Telegram Web Link
Forwarded from ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal (#Me_Lion)
በእስራኤል አራን ውጥረት ዙሪያ ትንታኔውን ከጋዜጠኛ ሚሊዮን ሙሴ እና ስምኦን ደረጄ ይመልከቱ👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://youtu.be/kdOk0mCXBao?si=HvJ7F3JLOhE8Eet7
👍18😁84👎2💯1
የቴል አቪቭ ቅርንጫፍ በመጎዳቱ በእስራኤል የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ተዘጋ

በእስራኤል የአሜሪካ አምባሳደር እንደተናገሩት የቴል አቪቭ ኤምባሲ ቅርንጫፍ ከኢራን በተፈፀመበት ጥቃት መጠነኛ ጉዳት ደርሶበታል። ማይክ ሃክካቢ በኤክስ ላይ እንዳሰፈሩት ቆንስላ ጽ/ቤቱ በቴል አቪቭ በሚገኘው ህንፃ አቅራቢያ “በኢራን ሚሳኤል በመመታቱ” ተጎድቷል። በእየሩሳሌም የሚገኘው ዋናው የአሜሪካ ኤምባሲም ተዘግቶ ይቆያል ብለዋል። በጥቃቱ ግን የአሜሪካ ሰራተኛ አልተጎዳም ተብሏል።

የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር ኢራን በእስራኤል ዜጎች ላይ ባደረሰችው ጥቃት  አምስት ሰዎች ከተገደሉ በኋላ እንል በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች መቁሰላቸውን ተከትሎ የቴህራን ነዋሪዎች ዋጋ እንደሚከፍሉ አስጠንቅቀዋል። የመከላከያ ሚኒስትሩ ኢዝራኤል ካትስ የኢራን መሪ አሊ ካሜኔይን ሆን ብለው በሲቪል አካባቢዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እንዲፈፀም አድርገዋል ሲሉ ከሰዋል።

ካትስ ካሜኔይን "ፈሪ ነፍሰ ገዳይ" እና "ጉረኛ አምባገነን" በማለት ጠርተዋቸል። እስራኤል “በቅርብ ጊዜ” አጸፋውን እንደምትመልስ ተናግረዋል።የቴህራን ነዋሪዎችን በአካል የመጉዳት አላማ የለምን ሲሉ ካትስ በኤክስ ላይ ፅፈዋል።ኢራናውያን የአምባገነኑን ስርዓት ዋጋ ለመክፈል እና በቴህራን ውስጥ የአገዛዙን ኢላማዎች እና የፀጥታ መሰረተ ልማቶችን ማጥቃት አስፈላጊ ከሆነ ግን ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ ይገደዳሉ ብለዋል። የእስራኤልን ነዋሪዎች መጠበቃችንን እንቀጥላለን ሲሉ አክለዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
🔥3724👍6😁3👏1
የዉጭ ሀገር ቱሪስቶች አርባምንጭ ከተማን ለመጎብኘት የክረምት ወቅትን ይመርጣሉ ተባለ

በበጋ ወቅት በርካታ የዉጭ ሀገር ቱሪስቶች አርባምንጭ ከተማን የሚጎበኙ ቢሆንም ከተማዋ ካላት ሞቃታማ የአየር ንብረት ጋር ተያይዞ በክረምት ጉብኝት የሚያደርጉ የዉጭ ሀገር ቱሪስቶች በየዓመቱ ከፍተኛ ቁጥር እንደሚኖራቸዉ ተገልጿል ።

ባለፉት ዘጠኝ ወራት 46ሺህ 2መቶ 87 የዉጭ ሀገር ቱሪስቶች ጉብኝት ያደርጋሉ ተብሎ ታቅዶ 25ሺህ 3መቶ 11 ቱሪስቶች ጉብኝት ማድረጋቸዉንና የቱሪስቶቹ ቁጥር ከዕቅድ በታች ቢሆንም ከገቢ አንፃር የተሻለ አፈፃፀም የነበረዉ መሆኑን በአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም መስሪያ ቤት የልማት ዕቅድ ባለሙያ ህይወት ወንድሙ  ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።

261ሺህ 286 የሀገር ዉስጥ ቱሪስቶች ጉብኝት ማድረጋቸው የተገለፀ ሲሆን ከሀገር እና ከዉጪ ቱሪስቶች በአጠቃላይ ከ530 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተገኝቷል ። በከተማዋ ዉስጥ በርካታ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎች ሲኖሩ የአዞ እርባታ ፣የጫሞ ምንጮች ፣አባያ እና ጫሞ ሀይቅ የትራንስፖርት ችግር ስለሌለባቸው በዘጠኝ ወሩ በይበልጥ ከተጎበኙ ስፍራዎች መካከል ዋነኞቹ መሆናቸውን ባለሙያዋ ተናግረዋል ።

በሁሉም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ወይንም ከትናንሽ ቁርስ ቤቶች አንስቶ እስከ ትላልቅ ሆቴሎች ደረስ ክትትል በማድረግ የመስተንግዶ እንዲሁም የመኝታ ክፍል እድገት ላይ ተሰርቷል ተብሏል ።

በመባ ወርቅነህ
#ዳጉ_ጆርናል
17👍1
ትራምፕ ግጭቱን የማስቆም ስልጣን አላቸው  ሲሉ የቀድሞ የእስራኤል ዲፕሎማት ተናገሩ

በእስራኤል እና በኢራን መካከል ያለውን ግጭት የማስቆም ሥልጣን በአብዛኛው ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ነው ሲሉ ለሁለት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ምክር የሰጡት የቀድሞ ዲፕሎማት አሎን ፒንካስ ተናግረዋል። ትራምፕ በሰላም ስምምነት ለመደራደር በሚያስችል ሁኔታ ላይ ናቸው ሲሉ ፒንካስ ለኒውስዴይ ዓለም አቀፍ አገልግሎት ገልፀዋል።

ፕሬዚዳንቱ በድርድር ላይ የተመሰረተ ሰላምን ለመቀበል የሚያስችል ሁኔታን ለቴህራን ሊያቀርቡ ይችላሉ። ነገር ግን ኢራን ደካማ የመደራደር ቦታ ላይ በመሆኗ ትግሉን እንድትቀጥል እና በእስራኤል ላይ የበለጠ ጉዳት ለማድረስ ማበረታቻ ነው በማለት "በአንጻሩ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ስልኩን አንስተው ኔታንያሁ 'በቃህ ይህን ለመጨረስ 24 ሰአት አለህ' ሊላቸው ይችላሉ ሲሉ ተደምጠዋል።

በሌላ በኩል የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እስማኢል ባቃኢ እንዳሉት የኢራን ፓርላማ የኒውክሌርን መከላከል ስምምነትን ለመተው ህግ ለማውጣት እየሰራ ነው ብለዋል። ሆኖም ግን ቴህራን ጅምላ ጨራሽ የጦር መሣሪያዎችን ማምረት እንደምትቃወመው ገልፀዋል። እ.ኤ.አ. በ1968 የተፈረመው እና በ1970 ሥራ ላይ የዋለው 190 አባላት ያሉት ስምምነት ከዩናይትድ ስቴትስ፣ ሩሲያ፣ ቻይና፣ ብሪታኒያ እና ፈረንሳይ ውጪ ያሉ ፈራሚዎች የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እንዳይገዙ ከልክሏል። በምላሹ በተባበሩት መንግስታት የሚመራውን ሰላማዊ የኒውክሌርየር ፕሮግራሞችን በሃይል ማመንጨት እንዲቀጥሉ ይፈቅዳል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
😁2714👎3🕊3
እስራኤል አዲስ የተሾሙትን የአብዮታዊ ዘብ ከፍተኛ አዛዥን መግደሏን አስታወቀች

የእስራኤል ጦር በቴህራን ላይ ባደረሰው ጥቃት የአብዮታዊ ዘብ  ኻታም አል-አንቢያ ማዕከላዊ ዋና መሥሪያ ቤት ኃላፊ አሊ ሻድማኒ መግደሏን ገልፃለች። ሻድማኒ የኢራን “ከፍተኛ የጦር አዛዥ” እና “የኢራኑ ጠቅላይ መሪ አሊ ካሜኔይ የቅርብ ሰው” ነበሩ ተብሏል።

የእስራኤል መረጃ ተከትሎ ዘገባው እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ከኢራን በኩል የተሰጠ አስተያየት የለም።

አሁን ተገድለዋል የተባሉት ሻድማኒ የተሾሙት እስራኤል የካታም አል-አንቢያ ማዕከላዊ ዋና መሥሪያ ቤት አዛዥ የነበሩትን ጎላም አሊ ራሺድን አርብ ዕለት ከገደለች በኋላ ነው።

በተያያዘ መረጃ እስራኤል ኢስፋሃን ላይ በፈፀመቺው ጥቃት 3 ሰዎች ተገድለዋል ተብሏል። የኢራኑ መህር የዜና ወኪል እንደዘገበው ከሆነ እስራኤል ዛሬ ማለዳ በካሻን ከተማ በማዕከላዊ ኢስፋሃን ግዛት የፍተሻ ኬላ ላይ በፈፀመችው ጥቃት በትንሹ 3 ሰዎች ሲሞቱ 4 ሰዎች ቆስለዋል ተብሏል።

የታስኒም እና የISNA የዜና ኤጀንሲዎችም ስለሞቱት ሰዎች ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ግን አልሰጡም። እንደዘገበነው ከሆነ እስራኤል በኢራን ላይ ባደረሰችው ጥቃት ከ220 በላይ ሰዎች ተገድለዋል የተባለ ሲሆን ከሟቾቹ መካከልም ቢያንስ 70 ሴቶች እና ህጻናት ይገኙበታል ተብሏል።

በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል
😢2714👍13😁13👎7🕊6👏5🤯2
በ2017 በጀት ዓመት በ11 ወራት ከግብር ከፋዩ ማህበረሰብ 91 ቅሬታዎች ቀርበው ሁሉም መፈታታቸውን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ

ቢሮው በሚሰጠው አገልግሎት ላይ ግብር ከፋዩ ማህበረሰብ ችግሮች ካጋጠሙት በየደረጃው ለሚገኙ ለቅሬታ የስራ ክፍሎች በማቅረብ እንዲፈታ ማድረግ ላይ እንዳለነት አስታውቋል።

በቢሮው የአጠቃላይ አገልግሎት አሰጣጥ ቅሬታ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት ወይዘሮ አበባዬነሽ መልሴ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት  በ2017 በጀት ዓመት በ11 ወራት ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ በቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች 68 እንዲሁም በዋና መስሪያ ቤት 23 በድምሩ 91 ቅሬታዎች ቀርበው  59ኙ ተገቢነት ያላቸው እና  32ቱ ተገቢነት የሌላቸው ሆነው ተገኝተዋል።

ቢሮው የቅሬታ አቀራረቡን በቴክኖሎጂ ለማዘመን ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶት እየሰራ በመሆኑ ግብር ከፋዩ ማህበረሰብ እንዲህ ዓይነት ቅሬታ ፣ ጥቆማ ወይም አስተያየት ሲኖራቸው  ቅሬታዎችን  በሀሳብ መስጫ ላይ ከመፃፍ ይልቅ  ለአሰራርና ለግልፀኝነት ያመች ዘንድ  በፅሁፍ ቢያቀርቡ የሚበረታታ መሆኑን ተናግረዋል።

አጠቃላይ አገልግሎት አሰጣጥ ቅሬታ በታክስ ቅሬታ ላይ የሚቀርብ አቤቱታ እና የሠራተኛ ቅሬታን እንደማይጨምር ተገልጿል።

በትግስት ላቀዉ
#ዳጉ_ጆርናል
😁429👍1👎1
በእስራኤል አራን ውጥረት ዙሪያ ትንታኔውን ከጋዜጠኛ ሚሊዮን ሙሴ እና ስምኦን ደረጄ ጋር ይከታተሉ

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://youtu.be/kdOk0mCXBao?si=HvJ7F3JLOhE8Eet7

#ዳጉ_ጆርናል
8👍6🤣5🤔2
ራሚስ ባንክ የሞባይል መተግበሪያ እና የካርድ ባንኪንግ አገልግሎት በይፋ አስጀመረ

ራሚስ ባንክ  ቅዳሜ ሰኔ 7 1 2017 ዓ.ም የሞባይል መተግበሪያ እና የካርድ ባንኪንግ አአገልግሎቶቹን ስራ ለማስጀመር በተካሄደው ፕሮግራም ላይ የባንኩ ቦርድ ሊቀመንበር አቶ ራቢ ሁሴን እና የባንኩ ስራ አስፈፃሚ አቶ አሊ አሀመድ አሊ ባደረጉት ንግግር ራሚስ በይፋ ስራ ከጀመረ ገና ሁለት አመት የሞላው ቢሆንም በቴክኖሎጂው ዘርፍ ላይ  በስፋት እየሰራ መሆን የሚያሳዩ አመላካች ውጤቶችን በዚሁ መልክ እያዳበረ ማቅረቡን እንደሚቀጥል አሳውቀዋል።

ለደንበኞቹ ክፍት ካደረጋቸው ሁለት የዲጂታል አገልግሎቶች ውስጥ አንዱ ራሚስ ሞባይል አፕ የተሰኘው የሞባይል መተግበሪያ ደንበኞች ስማርት ስልክ በመጠቀም ብቻ ያለምንም የጊዜ ገደብ  ገንዘብ እንዲያንቀሳቅሱ፣ ክፍያ እንዲፈፅሙ፣ የሞባይል ካርድ እንዲሞሉ እንዲሁም ወደ ቴሌ ብር ዋሌት እንዲያስተላልፉ በማስቻል የደንበኞችን እርካታ በእጥፍ እንደሚጨምር ተገልጿል።

የራሚስ ካርድ ባንኪንግ ደንበኞች ባሻቸው ቦታ እና በፈለጉት ባንክ በመጠቀም በኤቲኤም ገንዘብ እንዲያወጡ የሚረዳ  መሆኑና በተጨማሪም በፈለጉት የፖስ ማሽን በሱፐርማርኬቶችና በተለያዩ የግብይት ላይ ክፍያ መፈፀም እንዲችሉ ይረዳቸዋል ተብሏል።

ራሚስ ባንክ ለትግበራ ያበቃቸው ፕሮጀክቶች ደንበኞችን ወደ ላቀ የዲጂታል ምህዳር የሚመሩና ባንኩ በዲጂታሉ ዘርፍ ልቆ ለመታየት ያለውን ቁርጠኝነት በጉልህ ያሳዩ እንደሆኑ የባንኩ ስራ አስፈፃሚ ተናግረዋል።

በቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል
25👏6👎1🤝1
እስራኤል ኢራንን ስታጠቃ በጋዛ እንደሚገኙት የመጠለያ ድንኳን መስለዋት ነበር ሲል አንድ ዓለም አቀፍ ተቋም አስታወቀ

የኩዊንሲ ስቴት ክራፍት ተጠያቂነት ኢንስቲትዩት ስራ አስፈፃሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ትሪታ ፓርሲ በኢራን ጥቃቶች የሚደርሰው ጉዳት እየጨመረ በመምጣቱ የእስራኤል የሚፈሩ የሚሳኤል መከላከያ ስርዓቶች ስንጥቅ እያሳዩ እንደሆነ ግልፅ ነው ብለዋል ። ፓርሲ ለአልጀዚራ እንደተናገሩት "የተከሰተ የሚመስለው ኢራናውያን የእስራኤልን የአየር መከላከያ ስርአቶችን አዋርደዋል፣ እናም በጥቂት ሚሳኤሎች የብዙ ሚሳኤሎችን ውጤት እያገኙ ነው ብለዋክ።

የቪዲዮ ማስረጃዎች የዴቪድ ወንጭፍ፣ የአይረን ዶም እና የአሜሪካ መከላከያ ስርዓቶች THAAD "ውጤታማ አለመሆንን" ያሳያል ብለዋል። "በአጠቃላይ እስራኤላውያን በግልፅ የተሳሳተ ስሌት ሰርተዋ። ይህ ቀላል እንደሚሆን አስበው ነበር ምልክ አሁን ለአንድ አመት ተኩል ያህል ስደተኞችን በድንኳን ውስጥ በጋዛ ላይ በቦምብ ከማፈንዳት ጋር ተመሳሳይ አድርገውት ነበር።

ይልቁንስ እውነተኛ ፍልሚያ እያገኙ ነው። እናም ጥያቄው የእስራኤል መንግስትን ስሌት ምን ያህል ቀይሮታል?" የሚለውን ነው ሲሉ ተደምጠዋል።ፓርሲ እስካሁን ድረስ እስራኤል ያደረገችው ብቸኛው እርምጃ ዩናይትድ ስቴትስ ወደ ጦርነቱ እንድትገባ መጠየቅ ነው፣ "ነገር ግን አሜሪካ እንደዛ ለማድረግ ምንም አይነት ምልክት አላሳየችም" ብለዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
👍8727👎11😁8🕊1
የኃይል ስርቆት በሚፈፅሙ በመካከለኛ ኢንዱስትሪ ታሪፍ መደብ ተጠቃሚዎች ላይ የ1 ሚሊዮን ብር ቅጣት ይተላለፋል ተባለ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተደራሽነቱን ለማስፋት ፣ጥራት ያለዉና ያልተቆራረጠ አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እየሰራ ቢሆንም የኃይል እና የመሠረተ ልማት ስርቆት ፈተና እንደሆነበት አስታዉቋል ።

ተቋሙ በዛሬዉ ዕለት በኢነርጂ አጠቃቀም ፣ቆጣሪና ተያያዥ ዕቃዎች ምርመራ መመሪያ ላይ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ከዚህ በኋላ በኃይል እና በመሠረተ ልማት ላይ በሚፈፀሙ ስርቆቶች ላይ ትዕግስት እንደማይኖረዉ ገልጿል ።

ይህን እኩይ ተግባር በሚፈፅሙ መካከለኛ ኢንዱስትሪ ታርፍ መደብ ተጠቃሚዎች ላይ የ1ሚሊዮን ብር ቅጣት እንደሚተላለፍ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሽያጭና የደንበኞች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ይህይስ ስዩም ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ። ለዝቅተኛ ኢንዱሰትሪ ታሪፍ መደብ ተጠቃሚዎች 750ሺህ ብር ፣ለጠቅላላ ታሪፍ መደብ ተጠቃሚ 500ሺህ ብር ፣ለመኖሪያ ቤት ታሪፍ መደብ ተጠቃሚ 20 ሺህ ብር ቅጣት እንደሚተላለፍ አቶ ይህይስ አክለዋል ።

ይህንን የስርቆት ተግባር በተደጋጋሚ በሚፈፅሙ አካላት ላይ የቅጣት መጠኑ እጥፍ እየሆነ እንደሚሄድ ተገልጿል ። የኤሌክትሪክ ኃይል ስርቆት መፈጸሙ ለተረጋገጠበት ደንበኛ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦቱ በጊዜያዊነት ከምሰሶ ወይም ከአቅርቦት መነሻ ላይ የሚቋረጥ ሆኖ የድርጅቱ የህግ አካል የምርመራ ሂደቱን ማጠናቀቁን በጽሑፍ እስኪያሳውቅ እንዲሁም ደንበኛው የሚጠበቅበትን ክፍያ እስኪፈፅም እና መተማመኛ የውል ሠነድ ላይ እስኪፈርም ድረስ ተቋርጦ የሚቆይ ይሆናል ተብሏል፡፡

በመባ ወርቅነህ
#ዳጉ_ጆርናል
9👍5
ኢራን በከፍተኛ ደረጃ የበለጸገውን ዩራኒየም የምትከማችበትን ቦታ በተመለከተ የምናውቀው የለም ሲል የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ አስታወቀ

የአለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ጥበቃ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የእስራኤልን ጥቃት ተከትሎ በኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር ውስጥ ነገሮች የት እንዳሉ በትክክል አናውቅም ብለዋል። ኦሊ ሄይኖን እስራኤል በቴህራን የኒውክሌር አቅም ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሳ ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል።

በናታንዝ የሚገኘው ተቋም "ለመመለስ ቢያንስ አመታትን ይወስዳል" ሲሉ ተደምጠዋል። "እኔ እንደማስበው ከእነዚህ የቦምብ ጥቃቶች በኋላ በጣም መጥፎ ቅርፅ ላይ ነው" ነገር ግን ቁልፉ ጥያቄ ይቀራል የሚሉት ሄይኖን ኢራን በከፍተኛ ደረጃ የበለጸገውን ዩራኒየም ከ400 ኪሎ ግራም በላይ የምትከማችበትን ቦታ በተመለከተ የምናውቀው የለም ብለዋል።

ሚስጥራዊ ጣቢያ ካላቸው እና የአለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ የማያውቀው በሚስጥር የጦር መሳሪያ ደረጃ ዩራኒየም ማበልጸግ ከቻሉ በእጃችን ላይ ትልቅ ችግር አለብን ሲሉ ተደምጠዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
39🕊4
300 ሺህ ብር ተቀጡ

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በትላንትናው እለት በቂርቆስ ክፋለ ከተማ ወረዳ 03 ወሎ ሰፈር አካባቢ በተሠራው የኮሪደር ልማት መሰረተ ልማት የእግረኞች መንገድ ላይ በተሽከርካሪ በመሄድ ደንብ ተላልፈው የተሰወሩ አሽከርካሪዎች ከአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ፖሊሶች ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር በማዋል መቅጣቱን አስታወቀ ።

ግለሰቦቹ በህብረተሰቡ ጥቆማ መሠረት ክትትል በማድረግ 3 አሽከርካሪዎች ከነ ተሽከርካሪአቸው በቁጥጥር ስር በማዋል እያንዳንዳቸው 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር ) በድምሩ 300,000/ሦስት መቶ ሺህ/ ብር መቀጣቱን ገልጸዋል ።

#ዳጉ_ጆርናል
😁4417👎9👏6👍5😢2
ሩሲያ በኪየቭ ላይ በፈፀመችው ጥቃት ቢያንስ 15 ሰዎች ሲገደሉ በደርዘን የሚቆጠሩ ቆሰሉ

ሩሲያ በዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ ላይ በፈፀመችው ጥቃት ቢያንስ 15 ሰዎች ሲገደሉ በደርዘን የሚቆጠሩ ቆስለዋል ሲሉ ባለስልጣናት ተናግረዋል። ከሦስት ዓመታት በፊት ሙሉ በሙሉ ወረራ ሩሲያ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከ ዛሬ ማክሰኞ ድረስ ከተፈፀሙት ጥቃቱ በኪዬቭ ላይ የደረሰው ትልቁ የቦምብ ጥቃት አንዱ ነው። የዩክሬን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ኢጆር ክላይመንኮ በሀገሪቱ በአጠቃላይ 440 ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና 32 ሚሳኤሎች መተኮሳቸውን ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሩስያ አየር መከላከያ ሰራዊት በአንድ ምሽት 147 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በመጥለፍ ማውደሙን የሞስኮ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።በኪየቭ ላይ የተካሄደው ጥቃት ከዘጠኝ ሰአት በላይ ፈጅቷል። ነዋሪዎችን ከእኩለ ሌሊት በፊት ጀምሮ ፀሀይ እስክትወጣ ድረስ ወደ ድብቅ መጠለያዎች እንዲሸሹ አድርጓል። ባለሥልጣናቱ ባሊስቲክ ሚሳኤል በአንድ ወረዳ የሚገኝ ባለ ዘጠኝ ፎቅ ሕንጻን መምታቱን ገልፀው ፤ በ27 የከተማዋ ወረዳዎች ጥቃር እንደደረሰባቸው ተናግረዋል። የዩክሬን ፓርላማ ሌሲያ ቫሲሊንኮ በኤክስ ላይ “በፍፁም ቅዠት ውስጥ ሆነን ነቅተናል፤  በፍርስራሹ ውስጥ የታገቱ ሰዎች አሉ ፤ ሙሉ ህንፃዎች ወድቀዋል ብለዋል። ክላይመንኮ እንዳሉት የነፍስ አድን ቡድኖች አሁንም ሰዎችን ከፍርስራሽ ውስሕ ለማውጣት እየሰሩ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

ሩሲያ ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በዩክሬን ከተሞች ላይ የአየር ጥቃትን አጠናክራለች፣ የዩክሬይን የአየር መከላከያዎችን ለማጨናነቅ የተነደፉ ትልቅ የሰው አልባ አውሮፕላኖችን እና ማታለያዎችን በመላክ ታክቲክ በማድረግ ጥቅቷን ፈፅማለች። በተፋላሚ ወገኖች መካከል ቀጥተኛ ውይይት የተኩስ ማቆም ወይም ጉልህ ለውጥ ማምጣት ባለመቻሉ ኪየቭ የራሷን የአፀፋ ጥቃት ጀምራለች። የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ የሩስያ የጥቃት ማዕበል “ግልፅ ሽብርተኝነት” ብለውታል። የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጦርነቱን ለመቀጠል የሚያስችል አቅም ስላላቸው ብቻ ነው ትልቁን ጥቃት የፈጸሙት ሲሉ ከሰዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
14😢6
ሚኪያስ ጎማ ፣ ባትሪና ከመነዳሪ አከፋፋይ 

#ለቪትስ
#ለያሪስ
#ለዲዛየርና ስዊፍት
#ለኮሮላ
#3L & 5L እንዲሁም ለከባድ ተሽከርካሪዎች የሚሆኑ ጎማዎች እና ባትሪዎችን ይዘዙን ካሉበት እናደርሳለን

👉የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት ጎማዎች (ትሪያንግል ፣ ስፖርትራክ ፣ ኮምፈርሰር ፣ አፖሎ ፣ ብሪጅስቶን እና ሌሎችም)

👉 የተገለገሉበት ጎማ ን ዋጋ ተምነን በአዲስ እንቀይርሎታለን

👉 በስልክ ቁጥር 📞...+251-913-701702 / +251-975293297 ይደውሉልን አልያም ተክለሀይማኖት ከሚገኘው ሱቃችን ይምጡ በደስታ እናስተናግድዎታለን
12
በጌድዮ ዞን በቤት ሰራተኝነት የምትሰራውን የ18 ዓመት ታዳጊ አስገድዶ በመድፈር የግድያ ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጌዴኦ ዞን ኮቾሬ ወረዳ በአስገድዶ መድፈር እና በግድያ ወንጀል የተከሰሰው ግለሰብ በእስራት መቀጣቱን የዞኑ ፖሊስ አስታዉቋል።

ተከሳሽ ደሳለኝ አሰፋ የተባለ ሲሆን በኮቾሬ ወረዳ በሐማ ቀበሌ ልዩ ቦታ ድንጋቴ ህዋስ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የካቲት 22 ቀን 2017 ዓ/ም በግምት ከቀኑ 7:00 ሠዓት አከባቢ የግል ተበዳይን አስገድዶ በመድፈር ለሞት የዳረጋት መሆኑ በማስረጃ ተረጋግጧል።

የወረዳው ፖሊስ የምርመራ መዝገብ እንደሚያስረዳው ተከሳሹ ግለሰብ የግል ተበዳይ በምትሰራበት ቤት ዉስጥ ሰዉ አለመኖሩን ካረጋገጠ በኃላ ወደ ቤት በመግባት  የኃይል ድርጊት በመጠቀም የአስገድዶ መድፈር ወንጀል በመፈፀም ለሞት ከዳረጋት በኃላ ለመሰወር ሞክሯል፡፡ የኮቾሬ ወረዳ ፖሊስ በደረሠው ጥቆማ መሠረት ተጠሪጣሪውን ተከታትሎ  በሕግ ቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ አጣርቶ በሰውና የሰነድ መረጃ በማደራጀት ለወረዳ አቃቤ ህግ ይልካል።

ከፖሊስ የምርመራ መዝገብ የደረሰው የወረዳው  ዓቃቤ ሕግ ተከሳሹ አስነዋሪ ድርጊት በመፈፀሙ ክስ በመመስረት ለወረዳው ፍ/ቤት ያቀርበዋል።የኮቾሬ ወረዳ ፍርድ ቤት ጉዳዩን ስከታተል ቆይተው በተከሳሽ ደሳለኝ አሰፋ ሰኔ 6/2017 ዓ/ም በዋለው ወንጀል ችሎት ተከሳሹ በ25 ዓመት ጽኑ እስራት እንድቀጣ ወስኖበታል ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር አሸናፊ ኃይሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል
18👎9😢7
የኢራኑ ጠቅላይ መሪ ካሜኔይ እንደ ሳዳም ሁሴን ተመሳሳይ እጣ ፈንታ ሊገጥማቸው እንደሚችል እስራኤል ዛተች

የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር ኢዝራኤል ካትስ እስራኤል በኢራን ላይ የምትፈጽመዉ ጥቃት እንደሚቀጥል በመግለጽ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ካሜኒ እ.ኤ.አ. በ2003 በአሜሪካ መሪነት የተደረገውን ወረራ ተከትሎ ከስልጣን የተባረሩት እና የተገደሉት የኢራቅ መሪ ሳዳም ሁሴን ጋር ተመሳሳይ የሆነ ፍጻሜ ሊጠብቃቸዉ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

"የኢራናዊው አምባገነን የጦር ወንጀሎችን መፈጸምን እና በእስራኤል ሲቪሎች ላይ ሚሳኤል ከማስወንጨፍ እንዲቆጠቡ አስጠነቅቃለሁ" ሲሉ ካትዝ መናገራቸዉን የሀገር ዉስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡ባለፈው ሳምንት እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት መፈጸም ከጀመረችነት ጊዜ አንስቶ የኢራን ሲቪሎች ተገድለዋል ።

ካሜኔ በእስራኤል መንግስት ላይ ይህንኑ መንገድ ከመረጡ የአምባገነኑን እጣ ፈንታ ቢያስታውሱ ጥሩ ነዉ ሲሉ ካትዝ ሳዳም ሆሴይንን በመጥቀስ ተናግረዋል።"እኛ ዛሬ እንቀጥላለን እንዲሁም ቴህራን ውስጥ ገዥው አካል እና ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ እርምጃ እንወስዳለን" ሲሉ ካትዝ አክለዋል:: ነዋሪዎች ቴህራን ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
👎8731😁16👍7
2025/07/13 10:29:30
Back to Top
HTML Embed Code: