Telegram Web Link
የቻይናው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ አምራች ጂኤሲ ሁለት የመኪና ሞዴሎችን ለኢትዮጵያ ገበያ አቀረበ!

የሁዋጂያን ኢንዱስትሪ በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ አምራችነት ቀዳሚ ከሆኑ ኩባንያዎች አንዱ የሆነው የቻይናው የጓንግዙ አውቶሞቢል ኩባንያ (ጂኤሲ) ምርቶችን በኢትዮጵያ ለማቅረብ የሚያስችለውን የመኪና ሞዴል የማስተዋወቅ መርሃግብር አካሂዷል።ኩባንያው በመርሃ ግብሩ AION Y and ES9 የተሰኙ ሁለት የኤለኢክትሪክ ተሽከርካሪ ሞዴሎችን ማስተዋወቁን ገልጿል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን፣ "የኢትዮጵያ መንግስት በነዳጅ የሚሰሩ መኪኖችን ማምረት፣ ማስመጣትና መገጣጠም በመከልከሉ፤ ሀገሪቱ እንደ ጂኤሲ ላሉ ታዋቂ ኩባንያዎች ምቹ ገበያ ትሆናለች" ብለዋል።የትራንሰፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ደኤታ አቶ በርኦ ሀሰን በበኩላቸው፤ የኩባንያው ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ለሁለቱ ሀገሮች የንግድ ትስስር ትልቅ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።

አክለውም መንግሥት ለኤሌክትሪክ አውቶሞቢል አቅራቢዎች ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንደሚያደርግ ጠቅሰው ኩባንያው ወደ ኢትዮጵያ ገበያ መግባቱ ሰፊ የገበያ ዕድል እንደሚፈጥርለት ገልጸዋል።

የሁአጂያን ሊቀመንበር ዣንግ ሁአሮንግ በበኩላቸው፤ ኩባንያው በቀጣይ የኤሌክትሪክ መኪኖችን በኢትዮጵያ ለማምረት እቅድ የያዘ መያዙን እና ይህም ኢትዮጵያንና ቻይናን ይበልጥ በንግድ ለማጠናከር እንደሚረዳ ተናግረዋል።በአሁኑ ወቅት ከ100,000 በላይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በኢትዮጵያ የሚገኙ ሲሆን፣ መንግስት በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ውስጥ እስከ 500,000 የሚደርሱ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባ አቅዶ እየሰራ መሆኑ ይታወቃል።

@YeneTube @FikerAssefa
👍371
“የፌደራል መንግስት ስምምነቱን ለማፍረስ ብዙ ርቀት እየተጓዘ ነው”፣ “አቶ ጌታቸው ረዳን ተጠቅሞ ስም ማጥፋት ዘመቻ በክልሉ ተቋማት ላይ እያካሄደ ነው” - ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት፣ ህወሓት፣ የጸጥታ ቢሮ

ባሳለፍነው ሳምንት መጀመሪያ ቀናት የቀድሞ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አቶ ጌታቸው ረዳ በፋና ቴሌቪዢን ቀርበው ባካሄዱት ቃለምልልስ ያነሷቸው ጉዳዮች ከክልሉ የጸጥታና የሰላም ቢሮ፣ ከፕሬዝዳንቱ ጽ/ቤት እና ከህወሓት በኩል ከፍተኛ ተቃውሞ ተሰንዝሮባቸዋል።

የትግራይ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ “የፌደራል መንግስት አቶ ጌታቸው ረዳን ተጠቅሞ ከፕሪቶርያ ስምምነት ውጭ በተደጋጋሚ ትንኮሳ በማካሄድ የፕሪቶርያን የሰላም ስምምነት ለማፍረስ ብዙ ርቀት እየተጓዘ ነው” ሲል ተችቷል።

በሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ የሚመራው የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት በበኩሉ አቶ ጌታቸውን “የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕረዚዳንት በመሆናቸው ብቻ ሊያውቋቸው የቻሏቸውን፣ ብሔራዊ ጉዳዮች ተደርገው እስከ መጨረሻው ሊጠበቁ የሚገባቸውን ሚስጠሮች ለርካሽ አገልገሎት አውለውታል” ሲል ተችቷል።

በተመሳሳይ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ግንቦት 9 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ የፌደራል መንግስት የፕሪቶርያ የሰላም ስምምነትን በጣሰ መልኩ ባለስልጣናቱን እና የሚዲያ ሰራዊቱን በመጠቀም በትግራይ ህዝብ፣ በፖለቲካ ድርጅቶቹና በክልሉ ተቋማት ላይ ከፍተኛ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ እያካሄደ ይገኛል ሲል አስታውቋል።

Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
👍26😁165👎3
በኢትዮጵያ የውጭ ዜጎች በሊዝ የመሬት ባለይዞታ እንዲሆኑ የሚፈቅድ የአዋጅ ረቂቅ በነገው ዕለት ለፓርላማ ሊቀርብ ነው!

የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ መሬትን በሊዝ በባለቤትነት መያዝ የሚያስችላቸው የአዋጅ ረቂቅ፤ በነገው ዕለት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሊቀርብ ነው። ኢትዮጵያዊ ዜግነት የሌላቸው ግለሰቦች በኢትዮጵያ መሬትን፣ የመኖሪያ ቤትን ወይም ተያያዥ ግንባታዎችን በባለቤትነት ለመያዝ፤ ቢያንስ 150 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ሊመድቡ እንደሚገባ በአዲሱ አዋጅ ተደንግጓል። 

የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ የማይንቀሳቀስ ንብረት “ባለቤት” ወይም “ባለይዞታ” የሚሆኑበትን አግባብ ለመደንገግ የወጣውን ይህን አዋጅ፤ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ተወያይቶ ለፓርላማ የመራው ከሁለት ሳምንት በፊት ነበር። አዋጁ የተዘጋጀው “የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ የመኖሪያ ቤት ባለቤት የሚሆኑበት” ወይም “ለመኖሪያ ቤት ግንባታ የሚውል መሬት የሚያገኙበትን” ህጋዊ አሰራር ለመዘርጋት እንደሆነ በመግቢያው ላይ ሰፍሯል።

“መኖሪያ ቤት” ማለት “ለግለሰብ ወይም ለቤተሰብ መኖሪያነት የሚያገለግል፤ ለንግድ ዓላማ ማዋል የማይፈቀድ ቤት” እንደሆነ በአዋጅ ረቂቁ የትርጓሜ ክፍል ላይ ተቀምጧል። ሆኖም ይህን መሰሉን ቤት “ለመኖሪያነት ዓላማ የማከራየት መብት የተጠበቀ” መሆኑን አዋጁ አመልክቷል።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
👎50👍173😁1
ሶስት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ሆነው ተሾሙ!

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ  የፕላን እና ልማት ሚኒስትሯን ፍፁም አሰፋን (ዶ/ር)፣ የፍትህ ሚኒስትሯን ወ/ሮ ሃና አርአያሰላሴን እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑትን ዘለቀ ተመስገንን (ዶ/ር) የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል አድርጎ መሾሙን ዛሬ አስታውቋል።

ተቋሙ በሰጠው መግለጫ እነዚህ ሶስት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በመንግስት፣ በልማት እና በኢንቨስትመንት ዘርፎች ያካበቱት ሰፊ ልምድና አመራር፣ ኢትዮጵያ በስትራቴጂካዊ እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ኢንቨስትመንቶች እንዲሁም በፖርትፎሊዮ አስተዳደር የኢኮኖሚ ለውጥን በማፋጠን ረገድ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ገልጿል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
😁14👍134🔥1
የጤና ባለሙያዎች ሙሉ ለሙሉ የስራ ማቆም አድማ መጀመራቸውን ተከትሎ በአዲስ አበባና በተለያዩ ከተሞች በሚገኙ ሆስፒታሎች የህክምና አገልግሎት መቋረጡ ተገለጸ!

በመላ ሀገሪቱ የተጀመረው የጤና ባለሙያዎች የስራ ማቆም አድማ ስድስተኛ ቀኑን በያዘበት በዛሬው ዕለት ግንቦት 11 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ንቅናቄ ሙሉ በሙሉ የስራ ማቆም ጥሪ ማስተላለፉን ተከትሎ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች በሚገኙ አንዳንድ ሆስፒታሎች የህክምና አገልግሎቶች መስጠት ማቆማቸው ተገለጸ።

#በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ፍቼ ከተማ በሚገኘው የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሚሰሩ አንድ የጤና ባለሙያ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገሩት በሆስፒታሉ የሚገኙ አጠቃላይ ሐኪሞች "ሙሉ በሙሉ የስራ ማቆም አድማውን እየተሳተፉ ነው ሌሎች የሰራተኛ አባላት ግን አሁንም እየሰሩ ናቸው" ብለዋል።

አዲስ ስታንዳርድ በዛሬው ዕለት ማለዳ ላይ  በሶስት ዋና ዋና ሆስፒታሎች ማለትም በዳግማዊ #ምኒልክ ሪፈራል ሆስፒታል፣  #በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል እና #የካቲት 12 ሜዲካል ኮሌጅ ሆስፒታል ባደረገው ጉብኝት የአገልግሎት መስተጓጎል በስፋት ያስተዋለ ሲሆን የተወሰኑ የድንገተኛ ህክምና ክፍሎች ብቻ ስራቸውን ሲቀጥሉ ለመታዘብ ተችሏል።

በተያያዘ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኀበራዊ ፍትሕ (#ኢዜማ) ግንቦት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ መንግስት “የጤና ባለሙያዎቹን ጥያቄያቸውን ለመፍታት ፍላጎት እንዳለው ለማሳየት ሙከራ እንኳ አላደረገም” ሲል ተችቷል “ማስፈራሪያ አዘል አቅላይ መንገድን መከተሉ ሃላፊነትን በአግባቡ ካለመወጣት የሚመነጭ የመንግስት ስህተት ነው” ብሏል።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጠቀሙ :-
https://addisstandard.com/Amharic/?p=7822
👍108😭218😁5
በ490,000 ቅድመ ክፍያ  በመሀል ካዛንቺስ  የቤት ባለቤት ይሁኑ ‼️

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው አያት ካዛንቺስ መንደር

እጅግ ውብ ዕይታ ያላቸው ቤቶች

ከ 1 መኝታ እስከ ባለ 4 መኝታ
👉ባለ አንድ መኝታ 45, 55 ,60 ካ.ሜ
👉ባለ ሁለት መኝታ  80,ካ.ሜ
👉ባለ ሶስት መኝታ  95,105,115 ካ.ሜ
👉ባለ አራት መኝታ  140  ,160 ካ.ሜ

✍️ ቅድመ ክፍያ 10%
📹 (ከ490,000ብር ቅድመ ክፍያ  ጀምሮ)

❇️  በ 18 ወራት የሚረከቡት ቤት💁

      

       📍በግቢው ዙሪያ

   ➾ፓርኮች ና የወንዝ ዳር ልማት
    ➾አለማቀፍ ት/ቤትና ሆስፒታል
    ➾የእምነት ተቋማ

       📍የቤቶቹ እይታ

    ➤ ወደ ቤተ መንግስት ( ጊቢ ገብርኤል )
    ➤ ወደ ያካ ተራራ ጫካ
    ➤ ወደ ወንዝ ዳር ልማት
    ➤ ወደ ወዳጅነት ፓርክ

👉 ቀድሞ ለመጣ ቅድሚያ ይስተናገዳል

❇️  ከሀገር ውጭ ያላችሁ ደንበኞች በወኪል መግዛት እንደምትችሉ እናሳውቃለን ።

ለምዝገባ 📲 0950123353 ወይም
በ whatsapp :-https://wa.me/251950123353
አሁኑ ይደውሉ
2👍1
🟢 SAMSUNG M16 5G 🟢 (NEW)

✔️storage 128gb
✔️Ram 6gb
✔️Dual

💵Price 25,000 Birr

🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺

😀 0942405669
✈️@Endalk4240

Join channel https://www.tg-me.com/phonestore_22
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
900,000 ብር ምን መግዛት ይችላል?

መኪና? ቤት?

በዚህ ጊዜ 900,000 ብር ምንም መግዛት አይችልም ።

እኛ ጋር ግን በ900,000 ብር ሱቅ መግዛት ትችላላችሁ ።

ያውም እስከ 200,000 ብር መከራየት የሚችል ሱቅ።

ፒያሳ አድዋ ዜሮ ዜሮ አጠገብ 20 ካሬ ሱቅ አየሸጥን ነው።

ከግራውንድ እስከ 5ኛ ፎቅ።

ለሁለት ሳምንት ብቻ የሚቆይ ዋጋ ነው።

ፈጥነው ይደውሉ!

ለበለጠ መረጃ  (Direct/ Whatsapp) ፦ በ
0909253426 / 0940407294 ይደውሉ
👍41👎1
📒 ውድ የ International Student Community እና Refocus Africa ቤተሰቦች እንኳን ደስ አላችሁ 🎉

International Student Community ከ Refocus Afrika ጋር በመተባበር የፊታችን 🗓 May 24 እና 25 ( ግንቦት 16 እና 17) ልዩ የ Cultural Exchange እንዲሁም የ Scholarship Process Guidance 🎆ይዞላችሁ መቷል !!!

🗺️ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 6 kilo Alamudin ህንፃ አዳራሽ 🏚️
ከ ጠዋቱ 2:00 እስከ 11:00 ሰአት

ትምህርታቹን ውጭ ሀገር ሄዶ የመማር ፍላጎት ያላችሁ በሙሉ የዚህ ፕሮግራም ተሳታፊ እንድትሆኑ ተጋብዛችሁአል።

፨ በመጀመሪያ ዲግሪ ፣ በማስተርስ እንዲሁም በዶክተሬት ዲግሪ👨🏾‍🎓

በዕለቱ ሲገኙ ፦
📕ፓስፖርት/ የልደት ሰርተፍኬት
📝ትራንስክሪፕት ይዘው መምጣት እንዳይረሱ

🌍የዚህ እድል ተሳታፊ በመሆን የወደፊት የትምህርት ጉዞዎን ይጀምሩ✈️

ያለን ቦታ ውስን በመሆኑ ፈጥነው ይመዝገቡ ፧‼️

ለመመዝገብ ይህንን ሊንክ #ይጫኑ 👇👇
https://forms.gle/SJ6nzXdNAixTptGv5

Join our telegram channel
➡️ https://www.tg-me.com/isc_italy
👍41
"የጤና ባለሙያዎች ጥያቄ የሕዝብም ጥያቄ ነውና ትኩረት ይሰጠው!"

(በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከመኢአድ፣ ኢሕአፓ፣ እናት ፓርቲና ዐማራ ግዮናዊ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ)

@YeneTube @FikerAssefa
👍773👎3🔥1😁1
የትግራይ እና ኦሮሚያ ጤና ማህበራት ለጤና ባለሙያዎች ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ጠየቁ፣ የጤና ባለሙያዎች የጀመሩት የስራ ማቆም አድማ ስምንተኛ ቀኑን ይዟል!

የጤና ባለሙያዎች የጀመሩት የስራ ማቆም አድማ ስምንተኛ ቀኑን በያዘበት በአሁኑ ወቅት የትግራይ እና ኦሮሚያ ክልሎች ጤና ማህበራት ለጤና ባለሙያዎች ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ጠየቁ።

የትግራይ ህክምና ማህበር ግንቦት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ለጤና ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ መንግሥት ለጤና ባለሙያዎች ጥያቄና መብት ተገቢውን ትኩረትና ምላሽ ከመስጠት ይልቅ በአንዳንድ የአገሪቱ አካባቢዎች የጤና ባለሙያዎችን ጥያቄ እየጣሰ ተገቢ ያልሆነ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን አስታውቋል።

እነዚህ የሞያ አጋሮቻችን እንዲፈቱ አስፈላጊውን ጫና እንዲደረግ ሲል ለጤና ሚኒስቴር አሳስቧል፤ ሁሉም የሞያ ማህበራት እና ጤና ባለሞያዎች ችግሮቹን መፍትሄ ለማበጀት ግልፅ እና ሁሉን ያሳተፈ ውይይት እንዲደረግ ሲልም ጠይቋል።

በተመሳሳይ የኦሮሚያ ሐኪሞች ማኅበር በበኩሉ ትናንት ግንቦት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ "የጤና ባለሙያው የሚገባውን ለመስጠት የሀገሪቱ ኢኮኖሚ አይፈቅድም ቢባል እንኳን እየተራበ እንዳያገለግል እየተጠማ እንዳይማር እየታመመ ማስታገሻ እንዳያጣ የሚያደርግ የኑሮ ሁኔታ እንዲፈጠርለት ሲታገል ቆይቷል" ሲል አውስቷል።

አክለውም አሁን ላይ በጤና ባለሙያዎቹ እየተነሱ የሚገኙ ጥያቄዎችን እንደሚደግፍ ገልጾ እየተፈጠረ ያለው ሁኔታ ተባብሶ ጉዳት ከማስከተሉ በፊት ውይይቶች እንዲደረጉና እርምጃዎች እንዲወሰዱ ጠይቋል።

Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
👍351
የውጭ ሀገር ተጓዦች ማግኘት የሚችሉት የውጭ ምንዛሪ መጠን በእጥፍ አደገ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ወደ ውጭ ሀገር የሚሄዱ የግል ተጓዞች እንዲያገኙ የሚፈቀድላቸውን የውጭ ምንዛሪ መጠን ከአምስት ሺህ የአሜሪካ ዶላር ወደ 10 ሺህ ዶላር አሳደገ።ባንኮች ለሚሰጧቸው የውጭ ምንዛሪ አገልግሎቶች የሚያስከፍሉት የገንዘብ መጠንም "ከአራት በመቶ እንዳይበልጥ" እንዲሁም "ጥቃቅን የአገልግሎት ወጪዎችን እንዲያስቀሩ" መወሰኑንም አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በውጭ ምንዛሪ ገበያ ሥርዓቱ ላይ እነዚህን ማሻሻያዎች መውሰዱን ያስታወቀው ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 12/2017 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ነው። ብሔራዊ ባንክ ይፋ ያደረጋቸው የውጭ ምንዛሪ ሥርዓት አስተዳደር ማሻሻያዎች ሦስት ናቸው።

የመጀመሪያው ለውጥ፤ አስመጪዎች መፈጸም የሚችሉት ቅድመ ክፍያ (አድቫንስ ፔይመንት) ላይ የተጣለውን ገደብ ከፍ ያደረገ ነው። ከዚህ ቀደም በነበረው አሠራር ሸቀጦችን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት የሚፈልጉ አስመጪዎች መፈጸም የሚችሉት ቅድመ ክፍያ አምስት ሺህ የአሜሪካ ዶላር እንደነበር መግለጫው ያስረዳል።ይህ ገደብ "የቆየ" እና "ለብዙ ዓመታት ለውጥ ሳይደረግበት የቆየ" አሠራር እንደሆነም ጠቅሷል። በአዲሱ አሠራር መሠረት አምስት ሺህ ዶላር የነበረው ገደብ በአስር እጥፍ አድጓል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
👍284😁4😭3
🟥📣የመጨረሻ ዲያስፓራ ቁ3 ብሎክ 

🏫ከስቱድዮ እስከ ባለ 4 መኝታ ከተጨማሪ የሰራተኛ፣ ላውንደሪ ክፍል እና የዕቃ ክፍል ያካተቱ ቤቶች

💸ቅድመ ክፍያ
   
    💎ባለ 1 መኝታ  በ 431 ሺ ብር
    💎ባለ 2 መኝታ  በ 619 ሺ ብር
    💎ባለ 3 መኝታ  በ 751 ሺ ብር
    💎ባለ 4 መኝታ  በ 1,051,626 ብር 

🛍️🛒ሱቆች ከ 43 ካሬ ጀምሮ

🏦60% የባንክ ብድር የተመቻቸላቸው (እየኖሩበት ወይም አከራይተውት እስከ 20 አመት ቀስ ብለው የሚከፍሉት)

➡️በ 8% ቅድመ ክፍያ

➡️እስከ 30% በሚደርስ ቅናሽ ዋጋ (ለውስን ቤቶች) በመጠቀም
የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ


➡️☎️ 09 72 42 75 95     

➡️@Tirsit9 (telegram)

➡️Whatsapp Link-
https://whatsapp.com/dl/code=gsXOc8ttJB?mode=tac
👍85
Forwarded from YeneTube
በ490,000 ቅድመ ክፍያ  በመሀል ካዛንቺስ  የቤት ባለቤት ይሁኑ ‼️

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው አያት ካዛንቺስ መንደር

እጅግ ውብ ዕይታ ያላቸው ቤቶች

ከ 1 መኝታ እስከ ባለ 4 መኝታ
👉ባለ አንድ መኝታ 45, 55 ,60 ካ.ሜ
👉ባለ ሁለት መኝታ  80,ካ.ሜ
👉ባለ ሶስት መኝታ  95,105,115 ካ.ሜ
👉ባለ አራት መኝታ  140  ,160 ካ.ሜ

✍️ ቅድመ ክፍያ 10%
📹 (ከ490,000ብር ቅድመ ክፍያ  ጀምሮ)

❇️  በ 18 ወራት የሚረከቡት ቤት💁

      

       📍በግቢው ዙሪያ

   ➾ፓርኮች ና የወንዝ ዳር ልማት
    ➾አለማቀፍ ት/ቤትና ሆስፒታል
    ➾የእምነት ተቋማ

       📍የቤቶቹ እይታ

    ➤ ወደ ቤተ መንግስት ( ጊቢ ገብርኤል )
    ➤ ወደ ያካ ተራራ ጫካ
    ➤ ወደ ወንዝ ዳር ልማት
    ➤ ወደ ወዳጅነት ፓርክ

👉 ቀድሞ ለመጣ ቅድሚያ ይስተናገዳል

❇️  ከሀገር ውጭ ያላችሁ ደንበኞች በወኪል መግዛት እንደምትችሉ እናሳውቃለን ።

ለምዝገባ 📲 0950123353 ወይም
በ whatsapp :-https://wa.me/251950123353
አሁኑ ይደውሉ
👍4
Forwarded from YeneTube
🟢 SAMSUNG M16 5G 🟢 (NEW)

✔️storage 128gb
✔️Ram 6gb
✔️Dual

💵Price 25,000 Birr

🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺

😀 0942405669
✈️@Endalk4240

Join channel https://www.tg-me.com/phonestore_22
1👍1
Forwarded from YeneTube
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
900,000 ብር ምን መግዛት ይችላል?

መኪና? ቤት?

በዚህ ጊዜ 900,000 ብር ምንም መግዛት አይችልም ።

እኛ ጋር ግን በ900,000 ብር ሱቅ መግዛት ትችላላችሁ ።

ያውም እስከ 200,000 ብር መከራየት የሚችል ሱቅ።

ፒያሳ አድዋ ዜሮ ዜሮ አጠገብ 20 ካሬ ሱቅ አየሸጥን ነው።

ከግራውንድ እስከ 5ኛ ፎቅ።

ለሁለት ሳምንት ብቻ የሚቆይ ዋጋ ነው።

ፈጥነው ይደውሉ!

ለበለጠ መረጃ  (Direct/ Whatsapp) ፦ በ
0909253426 / 0940407294 ይደውሉ
Forwarded from YeneTube
📒 ውድ የ International Student Community እና Refocus Africa ቤተሰቦች እንኳን ደስ አላችሁ 🎉

International Student Community ከ Refocus Afrika ጋር በመተባበር የፊታችን 🗓 May 24 እና 25 ( ግንቦት 16 እና 17) ልዩ የ Cultural Exchange እንዲሁም የ Scholarship Process Guidance 🎆ይዞላችሁ መቷል !!!

🗺️ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 6 kilo Alamudin ህንፃ አዳራሽ 🏚️
ከ ጠዋቱ 2:00 እስከ 11:00 ሰአት

ትምህርታቹን ውጭ ሀገር ሄዶ የመማር ፍላጎት ያላችሁ በሙሉ የዚህ ፕሮግራም ተሳታፊ እንድትሆኑ ተጋብዛችሁአል።

፨ በመጀመሪያ ዲግሪ ፣ በማስተርስ እንዲሁም በዶክተሬት ዲግሪ👨🏾‍🎓

በዕለቱ ሲገኙ ፦
📕ፓስፖርት/ የልደት ሰርተፍኬት
📝ትራንስክሪፕት ይዘው መምጣት እንዳይረሱ

🌍የዚህ እድል ተሳታፊ በመሆን የወደፊት የትምህርት ጉዞዎን ይጀምሩ✈️

ያለን ቦታ ውስን በመሆኑ ፈጥነው ይመዝገቡ ፧‼️

ለመመዝገብ ይህንን ሊንክ #ይጫኑ 👇👇
https://forms.gle/SJ6nzXdNAixTptGv5

Join our telegram channel
➡️ https://www.tg-me.com/isc_italy
👍6
የውጭ ዜጎች የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት እንዲሆኑ የሚያስችላቸው አዋጅ “ጊዜውን የጠበቀ አይደለም” በሚል ተተቸ 

የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ የማይንቀሳቅስ ንብረት ባለቤት እና ባለይዞታ እንዲሆኑ የሚያስችላቸው አዋጅ “ጊዜውን የጠበቀ አይደለም” በሚል በፓርላማ አባላት ተተቸ። ትችቱ የቀረበው ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 12፤ 2017 በተካሄደው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው።

በአራት ክፍሎች እና በ20 አንቀጾች የተከፋፈለው የአዋጅ ረቂቅ፤ የውጭ ዜጎች የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት ወይም ባለይዞታ ለመሆን ማሟላት ስለሚጠበቅባቸው ቅድመ ሁኔታዎች፣ የፈቃድ አሰራሮች፣ ገደቦች፣ መብቶች እና ግዴታዎች አካትቶ ይዟል። የህግ ረቂቁ በዝርዝር እንዲታይ ለተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ከመመራቱ አስቀድሞ በተደረገ ውይይት ላይ፤ ሁለት የፓርላማ አባላት ትችት አዘል ጥያቄዎችን ሰንዝረዋል።

የአዋጁ ዋና ዓላማ “የውጭ ካፒታል ወደ ሀገር ውስጥ ማምጫ” እና “የውጭ ምንዛሬ ማግኛ እንደሆነ” መገንዘባቸውን የገለጹት የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የፓርላማ ተወካዩ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ፤ በህግ ረቂቁ ላይ ያላቸውን ስጋቶች እና አስተያየቶች በዝርዝር አቅርበዋል። የፓርላማ አባሉ ለስጋታቸው በምክንያትነት ካስቀመጧቸው ጉዳዮች አንዱ የሀገሪቱ የነፍስ ወከፍ ገቢ እና ደመወዝ በአለም አቀፍ ደረጃ ካለው ሲነጻጸር ያለውን ልዩነት ነው።

🔴 ዝርዝሩን ለማንበብ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/15990/

🔴 የፓርላማ አባላቱን አስተያየት ለማድመጥ ➡️ https://youtu.be/0WW5cfnTOJc
👍193
እንግሊዝ ፈረንሳይ እና ካናዳ እስራኤልን አስጠነቀቁ

እንግሊዚ፤ፈረንሳይ እና ካናዳ  እስራኤል በጋዛ ላይ እየፈጸመች ያለዉን  ጥቃት  እንድታቆም አስጠንቅቀዋል፡፡

የሃገራቱ መሪዎች እስራኤል በጋዛ የምታካሂደዉን ጦርነትን በተመለከተ ማስጠንቀቂያ የሰጡ ሲሆን በተለይም እስራኤል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጋዛን  ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር እያደረገች ያለችዉን ዘመቻ እንድታቆም አሳስበዋል፡፡

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ነታንያሁ እስራኤል መላ ጋዛን እንደምትቆጣጠር ትላንት ማስጠንቀቃቸው አይዘነጋም፡፡

አዲስ ዘመቻ መጀመሩን ባለፈው አርብ ያስታወቀው የእስራኤል ጦር የደቡባዊ ካን ዩኑስ ነዋሪዎች በአስቸኳይ አካባቢውን ለቀው በመውጣት ወደ ባህር ዳርቻ እንዲሄዱ አሳስቧል።

በአሁኑ ጊዜ ጋዛን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር መጠነ ሰፊ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን በቪድዮ መልዕክታቸው የተናገሩት ነታንያሁ በዘመቻው ሀማስ እስካሁን ጋዛ ውስጥ የያዛቸውን 58 ታጋቾችን ማስለቀቅና የፍልስጤም ተዋጊ ሚሊሽያዎች ቡድንን በማጥፋት ሙሉ ድል መቀዳጀትን እናሳካለን ብለዋል።

ይሁን እና መሪዎቹ እስራኤል እየፈጸመች ያለዉን መጠነሰፊ ዉድመትና ግድያ ካላቁመች፡፡ እንዲሁም ወደ ግዛቲቱ እንዳይገቡ የታገዱት የሰባአዊ እርዳታ ካልተለቀቁ እርምጃዎችን እንደ ሚወስዱ አስጠንቅቀዋል ሲል ሮይተርስ ነዉ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
👍31😁133
በትግራይ የሚገኙ የተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ አምባሳደር ማሲንጋ አስታወቁ፣ ከህወሓትና ከሰራዊቱ አመራሮች ጋርም መክረዋል

በትግራይ የሚገኙ የተፈናቃዮች ጉዳይ ግዜ የማይሰጠው እና አስቸኳይ መፍትሔ የሚያስፈልገው በመሆኑ ወደ ቀያቸው ለመመለስ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ በኢትዮጵያ #የአሜሪካን አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ አስታወቁ፤ ከህወሓትና ከሰራዊቱ አመራሮች ጋርም መምከራቸው ተገልጿል።

በኢትዮጵያ የአሜሪካን አምባሳደር ማሲንጋ ትላንት ግንቦት 12 ቀን 2017 ዓ.ም በሽሬ የሚገኙ የተፈናቃይ መጠለያ ካምፖችን ጎብኝተዋል፤ “ለተፈናቃዮች የሚደረገው ድጋፍ ዘላቂ መፍትሄ አይደለም፣ ዘላቂው መፍትሔ በአፋጣኝ ተፈናቃዮቹ ወደ መኖሪያ ቤታቸው እንዲመለሱ ማድረግ ነው ሲሉ ገልጸዋል”።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አማኒኤል አሰፋ በበኩላቸው ከአምባሳደር ማሲንጋ እና ልዑካቸው ጋር የተደረገው ውይይት ዋና ትኩረታችን በተፈናቃዮች መመለስ ላይ ነበር ብለዋል።

“ከአንድ ሚሊየን በላይ ተፈናቃዮች በልመና መልክ ከሚገኝ ድጋፍ ከማኖር እነዚህ አንድ ሚሊየን አርሶ አደሮች እና ነጋዴዎች እያረሱና እየነገዱ ወደሚኖሩበት ቀያቸው መልሶ ማኖር ነው የሚቀለው፤ ስለዚህ ዋነኛ መፍትሔው የዚህ ጉዳይ ወደ ቀያቸው መመለስ መሆኑን አስምረንበታል” ብለዋል።

https://addisstandard.com/Amharic/?p=7832
👍184😁2
2025/07/08 16:21:42
Back to Top
HTML Embed Code: