ዜጎች ለሚደርስባቸው ደብደባና እንግልት የ #ኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቁንስላዎች መብታቸውንና ደህንነታቸውን እያስጠበቁ አለመሆኑን ጥናት አመላከተ
ለስራ ወደ ውጭ ሀገር የሚሰማሩ ዜጎች ለሚደርስባቸው ደብደባና እንግልት የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቁንስላዎች መብታቸውንና ደህንነታቸውን እያስጠበቁ አለመሆኑን ጥናት አመላከተ።
የስራና ክህሎት ሚኒስቴር "የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት ለሙስናና ብልሹ አስራር ያለውን ተጋላጭነት" በሚል ሀሳብ ከፌዴራል ሰነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ጋር ውይይት እያደረገ ይገኛል።
በውይይቱ በስነ ምግባርና ፀረ ኮሚሽን የአስቸኳይ ሙስና መከላከል ዳይሬክተር ወይዘሮ ስመኝ ቀፀላ የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት ላይ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን በተመለከተ የተጠና ጥናት አቅርበዋል።
ባቀረቡት ጥናት ለስራ ወደ ውጭ የሚሰማሩ ዜጎች በሚሄዱበት ሀገር ለድብደባና ለእንግልት እየተዳረጉ ነው ሲሉ ገልጸዋል። አክለውም ለሚደርስባቸው ደብደባና እንግልት የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቁንስላዎች መብታቸውንና ደህንነታቸውን እያስጠበቁ አይደለም ሲሉ አመላክተዋል።
ወደ ውጭ ለስራ የሚሰማሩ ዜጎች ሄደው ለመስራት ከ35 ሺህ ብር እስከ 70 ሺህ ብር ክፍያ እየተጠየቁ ነው ያሉት ዳይሬክተሯ፤
ለስራ ወደ ውጭ የሚሰማሩ ዜጎች ጉዳዮችን ለማስፈፀም የት መሄድ እንዳለባቸው ግንዛቤ የላቸውም ብለዋል።
በውጭ የስራ ስምሪት ላይ የመንግስትና የግል ተቋማት የአሰራርና የተጠያቂነት ክፍተት አለባቸው፤ ለውጪ ሀገር የስራ ፍሰት የወጡ ህጎችንና ስረዓቶችን ለተገልጋዮች ግልጽ ከማድረግ አኳያ ክፍት አለ ሲሉ ተናግረዋል።
ለተገልጋዮች ተገቢውና ግልፅ ግንዛቤ ባለመሰጠቱም በርካታ ዜጎች ለእንግልት፣ለሙስናና ለብልሹ አሰራር እየተዳረጉ ነው በማለት መግለጻቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

👍19❤1😭1
YeneTube
Photo
ወደ ውጭ ለሚሄዱ ዜጎች የዱቤ አገልግሎት መመቻቸቱ ተገለፀ
ፍላይ አዲስ ዛሬ ይብረሩ ነገ ይክፈሉ በሚል መርህ ከዳሽን ባንክ ጋር በመተባበር ወደ ተለያዩ ሀገራት ለሚሄዱ ዜጎች ለጉዞና ለማማከር አገልግሎቶች የዱቤ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ስምምነት ማድረጉን አስታውቋል
ድርጅቱ ከዚህም ጋር በተያያዘ በአሁን ሰዓት እነዚህን የጉዞና የማማከር አገልግሎቶችን ይበልጥ በማዘመንና በማስፋት ከአውሮፓ፣ ፖላንድ፣ ቱርክ፣ ጣሊያን፣ ካናዳ፣ ሩሲያ ሀገራት በተጨማሪ በሌሎች ሀገራትም ዜጐች አገልግሎቱን ማግኘት እንዲችሉ ከዳሽን ባንክ ጋር በመተባበር የዱቤ አገልግሎት በመስጠት ሕብረተሰቡ በሚሄዱባቸው ሀገራት ሁሉ ለሚያስፈልጓቸው የጉዞና ሌሎች አገልግሎቶቹን በዱቤ ማግኘት እንዲችሉ ከባንኩ ጋር ስምምነት ላይ ደርሶ ወደ ስራ መግባቱን አስታውቋል
ደንበኞች የዱቤ አገልግሎቱን ለማግኘት በዳሽን ባንክ ሱፐር አፕ ላይ በሚያንቀሳቅሱት የገንዘብ መጠንና በሰው ዋስ እንደሆነ ተገልጿል
ዳሽን ባንክ ከድርጅቱ ጋር አጋር በመሆን የዱቤ አገልግሎት ሲሰጥ ማለትም ትኬት፣ የሆቴል፣ የኢንሹራንስ፣ ቪዛና መሰል ለጉዞ የሚያስፈልጉ ሰነዶችን ክፍያ በዳሽን ባንክ በኩል እንዲከፍሉና ክፍያውን እንዲፈፅሙ የዱቤ አገልግሎቱን በየወሩ የሚፈፀም ሲሆን ደንበኛው ማስያዣና ሌሎች ዶክመንቶች አቅርቦ ለጉዞ የሚያስፈልጉ ዶክመንቶች ይሟሉላቸዋል፡፡ ለሕክምና፣ ለትምህርት፣ ለሥራ፣ የሽርሽር ጉዞ ለሚያደርጉት ጉዞ ከዳሽን ባንክ ጋር በመሆን የዱቤ አገልግሎት በመስጠት እንደሚሰራ ተነግሯል፡፡
ፍላይ አዲስ ከሚመለከተው የመንግስት መ/ቤት ሕጋዊ እውቅና በማግኘት ላለፉት አራት ዓመታት አውሮፓ፣ ፖላንድ፣ ቱርክ፣ ጣሊያን፣ ካናዳ፣ ሩሲያ እና ሌሎች በርካታ ሀገራት ለትምህርት፣ ለሥራና ለሕክምና እንዲሁም ለጉብኝት ጉዞ ለሚያደርጉ ዜጎች ሕጋዊ የጉዞና የማማከር አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡
@Yenetube @Fikerassefa

👍31❤6
የካቶሊካዊ ቤተክርስትያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ በኋላ፤ የቤተክርስትያኒትዋ ካርዲናሎች ተተኪውን ለመምረጥ ትናንት ስብሰባቸዉን ጀምረዋል።
ከካርዲናሎቹ ስብሰባ በኋላ ትናንት አመሻሹ የተሰጠዉ የመጀመሪያ ድምፅ ጥቁር ጭስ በመታየቱ አዲስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እንዳልተሰየመ ታዉቋል።
ካርዲናሎቹ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለመምረጥ የሚያደርጉት ድምፅ አሰጣጥ እና ስብሰባ ፤ ለቀናት፣ ለሳምንታት አልፎ ተርፎም ለወራት ሊዘልቅ ይችላል። አዲስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እስኪመረጥ ድረስ በቀጣዮቹ ቀናት ዉስጥ፤ በየቀኑ አራት ጊዜ ድምፅ የመስጠት ሥነ ስርዓት እንደሚኖር ተመልክቷል።
ኢትዮጵያዊው ካርዲናል ብርሃነየሱስ በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን 252 ካርዲናሎች አንዱ ሲሆኑ አዲሱን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለመምረጥ ከተቀመጡት 135 ካርዲናሎች አንዱ መሆናቸዉ ተዘግቧል።
የካቶሊካዊ ቤተክርስትያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ማን ይመረጥ ይሆን? ከየትኛዉ አገር?

👍21😁14❤2🔥1
የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን አዲስ ርዕሳነ ሊቃነ-ጳጳሳት መረጠች።
አዲሱ ርዕሳነ ሊቃነ-ጳጳሳት ሮበርት ፕሬቮስት ሲሆኑ 69 ዓመታቸው ነው።ቤተ-ክርስቲያኒቱን ሲመሩ ርዕሳነ ሊቃነ-ጳጳሳት ሊዎ 14ኛ ተብለው ይጠራሉ።ሮበርት ፕሬቮስት የመጀመሪያው አሜሪካዊ የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ርዕሳነ ሊቃነ-ጳጳሳት ሆነዋል።
ለበርካታ ዓመታት በፔሩ የኖሩ ናቸው።ማንነታቸው ይፋ ከመደረጉ በፊት በቫቲካን ጭስ ማውጫ አዲስ ርዕሳነ ሊቃነ-ጳጳሳት የመመረጡ ምልክት የሆነው ነጭ ጭስ ታይቷል።በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የተሰበሰቡ ምዕምናን እና ታዳሚዎች በሆታ መልዕክቱን ተቀብለዋል።
Via DW
@YeneTube @FikerAssefa

👍40😁17❤6
በ490,000 ቅድመ ክፍያ በመሀል ካዛንቺስ የቤት ባለቤት ይሁኑ ‼️
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው አያት ካዛንቺስ መንደር
እጅግ ውብ ዕይታ ያላቸው ቤቶች
ከ 1 መኝታ እስከ ባለ 4 መኝታ
👉ባለ አንድ መኝታ 45, 55 ,60 ካ.ሜ
👉ባለ ሁለት መኝታ 80,ካ.ሜ
👉ባለ ሶስት መኝታ 95,105,115 ካ.ሜ
👉ባለ አራት መኝታ 140 ,160 ካ.ሜ
✍️ ቅድመ ክፍያ 10%
📹 (ከ490,000ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ)
❇️ በ 18 ወራት የሚረከቡት ቤት💁
📍በግቢው ዙሪያ
➾ፓርኮች ና የወንዝ ዳር ልማት
➾አለማቀፍ ት/ቤትና ሆስፒታል
➾የእምነት ተቋማ
📍የቤቶቹ እይታ
➤ ወደ ቤተ መንግስት ( ጊቢ ገብርኤል )
➤ ወደ ያካ ተራራ ጫካ
➤ ወደ ወንዝ ዳር ልማት
➤ ወደ ወዳጅነት ፓርክ
👉 ቀድሞ ለመጣ ቅድሚያ ይስተናገዳል
❇️ ከሀገር ውጭ ያላችሁ ደንበኞች በወኪል መግዛት እንደምትችሉ እናሳውቃለን ።
ለምዝገባ 📲 0950123353 ወይም
በ whatsapp :-https://wa.me/251950123353
አሁኑ ይደውሉ

👍12❤1
🚀 ትልቅ እድል በLinkedIn! 🚀
የLinkedIn መለያዎን ይከራዩ፡ በየሳምንቱ ተገብሮ ገቢ ያግኙ!
🔑 እንዴት?
LinkedIn መሆን አለበት። 1 አመት እና ከዚያ በላይ መለያው ይኖርበታል።
💰 የገንዘብ አማራጮች:
• 300+ ግንኙነቶች - 13$ በየሳምንቱ
• 500+ ግንኙነቶች - 15$ በየሳምንቱ
• 800+ ግንኙነቶች - 17$ በየሳምንቱ
• 1000+ ግንኙነቶች - 20$ በየሳምንቱ
• 2000+ ግንኙነቶች - 25$ በየሳምንቱ
👉 ፈጣን ክፍያ - በ24 ውስጥ ይክፈሉ።
🔔 መልካም ዕድል!
• 1 ዓመት ዕድሜ ወይም ከዚያ በላይ
• 300+ - 13$ በሳምንት
• 500+ - 15$ በሳምንት
• 800+ - 17$ በሳምንት
• 1000+ - 20$ በሳምንት
• 2000+ - 25$ በሳምንት
🚫 መግለጫ:
መለያዎን ሊከራዩ፣ መለያዎች ሳምንታዊ ገደቦች መድረስ የለበትም።
• ይህ እውነት ነው
• ምንም አደጋ የለም
• ወንጀል የለም።
📱 ቴሌግራם: @rwslimiited

👍6
YeneTube
Photo
ኢትዮዽያ ልክ እንደ አማዞን፣ አሊባባ እና ኢ-ቤይ አይነት የዲጂታል ገበያን ወደ ኢኮኖሚው አስገባች።
ይህ የዲጂታል ገበያ ወይም ማርኬት ፕሌስ “ዘመን ገበያ“ ይሰኛል።
በብሔራዊ ደረጃ የዚህ የዲጂታል ገበያ ባለቤት ኢትዮ ቴሌኮም ነው።
ኩባንያው ዘመን ገበያ የተሰኘ ፤
ሀገር አቀፍ የዲጂታል የገበያ ሜዳ ዛሬ በይፋ አስጀምሯል።
ኢትዮ ቴሌኮም ለኢኮኖሚ እድገት ያግዛሉ ያላቸውን ምዕራፎች በመለየት በቴክኖሎጂ እንዲታገዙ በማድረግ፤ ውጤታማና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በቴክኖሎጂ በማስታጠቅ ገበያውን በብርቱ እያገዝኩ ነው ብሏል።
ኢትዮ ቴሌኮም የዘረጋው የዲጂታል መሰረተ ልማቶች እና ፈጣን ኢንተርኔት ግንኙነት፣ የክላውድ፣ ሞጁላር ዳታ ሴንተር እና የቴሌብር ዲጂታል ክፍያ ሥርዓት መስፋፋት ይህን ዲጂታል ገበያ ወደ ፊት ይገፈትረዋል ተብሏል።
ኢትዮ ቴሌኮም በዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ የኤሌክትሮኒክ ንግድን ማእዘን፣ ብሔራዊ የዲጂታል ግብይት ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ምቹ ሜዳ ፈጥሬያለሁ ብሏል።
ኩባንያው ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ የዲጂታል ግብይት ሥርዓት እውን እንዲሆን እና የሰፊውን ገበያ ጉልበት እጠቀማለሁ ብሏል።
ይህን በማድረግም የዲጂታል ኢኮኖሚ ውጤቶችን በመዘርዘር ፤ በመቁጠር አስተማማኝ በተባለ ደህንነቱ በተጠበቀ እና ማእከላዊ ዲጂታል በተባለለት ገበያ ''ዘመን የዲጅታል ገበያን “ ወደ ኢኮኖሚው ወርውሮ ተግባራዊ ለማድረግ በብርቱ ሲደክም እንደነበር የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል።
በመሆኑም ኩባንያው የዲጅታል ግብይትን አንድ ወደፊት የሚያዘምነውን ሥርዓት ወደ ኢኮኖሚው ዛሬ በይፋ አስገብቷል ተብሏል።
ይህ ዘመን የተሰኘው የዲጂታል ገበያ ሜዳ፣ምርት እና አገልግሎት አቅራቢዎች ከሸማቾች ይገናኙበታል መባሉን ሰምተናል።
በተለይም በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ አነስተኛና መካከለኛ የንግድ ድርጅቶች ከሸማቾች ጋር በቀላሉ ለማገናኘት እድል ይሆናል ተብሏል።
አዳዲስ የገበያ እድል በመፍጠርም የዲጂታል ኢኮኖሚን ለማፍታታት እንደሚያግዝ ሰምተናል።
ዘመን ገበያ ንግድን በማቀላጠፍና ከአነስተኛ ጀምሮ እስከ ትላልቅ የንግድ ድርጅቶች በማገናኘት፣ የገበያ ተደራሽነትን በማስፋት፣ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዲጨምር፣ የሥራ ዕድል እንዲፈጠርና አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት (GDP) እንዲያድግ አስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሏል።
በሎጅስቲክስ፣ በዲጂታል አገልግሎቶች፣ በዲጂታል ገበያ፣ በችርቻሮና በቴክኖሎጂ ዘርፎች የሀገር ውስጥ የሥራ ዕድሎችን በማነቃቃት ዘላቂ የኑሮ መተዳደሪያንና የማኅበረሰብ እድገትን ይደግፋል ተብሎለታል።
ዘመን የዲጅታል ገበያ የከተማና የገጠር ማህበረሰቦችን በማገናኘት በመላው ኢትዮዽያ በዲጂታል ንግድ ውስጥ እኩል ተሳትፎ እንዲኖር ያስችላል መባሉን ከዛሬው ጉባኤ ሰምተናል።
ይህ ጅምር፤ የድንበር ተሻጋሪ የንግድ ዕድሎችን በማመቻቸት ፤ ወደፊት የአገር ውስጥ አምራቾችና ነጋዴዎች ዓለም አቀፍ ገበያዎችን እንዲያገኙ በማገዝ ፤ ለውጪ ንግድ ዝግጁነትን ከፍ በማድረግ ለኢኮኖሚው በብርቱ ያግዛል ተብሏል።

👍24😁10👎6❤4😭1
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ደንበኞች ቁጥር ስምንት ነጥብ ስምት ሚሊዮን መድረሱ ተገለጸ
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በ2017 ዓ.ም መጋቢት ወር ድረስ በኢትዮጵያ የሚገኙ የደንበኞቹ ቁጥር ላይ ከፍተኛ እድገት ማስመዝገቡን ገለጸ፤ የደንበኞቼ ቁጥር 8 ነጥብ 8 ሚሊዮን ደርሷል ብሏል።
ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ103 ነጥብ ሁለት በመቶ ዓመታዊ እድገት የታየበት መሆኑን የኬንያው ዘ ስታር ጋዜጣ ዘግቧል።
ኩባንያው ከፍተኛ የደንበኞች ቁጥር ማግኘት የቻለው ወደ ሀገሪቱ የቴሌኮም ገበያ ከገባ ከሦስት ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል።
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የኔትወርክ ተደራሽነቱን በማስፋፋት እና የሞባይል ገንዘብ አገልግሎትን (ኤም-ፔሳ) ጨምሮ የተለያዩ አገልግሎቶችን ማስጀመሩ ተጠቅሷል።
በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥም በሀገሪቱ ያለው የሳፋሪኮም ኤም-ፔሳ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር ሁለት ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ደርሷል የተባለ ሲሆን 160 ሚሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ መንቀሳቀሱ ተጠቁሟል።
በተጨማሪም ኩባንያው እስከ መጋቢት ድረስ ወር 2017 ዓ.ም ድረስ 3 ሺ141 የኔትወርክ ጣቢያዎች ላይ ኢንቨስት ያደረገ ሲሆን 898 ቀጥተኛ የስራ እድሎችን መፍጠሩ ተገልጿል።
ከእነዚህ ውስጥ 95 በመቶዎቹ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች ሲሆኑ የውጭ ዜጎች ደግሞ አምስት በመቶ ብቻ መሆናቸው ተመላክቷል።
ኩባንያው በ2013 ዓ.ም ፈቃድ ማግኘቱን ተከትሎ ለረጅም ጊዜ በኢትዮ ቴሌኮም ተይዞ በቆየው ገበያ ላይ መሰማራቱ ይታወቃል።

👍30🔥2❤1
53 በመቶውን የሀገር ውስጥ የአልባሳት ገበያ የሚሸፍኑት በሕገ-ወጥ መንገድ የገቡ እና ልባሽ ጨርቆች መሆናቸው ተገለጸ!
በአሁኑ ወቅት የሀገር ውስጥ የአልባሳት ገበያውን 53 በመቶ የሚሸፍኑት፤ በሕገ-ወጥ መንገድ የገቡ እና ልባሽ ጨርቆች መሆናቸውን የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅና አልባሳት ማኅበር አስታውቋል።ማኅበሩ ልባሽ ጨርቆች እና በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ አልባሳት፤ የሀገር ውስጥ አምራቾች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያሳደሩ እንደሚገኝ ገልጿል።
የማኅበሩ ፕሬዝዳንት ጎሹ ነጋሽ ለአሐዱ እንደተናገሩት፤ አሁን ላይ ልባሽ ጨርቆች የሀገር ውስጥ የአላባሳት ገበያውን 53 በመቶ ይሸፍናሉ። በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡት አልባሳት ከፍተኛውን የገበያ ድርሻ መያዛቸው ሕጋዊ አምራች እና ነጋዴዎችን ኪሳራ ላይ እየጣለ እንደሚገኝ ያነሱት ኃላፊው፤ "ድርጊቱ በነጋዴዎች ላይ ብቻ ሳይሆን በሀገር ኢኮኖሚ ላይም ጉዳት ያስከትላል" ብለዋል።
በተጨማሪም ግብር የሚከፍሉ፣ የሥራ ዕድል የፈጠሩና ሕግን ተከትለው የሚሰሩ ተቋማትን የሚጎዳው ሕገ-ወጥ ድርጊት፤ የሀገር ውስጥ አምራቾች ተቋማቸውን እንዲዘጉ ስለማስገደዱ አንስተዋል፡፡ አሁን ያለው ገበያ ለሕጋዊ አምራቾች ተስፋ የሚሰጥ ባለመሆኑ መንግሥት ትኩረት እንዲደጠውም ጠይቀዋል፡፡የኢትዮጵያ የጨርቃ ጨርቅ ዘርፍ እንዲያድግ ለሀገር ውስጥ አምራቾች የተጠናከረ ድጋፍ እንዲደረግ ማኅበሩ ጠይቋል።
Via Ahadu

👍34👎5😁2❤1
የንግድ ተቋማት ከምሽት 12 እስከ ንጋት 12 የውጭና የውስጥ መብራት የማብራት ግዴታ ተጣለባቸው!
-ደንቡን ያልፈጸሙ እስከ 10ሺ ብር ቅጣት ይጠብቃቸዋል
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ በመንገድ ዳር የሚገኙ የንግድ ወይም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ከምሽት 12 እስከ ንጋት 12 ድረስ የውጭና የውስጥ መብራት ካላበሩ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው አስታውቋል።
ከዚህ በተጨማሪ በምሽት ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸውን የሚያሳይ በመብራት የሚሰራ ምልክት ካላስቀመጡ እስከ 10 ሺህ ብር የሚደርስ ቅጣት ሊያስቀጣቸው የሚችል ደንብ ተግባራዊ ማድረግ ጀምሯል።
ደንቡ፣ በመንገድ ዳር የሚገኙ ማናቸውም የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ የንግድ መደብሮች እንዲሁም መኖሪያ ቤቶች በሕንጻቸው የፊተኛው ገጽ መብራት ወይም የፋሳድ ላይት መብራት የማስገባት ግዴታ ጥሎባቸዋል።

👎45👍34😁17❤4😭2
ኢትዮጵያ የዓባይ ግድብ ሐይቅን የሚጠብቅ የ"ባሕር ፖሊስ" ወይም “ኮስታል ፖሊስ ጋርድ” አደራጀሁ ብላለች!
የዓባይ ግድብ ሰው ሠራሽ ሐይቅ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር ጥበቃ የሚያደርግ የ “ባህር ፖሊስ” መደራጀቱን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ነው ያስታወቀው።
በፌዴራል ፖሊስ የሠራዊት ግንባታ ዋና መምሪያ ስር የኢንስፔክሽንና ስታንዳርድ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር እስከዳር ብርሃን ለኢፕድ እንደገለጹት የዓባይ ግድብ ላይ የተፈጠረውን ረጅምና ስፋት ያለውን ሰው ሠራሽ ሀይቅ ለመጠበቅ እና በአካባቢው ሊፈጸሙ የሚችሉ ወንጀሎችን አስቀድሞ ለመከላከል የ“ባሕር ፖሊስ” ወይም “ኮስታል ፖሊስ ጋርድ” ተቋቁሟል ፡፡
የዓባይ ግድብ ሰው ሠራሽ ሐይቅ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር የጥበቃ ሥራው የሚከናወነው በፌዴራል ፖሊስ ሲሆን ሰው ሠራሽ ሐይቁን ለመጠበቅ የሚያስችል የሎጀስቲክስ አቅምን የማጠናከር ሥራ እየተሠራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል ።
በሪፎርም ሥራው የወንጀል መከላከል፣ አድማ በታኝ፣ ፈጥኖ ደራሽና ሌሎች አደረጃጀቶች ላይ በተደረገው ጥናት ድሮን፣ ጀልባ፣ ሂሊኮፕተርና ሌሎች ትጥቆችን ማሟላት ትኩረት ተሠጥቷል ያሉት ኮማንደሯ፤ በዚህ መሠረትም የባሕር ላይ ውንብድናን መከላከል የሚችል ኃይልን ከትጥቅ ጋር የማደራጀት ሥራ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል።
በቀጣይ አደረጃጀቱን ወደ ሥራ ለማስገባትም ብቁ የሰው ኃይል የመመልመል እና የማሠልጠን ሥራን ከኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ጋር በትብብር እንደሚሠራ ጠቁመው፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚፈለገውን የሰው ኃይል በመመልመልና በማሠልጠን ወደ ሥራ ይገባል። ነገር ግን መቼ ወደ ሥራ እንደሚገባ ቁርጥ ጊዜው አልታወቀም ብለዋል።ይህ “ኮስታል ፖሊስ ጋርድ” ወይም የ“ባሕር ፖሊስ” ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገራችን የተደራጀ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

👍52😁23👀4❤2🔥1
የ12ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ይሰጣል!
የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈታናዎች አገልግሎት አስታወቀ፡፡
የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን፤ በበይነ መረብ ፈተናውን የሚወስዱ ተማሪዎች በሁለት ዙር እንደሚፈተኑ ተናግረዋል፡፡ይህም የሆነበት ዋናው ምክንያት በበይነ መረብ የመፈተን አቅምን ለመጨመር እና ያለውን የመሰረተ ልማት አቅም ለማሳደግ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ፈተናው በ2 ዙር በበይነ መረብ መሰጠቱ ከመኖሪያ ቤታቸው እየተመላለሱ በበይነ መረብ የሚፈተኑ ተማሪዎችን ቁጥር ይጨምራል ብለዋል፡፡
በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ፈተና 608 ሺህ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ገልጸው፤ ፈተናውን በወረቀት የሚወስዱ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ በዩኒቨርሲቲዎች የሚፈተኑ መሆኑን ጠቁመዋል።
ፈተናውን በበይነ መረብ የሚወስዱት ደግሞ በዩኒቨርሲቲዎች፣ በመንግስት እና በግል ትምህርት ቤቶች፣ በጤና እና መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጆች እንዲሁም በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ውስጥ ባሉ ኮምፒዩተሮች ይፈተናሉ ብለዋል።
Via FBC

👍20😭6❤4