Telegram Web Link
የሩሲያው ቅጥረኛ ተዋጊ ቡድን በማሊ ያለውን 'ተልዕኮ አጠናቆ' ሊወጣ መሆኑን አስታወቀ!

የሩሲያው ቅጥረኛ ተዋጊ ቡድን ፣ቫግነር በማሊ ያለውን 'ተልዕኮ አጠናቆ' ከአገሪቱ ሊወጣ መሆኑን አስታወቀ።ቫግነር በምዕራባዊቷ አፍሪካዊቷ አገር ማሊ ከአውሮፓውያኑ 2021 ጀምሮ ከአገሪቱ መከላከያ ሰራዊት ጋር በመጣመር ጽንፈኞችን ለመምታት እየሰራ ነበር።

ቫግነር "ከማሊ ሕዝብ ጎን በመሆን ሽብርተኝነትን ተዋግቷል፤ በዚህም ነዋሪዎችን ለዓመታት ሲያሸብሩ የነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች እና አዛዦቻቸውን ገድያለሁ" ሲል በቴሌግራም ገጹ አስታውቋል።

ቫግነር ከአገሪቱ እንደሚወጣ ያስታወቀው የማሊ ወታደሮች ከአንድ ሳምንት ባነሰ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የከፋ ጥቃት ከደረሰባቸው በኋላ በአገሪቱ ማዕከል ከሚገኘው ትልቅ የጦር ሰፈር መውጣታቸውን የሚገልጹ ዘገባዎች እየወጡ ባለበት ወቅት ነው።ማሊ ለአስርት ዓመታት ከእስላማዊ ታጣቂዎች ጋር ስትታገል ቆይታለች።

@YeneTube @FikerAssefa
ፀረ ጦርነት ዘመቻ ዛሬ በበይነመረብ ተጀምሮል።

በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ተመልካቾች በተከታተሉት ዉይይት ላይ የሃገሪቱ የተለያዩ አቆም ያላቸዉ ፖለቲከኞች እና ትጥቅ ትግል ላይ ያሉ ሃይሎች ተሳትፈዉበታል ፡፡

በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱት የፋኖ ሃይሎችን በመወከል ዘመነ ካሴ ንግግር አድርጎል ፡፡

በኢንተርኔት መቆረጥ ምክንያት ያልተመለከታችሁ
ቀጣዩን ሊንክ በመጠቀም መመልከት ትችላላችሁ👇👇👇
https://youtu.be/gkZic7SDHv8?si=ruIgaSJRBUiBkh7x
በነገው ዕለት በወላይታ ድቻ እና ሲዳማ ቡና መካከል የሚደረገው የኢትዮጵያ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት በዝግ እንዲካሄድ ተወስኗል።

ጨዋታው በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ETV) በቀጥታ ይተላለፋል።

መች ይሆን ህዝቡ እግርኳስ በነፃነት በስቴድየም ማየት የሚጀምረው??
የህክምና ጓንት እና ስሪንጅ ከውጪ ማስገባት ማቆሙን የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት አስታወቀ።

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዱልቃድር ገልገሎ እንደገለጹት በአገሪቱ ውስጥ ሁለት የጓንት አምራቾች ያሉ ሲሆን፣ ዘንድሮ ሙሉ በሙሉ የህክምና ጓንት በአገር ውስጥ ምርት እየተሸፈነ ነው፡፡

እንደ ጋዜጣ ፕላስ ዘገባ በሙሉ አቅሙ እያመረተ የሚገኝ አንድ ስሪንጅ ፋብሪካ በድሬዳዋ ላይ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ ፋብሪካው ምርቶቹን ለአገልግሎቱ እያቀረበ በመሆኑ ከአንድ ዓመት በፊት ጀምሮ ስሪንጅ ከውጪ ማስገባት አቁመናል ብለዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ሲዳማ ቡና ሻምፒዮን ሆነ


በኢትዮጵያ ዋንጫ ፍጻሜ ሲዳማ ቡና ወላይታ ድቻን  2 ለ 1 በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆኗል።
በአዲስ አበባ ስቴዲየም በተደረገው ጨዋታ ሀብታሙ ታደሰ እና የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና አጥቂ መስፍን ታፈሰ የሲዳማ ቡናን ግቦች  አስቆጥረዋል።

