Telegram Web Link
#ሞርያ
#እውነተኛ_የፍቅር_ታሪክ
#ክፍል8
#by_Adugna_Girma

@nahom20
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿»🌺̶̥✽̶┉┉┄┄

ይሄውልሽ አፎምያ ምን መሰለ ሚኪ ጋር እንደ ማትተዋወቁ ብትሆኑም እኔ ግን በመሃከላቹ የሆነ ነገር እንዳለ ጠርጥሬ ነበር ግን አንቺም ምንም ነገር ትደብቂኛለሽ ብዬ ሰለ ማላስብ በየዋህነት አመንኩሽ አንቺ ግን በጣም ድብቅ ሁነሻል ለምን እኔን መዋሸት እንደ ፈለግሽ ምንም አልገባኝም ብቻ አላውቅም ሰለ ሁሉም ነገር ይቅርታ ሁሉም ነገር የገባኝ ከረፈደ ነው ጓደኞችሽ ጋር ምን እንዳሰብሽ ጠፍቶኝ አደለም ትዝ ይልሻል ወደ ዚህ ልመለስ ሶስት ቀን ሲቀረኝ ስልክሽን ስጭኝ ባላንስ አልቆብኝ ነው ብዬ የተቀበልኩሽ ቀን ልክ ጓደኞቼን እውርቼ እንደ ጨረስኩ

በተደጋጋሚ ስልክ በመሃል ይገባ ነበር ልጠራሽ ስወጣ ሻወር ገብተሻል ላነሳው ስል ተዘጋ ረብቃ ነበረች ዋትስ አፕ ላይ ያወራቹህትን ሙሉ በሙሉ ሳይ በጣም ነበር የደነገጥኩኝ ብቻ ምንም ቢሆን ሚኪ እኮ ካንቺ አይበልጥብኝም እሱ ጋር ጭራሽ እንደ ማትተዋወቂ ነበር በሰአቱ የነገርሽኝ ምንም ቢሆን እህትሽ ነኝ ይሄን ነገር ልትደብቂኝ አግገባም ነበር አቃለው ሰው ውሎውን ይመስላል ጓደኞችሽ ጋር ምትፃፃፍያቸውን አንዴ ቆም

ብለሽ አስቢ ዛሬ የትኛውም ሶሻል ሚድያ ላይ እንዳለሽ ሁሉ ነገ በትዳር ህይወት ውስጥ መኖርሽን አትርሺ ዛሬ በምታደርጊያቸው ነገሮች ሁሉ አንድ ቀን ወይ ታፍሪበታለሽ ወይ ትደሰቺበታለሽ የዛሬ ህይወትሽ ለነገው ተስፋ ሊሆን እንጂ ዛሬን እያስደሰተሽ ነገን የሚያሸማቅቅሽ መሆን የለበትም ዛሬም ቢሆን ታናሽ እህቴ ነሽ እንደ ትናቱ ዛሬም እቆጣሻለሁ ስታጠፊ ዝም አልልሽም ስለ ሆነው ነገር ደግሞ ይቅር ብዬሻለሁ ይላል ልቤ ስንጥቅ አለ

መተንፈስ ራሱ አቃተኝ በራሴ በጣም አፈርኩ የእህቴ አስተዋይነት አየሁት ፊት ለፊቴ ሁና ይሄን ነገር ብትጠይቀኝ እንዴት እሆን ነበር አልኩ ምርር ቢለኝ ስቅ ስቅ ብዬ አለቀስኩ ሁሉም ነገር የራሴ ጥፋት ስለ ሆነ እኔው እንደ አበላሸሁት እኔው ማስተካከል አለብኝ ብዬ ወሰንኩ ግን ጓደኞቼ እኔ ጋር እስካሉ ድረስ ይሄን ነገር መቼም ማድረግ አልችልም ሲበዛ መውጣት የማንችልበት ሁኔታ

ውስጥ ነው ያለነው በሶሻል ሚድያ እኔነኝ ያለ ወንድ አያመልጠንም ከትንሽ እስከ ትልቅ ድረስ ፔጅ አለን አንዳንዴ ሳስበው ህይወቴ የተበላሸ መስሎ ይታየኛል ግን ደግሞ ሁሉንም አንድ ቀን እርግፍ አድርጌ እንደ ምተወው ይታወቀኛል ለጓደኞቼ ያለውን ነገር ላሳቀውቃቸው ብዬ ከቤት ወጥቼ ብዙም ሳልሄድ ፉገራ የሚመስሉ ቃላቶች ተወረወሩብኝ በሰፈሬ አሁን ገና ተደፈርኩ ብዬ ለስድብ ዞር ስል አቡሽ ነው ደነገጥኩ ዘለዬ ነበር የተጠመጠምኩበት አቡሽ ማለት የሰፈራችን

ልጅ ነው ከአመት በፊት ግን ወዴት እንደ ሄደ ባናውቅም ጠፍቶብን ነበር እኛም ቁምነገር አድርገን አልጠየቅንም በጣም አድጓል ጠፋህ የት ሂደህ ነው እላዋለው መብራት ሀይል ገብቼ አለኝ ቀልዱ ቅድሙንም ጥርስ አያስከድንም እየተሳሳቅን አብረን ሄድን ልክ እነ ረብቃ ቤት ልን ደርስ ስንል ጓደኞቹ አይቶ ጮህበት እኔጋርም ስልክ ተቀያይረን ማታ እንድት ደውልልኝ ብዬ ተለያየን ረብቃ ዘንድ ስሄድ ብቻዋን ነው ሌሎች ጓደኞቼ የሉም አቡሽን እንዳገኘኋት ስነግራት ደነገጠች ከእኛ ይልቅ እሷ ጋር በጣም ይቀላለዱ ነበር ስለሱ ትንሽ እንዳወራን እህቴ የፃፈችልኝን ወረቀት ልሰጣት ስል እህትሽ እኮ ምን

እንዳለችኝ አላየሁም ቆይ እስኪ ልግባ ብላ ስልኳ ላይ ተተክላ ቀና አልል አለች ምነው እላታለሁ የላኩበት አካውንት ረሳሁት የትኛው እንደ ሆነ አለች እኔ ሳቄን አልቻልኩም ምን ከፍታቸው የውሸት አካውንቶች ከመብዛት የተነሳ ቅጥ አንባሩ ጠፍቶብናል አገኝሁት ብላ ብዙም ሳትቆይ ከአልጋው ላይ ዘላ ተነሳች እይኖቿ ፈጧል በዛ ሰከንድ ውስጥ ላብ በላብ ሆነች ምን ሆንሽ ብዬ ስልኩን ከእጆቿ ስቀበል ከሷ የባሰ እኔ ደረኩ መሬት ተከፍታ በዋጠችኝ አልኩ እህቴ ፎቶውን አይታ…



#ይቀጥላል


#ሼርርርርር_ማድረግ_አይርሱ

@zahkyu
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿»🌺̶̥✽̶┉┉┄┄

╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
@zahkyu
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
Masenanatu enemanalan😭😭😭😔😔😔
#ሞርያ
#እውነተኛ_የፍቅር_ታሪክ
#ክፍል9


@nahom20
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿»🌺̶̥✽̶┉┉┄┄


ስቀበል ከሷ የባሰ እኔ ደረኩ መሬት ተከፍታ በዋጠችኝ አልኩ እህቴ ፎቶውን አይታ ሚሴጅ ልካለች ሀይ ረብቃ እንዴት ነሽ ሰላም ነው የኔን ስሜት በመጉዳት ሌላውን ማስደሰት ምትችይ መስሎሽ ከሆነ ተሳስተሻል ይላል በቃ ምሆነውን አጣሁኝ በርግጥ ቅሌቴን አቀዋለሁ ምን አለ ያስቀመጠችውን ወረቀት ባለየሁ አስባለኝ መቼም ያን ወረቀት እስከ አሁን ድረስ እንደ ማየው እርግጠኛ ናት ሆን ብዬ እንደዚህ አይነት ነገር ያደረኩ መሰላት በርግጥ እንደዚህ ብታስብም አይገርምም ሁሉም ነገር ከአቅሜ

በላይ ሲሆን ቀጥታ ደውልኩላት ዘግታ ደውለችልኝ ከዚህ በላይ ውስጤን ልሸውደው አልችልም አልኳት ስለተፈጠረው ነገር ሁሉ አንድም ሳላስቀር ነገርኳት ውስጤ ቅልል አለኝ እህቴም በጣም ደስ አላት እኔም ቢሆን መጀመርያም ከንቺ የጎደለብኝ ነገር ቢኖር ይሄ ግልፀኝነትሽ ነው አለችኝ ከአሁን በኋላ ስለ ምንም ነገር ይሁን እንዳትደብቂኝ አለች የተካፈው ያህል ውስጤ ደስ አለው ማታ ላይ አቡሽ ደወለልኝ ለረጀም ደቂቃ አወራን አቡሽ ማለት በባህሪው ቀለል ያለ ልጅ ነው ለማንም ቢሆን የሚመች ልጅ ነው ካበህሪው ውሸት አይወድም ከዛን ቀን ጀምሮ ግኑኝነታችን ጠበቀ ሚኪ ጋር እንደ በፊቱም ባይሆን እናወራለን ግን በምንም መንገድ

ከህሊናዬ ላወጣው አልቻልኩም ረብቃ ደግሞ በየቀኑ እየራቀችኝ ነው ነገሩ ምንም አልገባኝም ቤታቸው ስሄድ አላገኛትም ስደውልላት ያለችበትን ቦታ ለመናገር ይደብራታል ብዙ ነገሮቿ ተቀይረውብኛል በፊት አይደለም እንገናኝ ብያት ይቅርና የትነሽ ከማለቴ የት ልምጣልሽ ትለኛለች ዛሬ ግን ስንት ግዜ ደውዬላት እንኳ አንዴ አትመልስልኝም የተፈጠረ ወይም ያስቀየምኩሽ ነገር አለ ስላት እረ በጭራሽ ብላ ይሄን ለማረሳሳት ሌላ ወሬ ታመጣለች ነገሩ ግራ ቢገባኝ ሌሎች ጓደኞቼን ብጠይቅ ምን ተፈጠረ እኛጋር ሰላም ናት አሉኝ ነገርዬው ከኔ ጋር

ነው ማለት ነው እንዴ ብዬ እኔም ተውኳት ሳንገናኝ ሳምንት ሆነን በዚህ መሃል አቡሽ ጋር ሰፈር ውስጥ ቁጭ ብለን እያወራን ድንገት ሰለ ረብቃ አነሳና ተደባብረናል እኮ አለኝ ምን አልኩት አዋ ባክሽ ባለፎው እሷ ጋር እያለሁ አንቺ ስትደውይ አፎምያ ደወለችልኝ በኋላ እንገናኝ ስላት አሽቃባጭ ወንድ አይመቸኝም አለችኝ በሰአቱ ሰለ ተናደድኩ መልስ አልሰጠኋትም አለኝ በጣም ደነገጥኩ እርግጠኛ ነኝ በሱ ምክንያት ነው የዘጋችኝ እኔንም እንደ ዘጋችኝ አልነገርኩትም ድነገት አቡሽ ጋር

እንዳለን ሚኪ በኛ ሰፈር ከአንድ ጓደኛው ጋር ከታች ሲመጣ አየሁት ደነገጥኩ እሱ ነው አይደለም እያልኩ ራሴ ጋር ተሟገትኩ እየቀረበ ሲመጣ በጣም ደነገጥኩ እንደ ምንም ብዬ ባላየ ላሳልፈው ስል እሱ አፍጥጦ ወደኔ መጣ አንቺ ምን ትሰሪያለሽ ከሰፈራችን አለኝ እ አልኩት ስቆብኝ ሰላም ተባብለን አቡሽ ጋር አስተዋወኩት ሻይ ቡና ካላልኳቹ ብሎ ግግም አለብን እኔ አንደዚህ ለብሼ ከሰፈር መራቅ አልፈልግም አልኩ እህ ሲጀመር አንቺ የትኛው ወንድ ነው ቀና ብሎ ሚያይሽ ብሎ ሳቀብኝ አንዳንተ አይነቱ ፉዞ ነዋ ብዬ እዛው ሰፈር አከባቢ ጁስ ቤት ገብተን ስንጫወት ቆይተን ከደቂቃዋች በኋላ ልክ ልን ወጣ ስንል… , , , , ,
.
.
.
.
#ይቀጥላል
ለወዳጆ ሼር ማድረግ አይርሱ
👇👇👇👇👇👇👇👇
@zahkyu
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿»🌺̶̥✽̶┉┉┄┄

╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
@zahkyu
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
#ሞርያ
#እውነተኛ_የፍቅር_ታሪክ
#ክፍል10


@nahom20
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿»🌺̶̥✽̶┉┉┄┄

ሰፈር አከባቢ ጁስ ቤት ገብተን ተጫውተን ከደቂቃዋች በኋላ ልክ ልን ወጣ ስንል ረብቃ ጋር ፉት ለፊት ተፋጠጥን ሁኔታዋ ግራ ያጋባል ሰላም አለችኝና አልፋኝ ወደ ውስጥ ገባች ዞር ብዬ ሳያት አቡሽ ጋር ታየየን ሳቅ አለና ሙድ ያዘባት ወጠን ሄድነ ብዙም አልቆየንም በርግጥ ነገሯ ግራ ነው ሚያጋባ እኔ ግን ወደ ቤትም እንኳ ተመልሼ ውስጤ ምንም ሊረጋጋ አልቻለም ምክንያቱ ደግሞ በጣም የምወዳት ጓደኛዬ ናት በማይረባ ነገር እንዴት ታኮርፈኛለች ብዬ በጣም ነው የተሰማኝ ልክ በዚህ

እንዳለ ሌሎች ጓደኞቼ ቤት ሂጄ ተስብሰብን እያወራን ድንገት ረብቃ ከመጣች እኔ ካለው ደቂቃ መቆየት አትፈልግም ምክንያት ፈጥራ ነው ምትወጣው እኔም እሷ ያኮረፈችኝ በአቡሽ ብቻ እንዳልሆነ አሰብኩ ረብቃ ማለት የምትፈልገውን ለማግኘት በየትኛውም መንገድ ለመሄድ ወደ ኋላ ማትል ልጅ ናት ከግዜ ግዜ ግኑኝነታችን አየሻከረ መጣ እኔም ከአሁን በኋላ ከፈለገች ታውራኝ ከዛ ውጭ አለምናትም ብዬ ተውኩ እህቴ ጋር ልክ እንደ ጓደኛ በየ ግዜው መደዋወል ጀመርን የእውነት ለመናገር እስከ ዛሬ ከእህቴ የራኩባቸው አመታት ቆጩኝ እህቴ ማለት ከእህትነትም በላይ ናት

አቡሽም እህቴ ጋር ስለ ሚግባባ ድንገት ኦንላይን ከተገናኙ ቶሎ አይፋቱም በዚህ መሃል ጓደኞቼ ጋር እየተራራቅን መጣን እኔም ሲሩቁኝ ተውኳቸው አቡሽ ጓደኞችሽ ጋር ምነው ተደባበርሽ እንዴ አለኝ አረ በጭራሽ ምነው አልኩት ስትሄጂ አይቼሽ አላውቅም ብዬ ነው አለ ትንሽ አፋጠጠኝ ስለ ተፈጠረው ነገር ነገርኩት ሚገርመው ግን ከረብቃ ውጭ እነሱም እኔ እንደ ራኳቸው ለአቡሽ ነገረውታል እኔ ለነገሮች ብዙም ቦታ አልሰጣቸውም

ጭንቀት አልችልም አንድ ቀን ጓደኞቼ ደወሉልኝና ላገኛቸው ሄድኩኝ ስሄድ ከረብቃ ውጭ ሁሉም ጓደኞቼ አሉ ሰላም ተባብለን ገና ከመቀመጤ ወረዱብኝ እንቺ ረብቃ ጋር ስለ ተደባበራቹ እኛን የዘጋሽን ምን አድረገን ነው ብለውኝ ፋትራ ሳይሰጡኝ ወረዱብኝ እኔም በእነሱ መቀየም ስለ ማልችል ይቅርታ አልኳቸው ልክ እነሱ ጋር በተገናኘው በሁለተኛው ቀን ረብቃ ደውለችና ላገኘሽ ፈልጌ ነበር ስትል ሰፈረ ከመጣሽ ነይ ከዛ ውጭ ስራ አለብኝ አልኳት መልስ ሳትሰጠኝ ዘጋችብኝ ከሰአት አቡሽ ጋር ሰፈር ውስጥ ተቀምጠን እያለ መጣች አቡሽ ሲያያት

እቺ ውልቭልቭ መጣች ብሎ ተነስቶ ሄደ እኔን ሲያይነው እንዴ ምሄድ ብላ እንደ መሳቅ እያለች ሰላም ብላኝ ተቀመጠች ምን ሁነሽ ነው የጠፋሽው ምን አድርጌሽ ነው ግን እንደዚህ ዝግትግት ያደረግሽኝ አለች የባስ አታምጣ እያልኩ በልቤ አደል አልኳት የምሬን እኮ ነው ታሾፍያለሽ እንዴ አለችኝ በጣም ተናደድኩ ጓደኛዋ መሆኔን ረሳች እንዴ በእኔ ላይ ነው የማስመሰል ድራማዋን ምትስራ አልኩ በልቤ ተነስቼ ልሄድ ስል ይሄውልሽ ሁለት እግር ስላለሽ ሁለት ዛፍ አትወጪም ይልቅ ማትወጪበት ነገር ውስጥ እየ ገባሽ ነው እጅሽ ሰብስቢ አለችኝ ደነገጥኩ ረብቃ ያቺ እኔ ማውቃትና ምወዳት ጓደኛዬ ወይስ ሌላ ሰው ነው ይሄን የተናገረው ብዬ ቀስ ብዬ ዞርኩ መልስ አልሰጠኋትም ልሄድ ስል ላንቺ ብዬ ነው አለበለዚያ ግን ማልፈልገውን ለማድረግ እገደዳለሁ ለሚኪ…
.
.
.
#ይቀጥላል
ለወዳጅዋ ሼር ማድረግ አይርሱ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇

@zahkyu
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿»🌺̶̥✽̶┉┉┄┄

╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
@zahkyu
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
#ሞርያ
#እውነተኛ_የፍቅር_ታሪክ
#ክፍል11


@nahom20
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿»🌺̶̥✽̶┉┉┄┄

#የመጨረሻ_ክፍል_p12_ነው

ለሚኪ ምን አልኳት ፎቶውን ልልክለት እችላለሁ አለችኝ ደነገጥኩ ይሄን ሃሳብ አንቺ እንዳመጣሽው አትርሺ አለችኝ መቆም ራሱ አቃተኝ በጣም የምወዳት ጓደኛዬ እንደዚህ ስትለኝ ቃል ነው ያሳጣችኝ ብናደድም መልስ ግን አልሰጠኋትም በጥፊ ብጠፈጥፋት ደስታዬ ነበር እንደ ምንም ንዴቴን ዋጥ አድርጌ ተቀድመሻል አልኳት በቃ በሰአቱ እሷን መለማመጥ አልችልም ሽንፈት ሚባል አልወድም በሰአቱ እንደዛ ስላት ደነገጠች ይልቅ ለራስሽ

ተጠንቀቂ ካገኘሽ እንደ ስጋ ነው ሚዘለዝልሽ አልኳት የባሰ ደነገጠች እኔ ራሴ ይሄ ሃሳብ እንዴት እንደ መጣልኝ ገርሞኛል በሰአቱ ያን ተናግሬ የሷን መልስ ሳልጠብቅ ወደ ቤት ገባሁ ልቤ በጣም ፍረሃት ፍረሃት አለኝ አሁን ፎቶውን ከላከችለት እና እኔ ይህንን ነገር እንዳረኩት አስመስላ ከነገረችው ሚኪ ለኔ ምን አይነት አመለካከት እንደ ሚኖረው ሳስብ በጣም ዘገነነኝ በስራዬ በጣም አፈርኩ በርግጥ ሁሉንም ነገር ያደረገች ረብቃ ናት ለዚሁ ሁሉ ምንስኤ ግን ተጠያቂዋ እኔነኝ ከቤት

መውጣት አቆምኩ አቡሽ ሰፈር ካጣኝ እቤት ይመጣል እሱ ጋር ሳወራ ስቀልድ ሰአቱም ይመሻል ሚኪ ጋር በምንም ሳንገናኝ ወር ሞላን በዚህ መሃል ግን ባህሪዬ በጣም ተቀየረብኝ አቡሽን ሳለገኘው ውዬ ማደርል አልችልም እሱ ካልመጣ እኔው ራሴ ደውዬ ጠርቼ በሰበብም ቢሆን አይኑን አያለሁ ጓደኞቼ አንድ ቀን ተስብስቦ እቤት መጠው እያወራን እያለ ድነገት አቡሽ መጣ ገና ሲያዩት እርስ በእርስ ተያዩ የሆነ ነገር እንዳለ ገባኝ ሰላም ብሎን ተቀመጠ እሱ ከመጣ በኋላ ወሬያቸው ቀዘቀዘ ስልኩ ሲጠራ ወደ ውጭ እንደ ወጣ በዛው ቀረ ሁኔታቸው ቢያናድደኝ ምድነው አልኳቸው አይ ምንም ግን አንቺንና ረብቃን ያጣላ አቡሽ ነው አይደል

አሉኝ ተናደድኩና አዋ እና ምን ይሁን የሷን ወሬ ይዛቹ ነው ወደኔ የመጣቹ አልኩ ይሄውልሽ አፎምያ በርግጥ ብዙ ሚደብሩ ነገሮች አሉ ግን አሁን ላይ ረብቃ ባደረገችው ነገር በጣም ተጸፅታለች እና ይቅርታ አድርጊላት አሉኝ ሁሉም ነገር ፊቴ ላይ መጦ ድቅን አለ ወደ ተውኩት ማንነቴ ስመለስ ታየኝ ዛሬም እንደ ትናት ሶሻል ሚድያ ላይ ማንም ጋር ልቀላለድ ነው አልኩ በልቤ ዛሬም እንደ ትናቱ ሰው ላይ ልሳለቅ ነው እልኩ እንደምንም ብዬ ላሳምናቸው ሞከርኩ እነሱ ግን እንኳን ሊሰሙኝ ይቅርና ይባስ ሳቁብኝ እሺ ይቅርታ አደርግላታለሁ ግን አጠገቤ እንዳትደርስ አልኳቸው ታድያ ምኑን ይቅር አልሻት አሉኝ ከዚህ በላይ ላሰርዳቹም

ሆነ ልናገራቹ አልፈልግም ብዬ ወደ ውጭ ወጣሁ ተከትለውኝ ወጡ ይሄን ታክል ልንጫንሽ አንፈልግም
ያለውን እንነግራታለን አላስቀምጠን ስትል ነው የመጣነው በቃ አትጥፊ ብለውኝ ሄዱ ስሄዱ ተመስገን አልኩ ሁሎቹም እንደሷ መሰሉኝ በዚህ በሁለተኛው ቀን ሚኪ ደወለ ገና ሄሎ ከማለቴ…
.
.
.
.
.
.
.
#ይቀጥላል
#የመጨረሻ_ክፍል_p12_ነው

#ሼር ማድረግ አይርሱ




@zahkyu
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿»🌺̶̥✽̶┉┉┄┄

╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
@zahkyu
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
❤️❤️❤️💋💋💋
#ሞርያ
#እውነተኛ_የፍቅር_ታሪክ
#ክፍል12
@nahom20
#የመጨረሻ_ክፍል
@nahom20
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿»🌺̶̥✽̶┉┉┄┄
#የመጨረሻ_ክፍል

…አላስቀምጠን ስትል ነው የመጣነው በቃ አትጥፊ ብለውኝ ሄዱ ስሄዱ ተመስገን አልኩ ሁሎቹም እንደሷ መሰሉኝ በዚህ መሃል በሁለተኛው ቀን ሚኪ ደወለ ገና ሄሎ ከማለቴ አንቺ ምን ሁነሽ ነው የጠፋሽ ብሎ ጮኸብኝ እኔም ትንሽ ስራ ይዤ ነው ብዬ ቀበጣርኩበት እንዴት አድርጌ እውነቱን እንደ ምነግረው ግራ ገብቶኛል ይሄን ነገር ደግሞ ከሰው ከሚሰማ ከእኔ ቢሰማ ይሻለዋል ለአቡሽ ያለውን ነገርኩት እሱም እንደኔ እኔው መናገር እንዳለብኝ ነገረኝ እንደ ምንም ብዬ ልነግረው ወስኜ እንገናኝ አልኩት በሰአቱ በጣም ጨንቆኛል ግን እሱ ከእኔ እስኪ ሰማው ነው ከዛን በኋላ ግድ የለኝም

ሚኪ ጋር እንደ ተገናኘን ልነግረው ብዬ አቅሙን አጣሁ በጣም ከበደኝ የሆነ የደበቅሽኝ ነገር አለ ልበል ቅድም ጀምረሽ እኮ ሁኔታሽ እንደው ብሎ ሳቀበኝ ሚኪ ምን መሰለህ እንደ ትልቅ በደል ሰርቼብሃለው ብዬ ለመናገር እንኳ ከብዶኝ አንገቴን ደፋሁ እህ አፎሚያ ምን ሁነሻል ምን ያስቀየምሽኝ ነገር አለና ነው እንደዚህ ምትይኝ አለ እኔም እንደ ምንም ብዬ ከመጀመርያ እስከ መጨረሻ ነገርኩት ግን ሚገርመው ምንም አልደነቀውም ምንም አይነት ብስጭት አላየሁበትም ስለ ነገርሽኝ ከምንም በላይ ደስ ብሎኛል አለ እህ አልገባኝ አልኩት ሁሉንም ነገር እህትሽ ሜሊ ነግራኛለች አንቺም ደግሞ

ያደረግሽው ነገር ጸጽቶሽ ይቅርታ መጠየቅሽ ታላቅነትሽ ነው አለኝ ተነስቼ ነበር ያቀፍኩት በጣም ደስ አለኝ ቅልል አለኝ ይቅርታ ጠይቆ ምህረት እንደ ማግኘት ሚያስደስት ነገር ምን አለ አልኩ በልቤ ደስታዬ ወደር አጣ በዚ መሃል ግን አንድ ያልጠበኩት ነገር መጣ ልክ ከሚኪ ጋር ተለያይተን ወደ ቤት እየተመለስኩ እያለ ከታች አቡሽ በኃላው ሻንጣ ነገር ይዞ ከእህቱ ጋር ወደ መሰመሩ እየወጡ ነው ደነገጥኩ ሰላም ብያቸው ወዴት ነው አልኩ አቡሽ ወደ ነበርኩበት ልመለስ ነዋ አለኝ ፈገግ እያለ የእውነት ለመናገር ልቤ ተነጥሎኝ የሄደ ያህል ተሰማኝ ደነገጥኩ አሁን ላይ አቡሽ ጋር ያለኝ ቅርበት ከምንም በላይ ነው አይኑን እንኳ ሳላይ ማደር አልችልም እንባዬ ቀደመኝ አንቺ ምን ሆንሽ ብሎ እንባዬን ጠረገለኝ እህቱ

ይሄውልሽ አሁን እንደ ዱሮው አይቆይም እኔን ለማድረስ ነው ሚሄድ አለችኝ ብቻ ያለችኝን በቅጡ አልሰማኋትም ተሰናብተውኝ ሄዱ ሰፈር ውስጥ ብቻዬን የቀረው ያህል ተሰማኝ ጓደኞቼ ጋር ተለያይቼ አቡሽም ተለይቶኝ በጣም ተሰማኝ በአንድ በኩል ከጓደኞቼ መለየቴን ሳስብ ደስታን ይሰጠኛል ምክንቱም ዛሬ ከአስመሳይ ህይወት ወጥቻለሁ ሰላም ያለው እንቅልፍ እተኛለሁ እናታልል እናጭበርብር ሙድ እንያዝ ቺት እናድርግ ሚለኝ ሰው የለም አቡሽ ጋር ሁሌም እንደዋወላለን ቻት ላይ ገብቼ እሱ ከሌለ መልህክት አስቀምጬ እወጣለሁ እንደ በፊቱ

ማንም ጋር ስቀልድ ግዜዬን አላጠፋም እህቴ ከሚኪ ጋር ጓደኝነታቸውን ቀጠሉ በዚህ እንዳለሁ አንድ ቀን ድንገት እሁድ ጥዋት ላይ ከእቅልፌ ስነቃ ስገላበጥ ወደ አንድ ሰው የተጠጋው መሰለኝ ከሰመመን ውስጥ እንደ ምንም ተገላብጬም ቢሆን በእጆቼ ዳሰስኩ ደነገጥኩ ለገፋው ብል አልገፋኝ አለ ቀስ ብዬ ቀና አልኩ አንድ ሰው ተሸፋፍኖ ተኝቷል ከድነጋጤ የተነሳ መተፈስ ራሱ ተሳነኝ የሌሊት ልብሴን እንደ ለበስኩ ነው ምን
እንደ ተፈጠረ አላውቅም ቀስ ብዬ ከአልጋው ልወርድ ስል ወደኔ ተጠጋ በቃ ልጨው ትንሽ ሲቀረኝ እጆቹን ጫፋቸውን ወጣ አደረገ አቡሽ ነው በቃ የዛን ቀን ደስታዬ ልዩ ነበር እኔም የራሴን አዳም አገኘሁ ሁሌም የራሳችን ባልሆነ ነገር ላይ እንታገላለን ግድ የኛ ካልሆነ ብለን ከፈጣሪ ጋር እንጣላለን በየቀኑ ብዙ ሰው ጋር እንገናኛለን በየቀኑ ብዙ ነገር እናያለን እንሰማለን ማስመሰል እና ሰውን ማታለል በጣም ቀላል ነገር ነው ግን ከህሊና ቅጣት ማንም አይድንም ሁሌም ፈጣሪ ለኛ ያለውን በዚገይም አያስቀርብንም አመስግናለሁ አፎምያ ነኝ ከናንተው መሀል በእኔ ታሪክ ተምራቹበታል ብዬ አስባለሁ መልካም ግዜ።

ጓደኞቼ ከታሪኩ ብዙ እንደ ተማራቹበት ተስፋ አደርጋለሁ
በሌላ ታሪክ እስከምንገናኝ ሰላም ሁኑ
@zahkyu

╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
@zahkyu
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
❤️❤️❤️
@nahom20
@zahkyu
@nahom20
@zahkyu
😍😍😍😍
❤️❤️❤️
@nahom20
@zahkyu
Track 01
Soliana
Track 02
Soliana
2025/07/11 18:44:38
Back to Top
HTML Embed Code: