Telegram Web Link
በደራሲ ሚስጥረ አደራው የተፃፈው "እኔ" የተሰኘው መፅሐፍ ሰኔ 7  ቀን 2017 ዓ.ም ተመርቆ ለንባብ በቃ

ከዚህ ቀደም የተለያዩ ሃሳቦቿንና ስራዎቿን በተለይም የትርጉም ስራዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮቿ  በማቅረብ የምትታወቀው ሚስጥረ አደራው የመጀመሪያ ስራዋ የሆነውን "እኔ" የተሰኘ መፅሃፍ ለንባብ አብቅታለች።

ሚስጥረ በብዙዎች ዘንድ የፐርሺያውን ገጣሚ የሩሚን ስራዎች ወደ አማርኛ በመቅዳትና በማቅረብ በስፋት የምትታወቅ ሲሆን አሁን የተለያዩ ታሪኮችን የያዘ መፅሃፍ ነው ይዛ የመጣችው።

"እኔ" የተሰኘው መፅሐፍ፤ ፀሐፊዋ በተለያዩ ጊዜዎች ማህበራዊና መሰል ጉዳዮች የሚፈጥሯቸውን ሸክሞችና ጭቆናዎች በማጠየቅ የራስን ነፃነት ለመፈለግ የሚደረግን በጥያቄና መልስ የተሞላን የህይወት ትግልን የምታሳይበት ነው።

በዋልያ መፅሃፍት በተካሄደው የምረቃ ስነ ስርዓት ላይም ጋዜጠኛ የኋላሸት ዘሪሁን፣ አርታኢና ተርጓሚ ቴዎድሮስ አጥላው፣ አርቲስት አዳነች ወልደ ገብርኤል፣ ደራሲ ዘቢብ መልኬ፣ የስነ ልቦና እና የጤና ባለሙያ ሰላማዊት ሞሲሳን ጨምሮ ተጋባዥ እንግዶች ዲስኩርና ስለ መፅሃፉ ምልከታቸውን ተናግረዋል።

ደራሲዋ ሚስጥረ አደራው በ Health Informatics ዲግሪ እንዲሁም በ Health Information Data analytics የማስተርስ ዲግሪዋን በመያዝ በህክምና ዘርፍ ውስጥ በመስራት ላይ ትገኛለች።ከዛሬ ጀምሮ ለንባብ የበቃው "እኔ" መፅሃፍ 179 ገፆች አሉት።

#ዳጉ_ጆርናል
24👍9
ጄናሮ ጋቱሶ የጣሊያን ወንዶች ብሄራዊ እግርኳስ ቡድኑ አሰልጣኝ በመሆን ተሹሟል ✍🏻 🇮🇹

#ዳጉ_ጆርናል
🔥20👍75😁5
Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (Beⓒk)
መኸዲ ታሬሚ በእስራኤል እና ኢራን ጦርነት የተነሳ ለክለቦች የአለም ዋንጫ ኢንተር ሚላንን መቀላቀል አልቻለም

የኢንተር ሚላኑ ኢራናዊ አጥቂ መኸዲ ታሬሚ በእስራኤል እና ኢራን ጦርነት ለክለቦች የአለም ዋንጫ ኢንተርን መቀላቀል አልቻለም ተብሏል።

ታሬሚ ማክሰኞ እለት ኢራን ደቡብ ኮሪያን አስተናግዳ 3 ለ 0 ባሸነፈችበት ጨዋታ የሀገሩን መለያ አለብሶ ግብም አስቆጥሮ ነበር።

ታድያ ቅዳሜ እለት በሎሳንጀለስ የሚገኘዉን የኢንተር ሚላንን ቡድን እንዲቀላቀል ፕሮግራም ተይዞለት የነበረ ቢሆንም ከኢራን የሚነሱ በረራዎች ለደህንነት ሲባል በመቋረጣቸው ከኢራን መዉጣት አልቻለም ተብሏል።

እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት የከፈተችው ሀሙስ እለት ሲሆን ከሀሙስ ጀምሮ የኢራን የአየር ክልል ዝግ ሆኗል ተብሏል።

እስራኤል እና ኢራን ከቃላት መወራወር ወደ ሮኬት መወራወር ከዚህ ቀደም በቅርቡ በአንድ አጋጣሚ ገብተዉ የነበረ ቢሆንም የሮኬት ተኩሱን አቁመዉት ነበር። ሆኖም እስራኤል የተጠናከረ ጥቃት ከከፈተች በኋላ ኢራንም ሮኬት በቴላቪቭ ላይ ስታዘንብ አድራለች።

በሁለቱ ሀገራት ጦርነት በሰዉ ህይወት እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ መሆኑን እየተመለከትን ነዉ።

በበረከት ሞገስ

ለስፖርታዊ መረጃዎችን ይፋዊ የዳጉ ጆርናል ስፖርት ቻናል https://www.tg-me.com/Dagujournalsport ን ይቀላቀሉ

#ዳጉ_ጆርናል_ስፖርት
42😭6👍4🔥3
Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (....)
የኦክላንድ ሲቲ እና ባየር ሙኒክ የደረጃ ልዩነት..

- አንዳንድ የኦክላንድ ሲቲ ተጫዋቾች በመደበኛ ስራቸው የተነሳ ሙሉ ቡድኑ ወደ አሜሪካ አልተጓዘም። የቡድኑ አባላት የድርጅት ሥራ አስኪያጅ፣ መምህር፣ ፀጉር አስተካካይ፣ የሪል ስቴት ተወካይ እና ሌሎችም ከተለያዩ ሙያዎች የተውጣጡ ናቸው።

☑️ የኦክላንድ ሲቲ ከፍተኛ ተከፋይ ተጫዋች የሃሪ ኬንን ሳምንታዊ ደሞዝ ለማግኘት ለ 107 አመታት መጫወት ይኖርበታል!

☑️ 💵 የኦክላንድ ሲቲ አማተር ተጫዋቾች በሳምንት 90 ዶላር የሚከፈል ደሞዝ አላቸው! 🇳🇿

☑️ 💵 የባየር ሙኒኩ ተጫዋች ሃሪ ኬን በሳምንት 503,484 ዶላር ያገኛል! 🇩🇪

☑️ 🇳🇿 ኦፕታ ደረጃ ከሰጣቸው ከ13,000 በላይ የሀገር ውስጥ የእግር ኳስ ቡድኖች 5,074 ደረጃ ላይ ኦክላንድ ሲቲ ተቀመጧል።

☑️ 🇪🇸 በስፔን እግር ኳስ እርከን 6ኛ ደረጃ ላይ የሚጫወተው ካስቴላ ሲኤፍ ከነሱ ደረጃ በላይ ተቀምጧል ይህም የኦክላንድ ሲቲ ደረጃ ያሳያል።

ለስፖርታዊ መረጃዎችን ይፋዊ የዳጉ ጆርናል ስፖርት ቻናል https://www.tg-me.com/Dagujournalsport ን ይቀላቀሉ

#ዳጉ_ጆርናል_ስፖርት
30😁16
#Sleeping_Prince በድንገት ነቁ በሚል የሚሰራጨው መረጃ የሳዑዲ መንግስት ያላረጋገጠው ሀሰተኛ ዜና ነው።

#ዳጉ_ጆርናል
🤣35😢13🤔97😁2
ኢራን በእስራኤል የወደብ ከተማ ሀይፋ እና በመዲናዋ ቴላቪቭ በፈፀመችው ጥቃት ሶስት ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች ቆሰሉ

የኢራን ሚሳኤሎች የእስራኤልን ቴል አቪቭ እና የወደብ ከተማዋን ሀይፋን ዛሬ ሰኞ በመምታቱ ቤቶችን አውድሟል።  የአለም መሪዎች በዚህ ሳምንት በቡድን 7 ስብሰባ ላይ በሁለቱ የቀድሞ ጠላት ሀገራት መካከል የሚካሄደው ጦርነት ወደ ሰፊ ቀጠናዊ ግጭት ሊመራ ይችላል የሚል ስጋት አድሮባቸዋል። የእስራኤል ሚዲያ እንደዘገበው በሀገሪቱ ላይ በተፈፀመው ጥቃት ሶስት ሰዎች ሲገደሉ በደርዘን የሚቆጠሩ ደግሞ ቆስለዋል ብለዋል ።

በሃይፋ የወደብ ከተማ 30 ያህል ሰዎች ቆስለዋል ሲሉ የአደጋ ጊዜ ባለስልጣናት ተናግረዋል። በደርዘን የሚቆጠሩ የአደጋ ጊዜ የመጀመሪያ ምላሽ ሰጪዎች ወደ ጥቃት ዞኖች ሲጣደፉ የሚያሳይ ምስሎች ተሰራጭቱምተዋል። በወደቡ አቅራቢያ በሚገኝ የኃይል ማመንጫ ላይ የእሳት ቃጠሎ ታይቷል ሲል መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በቴላቪቭ ላይ በርካታ ሚሳኤሎች እና ፍንዳታዎች የነበሩ ሲሆን እየሩሳሌም ላይ ተመሳሳይ ጥቃት እንደነበር የቪዲዮ ምስል አመላክቷል።

በከተማዋ ከሚገኝ የአሜሪካ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ጥቂት መቶ ሜትሮች ርቆ የሆቴሎችን እና ሌሎች በአቅራቢያ ያሉ ቤቶችን መስኮቶችን የሰባበረ ጥቃት ደርሴክ። በቴል አቪቭ ሰፈር ውስጥ የሚገኙ በርካታ የመኖሪያ ሕንፃዎች ወድመዋል።

በኢራን የሟቾች ቁጥር 224 ደርሷል፤ ከነዚህም መካከል 70 ሴቶች እና ህጻናት ይገኙበታል። የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ጓድ (IRGC) የስለላ ሃላፊ እና ሌሎች ሁለት ጄኔራሎች እሁድ ዕለት በእስራኤል ጥቃት ተገድለዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሁለቱ ወገኖች ስምምነት ማድረግ አለባቸው ሲሉ ጥሪ በማቅረብ ስብሰባዎች እየተደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል። የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ “እዚህ ያለውን ጉዳይ ማባባስ ሳይሆን ኢራን የኒውክሌር አቅሟን እንዳታዳብር ማስቆም ነው” ብለዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
104👎10🕊4🤩3🤝3👍2😁2
አስከሬን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ መኪና ተገልብጦ የ5 ሰዎች ሕይወት አለፈ

በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በሰቆጣ ወረዳ 07 ቀበሌ ዳብል ማሪያም ዲብር ሳይል አፈራ ጎጥ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ።

የሰሌዳ ቁጥር አማ 30336 ኮድ 3 የሆነ ሚኒባስ ከደሴ ወደ ሰቆጣ አስከሬን ጭኖ ሲመጣ በደረሰ ድንገተኛ የትራፊክ አደጋ 3 ወንድ 2 ሴት በድምሩ የ5ሰዎች ሕይወት አልፏል።

በተከሰተው የትራፊክ አደጋ 7 ወንድ 4 ሴት ቀላልና ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን በሰቆጣ ፖሊስ ጽ/ቤት የመንገድ ደህንነት ትራፊክ ክፍል ሃላፊ ኢንስፔክተር ሲሳይ አበራው ገልጸዋል።

#ዳጉ_ጆርናል
😢43😭3117😁7💔7🤯1
5
መርማሪዎች ከተከሰከሰው የኤር ህንድ የአብራሪዎች ክፍል ውስጥ የድምጽ ቅጂ አገኙ

መርማሪዎች ከተከሰከሰው አውሮፕላን የበረራ ክፍል ውስጥ የድምጽ መቅጃውን (ሲቪአር) ከኤር ህንድ አውሮፕላን ማግኘታቸውን ገልፀዋክ። ወደ ለንደን ሲያቀና የነበረው ኤር ህንድ አይሮፕላን ቦይንግ 787-8 ድሪምላይነር አውሮፕላን ከህንድ ምዕራባዊ አህመዳባድ ከተማ ሃሙስ እለት ሲነሳ ተከስክሷል። ቢያንስ 270 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን አብዛኛዎቹ ተሳፋሪዎች ናቸው። ሲቪአር የአብራሪዎቹን ንግግር፣ ማንቂያ መልዕክት እና ድምፆችን ጨምሮ ከኮክፒት ክፍል ይይዛል።

እንደ ከፍታ፣ ፍጥነት እና ሞተር አፈጻጸም ያሉ ወሳኝ የበረራ መለኪያዎችን የሚመዘግብ የበረራ መረጃ መቅጃ (ኤፍዲአር) አርብ እለት ከፍርስራሹ ውስጥ ተገኝቷል።ሁለቱም CVR እና FDR በጋራ የአውሮፕላን "ጥቁር ሳጥን" በመባል የሚታወቁ ናቸው። የበረራውን የመጨረሻ ጊዜዎች እንደገና ለማጤን እና የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ ባለሙያዎችን በመርዳት በአየር አደጋ ምርመራዎች ውስጥ ወሳኝ መሳሪያ ነው። ጥቁር ሳጥኑ፣ ስሙ ባይገልፀውም፣ ከአደጋ በኋላ ሁለት ብሩህ ብርቱካናማ መሳሪያዎች በውስጡ ይዟል።አንዱ ሲቪአር ሲሆን ሌላው ኤፍዲአር  ይባላሉ። ሁለቱ እነዚህ መሳሪያዎች ከአደጋ በኃካ ለትንተና የተነደፉ ናቸው።

የህንድ መገናኛ ብዙሃን ምንጮችን ጠቅሰው እንደዘገቡት የቦይንግ እና የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር እንዲሁን የአሜሪካ የአቪዬሽን ደህንነት ኤጀንሲ ባለስልጣናትም የአደጋውን ቦታ ጎብኝተዋል። በተናጥል በህንድ መንግስት የተቋቋመው ከፍተኛ ኮሚቴ የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ የሚያስችል ከፍተኛ ኮሚቴ ሰኞ የመጀመሪያውን ስብሰባ አድርጓል። ኮሚቴው በሦስት ወራት ጊዜ ውስጥ የመጀመሪያ ሪፖርት እንደሚያቀርብ ኦል ህንድ ራዲዮ ዘግቧል።ወደፊት ተመሳሳይ አደጋዎችን ለመከላከል የሚረዱ አዳዲስ መደበኛ የአሠራር ሂደቶችን እንደሚያቀርብ ገልጿል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
23🙏3👏2🔥1
2025/07/14 14:09:42
Back to Top
HTML Embed Code: