የመላው ኢትዮጲያ ጨዋታ ከዘጠኝ አመታት መቋረጥ በኋላ ዛሬ በውቢቷ ጅማ በደማቅ ሁኔታ ተጀምሯል
👉 ከዘጠኝ አመታት በፊት አምስተኛው የመላው ኢትዮጲያ ጨዋታ በሀዋሳ ተካሂዶ እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም።
ዛሬ በጅማ ዩንቨርስቲ ስቴዲየም የመክፈቻ መርሀ ግብር የተካሄደ ሲሆን የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አወሉ አብዲ እና የባህልና ስፖርት ሚኒስትሯ ሸዊት ሻንካን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በኦሎምፒክ መርህ የሚካሄደውን መላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተመስገን ጥሩነህ የኦሎምፒክ ችቦውን በመለኮስ ለአትሌት ጌጤ ዋሚ እና አትሌት ኢብራሂም ጄይላን አስረክበዋል
“ስፖርት ለህብር ኢትዮጵያ አርበኝነት” በሚል መሪ ሀሳብ በሚካሄደው
በዚህ ውድድር ከ4500 በላይ ተሳታፊዎች በኦንላይን ምዝገባ ማድረጋቸውን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
ከዛሬ ከሰኔ 10-19 በጅማ ከተማ በሚካሄደው ውድድሩ ሁሉም ክልሎችና የከተማ መስተዳድሮች እንደሚሳተፉ ተረጋግጧል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ 26 የስፖርት አይነቶች የውድድሩ አካል እንደሚሆኑም ያወጣው መረጃ ያመለክታል።
የባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን ለመጀመሪያ ጊዜ በመላው ኢትዮጵያ ጨዋታ እንዲሳተፍ የተደረገ ሲሆን በስድስት የስፖርት አይነቶች በሁለቱም ጾታ ይሳተፋል።
ውድድሩ ኢትዮጵያ ለ2027 የመላው አፍሪካ ጨዋታ የምታደርገው ዝግጅት አካል መሆኑንም ተገንዝበናል።
በዳንኤል መምሩ
#ዳጉ_ጆርናል

❤25😁4👎3🔥1👏1
Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (Beⓒk)
የ 17 አመቱ ላሚን ያማል 30 አመት ከሆናት የበረራ አስተናጋጅ ከሆነች እንስት ጋር ግንኙነት መጀመሩ ተጠርጥሯል። ላሚን እና የተጠቀሰችዉ ሴት በጣሊያን በተመሳሳይ ቦታ ሆነዉ በኢንስታግራም ገጻቸዉ ላይ ፎቶ ከለቀቁ በኋላ በተከታዮቻቸዉ ግንኙነታቸው ተጠርጥሯል።
ሆኖም ላሚን ያማል ስለ ሁለቱ ሰዎች ግንኙነት ጥየቄ ቀርቦለት የሀሰት ነዉ ሲል አጣጥሎታል።
#ዳጉ_ጆርናል_ስፖርት
@Dagujournalsport

😁34❤4👎3🤬2🤔1
የሩስያ የጸጥታ ሃላፊ ከ2 ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ሰሜን ኮሪያ አቀኑ
የሩሲያ ከፍተኛ የደህንነት ባለስልጣን ሰርጌ ሾይጉ የሰሜን ኮሪያውን መሪ ኪም ጆንግ ኡን ለማግኘት ፒዮንግያንግ እንደደረሱ የሩሲያ መንግስታዊ መገናኛ ብዙሃን ማክሰኞ እለት ዘግበዋል። በዚህ ወር ባለፈው አመት በሁለቱ ወገኖች የተፈረመው አጠቃላይ የስትራቴጂክ አጋርነት ስምምነት የመጀመሪያ አመት በመሆኑ የሾይጉ ከሁለት ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ወደ ፒዮንግያንግ ያደረጉት ጉዞ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን ለመጨረሻ ጊዜ በጁን 4 የሰሜን ኮርያም መዲና ጎብኝተዋል።
ጉብኝቱ በድጋሚ "በሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን መመሪያ" የተደረገ ስለመሆኑ የሩሲያው ታስ የዜና ወኪል ዘግቧል። የሩስያ የፀጥታው ምክር ቤት መሪ የሆኑት ሾይጉ በቅርብ ወራት ውስጥ ወደ ሰሜን ኮሪያ በርካታ ጉዞዎችን አድርገዋል። የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም በፒዮንግያንግ የተፈራረሙትን የትብብር ስምምነት ተከትሎ ሰሜን ኮሪያ በዩክሬን ላይ በተከፈተው ጦርነት ሩሲያን ለመርዳት በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን አሰማርታለች።
ስምምነቱ ከሁለቱ ሀገራት በአንዱ ላይ በሶስተኛ ወገን ከተጠቃ ወታደራዊ ድጋፍን መስጠትን የሚያስችል ነው።
በስምኦን ደረጄ

👍16❤10
በሆለታ ከተማ አንዲት አህያ ፈረስ መውለዷ ተሰማ
በሆለታ ከተማ አስተዳደር ገልገለ ኩዩ ቀበሌ ውስጥ አንዲት አህያ ፈረስ መገላገሏን የከተማው አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ገልጿል ።
በሆለታ ከተማ ገልገለ ኩዩ የተባለ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት የአቶ ብርሀኑ ጐዳ ንብረት የሆነች የጭነት አህያ ፈረስ መውለዷ ተገልጿል ።
የአህያዋ ባለቤት የሆኑት አቶ ብርሀኑ ጐዳ እንደገለጹት ከአስር ዓመት በፊት የጭነት አህያዋን ከኤጀሬ ከተማ መግዛታቸውን ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም ባልታሰበ መንገድ በስድስተኛዋ እርግዝና ሆዷ ተልቆ የታየ እና ከዚህ ቀደም ግን አምስት አህዮችን ስትወልድ የተለየ የሰውነት አቋም እና ባህሪ እንዳልነበራት ተጠቁሟል።
የጭነት አህያዋ በስድስተኛ ወሊድዋ ሰኔ 5 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋት ሶስት ሰዓት ላይ ግን መጠኑ ከአህያ ውርንጭላ በአቋሙ የተለየና ሙሉ በሙሉ የፈረስ ዝርያ ያለው ውርጭላ መውለድዋን ተናግረው አጋጣሚው ግርምት እንደ ጫረባቸው አውስተዋል።
የሆለታ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ማዕከል አጠቃላይ የእንስሳት ጤና አጠባበቅ ዘርፍ አስተባባሪ ዶክተር ቤክሲሳ ኡርጌ እንደገለጹት በዘረ መል ምርመራ ሂደት የፈረስ እና የአህያ ክሮሞዞም ተመሳሳይነት ያለውና የአንደኛው የዘር ፈሳሽ የሚፈጠር ፅንስ ሲሆን በተለምዶ አህያ ከፈረስ ጋር የማዳቀል ሂደት በቅሎ የሚወለድ ይሆናል ማለታቸውን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።
አህያ ፈረስ የመውለዱ ሂደት የተለመደ ባይሆንም በሳይንስ የተረጋገጠ ቁጥር ባይኖርም አህያ ፈረስ መውለድ እንደሚችልና የተወለደውም በሽታን የመቋቋም አቅሙ ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል።
በአሁኑ ጊዜ የተወለደው ፈረስ ጤንነቱ ሙሉ ለሙሉ የተረጋገጠ እንደሆነና እናቱም በፍቅር ጡቷን እያጠባችው እንዳለ ተረጋግጧል።
በኤደን ሽመልስ

😁64❤26🤔11🤷♂3😱1
በባቢሌ ዝሆኖች መጠለያ ባለፋት አስር ዓመታት በሰዉና ዝሆን ግጭት 66 ሰዎች የሞት እና የአካል ጉዳት አደጋ አጋጥሟቸዋል ተባለ
በባቢሌ ዝሆኖች መጠለያ በሰዎችና በዝሆኖች መካከል በተፈጠሩ ግጭቶች ባለፋት አስር ዓመታት 66 ሰዎች ለህልፈትና የመቁሰል አደጋ አጋጥሟቸዋል ሲል የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል።
በባለስልጣኑ የጥበቃ ቦታዎች ልማት ዴስክ ኃላፊ አቶ ካሳዬ ዋሚ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት እኤአ ከ2016እስከ 2025 ድረስ በመጠለያው 86 የዝሆን ዝርያዎች እንደሞቱ ጥናቶች ያሳያሉ።ሰዎች ለእርሻና ለሌሎች ተግባራት በሚል በሚፈጥሩት ህገወጥ እንቅስቃሴ ምክንያት የህገወጥ ሰፈራ መበራከት ለችግሩ መፈጠር ከሚጠቀሱት ምክንያቶች መካከል ተጠቃሽ መሆኑ ተገልጿል።
በዚሁ መጠለያ ያሉት ዝሆኖች ከሰዎች ጋር በሚፈጥሩት ግጭት ሳቢያ ሰዎች ህይወታቸውን ሊያጡና የአካል ጉዳት ሊደርስባቸው እንደሚችል የገለፁት አቶ ካሳዬ በባቢሌ ዝሆኖች መጠለያ ቁልፍ ችግሮች እና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ባለስልጣኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ማካሄዱን ተናግረዋል።
ከኦሮሚያ እና ሱማሌ ክልል ከፍተኛ አመራሮች የመጠለያው አዋሳኝ ከሆኑ ዞኖች፣ ወረዳዎች እና ቀበሌዎች እንዲሁም ከሀሮማያ እና ጂግጂጋ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ውይይቱ መካሄዱ ታውቋል።
በቅድስት ደጀኔ

❤20😁16
አርኤስኤፍ በሊቢያ ድንበር አቅራቢያ ቁልፍ ቦታ መያዙን ገለጸ
የሱዳን ፈጣን ድጋፍ ሰጭ ኃይሎች ሰኞ እለት በሰሜን ሱዳን ግዛት ከሊቢያ እና ግብፅ ድንበሮች አቅራቢያ የሚገኘውን ኦሳይስ የተሰኘውን ስተራቴጂክ ቦታ መያዙን ገልጿል፣ ይህ እርምጃ የፓራሚሊታሪ ቡድኑ የአቅርቦት መስመሮቹን ለማጠናከር ይረዳል ተብሎለታል። አርኤስኤፍ ሀገሪቱን ለመቆጣጠር ከሁለት አመት በላይ በዘለቀው ጦርነት ከሱዳን ጦር ጋር እየተዋጋ ነው።
የአርኤስኤፍ አማካሪ መሀመድ ሙክታር ለሱዳን ትሪቡን እንደተናገሩት ኃይላቸው በጀበል አርኬኑ ተራራ ክልል አቅራቢያ የሚገኘውን “ካርብ አል ቱም” የተሰኘውን የባህር ዳርቻ ተቆጣጥረዋል። የተያዙት አከባቢዎች በሱዳን፣ ሊቢያ እና ግብፅ መካከል መገናኛ መስመር በሆነው ስልታዊ "ትሪያንግል" አካባቢ መያዙን ተከትሎ ነው።
በአካባቢው የተሰማራው የመከላከያ ሰራዊት ጥምረት ቃል አቀባይ ስለጉዳዩ ምላሽ ማግኘት አልተቻለም ተብሏል። ይህ የጦር ግስጋሴ የመጣእ የRSF መሪ ጄኔራል ሞሃመድ ሃምዳን ዳግሎ ጁን 2 በቪዲዮ ወደ ሰሜናዊ ግዛት ኃይላችን እየገባ እንደሆነ ከተናገሩ በኋላ ሲሆን ሰላማዊ ዜጎች በቤታቸው እንዲቆዩ አስጠንቅቀዋል።
በቀረጻው ላይ፣ ዳግሎ፣ RSF በአካባቢው “የISIS ታጣቂዎች” በማለት የገለጻቸውን የሱዳን ታጣቂዎች መረጃ እንዳላቸውና “ህጋዊ ኢላማ” እንደሆኑም ገልፆል። ዘመቻው በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት እንደማያደርስም ተናግረዋል።
ተንታኞች እንደሚሉት አርኤስኤፍ በኮርዶፋን እና በዳርፉር አካባቢዎች የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለማጠናከር ከሊቢያ የሚወስደውን የአቅርቦት መስመር ለማስጠበቅ እየሞከረ ነውም ተብሏል። በዳርፉር ክልል የሰራዊቱ የመጨረሻ ምሽግ በሆነው በኤል ፋሸር ላይ የ RSF ጥቃት ከተጠናከረበት ጋርም ይገጣጠማል።
በመሬት ላይ ያሉ ምንጮች እሁድ እለት በከተማይቱ ላይ የ RSF ጥቃት እጅግ በጣም ኃይለኛ ሆኖ እንደቀጠለ ገልፀዋል ይህም ከበባውን ለማጠናከር የተደረገው ጥረት አካል ነው ብለዋል።
በሚሊዮን ሙሴ

❤18👎2😁1
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የሕግ አገልግሎት መምሪያ በአቶ ትዝታው ሳሙኤል ላይ ክስ መሰረተ።
የቤተክርስቲያናችን ሕግ አገልግሎት መምሪያ ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ባቀረበው ክስ የወንጀል ምርመራ ተደርጎ የምርመራ መዝገቡ መብቱ ለሚፈቅድለት የዐ/ሕግ ዘርፍ እንዲተላለፍለፍ ጠይቋል።
በወንጀል ተጠርጣሪ /ተከሳሽ - አቶ ትዝታው ሳሙኤል
ተጠርጣሪ /ተከሳሹ ነዋሪነቱን በውጪ ሃገር በማድረግ የቤተክርስቲያኒቱ የበላይ ውሳኔ ሰጪ አካልን ለማዋረድ፣
ለመስደብ እና የምዕመኑን ስሜት ለመንካት ብሎም በሀገሪቱ ውስጥ ሁከትና ብጥብጥ እንዲነሳ በማሰብ በተለያዩ የመረጃ ማሰራጫ መንገዶች እና ከ5000 በላይ ተከታዮች ባሉት የራሱ የዪቲዩብ ቻናል በመጠቀም ከፍተኛ ቅስቀሳ ሲያደርግ መቆየቱን ገልጿል።
በማያያዝም ግለሰቡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብፁዓን አባቶችን፣ በየገዳማቱ ውስጥ የሚገኙ ገዳማውያን መነኮሳትና አገልጋዮችን <<ግብረ ሰዶማውያን ናቸው>> በማለት፣እንዲሁም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን <<የመተት እና ጠንቋይ ቤት ናት >>በማለት፣ሲቀሰቅስ የቆየ መሆኑን የገለጸው መምሪያው ግለሰቡ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የምትገለገልባቸውን ሃይማኖታዊ የፀሎት፣የታሪክ ፣የገድላትና ድርሳናት መጻሕፍትን <<ድውያን መጽሐፍት ናቸው መጥፋት አለባቸው>>ማለቱን ገልጿል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በቅድስናየምታ
ከብራቸውንና የምትዘክራቸውን ቅዱሳን አባቶች እና እናቶችን << ጣኦታትና ጣኦት አምላኪ>> ናቸው በማለት ግለሰቡ የፈጸመውን የወንጀል አድራጎት በመጥቀስም ክስ መስርቶበታል።
መምሪያው በአጠቃላይ ሰባት ነጥቦችን ያካተቱ የወንጀል ዝርዘርሮችን በመግለጽም ጉዳዩ ለሚመለከተው አካል ቀርቦ ግለሰቡ በሕግ ተጠያቂ እንዲደረግ ባቀረበው አቤቱታ ገልጿል።

👍95😁47❤26👎13🤷♂3🤔2
በአዲስ አበባ ሿሿ የሚሰሩ ወንጀለኞች ተያዙ
የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ በመምሰል በተለምዶ የሿሿ የተባለውን ወንጀል የሚፈፅሙ ተጠርጣሪዎችን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡
በተለምዶ ሿሿ የሚባለውን ወንጀል ለመከላከልና አጥፊዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል በጥናት ላይ በመመስረት እና ማስረጃ በማሰባሰብ ባደረገው እንቀስቃሴ ከዚህ ቀደም በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ በቂርቆስ፣ በቦሌ፣ በአቃቂ ቃሊቲ፣ በልደታ እና በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተሞች በልዩ ልዩ ስፍራዎች የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ በመምሰል በተለምዶ ሿሿ የሚባለውን ወንጀል የሚፈፅሙ አስራ አንድ አባላት ያሉት ሁለት ቡድኖችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ መቀጠሉን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ወንጀል ለመፈጸም ይገለገሉባቸው የነበሩ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2 አ/አ 53234፣ ኮድ 3 ኦ/ሮ 50777 እና ኮድ 2 አ/አ B 50438 ተሽከርካሪዎችን መያዙንና ከዚህ ቀደም በፈፀሙት የሿሿ ወንጀል አስፈላጊው ማስረጃ ተሰብስቦ አራት የምርመራ መዝገብ እንደተደራጀባቸው ፖሊስ መምሪያው ገልጿል፡፡
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በግለሰቦቹ ላይ ምርመራውን አጠናክሮ እንደቀጠለና አስፈላጊውን ማስረጃ እያሰባሰበ በመሆኑ ከዚህ ቀደም በእነዚህ ተሽከርካሪዎች የሿሿ ወንጀል የተፈፀመበት ማንኛውም ግለሰብ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በግንባር በመቅረብ ወንጀል ፈፃሚዎቹን በመለየትና በመምረጥ ማስረጃ መስጠት የሚችል መሆኑን ጥሪውን አስተላልፏል።

❤31👏24👍4🤔4😁1😭1