ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክተው አባታዊ የሰላም ጥሪ አስተላለፉ።

1386 አዳዲስ አማንያን የቅድስት ሥላሴ ልጅነትን አገኙ።
ጥር ፫ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም
በደቡብ ኦሞ እና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ዳሰነች ወረዳ 1386 አዳዲስ አማንያን በማኅበረ ቅዱሳን የሐዋርያዊ ተልእኮ አስተባባሪነት የቅድስት ሥላሴ ልጅነትን አግኝተዋል።
ተጠማቂያኑ ባለፉት ወራት መሠረታዊ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን መሠረተ እምነት ሲማሩ ከነበሩ ወገኖች መካከል ሲሆኑ ሥርዓተ ጥምቀታቸው በኦሞ ብሔረ ብፁዓን አቡነ ዜና ማርቆስ ወአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ አንድነት ገዳም ዛሬ ጥር 3 ቀን 2017 ዓ.ም ተፈጽሟል።
በዕለቱ ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ የደቡብ ኦሞ እና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ተገኝተው ሥርዓቱን ፈጽመዋል።
ቅድመ ጥምቀት ሐዋርያዊ ተልእኮ ማስፋፊያ እና ሥርዓተ ጥምቀት ማስፈጸሚያ ተግባራት ሙሉ ወጪ በማኅበረ ቅዱሳን ተሸፍኗዋል፡፡
የማኅበረ ቅዱሳን የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ አገልግሎት በተለያዩ አካባቢዎች ባለፉት ወራት ባከናወናቸው የሐዋርያዊ ተልእኮ ማስፋፊያ ተግባራት 8547 አዳዲስ አማንያን ተምረው አምነው በመጠመቅ የቅድስት ሥላሴ ልጅነትን እንዲያገኙ ማድረጉ ተገልጿል፡፡
ይህንን ሐዋርያዊ አገልግሎት ለመፈጸም የሚመለከተው ሁሉ በመሳተፍ ኦርቶዶክሳዊ ግዴታውን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።

ማኅበረ ቅዱሳን ለአንድ ዓመት ያህል ያሠለጠናቸውን ካህናት ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ (ዶ/ር) በተገኙበት ማስመረቁ ተገለጸ
ጥር ፭/፳፻፲፯ ዓ/ም
ማኅበረ ቅዱሳን ጎሬ ወረዳ ማእከል ለአንድ ዓመት ያህል ያሠለጠናቸውን 22 ካህናትን የኢሉ አባ ቦር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባልና የመቱ ፈለገ ሕይወት መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ጠባቂ ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ (ዶ/ር)፣ የኢሉ አባ ቦር ሀገረ ስብከት የመምርያ ኃላፊዎች ፣ የማኅበረ ቅዱሳን መቱ ማእከል ፣ ተመራቂ ተማሪዎችና ቤተሰቦቻው በተገኙበት በኖኖ ሳርዶ ማርያም በአቡነ ሚካኤል ካልዕ ስም በተገነባው አብነት ትምህርት ቤት ውስጥ አስመርቋል።
ካህናቱ በቆይታቸው ሰዓታት፣ ኪዳን፣ ሊጦንና ቅዳሴ በግእዝና በእዝል ተምረው ለአገልግሎት እንዲዘጋጁ የተደረገ ሲሆን ቀድሰው ከወጡ በኋላ ወንጌል እንዲያስተምሩ መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን ትምህርቶችንም መማራቸው ተጠቁሟል።
ብፁዕነታቸው ሀገረ ስብከቱ ከማኅበረ ቅዱሳንና ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የተዘጉትን አብያተ ክርስቲያናት ለማስከፈት እየሠሩ መሆኑን በመግለጽ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሰጥተዋል።
የጎሬ ወረዳ ማእከል ማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ቀሲስ ምትኩ ተፈሪ እንዳመለከቱት ለሥልጠናው ሀገር ውስጥና ሀገር ውጭ ከሚኖሩ የቤተ ክርስቲያን ልጆች በማሰባሰብ ከ750,000 ብር በላይ ወጪ መደረጉን በመግለጽ የተዘጉትን አብያተ ክርስቲያናት ለማስከፈት በ2015 ዓ.ም ዕቅድ ነድፎ እየሠራ መሆኑን አመላክተዋል።