Telegram Web Link
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
መልካም…

"…ከዛሬ ሰኔ 13/10/ 2017 ዓም ጀምሮ ዘወትር አርብ አርብ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ "ፍኖተ ርቱዓን" የተሰኘና በመምህር ፋንታሁን ዋቄ እየተዘጋጀ የሚያቀርብላችሁ መርሀ ግብር በዘመድ ቴቪ ይቀርብላችኋል። ይሄ የዛሬ ምሽቱ ማስታወቂያ ነው።

"…በዚያውም ለዛሬ የምትሆን ብዬ ያዘጋጀሁላችሁን ትንሽዬ ሚጢዬ ርእሰ አንቀጽ ከእረፍት ስፍራዬ ሆኜ ብለቅላችሁስ ምን ይላችኋል? ዝግጁ ናችሁ? ስል ዝግጁ ነነ ዘመዴ የሚለው ድምጻችሁ ሁሉ ነው የናፈቀኝ።

• ዝግጁ ናችሁ…?
"ርእሰ አንቀጽ"

"…24/7~ 365 ቱንም ቀናት ያለማቋረጥ ለዓመታት ስጮህ፣ ዓይኔን በስልክ እስክሪን ላይ ተክዬ ቀን ከሌሊት፣ ክረምትና በጋ፣ በእግሬ እየሄድኩ፣ አውቶቡስ ላይ፣ አውሮጵላንና ባቡር ላይ፣ በጀልባም በመርከብም ላይ፣ በእንግድነት በሄድኩበት ቤት፣ ከጓደኞቼም ጋር ሰብሰብ ብዬ፣ ከቤተሰቦቼም ጋር ለዕረፍት በወጣሁበት ስፍራ ሁሉ እጄንና አእምሮዬን አጣምሬ፣ አቀናጅቼ ስጽፍ፣ በብዕሬ ስጮህ፣ እሪሪ ስል ኖሬአለሁ። ከማየው፣ ከምሰማው፣ ከሚላክልኝ ሰቀቀናም መረጃ የተነሣ ጨርቄን ጥዬም ሳላብድ የቀረሁት የእግዚአብሔር ጥበቃ ከእኔ ስላልተለየኝ ነበር። ምግብ የማያስበላ፣ ውኃ የማያስጠጣ፣ እንቅልፍ የማያስወስድ የሰቀቀን ዓመታት ነበር ያሳለፍኩት። እንዲያም ሆኜ እስከአሁን ጤነኛ መሆኔም ለራሴ ይገርመኛል። እግዚአብሔር ይመስገን።

"…ወደ ቀልቤ ከተመለስኩ ሁለት ሳምንት ሊሆነኝ ነው። ጠዋት ጠዋት መመስገን ያለበት ልዑል እግዚአብሔር እንዲመሰገን በር እከፍታለሁ። ከዚያ የስልክ ቀፎዬን ከእኔ አርቄ ወደ መናፈሻ፣ ወደ ፓርክ በመሄድ ለዘመናት ያጣሁትን ፀሐይ ስቀጠቀጥ ውዬ፣ በእግሬ እስከ 20ሺ እርምጃ ስራመድ አምሽቼ በሰላም ወደ ቤቴ እገባለሁ። ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ ድሮው እራት ከበላሁ በኋላ ምሽት ላይ እንቅልፌ መጥቶ መተኛት ጀምሬአለሁ። ለዘመናት የ3 እና የ4 ሰዓት እንቅልፍ ብቻ ተጠቃሚ የነበርኩ ሶዬ አሁን አርፍጄ ሁላ ነው ተነሥቼ እንደምን አደራችሁ የምለው። በሥነ ሥርዓት ይርበኝ፣ ይጠማኝ ጀምሯል። በጭንቀት ሊፈነዳ ይደርስ የነበረው አዕምሮዬ፣ ጭንቅላቴም አሁን ሰላሙን አግኝቷል። ከመጨነቄ የተነሣ የተዛባው የአተነፋፈስ ችግሬም ተስተካክሏል። እግዚአብሔር ይመስገን።

"…መረጃዎች፣ ማስረጃዎች አሁንም እንደ ጉድ ወደ እኔ መጉረፋቸው አልቀረም። እኔም ለመረጃ እና ማስረጃ ላኪ ወፎቼ መረጃው እንዳይባክን ደግሞ እስኪ ለሌሎቹም በዚህ በማንቃት ሙያ ላይ ለተሰማሩት ወገኖች ላኩላቸው በማለት እኔን ለጊዜው ተወት እንዲያደርጉኝ ከመማጸን አልቦዘንኩም። እኔ ግን ሰላሜን ነው ያገኘሁት፣ እንደ ዘንዶ ቆዳዬን፣ እንደ ንሥር ክንፎቼን አድሼ ለመምጣት እረፍት መድረግ የግድ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። በዚህ የሚያዝንብኝ፣ የሚያኮርፈኝም የለም። እርግጥ ነው ጦማሮቼን እንደ ሱስ የሚናፍቁ የትየለሌ ወዳጅ ቤተሰቦች እንዳሉኝ የታወቀ ነው። ጦማር መረጃዎቼን ወዳጅም ጠላትም በጉጉት እንደሚጠብቃቸው የታወቀም ነው። ብዙዎችን አንባቢ ለመድረጌም ራሳችሁ ምስክር ናችሁ። እየተሰደብኩ፣ እየተረገምኩ፣ እየተወቀጥኩም ቢሆን ለዓመታት ሳላቋርጥ እንደዜጋ ለሀገሬ፣ እንደ አማኝ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያኔ የበኩሌን ጠጠር ወርውሬ ሚጢጢዬ አስተዋጽኦም እንዳደርግኩ አምናለሁ። ይህ አገልግሎቴ የሚቀጥል ቢሆንም ነገር ግን 24/7 እኚኝ፣ ችክ አይኖርም። በተመጠነ መልኩ ነው የሚቀጥለው።

"…በዩቲዩብ፣ በቴሌግራም፣ በፌስቡክ፣ በቲክቶክ የእኔን ጦማር መነሻ አድርገው ሲወቅጡኝ፣ ሲሰድቡኝ፣ ሲረግሙኝ፣ ሲያበሻቅጡኝ የሚውሉ፣ በዚያውም አንጀራ ሆኜአቸው የከረምኳቸው ወገኖች እንኳ እኔ እኚኝ እንችክ ምንችክ ማለቴን ካቆምኩ በኋላ የት እንደገቡ እንኳ ነው ያጣኋቸው። እኔው አፈር ደቼ ገብቼ ያመጣሁትን መረጃ ምንጭ ሳይጠቅሱ ልክ ራሳቸው እንዳገኙት አድርገው ያጯጩሁ የነበሩና እንጀራቸውን ይጋግሩ የነበሩ ወንድሞችም እምስጥ ይግቡ ስምጥ አልታወቀም። ድራሽ አባታቸው ነው የጠፋው። አንዳቸውም የሉም። ያሉትም ቢሆን "ሁለት ሚልሻዎች ከነቆመህ ጠብቀኛቸው ተማረኩ፣ በስቦ ማስከዳት አንድ የመከላከያ አባል ሁለት ክላሽ ይዞ ፋኖን ተቀላቀለ፣ የቀበሌው ሊቀመንበር በቆንጆዎቹ ተገደለ፣ ቦታው እንጂ ልብሳቸው የማይቀየር 60 ፍሬ ኮማንዶዎች ተመረቁ፣ እገሌ ጀግና መሪ ነው። ቼ ጉቬራ ነው። ወዘተረፈ የሚል አኞ የሆነ የተለመደ፣ ደግሞም የተሰለቸ ዜና ከመዘገብ ያለፈ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ አልታየም። ከዋሸሁ እቀጣለሁ።

"…ለማንኛውም በእረፍት ሰዓቴ ሌላ ወሳኝ ጉዳይ ላይም እያተኮርኩ ነው። የዘመድ ሚዲያን ማጠናከር፣ የዘመድ ሚዲያን ግዙፍ ተቋም ማድረግ፣ የዘመድ ሚዲያን ለሁሉም በሁሉም ስፍራ ተደራሽ ማድረግ፣ እርሱ ላይ እየሠራሁ፣ እየደከምኩም ነው። ዘመድ ሚዲያ ሳምንቱን 24 ሰዓት ሙሉ እጅግ ግሩም ግሩም የሆኑ መርሀ ግብሮችን በመሥራት ለአድማጭ ተመልካቾቹ በማድረስ ላይ ነው የሚገኘው። ከሰኞ እስከ እሁድ የአየር ሰዓቱ ሙሉ ነው። በተለይ ከዛሬ ምሽት 2:00 ሰዓት ጀምሮ ዘወትር አርብ በተከታታይ መቅረብ የሚጀምረውና የመምህር ፋንታሁን ዋቄ ተዘጋጅቶ በዘመድ ቴሌቭዥን የሚተላለፈው "ፍኖተ ርቱዓን" የተሰኘው ሳምንታዊ መርሀ ግብር በሚዲያው ላይ ሲታከልበት የሚዲያው ደረጃም በእጅጉ ከፍ ይላል። አሁን ያለው የሚዲያው ሳምንታዊ መርሀ ግብሮችም የሚከተሉት ናቸው።

ሰኞ፣ እነ ሊቀጠበብት ተክሌ ሲራክ "ቤተ ተክሌ"
ማክሰኞ፦ ያሬድ ኃይለ ገብርኤል "አስተዋይ ሚዲያ"
ረቡዕ፦ አለልኝ መኳንንት " ኤሶጵ ኢትዮጵያ"
ሐሙስ፦ ኢትዮ ቤተሰብ እና አዲሱ ሚዲያ፣
አርብ፦ ፍኖተ ርቱዓን በ/ር ፋንታሁን እና ሐተታ በልጅ ተድላ መላኩ
ቅዳሜ፦ ፍኖተ ዐማራ በ አቶ አንተነህ ገላዬ
እሑድ፦ "ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር" ባለማቋረጥ በተከታታይ በመቅረብ ላይ ይገኛሉ።

"…የዘመድ ሚዲያ እንደ ጀመሪነቱ አይደለም። በጥቂት ቁርጠኛ ልጆች መልካምና በጎ ፈቃድ ሁሉም ያለውን ዕውቀት እና ገንዘብ አዋጥቶ የጀመረው ሚዲያ ነው። 318 ሠራዊተ ጌዴዎን፣ 120 የዘመድ ሚዲያ ቤተሰቦች በአጠቃላይ 438 ኢትዮጵያውያን ተሰባስበው የጀመሩት ሚዲያ ነው። የዘመድ ሚዲያ በእኔ ምክንያት ፌስቡክና ዩቲዩብ አያስተናግደውም። እዚያ ዩቲዩብና ፌስቡክ ውስጥ የሚሠሩ በግል እኔንና የእኔን አመለካከት በሚጠሉ ሰዎች ምክንያት የተነሣ፣ ሚዲያው ዘመድ ሚዲያ የሚል ስያሜ ስላለው ብቻ የዘመድኩን ነው በሚል እሳቤ ሚዲያው በዩቱዩብ ፕላትፎርም ላይ የራሱን ሓሳብ እንዳይሸጥ እገዳ ተድጎበታል። ስለዚህ ዘመድ ሚዲያን ለጊዜው በዪቱዩብ ላይ አንመለከተውም ማለት ነው። ነገር ግን በራምብል፣ በቲዊተር እና በዌብሳይታችን ያለ ምንም እንከን እስከ አሁን ድረስ መርሀ ግብሮቻችን በጥራት እየተላለፉ ይገኛሉ።

"…የዘመድ ሚዲያ ከጀመረ ሦስት ወር የሆነው ሲሆን አራተኛ ወሩም እየገባ ነው። ልብ በሉ እስከአሁን በየትኛውም ፕላትፎርም የሳታላይት ክፍያ ተብሎ አልተለመነም። በጎፈንድሚም፣ በፌስቡክም ሆነ በቲክቶክ አልተለመነም። እኔ ከመረጃ ቴሌቭዥን በገዛ ፈቃዴ መልቀቄን ተከትሎ ለምን ራሳችንም፣ አንተም በምታዘው ሚዲያ አትከሰትም የሚል ሓሳብ ባመጡ ሰዎች ቀስቃሽነትና ወትዋችነት በራሴው ቴሌግራም በተደረገ ጥሪ እና ጥሪውን ሰምተው በመጡ 438 ሰዎች መዋጮ በአጭር ቀናት ውስጥ የተመሠረተ ሚዲያ ነው። ሁሉ ነገር እጅግ ይደንቃል። የእግዚአብሔር ታላቅነትን የተማርኩበትም ነው የዘመድ ሚዲያ ምሥረታ። ደግሞም 24/7 365 ቀናት ሙሉ የደከምኩትን ድካምም ፍሬ አፍርቶ ያየሁበትም ነው የዘመድ ሚዲያ። የዘራሁት ዘር ጭንጫ ላይ፣ እሾህ ላይ፣ ሜዳም ላይ ተበትኖ ባክኖና መክኖ እንዳልቀረም ያየሁበት ነው የዘመድ ሚዲያ። የምስጋና ቃላትም የለኝም።👇
👆 "…የቦርዱ ጥራት፣ የአባላቱ ጥራት የሚገርም ነው። እኔን ጨምሮ በሳታላይት የቴሌቭዥን ስርጭት ላይ ምንም ዓይነት ልምድ የሌለን ሰዎች ተሰብስበን ሳለ ነገር ግን በሠራዊተ ጌዴዎን ስብስብ ውስጥ ለዚሁ ዓላማ ሲባል የተመረጡ ይመስል ቁጥራቸው ቀላል ያልሆነ ባለሙያዎችም ተሳታፊ ነበሩ። የዘመድ ሚዲያ እነዚህን ባለሙያዎች በማጣመር ነው የሳታላይት ስርጭቱ ውጤታማና ተግባራዊ እንዲሆን ያደረገው። የዘመድ ሚዲያ የአይቲ ባለሙያዎች ስብስብ ሌት ተቀን፣ የግልም፣ የመንግሥትም ሥራቸውን በመበደል፣ ምሳና ቁርስ ሳይበሉ፣ አንዳንዴ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ከተቀመጡበት ሳይነሡ ከሠራን አይቀርማ የአንድ ተቋም ሳይሆን የአንድ ሀገር ተቋም እንሥራ በማለት ዕውቀታቸውን አዋጥተው የዘመድ ሚዲያን ከብዙ ወጪና ድካም ታድገው እውን አድርገውታል። ያለ ዘመድ ሚዲያ የአይቲ ግሩፕ አባላት የዘመድ ሚዲያ በጭራሽ እውን አይሆንም ማለት ይቻላል።

"…የዘመድ ሚዲያ የአይቲ አባላት ከወራት ድካም በኋላ የዘመድ ሚዲያ የራሱ መሥራችና ቋሚ አባላትን በመመዝገብ ተቋሙ ለልመና አደባባይ ሳይወጣ በአባላቱ ወርሀዊ መዋጮ ብቻ ለማስኬድ ይቻለው ዘንድ ዌብሳይቱን ሲያበለፅግ ከርሞ አሁን ባለፈው ሳምንት ፍጻሜውን አግኝቷል። በዚህም መሠረት ወደ ሰፊው ሕዝብ ከመምጣታችን በፊት የዘመድ ሚዲያን የመሠረቱት አባላት ቅድሚያ ማግኘት ስላለባቸው የዘመድ ሚዲያ መሥራች 438 አባላቱ በውስጥ መስመር በአባላቱ የቴሌግራም ገጽ ላይ ጥሪ ቀርቦላቸው አባላቱ መመዝገብ ጀምረዋል። እስከ አሁን ጥሪው ከደረሳቸው 438 አባላት መካከል መልእክቱን ያዩ ኢሜላቸውን በመላክ ማረጋገጫ የሰጡ 243 አባላት ተገኝተዋል። ይቅርታ አሁን ነው መልእክቱን ያየሁት በማለት ዛሬም ድረስ የአይቲው ቡድን ላቀረበው መልእክት መልስ በመስጠት ላይም ናቸው። በዚህ ሳምንት ተደጋጋሚ ጥሪ በማድረግ ሁሉም ማረጋገጫ ከሰጡን በኋላ ወደ ቀጣዩ መርሀ ግብር እንሄዳለን። ቀጣዩ መርሀ ግብርም የዘመድ ሚዲያ ባበለፀገው ቴክኖሎጂ ተጠቅመን ሁሉም አባላት የሚገኙበት ታላቅ ስብሰባ ማድረግ ነው። ከዚያ አለቀ።

"…በዘመድ ሚዲያ የኢትዮጵያን ትንሣኤ እናበሥራለን። በዘመድ ሚዲያ የፈራረሱ ጥንታውያን ገዳማትና አድባራት፣ በየመቃብር ቤቱ የወደቁ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እንደ ልጅነታችን በያሉበት ፈልገናቸው እንዲረዱ እናደርጋለን። በዘመድ ሚዲያ ወደፊት ወላጅ አልባ ሕፃናት ቢያንስ ከትምህርት የማይርቁበትን ዕድል እናመቻቻለን፣ በፈረሰው የኢትዮጵያ ገጽ በኩል ቆመን የልጅነታችንን ሓላፊነት እንወጣለን። ደሀ ተበደለ፣ ፍርድ ተጓደለ ማለታችንን አጠናክረን እንቀጥልበታለን። የዘመድ ሚዲያ እንደ አጀማመሩ ፍጻሜውም እንዲያምር አብዝታችሁ ትጸልዩልን ዘንድ እማጸናችኋለሁ። 🙏

"…በቀጣይ የዘመድ ሚዲያ የዜና ክፍሉን ያደራጃል። የተለያዩ መርሀ ግብሮችንም ይቀርጻል። አባላት በበዙ ቁጥር ኢትዮጵያ ውስጥ ላሉ ወጣቶችም የሥራ ዕድልም ይፈጥርላቸዋል። የዘመድ ሚዲያ እስከአሁን የሳታላይት ክፍያው ሳይቋረጥ፣ የሳታላይት ቴክኒሺያኑ ደሞዝም ሳይቋረጥ፣ የአይቲ ግሩፑም ለሚዲያው ዌብሳይት የሚፈለጉ ሶፍትዌሮች ግዢም ከፍሎ በመግዛት ያለተጨማሪ መዋጮ በአንድ ጊዜ መዋጮ ብቻ እስከአሁን ድረስ ቆይቷል። ብዙዎች የዘመድ ሚዲያ አባላት እንዴ ምንድነው አንዴ ባዋጣነው እኮ ነው እስከአሁን ያለነው። እናዋጣ እንጂ እያሉ በተደጋጋሚ ቢጠይቁኝም እያልኳቸው ያለሁት ይሄ የዘመድ ሚዲያ ነው። ያዋጣችሁት ብር ሳያልቅ የምን መዋጮ ነው። ከእንግዲህ መዋጮውም ቢሆን በሲስተም፣ የአይቲ ቡድኑ ባበለፀገው ሕጋዊ የገንዘብ መክፈያ ሲስተም እንጂ በልመና፣ በውትወታም አይሆንም። እሱን እንጠብቅ እያልኩ ነበር ለሁሉም ስመልስ የቆየሁት። ከ438 አባላት ውጪ ያሉትንም ወደ ሠራዊተ ጌዴዎን ለመቀላቀል የተዘጋጀም ፕላት ፎርም እንዳለ የአይቲ ባለሙያዎቹም አሳውቀውናል። የቋሚ አባላቱ ምዝገባ ከተጠናቀቀ በኋላ አዳዲስ ሠራዊተ ጌዴዎን የዘመድ ሚዲያ አባላትንም ወደመመዝገቡ እንሄዳለን ማለት ነው። የዘመድ ሚዲያ አባላት ሆናችሁ እስከአሁን በቴሌግራም ግሩፓችን ውስጥ ኢሜይላችሁን ላኩ ተብላችሁ ኢሜይል ያልላካችሁ 195 ቀሪ አባላትም በፍጥነት ትልኩልን ዘንድም በድጋሚ ጥሪያችንን እናቀርባለን። ፍጠኑ።

"…በተረፈ የዓለሙንም ሆነ የኢትዮጵያን ጉዳይ በአይነ ቁራኛ መከታተላችሁን አታቁሙ። መጪው ክረምት በኢትዮጵያ ከበድ ሊል ስለሚችል ከበዛ ጸሎት ጋር ራስን ማዘጋጀታችሁን አትዘንጉ። በሰሜን በኩል ሁለቱ ትግሬዎች ከታች አገዛዙ መሃል ላይ ዐማራን ሳንዱች እንዳያደርጉት ዐማሮቹ ከምንግዜውም በላይ በንቃት ልትዘጋጁ የሚገባ ሰዓት መሆኑን ዐውቃችሁ ልትንቀሳቀሱ እንደሚገባም ልታውቁ ይገባል። ትግሬ ወልቃይትን ካላገኘ ህልውና እንደሌለው ስለተሰበከ ወልቃይት ፀገዴና ራያ ዳግም ደም መፋሰስ ሊኖር ይችላል የሚለው ግምት እያየለ መምጣቱን ዐውቃችሁ ዐማሮች ከወትሮው በተለየ መልኩ በተጠንቀቅ ልትቆሙ እንደሚገባችሁ ዛሬም በድጋሚ ቢነገራችሁ አይረፍድም። እናም ራሳችሁን አዘጋጁ። ወልቃይቶችም ከብልፅግና ጋር ሆናችሁ ከፋኖና ከትግሬ ጋር ተዋግታችሁ አትዘልቁምና አሰላለፋችሁን ከወዲሁ ብትለዩ ለእናንተም ጥሩ ነው። ፋኖም ላይ ወያኔ ትግሬም ላይ ተኩሳችሁ ልታሸንፉ የምትችሉ አይመስለኝም። ከዳግም ስደት፣ ውርደት ለመዳን ወልቃይቶች ከወዲሁ ሚናችሁን ብትለዩ ለእናንተ ሸጋ ነው። ለወልቃይቶች የሚሻላችሁ የሚበጃችሁም ዐማራው ይመስለኛል።

"…ሰሞኑን በታዬ ደንደአ ንግግር እየተደመማችሁ ያላችሁ ባለ ሾርት ሚሞሪያም ዐማሮችም ወደ ቀልባችሁ ብትመለሱ ሸጉ ነው። እኔ የሚገርመኝ ለዘመናት የተቀዳ የስብሰባ የድምጽ ቅጂ አውጥቼ ስለቅላችሁ፣ ከፈረሱ ከሽመልስ አብዲሳ አፍ የተገኘውን ስነግራችሁ ከርሜ አሁን ደርሶ ታዬ ደንደአ አዲስ ግኝት ያገኘና ዛሬውኑ እንደ አዲስ እንደሰማ ሰው አፋችሁን ከፍታችሁ ፈዛችሁ የምትቀሩት ነገር ነው ያልገባኝ። ታዬ ደንደአ ምንም አዲስ የነገራችሁ ነገር የለም። ታዬ ደንደአ እንዲያውም አቢይ ዐማራን አጠፋለሁ ብሎኛል ብሎ በመናገር በስተመጨረሻ ለጽንፈኛ የኦሮሞ ብሔርተኞች "እንዲያማ ከሆነ፣ አቢይ አሕመድ ዐማራን የሚያጠፋልን ከሆነ፣ ይሄንንም ራሱ ታዬ ከነገረን ብንጠላውም ከአቢይ ጋር እንሰለፍ፣ ከአቢይ ጎን እንቁም እንዲሉና የበለጠ ከአቢይ ጎን እንዲሰለፉ የሚያደርግ ፕሮፓጋንዳ ነው የተሠራለት ለአቢይ። አንድም ሰው ዙሪያ ገባውን አይቶ በዚህ ጉዳይ ላይ ሾተላይ ሓሳቡን ነቅሶ አውጥቶ ግብረ መልስ ሲሰጥ አላየሁም። በተለይ የዐማራ ሚዲያዎች ፍጠኑ እንጂ። አትፍዘዙ።

"…አቶ ታዬ ደንደአ ቀደም ሲል በብዕር ስም ለኢትዮ ፎረም ሲሰጥ የነበረውን ነው አሁን በግንባር ወጥቶ ለኦሮሞ ሚዲያዎች በኦሮሚኛና በአማርኛ ደጋግሞ እንዲጮህ የተደረገው። መሳይ መኮንን፣ ፕሮፌሰር ትንግርቱ ገብረ ጻድቅ፣ ሌሎቹም የዐማራ አክቲቪስቶች በአቶ ታዬ ደንደአ ንግግር ተደምመው ለሃጫቸው እስኪዝረበረብ ድረስ ጉድ፣ ጉድ ሚስጢር ወጣ እያሉ ሥራቸውን ረስተው ነገር ዓለሙን ሁሉ ትተው " ኦቦ ታዬ አቢይ አሕመድ ዐማራን አጠፋለሁ" ብሎኛል ብሎ ነገረን በማለት ሥራ ሲፈቱ አያለሁ። ዐማራው እንደሚያጠፉት ዐውቆ ጫካ ከገባ እኮ ሁለት ዓመት ሆነው። ዐማራው ነገር ዓለሙ ገብቶት መሰባሰብ፣ በኅልውናው ላይ መምከር ከጀመረ እኮ ስድስት ዓመታት አለፉት። ዛሬ ነው እንዴ አቢይ ዐማራን እንደሚያጠፋው ከታዬ አፍ ተሰምቶ የምትደመመው? ሰማኸው እሺ ምን አደረግክ? ምንስ አመጣህ? አለቀ። ለወሬ የለውም ፍሬ።👇
👆 "…እስከአሁን የህልውና ስጋት የለብኝም የሚል ዐማራ ካለ መቼም ጉድ ነው። የህልውና ስጋት ስላለ መሰለኝ የዐማራ ፋኖ ዱር ቤቴ ብሎ የተቀመጠው፣ በዚያም ከአገዛዙ ጋር የሚፋለመው። እነ ሽመልስ በአደባባይ፣ አቢይ አሕመድ በባሌም፣ በነቀምቴም፣ በፓርላማም በድፍረት የተናገሩትን፣ በአምቦ ሺዎችን ሰብስቦ እናጠፋቸዋለን ብሎ ያለውን ዛሬ ከታዬ አንደበት ሰማሁ ብሎ እንደ አዲስ ያዙኝ ልቀቁኝ ማለትስ ምንድነው? ስለ ሰሜን ዕዝስ ቢሆን የኦሮሞ ጄነራሎቹ በቅድሚያ ተመረዝን፣ ሆዳችንን አመመን ብለው አስቀድመው ወጥተው፣ ከወያኔ ጋርም ተጠቃቅሰው በሰሜን ዕዝ ውስጥ ያሉ ከ600 በላይ የዐማራ የጦር መኮንኖች በተኙበት መታረዳቸውን፣ ኢትዮጵያዊነትን የሚያንጸባርቁ የደቡብ ልጆችም በዘዴ መጽዳታቸውን ቀድመን አይደል እንዴ የነገርናችሁ። ታዬ ደንደአ ስለ ሰሜን ዕዝ በሴራ መሞት እንጂ የሞቱት የሰሜን ዕዝ አባላት፣ የተጨፈጨፉት አብዛኛው ዐማሮች መሆኑን መች ነገራችሁ? እውነቱ ይኸው ነው። እናም በተለይ ጋሽ ፍሮፌሰር ትንግርቱ ገብረ ጻድቅ ትንሽ ብትረጋጋ ሸጋ ነው። ትግሬና ዐማራን እንድታባላ በአሚኮ የአየር ሰዓት ተሰጥቶህ ስታቅራራ ከርመህ፣ ቆይቶ ደግሞ መስከረም አበራ ታስራ ዘብጥያ ወርዳ አንተ በቀይ ምንጣፍ በቦሌ እንድትወጣ ተደርጎ ሲያበቃ አሁን ደግሞ ደርሰህ የታዬ ደንደአ ምላስ ልሁን ባትል ሸጋ ነው። ታዬ ደንደአ ራሱ የዐማራ ገዳይ፣ አስገዳይ፣ የፍትሕ ቀን ሲመጣ ለፍርድ የሚቀርብ ሰው ነው። ኦነግ ከመቼ ወዲህ ነው ለዐማራ ሲያዝን ያየኸውና ነው እንዲህ በደረቁ መላጣዬን ላበጥር የምትለው? እረፍ እንጂ ትንጌ፣ መሳይ መኮንን እና ኢትዮ ፎረሞች እንኳ እሺ ለደንታቸው ነው። አንተ ግን በዐማራ ሚዲያ ላይ ሆነህ ለዐማራ የሚጠቅመውን ብትሠራ ነው የሚበጀው ባይ ነኝ? ትግርቱ ግን ጴንጤ ነው ኦርቶዶክስ? ለማወቅ ያህል ነው።

"…በዚህ ሰዓት ከወደፊት ጉዞው ለአፍታ ያህል ቆሞ መንገድ ላይ "ስብሐት ነጋን፣ ስታሊን ገብረ ሥላሴን፣ አሉላ ሰሎሞንን፣ ልደቱ አያሌውን፣ ታዬ ደንደአን፣ ሕዝቅኤል ጋቢሳን፣ ፀጋዬ አራርሳን፣ ታዬ ደንደአን፣ ጃዋር መሀመድን የሚሰማ በተለይ ዐማራ የሆነ ሰው አእምሮው የተበላሸ፣ በሽተኛ፣ ማሰብ የማይችል፣ ዘገምተኛ የሆነ ብቻ ነው። እነዚህ ለዐማራው ትግል ምንም ዓይነት ረብ የማያስገኙ፣ በተለይም አንዳንዶቹ ዘመን ሲመጣ በዐማራ የዘር ማጥፋት ወንጀል ለፍርድ የሚፈለጉ አረመኔዎችን ቆሞ መስማት የምር የጤና መጓደል ምልክትም ነው። ስንትና ስንት የሚሰሙ ዐማሮች ሞልተው እያለ የዐማራን ጉዳይ ከፀረ ዐማሮች ለመስማት መጓጓት ከምር መረገም ነው። ሰማህ፣ ሰማህ፣ ሰማህ፣ አየህም ጭምር። አሁን መስማት አይደለም የሚፈለገው ፕሮፓጋንዳ፣ ማነቃቃትም አይደለም የሚፈለገው። አሁን ተግባር ብቻ ተግባር  ነው የሚያስፈልገው። አሁን መሰባሰብም፣ መምከርም አይደለም የሚፈለገው፣ አሁን የሚፈለገው፣ የሚጠበቀውም ተግባር ብቻ ነው። የወሬ፣ የፕሮፓጋንዳ ወራቶች አልፈዋል። የመቼህን ገና ድሮ ነው ያለፈው። አሁን እኮ ከድንጋይ ወደ ጥይት፣ ከምንሽር ወደ ሞርታር ባለቤትነት ተሸጋግረሃል። አሁን እኮ ቢያንስ ጥሎ የሚወድቅ እንጂ በብላሽ የማይገደል የዐማራ ትውልድ ተፈጥሯል። ዝብርቅርቅ ያለውን የዐማራ ፋኖ ወደ አንድ አምጥተህ ወደፊት መስፈንጠር ነው እንጂ ኦቦ ታዬ ደንደአ እኮ አቢይ እንደሚያጠፋን ነገረን፣ ስለዚህ ለታዬ ደንደአ ባህርዳር ላይ ነው ሃውልት የምናቆምለት እያልክ ራስህን በራስህ የምታረካበት ወቅት አይደለም። "በግሬደር ስትቀበር፣ ለአስከሬንህ ጥላ እንዲሆን ዛፍ እተክልልሃለሁ ሲልህ፣ ከአዲስ አበባ ሙልጭ አድርጎ ሲያፈናቅልህ፣ ቀበሌ ሙሉ ዐማራ ጨፍጭፎ ፎቶ አንሥቶ ሲለጥፍልህ፣ በኦሮሚያ አጋድሞ ሲያርድህ፣ ኧረ ሕዝብ አለቀ ብለው የተናገሩ ከንቲባ አርፈህ ተኛ ቢያልቅ ምንአገባህ መባላቸውን ከታዬ በፊት እኮ ነው የሰማኸው። በሻሸመኔ፣ በወለጋ፣ በጅማ፣ በባሌ፣ በአሩሲ፣ በሀረርጌ የተጨፈጨፉ ዐማሮችን በቪድዮና በፎቶ ስታይ የከረምከው እኮ ከታዬ በፊት ነው። ታዬ ኦነግ ነው። ታዬ ብልጽግናን የመራ፣ ያደራጀ ወንጀለኛ ግለሰብ ነው። እሱን ማድመጥ ትተህ ቀድመው ነቅተው ለህልውናህ ጫካ የገቡትን፣ ብረት ነፍጥ ያነሡትን ፋኖዎች አግዝ። እርዳ። ጸልይላቸውም።

"…በተረፈ እደግመዋለሁ። ሁሉንም ነገር በአንክሮ እየተከታተልኩ ነው። እያየሁትም ነው። የዘንድሮው ክረምት እንዳያመልጣችሁ መሳሳቡን ትታችሁ በአንድነት ቁሙ። እደግመዋለሁ። ዐማራ በአንድነት ቁም። ወያኔም ካይ፣ ከታች ኦሮሙማው በጥቅሴ ሰይፋቸውን ያነሡብሃል። አሁንም እደግመዋለሁ ሰዓት የላችሁም። ነፃነት ወይም ዘላመማዊ ባርነት ከፊታችሁ ቆሟል። እንደ ኩርድ ከመጥፋት እንደ እስራኤል በመከራ ውስጥ አልፎ ህልውናህን ማረጋገጥ ነው የሚበጅ የሚሻልህ። ከተኩሱ ባሻገር ፖለቲካውን የሚጫወቱ ተጫዋቾችን መርጣችሁ ቅረቡ። ተኩስ ብቻውን አሸናፊ አያደርግምና ዲፕሎማሲው ላይ የሚሠሩም ተጫዋቾችን መርጣችሁ በቶሎ አሳውቁ። በየጓዳው ራሳቸውን የሀብት አሰባሳቢ ያደ
አድርገው የሾሙ ልማደኛ ማጅራት መቺዎች ሕዝቡን ከመዝረፋቸው በፊት ያመናችሁባቸውን የሀብት አሰባሳቢ ግብረ ኃይልም ከወዲሁ አቋቁማችሁ ይፋ አድርጉ። ፍጠኑ።

• እንዲሁ አልፎ አልፎ ብቅ እላለሁ። በዘመድ ቴቪ የሚቀርበው ሳምንታዊው የእሑድ ምሽት ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር መርሀ ግብሬ አይቋረጥም። ከረጅሙ እረፍት መልስ ግን በተለመደው ባሕሪዬ ግብግቡን እቀጥላለሁ። በእረፍቴ መሃልም እንዲሁ አንዳንድ ጊዜ ብቅ እላለሁ። እስከዚያው ድረስ ግን ሁላችሁም ነቃ ብላችሁ ቁሙ። ነገ ይሄ ሊከሰት ይችላል ብላችሁ አስቀድማችሁ እንደ አስራኤል ራሳችሁን አጠንክሩ፣ እንደ ኢራንም በምድር ላይ ሳይሆን ከምድር በታችም አስቡ። ዘመኑን ዋጁ። አልፎ ሂያጁ አይቆጣጠራችሁ። ከሚነግሯችሁ ይልቅ የደረሰባችሁ ምስክር ይሁናችሁ። እደግመዋለሁ ዘመኑን ዋጁ።

• ቆይቼ የአስተያየት መስጫ ሰንዱቁን እከፍትላችኋለሁ። እስከዚያው መልካም ንባብ ጎዶኞቼ።

"…ሻሎም…!   ሰላም…!
የአፈና ዜና…

"…አቶ ዳንኤል ክብረት ቂም የያዘባቸው፣ በጦማሩ ሲጠቅሳቸው የከረመው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት ሰሜን ሜጫ ወረዳ ቤተ ክህነት ድል በትግል ቀበሌ የምትገኘው የፈለገ ብርሃን ናዳ ቅድስት ማርያም እና የክብረ ደናግል ናዳ ቅዱስ ላሊበላ አንድነት ገዳም
አበምኔት የሆኑትን ታላቁ አራት ዓይናው የአራቱ ጉባኤ መምህር፥ የፍትሐ ነገሥቱ፣ የአቡሻኸሩ ሊቅና የቅኔው ጌታ ሊቀ ብርሃናት ቆሞስ አባ ይባቤ በላይ ዛሬ ሰኔ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ወደ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት አካባቢ ወደ ገዳሙ ባቀኑ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ለጥያቄ እንፈልግዎታለን ተብለው በወታደር አጀብ መወሰዳቸው ተነግሯል።

"…የአይን ምስክሮቹ እንደነገሩኝ ከሆነ መጀመሪያ ለአንዳንድ ጥያቄ እንፈልግዎታለን ብለው ወደ ቢኮሎ ዓባይ ወሰዷቸው። በዚያም አርበኛ ዘመነ ካሤን ካለበት ፈልገው ካላመጡት አንለቅዎትም በማለት በዚያ አዋሉአቸው፣ በመቀጠልም ከቢኮሎ ዓባይ አዙረው ወደ ዱር ቤቴ ወሰዷቸው፣ በዚያም መንፈሳዊ ልጅዎ ነውና አርበኛ ዘመነ ካሤን ይውለዱ ሲሏዋቸው ዋሉ ከዚያ ሲመሽ አሁን ምሽት ላይ ወደ ባህርዳር አምጥተው ባህርዳር በመከላከያ ካምፕ መኮድ ውስጥ እንዳሰሯቸው ተሰምቷል።

"…አቶ ፓስተር ምስጋናው አንዷለም አስር ጊዜ የኔታ ይባቤ የኔታ ይባቤ እያለ የሚከሳቸው፣ የደቡብ ጎንደሮቹ አፍቃሬ ብአዴኖቹ እነ አያሌው መንበርም በተደጋጋሚ የሚዝቱባቸው አራት ዓይናው ሊቅ የኔታ ይባቤ በስተመጨረሻ በኦሮሙማው አገዛዝ እጅ ወድቀዋል። ቀጥሎ ምን ይሆናል? አብረን እናያለን። የክሱ መነሻም 7ተኛው ንጉሥ የአሕመድ ልጅ ሳይሞት አርበኛ ዘመነ ካሤን ለንግሥና ቀብተዋል የሚል ነው። ከዚህ ቀደም እስክንድር ነጋ ይነግሣል ተብሎ ደብረ ኤልያስ መውደሙ የሚታወስ ነው።

• ሻሎም…! ሰላም…!
"…መስማትን ትሰማላችሁና አታስተውሉም፥ ማየትንም ታያላችሁና አትመለከቱም፤ በዓይናቸው እንዳያዩ በጆሮአቸው እንዳይሰሙ በልባቸውም እንዳያስተውሉ ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአል ጆሮአቸውም ደንቁሮአል ዓይናቸውንም ጨፍነዋል… የሐዋ 28፥ 26-27

• እንደምን አደራችሁ?
• እንደምን አረፈዳችሁ?
• እንደምን ዋላችሁ?
• እንደምን አመሻችሁ?

• መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ
"…የመቅደሳችን ስፍራ ከጥንት ጀምሮ ክፍ ያለ የክብር ዙፋን ነው።” ኤር 17፥12… “…ምስጋናና ውበት በፊቱ፥ ቅዱስነትና ግርማ በመቅደሱ ውስጥ ናቸው።” መዝ 96፥6። “…ቤተ መቅደስህ ቅዱስ ነው በጽድቅም ድንቅ ነው። በምድር ዳርቻ ሁሉና በሩቅ ባሕር ውስጥ ላሉ ተስፋቸው የሆንህ፥ አምላካችንና መድኃኒታችን ሆይ፥ ስማን።” መዝ 65፥5

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ
አላችሁ አይደል…?

"…እሁድ ምሽትማ እረፍት ብሎ ነገር የለም። አረፍ ያልኩት ከቴሌግራም ላይ ችክቸካው ነው እንጂ ከዘመድ ቴቪው ሳምንታዊ መርሀ ግብሬማ አልቀርም። ዛሬም እንደሳምንቱ "ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር" የተሰኘው ተጠባቂው ሳምንታዊ የቴሌቭዥን መርሀ ግብሬ ከአዳዲስ ሓሳቦች ጋር በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ምሽት 1:00 ሰዓት ላይ ሰዓቱን ጠብቆ ከተፍ ይላል። ባለሁበት ሀገር በአጎት ሀገር ጀርመን የዛሬው የአየር ጠባይ ሙቀቱ ከባድ ነው። አጀዝቦም ነው የሚያስቀምጥ። አያላውስምም። የሆነው ቢሆን ግን ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር አይታጎልም። በረዶ ታቅፌም ቢሆን ይካሄዳል እንጂ መርሀ ግብሬ እንደሁ አይቋረጥም።

"…እንደተለመደው በዛሬው መርሀ ግብሬም የሚመከረው ይመከራል፣ የሚዘከረው ይዘከራል፣ የሚነቆረው ይነቆራል፣ የሚሸነቆጠው ይሸነቆጣል፣ ሾተላዩ፣ ሴረኛው ይነቀላል፣ አስመሳይ ቀጣፊ ወሻውም ይነከራል፣ ፊት ዓይቶ ማድላት፣ ዘመዴ ነው፣ ቤተሰብ ጓደኛዬ ብሎ መሸፋፈን በእኔ ዘንድ አይሠራም። "ነጭ ነጯን" ብቻ። የተኛው እንዲነቃ፣ የነቃውም ነቅቶ እንዲበቃ፣ የተሰወረው፣ የተሸሸገው፣ የተደበቀው እንዲገለጥ፣ የበግ ለምድ የለበሰው ነጣቂ ተኩላ መሆኑም እንዲታወቅ፣ ለመልካሙ ሥራ እና ሠራተኛም ዕውቅና በመስጠት፣ ደሀ ተበደለ ፍርድ ተጓደለም ለማለት፣ እኔ ዘመዴ ሰዓቴን ጠብቄ በዘመድ ቴቪ ከተፍ እላለሁ። ጠብቁኝ።

• አላችሁ አይደል…?
"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር

"…በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ምሽት ልክ 1:05 ሲሆን በዘመድ ቴቪ ላይ የቀጥታ ስርጭት መርሀ ግብሩ ይጀምራል። እንደተለመደው ገባ ገባ በሉና ጠብቁን።

• ZemedTv 👉 zemedtv.com

• በትዊተር (×) 👉 https://x.com/i/broadcasts/1dRKZYLQZygxB

• በራምብል 👉 https://rumble.com/v6v5usp--zemede-june-22-2025.html?e9s=src_v1_upp_a

• በሳታላይት ቴሌቭዥን 👉 Yahsat 52.5° East
                                       11977 H 27500
• ላይ ይከታተሉን።

"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።

👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia

👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።

• ሰብሰብ ብላችሁ ጠብቁን…!
• ጀምረናል…

ገባገባ በሉማ…

• አላችሁ አይደል…?
"…ምክራቸውን ጥልቅ አድርገው ከእግዚአብሔር ለሚሰውሩ፥ ሥራቸውንም በጨለማ ውስጥ አድርገው ማን ያየናል? ወይስ ማን ያውቀናል? ለሚሉ ወዮላቸው! ኢሳ 29፥15 

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ
ሌላ የአፈና ዜና…

"…የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት የሆኑ ጥንታውያን ገዳማትና አድባራትን በማስጎብኘት፣ ሕዝብ አስተባብሮም የፈረሰውን በማሳነጽ የሚታወቀው፣ የማኅበረ ወይንዬ አቡነ ተክለሃይማኖት መንፈሳዊ ማኅበርና ስለ ኢትዮጵያ ዝም አንልም ትውልድን ከግበረ ሰዶም እንታደግ የተሰኘው ማኅበር መሥራቹ የአደባባይ ሰው መምህር ደረጄ ነጋሽ (ዘወይንዬ) በዛሬው ዕለት ምሳ ሰዓት አካባቢ ሰዓሊተ ምህረት ኢትዮ ቻይና ኮሌጅ ፊት ለፊት ከሚገኘው ቢሮው ውስጥ በሥራ ላይ እንዳለ ታርጋ ቁጥሩ ኮድ ② አአ 64813 በሆነ መኪና በመጡና የደኅንነት ሰዎች እንደሆኑ የገለጹ አካላት አፍነው ይዘውት እንደሄዱ በስፍራው የነበሩ የዓይን እማኞች ለዘመድ ሚዲያ ገልፀዋል።

"…በጎጃም አራት አይናው ሊቅ የኔታ ይባቤ በታፈኑ፣ በምሥራቅ ሸዋ የዝቋላ መነኮሳት በታረዱና በተጨፈጨፉ ማግሥት በዛሬው ዕለት ደግሞ ደፋሩ፣ ፊትለፊት የግንባር ሥጋ የሆነው፣ ለተጎዱ፣ ለተጠቁ ሁሉ ያለመሳቀቅ በድፍረት ከፊት ረድፍ ተሰላፊው፣ በሀገሩ በኢትዮጵያና በሃይማኖቱ በተዋሕዶ ድርድር የማያውቀው መምህር ደረጄ ነጋሽም ዕጣው ደርሶት መታፈኑ ተገልጿል። ቤተሰቦቹ ፍለጋ ላይ ቢሆኑም እስከአሁን እኔ ጋር ነው የሚል ተቋም እንደሌለም ነው የተገለጸው።

"…በሌላ ዜናም በደብረ ከርቤ ግሸን ማርያም፣ በደብረ ሮሀ ቅዱስ ላሊበላ ራሳቸው ጠላ ጠምቀው፣ ዳቦ ደፍተው፣ እንጀራ ጋግረው፣ ራሳቸው ቆመው ነዳያንን በማብላት የሚታወቁትና በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት የታላቁ የአርበሐራ መድኃኔዓለም ገዳም አባት የሆኑት አባ ገብረመድህን አበበም ያለፈው አርብ ለሥራ ጉዳይ አዲስ አበባ መጥተው ለገጣፎ አካባቢ የመንግሥት ኃይሎች ነን በሚሉ አካላት ታፍነው ከተወሰዱ በኋላ እስከአሁን የት እንዳሉ እንዳልታወቀም ተሰምቷል።

• ማነህ ባለ ሳምንት…?
የግድያ እና የአፈና ዜና…!

"…በፎቶው ላይ የሚታዩት ቄስ ዮሐንስ ግርማ የተባሉና በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ሀገረ ስብከት በሸገር ሀገረ ስብከት የዓለም ገና ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የሆኑት ካህን ባለፈው ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ ለአገልግሎት ወደ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ ላይ ሳሉ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ደጃፍ ላይ ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ በተባሉ ኃይሎች በጩቤ ተወጋግተው መገደላቸውን ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ ዘግቧል።

"…በዚያው በሸገር ሲቲ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በሚያስተዳድሩት ሀገረ ስብከት የቦሌ አራብሳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም የስብከተ ወንጌል ሓላፊ እና የአንድ ልጅ አባት የሆኑት መምህር ብርሃነ መስቀል የካቲት 16/2017 ዓም ምሽት 4:00 ሰዓት ላይ በመኖሪያ ቤታቸው ሳሉ ምንም ዓይነት መለዮ ባልለበሱና የፖሊስ ፓትሮል በያዙ በቁጥር ስምንት በሚሆኑ አፋኞች ታፍነው የደረሱበት ከጠፋ እነሆ አምስት ወር እንደሆናቸው ተነግሯል።

"…በተያያዘ ዜና በዛሬው ዕለት ከሥራ ቦታው የታፈነው መምህር ደረጀ ነጋሽ (ዘወይንዬ) ከዜናው መበተን በኋላ በስተመጨረሻ ሜክሲኮ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ በሚገኘው የእስረኞች ማቆያ ውስጥ እንደሚገኝ የመረጃ ምንቼ አድርሰውኛል። የእስሩም ምክንያት መምህሩ በጤና ባለሙያዎቹ የደሞዝ ጥያቄ ዙሪያ በሠራው ቪድዮ ምክንያት በጠቅላይ ሚንስትሩ በአቢይ አሕመድ ቀጥተኛ ትእዛዝ ምክንያት ለምርመራ መወሰዱ ነው የፖሊስ ምንጮቼ የገለጹልኝ።

"… የሰኔ የደም ግብርም ያለእንከን እየተፈጸመ ነው። ከኦሮሚያና ከሸገር ሲቲም ካህናት መነኮሳትም እየጸዱ ነው። አቡነ ሳዊሮስ እና አቡነ ዲዮስቆሮስም ሥራቸውን አገዛዙን ደስ በሚያሰኝ መንገድ እየፈጸሙ ይመስላል። የኔታ ይባቤም እስከአሁን ድረስ አልተፈቱም። እዚያው ባሕርዳር መኮድ ጨለማ ቤት እንደታሰሩ ነው።

• ማነህ ባለ ሳምንት…?
"…እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ማን ነው? መዝ 25፥12

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ
2025/06/29 07:37:13
Back to Top
HTML Embed Code: