Telegram Web Link
አትሌት ሐጎስ ገብረህይወት በ5 ሺህ ሜትር የኢትዮጵያን ክብረወሰን አሻሻለ


ዛሬ በኦስሎ በተካሄደው የ5 ሺህ ሜትር የዳይመንድ ሊግ ውድድር አትሌት ሐጎስ ገብረህይወት የዓለም ሁለተኛውን ፈጣን ሰዓት አስመዝግቧል።

አትሌቱ ርቀቱን 12 ደቂቃ ከ36 ሴኮንድ ከ73 ማይክሮ ሴኮንድ በመግባት አሸንፏል።

በ5 ሺህ ሜትር አትሌት ቀነኒሳ በቀለ 12 ደቂቃ ከ37 ሴኮንድ ከ35 ማይክሮ ሴኮንድ ይዞት የነበረውን የኢትዮጵያ ክብረወሰን አትሌት ሀጎስ ማሻሻል ችሏል።

የዓለም 5 ሺህ ሜትር ክብረወሰን ባለቤቱ ዪጋንዳዊው አትሌት ጆሽዋ ቼፕቴጌ የገባበት ሰዓት 12 ደቂቃ ከ35 ሴኮንድ ከ36 ማይክሮ ሴኮንድ መሆኑ ይታወቃል ።

#ዳጉ_ጆርናል
ዶናልድ ትራምፕ በኒውዮርክ ፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተባሉ

ዶናልድ ትራምፕ በኒውዮርክ በቀረቡበት ታሪካዊ የወንጀል ችሎት በ34ቱም የቢዝነስ የክስ መዝገቦች በማጭበርበር ተከሰው ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል። የቀድሞ  የአሜሪካ ፕሬዝዳንት በወንጀል ሲፈረድባቸው በአሜሪካ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። እ.ኤ.አ. ጁላይ 11 ላይ የቅጣት ውሳኔ ይጣልባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

የቀድሞ ፕሬዚዳንቱ እስራት ሊጠብቃቸው ይችላል ነገር ግን የህግ ባለሙያዎች እንደሚናገሩት ከእስር ይልቅ የገንዘብ መቀጮ ሊሆን ይችላል ሲሉ ይናገራሉ። ትራምፕ ፍርዱን "አሳፋሪ" በማለት ጉዳዩን ሲመሩ የነበሩትን ዳኛ ወቅሰዋል። በቀጣዩ ዓመት በህዳር ወር ምርጫ ጆ ባይደንን ለማሸነፍ የምረጡኝ ዘመቻ ላይ ለሚገኙት ትራምፕ ከፍተኛ ትኩሳት ይሆናል።

ትራምፕ በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ቢባሉም አሁንም በምርጫው መወዳደር ይችላሉ። ፍርድ ቤቱ ከትራምፕ ጋር የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ነበራት የተባለችውን ስቶርሚ ዳንኤልን ጨምሮ 22 ምስክሮችን ለስድስት ሳምንታት ቃላቸውን ሰምቷል ።የኒውዮርክ ችሎት የቀድሞ ፕሬዚዳንቱ ከገጠሟቸው አራት የወንጀል ጉዳዮች መካከል አንዱ ነው። በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኙት የፌደራል አቃቤ ህጎች ትራምፕ እ.ኤ.አ. ጃንዋሪ 6 2021 በካፒቶል አመፅ ማስነሳትን ጨምሮ በ2020 ያጋጠማቸውን የምርጫ ሽንፈት ለመቀልበስ በማሴር ከሰዋቸዋል።

በጆርጂያ ግዛት ደግሞ ትራምፕ በ2020 ያጋጠማቸውን ጠባብ ሽንፈት ለመቀልበስ በማሴር በ18 መዝገቦች ክስ ተመስርቶባቸዋል። ትራምፕ በፍሎሪዳ የፌደራል ክስ የተመሰረተባቸው ደግሞ ከዋይት ሀውስ ከለቀቁ በኋላ ሚስጥራዊ ሰነዶችን በአግባቡ ባለመያዝ እና ሰነዶቹን ወደ ግል ቤታቸው በመውሰድ ተከሰዋል። በድጋሚ፣ ዩፍሎሪዳ ዳኛ ግን ከትራምፕ የህግ ቡድን የቀረበለትን አቤቱታ በማጤን ችሎቱ እንዲዘገይ አድርጓል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
በጂንካ ከተማ በኩፍኝ በሽታ ምክንያት የህጻናት ህይወት እያለፈ መሆኑ ተገለፀ

የኩፍኝ በሽታ ወረርሽኝ  ዳግም እየተከሰተ በመሆኑ  ማህብረሰቡ ጥንቃቄ እንድያደርግ የጂንካ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ ገልፀዋል ።

በጂንካ ከተማ አስተዳደር ከሚያዝያ 4 ጀምሮ የኩፍኝ በሽታ ስርጭት የቆመ ቢሆንም ከግንቦት 08 ቀን 2016 ጀምሮ ዳግም መቀስቀሱን በዚህ ህጻናት በህመሙ እየጠቁ ህይወታቸው እያለፈ መሆኑን የጂንካ ከተማ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊ አቶ በቃሃኝ ጥላሁን በተለይ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

በያዝነው ሳምንት ብቻ ሁለት ታዳጊዎች  ህይወት ሲያልፍ በርካታ ህጻናት በህመሙ እየተሰቃዩ መሆኑም ተጠቁሟል። በበሽታው የተጠቁ ሰዎች አሁን ላይ በጂንካ ሆስፒታል ከጂንካ ከተማና ከአጎራባች ወረዳዎች በመምጣት የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በሽታው የተወሳሰበ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ማህበረሰቡ ጥንቃቄ እንዲደርግ ሃላፊው አሳስበዋል።

የበሽታው ምልክት ሽፍታ ፣ ትኩሳት እና መሰል ምልክቶች ሲገኙ ወደ ጤና ተቋም ሪፖርት እንዲደረግ ተጠይቋል። በከተማ አስተዳደሩ የቤት ለቤት ጉብኝት የተጀመረ ሲሆን ትምህርት ቤቶች የጥንቃቄ መልዕክትና ምልክቱ የታየበት ህፃን ሲገኝ ለጤና ባለሙያ ወይም ተቋም ሪፖርት እንዲያደረጉ ሲሉ አቶ በቃሃኝ ጥላሁን ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል
ትሸታላችሁ በሚል ከአውሮፕላን እንዲወርዱ የተደረጉ ሶስት ጥቁር ወንዶች የአሜሪካ አየር መንገድን ከሰሱ

ሶስት ጥቁር ሰዎች በአሜሪካ አየበዘር መድልዎ ከአውሮፕላን እንዲወርዱ የተደረጉ ሶስት ጥቁር ወንዶች የአሜሪካ አየር መንገድን ከሰሱ

ሶስት ጥቁር ሰዎች በአሜሪካ አየር መንገድ ላይ የዘር መድልዎ ክስ አቅርበዋል ።በሰውነት አካል ጠረን ቅሬታ ከቀረበባቸው በኋላ ለአጭር ጊዜ ከበረራ እንዲወርዱ መደረጋቸውን ክስ አቅርበዋል። አብረው ያልተቀመጡ እና የማይተዋወቁት እነዚህ ሶስት ሰዎቹ፣ ሁሉም ጥቁር ሲሆኑ ከፎኒክስ፣ አሪዞና ወደ ኒውዮርክ በረራ ነበራቸው። "የአሜሪካ አየር መንገድ ጥቁር በመሆናችን ለይተውናል፣ አሳፍረውናል እንዲሁም አዋርደውናል ሲሉ በጋራ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

መቀመጫውን ቴክሳስ ያደረገው አየር መንገድ ክሱ ከእሴቱ ጋር የማይጣጣም በመሆኑ ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል።በፌደራል የመሰረቱት ክስ እንደሚያስረዳው ሰዎቹ መቀመጫቸውን ይዘው ከፊኒክስ ለመውጣት በዝግጅት ላይ እያሉ የበረራ አስተናጋጆቹ ወደ እያንዳንዳቸውን ጠጋ ብለው ከአውሮፕላኑ እንዲወጡ ጠይቀዋል።  ግለሰቦቹ አልቪን ጃክሰን፣ ኢማኑዌል ዣን ጆሴፍ እና ዣቪየር ቬል ከአውሮፕላኑ ስንወጣ  "በበረራ ላይ ያለ ጥቁር ሰው ሁሉ እንዲወርድ እየተደረገ" ስል መሆኑ ተረድተናል ብለዋል።

ከቆዳችን ቀለም ሌላ ምንም አይነት ማብራሪያ የለም” ሲሉ ሰዎቹ በሰጡት መግለጫ በመጥቀስ “ይህ የዘር መድልዎ እንደነበር ግልጽ ነው” ሲሉ ተደምጠዋል። የአሜሪካ አየር መንገድ ሰራተኞች ሰዎቹን በሌሎች በረራዎች ላይ በድጋሚ ለማሶሳፈር ሞክረዋል፣ ነገር ግን በዚያ ምሽት ወደ ኒውዮርክ ምንም ዓይነት የበረራ አገልግሎት አልነበረም። የአሜሪካ አየር መንገድ በመግለጫው ላይ ሁሉንም የመድልኦ ጥያቄዎችን በቁም ነገር እንይዛለን እናም ደንበኞቻችን ከእኛ ጋር ለመብረር ሲመርጡ እንዲህ ዓይነት ሁኔታ እንዲያጋጥማቸው አንፈቅድም ብሏል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
ፖሊሱ የ 600 ሺህ ብር ሎተሪ ደረሳቸዉ

የአዲስ አበባ ፖሊስ አባል የሆኑት ኮንስታብል ዘካሪያስ መንገሻ በትንሳኤ ሎተሪ የብር 600 ሺህ ብር ዕድለኛ መሆናቸዉን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል። ኮንስታብሉ የደረሳቻዉን ገንዘብ ከብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ቼክ ተረክበዋል፡፡

#ዳጉ_ጆርናል
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ህወሓት መልሶ ሕጋዊ እውቅና እንዲያገኝ የሚያስችለዉን የአዋጅ ማሻሻያ ወደ ፓርላማ መራ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት “ከሕጋዊ እና ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማዕቀፍ ውጪ” ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የፖለቲካ ቡድኖች መልሰው እንደ ፖለቲካ ፓርቲ ለመመዝገብ የሚያስችላቸውን ድንጋጌ የያዘ የአዋጅ ማሻሻያን ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መራ።

በሥራ ላይ ባለው “የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ” ላይ የተደረገው ይህ ማሻሻያ፤ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የተሰረዘበትን የፓርቲነት ሕጋዊ እውቅና መልሶ እንዳያገኝ ያደረገውን የሕግ ጥያቄ የሚመልስ ነው።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአዋጅ ማሻሻያውን ተቀብሎ ወደ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመራው ዛሬ አርብ ግንቦት 23/2016 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ እንደሆነ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል። ጽህፈት ቤቱ ያወጣው መረጃ እንደሚያስረዳው ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት በአራት ረቂቅ አዋጆች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

ከእነዚህ ረቂቆች መካከል በሕገ ወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አድርጎ ስለማቅረብ እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የቀረበው አዋጅ ይገኝበታል።

በተጨማሪም የንብረት ማስመለስ አዋጅ እና የነዳጅ ውጤቶች የግብይት ሥርዓትን ለመደንገግ የቀረበው አዋጅም ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ ውሳኔ የተሰጠባቸው ሕጎች ናቸው።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት፤ በዛሬው ስብሰባ ውሳኔ እንደተላለፈበት በቀዳሚነት የጠቀሰው የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ አዋጅ ነው። ማሻሻያ የቀረበበት በ2012 ዓ.ም. የወጣው የምርጫ ሕግ፤ እውቅና የተነፈጉ የፖለቲካ ፓርቲዎችን መልሶ ከመመዝገብ ጋር በተያያዘ ክፍተት ያለበት እንደሆነ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ጠቅሷል።

“ከሕጋዊ እና ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማዕቀፍ ውጪ የቆዩ የፖለቲካ ቡድኖች በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ ፍላጎት በሚያሳዩበት ጊዜ እነዚህን አካላት ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ አድርጎ ለመመዝገብ የሚያስችል ሥርዓት በነባሩ አዋጅ ላይ አልተካተተም” ሲል በሥራ ላይ ያለው አዋጅ ላይ የታየውን ክፍተት ይገልጻል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ የመራው ማሻሻያ ላይ የፖለቲካ ቡድኖች “በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ እና ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት ፍላጎት በሚያሳዩበት ጊዜ” መልሰው ለመመዝገብ የሚችሉበትን ሥርዓት የሚዘረጋ እንደሆነም ተጠቅሷል።

ዛሬው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔ ላይ የተጠቀሰው የፖለቲካ ቡድኖች መልሶ የመመዝገብ ጉዳይ ከህወሓት ዳግም ሕጋዊ እውቅና የማግኘት ጉዳይ ጋር በተያያዘ ውዝግብ ፈጥሮ ነበረ ጉዳይ መሆኑ ይታወሳል።

Via ቢቢሲ አማርኛ
#ዳጉ_ጆርናል
ብሪጅ ብረታብረትና የእንጨት ስራ ኃ/ቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከአርቲስት ሊዲያና ሰለሞን ጋር ይፋዊ የብራንድ አምባሳደር ስምምነት ፈፀመ

ብሪጅ ኃ/ቱ የተወሰነ የግል ማህበር በዛሬው እለት በሞናርክ ሆቴል አርቲስት ሊዲያና ሰለሞንን ይፋዊ ብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾሟል።

አርቲስት ሊዲያና ሰለሞን በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ስምምነት እንደፈፀመች የተናገረች ሲሆን ፣ የብሪጅ ኢትዮጵያ ምርቶችና ድርጅቶች ለማስተዋወቅ የበኩሏን ድርሻ እንደምትወጣ ገልፃለች።

የብሪጅ ብረታብረትና እንጨት ስራ ኃ/ቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ደረጄ በላቸው፣ ከአርቲስት ሊዲያና ሰለሞን ጋር የፈፀምነው ስምምነት ድርጅታችን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እና ተደራሽነቱን ለማስፋት በማሰብ ነው ሲሉ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡

ብሪጅ በ 2002 ዓ.ም በ 50 ሺ ብር ካፒታል፣ በአነስተኛና ጥቃቅን ተደራጅቶ ስራውን የጀመረ ሲሆን፣ አሁን ከ25.5 ሚሊየን ብር በላይ ካፒታል ማፍራት ችሏል ሲሉ አቶ ደረጄ በላቸው አክለው ተናግረዋል።

ሊዲያና ሰለሞን፣ ብሪጅ ኢትዮጵያ በስሩ ከሚያስተዳድራቸው ድርጅቶች አንዱ ከሆነው ከዳልማንት ትሬዲንግ ጋር የብራንድ አምባሳደር ውል ተፈራርማለች።

አርቲስቷ በምን ያክል ገንዘብ የስፖንሰርሺፕ ውል እንደፈፀመች ከመግለፅ ተቆጥባለች።

ሰላማዊ ነጋሲ
#ዳጉ_ጆርናል
የደቡብ አፍሪካው ገዢዉ ፓርቲ እሮብ በተካሄደዉ ምርጫ አብላጫውን ድምጽ ማጣቱን የምርጫዉ ከፊል ዉጤት አመላከተ

👉 ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎሳ ስልጣን ሊለቁ ይችላል


የደቡብ አፍሪካው ገዥ ፓርቲ የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ (ኤኤንሲ) ስልጣን ከያዘ ከ30 አመታት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ የፓርላማ አብላጫውን ወንበር ሊያጣ ስለመሆኑ የምርጫዉ ከፊል ውጤቶች ጠቁመዋል፡፡እስካሁን ከ57 በመቶው በላይ የመራጮች ድምጽ በተለያዩ ወረዳዎች የተቆጠረ ሲሆን ገዢዉ አፍሪካን ናሽናል ኮንግረስ 42 በመቶ ድምጽ በማግኘት ሲመራ ዴሞክራቲክ አሊያንስ በ23 በመቶ በመያዝ ይከተላል።የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ ኤምኬ ፓርቲ 11 በመቶ ድምጽ እንዲሁም የኢኮኖሚ ፍሪደም ፋይተርስ ፓርቲ ደግሞ ከተቆጠረዉ ድምጽ 10 በመቶ የሚሆነውን አግኝቷል።

የመጨረሻው ውጤት በሳምንቱ መጨረሻ ይጠበቃል። ዛሬ ጧት ላይ የምርጫውን ውጤት የሚያሰራጨው የኦንላይን ሲስተም ችግር አጋጥሞት የነበረ ሲሆን ይህንኑ ተከትሎ፣ የምርጫ ስክሪኖች ዜሮ ውጤት አሳይተዋል።የደቡብ አፍሪካ ምርጫ ኮሚሽን ለጉዳዩ ይቅርታ ጠይቆ አገልግሎቱን ወደነበረበት እንዲመለስ አድርጓል።የምርጫው ውጤት ላይ ችግር እንደማያስከትል አስታዉቋል፡፡በርካታ መራጮች በሀገሪቱ ያለው ከፍተኛ ሙስና፣ ወንጀል እና ስራ አጥነት የተፈጠረዉ በገዢዉ ፓርቲ አፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ ድክመት ነዉ ሲሉ ተጠያቂ ያደርጉታል።

የሳይንስ እና ኢንዱስትሪያል ምርምር ምክር ቤት (CSIR) እና ኒዉስ 24 የዜና ድህረ ገጽ የፓርቲው የመጨረሻ ድምጽ 42 በመቶ አካባቢ እንደሚሆን ተንብየዋል ይህም በ2019 ምርጫ ካገኘው 57 በመቶ አብላጫ ድምጽ ከፍተኛ ቅናሽ ያሳያል።ዉጤቱ በዚህ የሚጠናቀቅ ከሆነ በፓርላማ አብላጫ ድምጽ ለማግኘት ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ወደ ጥምረት እንዲገባ ያስገድደዋል። ዋናኛተቀናቃኙ ዴሞክራቲክ አሊያንሰዝ የሊበራል ኢኮኖሚ ፖሊሲዎች ሲኖሩት የኢኮኖሚ ፍሪደም ፋይተር እና ኤም ኬ ፓርቲዎች ደግሞ የመንግስት ጣልቃገብነት እና ብሄረተኝነትን ይደግፋሉ፡፡

መንግስት ለመመስረት የሚቸገረዉ ገዢዉ አፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ የአጋር ፓርቲዎች ጋር የሚኖረዉ ጥምረት በደቡብ አፍሪካ የወደፊት አቅጣጫ ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣል።ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎሳ በስልጣን ላይ ይቆዩ ወይም ይዉረዱ ግልፅ አይደለም፣ ምክንያቱም ፓርቲው ከ45 በመቶ ያነሰ ድምጽ ካገኘ በፓርቲዉ ዉስጠጥ በሚፈጠረዉ ግፊት ከስልጣን ሊነሱ ይችላል ሲል ለትርፍ ያልተቋቋመው የዲሞክራሲ ስራዎች ፋውንዴሽን ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ዊሊያም ጉሜዴ ተናግረዋል።

በፓርቲው ውስጥ ያለ አንጃ ራማፎሳ በምክትላቸዉ ፖል ማሻቲል እንዲተኩ ግፊት ሊያደርግባቸዉ ይችላል። እንዲሁም የኢኮኖሚ ፍሪደም ፋይተር እና ኤም ኬ ፓርቲዎች ከገዚዉ አፍሪካን ናሽናል ኮንግረስ ጋር ማንኛውንም ጥምረት ለመመስረት ከመስማታቸው በፊት የፕሬዝዳንቱን የስራ መልቀቂያ ሊጠይቁ ይችላሉ ሲሉ ፕሮፌሰር ጉመዴ ለቢቢሲ ተናግረዋል።ደቡብ አፍሪካውያን ባላቸዉ የምርጫ ስርዓት መሰረት በቀጥታ ፕሬዚዳንቱን አይመርጡም። ይልቁን የህዝብ ተወካዮችን ይመርጣሉ፡፡ ተወካዮቹ ደግሞ ፕሬዚዳንቱን ለመምረጥ ስልጣን ይኖራቸዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
ለመልሶ ማልማት በተወሰደ ይዞታ ላይ ኮኬይን ዕፅ በቅሎ ተገኘ!!

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው ከዋናው ፖስታ ቤት ጀርባ ለመልሶ ማልማት በተወሰደ ቦታ ላይ በቅሎ የተገኘ ከ70 ኪሎ ግራም በላይ የሚመዝን የኮኬይን ዕፅ ችግኝ ፍሬው በእንጭጭ እንዲቀር በዛሬው ዕለት ነቅሎ አስወገደ።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ የፀረ-ፈንጂ እና የአደገኛ ዕፅ ቁጥጥር መምሪያ ለመልሶ ማልማት ተወስደው ለታቀደው ልማት ሳይውሉ ታጥረው በቆዩ ይዞታዎች ላይ ትዉልድ ገዳይ የሆነው አደገኛ ዕፅ እየበቀለባቸው መሆኑን በሕዝብ ጥቆማ እና ባደረገው ክትትል ደርሶበት እያስወገደ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት እና ተቋማት ለመልሶ መልማት የተያዙ ይዞታዎች አስፈላጊ ላልሆነ ተግባር እንዳይውሉ ትኩረት መስጠት እንደሚጠበቅባቸው እና ህብረተሰቡም ይህን ትውልድ ገዳይ አደገኛ ዕፅ በየትኛውም ቦታ በቅሎ ወይም ሲዘዋወር በሚመለከትበት ጊዜ ለፀጥታ አካላት መረጃ በመስጠት እያደረገ ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

ምንጭ:- የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ

#ዳጉ_ጆርናል
በህገወጥ መልኩ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ የትምባሆ ምርቶችን መቆጣጠር ባለመቻሉ የበርካታ ዜጎችን ጤና እየጎዳ ይገኛል ተባለ

👉በዛሬዉ እለት በዓለም አቀፍ ደረጃ ትምባሆን የመከላከል ቀን ታስቦ ዉሏል

በአሁኑ ወቅት በተለያየ መልኩ ወደ ኢትዮጵያ በህገወጥ መልኩ የሚገቡ ልዮ ጣእም ያላቸው የትምባሆ ምርቶች በዜጎች ጤና ላይ ጉዳትን እያስከተሉ ይገኛሉ ሲል የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታውቋል።በባለስልጣኑ የትንባሆ ጉዳይ ተወካይ የሆኑት አቶ ሞላ ታደለ ለብስራት ሬድዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት በአዲስ አበባ ከተማ ትምባሆ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳትን እያስከተለ ይገኛል።

በተለይ ደግሞ ወጣቶችና የነገ ሀገር ተረካቢ የሆኑ ዜጎች ለችግሩ ያላቸው ተጋላጭነት የጎላ በመሆኑ ከጉዳዮ አሳሳቢነት አንፃር ልዮ ትኩረት በመስጠት መስራት ይገባል ብለዋል።በአሁኑ ወቅት ወደ ሀገር ውስጥ  በህገወጥ መልኩ የሚገቡና  ልዮ ጣአም ያላቸው የትምባሆ ምርቶችን መቆጣጠር ባለመቻሉ በዜጎችን ጤናና በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ተፅእኖን እያስከተሉ ይገኛሉ ሲሉ አቶ ሞላ ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል።

በሚመለከተው አካል በኩል በህገወጥ መልኩ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡትን እነዚህን የትምባሆ ምርቶችን ለመቆጣጠር ጥረት ሲደረግ ቢቆይም ከችግሩ ስፋት አንፃር  በሚፈለገው ልክ ውጤት ሳይመጣ ቀርቷል፡ ለችግሩ መፍትሄ ለማምጣት የሴክተር መስሪያ ቤቶች ቅንጅታዊ አሰራር ሊጠናከር ይገባል ሲሉ ጠቁመዋል።በተለይም ደግሞ በኢትዮጵያ ድንበሮች አካባቢ ያሉትን የቁጥጥር ስራዎች ማጠናከር እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

ህገወጥ የትምባሆ ዝውውር በዜጎች ጤናና የሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመከላከል የትምባሆ ምርት አቅርቦትንና ፍላጎትን ለመቀነስ የሚያስችሉ ስራዎች እንደሚከናወኑ ባለስልጣኑ አስታውቋል።

በቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል
2024/06/01 03:02:57
Back to Top
HTML Embed Code: