Telegram Web Link
ወሃቢያ በጦሳ…!

"…ወሃቢያ የኢትዮጵያ መከላከያን ልብስ ለብሶ በወሎ ተመረቀ ነው የሚሉኝ። በምረቃ ሥነ ሥርዓቱም ላይ ከኦርቶዶክስ፣ ከጴንጤም፣ ከሌላም ቤተ እምነት ለላንቲካ እንኳ የተገኘ የለም ነው የሚሉት። የተገኙት የወሃቢያ አደራጆች ናቸው፣ ወሎ ላይ የተደገሰ ድግስም አለ ነው የሚሉት።

• ወሃቢያ ለመሆናቸው ምልክቱ ምንድነው? ብዬም ላቀረብኩት ጥያቄ የሚከተለውን መልስ አግኝቻለሁ።

"…ዘመዴ እነሱን ለመለየት በጣም ቀላል ነው። አጠማጠማቸውን ማየት ብቻ በቂ ነው። ሻሹን ጣል ነው የሚያረጉት። በዚያ ሊሸውዱ ከሞከሩ በሱሪያቸው እጥረት ትለያቸዋለህ። በዚያም ከሸወዱህ በአዲዳስ ጫማቸው ትለያቸዋለህ። በዚያ እንኳ ከሸወዱህ ከከንፈራቸው በላይ ያለውን ጢም የፈገፈጉ ኾነው ታገኛቸዋለህ። በዚህ በወሃቢያ ጦር ምረቃ ይኸው እነሱ ብቻ ተገኝተው መርቀውልሃል።

• እነርሱበያለ ሃፍረት፣ ያለ እረፍትም በፈጣጣው ሥራቸውን እየሠሩ ነው። ደሴና ኮምቦልቻዎች ግን እግዚአብሔር ይሁናችሁ…! 🙏🙏🙏
839👍270💔45🙏41🤔40😡3722🤯13🕊9😱2🏆1
"…ይህንም ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ፤ ደመናም ከዓይናቸው ሰውራ ተቀበለችው። እርሱም ሲሄድ ወደ ሰማይ ትኵር ብለው ሲመለከቱ ሳሉ፥ እነሆ፥ ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች በአጠገባቸው ቆሙ፤" ሐዋ 1፥ 9-10

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ
1.02K🙏503👍108🕊23🔥17😡1612🏆9🤔4💔1
ማስታወሻ…

"…ለነገው ነጭ ነጯን መርሀ ግብሬ እደርሳለሁ። ለዛሬው የቅዳሜ ከሰዓት የተቀበል መርሀ ግብራችን ግን "ጥቂት ጊዜ አበድረን" ብለው ደጅ የጠኑኝን ቤተሰቦቼን ተከትዬ ከጀርመን ወጣ በማለቴ ምክንያት አለመኖሬን በትህትና እገልጻለሁ።

• ደሴና ኮምቦልቻ ግን "የግራኝ እመቤት" ትሁናችሁ። እስከ ነገ መልካም ጊዜ ለሁላችን።
🙏770181👍178🏆28😡2316🕊11🤯5🔥4😱2
በሰላም ተመልሰናል…!

"…ቤቴን በሩን ከፍት አድርጌ ነበር የሄድኩት። ሰላም ነው። የረበሸ አለ? ውሎ እንዴት ነበር…?

"…በነገራችን ላይ ብልጼዎችም፣ የብልጼ ገሌዎችም ብሬክስና አዲስ ገቢዋ ጌች ጭምር ምን ሆነው ያኮረፉት? የበለፀገ ሀገር እየመሩ የምን ሃሳብ ትካዜ ነው? የምን ጭንቅ ጥብብ ነው? ምን ሰምተው? ምን ዓይተው ይሆን?

"…አቶ አረጋስ እሺ እሱ እንኳ ይጨነቅ… ሽግሩም ይታወቃል። የሙስጠፌ ጭንቀት ባይገባኝም፣ የዲላሞም እንዲሁ የሙስና ክስ ስላለበት ቶክቻው የተባለ አዝማሪን ጥሎበት በዚያ ተጨነቀ እንበል፣ ብሬክስም ከኢሳያስ ከወዳጁ ጋር የተገባው አታካሮ ደስ ሳይለው ቀርቶ ማጠፊያው አጥሮት ተጨነቀ እንበል። የጌችም ጭንቀት ያው ይታወቃል። ብልፅግና ወደ ትግሬ ምድር ዳግም ከአረቄና ቢራ በቀር ምንም ዓይነት ሸቀጥም ሆነ ነዳጅ እንዳይገባ ስላደረገ በዚያ አዝኖ ሊሆን ይችላል እንበል። በዚያ ላይ አዲስ ገሌ ባሪያ፣ አዲስ ገረድ ስለሆነም በአቢይ መዠለጡን እስኪለምደው ድረስ ድንግርግር ሊለው ይችላል።

…ኦቦ ሽመልስ አብዲሳና አዳነች አበቤ ምን ሆንን? ምናችን ተነካ? ምን ሰማን? ምን ቀረብን ብለው ነው ያኮረፉት? ፊታቸውን እንደ ጌችና ብሬክስ ያጨፈገጉት? ነውር ነው። ከምር ኢደብራል።

• ኢማጂን ኢታያችሁ ያውም ኦሮሞን የሚመስል፣ ኦሮሞን ከፍ የሚያደርግ፣ የኦሮሞ ጳጳስ መርጠው፣ ሲኖዶሱንም እንደፈለጉት፣ እንደተመኙትም ተቆጣጥረው ሲያበቁ ጮቤ እንደመረገጥ፣ እንደ ሰላም ሚንስቴር የደስታ መግለጫ እንደማውጣት ምን ነካን፣ ምንገጠመን ብለው ነው? እንዲህ መተከዛቸው? ኧረ ደስ አይልም።

• አላችሁልኝ አይደል? የረበሸ አለ እንዴ…?
1.06K👍368🙏74👌29😡24🤔23🕊1514🔥14🏆7🤯3
"…ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ" ማር16፥19

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ
🙏1.17K299👍92🕊27😡18🏆11👌9🤔76🤯4
መልካም…

"…በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር በየሳምንቱ እሑድ ምሽት ከ1::00 ሰዓት ጀምሮ በዘመድ ቴቪ በቀጥታ ስርጭት የሚቀርበውን "ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር" የተሰኘውን ሳምንታዊ የቴሌቭዥን መርሀ ግብር ለማቅረብ ሰንዳ ሰንዳ እያልኩ ነው።

"…የመድኃኔዓለም ያለህ…! …አጀንዳው ግን መብዛቱ ለጉድ ነው። አደራረቡት እኮ። ሁሉንም ማቅረብ ባልችልም ከአጀንዳዎቹ መሃል መርጬ ግን የተወሰኑትን መቀጥቀጥ ነው። የፈጣሪ ያለህ…!

"…አንዳንዶች "ዘመዴ ሰሚ የለም፣ ሕዝቡ እንደው ደንዝዟል፣ ዝም ብለህ ነው እንደ እብድ የምትጮኸው፣ የሚሉ አሉ። ሰሚ ኖረ አልኖረ ለደንታው ነው። እኔ ግን እናገራለሁ። መሬት ስሚ፣ ሳማይ አድምጪ፣ ቤተ ክርስቲያን መስክሪ ብዬ እጮሃለሁ። ያው ቆይቶ፣ ቆይቶ "ዘመዴ እኮ ተናግሮት ነበር" መባሉ እንደሁ አይቀር። ኢንዴዢያ ኖ…!

• አዠንዳው ብዛቱ ያደክማል… ግን ደግሞ ይፈርሳል።

~ በሉ የምቀጠቅጠውን አዠንዳዬን ልምረጥበት…!
🙏666👍204184😡21🔥14🕊12🏆128🤔7
"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር

"…በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ምሽት 1:10 ላይ በዘመድ ቴቪ መርሀ ግብሩ ይጀምራል። እንደተለመደው ገባ ገባ በሉና ጠብቁን።

• ZemedTv 👉 zemedtv.com

• በትዊተር (×) 👉 https://x.com/i/broadcasts/1BdxYqRQkXgxX

• በራምብል 👉 https://rumble.com/v6u60g7--zemede-june-01-2025.html

• በሳታላይት ቴሌቭዥን 👉 Yahsat 52.5° East
                                       11977 H 27500
• ላይ ይከታተሉን።

"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።

👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia

👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።

• ሰብሰብ ብላችሁ ጠብቁን…!
👍383130🙏18😡16🏆10🤯4🕊3
• ጀምረናል ገባ ገባ በሉማ…!

• አላችሁ አይደል…?
👍661113😡22🏆19🙏11👌11🕊11🔥7🤔6
• ደኅና እደሩልኝ…
🙏658167👍109😡3519👌10🕊7🤯6🔥1
“…ወደ ላይ ዓረግህ፥ ምርኮን ማረክህ፥ ስጦታንም ለሰዎች ሰጠህ፥ ደግሞም ለዓመፀኞች በዚያ ያድሩ ዘንድ።” መዝ 68፥18

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ
1.07K🙏561👍129🕊34😡129🏆8🔥3😱2
“…አምላክ በእልልታ፥ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ።” መዝ 47፥5

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ
🙏1.18K249👍101🕊25😡12🏆10🤔4
መልካም…

"…በትናንትናው ዕለት በእረፍት ሰዓቴ በተደጋጋሚ የአስከሬን መዓት የያዘ መልእክት በመልእክት ማስቀመጫ ሳጥኔ ውስጥ ሲዘረገፍ ይውላል። አብዛኛው መልእክቱን የሚልኩልኝ ደግሞ በውስጥ መስመር ሲቋሰሉኝ የሚውሉት የኦሮሙማው፣ የስኳድ እና የሸንጎ ኃይሎች፣ እንዲሁም የመከታው ደጋፊ ነን የሚሉ የቀድሞው የባልደራስ፣ የግንቦት ሰባት፣ የኢዜማና የዲሲ ግብረ ኃይል ሰዎች ናቸው። እኔም ምላሽ ሳልሰጣቸው የእረፍት ቀኔን በአግባቡ ስጠቀም ውያለሁ።

"…ዜናው የመጣው ከጴንጤው ወሴ ከሉጢው ከናቲ አንደግምም ወይ? ነው። ናቲ ደግሞ በአባቷ ጎንደሬነት በዝናሽ በኩል፣ በእናቷ ጉራጌነት ብራኑ ነጋን ይዛ የምትንቀሳቀስ፣ መጠጥ ከመተውና ስካር ለመቀነስ በሚል ሰበብ በአባቱ በኩል የተቀበለው ጴንጤነት ለናቲም ተርፎ ጴንጤ መሆኑ የበለጠ የሥርዓቱ ቤተኛ ምስጢር ዐዋቂ ያደረገው፣ በፔጁ ላይ 8 ሰዎች የሚጽፉበት፣ ፔጁን አከራይቶ የሚኖረው ገሌ መጻፉ ነው። ይህ እንዳለ ሆኖ መንጋው ፀረ ዐማራ ቡድን ናቲን እንደመረጃ ቆጥሮ ግርር ብሎ ሲነጉድ ማየቴም ሲያስቀኝ ነው ያደረው።

"…ለመከታው አግዞ የሚጽፈው የናቲ አንደግምም ወይን ፎቶና ወሬ ይዤም በቀጥታ ወደ ወሎ ቤተ ዐምሓራና ወደ ሸዋም ወፎቼን ልኬ ነበር። የሞቱትን ሟቾች ፎቶ አስይዤ ነው ወፎቼን የላኩት። የወሎ ቤተ አምሓራንም፣ የሸዋዎቹንም የኢንጂነር ደሳለኝ ልጆችን አግኝቼ ብዙም አውግቼ ተመልሻለሁ።

"…የመከታው ቡድን መደምሰሱ አይቀርም። የብልፅግና ሽፋን፣ የእነ ናቲ አንደግምም ወይ ሟርትም አያድነውም። አይታደገውምም። ይሄ ውጊያ የመቼ ነው? እውን ወደ ሸዋ የወሎ ጦር ገብቷልን? ክረምቱ እየመጣ ነው አይደል? ለማንኛውም በዛሬው ርእሰ አንቀጻችን አጫጭር አፍራሽ መዶሻ፣ ድጅኖ፣ ድማሚትም የሆኑ መረጃዎችን በመለዋወጥ አብረን እናመሻለን።

• እህሳ…ዝግጁ ናችሁ…?
889👍378🙏87🕊27😡1716🔥6🏆4🤯3🤔1
በመታወቂያዋ እንጀምራለን…!

"…ናትናኤል ትላንት ከለቀቀው ፎቶ ውስጥ በእርግጥ የተሰዉ የ4 ልጆች ፎቶ እውነት ነው። ልጆቹ የተሰዉት ግን ሸዋ ሳይሆን ጉባላፍቶ ወረዳ እዜት ላይ ነው። ከ20 በላይ ክላሽ በተነሣበት፣ በርካታ ተተኳሽ ሠራዊቱ ባገኘበት ውጊያ ተሳትፈው የተሰው ልጆች ናቸው። ውጊያው የተመራው በበለጠ ሸጋው ሲሆን ውጊያው የተደረገውም ከትናንትና ወዲያ ጀምሮ ሌሊት ሌሊት በኮምቦልቻ አየር ማረፊያ ሲራገፍ ያደረውን የኮማንዶ ኃይል፣ ወደ ራያ ገብቶ ትንኮሳ የጀመረውን የብራኑ ጁላን ጦር ኃይል ለመበታተን ሲባል በተጠና መልኩ እዜት ያለውን ኃይል በመቱት ጊዜ በዚያ ውጊያ ላይ ነው ልጆቹ የተሰዉት።

"…ለምሳሌ ይሄ ናትናኤል የለጠፈውን ፎቶ እንመልከት። ፎቶው በእርግጥ ከሟች ፋኖ አስከሬን ላይ የተገኘ ነው። በእዜቱ ውጊያ ላይ ነው የተመታ ልጅ ነው። ባለመታወቂያው በሕይወት አለ። ባለመታወቂያው ወደ ከተማ ለሌላ ጉዳይ ሲሄድ ይራሱን መታወቂያ ለፋኖው ጓደኛው ሰጥቶ ነው የሄደው። መታወቂያውን የያዘለት ፋኖ ደግሞ በእዜቱ ውጊያ ይሰዋል። በዚህም ምክንያት መከላከያ ከአስከሬኖቹ ላይ መታወቂያ ለቅሞ ለናትናኤል ሲልክ የዚህም ልጅ መታወቂያ አብሮት ስለነበር ነው ለናትናኤልም የሞተ በሚል ዜና እንዲሠራ ያደረጉት።

"…ሟች ተብሎ የተለጠፈው ፎቶ በሕይወት ያለ የአርበኛ አበበ ፈንታው የአክስቱ የልጅ ልጅ ነው።

"…ጥያቄው በጁንታው ጊዜ በተደረገ ጦርነት ላይ እና መከታው ከዱኝ ብሎ የሚረሽናቸውን የሸዋ ፋኖዎች ፎቶ ለጥፎ መከታው ባልዋለበት ቦታ ጀግና ጀግና ማድረጉ ብልፅግና በእስክንድር ነጋና በመከታው ጦር ላይ ምን ስጋት ቢገጥመው ነው።

"…የመከታው ጦር እንደሁ ወይ ይደመሰሳል፣ አልያም ይማረካል። ወይ ደግሞ ወደ ብልጽግና ይፈረጥጣል። ሌላ አማራጭ የለውም። ይኸው ነው።

• ቆይቼ እመለሳለሁ…!
965👍275🙏140😡32🤔14🕊12🏆129🔥9
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
• ሸዋ ነው…የአሰግድ ልጆች…

"…ሙሉ ዝግጅቱን ሰሞኑን በዘመድ ቴቪ ይዤላችሁ እቀርባለሁ። የሸዋ ፋኖ ከፊት ከመከላከያ ጋር፣ ከጎን ከኦነግ ሸኔ ጋር፣ ከኋላው ከመከታው ማሞና ከእስክንድር ነጋ ታጣቂ ጋር እየተፋለጠ ነው። እንዴት የሚለውን በመረጃና በማስረጃ በተለቪዥን እንመጣበታል።

"…ሸዋ መጥቶ የተዋጋ፣ እነ መከታውም የደመሰሱት የወሎ ጦር የለም። ይሄ ይሰመርበት።

"…የመከታው ጦር አሁን የት ነው ያለው?

"…ከወንድሞቻችን ጋር አንዋጋም ያሉት ረሽኖ፣ የቀሩትን ሸክፎ ወደ በረኸት ሄጄ ጄነራል ተፈራ ማሞን ደምስሼ፣ የከሰምን ጦር አስገብሬ የይፋት ዳይነስቲን መልሼ፣ ብቸኛው የሸዋ ወኪል እኔ እሆናለሁ በማለት የመጨረሻ ዕድሉን በመሞከር ላይ የሚገኘው የመከታው ጦር ከአንኮበር በሕዝብ የተባረረውን ጦሩን ይዞ፣ ወደ በረኸትም መውረድ ፈርቶ ሚጣቅ አማኑኤል፣ ሳሲስት መንዝ ላይ ነው የሰፈረው።

"…አገዛዙ በድሮን እስኪያግዘውም እየጠበቀ መሆኑ ተነግሯል። የሆነው ሆኖ ግን በብሔራዊ ኃይሉ ከመደምሰስ የሚተርፍ አይመስልም። የከዱ የፋኖ ቤተሰቦችን እየረሸነ ያለው የመከታው ጦር ለዘር እንኳ የሚተርፍ አይመስልም።

• ቆይቼ እመለሰላሁ…!
🙏878312👍228😡34💔19🔥17🤔1211🕊10🏆63
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሰግድ መኮንን ባቀናው ሀገር
እስክንድር ፎከረ ውይ አለማፈር

"…ሰሞኑን የዐፋብኃ የሸዋ ጦር ግሼራቤ ላይ ከመከላከያ ጋር ጦርነት ይገጥማሉ። መከላከያም ምቱን መቋቋም ሳይችል ይቀርና ከተማዋን ለቅቆ ወደ ኋላ ያፈገፍጋል። አፈግፍጎም በርቀት ከተማዋን መደብደብ ይጀምራል። ቤቶች መቃጠል፣ ዜጎች መሞት ይጀምራሉ። ፋኖም ወደፊት ለመገስገስ በዝግጅት ላይ ሳለ ከኋላው ችግር ይገጥመዋል።

"…የመከላከያን ከተማዋን ለቅቆ መውጣት የሰማው የእስክንድር ነጋና የመከታው ታጣቂ ዐማብኃ ን ከጀርባው መውጋት ይጀምራሉ። የጨነቀ ነገር ገጠማቸው። ግሸራቤን ለመከላከያ ለቀውለት ወደ እነ መከታው ጦር ፊታቸውን አዞሩ። ያለ ርህራሄ መቷቸው። የሞተው ሞቶ 40 ያሕል ታጣቂዎች ተማረኩ። ሁለት ብሬን ጨምሮ የሸዋ ዐማሮች ለመከታው ያስታጠቁት በርካታ የጦር መሣሪያም ተማረከ።

"…አሁን እነ መከታው ዋና ሥራቸው የሸዋ ፋኖንን እየወጉ ቦታዎችን ለመከላከያ አስረክቦ መውጣት ነው። በራሳ የተወሰነ ታጣቂ አስቀምጠው ወደ ተሬ ሄደዋል። 7 ለ70 ለረጅም ዓመታት ይዞት የነበረውን ለቅቆ ወደ ማጀቴ ሲሄድ እነሱ ተከትለው ኤፌሶን፣ አላላ፣ አርብ ገበያን ለመከላከያ አስረክበዋል። ወደ ሬማና መራቤቴ ሄደው እዚያም ለመኴ አስረክበው ፈርጥጠዋል።

"…በመጨረሻም በራሳ ተሃድሶ አድርገው ሲያበቁ በአልዩ አምባ በኩል ወደ ከሰም ሄደዋል። አንኮንበሮች አናሳልፍም ብለው ጥሩንባ ነፍተው ነው የገጠሟቸው። አሁን ሚጣቅ አማኑኤል አካባቢ ዐፋብኃን ለመግጠም ሰፍረዋል። ይሄ ለአፋሕድ በሸዋ የመጨረሻ ዕድሉ ነው።

• ነፍስ ይማር…!
🙏1.28K421👍263💔51😡37🏆3416🔥15🕊147🤯3
“…እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ።” 1ኛ ጢሞ 3፥16

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ
🙏1.18K263👍78🕊32😡10🤔6🏆42
2025/07/13 14:08:11
Back to Top
HTML Embed Code: