Telegram Web Link
"…እየጠራ መጣ ኩል እየመሰለ…

"…የሚሰማኝ አድማጭ ባይኖርም እየሆነ ስላለው ነገር እንዲህና እንዲህ ይሆናል ብዬ አስቀድሜ የነገርኳችሁ ነገር እኮ ነው እየሆነ ያለው። መቼም ሐበሻ የሞተና ከዓይን የራቀ ሰው አመስጋኝ ሆኖ ነው እንጂ…ሃኣ…?

"…ምንም አትላኩልኝ። አዲስነቱ እያያችሁ ለማታዩ፣ እየሰማችሁ ለማትሰሙ ለእናንተ ነው እንጂ አይደለም። ከዚህም የባሰ የከፋው ቀን ደግሞ ከፊት የሚመጣው ቀን ነው። እኔማ በዚህ ጉዳይ እኮ ከስንቱ ተጣለሁ። ከምወደው ከመረጃ ቴቪና ከኤልያስ ክፍሌ፣ ከማከብራቸው እንደ ቤተሰብም ከማያቸው ከእነ ጋሽ ሰሌና ከመሲም የተለያየሁበት ጉዳይ እኮ ነው። ተፋቱኝ። ምንም አትላኩልኝ።

"…በእርግጠኝነት እነግራችኋለሁ እኔ ከኢዩ ጩፋ፣ ከእስራኤል ዳንሳና ከዮናታን በተሻለ መልኩ ትንቢት መናገር የምችል ይመስለኛል። ከምር እኔ እኮ የሚሰድበኝ፣ የሚረግመኝ፣ የሚያዋርደኝ እንጂ የሚሰማኝ፣ ከልቡ የሚያደምጠኝ የለም እንጂ ከዘመኑ የጴንጤ ማፍያ ነቢያት በብዙ ሳልሻል አልቀርም ብላችሁ ነው? 😂 ቀልድ ነው ደግሞ የምር አርጋችሁ እንዳትይዙት።

"…በአሁን ሰዓት አስረግጬ የምነግርህ ነገር ቢኖር እንደ እኔ የኢትዮጵያም፣ የዐማራም፣ የትግሬና የኦሮሞም ቦለጢቃ የገባው ሰው ያለ አይመስለኝም። ከምር እውነቴን ነው። ይሄ ጅማሮ ነው። ከባዱ ቀጥሎ የሚመጣው ነው። ዐማራ ግን ይሄንንም ተሻግሮ ያሸንፋል።

"…ይልቅ ልንገራችሁማ እስከ አሁን ባይፈቱም የኔታ ይባቤ ከፎሊስ ጣቢያ ወደ መንበረ ጵጵስና ተወስደው በዚያ ነው ያደሩት። ደረጄም ፍርድ ቤት ቀርቦ ወንጀሉ ተነብቦለታል። ሃኪሞች ሳይራቡ ተርበዋል ብለሃል ነው አንደኛው ክሱ። ዐቃቤ ሕግ ተጨማሪ የምርመራ ቀን ቢጠይቅም ፍርድ ቤቱ ግን ከሀገር እንዳይወጣ አግዶ በ50ሺ ብር ዋስ ይፈታ ዘንድ ወስኗል። ዐርብ ርዕሰ አንቀጽ ይኖረናል።

•ዘመዴ ነኝ ከጮቄ…
የፍርድ ቤት ውሎ…

"…ከቤሮው ለምሳ እየወጣ በመንግሥት የጸጥታ ሰዎች አማካኝነት በቁጥጥር ስር ውሎ ሜክሲኮ ፌደራል ፖሊስ የከረመው የማኅበረ ወይንዬ ተክለሃይማኖት መንፈሳዊ የጉዞ ማኅበር እና የስለ ኢትዮጵያ ዝም አንልም የፀረ ግብረ ሰዶማውያን ማኅበር መሥራችና ሊቀመንበሩ መምህር ደረጄ ነጋሽ በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት መቅረቡ ተሰምቷል።

"…ሦስት ጠበቆች የቆሙለት መምህር ደረጄ ነጋሽም በፌደራል ፎሊስ መርማሪ አማካኝነት የተከሰሰበትና ለእስር ያበቃውን ወንጀል በችሎቱ ላይ አንብቦ ለፍርድ ቤቱ አሰምቷል። ክሱ የሽብር ክስ ነው።

• መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመናድ
• ሃኪሞቹ ሳይራቡ ተራቡ ብሎ በሚዲያ አውርቷል
• መንግሥት በኅብረተሰቡ ዘንድ አመኔታ እንዲያጣ እያደረገ ነው ወዘተ በሚል ነው የከሰሰው። በዚህም ምክንያት የተጨማሪ 14 ቀን የምርመራ ጊዜ ይፈቀደለት ዘንድ ፍርድቤቱን ጠይቆም ነበር ተብሏል።

"…መምህር ደረጄም ይሄ ክስ ፍጹም ሐሰት ነው በማለት የመለሰ ሲሆን ተከላካይ ጠበቆቹም "ይሄ የሽብር ተግባር አያስብልም፣ ደንበኛችን ሓሳባቸውን በሚዲያ በነፃነት ነው የገለፁት በማለት በነፃ ይለቀቅ ዘንድ ወይም በዋስ ይፈታ ዘንድ ያቀረቡ ሲሆን መርማሪውም የዋስትና መብት እንዳይሰጠው ተቃውሟል።

"…በመጨረሻም ግራ ቀኙን ያየው ፍርድ ቤቱ መምህር ደረጄ ነጋሽ በተከሰሱበት ወንጀል በ50 ሺ ብር ዋስትና ከእስር ተፈተው መከራከር እንደሚችሉ ፈቅዶ ነገር ግን የፍርድ ሂደቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ ከሃገር እንዳይወጣ በሚል ወስኖ ፋይሉን ዘግቶ ወደ መዝገብ ቤት መላኩ ተነግሯል። ነገ ጠዋት የዋስትናው ሂደት ከተሟላ ደረጄ ወደ ቤቱ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል የፍርድ ቤት አከባቢ ወፎቼ።

• በዘማሪት ዮርዳኖስ ጉዳይ ላይ ነገ ከምስጋና በኋላ በርእሰ አንቀጽ መልክ የመጨረሻ ቃሌን እሰጣለሁ።

"…
"…በበሬና በአህያ በአንድነት አትረስ። ዘዳ 22፥10

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ
አጫጭር መረጃዎች

፩ኛ፦ በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ለዓመታዊው የብልፅግና ወንጌል ግብር የታረዱት አበው መነኮሳት የአስከሬን ለቀማ ተካሂዶ የኦሮሞ ብልጽግና እንደተለመደው የሬሳ ማስረከብ ሥርዓት ፈጽሟል።

፪ኛ፦ ለ7 ተከታታይ ቀናት በወኅኒ ቤት የከረሙት ሊቁ የኔታ ይባቤ ከወኅኒ ቤት መፈታታቸውና በዚህ ሰዓት ባሕርዳር ቅዱስ ጊዮርጊስ በመንበረ ጵጵስናው እንዳሉ ተነግሯል። ጉዞ ወደ ጉባኤ ቤታቸው።

፫ኛ፦ ከመሥሪያ ቤቱ ወደ መኖሪያ ቤቱ ለማምራት ወደ መኪናው እያመራ ሳለ በብልፅግና ፎሊሶች ተይዞ ሜክሲኮ ፌደራል ፖሊስ የከረመው መምህር ደረጄ ነጋሽ ፍርድቤቱ ትናንት በዋለው ችሎት የውጭ ጉዞ እገዳ ጥሎበት በ50 ሺ ብር ዋስትና ይፈታ ብሎ የነበረ ቢሆንም፣ ቤተሰብ ዛሬ የዋስትናውን ብር ይዞ ለማስፈታት ቢሄድም ከሳሽ ፖሊስ ይግባኝ ስለጠየቅኩበት አይፈታም ብሎ እዚያው ዘብጥያ እንዳስቀረው ተነግሯል።

፬ኛ፦ የአቡነ ቀለሜንጤስ ዘመድ ሁላ እንደሆኑ የሚነገርላቸውና ለገጣፎ ላይ ታፍነው እስከ አሁን የት እንዳሉ የማይታወቁት የአርበሃራ መድኃኔዓለሙ አባት አባ ገብረመድኅንም በእጅ ስልካቸው ወደ ቤተሰብ እየተደወለ እንድንለቃቸው ከተፈለገ አንድ ነጥብ አምስት ሚልዮን ብር በባንክ እንዲያስገቡ አፋኞቹ እየጠየቁ ስለመሆኑ ተሰምቷል።

• ሲኖዶሱ ግን 🙏🙏🙏

• ዘመዴ ነኝ ከጮቄ ተራራ…!
“…እናንተ ግን ተጠንቀቁ፤ እነሆ፥ አስቀድሜ ሁሉን ነገርኋችሁ።” ማር 13፥23። “…ለእናንተም የምነግራችሁ ለሁሉ እላለሁ፤ ትጉ።” ማር 13፥37። “…የምነግራችሁ ገና ብዙ አለኝ፥።” ዮሐ 16፥12። “…የማይገለጥ የተሰወረ የለምና፥ የማይታወቅም ወደ ግልጥም የማይመጣ የተሸሸገ የለም።” "…በልቡም የተሰወረ ይገለጣል… 1ኛ ቆሮ 14፥28

• እንደምን አደራችሁ?
• እንደምን አረፈዳችሁ?
• እንደምን ዋላችሁ?
• እንደምን አመሻችሁ?

• መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ
ሰላም ለእናንተ ይሁን…

"…ምንም እንኳ ለእኔና የእኔ ቤተሰብ ለሆናችሁ ለእናንተ ለእኔ ወዳጆች አዲስ ጉዳይ ባይሆንም በእኔ በኩል ለዓመታት ስጮህበት የነበረ ጉዳይ ቢሆንም አሁን ግን ከሁሉ ነገር ገለል ብዬ አየር እየሰበሰብኩ ካለሁበት የእረፍት ስፍራ ድረስ ስቅታ እስኪገድለኝ መተንፈስ እስኪያቅተኝ ድረስ ሰሞኑን ዘማሪት ዮርዳኖስ ደረጄን እና ቀሲስ ደበበ እስጢፋኖስን እንዲሁም ዘማሪት ፋንቱ ወልዴን በተመለከተ በተደጋጋሚ ስሜ የተነሣበት አጀንዳ ለመመከትና ለአስራ ምናምነኛ ጊዜም ልዘበዝባችሁ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ እንደተለመደው በቲክቶክ መንደር መድረኬ ላይ ነጭ ነጯን ልቀውጠው ለአጭር ሰዓት ልመጣ ነኝ። አላችሁ አይደል…?

http://tiktok.com/@zemedkun.b
“…እግዚአብሔርን ማመስገን መልካም ነው፥ ልዑል ሆይ፥ ለስምህም ዝማሬ ማቅረብ፤ በማለዳ ምሕረትን፥ በሌሊትም እውነትህን ማውራት…" መዝ 92፥ 1-2

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ
ፈረሰኛው እያፈረሰው ነው።

"…ሰኔ 19/2017 ዓም በብልጽግና ወንጌል እና በኦሮሞ የወሃቢይ እስላሞች የተሞላውና ፀረ ዐማራ፣ ፀረ ኦርቶዶክሱ የኦሮሙማው ጦር በሰሜን ወሎ በራያ ቆቦ የሚገኘውን የኩቢ ቀረንሳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያንን ይሁነኝ ብሎ በዚህ መልኩ በመድፍ ካወደመው እና ከቃጠለው በኋላ እግዚአብሔር ከሰማይ የዐማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምሥራቅ ዐማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ ከመሬት ያዘነበቡትን እሳት ወደ አካባቢው ደውላችሁ ጠይቁ።

"…ሠራዊቱ በዘመነ ጁንታ የገጠመው የመበተን፣ የመሸሽ፣ የመፈርጠጥ፣ የመደንገጥ ላማዱ ዳግም እንዳገረሸበት ነው የተነገረው። ፈረሰኛው ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ የዓድዋው ጌታ ሊቀሰማእቱ ቅድስ ጊዮርጊስ ፈረሰኛው ሥራውን መሥራት መጀመሩን ነው የዓይን እማኞች የሚናገሩት።

• ኦፍጡነ ረድኤት…

ኦ ፍጡነ ረድኤት ለጽኑዕ ወለድኩም፣
ወለነፍሰ ኵሉ ቃውም፣
ጊዮርጊስ የዋህ እንበለ መስፈርት ወዓቅም፣
ከመ እግዝእትከ ቡርክት ማርያም፣
እስመ ርኅሩኀ ልብ አንተ እምበቀል ወቂም።

ኦ ፍጡነ ረድኤት በብዙኅ ፆታ፣
ከመ እግዝእትከ ርግበ ኤፍራታ፣
በሰማይ በላዕሉ ወበምድር በታህታ፣
አምህለከ ጊዮርጊስ በስመ እምከ ቴዎብስታ፣
ሞገሰ ስም ሀበኒ ከመ ስምከ መንታ።

ኦ ፍጡነ ረድኤት እምሩፀተ ነፋስ ወዓውሎ፣
ለዘይጼውዐከ በተወክሎ፣
ጊዮርጊስ ቅረብ ለምሕረት ወለተሣህሎ፣
ተወከፍ ወትረ ጸሎትየ ወቃለ ጽራኅየ ኵሎ፣
እስመ ልበ አምላከ ርኅሩኀ በኀቤከ ሀሎ።

"…የዘንድሮው ክረምት የፍጻሜ ግጥምያ፣ የዋንጫ ጨዋታ ነው። ዝርዝሩን፣ ምርኮና ተኩለሽን ጨምሮ ሌሎች የወደሙ ካምፖችና ከብልፅግና እጅ የተለቀቁ ከተሞች ጭምር በነገው መርሀ ግብራችን ይዘን እንቀርባለን እና ጠብቁን።

• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!
"…እርስ በርሳችሁ ውሸት አትነጋገሩ…ቆላ 3፥9 …" ለክፉዎች ሰላም የላቸውም ይላል አምላኬ። ኢሳ 57፥21 "…ንጉሥ በሠራዊቱ ብዛት አይድንም፥ ኃያልም በኃይሉ ብዛት አያመልጥም። ፈረስም ከንቱ ነው፥ አያድንም፤ በኃይሉም ብዛት አያመልጥም። መዝ 33፥ 16-17

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ
"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር

"…በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ምሽት ልክ 1:00 ሲሆን በዘመድ ቴቪ ላይ የቀጥታ ስርጭት መርሀ ግብሩ ይጀምራል። እንደተለመደው ገባ ገባ በሉና ጠብቁን።

• ZemedTv 👉 zemedtv.com

• በትዊተር (×) 👉 https://x.com/i/broadcasts/1MYGNwVbmgnJw

• በራምብል 👉 https://rumble.com/v6vherv--zemede-june-29-2025.html?e9s=src_v1_upp_a

• በሳታላይት ቴሌቭዥን 👉 Yahsat 52.5° East 11977 H 27500 ላይ ይከታተሉን።

"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።

👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia

👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።

• ሰብሰብ ብላችሁ ጠብቁን…!
• አላችሁ አይደል…?

👉🏿zemedtv.com
👉🏿https://zemedtv.com/live.html
👉🏿 https://rumble.com/v6vherv--zemede-june-29-2025.html?e9s=src_v1_upp_a
👉🏿 Yahsat 52.5° East 11977 H 27500

• ነጭ ነጯን ጀምረናል…
“…ዳሩ ግን፦ መካኖችና ያልወለዱ ማኅፀኖች ያላጠቡ ጡቶችም ብፁዓን ናቸው የሚሉበት ጊዜ እነሆ ይመጣልና ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ አልቅሱ።” ሉቃ 23፥29

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጸሎተ አቡነ ሩፋኤል በእንተ ሃጫሉ…

ሃጫሉ…! ምንም ማድረግ አልቻልኩም። ነፍስህን አብርሃምና ይስሃቅ አጠገብ ያስገባልኝ። ሃጫሉ! እኔም ከአንተ በኋላ እመጣለሁ። ሃጫሉ! ሃጫሉ ልጄ ለኦሮሞ ሕዝብ እኮ አንተ፣ ለእምነትህም እኮ አንተ ኪዳነምሕረትን ትወዳት ነበር። ሃጫሉ ደምህን እግዚአብሔር ይበቀልልህ። እግዚአብሔር ቃየልን ጠርቶ የወንድሙን የአቤልን ደም እንደጠየቀ ደምህን እግዚአብሔር ይበቀልልህ።

ሃጫሉ፣ ሀጩ ኮ፣ በቋንቋችን ለሕዝብህ የታገልክ ነፍስህ በሰላም ትረፍ፣ እውነት ነው የተቀበረው። ልጆችህንም ያሳድግልህ፣ ሃጫሉ ምንም ላደርግልህ አልችልም፣ ነፍስህን ፈጣሪ ይቀበል፣ እንዳንተ መሆን አንችልም፣ ፈጣሪ እንዳንተ እንዲያደርገን እንማጸነዋለን። ነፍስህን በአብርሃም፣ በይስሐቅ አጠገብ ያኑርልን። በማለት የመቃብሩን ብረት በመሳም፣ ለሃውልቱም በመስገድ ፈጽመዋል።

"…ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል በአባታቸው ጎንደሬ በእናታቸው ትግሬ እንደሆኑ ነው የሚታወቀው። ምን ዓይነት ጉድ ነው ዘንድሮ የመጣብን። የዝቋላ ገዳም መነኮሳት ሲታረዱ ጭጭ የሚሉት ሁላ አንድ እነ አቢይ አሕመድና ሽመልስ አብዲሳ ከእነ ጃዋር መሀመድ ጋር ተጠቃቅሰው ነፃ እርምጃ ወስደው ያስወገዱትን አዝማሪ በዚህ መጠን ቅረጸኝና ቪድዮውን በትነው በማለት የዘቀጠ ፖለቲካ መሥራት አንድ ጳጳስ ነኝ ከሚል ሰው ዘንድ መታየቱ አስደማሚ ነው።

"…ፓትርያርክ አቡነ ማቲያስ ሲሞቱ ቀጥሎ የሚሾመው የኦሮሞ ጳጳስ ነው ሲባል በቃ አዳሜና ሄዋኔ በኦሮሞ ቄሮ ዘንድ ለመወደድ ሲል እንዲህ በአደባባይ ይላላጣል አይደል?  

• ቱ…! ሰውረነ 🙏 ሃጫሉኮ እኔም ወደ አንተ እመጣለሁ አላሉም። 😂😂 …ሃጫሉን የበላ ጅብ ፊት ሃጩሉ ጥራኝ ማለት የጤና ነውን?

© ቪድዮ ምንጭ ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ ነው።
2025/07/04 07:10:05
Back to Top
HTML Embed Code: