የኢራን ጠቅላይ መሪ ፑቲን ከአሜሪካ ጥቃት በኋላ የበለጠ ግፊት እንዲያደርጉ ጠየቁ
የኢራን ጠቅላይ መሪ እ.ኤ.አ. ከ1979 አብዮት በኃላ በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ከደረሰው ትልቁ የአሜሪካ ጦር እርምጃ ተከትሎ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን ሩሲያ ተጨማሪ እርዳታ ለኢራን እንድታደርግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸውን ሰኞ ዕለት ወደ ሞስኮ ልከዋል። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና እስራኤል ጠቅላይ መሪ አያቶላ አሊ ካሚኒን ስለመግደል እና የስርዓት ለውጥን በተመለከተ በአደባባይ መናገራቸው ሩሲያ መካከለኛው ምስራቅን ወደ ገደል ሊያስገባ ይችላል የሚል ስጋታቸውን ገልፀዋል።
ፑቲን የእስራኤልን ጥቃት ቢያወግዙም፣ አሜሪካ በኢራን የኒውክሌር ጣቢያዎች ላይ ስላደረሰችው ጥቃት እስካሁን አስተያየት አልሰጡም። ባለፈው ሳምንት መረጋጋት እንዲሰፍን ጠይቀው የነበረ ሲሆን የሞስኮን ሚና በኒውክሌር መርሃ ግብሩ ላይ አስታራቂ አድርገው አቅርበዋክ። ከፍተኛ የመረጃ ምንጭ ለሮይተርስ እንደገለፀው የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራክቺ ከካሜኒ የተላከላቸውን ደብዳቤ ለፑቲን በማድረስ የፑቲንን ድጋፍ የሚሹ ናቸው ብለዋል። ቴህራን ምን ዓይነህ እርዳታ እንደምትፈልግ ግን ምንጮቹ አላብራሩም።
ክሬምሊን ፑቲን የኢራንን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር እንደሚቀበሉ ቢናገሩም በምን ጉዳይ ላይ እንደሚወያዩ ግን አላሳወቀም። የኢራን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አግራቺን ጠቅሶ ታስ የዜና ወኪል እንደዘገበው ኢራን እና ሩሲያ አሁን ባለው የመካከለኛው ምስራቅ መባባስ ላይ አቋማቸውን አንድ ለማድረግ እየሰሩ ነው። ፑቲን በዩናይትድ ስቴትስ እና በኢራን መካከል ለማደራደር ደጋግመው ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፥ ኢራን የሲቪል ኒውክሌር ኢነርጂ ተጠቃሚነቷን ቀጣይነት ባለው መልኩ በማረጋገጥ ሞስኮ ውዝግብ መፍታት ላይ ሃሳብ ማቅረቧ ይታወሳል።
በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የነዳጅ እጥረት የፈጠሩ ማደያዎች ታሽገዋል
ሰኔ 15 ቀን 2017 ዓ.ም. በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ህብረተሰቡን ሲያማርሩ የነበሩ የነዳጅ ማደያዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል! የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ንግድ ጽ/ቤት ኃላፊ ወይዘሮ አስቴር ደሳለኝ እንዳስታወቁት፣ በቂርቆስ ነዳጅ በመደበቅ እጥረት እንደተፈጠረ በማስመሰል የንግድ አሻጥር ሲፈጽሙ የነበሩ ማደያዎች ታሽገዋል።
የታሸጉት ማደያዎች እና የተፈጸመው ጥፋት፦
1. ባምቢስ ኖክ ነዳጅ ማደያ (ወረዳ 01)፦ ከ12 ሺህ ሊትር በላይ ቤንዚንና ናፍጣ እያለ "አይሰራም" በማለት ለህገ ወጥ ንግድ አመቻችቷል።
2. OLA ነዳጅ ማደያ (ደምበል ፊት ለፊት)፦ ነዳጅ እያለ "የለም" በማለት እና ሰራተኛ ባለማስገባት ሰልፍ እንዲበዛ በማድረግ የንግድ አሻጥር ፈጽሟል።
ወይዘሮ አስቴር አክለውም፣ የእነዚህ ማደያዎች ስራ አስኪያጆች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ መሆኑን ገልጸዋል።
ህብረተሰቡ የነዳጅ አቅርቦት እጥረት እንደሌለ በመረዳት፣ "ናፍጣም ሆነ ቤንዚን የለም" በማለት አላስፈላጊ የንግድ አሻጥር የሚፈጥሩ የማደያ ባለቤቶች ሲኖሩ፣ በነፃ የስልክ መስመር 8588 እንዲሁም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ንግድ ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ጥቆማ እንዲሰጥ ወይዘሮ አስቴር ደሳለኝ ጥሪ አስተላልፈዋል።
መረጃው የቂርቆስ ክፍል ከተማ ነው

በአሰላ ከተማ የመስረታዊ ሸቀጦች ዋጋ ከፍተኛ የሆነ ጭማሪ ማሳየቱ ተነገረ
👉 ከዚህ ቀደም 900 ብር ሲሸጥ የነበረ አንድ ኪሎ ቡና በአሁኑ ሰዓት እስከ 1300 ብር እየተሸጠ ይገኛል
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመዲናችን አዲስ አበባ ጨምሮ በተለያዩ የክልል ከተሞች የመሰረታዊ ሸቀጦች ዋጋ ከፍተኛ ጭማሬ እያሳየ መሆኑ ተገልፆል። በዚህ ጉዳይ ብስራት የአሰላ ከተማ ነዋሪዎችን ያነጋገረ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አሳሳቢና ዝቅተኛ ኑሮ ላላቸው ሰዎች ብም ሳይሆን መካከለኛ ገቢ አለው ለሚባለው ማህበረሰብም ከባድ በሚባል ደረጃ በተለያዩና በዕለት ተዕለት ውሎ በጥቅም ላይ የሚውሉ ሸቀጦች ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ መስተዋሉ ተገልጿል።
ብስራት ያነጋገራቸው የአሰላ ከተማ ነዋሪዎች እንደጸናገሩት ከሆነም እስከ ቅርብ ጊዜ ከ 500 እስከ 700 ብር ሲሸጥ የነበረ አንድ ኪሎ በርበሬ አሁን እስከ 1200 ብር እየተሸጠ ነው ያሉ ሲሆን፣ በተመሳሳይ ከዚህ ቀደም እስከ 900 ብር ድረስ ሲሸጥ የነበረ አንድ ኪሎ ቡና አሁን ላይ ከ1200 እስከ 1300 ብር ድረስ እየተሸጠ መሆኑን አንስተዋል።
ከዚህ ቀደም ከ6ሺ እስከ 8ሺ ብር ሲሸጥ የነበረ 100 ኪሎግራም ገብስ አሁን ላይ እስከ 12 ሺ ብር ድረስ እየተጠየቀ መሆኑ ጣብያችን ያነጋገራቸው የአሰላ ከተማ ነዋሪዎች የገለፁ ሲሆን በተጨማሪም ከዚህ ቀደም 17 ብር ይሸጥ የነበረ አንድ እንቁላል አሁን ላይ በ23 ብር እንደሚሸጥ ገልፀዋል።
የዋጋ ጭማሬው ምክንያት ለማወቅ በተደረገ ጥረት ጣቢያችን በከተማይቱ ያሉ ነጋዴዎችንን ያነጋገረ ሲሆን ከጅምላ አከፋፋዮች እቃ ለማምጣት በሚሄዱበት ወቅት የዋጋ ጭማሬ ከመመልከታቸው ውጭ የዋጋ ጭማሬው ምክንያት ይህ ነው ብለው ለመግለፅ እንደማችይሉና እነሱም ከአከፋፋዮች የሚያመጡበት ዋጋ በመጨመሩ ምክንያት ዋጋ ለመጨመር እንደተገደዱ ነግረውናል።
ከአሰላ ከተማ በተጨማሪ በአዲስ አበባ ከተማም በቡና ዋጋ ላይ ጭማሪ መኖሩ የገበያ ዉሎ የሚያሳይ ሲሆን በአንድ አንድ አከባቢዎች አንድ ኪሎ ቡና እስከ 1200 ብር ድረስ እየተሸጠ መሆኑን ታዝበናል።
በሰብል አበበ

ከእስር ለማምለጥ ሞክሮ በፍሳሽ ማስወገጃ ውስጥ ተቀርቅሮ የቀረው ሰው ግርምትን ፈጥሯል
ብራዚል ውስጥ ያጋጠመው ክስተት ከእስር ለማምለጥ ሲል በፎሳሽ ማስወገጃ ውስጥ ለውስጥ እያተጓዘ በነበረበት ሰዓት ተቀርቅሮ የቀረው ሰው ማምለጡ ቀርቶብኝ አዱኑኝ ያለ ስለመሆኑ ተሰምቷል።
የ32 ዓመቱ ግለሰብ አለን ሊአንዶሮ ዳ ሲልቫ በመባል የሚታወቅ ሲሆን ከሪዮ ባርናኮ ማረምያ ቤት ለማምለጥ በሞከረበት ሰዓት በፍሳሽ ማስወገጃ ውስጥ ራቆቱን ተቀርቅሮ መገኘቱ ተነግሯል። ታድያ ወጣቱ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ሊያድኑት በሄዱበት ሰዓት የሚታዩ ቁስሎች እንደነበሩት የገለፁ ሲሆን ግለሰቦ ለማምለጥ ባደረገው ሙከራ ጉዳት ማስተናገዱም ተገልፆል።
የእስር ቤቱ ሀላፊዎች ከኩነቱ በኃላ በሰጡት መግለጫ የማረምያ ቤቱ ጠባቂዎች በሌላ ስራ ተወጥረው በነበሩበት ወቅት የማምለጥ ሙከራ መፈፀሙን የገለፁ ሲሆን ነገር ግን ሊያመልጥ የሞከረበት የፍሳሽ ማስወገጃ ቀዳዳ ስፋት በልክ አለማወቁ እንዲያዝ እንዳደረገው ተገልፆል።
አለን የተባለው እስረኛ ምንም እንኳ ለህይወቱ አስጊ በነበረ ሆኔታ ውስጥ ገብቶ የነበረ ቢሆንም በተቀናጀ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጥረት ተጨማሪ ጉዳት ሳያስተናግድ ሊያወጡት መቻላቸው ተነግሯል። በዚህም የመጀመርያ እርዳታ ተደርጎለት ወድያዉኑ ወደ እስር መመለሱ መረጃው አሳይቷል።
በሚሊዮን ሙሴ

በአፋር ክልል ባለፉት ሰባት ዓመታት ከ300 በላይ ፋብሪካዎች መገንባታቸው ተገለፀ
በአፋር ክልል ባለፉት ሰባት ዓመታት ውስጥ አነስተኛ፣ መካከለኛ እና ከፍተኛ ከ300 በላይ አምራች ፋብሪካዎች መገንባታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ፡፡
የአፋር ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ መሐመድ ዓሊ ቢኢዶ እንደገለጹት፤ ባለፉት ሰባት ዓመታት የአፋር ክልል ህዝብ በኢኮኖሚ እኩል ተጠቃሚ መሆን መቻሉ ተገልጿል፡፡
እንደ አቶ መሐመድ አሊ ገለጻ በክልሉ ባለፉት ሰባት ዓመታት ውስጥ አነስተኛ፣ መካከለኛ እና ከፍተኛ ከ300 በላይ አምራች ፋብሪካዎችና አንድ ኢንደስትሪ ፓርክ ተገንብተው ሥራ መጀመሩ ተገልጿል።
ከእነዚህ ከተገነቡ ፋብሪካዎች መካከል የጨውና የብሮሚን ማምረቻ ፋብሪካዎች ተጠቃሽ ሲሆኑ፤ አፍዴራ ላይ ብቻ ከ20 በላይ ፋብሪካዎች መገንባታቻውን ገልጸዋል፡፡
ይህም ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል የፈጠረ፣ የስራ ባህልን ያጠናከረ እንዲሁም እንደ ትምህርት ቤትና ንፁሕ የመጠጥ ውሃ የመሳሰሉ ፕሮጀክቶችን በመገንባት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ ያስቻለ መሆኑን አብራርተዋል።
በሰመኃር አለባቸው

ኢራን በኳታር እና በኢራቅ በሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ላይ የሚሳኤል ጥቃት ሰነዘረች
ኢራን ቅዳሜ እለት በኒውክሌር ጣቢያዎቿ ላይ ለተፈፀመባት ጥቃት የአፀፋ ምላሽ ለመስጠት በኳታር እና ኢራቅ በሚገኙ የአሜሪካ አየር ሰፈሮች ሚሳኤሎችን መተኮሷን የመንግስት ሚዲያ ዘግቧል።
ኳታር በአሜሪካ ቁጥጥር ስር በሚገኘው የአል ኡዴይድ ጦር ሰፈር ላይ የደረሰውን ጥቃት አረጋግጣ ድርጊቱን "ጥሰት" በማለት በቀጥታ ምላሽ የመስጠት መብቷ የተጠበቀ መሆኑን ተናግራለች። ኳታር ለጊዜው የአየር ክልሏን የዘጋች ሲሆን የአሜሪካ እና የዩናይትድ ኪንግደም ዜጎችም ደህንነቱ በተጠበቀ ስፍራ እንዲጠለሉ ተነግሯቸዋል።
ፔንታጎን አል ኡዴይድ ከኢራን በተተኮሱ የአጭር እና መካከለኛ ርቀት ባለስቲክ ሚሳኤሎች መጠቃቱን አረጋግጧል። አንድ የመከላከያ ባለስልጣን በጥቃቱ እስካሁን የአሜሪካን ጉዳት የደረሰበትን ሪፖርት አለመኖሩን ተናግረዋል። የመከላከያ ባለስልጣናት አሁንም ሁኔታውን እየተከታተሉ መሆኑን እና መረጃ በሚገኝበት ጊዜ ተጨማሪ መረጃ እንደሚሰጡ ተናግረዋል።

ዲሞክራቲክ ኮንጎ የኮባልት የውጪ ንግድ እገዳን በ3 ወራት አራዘመች
የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መንግስት የኮባልት ኤክስፖርት ጊዜያዊ እገዳን ለተጨማሪ ሶስት ወራት አራዝሟል፣ ለዚህም የሰጠው ምክንያት በአለም ገበያ ላይ ያለውን የምርቱን የተትረፈረፈ አቅርቦት በመጥቀስ ነው። የስትራቴጂክ ማዕድን ንጥረነገሮች ገበያ ቁጥጥር ባለስልጣን በሰጠው መግለጫ “የእገዳው መራዘም ያስፈለገው በገበያው ላይ ያለው ከፍተኛ የአክሲዮን መጠን በመቀጠሉ ነው” ብሏል።
ኤጀንሲው የተራዘመው እገዳ ከማብቃቱ በፊት ሁኔታውን ለመገምገም እና አዲስ ውሳኔ ለመስጠት ማቀዱን ይህም እርምጃው እንዲስተካከል፣ እንዲራዘም ወይም እንዲነሳ ሊያደርግ እንደሚችልም ገልጿል። እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 22 ላይ የተጣለው የመጀመሪያው የአራት ወራት እገዳ አለም አቀፍ የኮባልት ዋጋን ለማረጋጋት፣ በማዕድኑ አቅርቦት ሰንሰለት ውስጥ ግልፅነትን ለመጨመር እና የሀገር ውስጥ ማጣሪያ እና እሴት ጨምሮ የመላክ ሂደትን ለማበረታታት ያለመ ነበር።
ዲሞክራቲክ ኮንጎ ከ 70 በመቶ በላይ የሚሆነውን የዓለም ኮባልት የምታመርት ሲሆን ይህው ውድ ሀብት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ባትሪዎች እና ሌሎች ከፍተኛ የቴክኖሎጂ መተግበሪያዎችን ለማቅረብ ወሳኝ አካል እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ።

በእስራኤል ኢራን ውጥረት ዙሪያ ትንታኔውን
ከጋዜጠኛ ሚሊዮን ሙሴ እና ስምኦን ደረጄ ይመልከቱ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/SUqCVs3MXf4?si=f2OYdsn7uOPosB31

Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (Beⓒk)
በዋልታ ቴሌቪዥን የስፖርት ጋዜጠኝነት የምናዉቀዉ አብዱ መሐመድም ስለ ድሬዳዋ እና ስሁል ሽረ የጨዋታ ማጭበር በፌስቡክ ገጹ ላይ የጻፈዉን ዳጉ ጆርናል ስፖርት እንደሚከተለዉ ያቀርበዋል።
"300ሺ ኢንቨስት አድርገው 27 ሚሊዮን ብር በአንድ ቀን ሰርተው ያደሩ" ሰዎች አሉ ይለናል ጋዜጠኛዉ
"ይህን ኳስ የሞከረው አጥቂ መስሎህ ሙከራውን ብታደንቅ አይፈረድብህም:: እውነታው ግን የስሑል ሽረ ተከላካይ ራሱ ላይ ለማስቆጠር ነው ይህን የመሰለ ግሩም ሙከራ ያደረገው:: ግብ ጠባቂው ሚስኪን ነገሩ አልገባው ተዋደቀኮ😂 የጉድ ሃገር!
ዮኒ"almost የአጥቂ ኳስ ነው የሞከረው.... explain ለማድረግ የሚያስቸግር ይመስለኛል" የማርክ Markos Elias ሳቅ...
300ሺ ኢንቨስት አድርገው 27 ሚሊዮን ብር በአንድ ቀን ሰርተው ያደሩ ታታሪ ባለሙያዎችን የያዘ ውብ እግር ኳስ ነውኮ ያለን 😂😂😂" ሲል ትዝብቱን አስፍሯል።
#ዳጉ_ጆርናል_ጆርናል

የኮሎምቢያ ጦር 57 ወታደሮቹ በኮኬን ምርት በሚታወቀዉ አካባቢ በሲቪሎች መታገታቸዉን አስታወቀ
በደቡብ ምዕራብ ተራራማ አካባቢ ከ50 በላይ ወታደሮች በሲቪሎች መያዛቸውን የኮሎምቢያ ጦር አስታዉቋል።ቅዳሜ እለት በኤል ታምቦ ውስጥ በተደረገ ኦፕሬሽን የወታደሮቹ ቡድን በቁጥጥር ስር የዋለው ሚካይ ካንየን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሲሆን ፣ የኮኬይን ምርት ቁልፍ ቀጠና እና በሀገሪቱ የፀጥታ ችግር ባለበት ስፍራ መሆኑ ታዉቋል፡፡
እሁድ እለት፣ ሌላ የወታደር ቡድን እዚያው ክልል ወደምትገኘው ኤል ፕላቴዶ ከተማ ሲያመሩ ቢያንስ በ200 ነዋሪዎች ተከበዋልል።ሁለቱም አፈናዎች በድምሩ አራት መኮንኖች እና 53 ፕሮፌሽናል ወታደሮች መታገታቸዉን ጦሩ አስታዉቋል፡፡
በደቡብ ምዕራብ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን የሚመራው ጄኔራል ፌዴሪኮ አልቤርቶ ሜጂያ ማህበረሰቡን "ሰርገው የገቡ" አማፂያን "ጠለፋ" መሆኑን በቪዲዮ ላይ አክለዋል።የኮሎምቢያ ጦር በክልሉ ውስጥ ያሉ ሲቪሎች በ 2016 ከመንግስት ጋር የሰላም ስምምነት አካል ለመሆን ፈቃደኛ ያልሆነው የኮሎምቢያ አብዮታዊ ጦር ሃይሎች ዋና ተቃዋሚ ቡድን ከማዕከላዊ ጄኔራል ስታፍ ትዕዛዝ እንደሚቀበሉ አረጋግጠዋል ።

በተለያዩ ግለሰቦች የተዘረፉ ከ 10 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የመጠጥ ውሃማስተላለፊያ ትቦዎች በቁጥጥር ስር ዋለ
በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ግራዋ ወረዳ የግራዋ ወረዳ አስተዳደር ውሀ ማዕድን እና ኢነርጂ ፅህፈት ቤት ንብረት የሆኑ ከ10 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ እና በተለያዩ ግለሰቦች የተዘረፉ የመጠጥ ውሀ ማስተላለፊያ ቱቦዎች በቁጥጥር ስር በማዋል ለመንግስት ገቢ ማስመለሱን የግራዋ ወረዳ አቃቤ ህግ ፅህፈት ቤት ገልጿል።
ብስራት ሬዲዮ ከግራዋ ወረዳ አቃቤ ህግ ፅህፈት ቤት ባገኘዉ መረጃ መሰረት ንብረትነቱ የግራዋ ወረዳ የውሀ ማዕድን እና ኢነርጂ ፅህፈት ቤት የሆኑ እና ለገጠር ቀበሌዎች የንፁህ መጠጥ ውሀ ለማዳረስ በተዘረጋው እቅድ መሠረት የተከማቹ የመጠጥ ውሀ ቱቦዎች በተለያዩ ግለሰቦች የመዘረፋቸው ሪፖርቱ ለፖሊስ እና አቃቤ ህግ በደረሰው መረጃ መሠረት በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ከ10 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የውሀ ቱቦዎች ከተለያዩ ጎለሰብ መኖሪያ ቤቶች ተሰባስበው በንብረት አስተዳደር መመሪያ መሠረት ለግምጃ ቤት ገቢ እንዲሆኑ መደረጉን ፅህፈት ቤቱ ገልጿል።
ከተለያዩ ግለሰቦች እጅ የተገኙት በርካታ የውሀ ቱቦዎች 10 ሚሊየን 662 ሺህ 380 ብር እንደሚያወጣ የገለፀው ፅህፈት ቤቱ የመጠጥ ውሀ ቱቦዎች ዘረፋ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች ላይ በማስረጃ የተጠናከረ ምርመራ በማድረግ በቅርብ ቀን ለፍትህ ለማቅረብ እየተሰራ እንደሚገኝ የግራዋ ወረዳ አቃቤ ህግ ፅህፈት ቤት መግለጫ አመላክቷል።
በሰመኃር አለባቸዉ

እስራኤል የኢራንን ስጋትነት በማስወገዳችን በትራምፕ የተኩስ አቁም ሀሳብ ተስማምተናል አለች
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በትራምፕ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መግለጫ አውጥቷል። ኔታንያሁ ተቀብለውታል ሲል ይፋ አድርጓል። የእስራኤል መንግስት በኢራን ላይ ያደረሰውን ጥቃት “ዓላማውን” በማሳካቱ የተኩስ አቁም ሃሳብን ተቀብያለሁ ብሏል።
በመግለጫው መሰረት እስራኤል የኢራንን “ሁለት ፈጣን የህልውና ስጋት” የሆኑትን ከኒውክሌር ጦር መሳሪያ እና ባለስቲክ ሚሳኤሎች አስወግዳለች። በተጨማሪም እስራኤል "በወታደራዊ አመራር ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሳለች፣ እንዲሁም በደርዘን የሚቆጠሩ የኢራን መንግስት ኢላማዎችን አውድማለች" ብሏል። መግለጫው በመቀጠል የእስራኤል ሃይሎች በመጨረሻው ቀን በቴህራን እምብርት የመንግስት ኢላማዎችን ክፉኛ በመምታት በመቶዎች የሚቆጠሩ የባሲጅ ኦፕሬተሮችን በማስወገድ የኢራን መንግስት ተቃውሞዎችን ለማፈን ብዙ ጊዜ የሚጠቀመው ሚሊሻ እና "ሌላ ከፍተኛ የኒውክሌር ሳይንቲስትን ያስወግዳል" ብሏል።
"እስራኤል ፕሬዝዳንት ትራምፕን እና አሜሪካን በመከላከያ ላደረጉት ድጋፍ እና የኢራንን የኒውክሌር ስጋትን ለማስወገድ ላሳዩት ተሳትፎ ምስጋና አቅርበዋል" ሲል መግለጫው አክሎ ገልጿል።የኢራን መንግስት ሚዲያ እንደዘገበው ኢራን የተኩስ አቁም ስምምነት ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት የመጨረሻ ዙር ሚሳኤሎችን ወደ እስራኤል ተኩሳለች። በጥቃቱ ቢያንስ አራት ሰዎችን ተገድለዋል። የኢራን መንግስት ቲቪም በእስራኤል ላይ ኢራን ከፈፀመችው የጥቃት ማዕበል በኋላ የተኩስ አቁም ስምምነት ተጥሏል ሲል ዘግቧል።

ከሌላ ወንድ ጋር እጮኝነት ጀምራለች በሚል የገዛ እጮኛውን በጩቤ ወግቶ የገደለው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ
በኮንሶ ዞን ከነ ወረዳ ፋሻ ቀበሌ ልዩ ስሙ ኮቶላ ወንዝ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ግንቦት 3 ቀን 2017 ዓ.ም የወንጀል ድርጊቱን ፈጽሟል፡፡
ኩሻቦ ኩራዎ የተባለው ግለሰብ የገዛ እጮኛው የሆነችውን መምህርት ተዋበች ኩሲያን የተባለችውን እንስት ከሌላ ወንድ ጋር እጮኝነት ጀምራለች በሚል ጥርጣሬ በአሰቃቂ ሁኔታ በጩቤ ደጋግሞ ወግቶ መግደሉን ተከትሎ በቁጥጥር ስር ውሏል።
ፖሊስም በተከሳሹ ላይ የምርመራ መዝገብ በማጣራት ለኮንሶ ዞን ፍትህ መምሪያ የላከ ሲሆን የምርመራ መዝገብ የደረሰው የኮንሶ ዞን ዐቃቤ ህግም በተከሳሽ ላይ ክስ መስርቶ ለኮንሶ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይልካል።
የኮንሶ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ከዐቃቤ ህግ የደረሰው ክስ ሲመረምር ከቆየ በኃላ ሰኔ 13 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ኩሻቦ ኩራዎ በፈፀመው የግድያ ወንጀል ጥፋተኛ ነው በማለት ተከሳሽን ያርማል ሌሎችም ያስተምራል በማለት በ25 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።
ተከሳሹ ወንጀሉን የፈጸመው ማለዳ ሰው በደንብ በማይንቀሳቀስበት ብሎም በአሳቻ ሰዓትና ስፍራ በመሆኑና የወንጀሉ አፈፃፀም አሰቃቂ በመሆኑ ምክንያት ቅጣቱን እንዳከበደው ብስራት ከኮንሶ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያገኘው መረጃ ያሳያል።

ታሪፍ ላይ ተመጣጣኝ ማሻሻያ ካልተደረገ የፈሳሽ ጭነት ማጓጓዣ ባለንብረቶች ከገበያ ዉጪ ለመሆን እንገደዳለን አሉ
የኢትዮጵያ የፈሳሽ ጭነት ማጓጓዣ ባለንብረቶች ማህበር ባደረገዉ ስብሰባ የማህበሩ አባላት እራሳቸውን ማስተዳደር የማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸውንና ታሪፍ ላይ ተመጣጣኝ ማሻሻያ ካልተደረገ ከገበያ ዉጪ ለመሆን እንደሚገደዱ ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል ።
የማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ ፀጋ አሳመረ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት ከሆነ የታሪፍ ጭማሪ የጎማ ፣የነዳጅና የገበያ ሁኔታ ታይቶ በዓመት አንድ ጊዜ የሚከናወን ሲሆን እንደየሁኔታው ደግሞ በየስድስት ወሩ ጭማሪ እንዲደረግ የሚጠይቅ መመሪያ መኖሩን ገልፀዋል ። ለእነዚህ የፈሳሽ ጭነት ማጓጓዣዎች የታሪፍ ጭማሪ ከተደረገ ሀምሌ ወር ሲመጣ ሁለት ዓመት እንደሚያስቆጥር የማህበሩ ፕሬዝዳንት ተናግረዋል ።
ከማህበሩ አባላት ፣ከኢትዮጵያ ነዳጅ ቁጥጥርና ድርጅት ባለስልጣን ፣ከትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር እና ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሁለት ሁለት አባላት በመወከል ስምንት ሰዎች ጊዜያዊ የዋጋ ግሽበትን የሚመለከት ጥናት አድርገዉ ለነዳጅ ቁጥጥር ባለስልጣንና ለንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ የቀረበ ሲሆን የታሪፍ ጭማሪ እንደሚደረግ ቢገለፅም እስካሁን ምንም አይነት ጭማሪ አለመደረጉ ተነግሯል ።
ከዶላር ጭማሪ ጋር ተያይዞ የሚደረጉ ግብይቶች በሙሉ ጭማሪ ያሳዩ ሲሆን አምና 40ሺህ ብር የነበረዉ ጎማ ዘንድሮ 75ሺህ ብር ነዉ። የዘይት ፣የመለዋወጫ እና የሹፌሮችም ደሞዝ በዚህ መልኩ መጨመሩ ተገልጿል ። ባለፉት ዓመታት የተመዘገበዉን የኢኮኖሚ እድገት ተከትሎ የነዳጅ ስርጭት ፍላጎት ለሟሟላት ከጊዜ ወደ ጊዜ በዘርፉ ላይ የሚሰማሩ ተሽከርካሪዎች ቁጥር እያደገ በአሁኑ ሰዓት ከ4700 በላይ ቦቴ ተሽከርካሪዎች በ59 የነዳጅ ኩባንያዎች ዉስጥ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ።
ዘርፉ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ከፍተኛ ድርሻ ያለዉ ቢሆንም በዘርፉ የተሰማሩ ባለንብረቶች ጠንካራ አደረጃጀት የሌላቸው በመሆኑ ከመንግሥት ጋር በሚደረግ የታሪፍ ዝግጅት ፣ድርድሮችና ኢንዱስትሪውን አስመልክቶ በሚወጡ ህጎች ላይ የበኩላቸዉን ድርሻ ለማበርከትና እንደ የአስፈላጊነቱ የፖሊሲ ምክረ ሀሳብ ለማቅረብ የሚቻልበትን ሁኔታ ለመፍጠር ማህበሩ በአዲስ መልክ ተቋቁሞ ስራ ከጀመረ ሁለት ዓመታት ማሰቆጠሩን አቶ ፀጋ ተናግረዋል ።
በመባ ወርቅነህ

በአዲስ አበባ በመኖሪያ ግቢ በተሰራ የፍሳሽ ማጠራቀሚያ ታንከር ዉስጥ እድሜዉ 7 ዓመት የሆነ ታዳጊ ህይወቱ አለፈ
ትላንትና ሰኔ 16 ቀን 2017 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 14 ጋርመንት አካባቢ በመኖሪያ ግቢ ውስጥ በተሰራው የፍሳሽ ማጠራቀሚያ ታንከር ዉስጥ እድሜዉ 7 ዓመት የሆነ ታዳጊ ህይወቱ ማለፉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
ታዳጊዉ ህይወቱ ያለፈበት ምክንያት የፍሳሽ ማጠራቀሚያ ታንከር ምንም ዓይነት ከለላ ያልተደረገለትና የታንከሩ ክዳንም ክፍቱን የነበረ መሆኑን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል ።
በጋራና በተለያዩ መኖሪያ ቤቶች ቅጥር ጊቢ ዉስጥና አካባቢ የታዳጊዎች ጨዋታና እንቅስቃሴ የሚኖር በመሆኑ አካባቢው ምቹ መደረግ እንዳለባቸው ኮሚሽኑ አሳስቧል።
በመሰል ቦታዎች እና ቅጥር ጊቢ ውስጥ የሚገኙ የፍሳሽ ማጠራቀሚያ ታንከሮች ላይ በቂ ከለላና ክዳን በማድረግ ቸልተኝነትን በማስወገድ ሊያጋጥሙ የሚችሉ አደጋዎችን አስቀድሞ መከላከል ይገባል።
ከዚህ ቀደምም በቂርቆስ ክፍለ-ከተማ መስቀል ፍላወር አካባቢ በመኖሪያ አፓርታማ ቅጥር ጊቢ ዉስጥ እና በአዲስ ከተማ ክፍለ-ከተማ አዲሱ ሚካኤል አካባቢ ባለ ኮንደሚኒየም ጊቢ ዉስጥ ክዳንና መከለያ ባልተደረገበት የፍስሽ ማጠራቀሚያ ታንከር ዉስጥ ሁለት ታዳጊዎች ገብተዉ ህይወታቸዉ ማለፉ ይታወሳል።
በትግስት ላቀው

የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ከ90 በመቶ በላይ ተማሪዎችን በመውጫ ፈተና ማለፋቸዉን አስታወቀ
ወራቤ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ካስፈተናቸው ተማሪዎች 90 ከመቶ ማሳለፋቸዉን የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶክተር ቶፊቅ ጀማል ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
ከዚህ በፊት የመውጫ ፈተና ሲጀመር ፈተናው ያለፉ ተማሪዎች በ2015 62 በመቶ፣ በ2016 ደግሞ 84 በመቶ የነበረ ሲሆን የዘንድሮው ዓመት ጥሩ መሻሻል የታየበት መሆኑን ገልጸዋል። አክለው በፈተና ሰዓት ላይ የአሌክትሪክ መቋረጥ አጋጥሞ የነበረ መሆኑን በመግለጽ ይህ ባይፈጠፍ ኖሮ ከዚህ በላይ ከፍ ማለት ይችል እንደነበረም አንስተዋል።
በዚህም በመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ከነበሩት የሚጠበቅባቸውን ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ዲግሪ አጽድቋል።በተጨማሪም በቀጣይ የትምህርት ዘመን የቱሪዝም እና የሆቴል ማኔጅመንት ትምህርት ክፍል እንዲከፈት ስርዓተ-ትምህርት ጸድቋል።
ወራቤ የቱሪስት መዳረሻ መሆን የምትችል ከተማ በመሆኗ የዲፓርተመንቱ መካተት አስፈላጊ መሆኑ እና በየደረጃው ተከልሶ የተገመገመ የአምስት ትምህርት ክፍሎች ስርዓተ ትምህርትም በሴኔቱ መጽደቁ ተጠቁሟል።ወራቤ ዩኒቨርሲቲ ከመማር ማስተማር ባለፈ የተለያዩ የአካባቢውን ማህበረሰብ የሚረዱ ስራዎች እያከናወነ ይገኛል።
በዚህም ለአርሶ አደሩ የሚጠቅሙ የዘር ማሻሸያዎችን በምርምር ማቅረብ እንዲሁም ቅዳሜ እና እሁድ የዩኒቨርሲቲ መምህራን በየአካባቢው ባሉ ትምህርት ቤቶች በመሄድ የማጠናከሪያ ትምህርት እንዲሰጡ እንደሚደረግ የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ቶፊቅ ጀማል ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
በኤደን ሽመልስ

በኦሮሚያ ክልል በአንድ ሳምንት ውስጥ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ10 ሰዎች ህይወት አለፈ
በኦሮሚያ ክልል ከሰኔ 9 እስከ ሰኔ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናቶች በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የ10 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ፣በ15 ሰዎች ላይ ከባድ እና በ8 ሰዎች ላይ ቀላል አካል ጉዳት ደርሷል፡፡የሞት አደጋዎቹ በተለያዩ ዞኖች እና ከተሞች የተከሰቱ ናቸው።
በአንድ ሳምንት ውስጥ በደረሰው አደጋ ከ6 ዓመት እስከ 44 ዓመት የእድሜ ክልል ላይ የሚገኙ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን የኦሮሚያ ክልል የትራፊክ ቁጥጥር ክፍል ባለሙያ የሆኑት ኢንስፔክተር መሰለ አበራ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡
አደጋዎቹ የተከሰቱት በቀኑ እና በለሊቱ ክፍለ ጊዜ ሲሆን አደጋውን ያደረሱት ወንድ አሽከርካሪዎች ናቸው። የሞት አደጋዎች የደረሱት በጭነት፣በቤት ተሽከርካሪ፣ በህዝብ ማመላለሻ እና በባለ ሦስት እግር (ባጃጅ) የተከሰቱ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
የአደጋዎቹ መንስኤዎቹ ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር እና ለእግረኛ ቅድሚያ አለመስጠት እና ያለ መንጃ ፍቃድ ማሽከርከር መሆኑን ኢንስፔክተር መሰለ አበራ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡
በሳምራዊት ስዩም