Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (Beⓒk)
የ 40 አመቱ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በትናንትናው እለት የለቀቀዉ ምስዕል ነዉ👇🏼
ሮናልዶ ተክለ ሰዉነቱ ከዚህ ቀደም ባደረስናችሁ መረጃ መሰረት ዊፕ የተሰኘ ተቋም ባደረገዉ ግምገማ ባዮሎጂካል ዕድሜ 28 አመት ነው ብሎ ነበር።
ይህ ማለት ከትክክለኛው ዕድሜው በ 12 ዓመት ያነሰ ነው ማለት ነዉ። በእርግጥም የክርስቲያኖ ሰዉነት አስገራሚ ነዉ።
ሮናልዶም ይሄንን የተቋሙን ሪፖርት ሲመለከት "ይህ ማለት ተጨማሪ አስር ኳስ የመጫወቻ እድሜ አለኝ ማለት ነዉ" ብሏል።
#ዳጉ_ጆርናል_ስፖርት
@Dagujournalsport

❤65🔥19👍6🤣6😁2👌1
ፍርድ ቤት ችሎት ላይ ሀሰተኛ ምስክርነት የሰጡት ሁለት ወንድማማቾች በእስራት ተቀጡ
በምዕራብ ሀረርጌ ዞን አንጨር ወረዳ ጨለለቃ ከተማ ፍርድ ቤት ችሎት ላይ ሀሰተኛ ማስረጃ በመሆን በፍትህ አሰራር ሂደት ላይ የተዛባ ውሳኔ ለማሰጠት የሞከሩ ሁለት ወንድማማቾች በእስራት ተቀጡ።
የአንጨር ወረዳ ፍርድ ቤት እንደገለፀው
1ኛ ተከሳሽ አልዬ ሁሴን ፣ 2ኛ ተከሳሽ ሳዳም ሁሴን የተባሉ ሁለት ወንድማማቾች በወንድማቸው ሙሣ ሁሴን እና ዓቃቢህግ መካከል ባለው የወንጀል ክስ ክርክር ለወንድማቸው የመከላከያ ማስረጃ ሆነው ቀርበው በሀሰት ሲመሰክሩ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ ተጣርቶባቸው በእስራት ተቀጥተዋል።
ሁለቱ ወንድማማቾች በሀሰት ማስረጃ የፍትህ ሂደቱን ለማዛባት ባደረጉት ጥረት በወንጀል ህግ ቁጥር 453 በሀሰተኛ ምስክር እና ማስረጃ ክስ የመሰረተባቸው መሆኑን መግለጫው አመላክቷል።
በዓቃቢ ህግ የተመሰረተውን ክስ ሲከታተል የነበረው የአንጨር ወረዳ ፍርድ ቤት ሁለቱ ተከሳሽ ወንድማማቾች የዳኝነት ስርዓት በሚካሄድበት ሂደት የአንድ ወገን ለመጥቀም ሀሰተኛ ማስረጃ ሆነው በመቅረባቸው ሰኔ 4ቀን 2017 ዓ.ም እያንዳዳቸው በአንድ ዓመት ከሁለት ወር እስራት እንዲቀጡ የአንጨር ወረዳ ውስኔ መስጠቱ ብስራት ሬዲዮ ከወረዳው ያገኘው መረጃ ያመላክታል።
በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል

❤24👍4
የኒውክሌር ድርድር የሚቀጥል ከሆነ አሜሪካ የእስራኤልን ጥቃት እንድታወግዝ ኢራን ጠየቀች
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እንደተናገሩት እሁድ እለት ሊካሄድ የታቀደው የአሜሪካ-ኢራን የኒውክሌር ድርድር ከተሰረዘ በኋላ ድርድር እንዲቀጥል ከተፈለገ እስራኤል ኢራን ላይ ያደረሰችውን ጥቃት "ማውገዝ" አለባት ሲሉ ለአሜሪካ መልዕክት አስተላልፈዋል። ኢስሜል ባጋይ አሁን ባለው ሁኔታ ድርድሩን “ትርጉም የለሽ” በማለት በድጋሚ ዩናይትድ ስቴትስ በጥቃቱ “ተባባሪ” ነች ብለዋል። በተጨማሪም የኢራን ፓርላማ ከኒውክሌር መስፋፋት ስምምነት (NPT) ለመውጣት ከወሰነ "አስገዳጅ" እንደሚሆን ተናግረዋል።
ኢራን ሁል ጊዜ የኒውክሌር መርሃ ግብሯ ሰላማዊ ነው ስትል እስራኤል ግን ይህንን ውድቅ አድርጋለች። በሌላ በኩል ሁሉም ኢራናውያን "በአንድነት እንዲቆሙ፣ እንዲጸኑ እና ኢራን የምትደርስበትን የወንጀል ጥቃት እንዲጋፈጡ" የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ጥሪ አቅርበዋል። ሰኞ እለት በኢራን ፓርላማ ስብሰባ ላይ ፔዝሽኪያን እንደተናገሩት ኢራን "ዲፕሎማሲ እድል ሰጥታ ለድርድር እና ለውይይት መንገድ ከፍታለች" ብለዋል። "ጠላት ኢራንን እና ህዝቦቿን በአሸባሪነት ሊያጠፋቸው አይችልም ።ከእያንዳንዱ ኢላማ ጥቃት በኋላ ባንዲራውን የሚይዙ እና መንገዱን የሚቀጥሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ጀግኖች አሉ" ብለዋል ። ፔዝሽኪያን ሀገራቸው "የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ለመያዝ እንደማትፈልግ" ነገር ግን "ኢራን ከኒውክሌር ሃይል ህዝቦቿን በሚጠቅም ምርምር የመጠቀም መብት እንዳላት" በድጋሚ ተናግረዋል።
በሌላ መረጃ ፖላንድ በእስራኤል ከጉብኝት ላይ የሚገኙ 200 የሚጠጉ ዜጎቿን ለማስወጣት በዝግጅት ላይ ስትሆን በዮርዳኖስ ዋና ከተማ በኩል ለማለፍ አቅዳለች ሲሉ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ሄንሪካ ሞስኪካ-ዴንዲስ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት "በሚቀጥሉት ጥቂት ሰዓታት ውስጥ ዝግጁ እንደምንሆን እንገምታለን፣ ከእስራኤል የሚወጡት በቱሪስትነት የመጡትን እና ለአጭር ጊዜ የሚቆዩትን ይመለከታል ሲሉ ተደምጠዋል።
በስምኦን ደረጄ

❤41👍8😁5🙏1
በእስራኤል አራን ውጥረት ዙሪያ ትንታኔውን ከጋዜጠኛ ሚሊዮን ሙሴ እና ስምኦን ደረጄ ይመልከቱ👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/kdOk0mCXBao?si=HvJ7F3JLOhE8Eet7

❤12👎2🔥1😁1🙏1
በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ 150 ሚሊዮን ሴቶች ወሲባዊ ጥቃት ይደርስባቸዋል
👉በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ሴት ልጅ ከወንድ ቤተሰብ በሚመጣ ሀብት ማለትም ከብት እንዲሁም ወርቅ እንደየ አካባቢው የመቀየር ስርዓት መኖሩ ተነግሯል።
የሴት ልጅ ላይ የሚደርስ ጾታዊ ጥቃት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ከመሆኑ በላይ በኢትዮጵያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሴቶችን ወደ ተለያዩ ችግሮች የሚከት ጤናን የሚጎዳ እና ስር የሰደደ ችግር መሆኑ ተገልጿል ።በተለያዩ አካባቢዎች የሴት ልጅ ጥቃት ከባህል አኳያ የሚደርስ ሲሆን ከእነዚህ መካከል የልጅነት ጋብቻ ፣ የሴት ልጅ ግርዛት በተለያዩ አካባቢዎች የሚዘወተሩ እና እንደ ባህል የሚታዩ ልምዶች መሆናቸው ተጠቁሟል። በተለያዩ አካባቢዎች ሴት ልጅ ከወንድ ቤተሰብ በሚመጣ ሀብት ማለትም ከብት እንዲሁም ወርቅ እንደየ አካባቢው የመቀየር ስርዓት መኖሩ ተነግሯል።
በዚህም ሚስት ለማግኘት የሚበቃ ከብት የሌላቸው የወንድ ቤተሰቦች በአንዳንድ አካባቢዎች ትዳር ለማግኘት በመቸገራቸው ወደ ሌላ አካባቢዎች እንደሚሰደዱ በፕላን ኢትዮጵያ የኮሙኒኬሽን ክፍል ሃላፊ የሆኑት ዶክተር ምስክር ጌታሁን ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።በኢትዮጵያ ያለ እድሜ ጋብቻ ፣ጾታዊ እኩልነት፣ እንዲሁም በትዳር ውስጥ በኢኮኖሚ የሚደርሱ ጫናዎች እና ጥቃቶች ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገባ ጉዳዮች ናቸው ተብሏል። በዓለም ላይ ከሶስት ሴቶች አንዷ በህይወት ዘመኗ አካላዊ ወይም ለስነልቦናዊ ለሆነ ጾታዊ ጥቃት ትጋለጣለች ። በአፍሪካ ከስምንት ሴቶች መካከል አንዷ ከ15 ዓመት በታች እያለች እንደምትዳር ተገልጿል ። በ2016 የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው በአፍሪካ 25 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች አካላዊ ጥቃት የሚደርስባቸው ሲሆን 36 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ስነልቦናዊ ጥቃት ይደርስባቸዋል ።
በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ 150 ሚሊዮን ሴቶች ወሲባዊ ጥቃት፣ 200 ሚሊዮን የሴት ልጅ ግርዛት እና 700 ሚሊዮን ያለእድሜ ጋብቻ ይፈጸምባቸዋል ። በተጨማሪም በየቀኑ 137 ሴቶች በቅርባቸው ሰው ወይም በትዳር አጋራቸው ህይወታቸው እንደሚያልፍ ተነግሯል።በኢትዮጵያ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ስለማይደረግ እና ሴቶችም ሲደፈሩ በግዴታ እንዲያገቡ የሚደረጉበት ሁኔታ ሰፊ መሆኑ እና በተለያዩ ምክንያቶች የተረጋገጠ መረጃ ማግኘት እንዳይቻል እንቅፋት መሆኑን በፕላን ኢትዮጵያ የኮሙኒኬሽን ክፍል ሃላፊ የሆኑት ዶክተር ምስክር ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።

❤20🤬12💔4🤔1😢1
ግጭቱ በዚህ ፍጥነት ከቀጠለ መጀመሪያ መከራ የሚጋፈጡት የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ናቸው ስትል ቻይና አስታወቀች
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጉዎ ጂያኩን በቤጂንግ በተደረገ የቀጥታ ስርጭት የዜና ኮንፈረንስ ላይ እንደተናገሩት ቻይና “እስራኤል በኢራን ላይ የምታደርሰው ጥቃት በጥልቅ ያሳስባታል” ብለዋል።
"ሁለቱም ወገኖች በተቻለ ፍጥነት ውጥረቱን ለማርገብ እርምጃዎችን እንዲወስዱ እንጠይቃለን ያለው ሚኒስቴሩ ክልሉ ወደ ከፍተኛ ትርምስ እንዳይገባ እና ወደ ትክክለኛው መንገድ በውይይት እና በምክክር ለመፍታት ሁኔታዎችን እንዲፈጥሩ እንጠይቃለን" ብለዋል።
"በእስራኤል እና በኢራን መካከል ያለው ግጭት ተባብሶ ከቀጠለ አልፎ ተርፎም እየሰፋ ከሄደ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የመጀመሪያ ገፈት ቀማሽ ይሆናሉ" ሲሉም ተደምጠዋል።
በሚሊዮን ሙሴ

❤23👍10🙏2👌1💯1
Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (Beⓒk)
ቦካ ጁኒየርስ ታማኝ ታዳጊ ደጋፊዉን ማስታወቂያ አሰራ
በ2023 የተቀረጸዉና ብዙ የእግርኳስ አፍቃሪዎች የተመለከቱት አንድ ቪዲዮ ነበር። አንድ የቦካ ጁኒየርስ ታዳጊ ደጋፊ በምስዕሉ ላይ በስሜት ሲናገር ይታያል።
ይህ ታዳጊ የቦካ ጁኒየርስ ደጋፊ ቃለ መጠይቁን ካደረገ በኋላ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በመላዉ አለም ሲሰራጭ ብዙ አልቆየምም ነበር።
ታዳጊዉ ሲናገር "እኔና አባቴ የኮፓ ሊበርታዶሬስን የፍፃሜ ጨዋታ ለመመልከት ወደ ብራዚል ሪዮ ዴጄኔሮ ለመጓዝ የኔን ፕሌይስቴሽን 5 እና የአባቴን ሞተር ብስክሌት ሸጠናል" ሲል ይደመጣል።
በስሜት የሚናገረዉ ታዳጊ ቀጥሎም " ወደ ጨዋታዉ መግቢያ ቲኬት የለንም ግን በስታዲየም በራፍ ላይ ከደጋፊዎች ጋር አንድላይ ለመሆን ነዉ እንደዛ ያደረግነዉ። ይህ ቦካ ነዉ" ሲልም በስሜት ያክላል።
ታድያ በዚህ ሳምንት አዲሱን እና የቀጣይ አመቱን መለያዉን ያስተዋወቀዉ ቦካ ጁኒየርስ አዲሱን መለያ በዚህ ታዳጊ አስተዋዉቋል። በማስታወቂያዉ ላይም ይህንን ታዳጊ ደጋፊ አካትተዉታል።
በበረከት ሞገስ

❤39🔥5🥰2
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በእስራኤል እና ኢራን ጦርነት የተነሳ ከአዲስአበባ ወደ ቴላቪቭ የሚያደርገዉን በረራ አቋረጠ
አየርመንገዱ ለተፈጠረዉ ችግር ይቅርታ ጠይቆ ደምበኞቹ የቲኬት መሸጫ ቢሮዎቹን እንዲያናግሩ መክሯል። አየርመንገዱ በረራዉን መቼ እንደሚጀምር እና አዲስ መረጃዎችን እንደሚያሳዉቅ ጠቅሷል።
እስራኤል እና ኢራን መጠነ ሰፊ ጦርነት ከጀመሩ ቀናት ተቆጥረዋል።እስካሁንም በሁለቱም ወገን የሰዉ ህይወትና ንብረት ላይ ትልቅ ጉዳት ደርሷል።
በበረከት ሞገስ
#ዳጉ_ጆርናል
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በእስራኤል እና ኢራን ጦርነት የተነሳ ከአዲስአበባ ወደ ቴላቪቭ የሚያደርገዉን በረራ
ማቋረጡን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአዲስ አበባ እና በቴልአቪቭ መካከል በሁለቱም አቅጣጫ የሚደረጉ በረራዎች በአዉሮፓዉያን አቆጣጠር እስከ ሰኔ 22 ቀን 2025 ድረስ መቋረጣቸውን ባወጣዉ መግለጫ አሳዉቋል።
አየርመንገዱ ለተፈጠረዉ ችግር ይቅርታ ጠይቆ ደምበኞቹ የቲኬት መሸጫ ቢሮዎቹን እንዲያናግሩ መክሯል። አየርመንገዱ በረራዉን መቼ እንደሚጀምር እና አዲስ መረጃዎችን እንደሚያሳዉቅ ጠቅሷል።
እስራኤል እና ኢራን መጠነ ሰፊ ጦርነት ከጀመሩ ቀናት ተቆጥረዋል።እስካሁንም በሁለቱም ወገን የሰዉ ህይወትና ንብረት ላይ ትልቅ ጉዳት ደርሷል።
በበረከት ሞገስ
#ዳጉ_ጆርናል
👍31😁25❤8🔥1
በሀረሪ ክልል የወንጀል ምዝገባና የመረጃ አስተዳደር ስርዓት ስራ ማስጀመሪያ ስምምነት ሰነድ ተፈረመ
በሐረሪ ክልል የወንጀል ምዝገባና የመረጃ አስተዳደር ስርዓት ስራ ማስጀመሪያ ስምምነት ሰነድ ተፈርሟል።ስምምነቱ የተደረሰው በሐረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቢ ህግ፣በፖሊስ ኮሚሽን እና በክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ መካከል ነው።የወንጀል ምዝገባና የመረጃ አስተዳደር ስርዓት ሶፍትዌሩ በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ የበለጸገ ሲሆን በፍትህ ተቋማት ውስጥ የወንጀል ምርመራና የመረጃ አያያዝ ሂደትን በዘመናዊ መንገድ ለመምራት ያስችላል።
የሐረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቢ ህግ አቶ አዩብ አህመድ ስምምነቱ የወንጀል ምርመራ ስርዓቱን በማዘመን ዜጎች በእውነታ ላይ የተመሠረተ የፍትህ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ነው ብለዋል። የፍትህ ተቋማቱ በቀጣይ አገልግሎቱን ስራ ላይ ለማዋል አስፈላጊውን የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት ለማሟላት እቅድ ተይዞ እንደሚሰራም ገልጸዋል። የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ረምዚ ሱልጣን በበኩላቸው ስርዓቱ ፍትሐዊ አገልግሎት ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ያለውን ስራ በማገዝ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል።
በተለይ ወቅቱ የደረሰበትን የቴክኖሎጂ ውጤት መታጠቅ ከፍትህ ዘርፉ የሚጠበቅ መሆኑን አክለዋል። ኮሚሽኑ አሰራሮቹን ወደ ዲጂታል በማሳደግ ረገድ አበረታች ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል። በክልሉ የሚገኙ ተቋማትን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ዘመኑን የዋጁ እንዲሆኑ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ የገለጸዉ ደግሞ የክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ነዉ። በክልሉ ያሉ ተቋማትን የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ ወደ ስራ መገባቱንና ይህ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ይጠበቃል፡፡
የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ የምርምርና እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ተማም ስምምነቱ በቴክኖሎጂ የተመራ ዘመናዊ አሰራርን ለማላበስና ቀልጣፋ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ እንደሚረዳ ገልጸዋል። ዩኒቨርስቲው በቴክኖሎጂ ዘርፍ የተለያዩ ድጋፍና እገዛዎችን እያደረገ ይገኛል ያሉ ሲሆን በቀጣይም የተሻሉ አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ አሰራሮች እንዲኖሩ በማገዝ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።
በሰመኃር አለባቸዉ

❤15👍5
Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (Beⓒk)
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለምን የእግሩን ጥፍሮች የጥፍር ቀለም ይቀባቸዋል?
በትናንትናው እለት የአባቶች ቀንን ምክኒያት በማድረግ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከልጁ ጋር በመሆን ያጋራዉ ምስዕል ነበር። በዚህም ምስዕል ላይ የክርስቲያኖ ሮናልዶ የእግር ጥፍሮች የጥፍር ቀለም ተቀብተዉ ይታያሉ። ከዚህ ቀደምም ሮናልዶ የሴት ልጆቹ ጥፍር ቀለም ሲቀቡት በአንድ ቪዲዮ ላይ ታይቶ ነበር።
ታድያ የዳጉ ጆርናል ስፖርት አንድ ተከታያችንም ሮናልዶ ለምን የእግሩን ጥፍር ቀለም ይቀባል? ሲል በኮሜንት መስጫ ቦታችን ላይ ጠይቆ ነበር። እኛም ምክኒያቱ ምን ሊሆን ይችላል የሚለዉን ለማጣራት ሞክረናል።
እንደ ጀርመኑ ቢልድ ጋዜጣ ዘገባ ከሆነ ፣ ሮናልዶ ረጅም ሰዓታትን በሽፍን ጫማ እና በስፖርት እንቅስቃሴ የሚያሳልፍ በመሆኑ በእግር ላብ ምክኒያት ከሚመጣ የፈንገስ አይነት ራሱን ለመጠበቅ ነዉ ይለናል።
እንደ ሮናልዶ ያሉ አትሌቶች የእግር ጣት ጥፍርቸውን ቀለም መቀባት የሚመርጡበት ምክንያት ላብ ያደረባቸውን ጫማዎችን አድርገዉ ሰዓታትን ከቆዩ በኋላ በፈንገስ ኢንፌክሽን እንዳይያዙ ለመከላከል ነው።
የጥፍር ቀለም ባክቴሪያ ወደ ቆዳ ውስጥ እንዳይገባ የሚያግድ መከላከያ ሽፋን እንደሚጨምር ይታመናል።
በተጨማሪም ቀለሙ በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ወቅት የጥፍር መሰንጠቅ ወይም መከፈት እንደሚከላከል ይታሰባል። እንደ ቢልድ ዘገባ ከሆነ ሮናልዶ በነዚህ ምክኒያቶች የእግር ጥፍሩን ቀለም ይቀባል።

🔥25❤23😁12👍2🥰1
ኢራን ከአርብ ጀምሮ በእስራኤል ላይ በወሰደችው ጥቃት 24 እስራኤላውያን ተገደሉ
በእስራኤል እና በኢራን መካከል ግጭት ከጀመረ ወዲህ በእስራኤል ወገን 24 ሰዎች ሲገደሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቆስለዋል። በኢራን ደግሞ 224 ሰዎች ተገድለዋል። የቴህራን ነዋሪዎች ደህንነትን ፍለጋ ዋና ከተማዋን ለመሸሽ እየሞከሩ መሆኑም ተሰምቷል።
እስራኤል አንድ ሶስተኛውን የኢራን ሚሳኤል ማስወንጨፊያ ማውደሟን ተናግራለች። የእስራኤል ጦር ከ120 በላይ የሚሳኤል ማስወንጨፊያዎችን አውድማለች። ይህም ኢራን ካላህ አጠቃላይ ቁጥር አንድ ሶስተኛውን የሚያህለውን ሲሆን የመጀመሪያው ጥቃቱን ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ላይ ደርሷል።የአየር ሃይሉ እሁድ ምሽት ብቻ ከ20 በላይ አውድሟል። እስራኤል በማዕከላዊ ኢራን እስፋሃን ውስጥ ወደ 100 የሚጠጉ ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በማድረስ 50 የሚጠጉ ተዋጊ ጄቶች የሚሳኤል ማከማቻ ስፍራዎችን፣ ማስወንጨፊያዎችን እና የማዘዣ ማዕከሎችን መታለች።
ከኢራን አብዮት ጠባቂዎች ኮርፖሬሽን (IRGC) ጋር ግንኙነት ያለው የታስኒም የዜና ወኪል እስራኤል ከኢራቅ ጋር በሚያዋስነው ድንበር አቅራቢያ በሚገኘው ኢላም ግዛት ያለውን የሙሲያን ማዘጋጃ ቤት የእሳት አደጋ መከላከያ ክፍል ህንፃ ላይ አሰቃቂ ጥቃት ፈፅማለች ብሏል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የፋርስ የዜና ወኪል እንዲሁም ከኢራን አብዮታዊ ዘብ ጋር ግንኙነት ያለው አንድ ሆስፒታል መጎዳቱን ዘግቧል።

❤50🕊9😁4👍3👎2
የኢራን መንግስታዊ ቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት ላይ እያለ በእስራኤል በተፈፀመ ጥቃት በርካቶች ተገደሉ
የኢራን መንግስታዊ ቲቪ እንዳስታወቀው ቴህራን በሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤቱ እስራኤል በፈጸመችው ጥቃት "ቁጥራቸው በውል" ያልተገለፁ ሰራተኞቹ መገደላቸውን አስታውቋል። የስርጭት ዘጋቢ "ጥቃቱ ከመድረሱ በፊት እስከ መጨረሻው ጊዜ ድረስ እየሰሩ ነበር" ሲሉ የስርጭቱ ኃላፊ ፔይማን ጀቤሊ በማንሳት በመንግስታዊው ቲቪ ላይ በደም የተበከለ ወረቀት አሳይቷል።
የመንግስት ቴሌቪዥን እና ሰራተኞቹ "እስከ መጨረሻው ሲሰሩ ነበር " ብለዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ የመንግስት ቲቪ ሰራተኞች በሚሰሩበት አነስተኛ መንደር ውስጥ ጥቃቱ ደርሷል። እስራኤል ቀደም ሲል የቴህራን ዲስትሪክት 3 ክፍል ከጥቃቱ በፊት ለቀው እንዲወጡ የሚነግራትን ካርታ አሳትማ ነበር፤ የመንግስት ቲቪም እዚህ ካርታ ውስጥ ተካቷል።
የእስራኤል መከላከያ ሚንስትር የኢራን የመንግስት ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ላይ ጥቃት ማድረሱን አረጋግጧል። ሚኒስትሩ ኢዝራኤል ካትስ በሰጡት መግለጫ ጥቃቱ የተፈፀመው “በአካባቢው የሚኖሩ ነዋሪዎችን መጠነ ሰፊ መፈናቀልን ተከትሎ ነው” ያሉ ሲሆን እስራኤል “የኢራኑን አምባገነን ባለበት ትመታለች” ብለዋል።

👎65❤32👍7👏4🤔4🕊4
አቋማሪ ድርጅቶች ፊታቸውን ወደደቡብ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ማድረጋቸው ተነገረ
በአዲስ አበባና በተለያዩ አካባቢዎች ቢሯቸው የተዘጋባቸው የስፖርት ውርርድ አቋማሪ ድርጅቶች ፊታቸውን ወደ ደቡብ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ማድረጋቸውን የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት አስታውቋል።
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በውርርድ አጫዋቾች ፈቀድ አሰጣጥና ቁጥጥርን በተመለከተ በቀረበለት የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት ላይ ውይይት አድርጓል።
በወቅቱ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቤዛ ግርማ፤ በአዲስ አበባ፤ በድሬዳዋ፤ በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች፣ በትግራይና በአማራ ክልሎች አቋማሪ ድርጅቶች ቢሮ መዘጋቱን መናገራቸውን ዳጉ ጆርናል ከኢቢሲ ዘገባ ተመልክቷል።
አቋማሪ ድርጅቶች አሁን ላይ በደቡብ የኢትዮጵያ አካባቢዎች እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኝ እና በኦንላይንም በስፋት እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ባለፉት 11 ወራት ከአወራራጆቹ የተገኘው የኮሚሽን ገቢ 2.2 ቢሊዮን ብር መድረሱንም ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ አስታውቀዋል።

😁43❤22👎7😢3🔥1
የእናቴን ድርሻ የጫት መሬት ሊሰጠኝ ፍቃደኛ አይደለም በማለት አባቱን በስለት ወግቶ የገደለው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ
በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ግራዋ ወረዳ ጎሮ አካባቢ ተወልዶ ያደገው ኢብራሂም ሀሰን ለቤተሰቡ ብቸኛ ልጅ ቢሆንም ወላጅ እናቱ በልጅነቱ ህይወታቸው አልፎ አባቱ ሌላ ትዳር መስርተው አክስቱ ጋር እንዳደገ ተገልጿል።
ወጣቱ ጎጆ መውጫ የእናቴን ድርሻ የጫት መሬት ይሰጠኝ ብሎ አባቱን ይጠይቃል። በአካባቢው አንድ ትዳር ሊመሰርት ያሰበ ወጣት ለሚያገባት ልጅ የሚቆጥረው ሀብት እና ንብረት መሬት መገለፅ የግድ በመሆኑ ለአባቱ ድርሻዬን የሚል ጥያቄ ያቀርባል።አባትም የተጠየቁትን የጎጆ መውጫ ጥያቄ ለመቀበል ያንገራግራሉ፣ በዚህ ጊዜ ኢብራሂም የሰርጉ ጊዜ መድረስና የሰርጉ ቀን ለጎጆ መውጫ የሚያቀርበው መተዳደርያ የእናቱ ድርሻ የሆነው የጫት መሬት ነበረና ያንን አባት ለመስጠት ፍቃደኛ አለመሆናቸው ቂም እንዲቋጥር እንዳደረገው በሰጠው ቃል ማረጋገጡን የዞኑ ፖሊስ ዋና መምሪያ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ካስዬ አበበ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
ተከሳሹ መጋቢት 17 ቀን 2017 ዓ.ም ከለሊቱ አስራ አንድ ሰዓት ተኩል ላይ የአባቱን ግቢ በር ከፍቶ በመግባት አባቱን በተኙበት የተለያዩ የሰውነት ክፍሎቻቸውን በያዘው ስለታም መጥረቢያ በመምታት ሕይወታቸው እንዲያልፍ አድርጎ ይሰወራል።የአባት መኝታ ለብቻ በተሰራ ቤት በመሆኑ ጠዋት የመነሳት ልማድ የነበራቸው አባት በዚያ ዕለት አርፍደው መዋላቸው ያጠራጠራቸው ቤተሰብ ወደ መኝታ ቤታቸው ሲደርሱ የሚተኙበት ቤት ተከፍቶ አባትም የተለያየ ቦታ ተመተው ህይወታቸው ማለፉን ሲያዩ የድረሱልኝ ጩኸት በማሰማት የአካቢው ሰው እንዲሰባሰብ አደረጉ።ፖሊስም ከአካባቢው ሰው በደረሰው መረጃ በስፍራው በመገኘት አስክሬኑን በማስነሳት ለምርመራ ወደ ሆስፒታል ልኳል።
ፖሊስ ከአካባቢ ሰዎች እና ቤተሰብ የተለያዩ መረጃዎችን በማሰባሰብ ተጠርጣሪውን ኢብራሂም በቁጥጥር ለማዋል ክትትል ይጀምራል። በዚህም ከአራት ቀን በኋላ ተፈላጊው ኢብራሂም በሱማሌ በኩል ከሀገር ሊወጣ ሲል በቁጥጥር ስር ውሎ የድርጊቱን አፈፃፀምና ምክንያት በመናገር ለፖሊስ ቃሉን ይሰጣል። ፖሊስ አስፈላጊውን የምርመራ ሂደት አጠናቆ የምርመራ መዝገቡን ለዓቃቢ ሕግ ይልካል። ዓቃቢ ህግ በከባድ ሰው መግደል ወንጀል ክስ ይመሰርታል።
የተመሰረተውን ክስ ሲከታተል የቆየው የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰሞኑን በዋለው ችሎት ተከሳሽ ኢብራሂም ሀሰን ሰውን ለመግደል፣ አስቦ፣ አቅዶ ተዘጋጅቶ ወላጅ አባቱን ድምፅ በሌለው ስለታም መሳሪያ መግደሉ ሙሉ በሙሉ በማስረጃ በመረጋገጡ ተከሳሹ ጨካኝ፣ አደገኛ እና ነውረኛ በመሆኑ በ 20 አመት እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑን ምክትል ኢንስፔክተር ካስዬ አበበ ጨምረዉ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

❤29🤔17👎8💔4👍3😭2