በዝግ ስቴዲየም በተደረገው የፍጻሜ ጨዋታ ካርሎስ ዳምጠው የወላይታ ድቻን ብቸኛ ግብ ያስገኘ ተጫዋች ሆኗል።

ሲዳማ ቡና የኢትዮጵያ ዋንጫን ማንሳቱን ተከትሎ በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ  በቀጣይ አመት በካፍ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን የሚወክልም ይሆናል።

ወላይታ ድቻ በ2ኛው አጋማሽ ከተደጋጋሚ ሙከራዎች ባሻገር ግብ ቢያስቆጥርም ከጨዋታ ውጭ በሚል ተሽሮበታል።

በ2010 ዓ.ም በተሳተፈበት የኮንፌደሬሽን ዋንጫ በ1ኛው  ዙር ቅድመ ማጣሪያ የግብጹን ጠንካራ ክለብ ዛማሊክ በደርሶ መልስ አሸንፎ የነበረው ወላይታ ድቻ በድጋሜ በአፍሪካ መድረክ የሚሳተፍበትን ዕድል ሳይጠቀምበት ቀርቷል።

የኢትዮጵያ ዋንጫ ከአራት አመታት መቋረጥ በኋላ በ2016 ዓ.ም መጀመሩም ይታወሳል።

@Yenetube @Fikerassefa
Ethiopian Building Code Standards
Private Sector Engagement in Code Revision: Week 2 Sessions


We’re back with five expert-led sessions in Week 2 of our 14-part workshop series, continuing the dialogue between private sector professionals and code developers:

🏢 Building Facility Management
🧯 Fire Safety & OHS
🏗 Structural Design Fundamentals
🚿 Building Plumbing Systems
📐 Spatial Design in Buildings


📅 June 10, 12 & 14, 2025
📍 The Urban Center
🖥 Also, live on TUC Facebook page & Google Meet
☕️ Free sessions with refreshments

Participants are encouraged to register only for the sessions most relevant to them.

📲 Register now: https://forms.gle/NewtRdbnasiUFW6r7
🔗 Google Meet links will be shared 30 minutes before each session.

Many thanks to our partners for making this possible!

#EBCS #CodeRevision #BuiltEnvironment #ECA #CoTBE #TUC #FireSafety #StructuralDesign #Plumbing #FacilityManagement #SpatialDesign
Forwarded from YeneTube
#ከቴምር ሪልስቴት
7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ መሀል ሣር ቤት አፓርትመንት እና ሱቅ ፒያሳ ለሽያጭ ያወጣነው 

🎯የክፍያ አማራጮች 40/60 ለሚከፍል

👉1መኝታ 75ካሬ 4,815,000ብር ሙሉ ክፍያ
👉2መኝታ 94ካሬ 6,034,800ብር ሙሉ ክፍያ
👉2መኝታ 103ካሬ 6,612,600ብርሙሉክፍያ
👉3መኝታ 132ካሬ 8,474,400ብር ሙሉ ክፍያ
👉3መኝታ 146ካሬ 9,373,200ብር ሙሉ ክፍያ 9,373,000ብር 

‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ 
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
       👇👇👇👇👇👇
     +251939770177
     +251996856273
https://www.tg-me.com/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
Forwarded from YeneTube
🌺🌸  #ግእዝን_በርቀት 🌺🌸


የግእዝን ቋንቋ በ፲፬ ዙሮች እስካኹን ለብዙ ሺሕ ተማሪዎች በቀላል መንገድ ማስተማር ተችሏል። አኹን ደግሞ በ፲፭ኛ ዙር በቴሌግራም ለኹለት ወራት ( ከሐምሌ ፩ እስከ ነሐሴ ፴፥ ፳፻፲፯ ዓ.ም. በተመጣጣኝ ክፍያ ለጀማሪ ተማሪዎች የሚኾን ትምህርት ለመስጠት ስለታሰበ ባሉበት ኾነው በቀላሉ መማር ከፈለጉ አኹኑኑ
                  
@geezdistance15


የሚለውን የቴሌግራም የመጠቀሚያ ስም በመጫን ወደ ትምህርት መስጫ ቻናሉ መግባት ይችላሉ።



🌺🌸  #ግእዝን_በርቀት 🌺🌸
ዜና: "#በኢትዮጵያ የሚገኙ አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ብሔራዊ ጥቅምን ማስቀደም ሲገባቸው የግል ፍላጎታቸውን ለማሳከት የሚሰሩ ናቸው" - ጠ/ሚኒስትር አብይ

"በኢትዮጵያ የሚገኙ አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን የግል ፍላጎታቸውን ለማሳከት” የሚሰሩ ናቸው ሲሉ ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ተቹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሳለፍነው ሳምንት በበርካታ የሀገሪቱ የመንግስት መገናኛ ብዙኃን በአራት ክፍል በተላለፈው ቃለምልልሳቸው በመጨረሻው ክፍል ላይ የመገናኛ ብዙሃን ነጻነትን አስመልክተው ገለጻ አድርገዋል፡፡

አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን የግል ፍላጎታቸውን ለማሳካት ነው የሚሰሩት ሲሉ የተቹት ጠ/ሚኒስትሩ "እነዚህ መገናኛ ብዙሃን የሃሰት መረጃዎችን እና የፈጠራ ዜናዎችን በማሰራጨት ሕዝቡን ለማሳሳት ሲሞክሩ ተስተውለዋል” ብለዋል።

በገለጻቸውም "ሚዲያ ልክ እንደ እሳት ነው፤ ያጠፋልም ያለማልም፤ እንደቢላዋ ለጥሩ አሊያም ለመጥፎ ነገር ሊውል የሚችል ነው" ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ "በዓለም ላይ ገለልተኛ የሚባል ሚዲያ  የለም" ሲሉ ተደምጠዋል፣ “መገናኛ ብዙሃን ብሔራዊ ጥቅምን ያስቀደመ ዘገባ ሊሰሩ ይገባል” ሲሉም አሳስበዋል።

መገናኛ ብዙሃንን ለመልካም አላማ ከተጠቀምናቸው ውጤታቸው ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው፥ በተቃራኒው ሚዲያዎች ለጥፋት አላማ የሚውሉ ከሆነ ከፍተኛ አደጋን ያስከትላሉ ሲሉም ገልጸዋል።

በተጨማሪም "የለውጡ መንግስት ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው ነጻነት በኢትዮጵያ በርካታ አዳዲስ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ከ60 በላይ በሚሆኑ ቋንቋዎች እየተላለፉ ይገኛል" ብለዋል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa
ኢትዮጵያ መድን በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ ሻምፒዮን ሆነ

ኢትዮጵያ መድን እግር ኳስ ክለብ የ2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ሆኗል፡፡

በ34ኛ ሳምንት የኢትጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሀ ግብር 2ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው ኢትዮጵያ ቡና ከመቐለ ሰባእንደርታ ነጥብ መጋራቱን ተከትሎ መድን ሻምፒዮን መሆኑን አረጋግጧል፡፡

ኢትዮጵያ መድን ወደ ፕሪሚየር ሊግ በተመለሰ በ2ኛ አመቱ ሊጉ ሊጠናቀቅ 3 ጨዋታ እየቀረው በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ አሳክቷል፡፡

ከአሁን በፊት ከጅማ አባጅፋር እና መቐለ ሰባእንደርታ ጋር የሊጉን ዋንጫ ያነሳው የወቅቱ የመድን አሰልጣኝ ገብረ መድህን ሀይሌ ከሶስት የተለያዩ ክለቦች ጋር ሻምፒዮን በመሆንም ታሪክ ሰርቷል፡፡

ኢትዮጵያ መድን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ያነሳ 10ኛው ክለብም ሆኗል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና መሰጠት ጀመረ

ዘንድሮ በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠው የቅድመ ምረቃ የመውጫ ፈተና መሰጠት መጀመሩን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ፈተናው ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሰኔ 10 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

በ51 ዩኒቨርሲቲዎች በተዘጋጁ 87 የፈተና ማዕከላት ፈተናው እንደሚሰጥም ተናግረዋል፡፡

በዚህ ዓመት እየተሰጠ ባለው የመውጫ ፈተና 190 ሺህ 787 ቅድመ መደበኛ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ጠቅሰዋል፡፡

ከዚህም ውስጥ 102 ሺህ 360 ተማሪዎች ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወስዱ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
የቤት ውስጥ ሰራተኞችን የሚመለከተው ኮንቬንሺን 189 እንዲፀደቅ ጥረት እያደረግን ነው ሲል አንድነት ኢትዮጵያ የቤት ሰራተኞች ማህበር አስታወቀ።

የአንድነት ኢትዮጵያ የቤት ሰራተኞች ማህበር የህብረቱ ፕረዝደንት ሒሩት አበራ ስምምነቱ ኢትዮጵያ ከፈረመች አመታት ቢቆጠሩም እስካሁን ተግባራዊ አልሆነም ብለዋል። ፕሬዚዳንቷ የቤት ሰራተቾች በማህበረ ተደራጅተው ስለመብቶቻቸው ያለመጠየቅ፣እንደ ማኒኛውም ሰራተኛ የሰራተኞችን መብት በሚያስጠብቀው በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ 1156 ውስጥ እንዲሁም በሌልች የህግ ማእቀፍ ውስጥ ያለመካተታቸውና ያለመጠየቃቸው እስካሁን አዋጁ ሳይፀድቅ ቆይቷል  ብለዋል።

ስለቤት ውስጥ  ሰራተኞች የሚያወሳውን አለም አቀፍ ስምምነት 189 ኮንቬንሺን ለምን አልተፈረመም ብለን ስንጠይቅም ከሀገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ ጋር የማይጣጣም ነው ይባላል በህግ አውጪው በኩል ሲሉም አስረድተዋል። መመሪያው ፀድቆ በስራ ላይ ቢውል፣ የቤት ሰራተኞችን መሰረታዊ መብቶች የሚያስጠብቅ፣ ከአሰሪዎቻቸው ጋር የሚኖራቸውን ግንኙነት የሚያስተካክልና የስራ ከባቢያቸውንም ምቹ እንዲሆን የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡

ከሁሉም በላይ ግን፣ መመሪያውና የስራ ቅጥር ውሉ፣ የቤት ሰራተኞች ጉልበታቸው ሲደክም እንደ ጡረታ ያሉ የማህበራዊ ዋስትና አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያደርግ ነው በማለት ገልፀዋል፡፡በአሁን ወቅት የቤት ሰራተኞች በስራና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች የሚዋዋሉት ውል ምንም ዓይነት ህጋዊ መሰረት የሌለው፣ ሐላፊነትን የማይሰጥና መብትና ግዴታን የማይለይ ነው፡፡

ሆኖም ይህን ችግር ለመፍታት ነው ማህበሩ የተቋቋመው ያሉ ወ/ሮ ህሩት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራን እንገኛለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡ከአራት አመታት በፊት በተደረገ የዳሰሳ ጥናት መሰረት፣ በሀገሪቱ ወደ 5 ነጥብ 6 ሚሊዮን የሚገመቱ ሰራተኞች እንዳሉ የገለፁት ፕሬዚዳንቷ፣ እነዚህ ዜጎች የተለያዩ ችግሮች እንደሚደርሱባቸውም በጥናት አረጋግጠናል ብለዋል፡፡ 

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የተጀመሩ የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ እስከ 1.5 ትርሊዮን የሚገመት ሀብት ያስፈልጋል ተባለ

#ኢትዮጵያ የተጀመሩ የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ እስከ 1.5 ትርሊዮን የሚገመት ሀብት እንደሚያስፈልግ የገንዝብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ ገለጹ።

የገንዝብ ሚኒስትር ደኤታው እዮብ ይህን ያሉት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተካሄደው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 33ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው።

የምክር ቤት አባላቱ በሀገሪቱ ለተጀመሩት የመንገድ ፕሮጀክቶች ትልቅ ማነቆ የሆነውን በጀት መፍታት የሚያስችል የብድር ስምምነቶችን ገንዘብ ሚኒስቴር ሊያመጣ እንደሚገባ ጠይቀዋል።

በተጨማሪም የመንገድ መሰረተ ልማቶችን ለማስፋፋት ከአጋር የልማት ድርጅቶች ሀብት የማሰባሰብ ስራ በስፋት ሊሰራ እንደሚገባ በምክር ቤት አባላቱ አንስተዋል።

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ፤ ከተለያዩ የብድር አቅራቢ ተቋማት በተገኘ ብድርና ከልማት አጋሮች በተገኘ ድጋፍ በርካታ መንገዶች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።

ሆኖም በምክር ቤቱ በቂ አይደለም የተባለውን በመውሰድ የሀገር ውስጥ ገቢን ለማሳደግ እና ከልማት አጋሮች ሀብት ማሰባሰቡን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ ተናግረዋል።

አጠቃላይ እንደሀገር የተጀመሩትን የመንገድ ፕሮጀክቶች ለማጠናቀቅ ከአንድ ነጥብ ሶስት ትሪሊዮን እስከ አንድ ነጥብ አምስት ትሪሊዮን የሚገመት ሀብት እንደሚያስፈልግ አስታውቀዋል።

ችግሩን ለመፍታት የገንዘብ ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ማድረጉን አንስተው፤ ዘርፉን ለማሳደግ የመንግስትና የግሉን ዘርፍ አጋርነት ያስፈልጋል ብለዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ ልማት ባንክን ጨምሮ፤ ሌሎች አበዳሪ ተቋማት ከዚህ ቀደም ሲሰጡት የነበረውን ብድር ለማስቀጠል ፍቃደኛ ባለመሆናቸዉ የግብርናውን ዘርፍ ለማሳደግ በማደረገው ጥረት ላይ እንቅፋት ሆኖብኛል ሲል ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ ።

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የግብርና መዋለ ንዋይ ምርትና ግብይት መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ደረጀ አበበ እንደገለጹት፤ እንደ ሀገር የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ መደረጉም ምጣኔ ሀብቱ ላይ የራሱን ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል፡፡

"ይህንን በመቅረፍ የግብርና ሙዓለ ንዋዩን ለማሳደግ ደግሞ፤ አበዳሪ ባንኮች የተለያዩ ምክንያቶችን በማቅረብ ብድር ከልክለዋል" ሲሉ ተናግረዋል።

እንደ አሐዱ ዘገባ እንደ ሀገር ባጋጠመ የገንዘብ እጥረት፣ በጸጥታ ችግርና በመሠረተ ልማት አለመሟላት ዘርፋን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ላይ ተግዳሮት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ባለሃብቶችም ከገቡበት ሥራ በመውጣት በተለያዩ ሕገ-ወጥ ሥራዎች ላይ በመሰማራቸው በምክንያት፤ ተጨባጭ የሆነ ለውጥ እንዳያመጡ እንቅፋት እየሆነ እንደሚገኝ ተናግረዋል ፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from Hamrin A
🗝️ እጅግ አመቺ በሆነ አከፋፈል የቤት ባለቤት ይሁኑ

60% የባንክ ብድር የተመቻቸላቸውን ቤቶች በልዮ ቅናሽ

❇️ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው DMC Real Estate የመጨረሻው መንደር ወቅቱን ባገናዘበ  ቅናሽ ዋጋ በተለያዩ ካሬ አማራጮች አቅርቦሎታል : :

⭐️ከሀያ አምስት ዓመታት በላይ ግንባታ ላይ ከቆየ አንጋፋ ድርጅት

📍አድራሻ - በመሀል ከተማ ለቡ መብራት-ሀይል

💸ቅድመ ክፍያ
   
    💎ባለ 1 መኝታ  በ 431 ሺ ብር
    💎ባለ 2 መኝታ  በ 619 ሺ ብር
    💎ባለ 3 መኝታ  በ 751 ሺ ብር
    💎ባለ 4 መኝታ  በ 1,051,626 ብር 

🛍️🛒ሱቆች ከ 43 ካሬ ጀምሮ

🏦60% የባንክ ብድር የተመቻቸላቸው (እየኖሩበት ወይም አከራይተውት እስከ 20 አመት ቀስ ብለው የሚከፍሉት)

➡️በ 8% ቅድመ ክፍያ

➡️እስከ 30% በሚደርስ ቅናሽ ዋጋ (ለ20 ቤቶች) በመጠቀም የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ


➡️☎️ 09 31 14 82 42

➡️@Novi_03 (telegram)

➡️Whatsapp Link-
https://wa.me/251931148242
ለ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ዕጩዎችና መራጮች በኦንላይን መመዝገብ የሚችሉበት ሶፍትዌር ተዘጋጀ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ መራጮችና ዕጩዎች ካሉበት ሆነው በኦንላይን መመዝገብ የሚችሉበት ሶፍትዌር ማበልፀጉን አስታወቀ፡፡

የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ፤ ያለፉት ሥድስት የኢትዮጵያ የምርጫ ሂደቶች ማንዋል እንደነበሩ ጠቅሰው፤ በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ መራጮችም ሆኑ ዕጩዎች ካሉበት ሆነው በኦንላይን መመዝገብ የሚችሉበትን ሶፍትዌር ማበልፀግ መቻሉን አስታውቀዋል፡፡

ሰብሳቢዋ ይህን ያሉት፤  በዛሬው ዕለት በቴክኖሎጂው አሥተዳደር ሥርዓት ላይ ቦርዱ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ባደረገው ውይይት ነው።

ወ/ሮ ሜላትወርቅ ሂደቱ ኢትዮጵያ በምርጫ ሥርዓቷ “አንድ እርምጃ ወደፊት መራመድ የሚያስችላት” ከመሆኑ ባለፈ፤ በምርጫው ሂደት ላይ “ግልፅነትና ተጠያቂነትን” ለማስፈን ያስችላል ብለዋል።


የውይይቱ ተሳታፊ የፖለቲካ ፓርቲዎች በበኩላቸው ሶፍትዌሩ ጊዜ ቆጣቢና እንግልት የሚቀንስ መሆኑን ጠቅሰው፤ ለግልፅነትና ለተጠያቂነት ምቹ መደላድል እንደሚፈጥር ተናግረዋል ሲል ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል፡፡

ባሳለፍነው ወር ቦርዱ ለ7ኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ፤ ሁለተኛ ዙር የምርጫ ጣቢያዎችን በዲጂታል ሲስተም የመመዝገብ ሥራ ማከናወኑን ማስታወቁ ይታወሳል።

ቦርዱ ለ7ኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን በማከናወን ላይ መሆኑን ገልጾ ከዚህ በፊት ከተካሄዱት ምርጫዎች በአፈጻጸም ቀልጣፋና ጊዜው የሚጠይቀውን ዘመናዊነት የተከተለ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ጠቁሟል።

@Yenetube @Fikerassefa
ኦነግ አዲስ አበባ የሚገኘው ዋና ቢሮው ከአራት ዓመታት በኋላ እንደተመለሰለት አስታወቀ!

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ከነሃሴ 2012 ዓ.ም ጀምሮ ተዘግቶ የነበረውን እና በአዲስ አበባ የሚገኘውን ዋና ቢሮው በይፋ እንደተመለሰለት የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ለሚ ገመቹ ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።

"በይበልጥ የአዲስአበባ ከተማ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የቻለውን ያህል ጫና ሲያደርግ ነበረ" ያሉት አቶ ለሚ የምክር ቤቱ እንዲሁም ሌሎች ተወካዮች በተገኙበት ቢሯችን ለማስመለስ ችለናል ብለዋል።

አክለውም "ወደ ቢሯችን እንድንመለስ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የራሱን አስተዋጽኦ አድርጓል" ሲሉ አስታውቀዋል።አያይዘውም ፓርቲያቸው ከ200 በላይ ጽህፈት ቤቶች እንዳሉት ጠቅሰው በቀጣይ በተዋረድ የተዘጉ ጽሕፈት ቤቶቻችን እንዲከፈቱልን ውትወታችን ይቀጥላል ብለዋል። ወደፊትም አደረጃጀቶቻችንን ለማጠናከር ተስፋ አድርገን እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል።

Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
2025/07/05 12:20:16
Back to Top
HTML Embed Code: