ቅዳሜን ከእኛ ጋር" ፕሮግራም በተወዳጁ ብስራት ኤፍ.ኤም 101.1 ዛሬ ይመለሳል፤ ስንመለስ...
[ ] በልዩ ፕሮግራም ቅዳሜን ከእኛ ጋር ዛሬ የሬዲዮ ሞገዳችሁን 101.1 ላይ ካደረጋችሁ አብረን እንቆያለን።
[ ] የእስራኤል የረጅም ጊዜ መሪ ቤንያሚን ኔታንያሁ(ቢቢ) ማን ናቸው? በአክራሪ ብሄርተኝነታቸው የሚታወቁት ቢቢ ከቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ይስሃቅ ራቢን ግድያ ጋር በተያያዘ ለምን ስማቸው ይነሳል?
[ ] በራሪው ተወዳጁ የአዙሪ የግብ ዘብን ጂአንሉጂ ቡፎንን እናነሳለን።
[ ] የቅዳሜ ወሬዎችን እያነሳሳን እንቆያለን ምርጥ ምርጥ ሙዚቃ ትጋበዛላችሁ፤ ተረክም አለ ፣ ስፖርታዊ ጥንቅር ከወቅታዊ መረጃዎች ጋር ተዘጋጅቷል።
ስፖንሰሮቻችን ፦
👉 ዘመን ባንክ
👉 ቨርጂኒያ ፋርማሲውቲካልስ
👉 ጣዕም ዳቦና ኬክ ቤት-ሻወርማን ይቅመሱ
👉 ጃፋር የመፅሃፍት መደብር
👉ዲያፕላንትስ - ፍቱን የባህል ህክምና
👉 አውት ዲተርጀንት -የፅዳት መላ
ሁሌም ቅዳሜያችሁን ከ 5 እስከ 7 በተወዳጁ ጣቢያ ብስራት ኤፍ.ኤም 101.1 ላይ እንጠብቃችኃለን።
#ቅዳሜን ከእኛ ጋር
ለአዳዲስ እና ወቅታዊ መረጃዎች ቴሌግራም ቻናላችንን #ዳጉ_ጆርናል ይቀላቀሉ
ሊንክ :- @zena24now

Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (Beⓒk)
የቤኒቶ ሙሶሎኒ የልጅ ልጅ በቀጣይ አመት በጣሊያን ሴሪኤ ይጫወታል
የ22 አመቱ ሮማኖ ፍሎሪያኒ ሙሶሎኒ የውድድር ዘመኑን ከላዚዮ በሴሪ ቢ ጁቬ ስታቢያ በውሰት ተሰጥቶ አሳልፎ ነበር።
ተከላካዩ በአስደናቂ የውድድር ዘመን አሳልፏል የተባቤ ሲሆን ለጁቬ 37 ጨዋታዎችን አድርጓል።
በስታቢያ አስደናቂ የውድድር ዘመን ካሳለፈ በኋላ ክለቡ ላዚዮ የዉሰት ዉሉን በማቋረጥ ወደ ክለቡ እንዲመለስ አድርጓል። ጁቬ የመግዛት አማራጭ ባለዉ የዉሰት ዉላቸዉ መሰረት ተጨዋቹን ለመግዛት ጠይቀዉ ነበር። ሆኖም ላዚዮ ጥያቄዉን አልተቀበለውም።
ሙሶሎኒ ወደ ላዚዮ መንገዱን ከማግኘቱ በፊት በሮማ ወጣቶች አካዳሚ ውስጥ ጊዜ አሳልፏል።
እ.ኤ.አ. በ1943 ከስልጣን መመውደቁ እና በኋላም በ1945 ከመገደሉ በፊት የጣሊያን ፋሺስታዊ ገዥ ከነበረዉ ቅድመ አያቱ ተጨዋቹ እራሱን ለማራቅ ደጋግሞ ሞክሯል።
ስሙንም እስቀመቀየር ተገዶ እንደነበር ከዚህ ቀደም ዳጉ ጆርናል ስፖርት መረጃ አድርሷል።
በበረከት ሞገስ
#ዳጉ_ጆርናል_ስፖርት

የእግረኞች መንገድ ላይ በመኪና ሲያሽከረክር የተገኘው ግለሰብ 100 ሺህ ብር ተቀጣ
ትላንትና ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02፣ ቦሌ ማተሚያ ቤት አካባቢ በተገነባው የእግረኞች መንገድ ላይ በመኪና ሲነዱ የተገኙ ሁለት አሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ከእነዚህ ውስጥ አንዱ አሽከርካሪ 100,000 ብር ሲቀጣ፣ የሌላኛው ተሽከርካሪ ምርመራና ማጣራት እየተካሄደ መሆኑ ተገልጿል። ይህ የተደረገው ከትራፊክ ፖሊስ ጋር በመተባበር ሲሆን፣ መረጃው የተገኘውም ከህብረተሰቡ በተሰጠ ጥቆማ ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ለህብረተሰቡ ላደረገው ትብብር ምስጋና ያቀረበ ሲሆን፣ በከተማዋ መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት የሚያደርሱ እና ደንብ የሚጥሱ አካላት ላይ እርምጃ ለመውሰድ ህብረተሰቡ ጥቆማውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።
መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው::
#ዳጉ_ጆርናል

የ6ኛ ክፍል ተማሪ ሳለች ለእናቷ የገባችውን ቃል ያሳካችው ተመራቂ
የአብስራ ሽፈራው ትባላለች። የ6ኛ ክፍል ተማሪ ሳለች አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በእናቷ ምርቃት ላይ ተገኝታ ነበር።
ያኔ ታዲያ "በዚህ ግቢ ተምሬ እመረቅበታለሁ" ስትል ለእናቷ ቃል ገብታላት ነበር።
እንሆ ዛሬ የአብስራ ያን ቃሏን አሳክታለች። ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሳይኮሎጂ ትምህርት ክፍል 3.5 በማምጣት በከፍተኛ ማዕረግ በዲግሪ ተመርቃለች።
አካል ጉዳተኝነት ያልበገራት የአብስራ በመምህሮቿ የተመሰገነች ታታሪ ተማሪ ስትሆን፤ ለዚህ ስኬቷ ደግሞ የእናቷ አበርክቶ ትልቅ ድርሻ ይወስዳል።
በ4 ዓመታት የዩኒቨርሲቲ ቆይታዋ እናቷ እርሷን በማመላለስ እና በማበረታታት ለዚህ አብቅታታለች።
የአብስራ እናት፥ "ልጆቻችን አካል ጉዳተኞች ናቸው ብለን በየቤቱ ደብቀን ይበልጥ ከምንጎዳቸው፤ መስዋዕት ከፍለን ካሰቡበት እናድርሳቸው" ስትል ለወላጆች መልዕክት አስተላልፋለች።
Via EBC

በእስራኤል ኢራን ውጥረት ዙሪያ ትንታኔውን ከጋዜጠኛ ሚሊዮን ሙሴ እና ስምኦን ደረጄ ይመልከቱ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/W3o-tvV6238?si=TUJiSWsTiBjKxizo
#ዳጉ_ጆርናል
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/W3o-tvV6238?si=TUJiSWsTiBjKxizo
#ዳጉ_ጆርናል
YouTube
የእስራኤል እና ኢራን ከባዱ መዘዝ...
#BisratNews #Oyaya_Multimedia #ኦያያመልቲሚዲያ #BisratFm #BisratTv #ብስራትቴሌቪዥን #Ethiopia #ኢትዮጵያ #ኦያያ
ሶ ኢዝ ቴክኖሎጂ እና ስልጠና በ2 ዓመት ከ8 ወራት ውስጥ 4 ሺሕ ለሚሆኑ ታዳጊዎች የስቲም (STEM) ስልጠና መስጠቱን አስታወቀ
👉 ማዕከሉ በ10 ዓመት ውስጥ ዕድሜያቸው ከ4 እስከ 17 ዓመት የሆኑ 10 ሺሕ ታዳጊዎችን ለማሰልጠን አቅዷል
ሶ ኢዝ ቴክኖሎጂና ስልጠና ኃ/የ/የግ/ማ (STEM for Kids) በአፍሪካ ብሎም በኢትዮጵያ የመጀመርያ የአሜሪካ ፍራንቻይዝ ድርጅት ሲሆን፣ ባለፉት ሁለት ዓመት ከስምንት ወራት ውስጥ ዕድሜያቸው ከ4 እስከ 17 ዓመት ለሆኑ ታዳጊዎች የቴክኖሎጂ ትምህርት ሲሰጥ መቆየቱን አስታውቋል።
ፍራንቻይዙ በ2017 ዓ/ም በኮዲንግ፣ ሮቦቲክስ እና ኢንጂነሪንግ ስልጠና የወሰዱ ልጆችን በአንድ በማሰባሰብ የዓመቱ መዝግያ የስቲም ፌር መድረክ በዛሬው ዕለት አከናውኗል።
መድረኩ ልጆች ሳይንሳዊ ፕሮጀክቶችን እንዲያሳዩ፣ እርስ በእርስ የመማር ተሞክሮዎችን እንዲካፈሉና ለሳይንስ ያላቸውን ፍላጎትና ችሎታ እንዲያሳዩ ታልሞ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
ለዚህ ዘመን የሚያስፈልገው ሙሉ የስቲም ፕሮግራም እንደሚሰጥ የሚገልጹት የተቋሙ ዋና ሥራ አስከያጅ አቶ ኤርሚያስ ሃይለማርያም ''ፕሮጎራሚንግ የማንበብ እና መፃፍ ያክል አርገው እንዲያዩት፣ በኢንጂነሪግ ክህሎት ችግር እንዲፈቱና በሮቦቲክስ ደግሞ ፈጣራ ላይ እንዲሰማሩ ነው የምናደርገው'' ሲሉ ገልፀዋል።
''አሜሪካ ውስጥ ባሉ የቴክኖሎጂና የትምህርት ሞያተኞች የተሰራ ካሪኩለም ነው የምናስተምረው'' ያሉት ዋና ሥራ አስከያጁ፤ ለትምህርቱ ይሆናሉ የተባሉ መማርያ ቁሳቁሶችም ከዛው እንደሚያስመጡ ተናግረዋል።
ከትምህርት በኃላ ባለ ሰዓት፣ በቅዳሜና እሁድ ብሎም በክረምት (ሰመር ካምፕ) ፕሮግራሞች ተማሪዎችን ተቀብለው እንደሚያስተምሩም ተናግረዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በተለያዩ ትምህርት ቤቶችም የሚሰሩ ሲሆን፤ ስልጠናውን በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለማዳረስ እንዲችሉ ደግሞ በቀጣይ ከኢትዮ ቴሌኮም እና ከሳፋሪ ኮም ጋር በመተባበር የበይነመረብ ስልጠና ለመጀመር እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ማዕከሉ በዛሬው ዕለት ሰኔ 21 ቀን 2017 ዓ/ም ባካሄደው የዓመቱ መዝግያ የስቲም ፌር ፕሮግራም ላይ በስልጠናው ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎቹ ሽልማት አበርክቷል።
በሚሊዮን ሙሴ

ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ምክትል ሊቀመንበርና የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ሆነዋል
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) " ታሪካዊ " ሲል የጠራውን ጠቅላላ ጉባዔውን አካሂዶ አዲስ አመራር መምረጡን ይፋ አደረገ።
"በሀገሪቱ ብቸኛው ቀዳሚ የብሔር ብሔረሰቦች የፖለቲካ ጥምረት" እንደሆነ የገለጸው መድረክ 17ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን በተሳካ ሁኔታ በማካሄድ የውስጥ መነቃቃቱን የሚያበስር ወሳኝ እርምጃ እንደወሰደ ገልጿል።
በግንባሩ ጽ/ቤት የተካሄደው ጉባዔ፣ አዲስ አመራር በመምረጥና እውነተኛ ዴሞክራሲያዊትና ሰላማዊ ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚያስችል ስትራቴጂካዊ አቅጣጫ በማስቀመጥ መጠናቀቁን አሳውቋል።
አዲስ የተመረጠው አመራር፣ ወጣት አመራሮችን ከተመክሮና ልምድ ካካበቱ አንጋፋ ፖለቲከኞች ጋር በስትራቴጂካዊ ቅንጅት ያካተተ እንደሆነና ይህም መድረክ የኢትዮጵያን ውስብስብ ፖለቲካዊ ተግዳሮቶች በብቃት እንዲወጣ እንደሚያስችለው አመልክቷል።
በእዚህም መሰረት ፓርቲው
1. አቶ ዓምዶም ገብረስላሴን፦ ሊቀመንበር
2. አቶ ሱልጣን ቃሲም፦ ምክትል ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
3. ወ/ሮ መርየም ሓሰን ፦ ምክትል ሊቀመንበርና የፋይናንስ ጉዳይ ኃላፊ
4. አቶ ሙላቱ ገመቹ፦ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ መንበርና የህዝብ ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ
5. ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ፦ ምክትል ሊቀመንበርና የውጭ ጉዳይ ኃላፊ
6. አቶ ለገሰ ለንቃሞ፦ የመድረክ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ
7. አቶ ደስታ ዲንቃ፦ የመድረክ ምክትል ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ተመርጠዋል።
መድረክ ፦
- ዓረና ትግራይ ለዲሞክራሲና ሉዓላዊነት (ዓረና)፣
- የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ)፣
- የሲዳማ አርነት ንቅናቄ (ሲአን) እና የዓፋር ህዝብ ፍትህና ዲሞክራሲ ፓርቲን በአባልነት አቅፏል።
ምንጭ:- ቲክቫህ