በፎቶ፡ በትግራይ ክልል በመቀለ ከተማ “አምስተኛ ክረምት በሸራ መጠለያ ማሳለፍ ይብቃን” በሚል መሪ እየተካሄደ ያለው ሰላማዊ ሰልፍ ለሶስተኛ ቀን ዛሬም ሰኔ 13 ቀን 2017 ዓ.ም እየተካሄደ ይገኛል።
ሰልማዊ ሰልፉ በትግራይ ጦርነት ምክንያት የተፈናቆሉ ዜጎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ለመጠየቅ የተጠራ ነው።
በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ውሳኔ መሰረት የመንግስት ሠራተኞች ስራቸውን በማቆም በሰልፉ ታደመዋል።በተመሳሳይ የትግራይ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እና የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ለሰልፉ ያላቸውን አጋርነት በመግለጽ ተከታዮቻቸው በከተማዋ ሮማናት አረባባይ በሚካሄደው ሰልፍ እንዲሳተፉም ጠይቀዋል። በመቀለ ለተከታታይ ሶስት ቀናት የተካሄደው ሰልፉ ዛሬ የመርሃ ግብሩ የመጨረሻው ቀን ነው።
Via AS
@YeneTube @FikerAssefa

በወንጀል የተገኘ ንብረት ህጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ከፍርድ ቤት ፍቃድ ውጪ የሚደረግ ምርመራን እንደማይፈቅድ የፍትህ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡
የፍትህ ሚኒስቴር ይህን የተናገረው ባለፈው ሰኔ 10 ቀን በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ባጸደቀው በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ተሻሽሎ የቀረበውን አዋጅ ይዘት በተመለከተ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡መስሪያቤቱ አዋጁን አንዳንዶች የተረዱበት መንገድ ልክ አይደለም ብሏል፡፡
ስለ አዋጁ ማሻሽያ፣ ይዘት እና ምንነት ማብራርያ የሰጡት የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አማረ ኢትዮጵያ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ንብረትን ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀልን ለመቆጣጠር ተቋም ያቋቋመችው በ2002 ዓ.ም ነው ብለዋል፡፡በዚህም የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት መቋቋሙን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ ተልዕኮው ደግሞ ሀገራችን የአለም አቀፍ የፋይናንስ ድርጊት ግብረሃይል የሚባለው ምከረሃሳብን መተግበር ከሚጠበቅባቸው ከ200 በላይ ሀገራት አንዷ በመሆኗ ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡
የፋይናንስ ድርጊት ግብረሃይል 40 ቀጥታ አባል አገራት አሉት፡፡ እንዲሁም ደግሞ ዘጠኝ ቀጠናዊ አባል ሀገሮች አሉ ተብሏል። ከአፍሪካም ሶስት የምስራቅ እና ደቡቡን የሚያካትተው 21 አባል ሀገሮችን የያዘው የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካን የያዘው ኢስተርን ነደ ሶውዘርን አፍሪካ አንቲ ላውንድሪ ግሩፕ (eastern and southern africa anti money laundry group) ይባላል፡፡ ኢትዮጵያም ከ21 አባል ሀገራት አንዱ ናት ሲሉ ተናግረዋል፡፡
እነዚህ አባል ሀገራት የፋይናንስ ድርጊት ግብረሃይል ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀልን ለመከላከል የሚያስችሉ 40 ምክረ ሃሳቦችን ይተገብራሉ፤ በየአምስት ዓመቱም የእርስ በእርስ ግምገማ ያካሂዳሉ ያሉት አቶ ሙሉቀን ሶስተኛውም ገምገማ በመጪው ዓመት ይካሄዳል ብለዋል፡፡እነዚህን ምከረ ሃሳቦች ተግበባራዊ ከምናደርግባቸው ህጎች አንዱ ባለፈው የተሸሻለው በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ነው ሲሉ በመግለጫቸው ጠቁመዋል፡፡
የተሸሻለው አዋጅ ኢትዮጵያ ለ12 ዓመታ ስተገለገልበት መቆየቷን ያስረዱት ዳይሬክተሩ የተሸሻለበት ምክንያት ደግሞ አለም አቀፉ የፋይናንስ ድርጊት ግብረሃይል ምክረሃ ሰቦቹን እያሻሻለ በመሄዱ ነው ብለዋል፡፡በዚህም የተሸሻሉ ምከረ ሃሳቦች ስላሉ እነሱን ሊመልስ የሚችል ህግ በማስፈለጉ እና ግብረ ሃይሉም ወንጀሎች እየተለዋወጡ ስለመጡ ሀገራት እነሱን ለመከላከል የሚመጥን የህግ ማዕቀፍ እንዲኖራቸው ስለሚያዝ ነዉ ብለዋል፡፡
የቀድሞው አዋጅ አመንጪ ወንጀሎችን በዝርዝር አያስቀምጥም ይህም አንዱ የአዋጁ ችግር ነበር ብለዋል የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙለቀን አማረ፡፡ በፍትህ ሚኒስቴር የህግ ጥናት እና ማርቀቅ ዳይሬክተር ጀነራል አቶ አዲስ ጌትነት በበኩላቸው አዲሱ አዋጅ ከመደበኛ የወንጀል መርመራ ሂደት የወጣ መንገድን የሚከተል እንደሆነ ሰው ሊረዳው ይገባል ብለዋል፡፡
አዲሱ አዋጅ ልክ በመደበኛው የምርመራ ሂደት እንደሚደረገው ተጠርጣሪዎችን በፍርድ ቤት መያዣ መያዝ ፣ሰነዶችን ማሰባሰብ፣ ምስከሮችን መስማት እና መሰል ሂደቶችን አይከተልም ያሉት አቶ አዲስ ወስብስብ የሆኑ ወንጀሎችን ከመሰረቱ ለመለየት የሚስችል የምርመራ ሂደትን የሚከተል ነው ብለዋል፡፡
ለምሳሌም መርማሪው አካል ወንጀለኞችን መስሎ ተቀላቅሎ ወይንም አብሮ በመስራት፣ ተባባሪ መስሎ አብሮ ውሎ በማደር፣ ሲሸጡ ገዢ መስሎ፣ ሲገዙ ሻጭ መስሎ ሊሆን ይችላል ሲሉ በፍትህ ሚኒስቴር የህግ ጥናት እና ማርቀቅ ዳይሬክተር ጀነራል አቶ አዲስ ጌትነት ተናግረዋል፡፡
ምርመራውን የሚየካሂደው አካል ምረመራ ማድረግ የሚችለው የፍርድ ቤት ተዕዛዝ ካገኘ ብቻ ነው ያለው የፍትህ ሚኒስቴር እንደሚባለው አዋጁ ተጠርጣሪን አስሮ እያሰቃዩ አይመረምርም ይህም ፍጹም ስህተት ነው ብሏል፡፡
በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን የሚመረምር ሰው፤ በምርመራ ወቅት ከአቅሙ በላይ በሆነ ምክንያት ከግድያ ውጪ የትኛውንም ዓይነት ወንጀል ቢፈጽም ተጠያቂ የማያደርግ አዋጅ ከሰሞኑ መፅደቁ ይታወሳል፡፡ይህም መርማሪዎችን ወንጀል እንዲፈፅሙ በር ይከፍታል በሚል ከምክር ቤት ትችት ሲቀርብበት ነበር።
Via Sheger
@YeneTube @FkkerAssefa

በግብርና ምርቶች ዘርፍ የተሰጠው የደላላነት ፈቃድ ሙሉ በሙሉ መሰረዙ ተገለጸ!
በግብርና ምርቶች ዘርፍ የተሰጠው የደላላነት ፈቃድ ሙሉ በሙሉ መሰረዙን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴዔታ አብዱልሃኪም ሙሉ (ዶ/ር) በዘርፉ ምንም አይነት እሴት ሳይጨምሩ የንግድ ሥርዓቱን የሚረብሹ በርካታ ደላላዎች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም በእህል ምርት፣ በአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም በቁም እንስሳት ዘርፍ የተሰጠው የደላላነት ፈቃድ ሙሉ በሙሉ መሰረዙን ገልጸው፤ ከ3 ሺህ በላይ ደላሎች እና አገናኞች ላይ እርምጃ መወሰዱን ጠቁመዋል፡፡
ይህን ተከትሎ በቀጣይ በገበያው የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት በትኩረት ይሰራል ሲሉ መግለጻቸውን የዘገበው ኤፍ ኤም ሲ ነው፡፡
በተመሳሳይ በሲሚንቶ ገበያ ዘርፍ ነጻ የገበያ ሥርዓት በመዘርጋት “የሲሚንቶ ዋጋ ከግማሽ በታች እንዲቀንስ” መደረጉን አብራርተዋል፡፡የሲሚንቶ ግብይት ሥርዓትን ሲረብሹ የነበሩ ደላላዎችና በተለያዩ አካላት ስም ሲነግዱ የነበሩ ግለሰቦች ከዘርፉ እንዲወጡ መደረጋቸውንም አረጋግጠዋል፡፡

Forwarded from YeneTube
አቅመ ደካማወችን ሀረጋውያኖችን በነፃ
https://vm.tiktok.com/ZMSayMdXa
በተለያየ የጤና ችግር የሚሰቃዩትን እየ ፈወሰ
ደስታቸውን እየመለሰ የሚገኘውን የህክምና ተቋም https://vm.tiktok.com/ZMSay8eV2/
ሰወች እንዴት እንደተፈወሱ ሲመሰክሩ እንስማ እንይ ቻናሉን እንቀላቀል
https://vm.tiktok.com/ZMSaDEhoN
በስጋውይም ሆነ በመንፈስ ደውየ ከተቸገሩ መተው በመመርመር ይታከሙ ይፈወሱ
44ት አይነት በሽታወችን እየፈወስን እንገኛለን
አድራሻ አዲስ አበባ አየርጤና ወደካራ ናትራን ኩፓንያ ፊት ለፊት
ቁጥር ሁለት ባህርዳር ዲያስፖራ በአሮጌው አስፓልት መስጊዱ ፊት ለፊት
☎️ 0917040506
☎️0912718883
ይደውሉ ይምጡ ይታከሙ ይፈወሱ ይመስክሩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአልቤርቶ ቫርኔሮ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ፈር ቀዳጅ በነበሩት አልቤርቶ ቫርኔሮ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት የሀዘን መግለጫ መልዕክት፤ ከ1950ዎቹ ጀምሮ በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ፈር ቀዳጅ በነበሩት አልቤርቶ ቫርኔሮ ህልፈት የተሰማኝን ሀዘን ለመግለጽ እፈልጋለሁ ብለዋል።
ስራቸው የሀገራችንን የግንባታ ከባቢ እና ታሪካዊነት ያላቸው ምልክቶችን ላቅ ባለ ደረጃ የቀረፀ ነው ሲሉም ገልጸዋል።
ከታሪካዊ ስራዎቻቸው መካከል የአፍሪካ አዳራሽ (የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽን)፣ የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት፣ ሂልተን ሆቴል እና ሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚጠቀሱ አመልክተዋል።
እንዲሁም የጅማ አባጅፋር አውሮፕላን ማረፊያ ማሻሻያ፣ የአብርሆት ቤተመጻሕፍት፣ የአንድነት ፓርክ እና የብሔራዊ ቤተመንግሥት እድሳት ሥራ ይገኙበታል ነው ያሉት።
የሥራ ውርሳቸው በእነዚህ ብሔራዊ ምልክቶች እና በሚወክሉት የእድገት ትእምርት ሲታወስ ይኖራል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለነፍሳቸው ረፍትን፣ በረፍታቸው ላዘኑ ሁሉ መጽናናትን እንመኛለን በማለት ሀዘናቸውን ገልጸዋል።

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ለመሆን የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅቶችን ማጠናቀቁን ገለጸ!
#Ethiopia: ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቀጥሎ ሁለተኛው ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ለመሆን የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅቶችን ማጠናቀቁን፣ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አሥራት አፀደ ወይን (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ከአርባ በላይ የሚሆኑ ፖሊሲዎችንና መመርያዎችን ማዘጋጀታቸውን የተናገሩት አሥራት (ዶ/ር)፣ ራስ ገዝነትን ለመጠየቅ የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎች መጠናቀቃቸውን ተናግረዋል፡፡
ለዚህም ዓለም አቀፍና አገር አቀፍ ተሞክሮዎች መወሰዳቸውን የተናገሩት አሥራት (ዶ/ር)፣ ከአገር ውስጥ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ እንዲሁም ከውጭ ከተለያዩ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች አሉበት ብለዋል፡፡በቅርቡ የፈረንሣይ ዩኒቨርሲቲዎችን እንደሚጎበኙና ከአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ስለራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ በርካታ ተሞክሮዎችን እንደተገኙ አብራርተዋል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopianreporter.com/142387/

Forwarded from The Urban Center ( Kebet Eske Ketema)
Ethiopian Building Code Standards
Private Sector Engagement in Code Revision: Week 3 Sessions
We’re continuing our 14-part expert-led workshop series with four important sessions in Week 3:
🧱 Geotechnical Properties & Structures
🌍 Seismic Design & Earthquake Resistance
🏗 Steel & Composite Structures
🪟 Aluminum & Glass Design
📅 June 17, 19, & 21, 2025
📍 The Urban Center
🖥 Also streaming live on TUC Facebook page & Google Meet
☕️ Free sessions with refreshments
✨ Participants are encouraged to register only for the sessions most relevant to them.
📲 Register now: https://forms.gle/NewtRdbnasiUFW6r7
📩 Google Meet links will be shared 30 minutes before each session.
A big thank you to all our partners for making this series possible!
#EBCS #CodeRevision #BuiltEnvironment #ECA #CoTBE #TUC #Geotech #SeismicDesign #StructuralEngineering #FacadeDesign

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ልእልት ብራይዳል ሰርጋችሁን የሚያድምቁትን ቅሚሶች አስግብተን እየጠብቅናችሁ ነው።
አዳዲስ የሚገቡ ሰርጐትን የሚያሳምሩ ቀሚሶች ለማግኘት ቴሌግራማችንን ይቀላቀሉ
https://www.tg-me.com/leeltbridal
Call us for early reservations
+251920017385
+251 97 899 5369
📍22 ከጐላጐል ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ
ፀጋ የገበያ ማዕከል 3ኛ ፎቅ C4A

#ቴምርሪልስቴት መሀል ሣር ቤት አፓርትመንት ሽያጭ
‼️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ መሀል ሣር ቤት AU አፓርትመንት ሽያጭ
👉1መኝታ 75ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 802,500ብር
ሙሉ ክፍያ 8,025,000ብር
👉2መኝታ 94ካሬ
10% ቅድመ ክፍያ 1,005,800ብር
ሙሉ ክፍያ 10,058,000ብር
👉2መኝታ 103ካሬ
10%ቅድ ክፍያ 1,102,100ብር
ሙሉ ክፍያ 11,021,000ብር
👉3መኝታ 132ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 1,412,400ብር
ሙሉ ክፍያ 14,124,000ብር
👉3መኝታ 146ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 1,562,200ብር
ሙሉ ክፍያ 15,622,000ብር
‼️ቀሪውን 90% በ 18ዙሪ ያለምንም ጭማሪ በብር የሚከፍሉት ነው
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
👇👇👇👇👇👇
+251939770177
+251996856273
https://www.tg-me.com/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177

“የሰላም ስምምነቱን በመጠቀም የፌደራል መንግስት በምዕራብ ትግራይ የህዝብ አሰፋፈር ለመለወጥ እየሰራ ነው” - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር
“የፌደራል መንግስት የፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት በጦርነት ሊያሳካቸው ያልቻላቸውን ግቦቹን ለማሳካት እየተጠቀመበት ነው” ሲሉ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አማኑኤል አሰፋ ገለጹ።
ስምምነቱን ተጠቅሞ “የተቆራረሰች ትግራይ እንድትኖር ለማድረግ፣ የአከባቢውን የህዝብ አሰፋፈር (demography) ለመቀየር” እየጣረ ነው ሲሉ ተችተዋል። አቶ አማኑኤል ይህንን የተናገሩት ሰኔ 13 ቀን 2017 ዓ.ም በመቀለ ከተማ ሮማናት አደባባይ በተካሄደው የክልሉ ተፈናቃዮች ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።
“በሰላማዊ መንገድ ሁሉንም የትግራይ ጥቅሞች ለማረጋገጥ የተቻለንን ሁሉ ጥረት እናደርጋለን ማለት በሰላማዊ መንገድ ካልተፈታ የትግራይ ክብር ተደፍሮ እና ሉዓላዊነቷም ተጥሶ ይቀራል ማለት አለመሆኑ ሊታወቅ ይገባዋል” ብለዋል።
ከመቀለ በተጨማሪ የመርሃ ግብሩ አካል የሆነ የትግራይ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው በአስቸኳይ እንዲመለሱ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ ሰኔ 13 ቀን 2017 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በሲውዘርላንድ ጀኔቫ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
@YeneTube @FikerAssefa
“የፌደራል መንግስት የፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት በጦርነት ሊያሳካቸው ያልቻላቸውን ግቦቹን ለማሳካት እየተጠቀመበት ነው” ሲሉ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አማኑኤል አሰፋ ገለጹ።
ስምምነቱን ተጠቅሞ “የተቆራረሰች ትግራይ እንድትኖር ለማድረግ፣ የአከባቢውን የህዝብ አሰፋፈር (demography) ለመቀየር” እየጣረ ነው ሲሉ ተችተዋል። አቶ አማኑኤል ይህንን የተናገሩት ሰኔ 13 ቀን 2017 ዓ.ም በመቀለ ከተማ ሮማናት አደባባይ በተካሄደው የክልሉ ተፈናቃዮች ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።
“በሰላማዊ መንገድ ሁሉንም የትግራይ ጥቅሞች ለማረጋገጥ የተቻለንን ሁሉ ጥረት እናደርጋለን ማለት በሰላማዊ መንገድ ካልተፈታ የትግራይ ክብር ተደፍሮ እና ሉዓላዊነቷም ተጥሶ ይቀራል ማለት አለመሆኑ ሊታወቅ ይገባዋል” ብለዋል።
ከመቀለ በተጨማሪ የመርሃ ግብሩ አካል የሆነ የትግራይ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው በአስቸኳይ እንዲመለሱ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ ሰኔ 13 ቀን 2017 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በሲውዘርላንድ ጀኔቫ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
አቅመ ደካማወችን ሀረጋውያኖችን በነፃ
https://vm.tiktok.com/ZMSayMdXa
በተለያየ የጤና ችግር የሚሰቃዩትን እየ ፈወሰ
ደስታቸውን እየመለሰ የሚገኘውን የህክምና ተቋም https://vm.tiktok.com/ZMSay8eV2/
ሰወች እንዴት እንደተፈወሱ ሲመሰክሩ እንስማ እንይ ቻናሉን እንቀላቀል
https://vm.tiktok.com/ZMSaDEhoN
በስጋውይም ሆነ በመንፈስ ደውየ ከተቸገሩ መተው በመመርመር ይታከሙ ይፈወሱ
44ት አይነት በሽታወችን እየፈወስን እንገኛለን
አድራሻ አዲስ አበባ አየርጤና ወደካራ ናትራን ኩፓንያ ፊት ለፊት
ቁጥር ሁለት ባህርዳር ዲያስፖራ በአሮጌው አስፓልት መስጊዱ ፊት ለፊት
☎️ 0917040506
☎️0912718883
ይደውሉ ይምጡ ይታከሙ ይፈወሱ ይመስክሩ
https://vm.tiktok.com/ZMSayMdXa
በተለያየ የጤና ችግር የሚሰቃዩትን እየ ፈወሰ
ደስታቸውን እየመለሰ የሚገኘውን የህክምና ተቋም https://vm.tiktok.com/ZMSay8eV2/
ሰወች እንዴት እንደተፈወሱ ሲመሰክሩ እንስማ እንይ ቻናሉን እንቀላቀል
https://vm.tiktok.com/ZMSaDEhoN
በስጋውይም ሆነ በመንፈስ ደውየ ከተቸገሩ መተው በመመርመር ይታከሙ ይፈወሱ
44ት አይነት በሽታወችን እየፈወስን እንገኛለን
አድራሻ አዲስ አበባ አየርጤና ወደካራ ናትራን ኩፓንያ ፊት ለፊት
ቁጥር ሁለት ባህርዳር ዲያስፖራ በአሮጌው አስፓልት መስጊዱ ፊት ለፊት
☎️ 0917040506
☎️0912718883
ይደውሉ ይምጡ ይታከሙ ይፈወሱ ይመስክሩ
የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኢሶዴፓ) ምክትል ሊቀ መንበሩን ዶ/ር ራሄል ባፌን ከሃላፊነታቸው ማንሳቱን ገልጿል።
ፓርቲው ዶ/ር ራሄልን ያገደበት ምክንያት ከፓርቲው "ዕውቅና ውጪ" እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን በመጥቀስ ነው።
ባለፈው እሁድ ሰኔ 8 ቀን 2017 ዓ.ም. የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ፤ ዶ/ር ራሄል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የምክትል ሊቀ መንበርነት ሃላፊነት መያዛቸውን ጠቅሶ፣ "የፓርቲውን አሰራር ደንብ ባልተከተለ ሁኔታ እንዲሁም አንድ የፓርቲ አባል ሊወጣ የሚገባ ግዴታ" አለመወጣታቸውን አመልክቷል። አያይዞም፣ ገዢው ፓርቲና መንግስት ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል እንደሚያበረታቱ በማንሳት፣ ዶ/ር ራሄል ባፌ ግን "የአገሪቱን ሰላምና መረጋጋት በሚጎዳ መልኩ" ከስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ዕውቅና ውጪ "ፓርቲውን አደጋ ላይ የሚጥል" ዕንቅስቃሴ ማድረጋቸውን አስረድቷል።
ይህ "ፓርቲውን አደጋ ላይ የሚጥል ነው" ያለውን ዕንቅስቃሴ ፓርቲው ሲያብራራ፣ ከሰሞኑ በአቶ ልደቱ አያሌው አስተባባሪነት በበይነ መረብ በተካሄደውና በርካታ ፖለቲከኞች ከአገር ውስጥና ከባሕር ማዶ የተሳተፉበት የተቃውሞ ዕንቅስቃሴ ላይ ዶ/ር ራሄል ንግግር ማድረጋቸውንና መሳተፋቸውን ያነሳል። እንዲሁም በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን "መደመር ምን ፈየደ?" የሚልና የመሳሰሉ "ግልብ" ትችቶችና አባባሎችን "ተናግረዋል" ያለ ሲሆን፣ እነዚህም የፓርቲው ዕምነቶችና አቋሞች አለመሆናቸውን አስገንዝቧል።
በመሆኑም የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ "ባልተለያየ ድምጽ" ከሰኔ 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ዶ/ር ራሄል ባፌን ከፓርቲው ማገዱን አስታውቋል። በእርሳቸው ምትክ የፓርቲው ድርጅት ጉዳይ ሃላፊ የሆኑት አቶ አጫሞ ቦቄ፣ ምክትል ሊቀ መንበር ሆነው ፓርቲውን እንዲመሩ መወሰኑን ነው የገለጸው።
በመጨረሻም፣ "ዶ/ር ራሄል ባፌ በየትኛውም ፖለቲካዊና ሕዝባዊ መድረኮች በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጭ በማናቸውም መገናኛ ብዙሃን የምታቀርባቸው ሃሳቦችና አቋሞች፣ መግለጫዎችና ቃለ መጠይቆች ፓርቲያችንን የማይወክሉ መሆኑን እንገልጻለን" ብሏል፣ ኢሶዴፓ።

የነዳጅ ዋጋ በአለም ገበያ ሊወሰን ነው!
-መንግስት የነዳጅ ድጎማን ሙሉ በሙሉ ማንሳቱን አስታወቀ
ከሳምንት በፊት የበጀት ንግግራቸውን ያደረጉት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ መንግስት በድጎማ እንደማይቀጥል ማስታወቃቸው አይዘነጋም።የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፣ መንግስት ላለፉት ሶስት ወራት በነዳጅ ላይ ሲያደርግ የነበረውን ድጎማ ሙሉ በሙሉ አቁሟል። ይህ ውሳኔ ከግንቦት 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ቤንዚንና የአውሮፕላን ነዳጅን፣ ከግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ደግሞ ነጭ ናፍጣና ሌሎች የነዳጅ ውጤቶችን ይመለከታል ተብሏል።
መግለጫው እንደሚያመለክተው፣ መንግስት የውጭ ምንዛሬ በመጨመሩ ምክንያት ከሐምሌ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ለዝቅተኛ የህብረተሰብ ክፍል ሲል ጥቅል ድጎማ ሲያደርግ መቆየቱን አስታውቋል። ሆኖም፣ ከጎረቤት አገራት ጋር ባለው የዋጋ ልዩነት ምክንያት የሚፈጠረው የኮንትሮባንድ ንግድ እና በመንግስት ላይ ያለው ጫና ከፍተኛ በመሆኑ፣ ድጎማውን ለማንሳት ባለፉት 11 ወራት ሰፋፊ ስራዎች መከናወናቸውን አስታዉሷል።
በተጨማሪም፣ ሚኒስቴሩ በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጩ ያሉ የተሳሳቱ መረጃዎች የነዳጅ ማደያዎች ላይ ያልተገባ ወረፋ እየፈጠሩ መሆኑን ገልጿል፤ ይህም መንግስት ከድጎማው እንዳልወጣና ተጨማሪ ታክስ እንደሚጥል የሚገልጹ መረጃዎችን ውድቅ አድርጓል።
@YeneTube @FikerAssfa

እስራኤል በየቀኑ ለሚሳኤል መከላከያ 285 ሚሊየን ዶላር እያወጣች ነው ተባለ።
የእስራኤል ሚዲያና የቴክኖሎጂ ተቋማት ኢራን በዚህ መጠን ወደ እስራኤል ሚሳኤሎችን ማስወንጨፍ ከቀጠለች የመከላከያ ስርዓቷ በ12 ቀናት ውስጥ ሊዳከም ይችላል ሲሉ ግምታቸውን አስቀምጠዋል።
እስራኤል በመጀመሪያዎቹ የሁለት ቀናት ውጊያ እና መከላከል ብቻ 1.45 ቢሊየን ዶላር አውጥታለች ሲባል ኢራንን ለማጥቃት የምትጠቀምበት የጀት ነዳጅና ተተኳሽ ብቻ በቀን 300 ሚሊየን ዶላር ያስወጣታል ተብሏል።
የቀድሞ የእስራኤል ጦር ከፍተኛ አመራር ጀነራል ራሂም አሚናች እስራኤል በየቀኑ ለቀጥተኛ ወታደራዊ ወጪ ብቻ 725 ሚሊየን ዶላር እንደምታወጣ አንስተዋል።
እስራኤል ከኢራን በተጨማሪ ከሄዝቦላህ፣ ሃማስ እና ሁቲ ጋር ጦርነት ውስጥ የቆየች እና ያለች ሲሆን ኢኮኖሚዋ ጦርነቱን እስከመቼ እንደሚሸከመው የብዙሃኑ ጥያቄ ሆኗል።
@Yenetube @Fikerassefa
የእስራኤል ሚዲያና የቴክኖሎጂ ተቋማት ኢራን በዚህ መጠን ወደ እስራኤል ሚሳኤሎችን ማስወንጨፍ ከቀጠለች የመከላከያ ስርዓቷ በ12 ቀናት ውስጥ ሊዳከም ይችላል ሲሉ ግምታቸውን አስቀምጠዋል።
እስራኤል በመጀመሪያዎቹ የሁለት ቀናት ውጊያ እና መከላከል ብቻ 1.45 ቢሊየን ዶላር አውጥታለች ሲባል ኢራንን ለማጥቃት የምትጠቀምበት የጀት ነዳጅና ተተኳሽ ብቻ በቀን 300 ሚሊየን ዶላር ያስወጣታል ተብሏል።
የቀድሞ የእስራኤል ጦር ከፍተኛ አመራር ጀነራል ራሂም አሚናች እስራኤል በየቀኑ ለቀጥተኛ ወታደራዊ ወጪ ብቻ 725 ሚሊየን ዶላር እንደምታወጣ አንስተዋል።
እስራኤል ከኢራን በተጨማሪ ከሄዝቦላህ፣ ሃማስ እና ሁቲ ጋር ጦርነት ውስጥ የቆየች እና ያለች ሲሆን ኢኮኖሚዋ ጦርነቱን እስከመቼ እንደሚሸከመው የብዙሃኑ ጥያቄ ሆኗል።
@Yenetube @Fikerassefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ግዙፍ መርከብ እና ጀልባ በስዊዝ ካናል ተጋጩ
ትላልቅ ሸክሞችን እና የውሃ ውስጥ የመጥለቅያ መሳሪያዎችን ለመያዝ የተሠራው ሬድ ዜድ 1 የተሰኘው የጭነት መርከብ በመሪ ሲስተም ብልሽት ከጀልባ ጋር ተጋጭቷል።
እንደ ዘገባዎች ከሆነ መርከቡ በሰሜን አቅጣጫ በመጓዝ ላይ እያለ ከመንገዱ ወጥቷል። የነፍስ አድን ሠራተኞች ሁኔታውን በፍጥነት በመቆጣጠር ጉዳት እንዳይደርስ እና የተለመደው የስዊዝ ካናል ትራፊክ ፍሰት እንዳይስተጓጎል አድርገዋል።

ኢራን በእስራኤል ጥቃት የተገደሉባት የኒውክሌር ሳይንቲስቶች ቁጥር 10 ደረሰ
እስራኤል በሀገሪቱ ላይ ባደረሰችው ጥቃት ሌላ የኒውክሌር ሳይንቲስት መሞቱን፤ የኢራን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ይህም በእስራኤል የተገደሉ የኢራን ኒውክሌር ሳይንቲስቶችን ቁጥር 10 አድርሶታል።
ኢሳር ታባታቤይ የተባለው ተመራማሪ ሞት ይፋ የሆነው በቴህራን ሻሪፍ ዩኒቨርሲቲ ጋዜጣ ሲሆን፤ ኢሳር የዩኒቨርሲቲው የቀድሞ ተማሪ ነበር ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው።
ኢራን ቀደም ሲል ሌሎች ዘጠኝ የኒውክሌር ሳይንቲስቶች መሞታቸውን ማረጋገጧ ይታወሳል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ 'ቻናል 12' የተባለው የእስራኤል ሚዲያ እስራኤል በኢራን በጀመረችው ዘመቻ፤ 9 የኢራን የኑክሌር ሳይንቲስቶችን በአንድ ጊዜ፤ እንዲሁም አሥረኛውን የኒውክሌር ሳይንቲስት በሌላ ጥቃት መግደሏን ዘግቧል።

አሜሪካ የኢራን የኒውክሌር ጣቢያዎችን አጠቃች!
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ እንዳስታወቁት የሀገራቸው አየር ሀይል በሶስት የኢራን ኒውክሌር ጣቢያዎች ማለትም ፎርዶው፣ ናታንዝ እና እስፋሃን ላይ የአየር ጥቃት አድርሰዋል። የኢራንን የኒውክሌር አቅም ለማዳከም ፎርዶው የሚባለውን ጣቢያ ማውደም የምትችለው ብቸኛ ሃገር አሜሪካ እንደሆነች ሲነገር መቆየቱ የሚታወስ ነው።