Telegram Web Link
የስም ስረዛ…

"…በዛሬው የህንፃ ምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ የቀድሞው ጽርሐ ምኒልክ ህንፃ ከ ጽርሐ ምኒልክ ህንፃነት ወደ ሁለገብ ህንፃ ተሸጋግሯል። ሰዎቹ እንደምንም ብለው የአፄ ምኒልክን ስም ሠርዘውታል። 😂 ታሪክ ስረዛው ተጠናክሮ ቀጥሏል። የምኒልክ ቤተ መንግሥትን ቀደም ብሎ አንድነት ፓርክ ብሎ የሰረዘው ኦሮሙማ ዛሬ ደግሞ ጽርሐ ምኒልክን ወደ ሁለገብ ህንፃነት መቀየራቸወወ ነው የተሰማው።

"…እንደ ቡናቤት በዲም ላይት መብራት ከተንቆጠቆጠው የአዲስ አበባ አደባባይ አደባባዮች መሃል ተለይቶ የምኒልክ አደባባይ ብቻውን በጨለማ እንዲዋጥ እንደተደገም የሚናገሩ መተርጉማንም አሉ። እውን የኮሪደር ልማቷ አዲስ አበባ ለምኒልክ አደባባይ መብራት ማቅረብ አልቻለችምን? እስቲ ፎቶ አንሥታችሁ ላኩልኝማ። እውነት ሐሰት?

"…ቤተ ክርስቲያን ተቃጠለ፣ ሊቃውንቱ ታሰሩ፣ ካህናት መነኮሳቱ ተገደሉ፣ ታረዱ ተብሎ ጫጫታ ሲበዛ በዚያው ፍጥነት አቡነ አብርሃም ባህርዳር ላይ ለአረጋ ከበደ ከባ ይሸልሙታል። በርታ የሀገሬ ልጅ፣ የመንደር የወንዜ ልጅ ብለው ይሸልሙታል። አቡነ ሳዊሮስ ደግሞ ዕድለኛው ሊቀጳጳስ ተብለው አዳነች አበቤን ከምእመናን የተሰበሰበ፣ ከሙዳየ ምጸዋት የተለቃቀመ ፈረንካ ተሰባስቦ ለአዳነች አበቤ የ1 ሚልዮን ብር የወርቅ መስቀል ይሸልሟታል። 😂

• አዳነች አበቤ ጴንጤ ናት።
• በመስቀል አታምንም፣
• ለመስቀልም አትሰግድም
• መስቀል ኃይላችን ነው። መስቀል ቤዛችን ነው። መስቀል መድኃኒታችን ነው፣ መስቀል የነፍሳችን መዳኛ ነው ብላም አታምንም። እንደ አይሁድ መስቀልን የካደች፣ አንደኛ በመስቀል አዳኝነት የማታምን ናት።

"…የእምዬ ምኒልክን ስም ግን ከአዲስ አበባ እንደምንም ብለው እየሰረዙት ነው። ትታረዳለህ አራጅህን የግድህን ትሸልማለህ። አለቀ።

• ወይኔ በላቾ አለ ሰውዬው።
"…ይህ ነገር ይከብድብሃልና አንተ ከአንተም ጋር ያለው ሕዝብ ትደክማላችሁ፤ አንተ ብቻህን ልታደርገው አትችልም።” ዘጸ 18፥18

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ
መልካም…

"…ያን አድርጎ የናፈቃችሁን ርእሰ አንቀጽ እስቲ ለዛሬ ላቅርብላችሁ ብዬ ቀኝ ትከሻዬን ሲሸከሽከኝ ጊዜና ያን እንደ ኮሶ መራር፣ እንደ መተሬ፣ እንደ በረኪና መራር፣ እንደ ዳጣ፣ ቀሪያ በሚጥሚጣ አቃጣይ፣ አንዳጅ የሆነ ርእሰ አንቀጼን ላቀርብላችሁ ወደድኩ። ከርእሰ አንቀጹ በኋላ የተለመደው ጫጫታ ይኖራል ተብሎ ቢጠበቅም ደግሞም መኖርም አለበት ዩቲዩበሮች ምን ሠርተው ይብሉ? የቲክቶክ ኤክስፐርቶች ምን ተንትነው ያምሹ? ለእነሱም ሲባል፣ መንደራቸው ጭር እንዳይል ሲባል ዛሬ ዓለማዊ፣ ነገ መንፈሳዊ፣ ሃይማኖታዊ ርእሰ አንቀጽ ላቀርብላችሁ ወደድኩ። ደግሞም የእናንተም ያ የበሰለ የሚያጓጓ ኮመንታችሁም እንዴት እንደናፈቀኝ አትጠይቁኝ።

• እህሳ…ዝግጁ ናችሁ?
"ርእሰ አንቀጽ"

"…አይገፉበትም፣ ረዘም ሰፋ አድርገው አይተነትኑትም እንጂ፣ ቀጣይነት የለውም እንጂ አንዳንድ የቤተ ክህነቱም ሆነ የቤተ መንግሥቱ የቦለጢቃ ሴራ በደንብ የገባቸው የፌስቡክና የቴሌግራም ጸሐፍትን እያየሁ ነው። ሥራዬ ብለው ቢይዙት፣ ተከታታይነት ያለው ተግባር ቢፈጽሙ፣ አስሬ ለክተው አንዴ ቢቆርጡ ደግሞ ሸጋ ነበር። እሰደባለሁ፣ እነቀፋለሁ፣ ወዳጅ ዘመድ፣ ጓደኛ፣ ጧሪ ቀባሪ አጣለሁ ብለው ሳይሳቀቁ እውነትን መርሐቸው አድርገው ቢገለጡ ሸጋ ነበር። ጠንካራ፣ ታማኝ፣ አስተማማኝ የሆነ ጠንካራ የመረጃ ምንጭ ቢኖራቸው፣ ሁሉም ሥፍራ የሚገኝ ኔትወርክ ቢዘረጉ ደግሞ የበለጠ አሸወይና ይሆንላቸው ነበር። በመንደር፣ በጎጥ፣ በሰፈር ባይታጠሩም ሸጋ ነበር። የሆነው ሆኖ ገባወጣ እያሉ ብቅብቅ የሚሉ ጦማሪዎችን እያየሁ ነው። ችግሩ እንደ መስቀል ወፍ ናቸው ቶሎ ቶሎ አይመጡም እንጂ ጸሐፍትስ እያየሁ ነው። እንደ ዘመኑ የሴቶች ልብስ አጭር፣ ሚስኮል ነጠላ ዓይነት ድንክ ጦማር ይጦምራሉ እንጂ እያየሁ ነው። በርቱ ተበራቱ ብቅ ብቅበሉም።

"…ደስ የሚለው ነገር አሁን የተፈጠረው ትውልድ አዳዲስ ትግል አስቀያሽ አጀንዳ ከየትም ይምጣ ከየት፣ በማንም ይምጣ በማን እንዲህች አድርጎ የማይቀበል የባነነ፣ የነቃ ትውልድ ነው ነው የተፈጠረው። እነ ጌጡ ተመስገን፣ እነ ጉርሻ ቲዩብ፣ እነ ዮኒ ማኛ፣ ቲክቶከርና ፌስቡከር፣ እነ ጃዋርና አንከር አጀንዳ ፈብርከው ቢያመጡም የማይቀበል፣ እንዲች ብሎ በእጁ ንክች የማያደርግ ትውልድ ነው እያየሁ ያለሁት። በሆነው ባልሆነው በተፈጠረ አጀንዳ ዋናውን ጉዳይ ትተው በተፈበረኩ አጀንዳዎች ሁሉ ነጠላ ዘቅዝቀው በየፌስቡክና በየቲክቶክ ልጥፎች ስር ዋይ ዋይ ሲሉ ይውሉ ያድሩ የነበሩቱ በተለምዶ የማዳም ቅመሞች የሚባሉት የዓረብ ሀገር እህቶቻችን እንኳ በአብዛኛው የባነኑ፣ የነቁ ሆነው ነው ያገኘኋቸው። መሬት ላይ ካለው አንዳንድ ሾተለይ ፋኖ ነኝ ከሚለው ሰነፍ ባንዳ በተሻለ መልኩ የፖለቲካውን የዓየር ጠባይ ተረድተው መተንበይ የሚችሉ ሰዎች ሁላ ነው እያየሁ ያለሁት። ይሄ ይበል የሚያሰኝ ነው። ግፉበት። መርምሩ፣ ተመራመሩ። ፔኒስዮን አልጋ ላይ ተኝቶ በቲክቶክ ትግል የጀመረውን የደቡብ ጎንደሩን ፀዳሉ በቲክቶክ ሲሞግቱ የነበሩት እነዚህ እህቶች ነበሩ። ይሄ ድሮ የማይታሰብ ነው። አሁን ግን አብዛኛው ሰው ነቅቷል። እየበቃም ነው።

"…በእስከአሁኑ ትግል እንኳንም ፋኖ አሸንፎ አራት ኪሎ አልገባ። ሳይጠራ፣ ሳይነጻ፣ እንደቆሸሸ፣ አረሙ፣ እብቁ፣ እሾህ አመኬላው፣ እንክርዳዱ ሁሉ ተግበስብሶ እንኳንም አራት ኪሎ አልገባ። የረጋ ወተት ቅቤ እንደሚወጣው የፋኖም ሁኔታ እንደዚያው ነው እየሆነ ያለው። እንደዚያ ባይሆን ኖሮ የበግ ለምድ የለበሰው ተኩላ ሁላ በፋኖ ስም ተግበስብሶ አይደለም ዐማራን ሀገሪቷንም የሌለ ትርምስ ውስጥ ነበር የሚከታት። አይታችኋል ከዓመት በፊት ፋኖ ተግበስብሶ ወደ ሥልጣን ቢመጣ ሊፈጠር የሚችለውን? አራት ኪሎ ላይ ዘመነ ካሤና እስክንድር ነጋ ሲታኮሱ። ኮሎኔል ፋንታሁን እና ምሬ ወዳጆ ሲጠዛጠዙ፣ ደረጀ በላይና ሀብቴ፣ ጌታ አስራደና ባዬ ሲዋጉ፣ ደም ሲፋሰሱ። እንደው ታዝባችኋል ኢንጅነር ደሳለኝ እና መከታው ማሞ ከሸኖ ጀምሮ እስከ አዲስ አበባ ሲተራመሱ፣ ማስረሻ ሰጤና እነ ማርሸት ሲፋጩ፣ ይሄን የሚያውቅ የዐማራ አምላክ በዐማራ ሕዝብ ላይ መከራው ቢበዛ፣ ቢጠነክርበትም ስንዴው ከገለባ እስኪለይ፣ እስኪ በጠር ድረስ አቆይቶታል።

"…የዐማራ ትግል እየጠራ ነው። የዐማራ ትግል መስመር እየያዘ እየመጣ ነው። በዐማራ ትግል ውስጥ ማን ጎጠኛ፣ መንደርተኛ፣ ተረኛም ለመሆን እንደሚላላጥ በቆይታ እየተገለጠ ነው። የዐማራ ትግል ካንሰር፣ የዐማራ ትግል ደንቃራ ማን እንደሆነ በጊዜ ሒደት እየተለየ ነው የመጣው። አፈ ቅቤ ልበ ጩቤው ሁሉ እየተለየ ነው። ዐማራ መሳይ አሞራው ሁሉ እየተበጠረ ነው። ማን በዐማራ ትግል እንደሚቀልድ፣ ማን በዓማራ ትግል የኢኮኖሚና የሥልጣን ጥሙን ለማርካት እንደሚንከራተት፣ ማን የዐማራ ትግል ላይ ሽብልቅ ለመክተት እንደሚፍጨረጨር በሚገባ እየታየ፣ እየተለየም ነው የመጣው። ከዐማራነት ወርዶ ጎጥ ውስጥ እየተወሸቀ ያለው ማን እንደሆነም ከሊቅ እስከ ደቂቅ እየተረዳው፣ እየገባው ነው እየመጣ ያለው። ማን ከወያኔ ጋር፣ ማን ከብአዴን ጋር፣ ማን ከሻአቢያና ከኦሮሙማው ጋር ጭምር እንደሚሠራ ሁሉም ሰው እየገባው፣ እየተረዳው የመጣበት ወቅት ላይ ነው የምንገኘው። ሕዝቡም ጨክኖ መፍረድ ጀምሯል። በግልጽ መገሰጽም ጀምሯል። ይሄ መልካም ጅምር ነው። እግዚአብሔር ይመስገን።

"…አሁን ተወደደም፣ ተጠላም ሁለት ምርጫ ብቻ ነው ከዐማራ ፋኖ ፊት የተደቀነው። አንደኛው ምርጫ ልዩነትን አቻችሎ ፣ አቀራርቦ፣ አለዝቦ አንድነት ፈጥሮ ጠላቱን ተፋልሞ ማሸነፍ። በጎንደርና በጎጃም፣ በሸዋና በወሎ፣ በወሎና ጎንደር፣ በጎጃምና ወሎ፣ በሸዋና በጎጃም ወዘተ መሃል ጠላት የዘራውን የከረመ መርዝ አክሽፎ፣ ሴራውን በጣጥሶ የግዱን አንድ ሆኖ ጠላትን እንደ ዐማራ መጋፈጥ። ይሄ አይስማማኝም ካለ ደግሞ ሁለተኛው ምርጫ እርስ በእርስ ዐማራ ከዐማራ ይጨፋጨፋል፣ በዚያውም ልክ ጠላቱ ገብቶ ይጨፈጭፈዋል። ሰኔ 15 እያለ ለሞተ ብአዴን ጎራ ለይቶ መጠዛጠዝ አልያም የሰኔ 15 አጀንዳን ለብአዴን ትቶ አዲስ ትውልድ ፈጥሮ በአዲስ አጀንዳ አዲስ አስተሳሰብ ይዞ በአንድነት መታገል። ምርጫው የዐማራ ነው። በተለይ የጎጎዎች። የሁለቱ ጎጎዎች። ጎጃምና ጎንደሮች። አለቀ።

"…ባለፈው ጎርጎራ ላይ ሂልኮፕተር ተከሰከሰ በተባለ ጊዜ እኮ ነው የሁለቱ ጎጎዎች አክቲቪስቶች በሳቅ ያነፈሩኝ። እንዋጋዋለን የሚሉት የዐማራ ብአዴን ብልፅግና ባለሥልጣናት ከጎንደር ወደ ጎርጎራ በመሄድ ላይ ሳሉ ሂሊኮፍተሩ በብልሽት ቢሉ በአርፒጂ በዐማራ ፋኖ ተመትቶ ወደቀ ሲባል በአዝማሪዋ፣ በኦሮሸኔዋ ጋለሞታ በቅዳሜ ገበያ የሚመራው የጎጃም አክቲቪስት ቡድን አጓራ፣ ደነገጠ፣ ያዙኝ ልቀቁኝ አለ። ጎንደሬዎቹ ሆን ብለው ጎጃሜዎቹን ባለሥልጣናት በሂሊኮፕተር አንድ ላይ ጭነው ጨረሷቸው። ወይኔ ወይኔ፣ ወይኔ ብለው ፀጉራቸውን እየነጩ፣ ደረታቸውን እየደቁ እዬዬአቸውን አስነኩት። በተለይ አዝማሪዋ አያሌው መንበር እንኳን ደስ አለህ፣ ይኸው ጎጃሞች ተለይተው አለቁልህ ብላ አለቀሰች። ብአዴን የሆነ፣ ሕዝቡን እያስጨረሰ ያለ አካል በእግዜሩ መብረቅ፣ በፋኖ ጥይት፣ በራሱ በአቢይ አሕመድ ተንኮል ጅም ብለው ቢያልቁ የዐማራ ፋኖ ትግል እዳው ቀለለት ተብሎ ጮቤ ይረገጣል፣ ስለት ይገባል እንጂ እንዴት ድንኳን ደኩኖ፣ ነጠላ ዘቅዝቆ ለቅሶ ድረሱኝ ይባላል። ጉዱ እኮ ነው። እናም ነፍ የትየለሌ አፍቃሬ ብአዴን የሆነ መንጋ አሁንም የሆነውን የዐማራ ፋኖ ወሳኝ ክፍል ሁላ እንደተቆጣጠረ ይሰማኛል። ብአዴን በፋኖ ውስጥ አልሞተም የሚያስብል ነው።

"…የጎንደሮቹም አክቲቪስቶች እንደዚያው ነው የተንጫጩት። ጫጫታው ግን በስሱ ነው። ኋላ ላይ የተጎዳው በወልቃይት ጉዳይ በቀጣይ ለሚሠራው ፖለቲካ እንቅፋት ይሆን ይሆናል ተብሎ የሚገመተው ኡዞ አገኘሁ ተሻገር መሆኑ ሲሰማ የጎጃሙ ሸንጎ ሰጥ አለ። አረጋ ከበደ፣ ተመስገን ጥሩነህ ምንም እንዳልሆኑ ሲያውቅ እፎይ ተመስገን አምላኬ ብሎ ጭጭ አለ። አገኘሁ ተሻገር ከሆነስ ይበለው አሉ እነ አዝማሪዋ ቅዳሜ ገበያ። አገኘሁ ተሻገር መወገድ ስላለበት ነው የተወገደው። መጪው የወልቃይት ጉዳይ መታየት ያለበት በፌዴሬሽን ምክርቤት ነውና እዚያላይ ደግሞ አቃጣሪ፣ ታማኝ ባሪያ፣ የመጣ የሄደው ሁሉ የሚጭነው የህዳር አህያ ቢሆንም…👇
👆 …አገኘሁ ተሻገር መኖር የለበትም በሚለው የኦሮሙማው ውሳኔ መሠረት አገኘሁ እንደ ድመት ነፍስ አልሞት ብሎ አስቸገረ እንጂ እንዲወገድ መወሰኑን ማመን የግድ ነው። የወልቃይት ጉዳይ አሁን ሌላ ጣጣ ይዞ እየመጣ ስለሆነ ማለት ነው።

"…በአጠቃላይ የዐማራ ፋኖ ትግል ጠላው ተጠምቋል። አተላው ወደ ታች እየዘቀጠ፣ ገፈቱ ወደላይ እየተንሳፈፈ ነው ያለው። አተላው ፀዳሉ፣ አተላው ቆራጡ፣ አተላው አማኑኤል ከዐማራ ትግል ተደፍተዋል። አሁን የሚቀረው ወይ አተላ፣ ወይ ገፈት  ያልሆኑ ነገር ግን የጠራ ጠላ ያልሆኑቱ አካላት ናቸው። እነሱም ቢሆን የጊዜ ጉዳይ እንጂ እንደ አተላ ይደፋሉ፣ አልያም እንደ ገፈቱ ይተፋሉ። ቱፍ፣ ቱፍ፣ እንትፍ እንትፍ ይደረጋሉ። በሸዋ ያለው አተላና ገፈት፣ በጎጃም ያለው አተላና ገፈት፣ በጎንደር ያለው አተላና ገፈት ይደፋል፣ ይተፋልም። የዐማራ ትግል አሁን የሚያስፈልገው ኮፍጠን፣ ቆፍጠን፣ ኮምጨጭ ብሎ የሚወስን፣ ከዐማራ ሕዝብ በላይ በግለሰብ ስብዕና ላይ የማይንጠለጠል፣ አፍቃሬ ሥልጣን ያናወዘውን ግለሰባዊ አመለካከት፣ ወረዳዊ፣ ዞናዊ፣ ጎጤውን አስተሳሰብ አምክኖ አሽቀንጥሮ ወዲያም ንቆ ትቶ ዐማራን፣ ታላቁን ዐማራነትን ለማንገሥ ነው መፋለም ያለበት። ድሮን በላዩ ላይ፣ መድፍ በጆሮ ግንዱ ላይ፣ ጥይት በአፍንጫው ስር ሲያፏጭ፣ ሞት በአናቱ ላይ ተሸክሞ ዛሬ ይሙት ነገ ይሙት የማያውቅ የዐማራ ፋኖ ታጋይ እሱ እንደማይሞት፣ ድሮን እንደማይነካው፣ ጥይት አጠገቡ እንደማይደርስ፣ የመድፍ ድምጽ የማይሰማ፣ አራት ኪሎን በእርግጠኝነት አልሞ፣ አቅዶ፣ በሌላው ሞት እሱ ተሻግሮ፣ ተረማምዶ ሚንስትር፣ ባለሥልጣን እንደሚሆን ያረጋገጠ ያህል በራሱ ተማምኖ የዐማራ ፋኖ መሪ እኛ ካልሆን፣ አራቱም ወሳኝ የሥልጣን እርከን ለእኛ ካልተሰጠን፣ እኛ ብቻ የዐማራ ፋኖን ትግል ካልመራነው ሞተን እንገኛለን የሚል ጤናቢስ አመለካከት ላለው ቡድንም ሆነ ግለሰብ ቅንጣት ታህል ሊጨነቅ፣ ሼምም ሊይዘው አይገባም። ሞት በላዩ ላይ እያፏጨ ከዛሬ ነገ እኔ ሞቼ ወገኔን፣ ሕዝቤን ነፃ አወጣለሁ የሚል የዐማራ ፋኖ በግለሰቦች የሥልጣን ጥም መናወዝ ምክንያት ብናገር፣ አስተያየት ብሰጥ፣ ልክ አይደለም ብል እነ እገሌ ይቀየሙኛል፣ ሰዳቢ ሠራዊት አስነሥተው ስሜን ያጠለሹታል ብሎ ሊያፍር፣ ሊሽኮረመም አይገባም። ምንም አባቱ አያመጣም። ወጊድ በለው።

"…የጎጃም ዐማራ ሞት ከጎንደር ዐማራ ሞት አይበልጥም አያንስም። የወሎ ዐማራ ሞት ከጎጃም፣ ከሸዋ ከጎንደር አይበልጥም አያንስም። እኔ ከሌላው ዐማራ የተሻልኩ ነኝ የሚል አስተሳሰብ አይሠራም፣ አያዋጣም። እኛ ገንዘብ አለን፣ መሳሪያ፣ የሰው ኃይል አለንና ሁሉን ሥልጣን ጠቅልለን መውሰድ ይገባናል ማለትም ነውር ነው። ሌሎች ትግል ጀምረው በነበረ ሰዓት ይነግድ፣ ይዘፍን፣ ይጠጣ፣ ይዝናና ይጭፍር የነበረ ሁላ አሁን ድንገት መጥቶ የዐማራን አንድነት ሒሳብ እያወራረድን እኔ ልምራው ማለት ተገቢ አይደለም። ወደ ቀልቡ ከተመለሰ ተመለሰ፣ ካልተመለሰ ሌላው ወደፊት መቀጠል ነው ያለበት። አረቄያም ሁላ የሚያወራውን መስማት ትክክልም ልክም አይደለም። ሠራዊቱና መሪዎቹ የተለያዩ ናቸው። ታጋዩ ሁላ እንደ ዐማራ ነው መታገል ያለበት። የጎጃም ፋኖ ጎንደር፣ ወሎ፣ ሸዋ ገብቶ መታገል ነው የሚፈልገው። የጎንደሩም፣ የወሎና የሸዋውም እንደዚያው ነው የሚፈልገው። በአረቄ ተጽእኖ እየተነሣ፣ በብአዴን መርፌ እየተወጋ የሚለፈልፈው ሁሉ ታችኛውን ታጋይ አይወክልም። በጭራሽ አይወክልም። ተራው የእኛ ነው አይባልም። ተረኛ አገዛዝ ሊያስወግድ የተሰባሰበ ዐማራ ተረኛ ዲክታተር ከወዲሁ የሚያስተዋውቁትን ኢግኖር እየገጨ ወደፊት ሊስፈነጠር ነው የሚገባው። ተናግሬአለሁ።

"…እንድታውቁት ያህል እደግመዋለሁ አርበኛ ዘመነ ካሤን እንደሆነ የጎንደር፣ የጎጃም፣ የወሎና የሸዋ ፋኖዎች መሪያችን ብለው መርጠውት ነበር። ጎንደርም የሚገባውን፣ ሸዋም ወሎም የሚገባቸውን የሥልጣን እርከን ተቀብለው ጨርሰው ነበር። አርበኛ ዘመነ ካሤ የዐማራ መሪ ሆኖ እንዳይመረጥ ስልኩን ዘግቶ የጠፋው አስረስ መዓረይ ነው። ይሄንን ሁሉም ያውቃል። እነ አስረስ መዓረይ ዘመነን አስገድለው እነሱ መሪ ሆነው ለመምጣት ሲሉ ነው የዘመነ ካሤን ምርጫ ደብቀው የከረሙት። ዘመነም፣ የጎጃም ፋኖዎችም ሲጠይቁ አስረስ መዓረይ ራሱን የዘመነ ምትክ ሆኖ ለመገለጥ እየሠራ ስለነበር  ምላሽ አይሰጥም ነበር። የቆየ ሞላ በራሱ አንደበት "ምርጫው ካለቀ፣ ለምን እንደዘገየ ራሴ እጠይቃለሁ፣ የእኛ ሰዎች እምቢ ካሉ እንኳ ዘመዴ እመነኝ ሠራዊቱን ይዘን ሌላ አመራር መርጠን የዐማራን አንድነት በቅርቡ ዕውን እናደርጋለን ነበር ያለኝ። ይሄንኑ ጉዳይ አስረስ መዓረይም በደወለልኝ ጊዜ እኔ ዘመዴ አባደፋር ኮስተር ብዬ አንስቼለት ነበር። እርግጥ ነው ነገሮች ስላልተመቻቹ ተጓትቷል። መጀመሪያ አካባቢ እነ ባዬ ከእነ ሀብቴ ጋር እየተነጋገሩ ስለነበር ነው የተጋተተው፣ ኋላ ላይ ግን በእኛ ምክንያት ነው የተጓተተው። በእኛም መካከል የተጓተተው እነ ሻለቃ ዝናቡ የወታደራዊ ክፍሉ ካልተሰጠን አንቀበልም ስላሉ ነው። የመሪነቱንም፣ የወታደራዊ ክፍሉንም ደግሞ ለጎጃም አይሰጥም። ስለዚህ እሱን ችግር እስክንፈታው ነው ያለኝ። እኔም ዝናቡ እንዲያ የሚል አይመስለኝም። እስቲ እጠይቀዋለሁ ስል አስረስ በፍጥነት ዝናቡ አይደለም ያስቸገረን፣ ያስቸገሩት ከዝናቡ ሥር ያሉቱ ናቸው ነበር ያለኝ አስረስ መዓረይ። ይሄንንም ቅጂ እስከአሁን ደጋግሜ እየሰማሁት ነው።

"…እነ አስረስ መዓረይ እኔ ጎጃም እስክገባ ድረስ የዐማራ ፋኖ በጎጃም ነፍስ ነፍስ ያላቸውን፣ ዐዋቂ፣ ምሑራን፣ ታጋይ፣ በተለይ ደግሞ ለዘመነ ካሤ ቀኝ እጅ ናቸው የሚባሉትን፣ በሃይማኖታቸውም ቅባት በዘራቸውም ዐማራ የሆኑትን የጎጃም ልጆች እየለቀሙ አንደዜ በድሮን፣ ሌላ ጊዜ በጥይት ከጀርባ እየተመቱ፣ በጎጃም የጴንጤ አማኞቹና ፓስተሮቹ እነ ዳዊትና ተሰማ ግን ከድሮንም፣ ከጥይቱም ርቀው፣ ግንቦት ሰባቶቹ፣ ብአዴንና ኢዜማዎቹም መምህራንና ኦርቶዶክሳውያኑን እየገደሉና እያስገደሉ ዘና ብለው ነበር የቆዩት። እደግመዋለሁ ዛሬ እነ አስረስ መዓረይ፣ እነ ማርሸት፣ እነ ግርማ አየለ የሚወርዱበትና የጎንደሩ ኢያሱ፣ ሞዓ ተዋሕዶ እያሉ የሚከሱት የባዬ ልጆች ናቸው አርበኛ ዘመነ ካሤና አርበኛ ዝናቡን አንድ ላይ በድሮን ሊጨፈጭፏቸው የጨረሱትን የአገዛዙን ዕቅድ ያከሸፉት። የጎጃምን የፋኖ መሪ የዐማራ ፋኖ ምልክት የሆነውን አርበኛ ዘመነ ካሤን እና የጎጃምን የወታደራዊ መሪ አርበኛ ዝናቡን አንድ ላይ ለመግደል የታቀደውን ዕቅድ ለዝናቡም፣ ለዘመነም ደውለው ያከሸፉት ጎንደሮች ናቸው። ክብር ምስጋና ለቴዎድሮስ ለመይሳው ካሳ ለውባንተ ልጆች። እነ አስረስን የሚያንገበግባቸው ይሄ ነው። ዘመነ ሞቶ አስረስ የጎጃም ዐማራ መሪ ሆኖ ሊመጣ የነበረውን ዕቅድ ያከሸፉት ጎንደሮች ናቸው።

"…ከጫፍ ተደርሶ እኮ ነበር። እነ ጥልምያኮስ አማኑኤል አብነት፣ እነ ሥጋ ቆራጩ ይሄነው የሸበሉ፣ እነ በላይነህ ሰጣርጌ። (በላይ እንኳ አሁን በስተመጨረሻ እየባነነ ይመስላል። ከእኔ የባሰ ነጭ ነጯን መዘርገፍ እየጀመረ ነው። ቆሜ ነው የማጨበጭብለት። የበላይነህ ብዕር ማራኪ ነው። ፍሰቱም ግሩም ነው። አቋም ነው የሚያንሰው እንጂ የመረጃ እጥረት የሌለበት ሰው ነው። አስሬ ለክቶ አንዴ መቁረጥ ቢጀምር ደግሞ የድሮውን ጎንደሬ ሚኪ ዐማራን ይተካል ብዬ የምገምተው ሰው ነው። ለማንኛውም እነርሱ ሁሉ ዘመነ ካሤንና አስረስ መዓረይን ማወዳደር ጀምረው እንደነበር የጻፍኩት ቀደም ብዬ…👇
👆 …ነው። "አርበኛ ዘመነ ካሤ አስረስ መዓረይን የሚበልጠው ብረት በመጨበጥ ቀደም በማለቱ ብቻ እንጂ በንባብ፣ በዕውቀት እኩል ናቸው። ጎጃም ደስ ይበልህ ሁለት መሪ አለልህ ብለው ፕሮፓጋንዳ ሁላ መሥራት ጀምረው ነበር። በተለይ ከዘኘነ ካሤ ጋር ቆይቶ ከተለያዩ በ8 ደቂቃ ውስጥ በድሮን የተገደለው ኢንጅነር ከሞተ በኋላ ቀጣዩ ዘመነ ካሤና ልጁ ኪሩቤል ነበሩ። የምሥራቅ ጎጃሙ ተመስገን ጥሩነህ ድንቁም ባህርዳር ሄዶ ዘመነ ካሴ ሞቷል ብሎ ለብአዴን ተሰብሳቢዎች በአፉ የተናገረው ያኔ ነበር። እርግጠኛ ነበሩ ዘመነና ዝናቡ እንደሚገደሉ፣ የጋዜጠኞች ቡድን ተዘጋጅቶ፣ ሂሊኮፕተር ተዘጋጅቶ፣ እነ አንደግምም ወይ ናቲ መኮንን ሁላ የሆነ የሚሰማ ነገር አለ ብለው መለጠፍ ጀምረው፣ እነ ጌትነት አልማው እየጨፈሩ፣ የተመስገን ጥሩነህ አድናቂ እነ ፓስተር ምስጋናው አንዷለምም ዘመነ መሞቱን አላረጋገጥንም እንጂ መቁሰሉን ቆስሏል ብለው በቲክቶክ እስኪበጠረቁ ድረስ ደርሰው ነበር። ነገር ግን ዕድሜ ለሞዐ ተዋሕዶ፣ ዕድሜ ለዶክተር ወንደሰን፣ ዕድሜ ለመምህር ፋንታሁን ዋቄ፣ ዕድሜ ለዘመድኩን በቀለ፣ ዕድሜ ለአርበኛ ውባንተ ልጆች፣ ለአርበኛ ባዬ ልጆች ዛሬ በጎጃም ጎጠኛ ሸንጎ፣ በጎንደር የፖለቲካው ቅማንት ለዉሉደ ብአዴኑ የትግሬ ዲቃላው ስኳድ ቢሰደቡም በአንድም በሌላም አርበኛ ዘመነ ካሤን በእነ አስረስ መዓረይ ከመበላት ታድገውታል። አለቀ።

"…እነ ማርሸት፣ እነ አስረስ መዓረይ ይገደሉ፣ ይታሰሩ፣ ይወገዱ ብለው የፈረዱባቸውን አርበኛ ዘመነ ካሤ ጉዳዩን እንዲሰማ አድርገን ከሞት ያስመለጣቸውና ዛሬ በዐማራ ፋኖ በጎጃም ውስጥ በአመራርነት ያሉ ሺዎች ናቸው። ማርሸት እገሌ የሚባለው ሰው ቤተሰቦቹ ወዳጅ ዘመዶቹ ደውለው ግፍ ነው የተፈጸመበት ብለውኛል ብዬ ስለው "እኔማ ይገደል ብዬ ነበር ትእዛዝ የሰጠሁት፣ ቀሽሞች ትእዛዜን አልሰማ ብለው ነው ያዘገዩት እንጂማ እኔ እጨርሰው ነበር ብሎ በቃሉ፣ በድምፁ የነገረኝን ሰው ከአሜሪካ ድረስ ቤተሰቦቹ በእንባ ስለጨቀጨቁኝ አርበኛ ዘመነ ካሤ ሲደውልልኝ ራሴ ጉዳዩን በአቤቱታ መልክ አቅርቤለት መልካም ወደ እኔ ዘንድ እንዲመጣና ጉዳዩ እንዲታይ አደርጋለሁ። መግደልማ የለም ብሎ ቃል ገብቶልኝ፣ ሞት የተፈረደበትም ሰው አስታውሳለሁ ዘመነ ጋር ሄዶ፣ ግራቀኝ ክርክር ተደርጎ፣ አሸንፎ፣ እነ ማርሸትም እግሩ ላይ ወድቀው ይቅርታ ጠይቀውት አሁን ምን ላይ እንዳለ ባላውቅም ሥልጣን ተሰጥቶት እየሠራ እንደነበር ነው የማስታውሰው። መረጃ ማቅረብ እችላለሁ። አዎ ጎጃም ያለው የጴንጤና የቅባት፣ የአገው ሸንጎና የብአዴን ሴል ተሸናፊ ነው ነፈር ግን ለጊዜው ጎታች በመሆኑ ከባድ ይመስላል።

"…ዛሬ ወደዱም ጠሉም ዘመነ ካሤን የመጠበቅ፣ የመንከባከብ ግዴታ ተጥሎባቸዋል። ዘመነ ካሤ አይደለም በድሮን፣ አይደለም በጥይት በትንታ ቢሞት ተጠያቂው አንጃ በደንብ ይታወቃል። ዘመነ ካሴን አሁን ከአስረስ የበለጠ ውስጡ እያረረ፣ እኔን እየረገመ ጤንነቱን የሚከታተልለት ሌላ ሰው የለም። የዘመነ ልጁ ኪሩቤል እንኳን እንደ አስረስ ሊጠብቀው አይችልም። እኔ ጎጃም ገብቼ በድፍረት የምናገረው ነገር ቢኖር ዘመነ ካሤን በእነ አስረስ መዓረይ ከመበላት ማዳኔን ነው። መታደጌ ነው። የሄንን የምናውቅ እናውቃለን። ለመንጋው ግን አይገባውም። ዛሬ ዘመነ ካሤ ካልተመረጠ ሞተን እንገኛለን የሚሉቱ በሙሉ የዘመነ ካሤ ጠላቶች ናቸው። በቀደም ዕለት ማርሸት የጎጃም አክቲቪስቶች የተባሉት በሙሉ ሰብስቦ ከሀብቴ እና ከምሬ ወዳጆ ይልቅ ለጎጃም መከታው ማሞ ይሻላል ብሎ በድፍረት ሲናገር በጆሮዬ እየሰማሁት ነበር። አሁን የጎጃሙ ቡድን ጎጃምን ከጎንደር፣ ከወሎ፣ ከሸዋ ነጥሎ ደሴት ላይ ለማስቀረት እየደከመ ነው። ከእስክንድር ጋር ለመሥራት ፈልጎ የደከመ ቢሆንም እስክንድር ኢግኖር ገጭቶ አሳፍሯቸዋል። የጎጃም ፋኖዎችም ከእስክንድር ጋርማ አንሠራም በማለት ማደማቸው ነው የተሰማው። ዞር ብለው ከመከታው ጋር ለመሥራት የፈለጉ ቢሆንም እነመከታውም አስረስ መዓረይ፣ ማርሸት፣ የቆየ ሞላ ያለበትን ስብስብ አይደለም ማየት መስማት እንደማይፈልጉ መናገራቸው ነው የተሰማው። የጎጃሙን ቡድን የሚደግፉት የጎጃም የዳያስጶራ ምሁራንም አስረስ መዓረይ ወደ ገደል እየከተታቸው እንደሆነ ቢረዱም ገሚሱ ፀረ ጎጃም፣ ፀረ ኦርቶዶክስ ቅባቴና ሸንጎ የሆነ ጎጃሜ መሳይ አረም ስለሆነ አስረስንም እንደ ሊቅ ስለሚያዩት ጥፋት ቢኖርም ከአስረስ ተለይተን ማንን እናመጣለን፣ ትንሽ እናስታምመው በማለት እየተንፏቀቁ ይገኛሉ።

"…አሁን ተተኳሽ፣ መሣሪያ ለፋኖ ከበቂ በላይ አለው። አምና በእስክንድር ሰበብ ክረምቱን በጭቅጭቅ አሳልፎ ዓመቱን ሙሉ ዐማራን ሲያስጨፈጭፍ የከረመው የጎጃሙ የእነ አስረስና ማርሸት ቡድን አሁን ደግሞ ዘንድሮ የተፈጠረውን አንድነት ባለመቀበል የዐማራን አንድነት በማፍረስ ከዐማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይልነት ወርደው ወደ ዐማራ ፋኖ በጎጃም ጎጤ፣ መንደሬነት ወርደው ታይተዋል። ሌሎቹ የዐማራ ፋኖ በጎንደር በላይ ዘለቀ ዕዝ፣ የዐማራ ፋኖ በወሎዎቹ ምኒልክ ዕዝ፣ የሸዋዎቹ አሳምነው ጽጌ ዕዝ ተብለው ሲጠሩ። ዘገባም ሲሠራላቸው ጎጤው፣ መንደሬው፣ አፍቃሬ ወያኔ፣ ሸንጎና የቅባቴው ጥርቅም፣ አዝማሪዋ ጋለሞታ የምትመራው የጎጃሙ የአስረስና የማርሸት ቡድን በአፄ ቴዎድሮስ ስምማ አልጠራም በማለት የዐማራ ፋኖ በጎጃም ወይም አፋጎ ወደሚል ጎጤነት ተምዘቅዝጎ ወርዷል። የቴሌግራም የአፋጎ ዘጋቢዎችም ዐፋብኃን ትተው አፋጎ ነን ብለው ነው የሚዘግቡት። 3:1 ማለት ይሄ ነው።

"…በጎጃም ውድመት እያደረሰ ያለው ራሱ የዐማራ ፋኖ በጎጃም እና ኦሮሙማው ናቸው። በጎጃም ትምህርት ቤት፣ ጤና ጣቢያ ኦሮሙማው ሲያወድም መምህራንና ዶክተሮችን፣ ተማሪዎችን እየገደለ፣ እየረሸነ በአደባባይ የሚፎክረው አርበኛ ዘመነ ካሤ የሚመራው የዐማራ ፋኖ በጎጃም ነው። ተማሪ በመረሸኑ፣ መምህራን በመግደሉ፣ ዶክተሮችን በመግደሉ ሳይሳቀቅ ዐማራን በማጥፋቱ ልክ እንደ ጁንታው፣ ልክ እንደ ኦሮሙማው በአደባባይ የሚፎክረው የጎጃሙ ጁንታ በምንም መልኩ ከገዳዩ፣ ከጨፍጫፊው ኦሮሙማ ከአቢይ አሕመድ አገዛዝ አይለይም። አርበኛ ዘመነ ካሤ ይሄን ሁሉ እያየ ዝም፣ ጭጭ ጮጋ በማለቱ የዐማራ ፋኖ መሪነቱን ጥያቄ ውስጥ ነው ያስገባው። የጎጃም ፋኖን መርቶ፣ ሥነ ሥርዓት አስይዞ ወደ ከፍታ ማምጣት ያልቻለ ሰው ነው እናም ዐማራን ለመምራት የአቅም፣ የችሎታም ውስንነት ይታይበታል ብለው ለሚከሱት ከሳሾች ማረጋገጫ ነው እየሰጣቸው የሚገኘው። የጎጃም ፋኖ እንደማይታዘዝለት በቀደም ዕለት የኢዜማው መንግሥቱና ሌላ አንድ ልጅ ከዘመነ ጋር የተለዋወጠውን ቃለ መጠይቅ በዘመድ ቴቪ አሰምቼአችኋለሁ። እናም ዘመነ ራሱ ነፃ ሊወጣ የሚገባው ምስኪን ሰው ነው። ዘመነ ካሤ በግሉ እኔ ሳውቀው ሰው አማኝ፣ ሁሉን ለማስደሰት የሚጥር፣ የሚደክም፣ ሃይማኖተኛ፣ የንባብ ሰው፣ አድማጭ፣ ደግሞም ጸሐፊ፣ አንደበተ ርቱዕ ተናጋሪ ሰው ነው። ነገር ግን ዘመነ ካሤ በአራጆቹ ፊት የቆመ ቀን የሚጠበቅለት የአብርሃም በግ ነው። እንደዚያ ነው የማምነው። አንዳንድ ሰዎች ዘመነ ካሤን ሲሰድቡት፣ ሲያዋርዱት የምናደደውም የማውቀውን ስለማውቅ ነው።

"…ዘመነ ካሤን ከኋላው ፖለቲካ የሚሠሩበት ሌሎች ናቸው። ፎቶ እያነሱ እየለጠፉ የሚያሰድቡት እነ አስረስ መዓረይ ናቸው። በቀደም እንኳ ዘመነ ካሤ ከእነ ስብሃት ነጋ፣ ከእነ ገዱ አንዳርጋቸው ጋር፣ ከእነ አሉላ እና ጀዋር መሀመድ ጋር አንድ መድረክ ላይ ቀርቦ በዚያ መጠን እንዲሰደብ፣ እንዲዋረድ፣ ከፍ ዝቅ…👇
👆 …እንዲል፣ የከበረ ስሙ እንዲንቋሸሽ ያደረጉት እነ አስረስ መዓረይ ናቸው። ቀደም ብሎም በጉባኤውም ላይ ዘመነ ካሤ ይገኛል ብሎ በፌስቡክ ገጹ የለጠፈው ራሱ አስረስ መዓረይ ነበር። የትግሬ አክቲቪስቶች እነ ፓስተር ማርያማዊት "ዘመነካሤን እያንቆለጳጰሱ አቤት ግርማው፣ አቤቱ ሞገሱ እያሉ ያሞካሹት፣ የወያኔ ዳይፐሩ በመልኩ ራሱ ቅጭጭ ያለ ጁንታ የሚመስለው አፍቃሬ ወያኔው ጎጃሜው ጋዜጠኛ በቃሉም ዘመነ ካሤ ምን አጠፋ፣ ምን በደለ፣ እንዴት ከስብሃት ነጋ ጋር አንድ ላይ ተገኘ ተብሎ እንዲህ ይኮናል ብሎ ያጓራው በምክንያት ነው። እናም ዘመነ ሲቀጠቀጥ እነ አስረስ ይረካሉ። አለቀ።

"…አሁን ወደ ኋላ ብሎ ነገር የለም። ሦስቱ ወደፊት መቀጠል ብቻ ነው ያለባቸው። ከቋራው ስብሰባ በኋላ በተደጋጋሚ ስልክ ቢደወል አላነሣ ያሉት ጎጃሞቹ ናቸው። ስብሰባ ቢጠራ አልመጣ ያሉት ጎጃሞቹ ናቸው። ሥራው መቋረጥና መቆም ስለሌለበት ሦስቱ ጎንደር፣ ወሎና ሸዋ የሚገርም፣ የሚያረካ፣ የሚያስደስት ውሳኔ አሳልፈው ግሩም መልእክት አስተላልፈዋል። ውሳኔውን አልቀበልም ያለው የጎጃሙ አማፂ የእነ አስረስ ቡድን ነው። ይሄ የሁሉም የጎጃም ፋኖ ፍላጎትና ውሳኔ በው ብዬ ለመቀበል አልችልም። በአፄ ቴዎድሮስ ስም ዕዝ መስርተን አንዋጋም፣ አንታገልም ያሉት አፍቃሬ ጁንታዎቹ አስረስ መዓረይ እና ማርሸት ፀሐዩ ናቸው። አፄ ቴዎድሮስን አምርሮ የሚጠላው ደግሞ ወያኔ ትግሬ መሆኑ ይታወቃል። እናም እነዚህን ጎጃም ላይ የተተከሉ ሾተላዮች ስንዴውን ከአረሙ ጋር እንዳትነቅሉ እየተጠነቀቃችሁ ከወዲሁ መላ ልታበጁለት ይገባል። ደፍራችሁ መናገር ጀምሩ። መከራከር ጀምሩ። መወያየት ጀምሩ። ጎጃም ከሌላው ዐማራ ተልይቶ ምንም እንደማያመጣ አስረግጣችሁ ነግራችሁ ወደ መስመር እንዲገባ አስደርጉ። ፉከራ፣ ሽለላ ምንም እንደማያዋጣ ጨክናችሁ ንገሯቸው። በግድ ጆሮአቸውን ቆንጥጣችሁ ለዐማራ ቤት አለቃ ብቻ ሳይሆን ዘበኛም፣ ገረድም ሆነህ በተመደብክበት ምድብ ለማገልገል ዝግጁ ሁን በሏቸው። ድፈሩ።

"…አክቲቪስት አሰማርተህ፣ ገንዘብ ስላለህ የራበውን ሁሉ ገዝተህ፣ ጎንደር ወንድምህን፣ ወሎ ወንድምህን፣ ሸዋ ወንድምህን እያሰደብክ፣ እየዘለፍክ አንተ ጎጃምን አታስከብረውም። ደሴት ላይ ለብቻው እንዲቀር እያደረግከው ነው በሉት። አዎ የጎጃሙ ኃይል እንደ አሜሪካዋ ሆሊዉድ፣ እንደ ህንዷ ቦሊዉድ፣ እንደ ናይጄሪያዋ ኖልዊድ የካሜራ መዓት፣ የአክተሮችም መዓት አሏቸው። እንደ አሜሪካኖቹ ነፍ ጋዜጠኞች፣ ሚዲያዎችም አሏቸው። ከጎጃም የወጡ የብአዴን ጋዜጠኞች፣ አክቲቪስቶች የትየለሌ ናቸው። ቲክቶክ የተሞላው በጎጃሙ ኃይል ነው። ሲፈልግ የዐማራ ፋኖ ሆኖ የሚተውን፣ ሲያሻው የአገው ኃይል ሆኖ የሚተውን፣ ሲያሻው ኃይለየሱስ አዳሙን ሆኖ የሚተውን ጠሽ፣ አውቆ አበድ የኢንተርኔት እብዶች አሏቸው። አፍቃሬ ወያኔ ሆኖ ሲተውን ቆይቶ ወዲያው ደግሞ ጎጃሜ ነኝ የሚል እንደ ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው ዓይነት በሁለት ቢለዋ የሚበላ ነፍ ጋዜጠኞች ነው ያሉአቸው። የቴሌግራም ሚዲያው በአብዛኛው የግዮን ፕሬስ፣ የግዮን ሚዲያ፣ አሻራ፣ ብላክ ላየኑ ሁሉ በእነ አስረስ መዓረይ የተጠረነፈ ነው። እናም በወንዙ ውስጥ የሚጯጯኸውን ሁሉ እየሰማችሁ ሳትረበሹ ኮስተር ብላችሁ አንድም አራትም ሆነው ማሊያ እየቀያየሩ የሚያጇክቡአችሁን ገስጿቸው። ብአዴኑ አፍቃሬ ወያኔው አንሙት አብርሃ፣ የኢትዮ ፎረሙ አበበ ባዩ በሙሉ አፍቃሬ ብአዴን ወያኔ ናቸው። እናም የዐማራ መከራ በአጭሩ እንዲያበቃ ከፈለግክ ዐማራ የሆንክ የጎጃሙን ሾተላይ መስመር አስይዘህ ሌሎቹንም እየደገፍክ ወደፊት መስፈንጠር ብቻ ነው ያለባችሁ። በቴዎድሮስ የሚያፍር ዐማራ ሰምቼም አይቼም አላውቅም። ጎንደር በበላይ ዘለቀ ዕዝ ሲፋለም እነዚህ ጎጃምን እያሳነሱ ያሉ ሾተላዮች በአፄ ቴዎድሮስ ስም ዕዝ አንመሰርትም ብለው ማፈንገጣቸው ብቻ ማንነታቸውን ይገልጠዋል። ማርሸት ፀሐዩ ዐማራ ጄኖሳይድ አልተፈጸመበትም ያለው በአደባባይ ነው። ወያኔ ብትመጣ ጥይት አንተኩስባትም ያለው አስረስ መዓረይ በአደባባይ ነው። የወያኔን ኮሎኔልና የጦር መኮንኖች ፈትቶ መቀሌ የሰደደው ይሄው አፍቃሬ ወያኔ ቡድን ነው። ወያኔ አሁን በራያና በጠለምት፣ በወልቃይትም ዐማራን ልትወጋ በዝግጅት ላይ ናት። እነዚያ የጎጃም ፋኖ አመራሮች ፈትተው የለቀቋቸው የጦር መኮንኖች ወሎና ጎንደርን ሊወጉ በዝግጅት ላይ ናቸው። ዋጠው።

"…ወንዝ ለወንዝ እየተንከራተትክ በ5ዲ ካሜራ እየተቀረጽክ ለሕዝብ መከራ እየተቀበልኩ ነው ብለህ ፕሮፓጋንዳ ለመሥራት አትላላጥ። እናንት መሪዎች ቦምቦሊኖ ኡሙንዱኖ ኢሹ ጮርናቄ መስላችሁ። ቡርቱካን መስላችሁ፣ በሰም የተወለወለ ጣውላ፣ ቅቤ የጠገበ የቅቤ ቅል መስላችሁ፣ ብራንድ ጫማ፣ ብራንድ ልብስ፣ የአልማዝ ቀለበትና የወርቅ ሰዓት እያጠለቃችሁ፣ በ2025 ሞዴል በ30 እና አርባ ሚልዮን ዘመናዊ መኪና እየተንፈላሰሳችሁ። ሌላው ተዋጊ ቅማል ወርሮት፣ ቅጫም ፈልቶበት፣ ኮሸሮ እየበላ፣ ክረምትና በጋ እየተፈራረቀበት እናንተ ሙድ አትያዙበት። ያልተጠረነፈ፣ ሥርዓት የሌለው፣ በገጠር ከተሞች ከረንቡላና ጆተኒ ሲጫወት የሚውል፣ ቲክቶክ ላይቭ ገብቶ ከሞጣ ቀራኒዮ ጋ አበባ አውርዱልኝ የሚል ጉድ ይዛችሁ አትፎግሩ። አዎ ለመሪዎቹ ተስማምቷችኋል። በብአዴን ጥበቃ እና መልካም ፈቃድ የገበሬ መሶብ እያስደነገጣችሁ፣ የእርሻ በሬ አርዳችሁ እየበላችሁ፣ ግብር፣ ቀረጥ እያላችሁ ዘርፋችሁ እየበላችሁ፣ ለአንዲት ሴተኛ አዳሪ 50 እና 60 ሺ ብር እየከፈላችሁ። ሁለት ሴት አቅፋችሁ እየተኛችሁ። ወይን፣ ቢራ፣ አረቄ በአፍጢማችሁ እስክትደፉ እየጠጣችሁ። ባሕርዳር፣ አዲስ አበባና ደብረ ማርቆስ ቪላ እየገነባችሁ። በዘመድ አዝማድ ስም ባየሀገሩ መሬት እየገዛችሁ። መኪና እየገዛችሁ ሀብታም ሆናችሁ እየኖራችሁ ነው። አሁን ግን በቃችሁ ሊባሉ ይገባል። ምረሩ።

"…ሰበር ዜና በስቦ ማስከዳት ሁለት ሚሊሻ ተማረከ፣ ሁለት የመከላከያ ሠራዊት ተቀላቀለን እያልክ እየፎገርክ መኖር የተሰለቸ ሆኗል። ዓመት ሙሉ ሪፎርም፣ እገሌ ብርጌድ አመራር ለወጠ ዜና አይሆንም። ድልም አያመጣም። መከላከያ ሲመጣ እየፈረጠጥክ ወገንህን አታስጨርስ። አምልጥ፣ ሲመጣብህ ሽሽ የሚል የጦር መሪ የሰማሁት የኦሮሙማውን ብራኑ ጁላ ሠራዊት ብቻ ነው። ከመቀሌ እስከ ሞላሌ የፈረጠጠ የማውቀው ያንን ብቻ ነው። ዘመነ ካሤ አዝዞን ነው ብሎ በጎጃም የሚፈረጥጥ ሰራዊት መኖሩን የሠማነው በዚህ ዘመን ነው። ጎጃማ በመፈርጠጥ አይታወቅም። ጎጃም የበላይ ዘለቀ እስትንፋስ ጀግና የሞላበት ምድር ነው። ጎጃም የእነ እጅጉ ዘለቀ ምድር ነው። ጎጃም የባድመን ምሽግ የሰበሩ አናብስቶችን የፈጠረ ምድር ነው። ጎጃም በአረቄያሙ ማርሸት የሚለካ ሕዝብ አይደለም። በፍጹም ጎጃም በመልክም ቢሆን አስረስ መዓረይ የሚወክለው ሕዝብ አይደለም። አስረግጬ ነው የምነግርህ ከሌላው ዐማራ አንድነት የሚለይህን ጎጃሜ ነኝ ባይ እንዳትሰማው። ተሟገት፣ ተከራከር፣ ላለመስማማት ተስማምተህም ቢሆን ትግሉ በፍጥነት ከዐማራ ክልል እንዲወጣ አድርግ። ትግሉ ዐማራ ክልል በቆየ ቁጥር የሚደቅቀው ዐማራው ነው። ይሄን አስምሩበት።

"…አቢይ አሕመድ ዐማራን አጠፋዋለሁ ብሎናል የሚለውን የእነ ታዬ ደንደአ እማኝነት፣ የእነ ሚልኬሳ፣ የእነ ገዱ አንዳርጋቸው ምስክርነት እኮ አያስፈልግህም። ዐማራ እየጠፋ ያለው እኮ አሁን በምታየው መልኩ ነው። ዓምና ከእስክንድር ጋር ዘንድሮ ከሦስቱ የዐማራ ግዛት ፋኖዎች ጋር አልስማማም ብሎ ክረምቱን ከአቢይ አሕመድ ጋር ችግኝ እየተከለ፣ ጫካ…👇
👆 …ተቀምጦ በበጋ ዐማራን በድሮን የሚያስጨፈጭፈው የጎጃሙ የእነ አስረስ ቡድን በጊዜ ወደ መስመር እንዲገባ ካልተደረገ አደጋው ለዐማራ ከባድ ነው። እኔ የምጽፈው ሲያነቡት፣ እኔ የምናገረው ሲሰሙት ይመርራል፣ ያንገሸግሻል፣ ያልተሸቀጠ፣ ያልተቀባባ፣ በይሉኝታ፣ በሼም ያልታጠረ ስለሆነ፣ ኦሪጅናል መድኃኒት ስለሆነ፣ ጨክኖ ለዋጠው፣ በትእግስት ለሰማኝ ግን ፈዋሽ መድኃኒት ነው። ጨክናችሁ ስሙኝ። ስሙኝና ተወያዩ። ከመተኛታችሁ በፊት እኔ የጻፍኩትን እንደ ከብት መልሳችሁ አውጥታችሁ አመንዥኩት። አላምጡት። ታተርፉበታላችሁ።

"…ከእነ ሚሊኬሳ፣ ታዬ ደንደአ፣ ልደቱ አያሌው፣ ገዱ አንዳርጋቸው በፊት እኮ እኔው ዘመዴ አቢይ አህመድ ዐማራን ሊያጠፋ እንደሆነ፣ የሽመልስ አብዲሳን የድምጽ ቅጂ አውጥቼ አሰምቼ አሳይቼአችኋለሁ። ትምህርት ቤትህ ከወደመ፣ የጤና ጣቢያህ ከወደመ፣ ሊቃውንቶችህ ከታረዱ፣ ማዳበሪያ ክልክለህ ገበሬው ካላረሰ፣ ሃኪሞች፣ ዶክተሮች፣ መምህራንና ተማሪዎች ከተረሸኑ፣ መጪው ጊዜ ራብ ሲመጣ እኮ ኦሮሞ ያመረተውን ስንዴ እየበላ፣ በሀኪሞቹ እየታከመ፣ በትምህርት ቤቶቹ እየተማረ ይሻገራል። አንተ ዐማራው እኮ ነህ የምትደቅቀው። የዐማራ ነጋዴ በፋኖም፣ በመከላከያም ከተዘረፈ፣ ሕዝቡ በሁለቱም ከተጨፈጨፈ ዐማራ ከዚህ በላይ እንዴት ይጥፋ? ለትግሬው ጦርነት እኮ የሟቾች ቁጥር ይገለጽ ነበር፣ የወደመ ንብረት ይገለጽ ነበር። አቢይ አሕመድ አማራን ወርሮ በብአዴን ፊትአውራሪነት መጨፍጨፍ ከጀመረ ጀምሮ የሟቾች ቁጥር ይታወቃል? የወደመው ንብረት ዋጋ ይታወቃል? እንደ ዐማራ ነፍሱ ርካሽ የሆነ ዜጋ በዚህ ዘመን አለ እንዴ? በልጆቹ የተከዳ፣ የተናቀ፣ እንደ ዐማራ የለም።

"…ዋጠው የምነግርህን። ዐማራ እኮ መከላከያን አሸንፎ ነበር። ሬሳ በሬሳ ከምሮት ነበር። ኋላ ላይ ነው ኦሮሙማው ሓሳብ ቀይሮ ለምን ዐማራውን በሆዱ ገዝቼ እርስ በእርሱ  አላዋጋውም ብሎ፣ ሆዳም ብአዴን፣ ሆዳም የዐማራ ሚሊሻ፣ ሆዳም የዐማራ ፎሊስ፣ ሆዳም የዐማራ አድማ ብተና፣ ሆዳም ፀረ ዐማራ የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላ ከጎንደር፣ ሆዳም የፖለቲካው አገው ፀረ ዐማራ አገው ሸንጎ ከጎጃም፣ ከወሎ የከሚሴ ኦሮሞ ከኦሮሞም የወሃቢይ እስላም ገዝቶ ከፋኖ ጋር ማፋለም የጀመረው። እነ መከታው ከሸዋ፣ እነ ኮሎኔል ሙሀባው ከወሎ፣ እነ ደረጄና እነ ጌታ አስራደ ከጎንደር፣ እነ ማርሸትና አስረስ ከጎጃም ስለተመቹት የዐማራ መከራው የረዘመው። ለአስረስ ሚስት እኮ በአሜሪካ እኔ ትግል ላይ ስላለሁ ብሎ ዶላር እየተሰበሰበላት ልጆቿን ነው የምታሳድገው። የጎጃም ጎጠኛ አክቲቪስት በሙሉ ገና ለገና የሰፈሬ።ልጅ፣ አብሮአደጌ፣ ጓደኛና ወዳጄ፣ ዘመዴ ሥልጣን ሲይዝ ሀገር ቤት ገብቼ ኢንቨስተር እሆናለሁ ብሎ እኮ ነው የሚላላጠው።የእኔ ዘመዶች ቤት ሥጋ ቆራጭ ሆኖ የሚሠራው ይሄነው የሸበሉ እንኳን ብአዴንነቱ፣ የመሬት ደላላነቱ አልለቀው ብሎ እየዳከረ ነው። የዘመነ ካሤ ወንድም ነኝ ባዩ እኔን ከዘመነ ካሤ ጋር ካገናኘኝ አንዱ የሆነው ግርማ አየለ እንዲህ የሚወበራው ጎጃም የዐማራ ፋኖን ጠቅልሎ እነርሱ በአሸናፊው የፋኖ መንግሥት ውስጥ ጀዋር መሃመድን፣ አሉላ ሰሎሞንን ለመሆን ከመሻት ነው የሚንጠራወዙት። ለዚህ ነው ሌላው አደረጃጀት እኛን በመሪነት ካልተቀበለን የዐማራ ትግል በአፍንጫችን ይውጣ፣ እኛ ከሞትን ሰርዶ አይብቀል የሚል ካርድ መዝዘው እየተጫወቱ ያሉት። ቀሽም በለው።

"…አሁን ሌላውን ወያኔ ለማለት ተጎጃም ፋኖ መሪና አክቲቪዝስቶች ሞራል የላችሁም። ከገዱ አንዳርጋቸው ጋር በአንድ መድረክ ቁጭ ብሎ የመከረው የጎጃም ፋኖ እንጂ የወሎ፣ ወይ የጎንደርና የሸዋ አይደለም። ሌላውን ፋኖ ወያኔ ለማለት የጎጃም መሪዎችና አክቲቪስቶች ሞራል የላችሁም፣ ከዋናው የዐማራ ችግር ኢንኪዩቤተር ከስብሃት ነጋ ጋር በአንድ መድረክ ቁጭ ብላችሁ የመከራችሁ እናንተ እንጂ ጎንደር፣ ወሎና ሸዋ አይደሉም። ከጃዋር መሀመድ ጋር ሸዋ፣ ወሎ፣ ጎንደር አይደለም የመከረው፣ የሥልጣን ጥም ብቻ ሳይሆን የዐማራን ትግል የጭቅጭቅ፣ የንትርክ መድረክ ከማድረግ ሌት ተቀን ከሚሠራው፣ በሚዲያ ሞኖፖሊ ብቻ ድምጹ ጎላ ብሎ የሚሰማው፣ መሬት ላይ ጠብ የሚል ሥራ ልጆቹ እንዳይሠሩ እጅ እግራቸውን ጠፍሮ ካሠረው ከጎጃሙ የእነ አስረስ መዓረይ ቡድን ዘንድ ነው የችግሩ ምንንጭና መንስኤው። እደግመዋለሁ በባዶ ሆድ ከመፎከር፣ ከመሸለል፣ ፍርጥ አድርጋችሁ አንደዜ መነጋገር።

"…ይሄ ርእሰ አንቀጽ ከተነበበ በኋላ ምንአልባትም የጎጃሙ ብአዴን ከኦሮሙማው ጋር በመመሳጠር የጎጃሙ ሾተላይ ቡድን ከእጁ እንዳይወጣ ጥቂት የደቡብ ልጆች፣ የኦሮሞና የዐማራ ሚሊሻዎችን እንዲደመስሱ፣ እንዲማርኩ፣ የገጠር ከተሞችንም እንዲቆጣጠሩ ሊያደርጉላቸው ይችሉ ይሆናል። የቆየ የወታደር ሬሳም፣ የቆየ ምርኮም ሊያሳዩን በሚዲያዎቻቸው ሊላላጡ ይሞክሩ ይሆናል። ብአዴን በሪሞት ኮንትሮል የሚመራው ፋኖ ከዚህ በዘለለ ምንም ሊያደርግ አይችልም። አክተሮቹ የማይሞቱበት፣ በዘመናዊ መኪና የሚምነሸነሹበት፣ ያበጠ ጳጳዬ መስለው የሚምነሸነሹት የዐማራ ፋኖ በጎጃም ሾተላይ መሪዎች ዶክመንተሪ ተሠርቶላቸው፣ ወንዝ ሲሻገሩ፣ ተራራ ሲቧጥጡ፣ ሲጋጋጡ ቀርጸው "ይሄ ሁላ ለእናንተ የምንከፍለው መስዋእትነት ነው" ለሊሉ ይችላሉ። እናንተመወ በሏቸው። በቃ አየናችሁ፣ ተመለከትናችሁ። አሁን የምንፈልገው ከጎንደር፣ ከወሎና ከሸዋ ወንድሞቻችሁ ጋር አንድነት ፈጥራችሁ የመከራ ሌሊታችንን እንድታሳጥሩት ነው እንድትሏቸው ነው። ድፈሩ። ያለበለዚያ ኦሮሙማው ይውጣችኋል።

"…ትግሬ የራሱ ሲኖዶስ አቋቁሟል። ኦሮሞም እንደዚያው። የዐማራው ብቻ ነው ሲሾም ዐማራን እያዋረደ፣ ዐማራን እያሳነሰ፣ ዐማራን እያንኳሰሰ ሲያበቃ ይቆይና ሲሻር እንደ አቡነ ጴጥሮስ ኒውዮርክ ተቀምጦ እንደ አዲስ እኛ ስንጮህ ሲያላግጡብን ቆይተው አሁን ደርሰው የሕዝብ አዛኝ፣ ተቆርቋሪ ለመሆን የሚላላጡት። ይሄ ሁሉ መነኩሴ፣ ካህን ሲታረድ ደንታ የማይሰጠው በትግሬና በኦሮሞ የተሞላው ሲኖዶስ ብቻ ሳይሆን ወገናቸው እያለቀ እኔ ከተመቸኝ ሌላው የራሱ ጉዳይ በሚሉ ራስወዳድ አባቶች ምክንያት የተነሣ ነው። አቡነ አብርሃም የአስረስ መዓረይ የአጎት ወይም የአክስት ምናምን ናቸው አሉ። አረጋ ከበደ ለጨፈጨፈው ሕዝብ ባሕርዳር ላይ ካባ እንዲያለብሱት በማድረግ የጅማ ኦሮሞዎቹ  ጢባጢቤ ተጫወቱባቸው። ትግሉ አይቆምም። በሰልፍም፣ በሽማግሌም አይቆምም። በጎጃምም፣ በጎንደርም፣ በሸዋና በወሎም ፍልሚያው አይቆምም። እንዲያውም እዚህ ፍልሚያ ውስጥ ወያኔና ሻአቢያም ይሳተፋሉ። ያነዜ ኤምሬት፣ ቱርክ፣ ግብጽና ሳዑዲም ይሳተፋሉ፣ እስራኤል፣ አሜሪካና እንግሊዝም ይሳተፋሉ። ጦርነቱ ገና አልተጀመረም። ነገር ግን ጎጃም በጊዜ ከታ ተካከለ የድል ቀኑ ያጥራል፣ ጎጃም ካልተስተካከለ ግን መዝግቡልኝ የዐማራ መከራው፣ ፍዳው ይረዝማል። የአገው ሸንጎ የጎጃም ፋኖን 90% ተቆጣጥሮታል። ትዕቢቱ ጣሪያ የነካውም ይኸው ቡድን ነው።…👆
👆

"…ለዛሬ እዚህ ላይ ላብቃ። በዚህ ላይ ሳምንቱን ሙሉ ተጨቃጨቁበት። ስደቡኝ፣ አዋርዱኝ፣ ኡኡም፣ ቁቁም በሉብኝ። ለደንታችሁ ነው። እኔ ግን ከራሴ አውርጃለሁ። ምስክሬም ማርያም ናት። ሰማይ አድምጪ፣ ምድርም ስሚ፣ ቤተ ክርስቲያን መስክሪ። እናንተም አንባቢዎቼ ምስክሮቼ ናችሁ። የተለመደው የጎጃም ጥላቻ አለበህ፣ ወዘተረፈ አስቀያሽ ትውከት አኞ የሆነ ጋጋታም እንሰማለን። ጎጃምማ የወንዶች ቁና፣ የጀግኖች ምድር፣ የሊቃውንት መፍለቂያ ምድር ነው። እኔ ሠራዊቱን፣ ሕዝቡንና ሙሉ መሪዎቹን ሸክፉ አላነሣሁም። ወመኔውን፣ ሴረኛውን፣ ቀጣፊውን ሁሉ ለይቼ ነው የመታሁት። የቀጠቀጥኩት። እናንተም ምስክሮቼ ናችሁ። ምክሬን ስማ ባትሰማም መከራው ልክ አስገብቶ ይመክርሃል። እኔን ከመሃል አውጡና ደፈር ብላችሁ ለመነጋገር ሞክሩ። እያለቀ ያለው፣ እየወደመ ያለው የእናንተው ቤተሰብ ነው። ድፈሩ፣ ፍጠኑ፣ ልዩነት ካለም ልዩነቱን አጥብባችሁ ወደ አንድነት ኑ። እልኸኞች አትሁኑ፣ እርስ በእርስ መነቋቆሩን ትታችሁ እርስ በእርስ ተመካከሩ። በደጉ ጊዜ ታላላቆቻችሁ ጎንደር ጎጃም ብለው ቢነቋቆሩ የጭንቁ ቀን ሲመጣ እኮ ጎጃምና ጎንደር አንድ ላይ ነው ያበረው፣ ጎንደርን ያወደመው የዓድዋ ትግሬውን ስሁል ሚካኤል ከጎንደር ዐማራ ጫንቃ ላይ ገልብጠው ያራገፉት እኮ ላስታዎችና ጎጃሞች ናቸው። ወልቃይት ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ ብለው በጎጃም ምድር በትግሬ አግአዚ ስናይፐር አናታቸው የፈረሰው እኮ የጎጃም ልጆች ናቸው። ዘመነ ኳሴ ይፈታ ብለው ባሕርዳር ድረስ መጥተው የጨፈሩት እኮ የጎንደር ከነማ ደጋፊ የአፄ ቴዎድሮስ ልጆች ናቸው። እናም እነ አስረስ ሊመከሩ፣ በጊዜ ሃይ ሊባሉ ይገባል። እንደ አቢይ አሕመድ በፎቶ ቦለጢቃ የሰው አንጀት ውስጥ መጎዝጎዣ ጊዜና ዘመኑም አልፏል። አሁን ዐማራ የሚፈልገው ተግባር እንጂ ፎቶ ሾው አይደለም። ተወደደም ተጠላም በጎጃም ምድር እንዲህም ሆኖ መዋደቁ አይቀርም። ለጎጃም ዐማራ ጀግንነቱ የዘሩ ነው። ኦሮሙማው ሲያወድመው እነ አስረስ ዝም ብለው ቢያዩ ሌላው ዝም ብሎ ያያል ማለትም አይደለም። እዚያው ሞቆ እዚያው መፍላት። 10 መከላከያ ገድለህ 1ሺ ንፁሐንን ማስፈጀት ልክ አይደለም። በፍጹም ልክም አይሆንም። በአንድነት ወደፊት ተስፈንጠሩ። የምናገረው ይመርራል። ግን ዋጠው።

• የአንድ የ10 ሰዎችን አስተያየት ለመቀበል ስል ቆይቼ የአስተያየት ሰንዱቁን እከፍትላችኋለሁ። እስከዚያው መልካም ንባብ።

• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!

~ ዘመዴ ነኝ ከጮቄ ተራራ…!
መልካም…

"…አሁን ደግሞ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ በተለመደው መልኩ የእናንተን ሓሳብ የምናደምጥበት ጊዜ ነው። መሳደብ፣ ነውረኛ ቋል፣ ቀፋፊ ቃል በመናገር የአንባቢ ዓይን ላይ ማስታወክ ክልክል ነው። ጦማሬ የሚያበሳጭ እንኳ ቢሆን ብስጭታችሁን፣ ንዴታችሁን ዋጥ አድርጋችሁ በጨዋ ደንብ መቃወም መብታችሁ ነው። አጀንዳ ማስቀየር አይፈቀድም። ለአስተያየት ሰጪዎች የጎንዮሽ መልስ በተለይ ስድድብ አይፈቀድም። ተሳዳቢዎችን በፍጹም አልታገስም። በጨዋ ደንብ መሞገት እየተቻላችሁ ነውረኛ ስድብ ተሳድባችሁ ባትቀሰፉ መልካም ነው።

"…1…2…3…ጀምሩ…
• ለዛሬ ይበቃል…!

"…ከስንት ሳምንት እረፍት በኋላ ብቅ ብል ይኸው አነቃቃኋችሁ። አወያየኋችሁ። ሰፈር መንደሩ ብዕር መዝዞ እንዲወያይ አደረግኩት። የተቃውሞ መልስ እንኳ እንዲህ በጨዋ ደንብ ሲቀርብ እንዴት ደስ ይላል። ዘመዴ ማለት ይሄ ነው። እኔማ ሰሞኑን በየቤቱ ዞርኩ፣ በየመንደሩ ተንከራተትኩ ወፍ የለም። ይኸው ዛሬ ብቅ ብል መንደሩ ሁሉ ደመቀ። አእምሮአችንም ምግብ አገኘ። የመኖሬ ጥቅም ለዚህ ነው። እንዲያ ነው በልልኝማ።

"…ነገን ወይም ከነገ ወዲያን ውዬ ደግሞ የቤተ ክህነቱን አካባቢ የጭቃ ዥራፌን ልለጥፈበት ብቅ እላለሁ። አስገድጄ ብደፍርም ኦሮሞ ስለሆንኩ ክህነቴ ታገደብኝ ብሎ እያለቃቀሰ ስላለው ቄስም፣ ስለ ቀጠለው የካህናት እርድ እና የአራጆቹ የወርቅ ሽልማትም እናወጋለን። ያንን አካባቢ የሚያደባይ አንድ ድሮን የመሰለም ርእሰ አንቀጽ ሰሞኑን እለቅባችኋለሁ። እስከዚያው የዛሬውን ርእሰ አንቀጽ ይዛችሁ ስትንጫጩ ክረሙ። ተወያዩ፣ ተከራከሩ። ተሟገቱ። ተጨቃጨቁ። እኔንም በየቤታችሁ ስትዘነጥሉኝ ዋሉ እደሩም።

"…የዘመድ ሚዲያ ቋሚ አባላትም የቋሚ አባልነት ምዝገባችሁን አጠናክራችሁ በሰፊው ቀጥሉ።

• ዘመዴ ነኝ ከጮቄ ተራራ…!
“…በደም አፍሳሹ ደም ካልሆነ በቀር ምድሪቱ ከፈሰሰባት ደም አትነጻም።” ዘኍ 35፥33

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ
“…ትታረዱና ትበተኑ ዘንድ ቀናችሁ ደርሶአልና፥ እንደ ተወደደም የሸክላ ዕቃ ትወድቃላችሁና እናንተ እረኞች፥ አልቅሱ ጩኹም፤ እናንተ የመንጋ አውራዎች፥ በአመድ ውስጥ ተንከባለሉ።” ኤር 25፥34

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ
መልካም…

"…ዛሬ ቤተክርስቲያን ግብር ትከፍል ዘንድ ተወስኖባት፣ ውሳኔውንም ለአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች እንዲሰጡ ቀበሌና ወረዳዎች ታዘው፣ እምቢ አልቀበልም የሚል የደብር አለቃ ካለ እየጠፈጠፋችሁ ዘብጥያ አውርዱት ተብለው ቀበሌና ወረዳዎች ጭንቅ ውስጥ ወድቀው እያየሁ ስለሱ ልጽፍ ነበር የፈለግኩት። መርካቶ አውቶቡስ ተራ ያለው አዲሱ ሚካኤል ብቻውን 2 ሚልዮን ብር ግብር እንዲከፍል መወሰኑን ሁላ ነው የሰማሁት። እነ አቡነ ሳዊሮስ ይሄን ለማስፈጸም ነው የተሾሙት። አዳናች አበቤን የሚልዮን ብር ዋጋ ያለው ወርቅ በመሸለምም ነው ሥራቸውን የጀመሩት። ገንዘብ የጠረረበት አገዛዙ ሙዳይ ምጽዋት ሰበራ ሊጀምርልህ ነው።

"…እኔ ግን እዚያው ጮቄ ሆኜ የዐማራ ፋኖ በጎጃምን አሁናዊ አደጋ፣ ለዐማራ እንደ ሕዝብ፣ ለጎጃም እንደጎጃም የደቀኑበትን የከፋ አደጋ ብንወያይበት ብዬ ቀኝ ትከሻዬን ስለሸከከኝ ምርጫዬን አፋጎ አደረግኩ። መቼም እንደድሮው የሚሰድበኝ ባይኖርም ጓ የሚል ጥቅመኛ የአፋጎ ካድሬ አይጠፋም እና፣ በተጨማሪም የአፋጎ የቴሌግራም፣ የፌስቡክ፣ የዩቱዩብ እና የቲክቶክ አክቲቪስቶችም አውርተው የሚበሉበት አጀንዳም ስለጠረረባቸው ለእነሱም በትበት የሚሉበት አጀንዳ ይሆን ዘንድ እንደ ኮሶ የመረረ፣ ቃሪያ በሚጥሚጣ የሆነ ደፋር ርእሰ አንቀጽ አዘጋጅቼላችኋለሁ።

• ዝግጁ ናችሁ ጎበዝ…? እስቲ አንድ 100 ያህል የቤቴ ሠራዊት ዝግጁ ነነ ዘመዴ ይበል።
"ርእሰ አንቀጽ"

"…የበቀደም ዕለቱን በጎጃም ያለውን የእነ አስረስ መዓረይን ቡድን አፈንጋጭ እና ትግል ጠላፊ ተግባር በተመለከተ በርእሰ አንቀጽ መልክ ከጻፍኩ በኋላ እንደድሮው በየፌስቡኩ፣ በየዩቲዩቡ፣ በየቲክቶኩ ቅጥረኛው የአፋጎ አክቲቪስት እንደተልባ ይንጫጩብኛል ብዬ ጠብቄ ነበር። ነገር ግን እንደጠበቅኩት አይደለም የሆነው። በረዶ እንደመታው ሰብል ስብርብር ያሉ ጥቂት ድምጾች ሲንፈራገጡ ከማየቴ በቀር አብዛኛው የጎጃም ዐማራ አርምሞን መርጦ ወደ ምርምር፣ ወደማንሰላሰል ነው የገባው። ጥቂት የጎጃም ፕሮፌሰር፣ ዶክተር ነን ባዮችና ከእነ አስረስ መዓረይ ጋር ተጣምረው የዐማራ ፋኖ በጎጃም ሥልጣኑን ሁሉ ጠቅልሎ ወስዶ ዙፋኑ ላይ ከወጣ በስተ እርጅና ሥልጣንና ሀብት እናገኛለን ብለው ከሚዳክሩት በቀር እውነተኛ የጎጃም ልጆች ነገሩን መመርመር ጀምረዋል። ይሄ መልካምና በጎ ጅምርም ነው።

"…እኔም ጎጃም ገብቼ ጮቄ ተራራ ላይም ወጥቼ አልወርድም ካልኩ መንፈቅ ሊሞላኝ ነው። ጮቄ ተራራ የኢትዮጵያ የውኃ ታንከር ነው። አየሩ ተስማሚ ነፍስን የሚያረካ፣ ሥጋን የሚያለመልም ነው። በአርምሞ ነገሮችን ለማጥናት ለተቀመጠበት ምስጢር ገላጭ ስፍራ ነው። አሁን አሁን ፈረንጆችም ሳይቀሩ እግር ያበዙበት ስፍራ ነው። እዚያ ሆኜ ነው የጎጃምን፣ የወሎና የጎንደርን እንዲሁም የሸዋን እንቅስቃሴ እየጎበኘሁ የምገኘው። እነ ግርማ ካሣ እነ ደሳለኝን በስልክ ሰብስበው ገንዘብ እናፈስላችኋለን እናንተ እኛ የምንላችሁን ሁሉ ስሙን ሲሉም በስብሰባው ላይ ገብቼ እየሰማሁ ነበር። ከእነ መከታው ወደ እነ ደሳለኝ የዞረው የግርማ ካሣ ቡድን አንድ የባህርዳር ተወላጅ የጎጃም ጋዜጠኛም ይረዳቸው ዘንድ ወደ ሸዋ መላኩን እና እነ ደሳለኝም ይቀበሉት ዘንድ እንደተነገራቸው፣ ኢንጂነር ደሳለኝም ጉዳዩን ወደ ዶክተር አብደላ እንደመራውም ሰምቻለሁ። ሸዋን ሊበሉት ነው። የደሳለኝም ሆነ የሸዋ መሪዎች እነ ቡሩኬ፣ እነ ፕሮፌሰር ማርከው፣ እነ ዳግም፣ እነ አብደላና ካሣም የሚፈተኑት አሁን ነው። ግርማ ካሣ ገንዘብ አቅርቦ አፈር ከደቼ ሊያበላህ ነው። አሰግድ መሰበር አለበት ብሎ አሰግድን የሰበረው ግርማ ካሣ እነ ደሳለኝን በፈረንካ ሳያማልል አልቀረም የሚሉ መተርጉማንም አሉ። እኔም ከሸዋ በጉዳዩ ዙሪያ ማብራሪያ እየጠበቅኩ ነው።

"…ወደ ጎጃሙ አፋጎ ጉዳይ እንመለስ።  በአፋጎ ውስጥ ያለው ድብቅና ግልጽ ችግር የሆነውን አንድ ሁለት ብለን ከስር መሠረቱ ጀምረን ጥቂት በጥቂት ወደመመልከቱ እንግባ። እዚያው ጮቄ ተራራ ላይ ቁጭ ብዬ ከመላው ጎጃም እኔን ለመጠየቅ የመጡ መንፈሳውያን ከሆኑ እውነተኛ የአፋጎ ታጋዮች ጋር ጥልቅ የሆነ ውይይትም አድርጌ ነበር። በውይይታችንም መሠረት ነገርየውን በስሱ ከመነካካት በጥልቀት መመርመሩ ይበጃል፣ ይሻላል በሚልም ለምን ነጭ ነጯን አንነጋገርም። ሕመሙን የማይናገር በሽተኛ መድኃኒት ሊገኝለት አይችልም በማለት ተወያይተን በመጨረሻም የአፋጎ ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች የሆኑ ታጋዮች ትክክለኛውን የዐፋጎ የዐማራ ፋኖ በጎጃም ህመምና በሽታ ከነምልክቱ እንደሚከተለው ነግረውኛል። እናም እናንተም በአፋጎ ህመምና የበሽታ አምጪ ቫይረሶች ላይ ተነጋግራችሁ ለአፋጎ ብቻ ሳይሆን ለመላው ዐማራ ፈውስ የሚሰጥ መድኃኒት ትሰጡ ዘንድ እንደሚከተለው አድርጌ አቅርቤላችኋለሁ። የምጽፈው ርእሰ አንቀጽ ይመርራል ግን ይፈወሳል። ያደፈርሳል ግን ደግሞ ይጠራል።

1ኛ፥ ጎጃም ውስጥ ያሉ የፋኖ ጎጠኛ አመራሮች በዋነኝነት የሚሉት "በአሁኑ የዐማራ ፋኖ ውስጥ ሥልጣን ያለ ገደብ ያለማንም ከልካይነት ሰፋ አድርጎ የማይሰጠን ከሆነ ከዐማራ ፋኖ ኅበረት፣ አንድነት መውጣት ብቻ ሳይሆን ጎጃምን ራሱ ራሱን የቻለ ክልል አድርገን ከዐማራው ኅብረት እና አንድነት እንገነጠላለን" በማለት ነው የሚደሰኩሩት። የዓባይ ወንዝ በጎጃም መኖሩ ብቻ የውጪውን የዓረብና የእስራኤል ኃይል ትኩረት ስበን ራሱን የቻለ የፖለቲካ የስበት ማእከል እንሆናለን። በተለይ የዕዝ አመራር ነን የሚሉ ሰዎች ከእነ አስረስ መዓረይ ጀምሮ ይህን ሓሳብ ገዝተው አትርፈው ለመሸጥ እየተፍጨረጨሩ ነው። አይደለም ክልል በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ውስጥ በሱዳን መንግሥት ድጋፍ ከሚንቀሳቀሰው ከጉምዝ ነጻ አውጪ ግምባር  ጋራ ተስማምተን፥ መተከልን ይዘን ቦርደር ስለምናገኝ ሀገር እስከ መሆን እስከ መገንጠል ድረስ መሄድ እንችላለን እያሉ ነው። እኛ ጎጃሞች ሀገር ለመሆን ምንም የሚያንሰን ነገር የለም ስለ አዲስ አበባም ሆነ ስለ ሌላው ዐማራ ምን አገባን? በማለት በአጃቢዎቻቸው በኩልና በሚድያ ተከፋዮቻቸው በኩል እንደምታዩት ቱሪናፋቸውን እየነዙ ነው። ይሄ የጥፋት ቡድን ፈጽሞ በቀላሉ የሚናቅ አይደለም። ቡድኑ የሚደገፈው በሻአቢያ እና በግብጽ ጭምር ነው። ሻአቢያና ግብጽ ደግሞ ይሄ የጎጃሙ ቡድን አሸባሪ ቡድን ሁኖ እንዲኖር ነው እንጂ የሚፈልጉት ቡድኑ ከሌሎች የዐማራ ፋኖዎች ጋር ኅብረት አንድነት ፈጥሮ አራት ካሎ እንዲገባ አይደለም። ምን አልባት ከተሳካለት ባሕርዳርን ይዞ የጎጃም ክልል መንግሥት ለመሆን ሊጣጣር ይችል ይሆናል። ለዚህም ሲባል ከክልልነት አልፎ የእነ ዶክተር ሙሴን ህልም ለማሳካት ሀገር የመሆን ዕቅድ አለኝ ብሎም ከጎንደር መሬቶች የእኔ ናቸው ብሎ በቤተ ክህነቱም፣ በመንግሥታዊ አስተዳደር መዋቅሩም በኩል ድንበር እየገፋ ትንኮሳና ቁርሾም በመፍጠር በዐማሮች መካከል ራሱ የማያባራ ሁከት ለመፍጠር መንደርደር ጀምሯል።

2ኛ፥ እንደ ፋኖ የዐማራ ፋኖ በጎጃም ውስጥ ያሉት የዐማራ ፋኖዎች በቁመናቸውም ሆነ በአስተሳስባቸው ልከኛ መሪና በመርህ የሚመራቸው ድርጅት ካገኙ ምንም ችግር የለባቸውም። ሃይማኖተኞች ናቸው። በአንድ ዐማራ ያምናሉ። ከጎንደርና ከወሎ ከሸዋም ዐማራ ተለይተው ብቻቸውን ምንም ማምጣት እንደማይችሉም በሚገባ ይገነዘባሉ። ያውቃሉም። ነገር ግን አሁን ላይ በአረቄ መንፈስ እየተመሩ ከተመስገን ጥሩነህ ጋራም እየተማከሩ በሚዘውሩት የአፋጎ መሪዎች ምክንያት የዐማራ ፋኖ በጎጃም የትም በማይደርስ የመንደር ትግል እንዲታገል ተፈርዶበታል። ጎጃምን ከማውደም፣ ሊቃውንቶቿን ከማስፈጀት፣ ጎጃምን ከማድቀቅ የዘለለ ምንም ዓይነት ትርፍ አያመጡም። እንደ ሆሊውድ በሚዲያ ብዛት የሌለ ድል እዘበዘቡ ጠብ የሚል ነገር ሳይሠሩ ከመኖር፣ እዚያው ባሉበት ከመርገጥ በቀር ምንም አይፈይዱም። አብዛኛወን የአፋጎ የዕዝ መሪዎች ስንመለከት በብዛት ኤርትራ የከረመው የአዴኃን ሰዎች እንደሆኑ እንመለከታለን። ሻአቢያ በጎጃም አስቀድሞ ነው ስፍራ የያዘው። አርበኛ ዘመነ፣ ጥላሁን፣ ዝናቡ ወዘተረፈ በሙሉ ረጅም ዓመታት ግንቦት 7 ሆነው ኤርትራ የከረሙ ናቸው። ስለዚህ የጎጃም ፋኖ ከላይ በሻአቢያ፣ ከጎን በወያኔ፣ በግራና በቀኝ በኢዜማ፣ በአብን፣ በብአዴንና በኦሮሙማው ሳይቀር የተያዘ፣ የተጠረነፈ ነው። አገው ሸንጎና ቅባትን ስትጨምሩበት ደግሞ ይብሳል። ይሄንን ስብስብ ደግሞ መናቅ፣ ቸል ማለት ዋጋ ነው የሚያስከፍለው። የግንቦት ሰባት፣ የኢዜማና የብአዴን ኃይሉ እንዳለ ሆኖ ማለት ነው። የቅባት ሃይማኖትና የአገው ሸንጎ ፍላጎት እንዳለ ሆኖ ማለት ነው። እነግብፅ ሲጨመሩበት አስቡት። 👇
👆

3ኛ፥ በአፋጎ ከክፍለ ጦር በላይ ያሉ መሪዎች ከዚህ የተሻለ የጥቅም ቦታ ስለማያገኙ ትግሉን ለማራዘም ይገደዳሉ። ትግሉ በአጭር ጊዜ ከተጠናቀቀ ኪሣራ ስለሚገጥማቸው፣ የጀመሩትንም ኢንቨስትመንትና ልክና ገደብ የሌለው ገቢ ስለሚያስቀርባቸው ትግሉ በአጭሩ እንዲቋጭ አይፈልጉም። ሕዝብ አለቀ ለእነሱ ደንታቸው አይደለም። ዛሬ ያለ ከልካይ በሳምንት ውስጥ በሚልዮን ተከፋዮች ናቸው። የገቢ ምንጫቸውም ሰፊ ነው። ራሱ መንግሥት ተብዬው በእጅ አዙር ከፋያቸው ነው። የዐማራን አንድነት በየጊዜው ለሚያኮላሸው ለእነ አስረስ ቡድን አገዛዙ ራሱ በብአዴን በኩል የጠየቁትን ቢሰጥ ምኑ ይጎዳል? አግኝቶ ነው? የባለሀብቶች እና የድርጅት ንብረቶች በጎጃም ምድር በሚያልፉበት ጊዜ ችግር እንዳይገጥማቸው ከተለያዩ ድርጅቶች በሚልዮን የሚቆጠር ገንዘብ እየተከፈላቸው የሚሠሩ ናቸው። ለምሳሌ ከዳሽን ቢራ የማከፈለው አለ። ከሐበሻ ቢራ የሚከፈለው አለ። ከዱቄት ፋብሪካ፣ ከፌቤላ፣ ከብረታ ብረት ምርት፣ ከቀለም ፋብሪካዎች ወዘተ የሚከፈለው አለ። እርሻ ጠብቀው፣ ምርት አሳልፈው የሚከፈላቸው አሉ። እነዚህ ድርጅቶች የጭነት መኪናዎቻቸው በቀረጥም ሆነ በኬላ ከተያዘ አመራሮቹ በአስቸኳይ ተደውሎላቸው ይነገራቸውና ለኬላ ላይ ቀረጥ ሰብሳቢዎች "እሱ የእኛ ነው ልቀቀው" እያሉ በነፃ የሚያስለቅቁለት እነዚህ ዘናጭ የዕዙ የውስጥ አመራሮች ናቸው። ጫማቸው ውድ፣ ልብሳቸው ነጭ ነው የዕዙ አመራሮች። የጀነራል ውባንተ አባተን ሚስት 30 ሚልዮን ብር የሚያወጣ ምርት በወረሱ ጊዜ የውባንተ ሚስት ለአቤቱታ አስረስ መዓረይ እና ዘመነ ካሤን ጭምር ተማጽና፣ አንቺ የውባንተ ሚስት ስለመሆንሽ የጋብቻ ሠርተፍኪቴ ሁላ አቅርቢ ብለዋት፣ ለአስረስና ለዘመነ ካሤ ጭምር በኋትስአፕ የሠርጋቸውን ሙሉ ዶክመንትም ማስረጃና መረጃ ልካ ጥፊ ከዚህ ብለው ነው ሞጣ ላይ ገሚሱን ጠጥተው፣ ገሚሱን ሽጠውባት የ30 ሚልዮን ብር ንብረት አውድመው ያባረሯት። ሰዎቹ ሲበዛ ጨካኝ ናቸው። መረጃው በሙሉ ስላለኝ ነው እኔ የምናገረው። እኔ በበኩሌ አስረስ መዓረይን ፊቱን ሁላ ትኩር ብዬ ሳየው ከምር ዐማራም አይመስለኝ። የዐማራ መልክም፣ ወዝም የለው። ከምር እውነቴን ነው። የእናንተን ዐላውቅም እኔ ግን እንደዚያ ነው የሚታየኝ።

"…ተመልከቱ ይሄ ብቻ አይደለም ከዚህ በተረፈም በመላው ጎጃም የሚገኘውና በተለያየ መልክ በግብር፣ በቀረጥ የሚሰበሰበውም ገቢም 25% ለዕዙ ነው የሚገባው። በቀን ከ10 ሚልዮን ብር በላይ ገቢ አላቸው። እኔና ዘመነ ካሤን በስልክ አገናኝቶ ካስተዋወቁን ሰዎች መካከል አንዱ የሆነው አቶ  ግርማ አየለም ከዚህ ተነሥቶ ነው እኛ ጎጃሞች ሀብታም ነን፣ አቅምም አለን እናም ከማንም ሳንቀናጅ ብቻችንን ሁሉንም ነገር መፍጠር እንችላለን እስከማለት የደረሰው። አስረስ መዓረይም "ዘመዴ ቤተልሔምንና ግርማ አየለን ከሰው ቆጥረህ ነውን" ቢለኝም የእነ አስረስን ፍላጎትና ዕቅድ የማውቀው በእነዚሁ ገንገበቶች በኩል ነው። ልብ በሉ በቀን 10 ሚልዮን ብር በወር ስንት እንደሚመጣ ምቱት። በዚህ ብር ደግሞ በተወሰነው ብር አክቲቪስት ገዝተው ይቀጥሩበታል። ከጎጃም ወደ ዶላር ተቀይሮ ኡጋንዳና ካናዳ አሜሪካም ጭምር በዶላር ተመንዝሮ ይገባላቸዋል። በተለይ ደግሞ በአፋጎ ስም የሚሰበሰብ ዶላር በውጭ ሀገር ካለም ለአስረስ ሚስትና ልጅ ጨምሮ ለሰብሳቢ አክቲቪስቶቹ እንዲከፋፈሉት ይደረጋል። የቀረውን ብር ግን አመራሮቹ ይከፋፈሉታል። በየወሩም፣ በየሳምንቱም 400ሺህ 500ሺህ ስለ ሚደርሳቸው እነዚህ አመራሮች ትግሉ ቢቋጭ ይሄን ማግኘት ህልም ስለሚሆንባቸው የዐማራ ፋኖ አንድ ሁኖ መንግሥት ከሆነም ይሄ ሁሉ ጥቅም ስለ ሚቀርባቸው ካሉበት ንቅንቅ ማለት አይፈልጉም።

"…በዚህ ብር አንዲት ሴተኛ አዳሪ ሴት በ60 ሺህ ብር ይገዛሉ። ድሮ ሲመኟት የነበሩዋቸውን ሴቶች ያሉበት ጫካና የገጠር ቀበሌ ድረስ በእግር እና በሞተር ሳይክል አስጭነው አምጥተው ይጎለምቱበታል። ድህነት በተንሠራፋበት ማኅበረሰብ ውስጥ ለአንድ አዳር 60 ሺ ብር መክፈልና 60 ሺ ብር ማግኘት ማለት እንደቀላል የሚታይ አይደለም። ሴቶቹ ሴተኛ አዳሪ ብቻ አይደሉም። ኑሮ የከበዳቸው፣ ድህነት ያደቀቃቸው የቤት ልጆች ሁሉ ናቸው በዚህ ተግባር ላይ የተሰማሩት። 2 ሴት ይዞ የሚተኛ ሁሉ እንዳለ ነው የሚነገረው። ውስኪ እንደ ጉድ ነው የሚወርደው። ጾም የለ ፍስግ ፍየል እንደጉድ ነው የሚታረደው። እንዲያውም አንድ ጊዜ ወደ ዳሞት ለግምገማ የተጠሩ የፋኖ አመራሮች የምሳ ሰዓት ደርሶ ምሳ እንብላ ብለው ገምጋሚዎቹ ወደ ገበታው፣ ወደ ማዕዱ ተሰብሳቢ አመራሮቹን ይጋብዛሉ። ተጋባዦቹም ዕለቱ ረቡዕ ሆኖ በዚያ ላይ ጾም መሆኑን ዓይተው እንኳ ስሜታቸውን መደበቅ አልቻሉም። በቀጥታ ሽሮ አንበላም። ለህዝብ ነፃነት ብዬ ወጥቼ ነገ ልሙት ዛሬ ለማላውቀው ሽሮ አልበላም ይላሉ። አመራሩም ግራ ተጋብቶ ኧረ ሽሮ አትበሉም? በሉ እሺ ለእናንተ የፍስክ ምግብ የተዘጋጀው ከዚህ ትምህርት ቤት ጀርባ ነው። መሳሪያችሁን አውርዱና ተከተሉን በማለት፣ መሣሪያ አስወርደው ወደ ጓሮ በመውሰድ አንበርክከው በከዘራ ሳይቀር ቆምጠው፣ ቆምጠው የለቀቋቸው። አክቲቪስቶች ደጋ ዳሞትን ሞልጨው የሚሰድቡትም በብዙ ምክንያት ነው። ደጋ ዳሞት ግን ጀግንነቱ አሁንም አልተቋረጠም።

"…የዐፋጎ አመራር ዘወትር በቃ መቦረቅ ዘና ፈታ ማለት ነው። ባልተገደበው ገንዘብ ፍሰት ምክንያት ዩጋንዳ የነዳጅ ማደያ የሠራ አለ። ባህርዳርና አዲስ አበባ ሪልእስቴት የገዛ አለ። በቤተሰቡ የኢንቨስትመንት ቦታ ተቀብሎ መአድን ቁፈራ የገባ አለ። 4 እና 5 ሲኖትራክ የገዛም አለ። ባህርዳር ላይ ሁለገብ የኤሌክትሮኒክስ ሴንተር የከፈተም አለ። በገጠር የጎጃም የቀበሌ ከተማ ውስጥ ባለ 6 ወለል ፎቅ እየሠራ፣ እየገነባ ያለም አለ። አዲስ አበባ የባህል ልብስ መሸጫ ሱቅ የከፈተ አለ። የሚሆነው አይታወቅምና ዘሬን ሳልተካ እንዳልሞት በማለት ሴቶችን ሲያስወልድ የሚውል አለ። ባህርዳር መሬት ሊገዛ መጥቶ ዋጋው ይሄነው ተብሎ ተነግሮት ችግር የለም ሽጥልኝ ብሎ ሳይከራከር የሚከፍል ከሆነ ወንድሙ የፋኖ አለቃ ነው ማለት ነው። እገታው፣ ዘረፋው ሳይጨመር ማለት ነው። በሶማሌ ክልል በኩል በሶማሊላንድ የገባ 100 ሚልዮን ብር በልቷል የተባለው ማንችሎትን ከሥልጣን ካባረሩት በኋላ አሁን ሲጨንቃቸው ጥያቄ ሲበዛባቸው አጠገባቸው ያስቀመጡትም በምክንያት ነው። ይሄ በውል የሚታወቀው ነው። ያልተወቀውን ደግሞ እግዚአብሔር ይቁጠረው። አስረስ እንኳ አሜሪካ ለሚስቴና ለልጆቸ ቤት የገዛሁት ቪትስ መኪና ነበረችኝ እሷን ሽጨ ነው ሲል ቅሽሽ አላለውም። በዶክተሩ በኩል ተሰብስቦ ለሚስቱ የተሰጠውን ዶላር ግን አይተነፍሳትም። ቪትስ ተሽጦ ሚስቱ በአሜሪካ ቤት ሲኖራት ፈጣሪ ያሳያችሁ።

4ኛ፣ ብዙኀኑ የአፋጎ መሪዎች አማካሪዎቻቸው ሀገር ውስጥ አይደሉም ያሉት። ሀገር ውስጥ ያሉትም ቢሆኑ ብአዴኖች ናቸው። ከውጭ ያሉት ደግሞ እምነት የለሾች፣ ሊበራሎች እና ፓስተሮች ናቸው። እነሱ ደግሞ ከዐማራው ይልቅ አቢይን ስለሚወዱት ትግሉ እንዳያልቅ የማይሆን የህልም እንጀራ ምክር ይመክሯቸዋል። የብአዴን ሰዎች ደግሞ እንዲህ እንዲህ እያደረጉ በፋኖ በኩል የብልጽግናን መንግሥት ከውስጥ ሲያዳከሙ ቆይተው እነሱ ልክ እንደ ኦህዴዶቹ የውስጥ ሰርጄሪ ሠርተው ወደ ፊት መውጣት ይፈልጋሉ። ተመስገን ጥሩነህ ቀጣዩ ጠቅላይ ሚንስትር ለመሆን እያደረገው ያለው ጥረትም የሚዘወረው በዚህ በኩል ነው። ተመስገን ጥሩነህ ድንቁ ከወለጋ የሚመዘዝ ኦሮሞነት ስላለው እነ ሽመልስ…👇
👆 …አብዲሳ ሳይቀር የሚመኩበት ሰው ነው። ምንአልባትም ብለው አቢይ ቢወድቅና የጎጃሙ ቡድን እንደተባለው ሁሉን ሥልጣን ጠቅልሎ ቢመጣ ተመስገንን ሥልጣን በመስጠት ይኸው አሁን ደግሞ ዐማራ ነው የነገሠው በማለት ማስተንፈስ ይፈልጋሉ። ይሄ ፕላን B ነው እንጂ ዋነኛው ግን አይደለም። ዋነኛ ዓላማቸው ፋኖን ባለበት ማምከን እና እዚያው ባለበት እየረገጠ አርመጥምጦ ማስቀረት ነው። ይመርራል ግን እውነታው ይሄው ነው።

5ኛ፥ ከጎጃም ፋኖ የዕዝ መሪዎች መካከል ዳብል ኤጀንት ሁነው የሚሠሩቱ ብዙዎች ናቸው። ከብአዴን አመራሮች ጋራ "እኛ ብንጨርስ እናንተን እንጠብቃችኋለን እናንተ ብትጨርሱ እኛን ትጠብቃላችሁ" ተባብለው ተማምለውና ተስማምተው የሚኖሩ አሉ። አርበኛ ዘመነ ካሤና ጠበቃ አስረስ መዓረይ የሚንቀሳቀሱበትን ዘመናዊ መኪና መመልከት ይቻላል። ገና መከላከያ ስምሪት ሲሰጠው በዚህ በኩል ይመጣል ወጣ በል ቦታ ያዝ እየተባባሉ መረጃ ከብአዴኖቹ ጋር ይለዋወጣሉ። ፋኖም ለማጥቃት ወደ ከተማ ሲወጣ ለብአዴን መሪዎች አስቀድሞ እንዲጠነቀቁ መረጃ ይሰጣቸዋል። በሁለቱም መካከል ከፋኖም ሆነ ከብአዴን የሚያስቸግራቸው ካለ በጋራ ያስመቱታል። ያስወግዱታልም። ወደ ፊት በዐማራነቱ ክችች የሚል በዚያ ላይ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኝ ፋኖ ከሆነና አቅም እንዳለው ከታወቀ በድሮንም፣ በደፈጣም፣ ከጀርባም መትተው በስሙ ብርጌድ ያቋቁሙለታል። እንደዚህ አይነቶቹ ከፋኖ ዘንድ በቶሎ ይወገዳሉ። ከብአዴን በኩል ደግሞ በአፋ ፋኖን እያወገዘ በተግባር የሚረዳቸው አይነካም፣ በአፉም፣ በልቡም ብልፅግና የሆነ አመራር ሊስቱን ብአዴኖቹ ለፋኖዎቹ ይሰጣሉ፣ ከዚያ እያንበረከኩ ቆይተው ይረሽኑአቸዋል። እየሆነ ያለው ይሄ ነው።

"…በ2017 ዓም  ሙሉ የፋኖ የማጥቃት ኦፕሬሽኖች በበቂ ሁኔታ ሳይሳኩ የቀሩት እነዚህ አመራሮች ቀድመው መረጃ አውጥተው እየሰጡ በመሆኑ ነው። በዕዝ አመራሮቹ መረጃው እየወጣበት ኦፖሬሽኑ ያልከሸፈበት ብርጌድ እና ክፍለ ጦር የለም። ካሜራ ብቻ። ፕሮፓጋንዳ ብቻ። ሰሞኑን እንዲያውም "አይማን ፍለጋ" የሚል ዶክመንተሪ ይለቀቃል ብለው ሲሉ ሰምቼ ራሳቸው ፋኖዎቹን አይማን ደግሞ ምንድነው ብዬ ጠይቄ ነበር። አርበኛ ዘመነ ካሤና አስረስ መዓረይ በወንዝ ውስጥ እያቋረጡ ቪድዮ ተነሥተው የለቀቁትን አይቼ ነው የጠየቅኳቸው። አይማን ማለት ዘመዴ ወንዝ ነው። ያውም በክረምት ብቻ የሚወርድ እና የሚሞላ ወንዝ ነው። አይማን ወንዝ ከበሙር በእግር ሁለት ሰዓት ይወስዳል።  የነሳሚ እና የነሸጋ ጦር መዋያ ቦታ ነው። ከዚህ ወንዝ ተሻግሮ 30 ደቂቃ ከተጓዙ በኋላ አባይ ዳር የምትባል የገጠር  ከተማ ትገኛለች። አባይዳር በጣም ሰፊ የእርሻ ቦታ ያለበት ስፍራ ነው። ከዚህ አለፍ ብሎ ደግሞ በጣም ሰፊ የወርቅ ቦታ አለው። የወርቁን ማውጫ ቦታ የሚያስተዳድሩት ደግሞ ወርቀኞቹ የሚያገኙትን ገንዘብ እየቀረጡ የተቀመጡ ፋኖዎች ናቸው። የሰሊጥ ምናምን ሳይጨመር ማለት ነው። እናም "አይማን ፍለጋ" ሲሉ የወንዙን መነሻውን ወይስ መድረሻው ነው? የሚፈልጉት ብለን ዶክመንተሪውን በጉጉት እየጠበቅን ነው የሚሉኝ። ምን አልባት ወደሱዳን ለመሄድ ወንዙን እያቋረጡ ነው ከተባለ እንኳ ከወንዙ ጋር አብሮ በመጓዝ ነው እንዴ የሚሻገሩት። ወንዝን ቆርጠህ ትሻገራለህ እንጂ ወንዙ ወደሚፈስበት እየሄዱ ቪድዮ መቀረጽ አይነፋም። ስንጠረጥር ስንጠረጥር ግን ወርቅ ጭረት ላይ በሰፊው መሰማራታቸው አልቀረም። ሀብታሙ፣ ኢንቨስተሩ የጎጃም ፋኖ በጊዜ ካልታረመ ከአልሸባብም ሆነ ከቦካ ሀራም የከፈ ጨካኝ ሆኖ ጎጃምን ሲኦል እንደሚያደርገው ከወዲሁ መናገር ነቢይ አያስብልም።

6ኛ፦ የአፋጎ መሪዎች ለጎጠኝነቱም፣ ለክልልነቱም ለሀገርነቱም አስቸጋሪው ኢትዮጵያኒስቱና ሃይማኖተኛነቱ ነው ብለው ያምናሉ። ተሞክሮውን የወሰዱት ደግሞ ከህወሓት ነው። ህወሓት ብሔርተኝነቱ የተሳካላት ሕዝቡን ከእምነት እና ከሀገራዊ ስሜት አውጥታ ትግራዋይ ስላደረገችው ነው። እኛም ያሰብነውን ለማሳካት ሃይማኖተኞችን ገለል አድርገን ጎጃሜነትን ብቻ በመስበክ በታጋዩም በማኅበረሰቡም ዘንድ ማስረጽ አለብን ነው የሚሉት። በዚህ ምክንያት 99%ኦርቶዶክስ የሆነ ማኅበረሰብ ከጎንደር፣ ከሸዋ እና ከወሎ መገንጠልን አይወድልንም በማለት በማጥላላት ላይ ተሰማርተዋል። አማኙን ለማሸማቀቅም "የነጠላ ሥር ቁማርቸኞች፣ አክራሪ ኦርቶዶክሶች፣ ሞዐ ተዋሕዶዎች፣ ቲም ክርስቲያኖች፣ ወግ አጥባቂዎች፣ ትግላችንን የጎተተው ፖለቲካ ነው" እያሉ ለማሳቀቅ በስፋት እየሞከሩ ነው። ለዚህ ደግሞ በየጊዜው በአፋጎ የቀረጥ ብር የሚተነፍሱት እነ ሥጋ ቆራጩ ይሄነው የሸበሉ፣ እነ ጥልሚያኮስ አማኑኤል አብነት፣ እነ አስረስ ማረይ እና በመጠጥ፣ በአረቄ ብዛት ጉበቱ ፈርሶ የበለዘው ማርሸት ፀሐዩ ምስክሮች ናቸው።

"…ለምሳሌ በስፋት ዘመቻ የተከፈተባቸው ከጎንደር ዘመነ ካሤንና ሻለቃ ዝናቡን ከድሮን ጥቃት የታደገው ትልቁ ኢያሱን ሲሆን፣ ከወሎ ደግሞ የምሬ ወዳጆን ቀኝ እጆች ሄኖክ አዲሴን እና አበበን ነው። ኤልሻዳይ የጊዮን ልጅ የሚባለው የጎጃም አክቲቪስት እንኳ ነገር ዓለሙ ድንግርግር ሲልበት፣ በሄኖክ አዲሴ ላይ የተከፈተው የጎጃም አክቲቪስቶች ዘመቻ ሲደብረው እንዲህ ብሎ ነው በፌስቡክ ገፁ ላይ ያሰፈረው።

ለመረጃ ያክል

"…ሄኖክ አዲስ የፋኖ መሪዎችን ለመምረጥ በተሳተፈባቸው ሦስት ምርጫዎች ድምጽ የሰጠው ለዘመነ ነው። ዘመነን ነው መሪየ ይሆናል ብሎ በተደጋጋሚ ጊዜ ድምጽ የሰጠው። የመጀመሪያው አፋህድን በፈጠረው ምርጫ ከእስክንድር ይልቅ ዘመነን መርጧል፤ ባለፈው መስከረም ለሚዲያ ይፋ ባልሆነ ምርጫም ለዘመነ ድምፁን ሰጧል። በቅርቡ አፋብኃ ምስረታ ወቅት የመሪዎች ምርጫ ውጤት ተቀባይነት አጦ ሴንትራል ኮማንድ ቢመሰረትም ድምጽ የሰጡው ግን ዘመነ መሪ እንዲሆን ነበር።

"…ሄኖክ ያመነበትን እውነት በጊዜ እና በቦታ ሳይለዋውጥ አንድ ወጥ ሆኖ ቢገኝም ዛሬ ጠላት ተደግጎ በፌስቡክ እና በቲክቶክ እየተዘመተበት ነው። ሄኖክ ከዚህ በላይ ምን ያድርግ? እንደ እየሱስ ክርስቶስ  ፍቅሩን ለመግለጽ ተሰቅሎ ማሳየት ነበረበት? በጣም የሚገርመው ነገር ይህ ሁሉ የስድብ እና የስም ማጥፋት ዘመቻ እየተደረገበት አቁሙ የሚል አንድ አመራር መጥፋቱ ነዉ። ከሰኔ 15 ማግስት ጀምሮ በጎጃም የፓለቲካ፥ የኢኮኖሚ እና የባህል ሊህቃን ላይ የተቀናጀ እና ተከታታይነት ያለው የሚዲያ ዘመቻ ሲከፈት የወሎ ሊህቅ እና አክቲቪስት ነበር  ከጎናችን የነበረው። ከዚህ በኋላ የጎጃም ፋኖ አጋርስ ማን ነው? በማለት ነው መልስ የሌለው ጥያቄ የሚጠይቀው። ዘመነ ካሤ በጎንደር፣ በጎጃምና በሸዋ አመራሮች ተመርጦ ሳለ የዘመነ ምርጫ ለአፋጎ እንዳይደርስ ይዘው፣ ደብቀው አቆይተው ዘመነካሤን አፈር ደቼ ያበሉት እነ አስረስ መዓረይ አሁን ደግሞ ዘመነን ብቻ አይደለም እንዳለ ጎጃምን ከዐማራነት አውጥተው ወይ ክልል አልያም ሀገር እናደርጋለን ብለው ነው የሚወበሩት። አዋሳን ደቡቦች ገንብተው ለሲዳማ እንዳስረከቡት ባህርዳንም ዐማሮች ገንብተው ለጎጃም ያስረክቡናል ነው ምኞታቸው። ከጎንደር፣ ከሸዋ፣ ከወሎ የተለየ ጎጃሜነት በራሱ የሞተ ነው። ፕሮፌሰር ሀብታሙ ሰምተሃል። እነ አስረስን ገደል ባትከታቸው ጥሩ ነው። እየመከርኩህ ነው አባቴ። 👇
2025/07/04 23:51:32
Back to Top
HTML Embed Code: