Telegram Web Link
ቋሚ ሲኖዶስ ልዩልዩ ውሳኔዎችን አስተላለፈ።
*******
ሚያዚያ ፳፪ ቀን ፳፻ ፲ዘ፯ ዓ.ም
+++++++++++++++++++
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
"""""""""""""""""""""""""""
ቋሚ ሲኖዶስ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ከቤተክርስቲያናችን የነገረ ማርያም አስተምህሮ ውጪ በፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር አዳራሽ የሰጡትን ትምህርትና በማኅበሩ ሚዲያ የተላለፈበትን ሁኔታ በተመለከተ በዛሬው መደበኛ ጉባኤው በሰፊው ተወያይቶ ለመወሰን በያዘው ቀጠሮ መሰረት በጉዳዩ ዙሪያ ጥልቅ ውይይት ካደረገ በኋላ የሚከተሉትን ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

1. ፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማህበር በተለያዩ ጊዜያት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ውጪ በሚዲያው ያስተላለፈው የስሕተት ትምህርት የቤተክርስቲያናችንን አባቶች፣ሊቃውንቱንና መላው ሕዝበ ክርስቲያኑን ያሳዘነ በመሆኑ በማህበራት ምዝገባ ክትትልና ቁጥጥር መምሪያ በኩል ጊዜያዊ የእገዳ ደብዳቤ እንዲደርሰው እና በመምሪያው በኩል አስፈላጊው ጥብቅ ክትትል እንዲደረግ ሆኖ በጉዳዩ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ መስጠት ይቻል ዘንድ አምስት አባላት ያሉት ኮሚቴ እንዲቋቋም አድርጓል።
በዚህም መሰረት ቋማ ሲኖዶስ ያቋቋማቸው አጣሪ ልዑካን አጠቃላይ የማህበሩን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ እና በሚዲያው ያስተላለፋቸውን የስህተት ትምህርቶች በተመለከተ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እና ከማህበራት ምዝገባ፣ ቁጥጥርና ክትትል መምሪያ ጋር በመነጋገር በሚገባ መርምርውና አጣርተው በአጭር ጊዜ ውስጥ ከውሳኔ ሐሳብ ጋር ለቋሚ ሲኖዶስ እንዲያቀርቡ፣

2. ብፁዕ አቡነ ገብርኤል “ማርያም ቤዛዊተ ዓለም” አትባልም በማለት ከቤተ ክርስቲያናችን የነገረ ማርያም አስተምህሮ ውጪ የሰጡት ሕጸጽ ያለበት ትምህርት በሊቃውንት ጉባኤ በኩል በሚገባ ተመርምሮና ተጣርቶ ከመፍትሔ ሐሳብ ጋር ለቋሚ ሲኖዶስ በአስቸኳይ እንዲቀርብ ብፁዕነታቸውም ጉዳዩ ተጣርቶ የመጨረሻ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በተአቅቦ እንዲቆዩ፣

3. ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት እና ብፁዕ አቡነ በርናባስ የደቡብ ካሊፎርኒያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ያስተላለፏቸው የስሕተት ትምህርቶችና በሌሎችም መምህራን የተላለፉ ነቀፋ ያለባቸው ትምህርቶች ካሉ የሊቃውንት ጉባኤ ከቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮ አንጻር በሚገባ መርምሮና አጣርቶ ከመፍትሔ ሐሳብ ጭምር በአጭር ጊዜ ውስጥ ለቋሚ ሲኖዶስ እንዲያቀርብ፣

4. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኝ ብዙኃን ስርጭት ድርጅት ለፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማህበር ሚዲያ የአየር ሰዓት የሰጠበትን ዝርዝር ሁኔታና ከማኅበሩ ጋር በተያያዘ አየር ላይ ያዋላቸውን ትምህርቶች የሚያሳይ ሪፖርት እንዲያቀርብ ይደረግ በማለት ቋሚ ሲኖዶስ ወስኖ የዕለቱን ጉባኤ በቅዱስነታቸው ጸሎተ ቡራኬ አጠናቋል።

መረጃው የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ/Department of Public Relation ,EOTC ነው።
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለአገልግሎቷ መሻሻል ዘመናዊ የአስተዳደር ተቋም መፍጠር እንደሚገባት ተገለጸ፡፡

ሚያዝያ ፳፬/፳፻፲፯  ዓ.ም

ለተከታታይ ሦስት ቀናት ከሚያዚያ 20 እስከ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በተካሄደው የዝክረ ኒቅያ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ተሳታፊ የሆኑ  ሊቃውንት በቤተ ክርስቲያን አሁናዊ ሁኔታ ላይ ሐሳባቸው ሰጥተዋል፡፡

ሊቃውንቱ በሰጡት ሐሳብ እንደገለጹት ከመቼውም ጊዜ በላይ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ትኩረት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት መሥጠት እና ሥርዓቷን ማስከበር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ 

በተለይም ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን በመራራቃቸው አገልጋዮች የውስጥ እና ምእመናን ደግሞ የውጭ አካላት መሆናቸው፣የቤተ ክርስቲያንን አገልጋዮችን የመንቀፍ ዝንባሌዎች መብዛት፣የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት አለመጠበቅ አሁናዊ ሁኔታዎች መገለጫዎች እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡

አክለውም የምኩስና ሕይወት የሥራ ዘርፍ እየሆነ መምጣት፣ከላይ እስከ ታች የሚገኙ የቤተ ክርስቲያን መዋቅሮች አለመናበብ እና የአምባገነናዊ አስተዳደሮች መበራከት እንዲሁም በአንድ ደብር ላይ የአገልጋዮች መብዛት ይህም ቤተ ክርስቲያንን ከመንፈሳዊ ዓለምነቷ ይልቅ ድርጅት እንድትሆን እንዳደረጋት ሌሎች የአሁናዊ ሁኔታዎች ማሳያ ናቸው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ምእመናንን በማሳተፍ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎቷ እንዲሻሻል እና ችግሮች እንዲቀረፉ የዘመኑ አስተዳደራዊ ተቋማትን መፍጠር እንደሚገባት ሊቃውንቱ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ዝክረ ኒቅያ ዓለም አቀፍ ጉባኤ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ስብራት የሚጠግን መሆኑን ሊቃውንት ተናገሩ፡፡

ሚያዝያ ፳፬/፳፻፲፯ ዓ.ም

በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ጽርሐ ተዋሕዶ በተካሄደው የዝክረ ኒቅያ ዓለም አቀፍ ጉባኤ የተሳተፉ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ጉባኤው የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ስብራት የሚጠግን፣በተለይም በሃይማኖት በኩል የነበረውን ብዥታ የሚያጠራ እንዲሁም ለምእመናን ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በጉባኤው ላይ የተነሱት ሐሳቦች ለወደፊት ለቤተ ክርስቲያን ጠቃሚ እንዲሆኑ  በንግግር ብቻ ሳይሆን ወደ ተግባር እንዲቀየሩ ቅዱስ ሲኖዶስ ማጽደቅ እንደሚጠበቅበት ተናግረዋል፡፡

የጉባኤው ተሳታፊዎች እንደገለጹት ለቤተ ክርስቲያን ችግሮች ዘለቄታዊ መፍትሔ እንዲመጣ ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ጉባኤው መካሄድ እንዳለበት አንሥተው የሊቃውንት ጉባኤ በየሀገረ ስብከቱ እንዲቋቋም ጠይቀዋል፡፡
#ተይ #አትድከሚ

አንዲት ሴት ልብስ ልታሠራ ፈትል እየፈተለች ነው፡፡ ልቁ የማይበቃ መስሏት ከዚያ ከዚያ እያለች ለልብስዋ እንዲበቃ ለማድረግ ቁጥሩን አትርፋ መፍተልዋን ቀጠለች፡፡ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በዚያ እያለፈ ነበርና ከሩቅ አያት፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ጸጋው የፈተለችው ለምታሠራው ልብስ የሚበቃ መሆኑን አውቆ ሴቲቱን እንዲህ አላት፥

👉ሞልቷልና አትድከሚ' በዚህ ምክንያት የዚያ አካባቢም ሥፍራ “ኀድጊ ወትጻምዊ/ተይ አትድከሚ' ተብሎ ይጠራል፡፡

ይህንን ታሪክ ሳነብ ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ስለ አንዲት ሴት ጥጥ መባከን ብቻ የተናገረው ሆኖ አልተሰማኝም፡፡ ከሚያስፈልገን በላይ እየፈተልን የምንደክምባቸው የሕይወት ልቃቂቶች ስንት ናቸው? ስምንኖረው ዕድሜ የሚበቃንን ሳናውቅ የሚንኳትንባቸው ስንት ጉዳዮች አሉ? ቅዱስ አባታችን ሆይ እኛንም 'ሞልቶአልና አትድከሙ በለን፡፡

የግዮን ወንዝ
@zemariian
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
@zemariian
አምስቱ ጸዋትወ ዜማ?

ጸዋትወ ዜማ፦ ጸዋትው ስንል ወገኖች ማለት ሲሆን ጸዋትወ ዜማ ደግሞ የዜማ ወገኖች ማለት ነው።

ጠቅላላ የቅዱስ ያሬድ የዜማ ድርሰት በአምስት ይከፈላሉ፦
፩፦ ድጓ
፪፦ ጾመ ድጓ
፫፦ ምዕራፍ
፬፦ ዝማሬና
፭፦ መዋሥዕት ናቸው።

የቅዳሴን ዜማ እርሱ ስለደረሰው እንደ፮ኛ አርገው የሚወስዱት አሉ። በወገንነት ሆነ በምልክት ከአምስቱ ጸዋትወ ዜማ ጋር ተመሣሣይነት አለው። በመሠረቱ ዜማ የሚለው ስም ሁሉንም የዜማ አይነቶች የሚያጠቃልል ነው።
@zemariian
፩፦ ጾመ ድጓ
የስሙ ትርጓሜ፦ ድጓ ማለት ትርጉሙ ከጽሕፈቱና ከምልክቱ ረቂቅነት የተነረሳ ድግድጉ ጽሑፍ ፣ጽሑፉ ጥቅጥቅ ያለ ረቂቅ መጽሐፍ ማለች ነው። በሌላ አገላለጽም #እስትጉቡዕ ይባላል፤ #እስትጉቡዕ ማለትም #ስብስብ ማለት ነው።
እሱም የዓመቱ መዝሙርሸ
፩፦ ጸደይ
፪፦ መጸው
፫፦ ኀጋይ
፬፦ ክረምት ብሎ በአምናት በመከፋፈል በአንድ ላይ ሰብስቦ ይዞ በመገኘቱ ይህን ትርጉም አግቷል። ከዚህ በተጨማሪ #ድጓ #ላልቶ #ሲነበብ #የቤተክርስቲያን_ትጥቋ#መቀነቷ#ውበቷ ነው የሚለውን ትርጉም ይሰጠናል።

አከፋፈሉ፦ ድጓ በሦስት ዐበይት ክፍሎች ይከፈላል እነርሱም፦
፩፦ ዮሐንስ
፪፦ አስተምህሮ
፫፦ ፋሲካ ይባላሉ።
እነዚህም የድጓ ክፍላት በአራቱ ክፍላተ ዘመን ይነገራሉ። ዘመናቱም መጸው፣ኀጋይ፣ፀደይ፣ክረምት ናቸው።

ፀሐፊ®ዲ.ን ሱራፊ
@zemariian
፩ኛ #ዘመነ_ዮሐንስ

ዘመነ ዮሐንስ የሚለው የዮሐንስ ድጓ #ከመስከረም ፩ ጀምሮ እስከ ኅዳር ፴ ሰማዕት ድጓ ድረስ ባለው ዘመን የሚዘመረው ቀለም (ቃለ እግዚአብሔር ) ሲሆን በዘመናት አከፋፈልም ዘመነ መጸው ይባላል።

፩.፩ #ወርኃ_መስከረም
ወርኃ መስከረም በድጓው አቀማመጥ እነዚህን በዓላት ይይዛል፦
#ዘዮሐንስ#ዘተከዚ#ዘኤልሳቤጥ _ዘሰንበት ፣#ኤልሳቤጥ_ዘዘወትር#ዘዘካርያስ#ዘፍሬ_ሰንበት#ዘፍሬ_ዘዘወትር#ዘጼዴንያ#ዘእስጢፋኖስ ፣ # ዘሕነፀተ_ቤተክርስቲያን ፣ #ዘመስቀል#ዘዕሌኒ#ዘመስቀል_ዘሰንበት#ዘመስቀል_ዘዘወትር#ዘብዙኃን_ማርያም#ዘኤዎስጣቴዎስ#ዘጸአተ_ክረምት ፣ ዘጴጥርስ_ወጳውሎስ ፣ #ዘያዕቆብ_ወዘዮሐንስ ናቸው።
@zemariian
2025/07/05 20:43:02
Back to Top
HTML Embed Code: