Telegram Web Link
ኢራን የሆርሙዝ ሰርጥን እንዳትዘጋ ቻይና እንድታግባባት አሜሪካ ጠየቀች

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ኢራን ከዓለማችን እጅግ አስፈላጊ የመርከብ መንገዶች አንዱ የሆነውን የሆርሙዝ ሰርጥን ከመዝጋት እንድትከላከል ለቻይና ጥሪ አቅርበዋል ። ማርኮ ሩቢዮ ይህንን አስተያየት የሰጡት በኢራን መንግስት ስር የሚተዳደረው ፕሬስ ቲቪ የህዝብ እንደራሴዎች የባህር ዳርቻውን የመዝጋት እቅድ ማፅደቃቸውን ከዘገበ በኋላ ሲሆን የመጨረሻው ውሳኔ የጠቅላይ ብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት ነው ሲል በዘገባው አክሏል።

በነዳጅ አቅርቦት ላይ የሚፈጠር ማንኛውም መስተጓጎል በኢኮኖሚው ላይ ከፍተኛ መዘዝ ያስከትላል። ቻይና በተለይ የኢራንን ዘይት በመግዛት በዓለም ቀዳሚ ስትሆን ከቴህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት አላት። አሜሪካ በኢራን የኒውክሌር ቦታዎች ላይ የፈፀመችውን ጥቃት ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ጨምሯል።በቤጂንግ የሚገኘው የቻይና መንግስት ስለዚህ ጉዳይ እንዲሰራ አበረታታለሁ ምክንያቱም በሆርሙዝ የባህር ዳርቻ በሚወጣው የነዳጅ ዘይት ላይ በእጅጉ ጥገኛ ናቸው ሲሉ ሩቢዮ ከፎክስ ኒውስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል።

ኢራን የባህር ዳርቻውን ከዘጋች ኢኮኖሚያዊ ራስን ማጥፋት ይሆናል። ይህንን ለመቋቋም አማራጮችን ይዘን እንቀርባለን፤ ሌሎች ሀገራት ያንን መመልከት አለባቸው። ከኛ የባሰ የሌሎች ሀገራትን ኢኮኖሚ ይጎዳል ሲሉ ሩቢዮ አክለዋል። 20 በመቶ የሚሆነው የአለም ዘይት በሆርሙዝ ባህር ላይ ያልፋል፣ በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ ዋና ዋና ዘይት እና ጋዝ አምራቾች የውሃ መንገዱን ኃይል ለማጓጓዝ ይጠቀሙበታል።ቻይና በተለይ ከኢራን አብላጫውን የነዳጅ ዘይት ፍላጎቷን ትገዛለች። ከኢራን የምታስገባው ነዳጅ ባለፈው ወር በቀን 1.8 ሚሊዮን በርሜል እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
የፕላስቲክ ከረጢት ማምረት ላይ የወጣው አዋጅ ተግባራዊ ሲደረግ ከ800 በላይ ፋብሪካዎች ስጋት እንዳለባቸው ተገለፀ

የኢትዮጵያ የፕላስተቲክ እና ጎማ አምራች ማህበር የፕላስቲክ ከረጢት ወይም ፌስታል  አንድ ግዜ ብቻ ተጠቅመን የምንጥለው ሳይሆን መልሰን ጥቅም ላይ የምናውለው ምርት ነው ሲሉ አስታወቀ

በቅርቡ ማንኛውም ሰው አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውል የፕላስቲክ ከረጢት ይዞ ከተገኘ ከ2 እስከ 5 ሺህ ብር የሚያስቀጣው አዋጅ መፅደቁ ያስታወሰው ማህበር ያለውን ቅሬታውን አቅርቧል ።

የማህበሩ አባል እና የወቅታዊ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ አዋጅ ዙሪያ ማህበሩ ያቋቋመው ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ በረከት ገ/ህይወት ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት የፌስታል ምርትን በመሰብሰብ መልሶ ጥቅም ላይ ውሎ አገልግሎት እንዲሰጥ እያደረገ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ደረጃው የጠበቀ ፌስታል እንዲመረት ግን መደረግ እንዳለበት አስታውቀዋል።

ከመላው ሀገሪቷ ተሰብስቦ በግዢ የሚረከቡት የፌስታል ደርቅ ቆሻሻን በኪሎ 30 ብር በመግዛት በመልሶ ምርት ፌስታል፣ የኤሌክትሪክ ኮንዲውት እና ለኮሪደር ልማት ላይ እየዋሉ የሚገኙትን ኤችዲ ፓይፕ እያመረቱ መሆኑን አስታውቀዋል።

ሆኖም በአዋጁ መሰርት  አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውል የፕላስቲክ ከረጢት ያመረተ ወይም ወደ ሀገር ውስጥ ያስገባ፣ ለገበያ ያቀረበ ወይም የሸጠ፣ ለንግድ ዓላማ ያከማቸ ወይም ይዞ የተገኘ ከ50 ሺህ ብር በማያንስና ከ200 ሺህ ብር በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ እና ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት  እንዲቀጣ አዋጁ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ ተፈጻሚ ይሆናል መባሉ ይታወሳል።

በመላው ሀገሪቱ መልሶ ጥቅም ላይ የሚያውሉ ከ8መቶ በላይ የፕላስቲክ ማሽጊያ ፌስታል የሚያመርቱ  ፋብሪካዎች ያሉ ሲሆን ከ268 ሺ በላይ  በስራው ላይ የተሰማሩ ዜጎች ይገኛሉ። አዋጁ ተግባራዊ ሲደረግ በዘርፉ የተሰማሩ ፋብሪካዎችን ሆን ሰራተኞችን ከመስኩ የሚያስወጣቸው እና ሲሳራ ላይ የሚጥላቸው መሆኑ ተነግሯል።

አዋጁ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ አስፈፃሚ አካላት ፌስታል ከእንግዲህ ተከልክሏል በሚል ነጋዴዎች ላይ በፈጠሩት  ጫና ምክንያት የምናመርተው ፌሰታል ወደ ገበያ ሊውጣ ባለመቻሉ አዋጁ ከአሁኑ ተፅኖ በማድረጉ በርካታ ፋብሪካዎች ስራ ፈተዋል ሲሉ  አቶ በረከት ገ/ህይወት ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል
Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (Beⓒk)
ሳሙኤል ኤቶ ከእርሱ ጋር ግጭት ዉስጥ ገብቶ የነበረዉ የቀድሞ የብሔራዊ ቡድን አጋሩ ለ 5 አመታት ወደ እግርኳስ ዝር እንዳይል አስቀጣ

የካሜሩን እግርኳስ ፌደሬሽን የቀድሞ የብሔራዊ ቡድን ፣ የቼልሲ እና የሪያል ማድሪድ ተጨዋች የነበረዉን ጄሬሚ ሶሬል ለአምስት አመታት ወደ ሀገሪቱ የእግርኳስ ዘርፍ ዝር እንዳይል አግዶታል።

የካሜሩን እግርኳስ ፌደሬሽን ከዚህ ዉሳኔ የደረሰዉ ጄረሚ ፤ ከቀድሞ የብሔራዊ ቡድን አጋሩ እና ከአሁኑ የካሜሩን እግርኳስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ከሳሙኤል ኤቶ እና ቦርድ አባላት ጋር ግጭት ዉስጥ ከገባ በኋላ ነዉ።

በ 2023 በተፈጠረው በዚህ ዉዝግብ ወቅት ካሜሩን ከ ጋምቢያ ጋር ጨዋታ ነበራት። በጨዋታዉ ላይ በተፈጠረው ግጭት ጄረሚ በስተመጨረሻ በጸጥታ ሀይሎች ከስታዲየሙ እንዲወጣ ተደርጓል።

በዚህ ምክኒያት ለአምስት አመታት ወደ እግርኳስ እንዳይመጣ እንዲሁም 10 ሚሊዮን የካሜሩን ፍራንክ ወይንም 13 ሺህ ፓዉንድ ቀጥቶታል። በተመሳሳይ የጄረሚ የቅርብ ረዳትም የ 2 አመት ቅጣት እና የ 6 ሺህ 500 ፓዉንድ ቅጣት ተጥሎበታል።

ጄረሚ ከሪያል ማድሪድ ጋር 2 ሻምፒዮንስ ሊግ ያሳካ ሲሆን ለኒዉካስትልም ተጫዉቷል።

በበረከት ሞገስ

#ዳጉ_ጆርናል_ስፖርት
@Dagujournalsport
ሩሲያ በዩክሬን ዋና ከተማ በፈፀመችው ጥቃት ሰባት ሰዎች ተገደሉ

በኪየቭ ክልል በአንድ ሌሊት በተፈፀመ የሩስያ የሚሳኤል እና የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ቢያንስ ሰባት ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች ቆስለዋል ሲሉ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል። ኢጆር ክላይመንኮ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በለጠፉት ጽሁፍ የመኖሪያ አካባቢዎች፣ ሆስፒታሎች እና የስፖርት መሠረተ ልማቶች በጥቃቱ ተጎድተዋል።

ከሞቱት መካከል ቢያንስ ስድስቱ በዋና ከተማው ባለ ከፍተኛ ፎቅ ላይ የሚገኙ ነዋሪዎች መሆናቸውን የኪየቭ ከንቲባ ቪታሊ ክሊችኮ ገልፀው ሌሎች 22 ሰዎች በከተማዋ ቆስለዋል ብለዋል። ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ሩሲያ በዩክሬን ከተሞች ላይ ከፍተኛ የአየር ላይ ጥቃቶችን እየፈፀመች ትገኛለች። የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ ሰኞ እለት ስለግጭቱ ለመወያየት ወደ ለንደን አቅንተዋል።

በቅርቡ ቀናት ውስጥ ሩሲያ 352 ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና 16 ሚሳኤሎች በዩክሬይን ግዛቶች በተለይም በኪየቭ አካባቢ ላይ ጥቃት መፈፀሟን የዩክሬን አየር ሃይል አስታውቋል። የዩክሬን የድንገተኛ አደጋ አገልግሎት የተደናገጡ ነዋሪዎች እየነደደ ካለው እና ከፈራረሰው ህንጻ ሲወሰዱ የሚያሳይ ምስል አጋርቷል። በርካታ ነዋሪዎች በሜትሮ የባቡር ጣቢያ ውስጥ ተጠልለው አድረዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
በሁሉም ክልሎች 125 የኤም ፖክስ  የለይቶ ማከሚያ ማዕከላት ተደራጅተው ለአገልግሎት ዝግጁ ሆኑ

የኤም ፖክስ በሽታው በተከሰተባቸው ክልሎች የለይቶ ማከሚያ ማዕከላትን በማቋቋም ለታማሚዎች ህከምና እየተሰጠ እንዲሁም በሽታው ባልተገኘባቸው ክልሎች ደግሞ በሽታው ቢከሰት ለማከም የሚያስችሉ የለይቶ ማከሚያ ማዕከላትን በማዘጋጀት ዝግጁ ማድረጉን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በኢትዮጵያ የመጀመሪያዉ የኤምፖክስ ታማሚ ከተገኘበት ግንቦት 16 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ሰኔ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በአጠቃላይ ለ324 በበሽታው ለተጠረጠሩ ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 22ቱ በበሽታው መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡

ከነዚህም መሃል የአንድ ህጻን ህይወት ሲያልፍ፣ 15ቱ ከበሽታው ሙሉ በሙሉ አገግመው ከለይቶ ህከምና ማዕከላት የወጡ ሲሆን የተቀሩት 6 ታማሚዎች በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች በሚገኙ ለይቶ ማከሚያ ማዕከላት ውስጥ ህክምናቸውን በመከታተል ላይ እንደሚገኙ የጤና ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ኤም ፖክስ ወረርሽኝ ከተከሰተባቸው 7 ሀገራት በአለም አቀፍ አየር ማረፊያዎች ለመጡ 179 ሺ 228 መንገደኞች የኤምፖክስ በሽታ ማጣራት የተደረገ ሲሆን በሁሉም የጎረቤት ሀገራት መግቢያና መውጫን ጨምሮ የየብስ እና አየር መንገድን በመጠቀም ወደ ኢትዮጵያ ለገቡ ከ6 ሚሊዮን በላይ መንገደኞች የማጣራት ስራ በማከናወን ሊከሰት የሚችለውን ድንበር ተሻጋሪ የበሽታውን ስርጭት ለመቀነስ መቻሉን ተገልፃል።

ለበሽታው አጋላጭ ሁኔታዎች ተብለው ከተለዩት መንገዶች መካከል በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር የሚደረግ የሰውነት ንክኪ፣ የግብረ ስጋ ግንኙነት እንዲሁም ከታማሚ ሰው ጋር ንክኪ ያለውን ቁስ በጋራ መጠቀም በዋነኝነት እንደሚጠቀስ ሚኒስቴር መስራቤቱ የገለፀ ሲሆን ህብረተሰቡ የበሽታውን አሳሳቢነት ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት  ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስባል።

ህብረተሰቡም ከፍተኛ ትኩሳት ፥ራስ ምታት፥ የጀርባና የጡንቻ ህመም ፥ የእጢ ማበጥ፥ ለመተንፈስ መቸገር እና የቆዳ ላይ ሽፍታ ሲያሳዩ ወዲያዉኑ ራስን ከሌሎች ሰዎች መለየት እና ወደ ጤና ተቋም በመሄድ የሕክምና እርዳታ ማግኘት፣ እንዳለበትም ተገልፃል።

#ዳጉ_ጆርናል
የኢራን ጦር ዩናይትድ ስቴትስ ኃይለኛ ምላሽ እንደሚጠብቃት አስጠነቀቀ

የኢራን ጦር ካታም አል-አንቢያ ክፍል ቃል አቀባይ ዩናይትድ ስቴትስ በሦስት ዋና ዋና የኒውክሌር ቦታዎች ላይ የቦምብ ድብደባ ከፈጸመች በኋላ “ከባድ መዘዞችን የሚያስከትሉ ተግባራት ይኖራሉ” ሲሉ አስጠንቅቀዋል። የኢራን የዜና ኤጀንሲዎች ስማቸውን ያልተጠቀሷቸውን ቃል አቀባይ ዋቢ በማድረግ እንደዘገቡት ዩናይትድ ስቴትስ እስራኤልን ወክላ “ወንጀለኛ” ድርጊት ፈጽማለች በማለት ክስ ሰንዝረዋል፣ይህም የኢራንን ሉዓላዊነት “በአደባባይ ይጥሳል” ሲሉ አክለዋል።

ቃል አቀባዩ ስለ እስራኤል ሲናገሩ "ይህ የጥላቻ ተግባር የተፈፀመው እየሞተ ያለውን የጽዮናዊ አገዛዝ ለማንሰራራት በማለም ነው። የዩናይትድ ስቴትስ ጥቃት የኢራንን “ህጋዊ እና የተለያዩ ኢላማዎች”  እንደሚያሰፋም አክለዋል። ኻታም አል-አንቢያ ከኢራን አብዮታዊ ጥበቃ ኮርፖሬሽን ተለይቶ የሚንቀሳቀስ በኢራን ጄኔራል ስታፍ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ስር የሚገኝ የወታደራዊ ሃይል ልዩ ክፍል ነው።

በሌላ በኩል ታይምስ ኦፍ እስራኤል እንደዘገበው የእስራኤል ኤሌክትሪክ ኮርፖሬሽን "ስትራቴጂያዊ የመሠረተ ልማት ተቋማት" አቅራቢያ መመታቱን አረጋግጧል። በአካባቢው በሚገኙ በርካታ ከተሞች የኃይል መቆራረጥ እንዳለ ገልጿል። "ቡድኖች በተቻለ ፍጥነት የኃይል አቅርቦትን ወደነበረበት ለመመለስ በማቀድ መሬት ላይ ወደተለያዩ ቦታዎች በመጓዝ ላይ ናቸው፤ ኦፕሬሽኑ የመሠረተ ልማት ጥገና እና የደህንነት አደጋዎችን ማስወገድን ያካትታል እንዲሁም ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በቅንጅት እየተካሄደ ነው" ሲል የእስራኤል ኤሌክትሪክ ኮርፖሬሽን አስታውቋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
ኢትዮጲያ በ 2018 የጋዝ ምርትን ወደ ገበያ ልታቀርብ ነው ሲሉ ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ ተናገሩ

👉🏼ጠ/ሚኒስትሩ ከሰባት አመታት በፊትም ኢትዮጵያ ድፍድፍ ነዳጅ ማዉጣት ሙከራ እና ሽያጭ እንደምትጀምር ተናግረዉ ነበር


ኢትዮጲያ የራሷን ጋዝ ለማምረት  ጥረት ስታደርግ መቆየቷ የተገለፀ ሲሆን በመጪው መስከረም  የ 2018  ዓ/ም   አዲስ አመት ላይ ወደ ገበያ ሊቀርብ መሆኑን ሰምቻለሁ ሲል ኢትዮ ኤፍኤም ዘግቧል፡፡

ይህ የተሰማው ጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ  አሕመድ (ዶ/ር ) በሀገሪቱ ከሚገኙ የሚዲያ አመራሮች እና የኮሚኒኬሽን ባለሙያዎች ጋር በዛሬው ዕለት እያደረጉት ባለው  የጋራ ውይይት ላይ ነው፡፡

ይህ ምርት የት አካባቢ እንደሆነ በቀጥታ ባይናገሩም በንግግራቸው ወቅት " ላለፉት ሁለት ሦስት ዓመታት እኔ የምጎበኘው ጋዙን ነው እናንተ የምታዩት ስንዴውን " ሲሉ ተናግረዋል።

ከሰባት አመታት በፊትም ጠ/ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ድፍድፍ ነዳጅ የማምረት ሙከራ እና መሸጥ እንደምትጀምር ተናግረዉ ነበር። በተለያዩ ምክኒያቶች ስራ ላይ ባይዉልም።

በዚህ መድረክ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጲያ ማዳበሪያን  ከዳንጎቴ ግሩፕ ጋር  ለማምረት ከስምምነት ላይ መድረሷንም  አስታውቀዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ የማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ውጥን መያዙን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የመንግስትን የ2017 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸምን በተመለከተ ለምክር ቤት አባላት ባቀረቡበት ወቅት መናገራቸው የሚታወስ ነው፡፡

በወቅቱም የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታው ከ2.5 እስከ 3 ቢሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚጠይቅ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረው ነበር፡፡

በተጨማሪም   ጠቅላይ ሚኒስትሩ  በመጪው የ 2018 መስከረም ወር ታላቁ የህዳሴ ግድብ ተጠናቆ ሪቫኑ እንደሚቆረጥ በዚሁ መድረክ ላይ  ተናግረዋል።

#ዳጉ_ጆርናል
በእስራኤል ኢራን ውጥረት ዙሪያ ትንታኔውን
ከጋዜጠኛ ሚሊዮን ሙሴ እና ስምኦን ደረጄ ይመልከቱ


👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://youtu.be/SUqCVs3MXf4?si=f2OYdsn7uOPosB31

#ዳጉ_ጆርናል
በአዲስ አበበ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ9 ሰዎች ህይወት አልፏል

ከሟቾቹ መካከል የ3 ዓመት ዕድሜ ያለው ህፃን የሚገኝበት ሲሆን በ8 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ከክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ሰኞ ሰኔ 16 ቀን 2017 ዓ/ም ረፋድ ላይ በግምት 3 ሰዓት ገደማ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በተለምዶ አባሳሙኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ባጋጠመ የተሽከርካሪ አደጋ የሞት እና የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡

በክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ አደጋ ምርመራ ማስተባበሪያ ሃላፊ  ዋና ኢንስፔክተር መርዕድ ደበሌ እንደተናገሩት አደጋው ሊከሰት የቻለው ከሃይሌ ጋርመንት ወደ ዩኒሳ አደባባይ ይጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-78979 ኢት የሆነ የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት አውቶቡስ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-04273 ኢት ከሆነ ሌላ ከባድ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ እና መንገድ ስቶ ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ በመግባቱ ነው፡፡

አውቶቡሱ ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ ከገባ በኋላ ከዩኒሳ አደባባይ ወደ ሃይሌ ጋርመንት ሲጓዝ ከነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-77970 ኦሮ ከሆነ ዶልፊን ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ በዶልፊኑ ውስጥ ከነበሩት ተሳፋሪዎች መካከል አሽከርካሪውን ጨምሮ የዘጠኝ ሰዎች ህይወት ማለፉን ዋና ኢንስፔክተር መርዕድ አስረድተዋል፡፡

ከሟቹቹ መካከል የ3 ዓመት ህፃን እንደሚገኝበት የጠቀሱት ዋና ኢንስፔክተሩ፤ በሌሎች 8 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ጠቅሰዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በአካባቢው ላይ የቆመ እና በጉዞ ላይ የነበረ ሌሎች ሁለት ተሽከርካሪዎች በአውቶቡሱ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ የአደጋው መንስኤ እየተጣራ እንደሚገኝ ዋና ኢንስፔክተር መርዕድ ደበሌ አስታውቀዋል፡፡


#ዳጉ_ጆርናል
በወሊድ ምክንያት የሚከሰት የእናቶችን ሞት በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ መቻሉን የአዳማ ከተማ ጤና ፅህፈት ቤት አስታወቀ

ባለፋት 10 ወራት 22 ሺህ እናቶች በሰለጠነ ባለሙያ በጤና ተቋማት የወሊድ አገልግሎት ማግኘታቸዉን የአዳማ ከተማ ጤና ፅህፈት ቤት አስታዉቋል ።

የአዳማ ከተማ ጤና ፅህፈት ቤት ሀላፊ ሲስተር ሰሚራ መሀመድ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት በወሊድ ምክንያት የሚከሰት የእናቶችን እና የህፃናትን ሞት ለመቀነስ ሰፊ ስራ በመሠራቱ ከአቅም በላይ ከሆነ ምክንያት ዉጪ በወሊድ ወቅት የሚከሰት የእናቶችን ሞት በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ መቻሉን ተናግረዋል ።

ነፍሰጡር እናቶች ከእርግዝና ወቅት አንስቶ እስከ ወሊድ ባለዉ በጤና ተቋማት ክትትል እንዲያደርጉ በሰለጠነ ባለሙያ ተገቢዉን አገልግሎት እንዲያገኙ  ማድረግ ተችሏል ብለዋል ። ከሆስፒታሎች ዉጪ በ2015 በጀት ዓመት በአንድ ጤና ጣቢያ ላይ የቀዶ ህክምና አገልግሎት ይሰጥ አንደነበረ የገለፁት ሀላፊዋ በዚህ ዓመት አዋሽ መልካሳ በተባለ ጤና ጣቢያ ላይ የቀዶ ማዋለድ ህክምና የተጀመረ ሲሆን ይህም የህፃናትንና የእናቶችን ሞት በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል ።

በተጨማሪም የጤና መድህን ኢንሹራንስ አባላት ቁጥር በየዓመቱ እየጨመረ መምጣቱ የተገለፀ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም አዳዲስ አባላትን በማፍራት ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኙ ተደርጓል ። ባለፉት 10 ወራት ከ76ሺህ በላይ አባላትን በማፍራት 96 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን ሲስተር ሰሚራ ጨምረዉ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።

በመባ ወርቅነህ
#ዳጉ_ጆርናል
Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (Beⓒk)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የስፖርት ጋዜጠኛ አሉላ ፍሬዉ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ላይ ድሬዳዋ ከተማ እና ስሁል ሽረ ያደረጉት ጨዋታ የጨዋታ መጭበርበር የነበረበት ነዉ ሲል ማስረጃዎችን በማቅረብ እየተሟገተ ነዉ።

ጋዜጠኛዉ ጨዋታዉን ድሬዳዋ ከተማ 4 ለ 2 አሸንፎ ይጠናቀቃል ብለዉ በርካቶች ትክክለኛ ዉጤትን እየገመቱ አቋማሪ ድርጅቶችን ገንዘብ በልተዋል ሲልም በኤንቢሲ ቴሌቪዥን በሚተላለፍ የስፖርት ፕሮግራም ላይ ተናግሯል።

በማህበራዊ የትስስር ገጽም በሚሊዮኖች ገንዘብ ያሸነፉ ሰዎች አሉ መባሉን ዳጉ ጆርናል ስፖርት ከተመልካቾች አስተያየቶች/ኮሜንቶች ላይ ተመልክቷል።

በቪዲዮዉ ላይ እንደሚታየዉም ሀብታሙ የተሰኘዉ የስሁል ሽረ ተከላካይ ራሱ ላይ ለማግባት ሙከራ ሲያደርግ በግልጽ ይታያል።👇🏼

#ዳጉ_ጆርናል_ስፖርት
@Dagujournalsport
አዲስ አበባን ጨምሮ በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች ኤሌክትሪክ ተቋርጧል

አዲስ አበባን ጨምሮ በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡

የኤሌክትሪክ ሃይል በከፊል የተቋረጠው ከዋናው ግሪድ ባጋጠመ የቴክኒክ ችግር ምክንያት ነው፡፡

አሁን ላይም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያጋጠመውን ብልሽት ለማስተካከል ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ ይገኛል፡፡

ለተፈጠረው ችግር ደንበኞችን ይቅርታ የጠየቀው አገልግሎቱ÷ በትዕግስት እንዲጠብቁም ጥሪ አቅርቧል፡፡

#ዳጉ_ጆርናል
2025/07/03 23:54:15
Back to Top
HTML Embed Code: