታል በሰላማዊ መንገድ ጥያቄ ማቅረብ ጀምረዋል።

የጤና ባለሙያዎችን ጥያቄ በተመለከተ የጤና ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነትና ጤና ኮሚኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ተገኔ ረጋሳ በሰጡት ማብራርያ የአጭር፣ የመካከለኛ የረጅም ጊዜ ዕቅድ ይዞ ለችግሮች መፍትሔ ለመስጠት በሒደት ላይ እንደሚገኝ ከቀናት በፊት ለሪፖርተር ተናግረዋል።
"በጤና ባለሙያዎችና ሠራተኞች የሚነሱ ጥያቄዎች ተገቢና ዕውቅና የምንሰጣቸው ናቸው" ብለው ለሪፖርተር የተናገሩት ዶ/ር ተገኔ ከደመወዝ ጭማሪ ጋር በቀጥታ የማይገናኝ ማበረታቻ ወይም (Non Salary Incentives) ለጤና ባለሙያውና ለሠራተኛው ጠቀሜታው የጎላ ነው ተብሎ ተለይቶ እየተሠራበት ያለ አንዱ ፓኬጅ ነው ብለዋል።

Via:- አዩዘሀበሻ
@Yenetube @Fikerassefa
👍403🔥1
2025/07/12 19:21:07
Back to Top
HTML Embed Code: